cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

💞አውደ💞 ቃል 💞💖

የግጥም መንደር አብረን በቃላት ስሜታችንን እንገላላፃለን join & share እንዳይረሳ

Show more
Advertising posts
439
Subscribers
+124 hours
+207 days
+5830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን/×3/ ኪሪያላይሶን/×3/ ኪሪያላይሶን/×2/ አማኑኤል ጌታ       >>           በጥፊ ተመታ       >>           አለምን ሊታደግ       >>           ተነዳ እንደበግ       >>            አዳምን ሊፈውስ       >>            ቆመ ከጲላጦስ ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ  ኪሪያላይሶን ጽብኦሙ እግዚኦ ለእለ ይፀብኡኒ ኪሪያላይሶን ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ  ኪሪያላይሶን አዝ ኪሪያላይሶን/×2/ እጁን ቸነከሩት       >>            አጥንቱን ቆጠሩት       >>            የሾህ አክሊል ደፍቶ       >>            ገዳዩን ረቶ       >>            የሁላችን በደል       >>           ተሻረ በሱ ቁስል ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ ኪሪያላይሶን ወኈለቊ ኵሎሙ አዕፅምትየ ኪሪያላይሶን ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ ኪሪያላይሶን አዝ ኪሪያላይሶን/×2/ እጣ ተጣጣሉ       >>            ልብሱን ተካፋሉ       >>            ለፍርድ ተወሰደ       >>            እንደግ ታረደ       >>            ለብሶ ከለሜዳ       >>            ተከፈለ ዕዳ ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን ኪሪያላይሶን ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን ኪሪያላይሶን ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን፤ ኪሪያላይሶን አዝ ኪሪያላይሶን/×2/ ሆምጣጤ አጠጡት       >>      በገመድ ጎተቱት       >>        በወንበዴው ፈንታ       >>       ተሰቀለ ጌታ       >>       ሁሉም ዘበቱበት       >>       በዘላለም ህይወት ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ ኪሪያላይሶን ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ ኪሪያላይሶን ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ ኪሪያላይሶን
Show all...
Repost from N/a
🍀አንዱ ስለሁሉ ሞተ🍀 የስሞነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያናችን ልዩ ቀን ነው፡፡ ይህ ቀን ልዩ ነው፣ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁትን ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሣ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ ግርፋት ነፃ የሚያወጣ ሲገረፍ የዋለበት ወልደ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ድኅነት በመስዋዕትነት ሙሽራ የሆነበት የደስታ ቀን የዓመፃ መዝገባችን መገልበጡ እርግጥ የሆነበት ፣ አሳዳጃችን አሳሪያችን ዲያብሎስ ከነወጥመዱ ድል የተነሳበት ቀን ነው የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለም ድኅነት መስዋዕት ሆኖ የዋለበት ዕለት በመሆኑ የስቅለት ዓርብ ተብሏል (ማቴ 27፡35) መልካሙ ዓርብ (GOOD FRIDAY) ይባላል ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት ማንም ሰው ስያጠፋ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት ይደረግ ነበር፡፡ በተለይ በሮማውያንና በፈሪሳውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ነበረ፣ በዚህ ዕለት ግን ታሪክን የሚቀይረው፣ ነገርን የሚገለብጠው አምላክ የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምህረት ምልክት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ፣ የቤተክርስቲያን ጌጥ፣ የገዳማት ዘውድ፣ ስለአደረገውና በዕለተ ዓርብም በሞቱ ሕይወትን ስለአገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡ ነፍሳት ከሲኦል የወጡ መቼ ነው? ነፍሳት ከሲኦል የወጡ ዓርብ በሠርክ ነው፡፡ ሐዋርያው ጴጥሮስ “ነጻነት አወጃላቸው” ይላል፡፡ ጌታ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ “ሰላም ለኵልክሙ” “ሰላም ለእናንተ ይሁን” እንዴት ሰነበታችሁ? አስታረቋችሁ ሲላቸው ነው፡፡ አዳም ቀጠሯችን ደረሰ የድኅነት ዕለት ዛሬ ናት ተንሥኡ ለጸሎት ሲል ነፍሳትም ምስለ መንፈስከ አሉ፡፡ጌታም “በጽልመት ውስጥ ያላችሁ ውጡ፣ በሲኦል ያላችሁ ተገለጡ ብርሃንም አዩ” ብሎ እልፍ ፀሐይ ቢገባበት የማይለቅ የሲኦልንም ጨለማ ብርሃነ መለኮቱን ነዛበት ያኔ ጨለማው ለቀቀ የዚያን ጊዜ ወጐዩ ዓቀበተ ሥጋ መናፍስት /አጋንንት/ በዚህ ጊዜ ነፍሳትን የተቆራኙ አጋንንት ሸሹ፣ እለ ውስተ ሲኦል ጻኡ፤ ወእለ ውስተ ጽልመት ተከሠቱ ብሎ ባሕረ እሳትን ከፍሎ ወደ ገነት አገባቸው፡፡ በዕለተ ዓርብ ስንት ታምራት ታይቷል? ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ የታዩ ተአምራት የሚከተሉት ናቸው፤ በሰማይ፤ /ማቴ 24፦29 እና 27፦45/ 1. ፀሐይ ጨለመች 2. ጨረቃ ደም ሆነች 3. ከዋክብት ረገፉ በምድር፤/ማቴ        27፦51_53/ 4. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይእስከ      ታች ተቀደደ 5. ምድር ተናወጠች 6. መቃብሮች ተከፈቱ 7. ሙታን ተነሱ ለምን 400 ጊዜ እግዚኦ ይባላል? በዚሁ ዕለት በአራት መዓዘን እየዞርን 400 ጊዜ ምሕላ እናደርጋለን፣ ምሕላ የምናደርገውም አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የአዳም ልጆች በሲኦል ሆነው አቤቱ ይቅር በለን ብለው የለመኑትን ለማስታወስ ነው ከምሕላው በኋላ በወይራ እየተጠበጠቡ የንስሐ ስግደት እንደየ አቅሙ ይሰጣል፡፡ ከምን የተነሣ ነው ቢባል የክርስቶስን መከራ እንቀበላለን፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን ተብለናልና፡፡ የኛን መከራ ተቀብሎ እንዳዳነን እሱ የተቀበለውን መከራ እንቀበላለን፣ እንገረፋለን፣ አላውያን ነግሥታት፣ አላውያን መኳንንት፣ ሃይማኖታችሁን ካዱ ቢሉን ቢገርፉን እንገረፋለን በሰይፍ ቢመቱን፣ ቢሰቅሉን፣ መከራውን በጸጋ እንቀበላለን ለማለት ነው፡፡ እሱ የተቀበለው መከራ ተቀበሉ ተብሎ ታዟልና፡፡ በዕለተ ዓርብ ንሴበሖ ለእግዚአብሔር የሚባለው ለምንድነው? በስቅለት፣ ዓርብ ማታ ከእግዚኦታ /ምሕላ/ በኋላ ንሴብሖ ይባላል፡፡ ምክንያቱም እስራኤል በምድረ ግብጽ 215 ዘመን በባርነት ቀንበር ሲገዙ ከነበሩ በኋላ በሙሴ መሪነት የኤርትራን ባሕር ስላሻገራቸው “ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ” እያሉ አመስግነውታል፡፡ እኛ ደግሞ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ አውጥቶ ባሕረ እሳትን ከፍሎ ወደ ገነት ስለአገባን “ንሴብሖ” እያልን እናመሰግነዋለን፡፡ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ከተባለ በኋላ እግዚአብሔር ይፍታህ ይባላል፡፡ እግዚአብሔር ይፍታህ የሚባልበት ምክንያትም ካሣ ከተፈጸመ ወዲያ፣ ልጅነት የተመለሰ፣ ነጻነት የተገኘ ነፍሳት ከሲኦል የወጡ ስለሆነ ነው፡፡ በዓመት አንድ ጊዜ የምናገኘው ይህ ዕለት ቀራንዮን የምናስብበት ነገረ መስቀሉን የምናስተውልበት እንጂ ስለምድራዊ ኑሮአችን ስንባክን ኃጢዓት ስንሰራ የምንውልበት ሊሆን አይገባም፡፡ ለብርሃነ ትንሣኤው አምላካችን በሰላም ያድርሰን አሜን።
Show all...
አምስቱ ቅንዋተ መስቀል (ችንካሮች) የሚባሉት እነማን ናቸው? አምስቱ ቅንዋተ መስቀል፦የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው። #ሳዶር ፦ኢየሱስ ክርስቶስ የቀኝ እጁን የተቸነከረበት ችንካር ነው፤ #አላዶር ፦ኢየሱስ ክርስቶስ የግራ እጁን የተቸነከረበት ችንካር ነው፤ #ዳናት ፦ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት እግሮቹ የተቸነከሩበት ችንካር ነው፤ #አዴራ ፦ኢየሱስ ክርስቶስ መሐል ልቡን የተቸነከረበት ችንካር ነው፤ #ሮዳስ ፦ኢየሱስ ክርስቶስ ደረቱን የቸነከሩበት ችንካር ነው። @awdekalat_2112 @awdekalat_2112 @awdekalat_2112
Show all...
​​1️⃣ በሕማማት የሚጸለዩ ፀሎቶች ምን ምን ናቸው? 2️⃣ በሕማማት ወቅት የሚሰሙ የምንላቸው ከሌላ ቋንቋ የተወሰዱ ቃላት ትርጉም 3️⃣ የ41 ስግደት ምን እየተባለ ነው የሚሰገድ?       📚 የሕማማት ጸሎት 📚 በሕማማት የሚጸለየው በአብዛኛው ውዳሴ ማርያም እና መዝሙረ ዳዊት፤ የነቢያት ጸሎት ሲሆን የጌታን መከራ መስቀል የሚያነሱ መጻሕፍት ይጸለያሉ፡ ሕማማተ መስቀል፣ ድርሳነ ማሕየዊ የመሳሰሉ። መልክአ መልኮች፣ ድርሳናትና ገድላት የማይጸለዩት ዋናውን ጸሎት በጌታ ሕማማና መከራ መስቀል ለመስጠት ስለሆነ ነው። በአጠቃላይ በቤተክርስቲያን የሚነበበው ንባብ (ግብረ ሕማም) ዋናው የጸሎት ክፍል በመሆኑ ያንንም መሳተፍ ትልቁ ጸሎት ነው።           🌿 ጥብጠባ 🌿 በሰሙነ ሕማማት እለተ ዓርብ ስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡ ምእመናኑ በሰሙነ ሕማማት የሰሩትን ይናዘዛሉ  ካህናቱን በወይራ ቅጠል ትከሻቸውን እየጠበጠቡ  ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ ምሳሌ ነው፡፡ ይህ በስቅለተ ቀን የሚፈጸም ስነ ስርዓት ሲሆን ጥብጣቤ ማለት ቸብ ማድረግ ማለት ነው፡፡  ይህም የጌታን ግርፋት ያሳያል።፡ሕዝብ ክርስቲያኑ በእለተ ስቅለት ሲሰግድ ሲጸልይ ሲያነብ ከዋለ በኋላ ሰርሆተ ሕዝብ ይሆናል። አርብ ከ 11 ሰአት በኋላ ስግደት እንደሌለ ግብረ ሕማሙ "አልቦ ስግደት "ይላል። 📚 በሕማማት ወቅት የሚሰሙ የምንላቸው ከሌላ ቋንቋ የተወሰዱ ቃላት ትርጉም 📚 በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡         📌 "ኪርያላይሶን" 📌 ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ “ኪርዬ ኤሌይሶን” ነው፡፡ “ኪርያ” ማለት “እግዝእትነ” ማለት ሲሆን “ኪርዬ” ማለት ደግሞ “እግዚኦ”ማለት ነው፡፡ ሲጠራም “ኪርዬ ኤሌይሶን” መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም “አቤቱ ማረን” ማለት ነው፡፡ “ኪርያላይሶን” የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው “ዬ”ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ “ኤ” በመሳሳባቸው በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረው ነው፡፡             📌 "ናይናን" 📌 የቅብጥ(ጥንታዊው የግብጻውያን ) ቃል ሲሆን ትርጉሙ “መሐረነ፣ ማረን” ማለት ነው፡፡              📌 "እብኖዲ"  📌 የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “አምላክ” ማለት ነው፡፡ “እብኖዲ ናይናን” ሲልም “አምላክ ሆይ ማረን” ማለቱ ነው            📌 "ታኦስ" 📌 የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ጌታ፣ አምላክማለት ነው፡፡ “ታኦስ ናይናንማለትም “ጌታ ሆይ ማረን” ማለት ነው፡፡             📌 "ማስያስ" 📌 የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ “መሲሕ” ማለት ነው፡፡ “ማስያስ ናይናን” ሲልም “መሲሕ ሆይ ማረን” ማለት ነው            📌 "ትስቡጣ" 📌 ደግ (ቸር) ገዥ ማለት ሲሆን "ትስቡጣ ናይናን" ማለት ቸር ገዥ ማረን ማለት ነው።   📌 "አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ" 📌 የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ” ማለት ነው፡፡ 📌 "አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ" 📌 የቅብጥ ቃል ሲሆን “ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ  ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው 📌 "አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ" 📌 የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ፤የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው፡፡ 👉 የ41 ስግደት ምን እየተባለ ነው የሚሰገድ? አንድ ክርስቲያን በፆም ጊዜ ከፀሎት በኋላ የጌታን መከራና ለእኛ ያሳየውን ፍቅር እያሰበ ከሐጢያቱ ብዛት ከአምላኩ ይቅርታ ያገኝ ዘንድ 41 ጊዜ እንዲህ እያለ ይስገድ። 12 ጊዜ ---- እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ 12 ጊዜ ---- በእንተ እግዝዕትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ 12 ጊዜ ----ኪራላይሶን (አቤቱ ማረን) 5 ጊዜ ---- ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ፣ ሮዳስ (አምስቱ የጌታ ችንካሮች) @awdekalat_2112 @awdekalat_2112 @awdekalat_2112
Show all...
👍 1
Repost from N/a
፭. ዕለተ አርብ ዕለተ ዓርብ አዳምን ከሰይጣን ባርነት ነፃ ለማውጣትና የእርሱን የበደል ዕዳ ለመክፈል አምላካችን መከራ መስቀሉን የተሸከመበት ዕለት፣ የኀዘን ዕለት፣ የድኅነትም ዕለት ነው፡፡ ዓርብ ማለት ዐረበ ገባ (ተካተተ) ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም መካተቻ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረቱን ከእሑድ ጀምሮ በስድስተኛው ቀን ዓርብ አዳምን በመፍጠር ሥራውን ሁሉ አጠናቋልና (አካቷልና)፡፡ በኋላም በኦሪት ሕዝበ እስራኤል ከሰማይ የሚወርድላቸውን መና በሙሴ ትእዛዝ መሠረት ዓርብ ዕለት የቅዳሜን ጨምረው (ቅዳሜ ሰንበት ስለሆነ እህል መሰብሰብ ስለማይገባ) አካተው ይሰበስቡ ነበር፡፡  (ዘፀ.፲፮፥፬) በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ብርሃነ ዓለም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት»  እንዳለ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለበደል ያለጥፋት ንጹሕና ጻድቅ የሆነውን ጌታ የሰቀሉበት ዕለት ነው፡፡ ዕለቱም የዓለም ሁሉ መድኃኒት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበትና የሰው ልጅ ድኅነት የተፈጸመበት (የተካተተበት) በመሆኑ (ዓርብ) ተብሏል፡፡  (፩ኛቆሮ.፩፥፲፰፣ማቴ.፳፯፥፴፭-፸፭) ዓርብ ጠዋት ጎህ ሲቀድ አይሁድ ጌታችንን በጲላጦስ ፊት አቀረቡት፡፡ ጲላጦስም ወደነርሱ መጥቶ ‹‹የዚህ ሰው በደሉ  ምንድነው?››  አላቸው፤ የካህናት አለቆቹም ‹‹ክፉ አድራጊ ባይሆን ወዳንተ እናመጣዋለን? ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር ያስተካክላል፤ ለቄሳር አልገዛም ይላል፤ የሰንበትን ቀን ይሽራል….›› በማለት የተለያዩ ክሶች አቀረበቡት፡፡ ጲላጦስም ‹‹እናንተ ወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት›› አላቸው እነርሱም ‹‹እኛ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም›› አሉት፡፡  ጲላጦስም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሊጠይቀው፣ ሊመረምረው ወደውስጥ አስገባው፡፡ ያንጊዜም ጲላጦስ ‹‹የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹ይህን የምትናገር ከራስህ ነውን ወይስ ስለእኔ የነገረህ ሌላ አለን›› ብሎ መለሰለት፤ ጲላጦስም ‹‹እንዲያ የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህ›› አለው፤ ጌታችንም ‹‹እኔ ንጉሥ እንደሆንኩ አንተ ራስህ ትላለህ›› አለው ጲላጦስም ምንም ያገኘበት በደል የለም፡፡ ወደ ውጭም ወጥቶ ይህን ሰው በምትከሱበት ገንዘብ በደል አላገኘሁበትም፤ ነገር ግን በየዓመቱ በየፋሲካ በዓል ከእስረኞች አንድ እንድፈታላችሁ ልማድ አላችሁ፤ እንግዲህ የአይሁድን ንጉሥ ልፈታላችሁ ትወዳላችሁን?›› አላቸው፡፡ እነርሱም በአንድ ድምጽ ከፍ አድርገው ‹‹በርባንን እንጂ ይህን አይደለም›› አሉ፡፡ በርባን ግን ወንበዴ ነበር፡፡  አይሁድም ‹‹ሕግ አለን እንደ ሕጋችን ይሞት ዘንድ ይገባል፤ ራሱን የእግዚብሔር ልጅ አድርጓልና›› አሉት፡፡ ጲላጦስም ሊያስተዋቸው እንዳልተቻለው ባየ ጊዜ አውጥቶ ገረፈው፤ ምክንያቱም በሀገራቸው የሚሰቀል አይገረፍም፤ የሚገረፍም፤ አይሰቀልም፤ ስለዚህ እንዳይሰቅሉት ራርተው ይለቁታል ብሎ ነው፡፡ ነገር ግን  ‹‹መጠውኩ ዘባንየ ለቅሥፈት›› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው፤ እንደዚሁም ዲያብሎስ የአዳምን ዘባነ ልቡና እየገረፈ ገሃነም አውርዶት ነበርና ለእርሱ ካሣ ሊሆን እንደመጣ ለማጠየቅ ጀርባውን ተገረፈ፡፡ (ዮሐ.፲፰፥፳፰-፴፩) ጲላጦስም ‹‹እነሆ ንጉሣችሁን ልስቀለውን?›› አላቸው፤ እነርሱም ‹‹ከቄሳር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም፤ ስቀለው፤ ስቀለው›› አሉ፡፡ ይህንን ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲተረጉሙት ‹‹ልደቱ ከዳዊት ዘር እንደሆነ ሲያመለክታቸው በመንግሥትም ደም በማስፈራራት ያስጥለው ዘንድ ነው፤ እነርሱ ግን እርሱን ለመግደል ጨከኑ፤ ከቄሳር በቀር ንጉሥ የለንም ብለው የዳዊትን ዘር መንግሥት ካዱ›› ብለውታል፡፡ ዳግመኛም አይሁድ በሕዝቡ መሐል እየተሽሎኮሎኩ ‹‹በርባንን ፍታልን፤ ክርስቶስን ስቀልልን›› በሉ እያሉ ሕዝቡን አሳመፁ፡፡ ጲላጦስም የሚረባና የሚጠቅም ነገር እንደሌለ ባየ ጊዜ ውኃ አምጡልኝ ብሎ ‹‹እኔ ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ራሳችሁ ዕወቁ›› ብሎ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ፡፡ ሕዝቡም መልሰው ‹‹ደሙ በእኛና በልጅ ልጆቻችን ላይ ይሁን›› አሉ፡፡  ከዚያን ጊዜም ጀምሮ ልጆቻቸው ደም ጨብጠው የሚወለዱ ሆነዋል፡፡ (መጽሐፈ ምሥጢር- ምዕራፍ ፩፥፬)
Show all...
                         †                          🕊    †    ሰሙነ ሕማማት   †    🕊 ▬▬▬▬▬▬  â€   â–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Ź                 [     ላሐ ማርያም [  የማርያም ለቅሶ  ]      ------------------------------------------------ 🕊 " ልጄ ፡ ሆይ ከዚህ ፡ ካገኘህ ፡ የሞት ፡ ፃዕር ፡ የተነሣ ፡ ግፌን የሚመለከትልኝ ፡ ሹም ፡ ወይም ፡ በሐዘን ፡ የተሰበረውን ፡ ልቤን ፡ አይቶ ፡ በማስተዋል ፡ የሚፈርድልኝ ፡ ዳኛ ፡ አላገኘሁም። " ላሐ ማርያም [  የማርያም ለቅሶ  ] ▬▬▬▬▬▬  â€   â–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Ź [   ከመስቀል ሼር  ያለች መስቀል    ]         - በገጣሚ ኅሊና ደሳለኝ          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ @awdekalat_2112
Show all...
Repost from N/a
                         †                          🕊    †    ሰሙነ ሕማማት   †    🕊 ▬▬▬▬▬▬  â€   â–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Ź          [    አርብ   ] ▬▬▬▬▬▬  â€   â–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Ź †   የስቅለት ዓርብ ይባላል   † ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና [ ማቴ ፳፯፥፴፭ ] የስቅለት ዓርብ ይባላል። †   መልካሙ ዓርብ ይባላል   â€  ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት ፣ የሕይወት አርማ ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው ፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል። ▬▬▬▬▬▬  â€   â–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Ź - [  áˆ°áˆ™áŠ ሕማማት ዘአርብ [ á‰ áˆŠá‰ƒá‹áŠ•á‰° ቤተክርስቲያን  ] - [  ሰሙነ ሕማማት ሥርዓት ዘአርብ [ á‰ áˆŠá‰ƒá‹áŠ•á‰° ቤተክርስቲያን ] †    ድንቅ ትምህርት    †          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ -------------------------------------------------                         👇
Show all...
                         †                          🕊    †    ሰሙነ ሕማማት   †    🕊 ▬▬▬▬▬▬  â€   â–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Ź [      በእንተ ጸሎት ሐሙስ     ] " ተራሮችን በኃይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፡፡ የባሕርን ውኃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በቀላያትም መዝገቦች የሚሾማቸው ርሹ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውኃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ  ኩስኩስት አፈሰሰ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሚታጠቡበት ገንዘብ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በደብተራ ኦሪት ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውኃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ጀመረ፡፡ የተረከዞቻቸውንም እድፍ በታጠቀው ማበሻ ጨርቅ አሸ፡፡"  [    አባ  ጊዮርጊስ ዘጋስጫ      ] †                       †                         † " በወገቡ የታጠቀውን ማድረቂያ አይተው መላእክት አደነቁ ፤ ስሙ ከፀሓይና ከጨረቃ በፊት የነበረ ርሹ አገልጋይ ኾነ ፤ ሕያው ጌታን ሱራፌል ያመሰግኑታል ፤ ቦታውን ግን አያውቁም ፤ ሱራፌልን የፈጠረ ርሹ በራት ጊዜ ወገቡን ዘርፍ ባለው ዝናር ታጠቀ ፤ እንዳያቃጥል በመፍራት የማይታይ እሳት ለሐዋርያት አገልጋይ ኾኖ አብነት ይኾናቸው ዘንድ የትሕትና ሥራን የሚሠራበትን ውሃ በኩስኩስት ቀዳ የደቀ መዛሙርቱን አለቃ ጴጥሮስንም እግሩን ሊያጥበው ጠራው" [   ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘሥሩግ   ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ @awdekalat_2112
Show all...
👍 1