cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Hear me out

ምርጥ ፅሁፎችን አስተማሪ እና አዝናኝ ታሪኮች የምናጋራበት አዳማጭ የሚሹ ሹክሹክታዎች የሚሰማበት..... ቻናሉን ከወደዱት ለወዳጆ ሼር ማረግ አይርሱ።

Show more
Advertising posts
203
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
+330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

❥:::::::::::: ልብ በል:::::::::::❥ ☞ችግርህን አላህ ካልፈታው ገንዘብ ችግርህን አይፈታውም አላህ ካልሞላው ሰው ጎንህን አይሞላውም አላህ ካልገለጸልህ እውቀት ጥበብ አይሆንም ፡ ይቺ ዓለም ለሁሉም እኩል ናት፡፡ ዛሬ ብታገኝ ነገ ታጣለህ ዛሬ ብታሸንፍ ነገ ትሸነፋለህ፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው የሚባል መዶሻ አለ፡፡ መልካምነት ዋጋ ይከፍልሃልና ሁሌም ፍጹም መልካም ሰው ሁን ፡ ህይወትህ ትርጉም እንዲኖራት ዓላማ ይኑርህ፡፡ ፡ የአንተነትህ ትልቁ ምዕራፍ ከእውቀትህ በላይ ስራህ መሆኑን አትርሳ፡፡ ፡ ንጹህ ልብ ልክ እንደ አበባ ናት! ፍሬ ባናገኝባትም ውበቷ ግን እጅግ ማራኪ ነው፡፡ : የውድቀት መጀመሪያ ራስህን አዋቂና ብቸኛ አድርጎ ማሰብ ነው ፡ ፍጻሜህ እንዲያምር ራስህን አታመጻድቅ ሁሌም ከስህተትህ ለመታረም ፈቃደኛ ሁን ጥፈፋትህን አሜን ብለህ መቀበልህ ክብርህን የሚጎዳብህ አይምሰልህ፡፡ ፡ ጠቢብ ሰው እንኳን ከራሱ ከሰው ስህተት ተምሮ ራሱን ይጠብቃል ይመለሳልና፡፡ ፡ በህይወት ውስጥ አንዱ ሲታወር አንዱ መሪ መሆን አለበት ፡ እውነትነ የሚናገር ሰው አፉ ክፉ ይመስላል ልቡ ግን ንጹህ ነው ፡ ህይወት በመደጋገፍ የተሞላች ናትና ወንድምህን ለመርዳት ወደሗላ አትበል! @lendmeurear1
Show all...
👌 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
✨ صلو الارسول الله @lendmeurear1
Show all...
1
You never know how your life is going to change. You may be complaining about something insignificant when suddenly tragedy hits. Even when faced with difficulties you need to remember that it's the qadr of Allah and it's a form of mercy. So be grateful for the hardships because Allah in His infinite mercy has chosen this as a way to purify you and help you to shape your character. It’s also a good reminder to always be grateful for everything you have and to keep your complaints to a minimum. Life is so fragile and your world could shatter in minutes. - Halleh Banani @lendmeurear1
Show all...
❤‍🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሰባሀል   ኸይር አነጋን        الحمدلله 
Show all...
ድንቅ ክስተት - ሶሉ አለ ነቢ!✨ ሚካኤል ሀርት ነው:: 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች የሚለውን መፅሐፍ ለመፃፍ 28 አመታት ፈጅተውበታል::  ከ100ዎቹ ሁሉ አስቀድሞ በአንደኛ ደረጃ ላይ የእኛን ነቢ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አስቀመጠ:: ለንደን ላይ ትምህርት እየሰጠ ባለበት ሰዓት ሰዎች "ለምንድን ነው ሙሐመድን አንደኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጥከው?" በማለት ንግግሩን በማቋረጥ ረበሹት:: እሱም "ሙሐመድ ከ1400 አመታት በፊት ለሰዎች 'እኔ የአምላክ መልዕክተኛ ነኝ!' ብሎ ሲናገር ያመኑበት ሰዎች 4 ሲሆኑ ጓደኛው ሚስቱና ሁለት ህፃናት ብቻ ነበሩ::" አለ:: በመቀጠልም "ከ1400 አመታት ቡሃላ ዛሬ ላይ ከ1 ቢልዬን በላይ ተከታዮችን አፍርቷል:: ስለዚህ ውሸታም ሊሆን አይችልም:: አንድ ሰው አንድ ቢልዬን ሰውን መዋሸትም ሆነ መሸወድ አይችልም:: ውሸትም ለ1400 አመታት ሊቆይ አይችልም::" ሲል አከለ:: ከዚህም በመጨመር ለአድማጮቹ "ከዚህ ሁሉ አመታት ቡሃላ እንኳ በሚልዬን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ነፍሳቸውን እርሱን ለማንቋሸሽ ለምትወረወር አንድ ቃል ሲባል መስዋዕት ለማድረግ ዝግጁ ናቸው::" ሲል ነገራቸው:: በማስከተልም "ከእናንተ መካከል አንድ ክርስቲያን እንኳ ይህንን መስዋዕትነት ለእየሱስ ለመክፈል ዝግጁ አለ?" ሲል ጠየቃቸው::: መልስ አልነበረም:: አዳራሹ በፀጥታ ተሞላ:: ፊዳከ ኡሚ ወአቢ ያኸይረልወራ! @lendmeurear1
Show all...
4
Biggest lie i tell my self in lectures "I don't really need to write this down ኢሄንማ ማስታወስ አያቅተኝም" 🤦🏼‍♀😅 @lendmeurear1
Show all...
🤝 3😁 2
ሁሌ ነገሬ በዉስጤ ሞቶ፣ ኢማኔ ደክሞ፣ አካሌ ለሶላት ሰንፎ፣ ዚክርና ዱዓ የማድረግ ሞራሌ ወርዶ፣ ከቁርኣን ጋር ያለኝ ትስስሬ ተበጥሶ፣ ኃጢኣት ነግሶብኝ፣ ወንጀል ተከምሮብኝ፣ ዉስጤ ቆሽሾ፣  .... በዚህ ሁኔታዬ አላህዬ ይቀበለኝ ይሆን? እላለሁ አንዳንዴ። ግና ድንገይ ከድንጋጤዬ ብንን ስል "ከአላህ እዝነት ተስፋ የሚቆርጡት ጠማሞች ብቻ ናቸው።" የሚለው የአላህ ቃል ይደዉልብኛል። የጌታዬ እዝነቱ ዳር የለዉም። በምህረት ተስፋው እንደተሞላሁ እጋደማለሁ። ያ ረብ እዘንልኝ። @lendmeurear1
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
I am scared I won't be as good as I and others think I will be in the future.✨🍃 @lendmeurear1
Show all...
💔 1
የኢስላም አርበኞች ምዕራፍ አንድ ክፍል አስራ ስድስት(ስንብት) "እናትና አባትህን እንዳጣኸው ኢኽላስንም እንዳታጣት ትፈራለሀ?" "መጠየቁ ለምን አስፈለገ?" "ይኸውልህ ማሂ! ነፍስ ሁላ ሞትን ቀማሽ ናት። እኔም አንተም ሁላችንም አይቀርልንም። እስልምና ውስጥ ስለገባ ይሞታል የሚለው አስተሳሰብ ለእንዳንተ አይነቱ ሰው አይመጥንም!" "ኢምራን ሌላ የምትነግረኝ ነገር ካለ ንገረኝ። ስለዚህ ጉዳይ ግን ማውራት አልፈልግም!" "ለምን? ስለምትፈራ አይደል? ንገረኝ ማሂ! አላህ እኮ ጥበበኛ ነው። በደንብ ብታስተነትነው ኑሮ.... እናትህ እና አባትህ አራስ ወንድምህ ጨምሮ ጥሪውን አቤት ብለው ከቤቱ ሲደርሱ ሞትን መጎናፀፋቸው ምነኛ ደስ የሚል ነው" "እንዴት?" "አንድ ሰው በመልካም ስራ ላይ መሞት የሁል ጊዝል ምኞቱ ነው። ሀጅ ደግሞ ወንጀልህ እጥብጥብ የሚልበት ነው። እና ወንጀሉ ታጥቦ መሞት የማይፈልግ ማን አለ?" "እሱማ ልክ ነህ ግን....... እኛስ? ከአባት ከእናት ፍቅር ርቀን.." አለቀሰ። "አየህ ማሂ! አላህ ጥበበኛ ነው አላልኩህም? እንደ አባት የሚሆንላችሁ አያት እና እንደ እናት የምታዝንልህ እህት ሰጥቶሀል። በኡስታዝ አብዱሰላም ክሷችኋል።" "ግን እኮ እነሱ እሱን ብለው ቢሄዱ እኛን መና አስቀረን እኮ.." "ማሂ! ሰው ከተፃፈለት እለት ፈቀቅ አይልም። አንድ ምሳሌ ልስጥህ.... ታስታውስ ከሆነ የመጀመሪያ ቀን ሳገኛችሁ.. ፋሪስ አንድ ጥያቄ ጠይቆኝ ነበር። "እናንተ ሶስት ናችሁ እኛ ደግሞ አምስት! ታዲያ አንበዛም?" ብሎ። ግን ሁለቱ በስራ ምክንያት ወደ ውጭ እንደሄዱ ነበር የነገርኳችሁ። እውነታው ግን እነሱ ወደ አኼራ ነው ያሸለቡት። አላህ ይዘንላቸው። እኛም እነሱም እኩል ነው ተውበት ያደረግነው። ግን አላህ ለሞት አስቀደማቸው። እኛም እነሱም እሱን ብለን ነው ይህን ስራ የምንሰራው። ግን..... ለምን እኩል አልሞትንም? ቀናችን ስላልደረሰ! አየህ የሰው ልጅ ከቀኑ ዝንፍ አይለም። እኔም አንተም ብንሆን!"... አሚር እና ፋሪስ ደውሎላቸው ስለነበር በሩን ከፍተው ገቡ። "እና.... በሰዓቱ ለምን ዋሸኸን?" "እስኪ አንተኑ መልሼ ልጠይቅህ! በዚያ ሰዓት ነግሬያችሁ በነበር ምን ልታስቡ እንደምትችሉ?" "of course! እናምፅ ነበር" አለቀሰ። "እና ምን ትላለህ ማሂ?" "ያ ረቢ! ምን አይነት ቀሽም ነኝ! እድሉ ፊትለፊቴ ሆኖ ማየት ያቃተኝ!" "አሁንም እኮ አልረፈደም!" "ልክ ነህ! ያ ረቢ ይቅር በለኝ!.... " ተንሰቀሰቀ። አሚርና ፋሪስ በደስታ ተቃቀፉ። አሚር ሳቅ አለና "እናሳ ወደ መርከዝ እንሂዳ!" አለው። ማሂ እንባውን ጠረገና "ከዛ በፊት ማድረግ ያለብኝ ነገር አለ!" አለ። "ምን?" አሉት በግርምት። የመጨረሻው እንቆቅልሽ ምን ነበር? ነጥብ ኣ?" "እና ፍቺውን አገኘኸው?" አሚር ነበር። "አዎ! እንደስሜ! ደምሳሽ ወይም መጨረሻ! ተውበቴ ከሁላችሁም መጨረሻ... የመጨረሻውንም እንቆቅልሽ አገኘሁት። እውነት ስሜን ተላበስኩት!" ፈገግ አስባላቸው። "እና ንገረና!" "እዚህ አይደለም! ተነሱ!" ብሎ ይዟቸው ወጣ። የፊርደውስ መኪና በር ላይ ቆማ ነበር። አራቱም ተከታትለው ገቡና ማሂ መኪናዋን በፍጥነት አስፈነጠራት። መንገዱ አዲስ አልሆነባቸውም። አዎ! ወደ ሚፍታሁል ቀልብ የሚወስደው መንገድ ነው። ማሂ መኪናዋን ግቢው በር ላይ አቆማትና ወርደው ወደ ምስጢራዊ ምሽጋቸው እየመራ ወሰዳቸው። ሲገቡ ሀሩን ክፍሉን እያፀዳ ነበር። ሴቶቹ የሉም። መምጣትም እንደሌለባቸው ያምናሉ! ለዚያ ሲባል ፋሪስ ለኢኽላስ፣ አሚር ለፊርደውስ፣ ኢምራን ደግሞ ለነባት ደውለው መስመር ላይ እንዳሉ እንዲያዳምጡ ያረጉት። አሚር፡- "እሺ ማሂ! አሁን ደግሞ እዚህ ለምን እንዳመጣኸን ንገረን!" ማሂ፡- "ነጥብ የመስመሮች መነሻ መጀመሪያ ነው። ነጥቦች ተሰባስበው መስመርን እንደሚሰሩት ለእኛ መስመር መያዝ ይህ ቦታ መነሻው ነው።" አሚር፡- "ስለዚህ የመጨረሻው እንቆቅልሽ ፍቺ ይሄ ቦታ ነው!" ማሂ፡- "እንደዛ አስባለሁ እ ኢምራን?" አለ። ከአሚር ስልክ ውስጥ 'እንደዛ አይመስለኝም' የሚል ደምፅ ተሰማ። ፊርደውስ ነበረች። አሚር የስልኩን ስፒከር ከፈተና "እንዴት ፊርዱ?" አላት። "በእርግጥ ማሂ ልክ ነው! የነጥቡ መልዕክት መነሻን ያመለክታል። ስህተቱ ግን መነሻ ብሎ ያሰበው ቦታ ነው። የኛ መነሻ ይህን ትምህርት ቤት መስርተው እየተንቀሳቀሱ ያሉት ኡስታዛችን ናቸው። ይህ ቡድን ባይመሰረት፤ ይህ ትምህርት ቤት ባይከፈት የስንቱ ህይወት ነበር መና ሚቀረው። የኛም ጭምር!" አለች። ሁሉም በመልሷ ሊከራከሯት አልቻሉም። ወዳው ኡስታዝ አብዱሰላም በሩን ከፍተው ገቡና "አሰላሙ አለይኩም" አሉ። ሁሉም በአንድላይ አፀፋውን መለሱላቸው። ኡስታዙ ፊታቸው ላይ ደስታ ይነበባል። የልጅ ልጆቻቸውን ከስንት አመት በኋላ ከልባቸው ሆነው አገኟቸው። ሰው ሆነው አገኟቸው! እንዴት አይቦርቁ! ኡስታዙ በደስታ ይመክሯቸው ጀመር። "ልጆቼ አላህ ለተውበት ከመረጣቸው አድርጓችኋልና ልታመሰግኑት ይገባል" ሁሉም በአንድ ድምፅ "አልሀምዱሊላህ!" አሉ። "ለእናንተ የተሰጠውን እድል ሳያገኙ የሞቱ ብዙ አሉ። ለዱንያ ሰዎች ለህድ ውስጥ ሆነው ህይወታችሁን ተጠቀሙበት የሚሉ ሞልተዋል። እናንተ ግን የሱ ፍቃድ ሆኖ ወደ ሀቁ መንገድ ስድስት ወር በማይሞላ ግዜ ውስጥ ተቀላቅላችኋል። ልጆቼ ወደፊታችሁ ያማረ ይሁን፣" "አሚን!" በህብረት። "በዲናችሁ ላይ ፅኑ፣ ትጉህ እና ጠንካራ ያድርጋቸሁ!" "አሚን!" "የዱንያንም የአኼራንም ደስታ አላህ የምትጎናፀፉ ያድርጋችሁ!" "አሚን!" "ያው እኔንም በዱዓ አትርሱኝ።" ፈገግ ብለው ፈገግ አስባሏቸው። ኢምራን የኡስታዙን መጨረስ አየና ወደሳቸው ጠጋ ብሎ "እና እኛን መተካት ይችላሉ ወይስ?....." በመካከለኛ ድምፅ ጠየቀ። እነ አሚር መስማት የፈለጉትን ጥያቄ ስለጠየቀላቸው ልባቸው በሀሴት ተሞላች። ምን ይሉ ይሆን? በሚል ውጥረት ሁሉም ተጨንቋል። ፊርደውስና ኢኽላስ ስልኩ ውስጥ ሊገቡ ምንም አልቀራቸውም። ኡስታዙም ልባቸውን ለመስቀል ይመስላል ዝምታቸውን ያዘገዩት። ምን ይፈጠር ይሆን? አሚር፣ ፊርደውስ፣ ማሂ፣ ኢኽላስና ፋሪስ... የኢስላም አርበኞች ለመባል ይበቁ ይሆን? ያስተማራቸውን ትምህርት ቤት ለመምራት ይበቁ ይሆን?..... . . . . . . . . .#ተፈፀመ! ውድ ቤተሰቦቻችን የኢስላም አርበኞች ምዕራፍ አንድ ድርሰታችንን በዚሁ አብቅተናል። የአላህ ፍቃድ ከሆነ ወደፊት በምዕራፍ ሁለት እንመለሳለን። በምዕራፍ አንድ ላይ የተሰማችሁን በሙሉ ኮሜንት ላይ ዘርገፍገፍ አድርጉት። እኔ በዚሁ ላብቃ። . . . ላሁን አይቀጥልም✨ .. . . ይቀላቀሉን👇                  @lendmeurear1
Show all...
👍 3
Saying our beloved goodbyes to የኢስላም አርበኞች ዛሬ 2:00 የመጨረሻ part ይለቀቃል። Stay with us.✨ 😊 @lendmeurear1
Show all...
🙏 1