cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አዲስ ሚዲያ

ሰላም የተከበራችሁ ቤተሰቦቻችን በዚህ ቻናል ➮ የተለያዩ የመዝናኛው አለም መረጃዎች ➮ አስገራሚ የፍቅር ታሪኮች ➮ ጨዋታዎች ➮ የሙዚቃ ስራዎች እንዲሁም ➮ አጫጭር ፊልሞች ይቀርባሉ ሰብስክራይብ በማድረግ አባል ይሁኑ👇👇 @ADISS_MEDIA_NET

Show more
Advertising posts
238
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ መሀመድ ከክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ጋር ውይይት አደረጉ ። **** ርእሰ መስተዳድሩ በጅግጅጋ ፕሬዝደንት ፅ/ቤት አደራሽ በተካሄደው ስነ ስርአት ላይ  ስለ አዲሱ የልዩ ኃይል አደረጃጀት እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ለሰራዊቱ አባላት ዝርዝርና የተሟላ ግንዛቤ ሰጥተዋል። በመድረኩ ላይ የክልሉ ፀጥታ ቢሮ  ምክትል ኃላፊ፣ የፀጥታ አማካሪዎች፣ የልዩ ኃይሉ አመራሮችና አባላት የተገኙ ሲሆን ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎችም ርእሰ መስተዳድሩ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።  ሱማሌ ፈጣን መረጃ
Show all...
👍 7
Photo unavailable
#እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ/ሼር ይደረግ! #የአማራ ህዝባዊ ሠራዊት በጎንደር "ኮማንድ ፖስቱን"እንደማይቀበለው እና በቀጣይ 10 ቀናት የሚያደርገውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ለማስተጓጎል የሚሞክር ማንኛውም አካል ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠነቀቀ። ከነገ ሚያዚያ 04/2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 13/2015 ዓ.ም ለአስር ቀናት በጎንደር ከተማና አካባቢው የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እናስተላልፋለን። ይህን አድማ ኮማንድ ፖስት በሚል አጉል ክልከላ ለማደናቀፍ በሚሞክሩና በሚያደናቅፉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት በጎንደር ያስጠነቅቃል። የትግሉን አቅጣጫ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ብያኔ ለማበጀት፤ ከሌሎች አካባቢ የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት መሪዎች ጋር በመነጋገር ቀጣይ አቅጣጫዎች እያስቀመጠ እንደሚቀጥል ጨምሮ ይገልፃል። ከአማራ ህዝባዊ ሰራዊት በጎንደር አስተባባሪ ኮሚቴ ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
Show all...
Photo unavailable
ከኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በ“ከባድ የሙስና ወንጀል” ከተከሰሱት ግለሰቦች ውስጥ አምስቱ በፍርድ ቤት ነጻ ተባሉ ከአዲስ አበባ ኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በ“ከባድ የሙስና ወንጀል” ክስ ከተመሰረተባቸው ግለሰቦች ውስጥ የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱን ጨምሮ፤ አምስት ግለሰቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ ተባሉ። በዚሁ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ግለሰቦች መካከል አንድ ተከሳሽ በሌሉበት ጥፋተኛ ሲባሉ፤ ቀሪ አምስት ተከሳሾች ደግሞ የተከሰሱበት ድንጋጌ ተቀይሮ እንዲከላከሉ በፍርድ ቤቱ በይኗል። ይህን ብይን የሰጠው ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 4/2015 የዋለው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ችሎት ነው። ችሎቱ አምስት ተከሳሾችን በነጻ ያሰናበተው፤ “ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ፤ ወንጀሉን በበቂ ሁኔታ ባለማስረዳቱ” መሆኑን ገልጿል። በነጻ ከተሰናበቱት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አብርሃም ሰርሞሎ እና የከተማይቱ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ቢሮ የአይሲቲ ዳይሬክቶሬይትን ሲመሩ የነበሩት ኩምሳ ቶላ እንደሚገኙበት ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።    
Show all...
1
አሁን ከራያ ቆቦ የደረሰን መረጃ  ‼️ #ሪፖርተር_ET ጧት የጀመረው በከባድ መሳሪያ የታጀበው የተኩስ ልውውጥ አሁንም ተባብሶ መቀጠሉን አረጋግጠናል!! ጧት ከነበረው አሁን ተባብሶ መቀጠሉን በዚህም መድፍ የዙ 23 እና ሌሎችም ከባድ መሳሪያ ድምፅ እንደሚሰማ ነገረውኛል፤በአሁኑ ሰዓት ሰፈር ለሰፈርም ጭምር የጨበጣ ተኩስ እንዳለም ነገረውኛል።ፋኖ ከአማራ ልዩ ሀይል ጋር በመሆን የመከላከያ ሰራዊትን እየተዋጉት እንዳለና ከሁለቱም በኩል መስዕዋት የሆኑም እንዳሉ ለማወቅ ችለናል።(©️ ሪፖርተር ET) ከቀኑ 10:35 ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ👇👇
Show all...
👍 2
ስልጣን ለምን አለቁም ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ የጠቅላይ ሚንስሩ ምላሽ‼️ ስልጣን መልቀቅ ካለብን ሁላችንም መሆን አለበት። ጥያቄው እኔን ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ስልጣን እንልቀቅ የሚል ቢሆን መልካም ነበር። እረስዎም (አቶ ክርስቲያን ታደለ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የአንድ ንዑስ ኮሚቴ ሀላፊ ነዎት ስለዚህ ስልጣን መልቀቅ ካለብን በጋራ ሁላችንም ነው መሆን ያለበት፣አሁን እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች የሁላችንም እጅ አለበት ያሉ ሲሆን ይሄ መንግሥት ስልጣን የሚለቀው የተሻለ ሀሳብ ሲመጣ እና በምርጫ ብቻ ነው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ስልጣን በመናጆ አይገኝም ብለዋል
Show all...
Photo unavailable
በእንግሊዝ ለ20 ዓመታት ባሏን ስትደበድብ የነበረችው ሚስት በአራት ዓመት እስር እንድትቀጣ ተወሰነ በእንግሊዝ የሶስት ሴት ልጆች እናት እና የፍትህ ሚኒስቴር ከፍተኛ ስራ አስኪያጅ የሆናችው ሺሪ ስፔንሰር ለ20 ዓመታት ያህል ባለቤቷን ሪቻርድ ትደበድበው እንደነበር በማስረጃ ተረጋግጧል።የ46 አመቱ እንግሊዛዊ በሚስቱ የደረሰባትን ጉዳት ለመደበቅ ሜካፕ ይጠቀም እንደነበር ገልጿል። ሪቻርድ ለልጆቹ ብሎ ትዳሩን መፍታት ባይፈልግም የደረሰበትን በሙሉ ግን በቪዲዮ ማስረጃ አስደግፏል።ፊት ላይ ምራቅ መተፋት እንዲሁም ሸሪ በእጇ የያዘችውን ማንኛውም ነገር ጠርሙስ፣ ሞባይል እና የቲቪ ሪሞትን ወርውራ ትመታው ነበር። አንድ ጊዜ የቤቱ ወለል ላይ ተጸዳዳች እናም እንዲያጸዳው አስገድዳዋለች። በልጆች የመጫወቻ ክፍል ውስጥ ባለው የደህንነት ካሜራ በተገኘው ምስል መሰረት በቢላ ስታስፈራራው፣ ወለሉ ላይ ስትጎትተውና ስትደበድበው ያሳያል።የሪቻርድ ጓደኞች ሼሪ እንዲህ ዓይነት ነገር ታደርጋለች ብለው እንደማይጠብቁና ሁኔታ እንዳስገረማቸው ገልፀዋል።ጉዳዩ ለፖሊስ የደረሰው በሪቻርድ ጓደኛ አማካይነት ነው። ሸሪ በዩናይትድ ኪንግደም ሃል ክራውን ፍርድ ቤት የአራት አመት እስራት የተፈረደባት ሲሆን የቀረበባትን የወንጀል ክስ አምናለች። Via ዳጉ ጆርናል
Show all...
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
ይነበብ‼️    ወደ ሳኡዲ የተላኩ ኢትዮዽያዊያን የቤት ሰራተኞች ስፖንሰር ከሁሉም አገራት ዝቅተኛ ክፍያን በያዘ ዋጋ ነው የተላኩት። ከዚህ በታች በምስል እንደምታዮት ከሆነ አንዲት ኢትዮዽያዊ የቤት ሰራተኛ ለመውሰድ 6,900 የሳኡዲ እሪያል ብቻ ነው የሚከፍሉት። አንዲት የኢንዶኔዥያ ሰራተኛ ለመውሰድ  17ሺ 288 ሪያል ሲከፍሉ አፍሪካዊቷ የኬኒያ ልጆች ደግሞ 7500 ሪያል ይከፈላቸዋል። ከሌሎች አገሮች ሲሰላ የሀገራችን ልጆች ከኬኒያ በ100ሪያል ዝቅ ባለ የክፍያ ዋጋ ይይዛሉ በመሰረቱ ይህ ክፍያ አሁን ባለው ኢኮኖሚ ምንም አይነት ጥቅም የሚያስገኝ ሳይሆን ዜጋን በግልፅ አጫርቶ የመሸጥ ያህል ነው።  ስለዚህ ነውር ግን አንድም ትንፍሽ ያለ አመራር የለም (ሱሌማን አብደላ)
Show all...
Photo unavailable
ባልደራስ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን እንዳያደርግ ተከለከለ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ እሁድ መጋቢት 3፤ 2015  ሊያካሄድ የነበረውን ጠቅላላ ጉባኤውን እንዳያደርግ ተከለከለ። ጠቅላላ ጉባኤው ሊካሄድ የነበረበት ጋምቤላ ሆቴል፤ ስብሰባውን ማስተናገድ እንደማይችል እንደነገራቸው የፓርቲው አመራሮች አስታውቀዋል። የተቃዋሚ ፓርቲው አባላት በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ለመገኘት በአዲስ አበባ ራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ በሚገኘው ጋምቤላ ሆቴል የተገኙት ሁለት ሰዓት ጀምሮ ነበር። የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አርማ በለጠፉ ተሽከርካሪዎች ላይ የተጫኑ የፖሊስ አባላት፤ በሆቴሉ መግቢያ አካባቢ ቆመው ሁኔታውን ሲከታተሉ የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ ተመልክቷል። ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ከ30 ገደማ ላይ አንድ የጋምቤላ ሆቴል አስተዳደር ሰራተኛ፤ ለጠቅላላ ጉባኤው አስተባባሪዎች እና ተሳታፊዎች  “የተፈቀደ ስብሰባ” እንደሌለ አስታውቃለች።  በሆቴሉ ስብሰባ እንደማይኖር መገለጹን ተከትሎ፤ የባልደራስ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አምሃ ዳኘው እና ሌሎች የፓርቲው ተወካዮች ከሆቴሉ አስተዳደር ጋር ለ20 ደቂቃ ገደማ ውይይት አድርገዋል። ከውይይቱ በኋላ የባልደራስ አመራሮች በሆቴሉ መግቢያ በር ላይ ሆነው ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል። የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት፤ ባልደራስ ጋምቤላ ሆቴል ጉባኤውን ለማድረግ “ፈቃድ ማግኘቱን” ተናግረዋል። ሆኖም ለጉባኤው የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን ለማስፈጸም የፓርቲ አመራሮች ባደረጓቸው ሂደቶች፤ ተደጋጋሚ ተግዳሮቶች እንዳጋጠማቸው አስረድተዋል። Via: - ethiopiainsider
Show all...
በ5 ወሯ የተወለደችው እንግሊዛዊ በአስደናቂ ሁኔታ ከሞት ተረፈች!! ከተጸነሰች በ22 ሳምንቷ (154 ቀን) የተወለደችው “ኢሞጀን” የተሰኘች ህጻን ግምቶችን ውድቅ አድርጋ ከ132 ቀናት የሆስፒታል ቆይታ በኋላ በእናቷ እቅፍ ውስጥ ሆናለች። ኢሞጀን እናቷ ሪቼል ስቶንሃውስ በድንገተኛ ህመም ወደሆስፒታል አቅንታ መወለድ ከነበረባት 126 ቀናት አስቀድማ ስትወለድ 515 ግራም ትመዝን ነበር። በእናቷ ማህጸን እድገቷን ሳትጨርስ ስዋንሲ ሲንግልተን በተባለ ሆስፒታል መወለዷ ግድ የሆነው ህጻን፥ ወዲያውኑ ሰው ሰራሽ ማሕጸን ውስጥ እንድትገባ ተደርጎ ክትትል ይደረግላት ጀመር። ሀኪሞችም የህጻኗ የመትረፍ እድል ከ10 በመቶ በታች እንደሆነ ቢያውቁም ተስፋ ሳይቆርጡ ለ132 ቀናት የዘለቀ ድንቅ ጥረታቸውን ቀጠሉ።ያለጊዜዋ የተወለደችው ኢሞጀን በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ ሆና ያሳለፈችውን ስቃይ ማየት እጅግ ሰቅጣጭ ነበር የምትለው እናቷ ሪቸል፥ “ልጄ እኛ ትልልቆቹ የማናልፈውን ፈታኝ ጊዜ አሸንፋ አልፋዋለች፤ ያመንኳቸው የህክምና ባለሙያዎችም አላሳፈሩኝም” ብላለች። ሪቼል በማህጸኗ ውስጥ የሚገባትን ማግኘት ያልቻለችውንና የገጠማትን የልብ ህመም ጭምር ለማስተካከል ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ባለሙያዎችም አመስግናለች።ሪቸል እና ባለቤቷ በአስደንጋጩ ክስተት ምክንያት የአዕምሮ መቃወስ እንዳይገጥማቸው ለሶስት ወራት በሆስፒታሉ ውስጥ ማረፊያ ተዘጋጅቶላቸው የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ቢቢሲ ዘግቧል። በ22 ሳምንቷ ተወልዳ፤ በብዙ ስቃይ ውስጥ አልፋ ከሆስፒታል የወጣችው ኢሞጀን አሁን በወላጆቿ እንክብካቤ እየተደረገላት ነው።ለመተንፈስ ስለምትቸገር ኦክስጂን የሚያስፈልጋት ቢሆንም ማየትም ሆነ መስማት መቻሏ እና የከፋ የጤና ችግር የለባትም መባሉም ከ4 ወራት በላይ በስቃይ ላሳለፉት ወላጆች ትልቅ ደስታን ፈጥሯል። በአለማችን ያለጊዜው ተወልዶ በህይወት በመትረፍ ክብረወሰኑን የያዘው ክሪስ ኬት ሚንስ የተባለ አሜሪካዊ ህጻን ነው።ክሪስ በአላባማ በርሚንግሃም ሆስፒታል በ21 ሳምንት ከ1 ቀኑ (ከተጸነሰ በ148 ቀናት) ሲወለድ 420 ግራም ይመዝን የነበረ ሲሆን፥ የመትረፍ እድሉም ከ1 በመቶ በታች ነው ተብሎ ነበር።ክሪስም ሆነ ኢሞጀን ግን ሞትን ታግለው ሳይንሳዊ ግምቶችን መሻር ችለዋል። @ADISS_MEDIA_NET @ADISS_MEDIA_NET  
Show all...
" ተጥሎ የነበረው የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት እግድ ተነስቷል " - ዶ/ር ቀንኣ ያደታ በአዲስ አበባ ከተማ ተጥሎ የነበረው የመሬትና መሬት ነክ  አገልግሎት እግድ መነሳቱን የከተማዋ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ቀንአ ያደታ ፤ የመሬትና መሬት ነክ መረጃዎችን ለማጥራት ሲባል በጊዜያዊነት ተጥሎት የነበረው የአገልግሎት እግድ ተነስቷል ብለዋል። እግዱ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከትናትን የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱን ሃላፊው ተናግረዋል። የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ባለጉዳዮችም አስፈላጊ መረጃዎችን በመያዝ ከሚመለከተው አካል አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡ በመዲናዋ የመሬት ወረራንና ሕገወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሲባል የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት ከጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በጊዜያዊነት ታግዶ መቆየቱ ይታወሳል፡፡  https://t.me/ADISS_MEDIA_NET https://t.me/ADISS_MEDIA_NET
Show all...
አዲስ ሚዲያ

ሰላም የተከበራችሁ ቤተሰቦቻችን በዚህ ቻናል ➮ የተለያዩ የመዝናኛው አለም መረጃዎች ➮ አስገራሚ የፍቅር ታሪኮች ➮ ጨዋታዎች ➮ የሙዚቃ ስራዎች እንዲሁም ➮ አጫጭር ፊልሞች ይቀርባሉ ሰብስክራይብ በማድረግ አባል ይሁኑ