cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

BATALIYON (ባታሊዮን) 📘📙📗

👉 ማንበብ ለራስ ነዉ 📚📗📘📙

Show more
Ethiopia12 828Amharic9 314The category is not specified
Advertising posts
196
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from N/a
እንዴት አደራችሁ እንደ ህጻናት ካልሆናችሁ መጽሐፍ ላይ “ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።” ይላል። ይሄ ነገር እውነት ለመንግስተ ሰማያት ብቻ ነው? ወይስ በዚህ አለምም ስኬታማ ለመሆን? ብዬ አሰብኩ። የመጣልኝ መልስ በዚህም የሚል ነው። ጥቂት ነጥቦች 1. አጥብቆ መፈለግ። ህጻን ልጅ የሆነ ነገር ሲፈልግ አጥብቆ ይፈልጋል። ለህጻን ልጅ መፈለግ ወይም አለመፈለግ የሚባል ነገር የለም።በቃ ህጻን ልጅ የሚፈልገው ነገርን ካላገኘ መፋታት የሚባል ነገር የለም። ብዙ አዋቂ ሰው ግን ይፈልጋልም አይፈልግምም። ቀዝቃዛ ነው። ቢሆንለት ደስ ይለዋል። ባይሆንም እንደህጻን አያደርገውም። አዋቂ ነዋ! ሰው ምን ይለዋል! ህጻን ግን ይሉኝታ አያውቅም። ይፈልጋል ይፈልጋል። እና አንተ የምትፈልገው ነገር ለአንተም ለሰውም የሚጠቅም ከሆነ አጥብቀህ ፈልገው። ካስፈልገም አልቅስ። ምክንያቱም ጥልቅ ፍላጎት አለህና። 2. የሚፈልጉትን በግልጽ ማወቅ። ህጻን የሆነ ነገር ሲፈልግ በተመሳሳዩ አይሸወድም። የሚፈልገውን በግልጽ ያውቃል። ከእሱ ውጪ አማራጮችን አይቀበልም። ብዙ ትልቅ ሰው የሚፈልገውን በግልጽ አያውቅም። የሚመኘውም ጥሩ ኑሮ! የተሻለ ኑሮ የሚባል ነገር ነው። ለመሆኑ የተሻለ ኑሮ፣ ጥሩ ኑሮ የሚባል ኑሮ ነገር አለ? የለም። እንደዛ ካልን ሁሉም ሰው የተሻለ ኑሮ ላይ ነው። ምክንያቱም በአንጻራዊነት ከእሱ ያነሰ ኑሮ ውስጥ ያለ ሰው ስላለ የእሱ ኑሮ የተሻለ ነው። ምን አይነት ኑሮ ነው ምትፈልገው? ሲባል እንዲህ ልሆን እፈልጋለሁ፣ እንዲህ ማድረግ እፈልጋለሁ እንዲህ እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ ማለት አለብን። ይሄ ለስኬት ትልቅ ቁልፍ ነው። ህጻናት የሚፈልጉትን በግልጽ ያውቃሉ። 3. ህጻን በእምነት ይጠብቃል። ብዙ ሰው አምኖ ለሚፈልገው ነገር መስራት ይቸግረዋል። ህጻናት አንዴ እሺ ከተባሉ በኋላ አምነው ለጥ ነው የሚሉት። ይሆናል ወይ ይሳካል ወይ ብለው ምናምን ሲባዝኑ አያድሩም። እስቲ መኪናዬ ይገዛልኝ ይሆን ወይ ብሎ እጁን አገጩ ላይ አስደግፎ በጭንቀት እህህ እያለ የሚያሰላስል ህጻን ልጅ ፎቶ አሳየኝ። የለም። በቃ ያምናል። ስለዚህ የምትፈልገውን በግልጽ ካወቅክ፣ አጥብቀህ ከፈልግከው። በእምነት የገባህን ስራ። ያመንከው ይመጣል። 4. ህጻናት አስቀድመው ይደሰታሉ፣ ያመሰግናሉ! ይስቃሉ። ብዙ አዋቂ ሰው የሚፈልገውን ነገር በጉንጩ ይዞ፣ በእጁም ሌላ አዘጋጅቶ፣ በአይኖቹም ወረፋ ይዞ፤ በእጁ እና በአፉ ያለውን ነገር ማጣጣም ስለማይችል እየበላ ይርበዋል። ይዞ አይደሰትም። ለምስጋናም ይዘገያል። ህጻን ግን እንኳን የሚፈልገው ቃል ተገብቶለት ያለምክንያት ይደሰታል፣ በትንሹ ያመሰግናል። ህጻን እስኪያድግ ድረስ ደስታ ቋሚ ማንነቱ ነው። መደሰት፣ ማመስገን ተፈጥሯዊ ዝንባሌያችን ነው። የምንፈልገው ነገር ላይ አተኩረን በምስጋና እና በደስታ ውስጥ ስንሆን የኤሌክሮ ማግኔቲክ ፊርማችንን እናስተካከላለን በእዛም ከምንፈልገው ነገር ጋር እንገጣጠማለን። በአለንም በቀብድም እናመስግን እንደሰት! 5. ህጻን አይደክመውም። አንዳንዴ 11 ሰአት ወይም 12 ሰአት ወደቤት ለምንድነው የምሄደው ብዬ ሳስብ ደክሞኛል ብዬ ለእራሴ ስለነገርኩት ወይም ሌላ ሰው ወደቤቱ ስለገባ ነው ብዬ አስባለሁ። ህጻናትን ካስተዋላችሁ አለመድከማቸው አይናችንን ያደክመናል እንጂ ብዙም አይደክሙም። በቃ ምናልባት ጥቂት ቢያርፉ እንጂ እንደኛ ደከመኝ ምናምን አያውቁም። Real hustler ናቸው። አዋቂዎች እኛ ካልሰሰትነው በቀር ልክ እንደህጻን የማያልቅ እንደወንዝ የሚፈስ ሃይል እና ጉልበት አለን። ደከመኝ በሂደት የተማርነው ነገር እንጂ እኛ አዋቂ ሰዎች ልክ እንደህጻን ብርቱዎች ነን። በቀጣይነት የምንተጋ እንሁን! ✍#አብርሽ_ባታሊዮን Join👉 t.me/+96AXg7Xu84ExNM0 ☝ shear & Join ☝☝ ☝☝☝☝☝☝☝☝☝☝☝ መልካም ማታ ይሁንላቹ🙏
Show all...
Bradley Cooper አንድ የመድሃኒት እንክብል ህይወቱን በሙሉ ትቀይራዋለች። ከ ጅዝብና አለም አንስታ ወደ ባለሃይል ምጡቅ አዕምሮ ባለቤትነት ትወስደዋለች። ከወሰደችው ቦታ ደግሞ መልሳ ነጥቃ ከነበረበት የስንፍናና የድንዛዜ አለም ትጥለዋለች። ከዚህ በኋላ ህይወቱን ሙሉ ይሄን እንክብል በህይወቱ ውስጥ ዳግም ላለማጣት ሲፍጨረጨር ይታያል። Limitless በአውሮፓውያኑ 2011 የወጣ ፊልም ነው። በአይነቱ የተለየው እንክብል አስካሁን አዕምሮ የሚጠቀመውን 10% በማመንደግ ሙሉ አቅሙን እንዲጠቀምና የበራለት በመሆን በተሰማራህበት መስክ ተፈላጊ ያደርግሃል— የፊልሙ ሃሳብ። በነባራዊው አለም እንዲያ የሚባለው ነገር በኒውሮ ሳይንስም ሆነ በስነልቡናው ዘርፍ ከተረትነት ያለፈ ነገር የለውም። 10% የሚባለው የአዕምሮ አጠቃቀምም የተለመደ ሜታፈር ከመሆን እንደማይዘል ሳይንስ ያስረዳል።(ጆን ሆፕኪንስ የሜድስን ት/ቤት የሚያወጣቸውን ጥናቶች ማየት ይቻላል።) ይልቁንም እንደ ጥናቶቹ ከሆነ አዕምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሁሉንም ክፍሎቹን በየቀን አውዶች ይጠቀማል። በኛ ሃገር "አፍልኦ" የሚባል በአብነት ትምህርት ጊዜ ለበረቱት የሚሰጥ መድሃኒት እንዳለ ይነገራል። በተለምዶ አብሾ እያልን የምንለው። የወሰዱት ሰዎች ከሌሎች የላቀ የአዕምሮ ትግበራ እንዳላቸው ይነገራል። በዘርፉ ሳይንሳዊ ጥናት ተካሂዶ አልሰማንም።። በህክምናው ደግሞ ADHD (Attention-deficit/hyperactivity disorder) እየተባለ የሚጠራውን የትኩረት ማነስ መቃወስን የሚያግዙ Cognitive Enhancers እንዳሉ ይታወቃል። ይሁንና እነዚህም መድሃኒቶች እንደ Bradley Cooper የበራለት ምጡቅ ያደርጉሃል ማለት አይደለም። ትኩረትን ለማስተካከል ለባሰ የ ADHD ቀውስ ከስነልቡናው ቴራፒ ጎን ለጎን በሃኪም የሚታዘዙ እንጂ። ከላይ ባነሳነው አይነት " Limitless" የመሆን ፍላጎትን በተለያዩ እንክብሎች የማገዝ ብልሃት በስነልቡናው የ Self-Esteem መዋዠቅ ምክኒያት እንደሆነ ይታመናል። አዕምሮ ከጅምሩ ጀምሮ "Limitless" ሆኖ ተፈጥሯል። ባፍታታኸው፣ ባሰራኸውና በገራኸው ቁጥር ለራስህ የሚገርሙ ተዓምራትን ሲሰራ ታስተውለዋለህ። Limitless መሆን ካሻህ ልብህ ያረፈበትን የህይወት መስመር መለየት፣ አላማና ግብ ማበጀት ለዚያ የሚያደርሱህን ማንኛውም ፈተኛኝም ሆነ ቀላል ልምምዶች ማድረግ ትልቁ ቁልፍ ነው። ከልምምዶችህ መሃል ወደ ግብህ የሚያደርሱ ዕውቀቶችን ለመሰብሰብ "ማንበብ" አሁኑኑ ልትጅምረው የምትችለው መተኪያ የሌለው ልምምድ ነው።
Show all...
👍 1
ሥጋው እሄውና ሰውየው ለበአል 3ት ኪሎ ሥጋ ገዝቶ ለሚስቱ ይሰጣታል.... ከዛ ለመዝናናት እንደወጣ ትንሽ ቆይቶ ይመጣና ምሳ እንድትሰጠው ሚስቱን ይጠይቃታል?? ሚስት:- 3ቱን ኪሎ ሥጋ ድመቷ በላቺው አለቺው!! . ባል:- በድንጋጤ ምን እያልሽ ነው እንዴት ይህን ሁሉ በልታ ትጨርሰዋለች?? . ሚስት:- ምንም ሳታስቀር ጨረሰቺው! . ባል:- በይ ሚዛን አምጪልኝ ብሎ ድመቷን ሲመዝን 3ት ኪሎ ነች:: ባል ወደ ሚስትየው ዞሮ ምን ቢላት ጥሩ ነው..... . . . . ሥጋው እሄውና ድመቷስ??
Show all...
➡️ #ክፍል_አንድ1⃣ ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ #አዉሬ_እየመጣ_ነዉ የካህን ቅዳሴ ንጉሱን ረብሿል ጥይት በብብቱ አድብቶ ይስቃል የደሃ አደጎች እመ መኔት ሲቃ እኛን የሚያስጨንቅ መች ነው የሚያበቃ ዘንበል ብለህ ስማ ልጠይቅህ በቃ፤ በባሩድ የተኛ እንዴት አርጎ ነው በፀሎት ሚነቃ❓ ድውይ የሚፈውስ ለምፅን የሚያነፃ ዝባ ሚተረትር ከቤት ወቶ መግባት እድሜን የሚጨምር ሰላምን የሚያመጣ የሚሰብክ ፍቅር ከፀሎት ሀይል ና ከአንድዬ በቀር እኮ ንገሩኝ ሌላማ ምን ነበር? ከዳተኛው ጊዜ ዛሬ ጀገነና ለምላሳም አሽቃብጣ ብትል ደፋ ቀና ዉሸት ብትነግስ ምን ያስፈራና አሸዋ ላይ የቆመ ቤት መፍረስ አይቀሬ ነዉ እና ጊዜ የሰጠቺዉን ሁሉን ትነሳና ባዶዉን ታያለክ ነገም ቀን አለና፤ ዳሩ ምን ያረጋል ትንቢቱ ሊፈፀም ዳር ዳር እያለ ነው ለዚህም ይመስለኛል ሐሰት የምትነግሰው አንድ ካህን ይጠፋል ንስሃ ሚቀበል በቤተክርስቲያን መቅደስ ካህን ይታረዳል የምህመን ደም በአጥቢያው ይፈሳል የሀይማኖት መሪ በመንግስት ይሾማል ካድሬ መሆን ያልቻለ ከመሪነቱ ይነሳል ፀሐዩ ሳይጠልም ቶሎ ዘንበል እንበል ፤ መፍታት እና ማሰር የካህን ነበረ ግዜዉ ተገልብጦ ሁሉም ተቀየረ ቤተመንግስት የገባ ጠመንጃ ያሰረ መፍታት እና ማሰር የሱ ሆኖ ቀረ ፤ በተረት ሲወሳ ሲነገር የኖረው ያዉሬዉን መንገድ የሚጠራርገው የበግ ለምድን ለብሶ ተኩላ ግን የሆነዉ ሥጋ የለበሰ ይኸው ታየ አውሬው ደምን የሚጠጣ ሹመኛ የሆነዉ ፤ ፀሎትን ሊገታ የግዜሩን ቅሩብ መንገድ ገደል ሊገነባ እዩት ሲንገዳገድ ሲዖልን ሊገነባ በየአዉራጃዉ ሲወርድ ጎበዝ ንቃ ታጠቅ በፀሎት ተዋጋ ለሥጋህ እረፍት ለነፍስም አለው ዋጋ ፍሬ የሌለው ግን ይቆረጣል ዛፉ ሲበጠር እንክርዳድ ንፁህ የሚታየው ሚዛን ላይ ነው ትርፉ ሊያጠፉን ሲገድሉን ሕየሞትን እንበዛን ከምድርም ከሰማይ ዕርስተን አትርፈን። 🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢 🪢 🙅‍♀መታሰቢያነቱ 🪢 🪢 #በዝቋላ መስዋት 🪢 🪢 ለሆኑ እህትእና ወንድሞቼ 🪢 🪢 እንዲሁም ለሀይማኖት 🪢 🪢 መሪዎቼ ይሁንልኝ👈 🪢 🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢 ➻➻ጌታ ሆይ መቼ ትመጣለህ❓ ➻➻እባክህ ቶሎ ና ፍርድህ ናፍቆናል ❗❗ ✍ #Bataliyon(አብርሽ) 👉 ቻናሉን መቀላቀል እና ማጋራት አይዘጋ ❗❗👇👇👇👇 👉t.me/+96AXg7Xu84ExNmM0👈 🔚🔚🔚🔚🔚🔚🔚🔚🔚🔚🔚🔚🔚
Show all...
➡️ ክፍል አንድ1⃣ #አዉሬ_ እየመጣ_ነዉ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 የካህን ቅዳሴ ንጉሱን ረብሿል ጥይት በብብቱ አድብቶ ይስቃል የደሃ አደጎች እመ መኔት ሲቃ እኛን የሚያስጨንቅ መች ነው የሚያበቃ ዘንበል ብለህ ስማ ልጠይቅህ በቃ፤ በባሩድ የተኛ እንዴት አርጎ ነው በፀሎት ሚነቃ❓ ድውይ የሚፈውስ ለምፅን የሚያነፃ ዝባ ሚተረትር ከቤት ወቶ መግባት እድሜን የሚጨምር ሰላምን የሚያመጣ የሚሰብክ ፍቅር ከፀሎት ሀይል ና ከአንድዬ በቀር እኮ ንገሩኝ ሌላማ ምን ነበር? ከዳተኛው ጊዜ ዛሬ ጀገነና ለምላሳም አሽቃብጣ ብትል ደፋ ቀና ዉሸት ብትነግስ ምን ያስፈራና አሸዋ ላይ የቆመ ቤት መፍረስ አይቀሬ ነዉ እና ጊዜ የሰጠቺዉን ሁሉን ትነሳና ባዶዉን ታያለክ ነገም ቀን አለና፤ ዳሩ ምን ያረጋል ትንቢቱ ሊፈፀም ዳር ዳር እያለ ነው ለዚህም ይመስለኛል ሐሰት የምትነግሰው አንድ ካህን ይጠፋል ንስሃ ሚቀበል በቤተክርስቲያን መቅደስ ካህን ይታረዳል የምህመን ደም በአጥቢያው ይፈሳል የሀይማኖት መሪ በመንግስት ይሾማል ካድሬ መሆን ያልቻለ ከመሪነቱ ይነሳል ፀሐዩ ሳይጠልም ቶሎ ዘንበል እንበል ፤ መፍታት እና ማሰር የካህን ነበረ ግዜዉ ተገልብጦ ሁሉም ተቀየረ ቤተመንግስት የገባ ጠመንጃ ያሰረ መፍታት እና ማሰር የሱ ሆኖ ቀረ ፤ በተረት ሲወሳ ሲነገር የኖረው ያዉሬዉን መንገድ የሚጠራርገው የበግ ለምድን ለብሶ ተኩላ ግን የሆነዉ ሥጋ የለበሰ ይኸው ታየ አውሬው ደምን የሚጠጣ ሹመኛ የሆነዉ ፤ ፀሎትን ሊገታ የግዜሩን ቅሩብ መንገድ ገደል ሊገነባ እዩት ሲንገዳገድ ሲዖልን ሊገነባ በየአዉራጃዉ ሲወርድ ጎበዝ ንቃ ታጠቅ በፀሎት ተዋጋ ለሥጋህ እረፍት ለነፍስም አለው ዋጋ ፍሬ የሌለው ግን ይቆረጣል ዛፉ ሲበጠር እንክርዳድ ንፁህ የሚታየው ሚዛን ላይ ነው ትርፉ ሊያጠፉን ሲገድሉን ሕየሞትን እንበዛን ከምድርም ከሰማይ ዕርስተን አትርፈን። 👉መታሰቢያነቱ #በዝቋላ መስዋት ለሆኑ እህት እና ወንድሞቼ እንዲሁም ለሀይማኖት መሪዎቼ ይሁንልኝ👈 ➻➻ጌታ ሆይ መቼ ትመጣለህ❓ ➻➻እባክህ ቶሎ ና ፍርድህ ናፍቆናል ❗❗ ✍ #Bataliyon 👉 ቻናሉን መቀላቀል እና ማጋራት አይዘጋ ❗❗👇👇👇👇 👉t.me/+96
Show all...
✍ የተክልዬዋ 🎙ፋሲክ
Show all...
00:56
Video unavailable
Fkrrr❤
Show all...
#ባንጾም_አይሻልም 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➫ አብዛኛዎቻችን ምግብን ብቻ ስለተዉን እንደጾምን እናስባለን፤ እስከ ዘጠኝ ስዓት አሊያም እስከ አስራ ሁለት ስዓት ስለቆየን ጾመናል ማለት አይቻልም። 👉 አዎ! መጾም ብቻ አያፀድቅም ❗ ምግብን ጾመን በዓይናችን መጥፎ ስራዎችን የምንሰራ ከሆነ ፤ዓይናችንን ለክፉ ነገር የምንጠቀም ከሆነ ምኑን ጾምን❓ ከአንደበታችን አስቀያሚ እና ሰዉን የሚያሳዝን ቃሎችን እያወጠን ከሆነ ባንጾም ይሻላል። አሆን መጾም ያለብን ከምግብ ብቻ አይደለም ❗❗ ዓይናችን ሊጾም ይገባል ፤አንደበታችን ሊጾም ይገባል ፤ጆሮ እና ህሌናችን ሊጾም ይገባል እንዲሁም እጅ እና እግራችንም ሊጾሙ ይገባቸዋል ❗❗ 👉 በተለይ አንተ ባጾም ይሻልካል ማንን ነዉ የምታታልለዉ❓ እራስክን ወይስ................አሆን አብሮክ ላለ ሰዉ ክፋትን እያሰብክ ፤ የወዳጆችህን ዉድቀት እየተመኘክ ፤አባቶችህን እያገላመጥክ እናትህን እያመናጨክ፤ታላቅህን እያቃለልክ ፤ጓደኛክን እየሰደብክ፤እየዋሸክ መዋሸትክ ሳያንስ ግጥም አድረገክ እየማልክ እያስማልክ፤እያጭበረበርክ እያለልክ ፤በሐሰት እየመሰከርክ በሐሰት እየወነጀልክ ከሆነ ባጾም ይሻልካል #ለምን _ትጾማለክ❓ 👉 አንተም አድምጠኝ ባለንጀራ ተቸግሮ እያየክ ባላየ እያለፍከዉ ሰዎች ያንተን እርዳታ ፈልገዉ እርዳታክን እየነፈክ ለምን ትጾማለክ? ስንቱን እያስለቀስክ ቢሮ ቁጭ ብለክ የስንቱን እንባ እያፈሰስክ ላንተ አንዲት ፊርሚያ ሳምንት እያመላለስክ መቼ በዚህ አበቀክ ጉቦ እየጠየክ ፤ ይህም አልበቃ ብሎክ ባንተ ተራ ወሬ ስንቱን ደም እያቃበክ የሰንቱን ደም እና ላብ እየጠጠክ ለምን ምግብ ትጾማለክ? ለምንስ ትሰግዳለክ አንተን ብሎ ሰጋጅ❗❗ ➫ ሆድክን ከመጾምክ በፊት ዓይንክ ይጹም ፤አንደበትክ ይጹም፤ጆሮክ ይጹም ፤እጅና እግርክ ይጹሙ፤ ወዳጄ ሆይ ምግብን ጾመክ የሰዉ ስጋ የምትበላ ከሆነ ለምን ትጾማለክ? ከሰዉ ስጋ ምግቡን ብትበላ አይሻል፤ የሚጠጣውን እየጾምክ የሰዉን ደምና ላብ የምጠጣ ከሆነ መጠጡን እንደልብክ ብጠጣ አይሻልም ከሰዉ ደምና ላብ ❗ 👉 እባካችሁን ምግብና መጠጥን እየጾምን ከላይ ያሉትን ነገሮች የምናደረግ ከሆነ ባንጾም ይሻላል ምክንያቱም ጾም ቅዱስ ነዉ በእኛ እርኩስ ስራችን አናርክሰዉ ፤ እራሳችንን እንጠይቅ እስኪ የምንጾመዉ ምን ዓይነት ጾም ነዉ? ምግብን ብቻ ነዉ? ምግብን ብቻ የምንጾም ከሆነ ለምን እንጾማለን❓ ምን ፈልገን ነዉ❓ብንጾምስ ጥቅሙ ምንድነዉ? #ባንጾም_አይሻልም❓❓ ➰➰➰➰➰➰➰➰➰➰➰➰ 👇👇 መልሱን በታች ባለዉ ሊንክ ላኩልኝ 👇👇 #ሀሳብ ለመላክ 👉👉👉 @icanwin ✍ #አብርሃም_Bataliyon 👉 ማካፈል እና ማጋራት አይረሳ👇👇 👇 ቤተሰብ ይሁኑ ቻናላችንን ያጋሩ👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👉 t.me/+96AXg7Xu84ExNmM0 ➺➺➺➺➺➺➺➺➻➻➻➻➻➻➻➻
Show all...
BATALIYON (ባታሊዮን) 📘📙📗

👉 ማንበብ ለራስ ነዉ 📚📗📘📙

Anyways መልካም የ አብይ ፆም እና የ ረመዳን ፆም ይሁንላችሁ ❤️ ሳንቡሳዋን ግን አደራ😭🤲
Show all...
🎯🎯🎯🎯🎯🎯 በአንገታችን ላይ ያለውን ሀብል ፍለጋ…… 🔹 🎯 ሳምንቱን ሙሉ የስልኬን ቻርጀር ፈልጌ አጥቼው ጠፋ ብዬ ተስፋ ቆረጬ ነበር። አዲስ ቻርጀር ለመግዛት በማሰብ ላይ ሳለው፤ ዛሬ ጠዋት ድንገት አገኘሁት። ያገኘሁት ደግሞ አስር ጊዜ ፈልጌ ካጣሁበት ከቦርሳዬ ውስጥ ነበር። በራሴ ሳቅኩኝ……እንኳንም ሌላ ከመግዛቴ በፊት አገኘሁት ብዬ ደስ አለኝ። ግራ የገባኝ ግን፤ ያለማጋነን ይህንን ቦርሳ ደግሜ ደጋግሜ ፈትሼዋለው፤ እንዴት አላየሁትም? የሚለው ነው። ነገሩ የገባኝ በኋላ ነው፤ ለካ ቻርጀሩን ያስቀመጥኩት ብዙም በማልጠቀምበት ኪስ ውስጥ ነበር። 🔹🔹 እዚህ ላይ ነው ከዚህ በፊት ደጋግሜ የሰማሁትን የሩሚን ግጥም ያስታወስኩት። “You wander from room to room Hunting for the diamond necklace That is already around your neck!” “በአንገትህ ላይ ያለውን ሀብል ፍለጋ፤ ከክፍል ክፍል ትዞራለህ” ማለቱ ነው። 🔹🔹🔹 🎯የኔም የዛሬው ጠዋት ገጠመኝ ከዚህ አልተለየም። ነገር ግን ይህ የህይወት ሚስጥር በስልክ ቻርጀር ወይም በአንገት ሀብል የሚያቆም አይምስለኝም። አጠጋብችን ሆነው ሳሉ፤ እሩቅ ቦታ የምንፈልጋቸው ስንት ነገሮች አሉን? አንገታችን ላይ ታስረው በየክፍሉ እየበረቀስን ለማግኘት የምንደክምላቸው ፤ብዙ አመት አብረውን ከርመው ሳለ፤ እኛ ግን ገና ይመጣሉ ብለን የምንጠብቃቸው ብዙ ነገሮች አሉን። የሌሉን የሚመስለን፤ በሚስጥር ኪሳችን ውስጥ ተደብቀው ያሉ እጅግ ብዙ ሀብቶች አሉን። 🔹🔹🔹🔹 🎯አንዳንድ ሰዎች ለምን እራሳቸውን እንዳማይለውጡ ስትጠይቋቸው እንዲህ አይነት መልስ ይሰጣሉ “እራሴን እስካገኝ”፤ ታዲያ ይህ አንገት ላይ የታሰርን ሀብል ሌላ ቦታ እንደመፈለግ አይደለም? ተሰጥዋችን እና ችሎታችን እንዲሁም ማንነታችን እኮ አንገታችን ላይ እንደታሰረው ሀብል ነው። አብሮን የኖረ ሆኖ ሳለ….እኛ ግን ሁሌም ፍለጋችን ውጪ ውጪውን ነው። ለዚህም ነው ለምንፈልገው ኑሮ የሚረፍድብን ብሎም የማንደርሰው። 🔹🔹🔹🔹🔹 🎯ከዚህ ጋር የሚያያዝ አንድ ሌላ ታሪክ ጨምሬ ላካፋልችሁ፤ ሰውየው የቤቱን ቁልፍ ቤቱ ውስጥ ይቆልፍበትና ይወጣል። ከሄደበት ሲመለስ ቁልፉን ፍለጋ ይጀምራል። ከበሩ ደጃፍ ላይ እየተዘዋወረ ፍለጋውን ይያያዘዋል። በእሱ በኩል የሚያልፍ አንድ ሰው ይመለከተውና “ቁልፍህን እዚህ አካባቢ ጥለኸው ነው?” ሲል ይጠይቀዋል። አብሮት ለማፈላለግ ማለት ነው። ይሄኔ ሰውየው “አይ ቁልፉን እንኳን ውስጥ ነው የቆለፍኩበት” ይላዋል። መንገደኛውም ግራ ተጋብቶ “ታዲያ ለምን ውስጥ የጣልከውን ቁልፍ ውጪ ትፈልጋለህ” ሲለው፤ ሰውየውም “አይ ውስጥ ጨለማ ስለሆነ ነው” ሲል መለሰለት አሉ። 🔹🔹🔹🔹🔹 🎯ውጪ ብርሃን ስለሆነ ብቻ ውስጥ የጣልነውን ነገር መፈለግ የእኛም ልማድ ነው። በቤታችን ያጣነውን ሰላምና ፍቅር ውጪ የምንፈልግ ስንቶቻችን ነን? ውስጣችን የጠፋውን ማንነት ብርሃን ባየንበት የምንፈልግ በጣም ብዙዎቻችን ነን። 🔹🔹🔹🔹🔹🔹 🎯በህይወታችን ለሚገጥሙን ችግሮች አብዛኛው መፍትሄ ውስጣችን ነው ያለው። የኛ ሞኝነት ግን ልክ ሀብሉን በአንገቱ አስሮ በፍለጋ እንደሚደክመው ሰውዬ ወይም የቤቱን ቁልፍ በውስጥ ዘግቶበት ብርሃን ስላገኘ ብቻ ውጪ ውጪውን እንደሚፈልገው ሰው መሆናችን ነው። ፍለጋችን ከውስጣችን ካልጀመረ…..የምንፈልገውን ማንኛውንም ነገር ለማግኘት ብዙ መድከማችን አይቀርም። 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 🎯የምንመኘው ፍቅር፤ የምንጓጓለት ቤተሰብ፤ የምንፈልገው ማንነት ምናልባት አንገታችን ላይ ታስሮ ሊሆን ይችላልና፤ ውጪ በፍለጋ ከመድከማችን በፊት መፍትሄውን ውስጣችን እንፈልግ። የጠፋብን ሰላም እና ፍቅር የተደበቀው እኛው ውስጥ ቢሆንስ…..ከሌላ ሰው ልብ ውስጥ ከመፈለጋችን በፊት የኛን ጓዳ እንፈትሽ። አብዛኛው የችግሮቻችን መፍትሄ በእርግጥም አንገታችን ላይ ታስሯል። ሲጀምር ሳይጠፉብን ለምን በፍለጋ ህይወታችን ይባክናል? ✍ #Bataliyon(አብርሽ) 👉👉 ለሁላችንም ያማረ የደመቀ የተዋበ እና የስኬታችን የጾም ጊዜ ይሁንልን❗❗ 🎯🎯🎯🎯🎯 የቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ ለአስተያየትዎ እና ጥያቄ @icanwin
Show all...