cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኦሮቶዶክ መንፈሳዊ ምስል

መንፈሳዊ ምስሎችን ከፈለጋቹ ይህንን ቻንል መቀላቀል ነዉ ቀላል ነዉ በ @ortodox1621 ማግኘት ይችላሉ

Show more
Advertising posts
203
Subscribers
No data24 hours
+27 days
-330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ብፁ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ
Show all...
እለተ ስቅለት 🙏
Show all...
🙏 1
                         †                          🕊    †    ሰሙነ ሕማማት   †    🕊 ▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬                [       አርብ      ] ▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬ †   የስቅለት ዓርብ ይባላል   † ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና [ ማቴ ፳፯፥፴፭ ] የስቅለት ዓርብ ይባላል። †   መልካሙ ዓርብ ይባላል   † ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት ፣ የሕይወት አርማ ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው ፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል። ▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬ - [  ሰሙነ ሕማማት ዘአርብ [ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን  ] - [  ሰሙነ ሕማማት ሥርዓት ዘአርብ [ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ]          †    ድንቅ ትምህርት    †          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ -------------------------------------------------                         👇
Show all...
👍 1
🙏 1
🙏 1
🕊 [  † እንኩዋን ለቅዱስ ፃና ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ  †   ] 🕊  †   ቅዱስ ፃና    †    🕊 በቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳን አሉ:: ዛሬ የምናከብረው ሰማዕቱ ቅዱስ ፃና ፦ - በዘመነ ሰማዕታት የነበረ: - ቅዱስ ኤስድሮስ የሚባል ደግ ጉዋደኛ የነበረው: - ሁለቱንም እናቶቻቸው እንደሚገባ ያሳደጉዋቸው የ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያኖች ነበሩ:: በወጣትነት ዘመናቸው በድንግልና: ቅዱስ ፃና የሠራዊት አለቃ: ቅዱስ ኤስድሮስ ደግሞ የልብስ ዝግጅት ባለሙያ ነበሩ:: ከሚያገኙት ገቢ ለዕለት ጉርስ ብቻ እያስቀሩ ለነዳያን ይመጸውቱ ነበር:: በመከራ ዘመን [ዘመነ-ሰማዕታት] ቅዱሳኑ ያላቸውን ሁሉ ለነዳያን አካፍለው በክርስቶስ ስም መሞትን መርጠዋል:: አስቀድሞ ቅዱስ ኤስድሮስ አንገቱን ተሰይፎ የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል:: ሰማዕቱ ቅዱስ ፃና ባልንጀራው ኤስድሮስ ከተገደለ በሁዋላ ለ፴፮ [36] ቀናት በጨለማ እሥር ቤት ውስጥ ከብዙ ስቃይ ጋር ቆይቷል:: መከራን ቢያፀኑበትም በሃይማኖቱ ጽኑ ነበርና እርሱንም በዚሕች ቀን ገድለውታል:: ደግ እናቱ በቦታው ነበረችና መላዕክት በክብር ነፍሱን ሲያሳርጉ ተመልክታለች:: ፈጣሪ ከሰማዕቱ ክብር ያድለን:: 🕊 [  † ሚያዝያ ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ] ፩. ቅዱስ ፃና ሰማዕት ፪. አባ ሱንቱዩ ሊቀ ዻዻሳት ፫. አባ ይድራ ፬. የደብረ ሲና ቅዳሴ ቤት [   † ወርኀዊ በዓላት    ] ፩. ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፪. ቅዱስ አጋቢጦስ [ ጻድቅ ኤዺስቆዾስ ] ፫. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ፬. ቅዱስ ሙሴ ፀሊም ፭. ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ ፮. ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ ፯. "24ቱ" ካኅናተ ሰማይ [ሱራፌል] ፰. አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ [ኢትዮዽያዊ] " ልጆች ሆይ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ: አሸንፋችሁአቸውማል:: በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና:: እነርሱ ከዓለም ናቸው:: ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ:: ዓለሙም ይሰማቸዋል:: እኛ ከእግዚአብሔር ነን:: እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል:: ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም :: " [፩ዮሐ.፬፥፬] (4:4) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Show all...