cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Hjgnhttxvgcyvuvyc

Show more
Ethiopia6 590The language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
752
Subscribers
No data24 hours
-107 days
-5430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ይሄን Channel የጀመርኩት ወይም የከፈትኩት ፊያሚታ ከምትባል ልጅ ጋር የፍልስፍና ክርክር ስንጀምር ነበር እና ልላት ምፈለገውን በዚ Channel በኩል ነበር የምነግራት.....ከዚያም ተባጠስን ክርክራችንም ፍልስፍናችንም ቆመ ንግግራችንም ቀመ...... . . እኔም የ Channelen purpose ቀይሬ በጥቂቱም ቢሆን የተሻለ አስተሳሰብ በሰዎች ውስጥ ማኖርን ፈለኩ በጥቂቱም ቢሆን አንባቢ እንዲሆኑ ፈለኩ...... Geta ይመስገን በጥቂቱ የፈለኩትን በብዙ አሳክቼዋለው....... እና ከ 2 አመት በላይ ለነበረን ቆይታ የምር ከ ልብ አመሰግናለው ደና ሁኑልኝ 😊......😞😞❤️‍🔥😞😞❤️‍🔥
Show all...
💗ሮ💗ማ💗ን💗 የመጨረሻው ክፍል😌 🖍...<<ለዛሬ የቀጠርኩህ በሲጋራ ማጨስና ጉዳቱ ዙሪያ ለጤናችን ፕሮግራም ካንተ ጋር ቃለ መጠይቅ ለመስራት ስለፈለግኩ ነው›› የመጨረሻዎቹን ቃላት በውል አላዳመጥኳቸውም፡፡ የተቀመጥኩበት ወንበር ወደ ውስጥ ይዞኝ የገባ መስሎኝ ከንፈሬን በጥርሴ እንደነከስኩ አይኖቼን በሀይል ጨፈንኳቸውና በዝምታዬ ውስጥ ራሴን ገደልኩ፡፡ ከተቀበርኩበት ድንገተኛ ሰመመን ስነቃ ሮማን በእጇ የያዘችውን የድምጽ መቅጃ እያሻሸች በድንጋጤ እየተመለከተችኝ ነበር፡፡ ‹‹ ደህና ነህ? ›› አለችኝ፡፡ ጭንቅላቴን በአዎንታ ነቀነቅኩላት፡፡ ከዚያም እጄን ወደኪሴ ሰድጄ የተጨማተረ ሲጋራ መዘዝኩና አቀጣጠልኩ፡፡ ወደ ውስጥ የሳብኩት ጭስ ከአፌ እየወጣ አየር ላይ ተበታትኖ ወዲያና ወዲህ ሲቅበዘበዝ ሳይ እምባዬ መጣ፡፡ 🚬🚬🚬🚬 መድረሻውን የማያውቀው ጭስ የኔ ህይወት ተምሳሌት መሰለኝ፡፡🚬🚬 እንዲያውም ይህ የሲጋራ ጭስ መነሻውን ያውቃል፡፡ እኔ ግን መነሻና መድረሻዬን የማላውቅ፣ ከየት መጥቼ ወዴት እየሄድኩ እንደሆነ ያልተረዳሁ ምስኪን ሠው ነኝ፡፡ ሲጋራውን ጠላሁት፡፡ ጭሱን ማየት ቀፈፈኝ፡፡ መሬት ላይ ጣልኩትና በጫማዬ ደፈጠጥኩት፡፡ ኪሴ ውስጥ የነበረውን ሁሉ እያወጣሁ ስብርብር አደረግኩት፡፡ ነፍሴ ስትረጋጋ ታወቀኝ፡፡ በዛፎቹ መካከል እየተሽሎከለከ እኛ ወዳለንበት ጎጆ ቤት የሚገባው ነፋስ አዲሱን የህይወቴን ገጽ መግለጥ ጀመረ፡፡ ከዚህ በፊት የማላውቀው አዲስ ስሜት ውስጤ ገብቶ ቦታ ሲፈልግ አገኘሁት፡፡ ልቤን ሰጠሁት፡፡ በደስታ ተሞላሁ፡፡ መጮህ አማረኝ፡፡ ሮማን በሁኔታየ ግራ ተጋብታለች፡፡ ከአፏ ቃል ሳታወጣ በጭንቀት እየተነፈሰች የማደርገውንና የምሆነውን ትከታተላለች፡፡ የውስጤን ስሜት ሳዳምጥ ቆይቼ ዝቅ ባለ ድምጽ‹‹ አመሰግናለሁ ›› አልኳት፡፡ ከፀጉሯ ጋር በጣቷ እየተጫወተች በዝምታ ተመለከተችኝ፡፡ ‹‹ ከረዥም ጊዜ ፍቅረኛዬ ጋ አለያዬሽኝ ›› ደነገጠች፡፡ ‹‹ ምን; ›› እንደምንም ከአፏ የወጣ ቃል ነው፡፡ ‹‹ ለረዥም ጊዜ እንደ ፍቅረኛዬ ስንከባከበው ከነበረው ሱስ ጋር ዛሬ አለያየሽኝ›› ከተቀመጠችበት ድንገት ተነስታ ተጠመጠመችብኝ፡፡ ሽቶዋ ልቤን አጠፋው፡፡ ከልቤ ጋር ፍርሃቴም አብሮ ጠፋ፡፡ ለካ የፍርሃት ቤቱ ልብ ነው! እንደተቃቀፍን የመጣው ይምጣ ብዬ ከንፈሯን ፍለጋ ስኳትን ያ- ክልፍልፍ አስተናጋጅ ዘው ብሎ ገባ፡፡ ‹‹ ጠራችሁኝ እንዴ? ›› እያለ፡፡ 📓ተፈፀመ📓 JOIN & SHARE @ethio_lebold CONTACT US @typing080 💞የፍቅር ጐጆ❤ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Show all...
💗ሮ💗ማ💗ን💗 ክፍል4⃣ 🖍...ይሁንና አንዴ ሲጋራውን ሌላ ጊዜ ደግሞ አይኔን እያፈራረቀች መመልከቷን አላቆመችም፡፡ ይህቺ ቆንጆ ሴት ከዚህ በፊት እንደምታውቀኝ እርግጠኛ ሆኛለሁ፡፡ በውበቴ ሳትነደፍ አልቀረችም፡፡ የአበሻ ልማድ ይዟት እንጂ የፍቅር ጥያቄ ልታቀርብልኝ ፈልጋለች፡፡ አይኖቿ ውስጥ ‹እወድሃለው› የሚሉ ፊደላትን እያስነበበችኝ ነው፡፡ በአፏ የምታወራው ግን የማይጨበጥ ነገር ነው፡፡ ‹‹እነዚህ አስተናጋጆች አለባበሳቸው በጣም ያምራል፤ አለባበስ ደንበኞችን ለመሳብ ከሚያስፈልጉ ወሳኝ ነገሮች አንዱ ነው፡፡›› ትለኛለች፡፡ እኔ ጭንቅላቴን ከመነቅነቅ ውጪ መልስ አልሰጣትም፡፡ ትንሽ ቆይታ ደግሞ ሎተሪ አዟሪ በፊታችን ሲያልፍ አይታ ‹‹ሎተሪ አዟሪዎች እድለኛ ባይሆኑም ሊከፋቸው አይገባም፡፡ ምክንያቱስ በለኝ.....›› የምትፈልገውን ልልላት ምላሴን ሳዘጋጅ የኔን ‹ምክንያቱስ› ሳትጠብቅ ‹‹ምክንያቱስ ብትለኝ ሎተሪ አዟሪዎች እድል ባይኖራቸውም ይዘውት የሚዞሩት ግን አድልን እራሱን ነው፡፡ ስለዚህ ደስ ሊላቸው ይገባል›› አለችኝ፡፡ ሀሳቧ ቢገባኝም እኔ ግን ምንም አልተናገርኩም፡፡ በዚህ መሃል ‹‹የጋዜጠኛ ነገር የኔን ወሬ ብቻ እንድታዳምጥ አደረግኩህ አይደል?›› አለችኝ ያንኑ ልብ የሚሰውር ፈገግታዋን በፊቷ እየረጨች፡፡ ተገረምኩ፡፡ ከአንደበቴ ድንገተኛ ቃላት ወጡ፡፡ ‹‹እንዴ ጋዜጠኛ ነሽ እንዴ?›› ስል ጠየቅኳት፡፡ ‹‹ምነው አንሳለሁ ወይንስ....›› ‹‹አይ እንደዛ ማለቴ ሳይሆን........›› ንግግሬን ገታ አድርጌ ፈገግ ለማለት ሞከርኩ፡፡ ለጥቂት ጊዜ በመካከላችኝ የፀጥታ ድባብ ተዘረጋ፡፡ በዝምታ ውስጥ ሆነን በአይን መጠናናት ያዝን፡፡ ከዚያም ድንገት ‹‹ነገ 12 ሰዓት አካባቢ ስራ ይኖርሃል፡፡ ማለቴ ‹ቢዚ› ነህ?›› ጠየቀችኝ፡፡ የፈጣሪ ያለህ! ድንጋጤ ነፍሴን ሊነጥቀኝ ደረሰ፡፡ የልብ ትርታዬ ከመጠን በላይ መታ፡፡ ማራቶን የሮጥኩ መሰለኝ፡፡ ‹እወድሃለሁ› የሚል ቃል ብትናገር ምን ልሆን ነው? ድንጋጤዬን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ ይቀጥላል... አንብቦ ማለፍ ትንሽነት ነው፡፡የ👍 ምልክት በመጫን አበረታቱን። JOIN & SHARE @ethio_lebold CONTACT US @typing080 💞የፍቅር ጐጆ❤ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Show all...
💗ሮ💗ማ💗ን💗 ክፍል6⃣ 🖍...አለባበሷ እንደነገሩ ነው፡፡ ‹‹ከስራ ቦታ በቀጥታ ነው እንዴ የመጣሽው?›› አልኳት ደግማ ስለመዘግየት እንዳታወራኝ አቅጣጫ ለማስቀየር፡፡ ቀስ በቀስ ፍርሃቴ እየጠፋ መጥቷል፡፡ ‹‹አዎን ከዚያው መምጣቴ ነው›› አለች አረማመዷን ከኔ ፍጥነት ጋር ለማስተካከል እየሞከረች፡፡ ዝናቡ ማንጠባጠብ ጀምሯል፡፡ መናፈሻ ውስጥ ካሉት ትንንሽ ጎጆ ቤቶች መካከል አንዱን መርጠን ገባን፡፡ ወዲያው የሆነ ክልፍልፍ አስተናጋጅ እየተንደረደረ መጥቶ የምንፈልገውን ጠየቀን፡፡ ፈጥኖ መምጣቱ አበሳጭቶኛል፡፡ ‹‹ቡና!›› አልኩት በቁጣ፡፡ የኔን ትዕዛዝ ተቀብሎ በመጣበት አኳኋን እየተክለፈለፈ ተመልሶ ሄደ፡፡ ሳቄ መጣ፡፡ ከጥድፊያው የተነሳ እሷን ሳይታዘዛት ነው የሄደው፡፡ እጄን ላጨበጭብ ስዘጋጅ ሮማን ድንገተኛ ወሬ ጀመረች፡፡ ‹‹ያው ለዛሬ የቀጠርኩህ.....›› ከማለቷ አስተናጋጁ ተመልሶ መጣ፡፡ ‹‹ለእርስዎስ ምን ላምጣልዎት እመቤቴ?›› ሲል ጠየቃት እየተቅለሰለሰ፡፡ ‹እርስዎ› ስላላት ይሁን ወይም ንግግሯን ስላቋረጣት እንጃ ቆጣ ብላ ‹‹ለኔም ቡና!›› አለችው፡፡ እየሮጠ ወጣ፡፡ ሲሮጥ ድንጋይ አደናቅፎት ሊወድቅ ነበረ፡፡ እንደሰካራም ተንገዳግዶ ለጥቂት ተረፈ፡፡ እሱ እንደወጣ ሮማን ንግግሯን ቀጠለች፡፡ ‹‹ምን መሰለህ? ለዛሬ የቀጠርኩህ...እ...›› ጭኗ ላይ ያስቀመጠችውን ቦርሳ መደባበስ ያዘች፡፡ ልቤ በድንጋጤ መምታት ጀምሯል፡፡ አፈቅርሃለው የምትለዋን ቃል ለመስማት መቁነጥነጥ ያዝኩ፡፡ ግን ምንድነው የምመልስላት? እኔም አፈቅርሻለሁ ልበላት? ይሄ እንኳን አይሆንም፡፡ ገና በአንድ ቀን እንደዛ ብላት ትንቀኛለች፡፡ በቃ ላስብበት እላታለሁ፡፡ ወይኔ ጉዴ! ምንድነው የሚያቃዠኝ? እኔ በሃሳብ ስዳክር ሮማን ጉሮሮዋን አፅድታ የጀመረችውን ንግግር ጨረሰችው፡፡ ‹‹ያው ለዛሬ የቀጠርኩህ..... ይቀጥላል.... አንብቦ ማለፍ ትንሽነት ነው፡፡የ👍 ምልክት በመጫን አበረታቱን። JOIN & SHARE @ethio_lenold CONTACT US @typing080 💞የፍቅር ጐጆ❤ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Show all...
💗ሮ💗ማ💗ን💗 ክፍል2⃣ 🖍....ፈገግ አለች፡፡ ፈገግታዋን ከመብረቁ ብልጭታ ጋር ማወዳደር ጀመርኩ፡፡ በምድር ስትመጣ እንዳላየኋት ሁሉ ከሰማይ የወረደች መሰለኝ፡፡ እኔም ፈገግ አልኩላት፡፡ ጥርሶቼን ግን አልገለጥኳቸውም፡፡ ሁሌም እንዲህ ነኝ፡፡ በዓይኖቼ እንጅ በጥርሶቼ አልስቅም፡፡ በልጅነቴ ህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ እያለሁ ጓደኞቼ አይኖቼ እንደሚያምሩ ይነግሩኝ ስለነበር ከጥርሶቼ ይልቅ በአይኖቼ እኮራለሁ፡፡ በርግጥ ያኔ ጥርሶቼ ያምሩ ነበር፡፡ ዛሬ ግን በሲጋራ ጭስ በልዘው አፌን የሲኦል መንገድ አስመስለውታል፡፡ ሮማን እጆቿን ለሰላምታ ዘረጋችልኝ፡፡ ስለኔ ጥርስና ስለእሷ ውበት እያሰብኩ ለሰላምታ የትኛውን እጄን መዘርጋት እንዳለብኝ ጠፋኝ፡፡ ሁለት እጆቼን አነባብሬ ሰጠኃት፡፡ በሚያማምሩ ጣቶቿ የቀኝ እጄን ለቀም አደረገችውና ለአፍታ በአይኖቿ ገላይን ከላይ እስከታች ዳበሰችው፡፡ ዛሬ ያለወትሮዬ ሽክ ብያለሁ፡፡ አለባበሴን እንደወደደችው ከአስተያየቷ ተረዳሁ፡፡ ከጓደኛዬ የተዋስኩትን ጥቁር ሱፍ ጀርባዋ ከተቀደደ ባለነጠብጣብ ሸሚዝ ጋር ለብሻለሁ፡፡ የጨበጠችውን እጄን ሳትለቅ ‹‹ ወደመናፈሻው እንግባ?›› ስትል ጠየቀችኝ፡፡ ስትናገር የምትዘፍን ትመስላለች፡፡ ‹‹ደስ ይለኛል›› አልኳት ሊስም ፈልጎ ያሞጠሞጠ ከንፈሬን ወደ ቦታው እየመለስኩ፡፡ ሰላሳኛ አመቴን እየደፈንኩ ቢሆንም ካሁን በፊት የሴት ጓደኛ ኖሮኝ አያውቅም፡፡ ፍቅሬን ለሲጋራ እንጂ ለሴት የሰጠሁበት ጊዜ አልነበረም፡፡ የወንድ ጓደኞቼ በየጊዜው ፍቅረኛዬ ናት እያሉ የተለያዩ ሴቶቻቸውን ያስተዋውቁኝና ‹‹ያንተን ፍቅረኛ ግን ለምን አታስተዋውቀንም?›› ይሉኛል፡፡ ‹‹የለኝም›› ስላቸው አያምኑኝም፡፡ ‹‹እንዴት ላይኖርህ ይችላል አንተኮ ለሴት እንጂ ለወንድ የማይገባውን ውበት ይዘሃል፡፡ መልከ መልካም ነህ፡፡ በዚያ ላይ ገንዘብ ባይኖርህ እንኳ አሪፍ ጭንቅላት አለህ፡፡ ታዲያ እንዴት ፍቅረኛ የለኝም ትላለህ?›› ይሉኛል፡፡ ዝም እላቸዋለሁ፡፡ እነሱን ለማስረዳት ከምሞክር ከአዲስ አበባ ባህርዳር በእግሬ ብጓዝ እመርጣለሁ፡፡ ፈፅሞ ሊያምኑኝ አይችሉም፡፡ እኔና እግዚአብሔር በምናውቀው ሃቅ ግን እኔ እንኳን ሴት ፍቅረኛ ሴት እህት የለኝም፡፡ ብዙ ጊዜ ቆንጆ ሴቶችን ሳይ ቀድሞ ጉልበቴ ይዝላል፡፡ ላብ በጀርባዬና በግንባሬ ይፈሳል፡፡ ያደኩት ህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ከወንዶች ጋር ስለነበር ሴቶች ባሉበት ቦታ መገኘት ያስፈራኛል፡፡ ሴቶችን እንዴት ማናገር እንዳለብኝ እንኳን ጠንቅቄ አላውቅም፡፡ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እያለሁ ጓደኞቼ ከሴቶች ጋር ‹በግተራ› ሲያመሹ እኔ ቤተመፅሐፍት ውስጥ ተቀብሬ ምሽቱን አሳልፍ እንደነበር አልዘነጋውም፡፡ አንዳንዴ ፍቅረኛ የሚኖረኝ መቼ ነው ስል እራሴን እጠይቅና አንድ ቀን በሚል መልስ እዘጋዋለሁ፡፡ እንዳልኩትም ያ - አንድ ቀን ከረጅም አመታት በኋላ ዛሬ ከተፍ አለ፡፡ ይቀጥላል... JOIN & SHARE @ethio_lebold CONTACT US @typing080 💞የፍቅር ጐጆ❤ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Show all...
💗ሮ💗ማ💗ን💗 ክፍል3⃣ 🖍...በትናንትናው ቀፋፊ ቀን ከአለቃዬ ጋር በመጣላቴ በንዴት ስራ አልገባሁም ነበር፡፡ ቀኑ ብርዳምና አልፎ አልፎ እንደህፃን ልጅ ሽንት እየተቆራረጠ የሚዘንብ ካፊያ ዝናብ የነበረበት ቀን ነው፡፡ የጥጥ ነጋዴ የሚያስመስለኝን ወፍራም ካፖርት ለብሼ የለመድኳት ካፌ ውስጥ ገብቼ ቁጭ አልኩ፡፡ ራሴን ከብርዱና ከንዴቱ ለመገላገል አስቤ ኪሴ ውስጥ ያከማቸሁትን የተጨማተረ ሲጋራ በጣቶቼ እያልመዘመዝሁ በላይ በላዩ ማጨሴን ተያያዝኩት፡፡ ካፌዋ ‹ማጨስ ክልክል ነው› የሚል ማስታወቂያ የተለጠፈባት ቢሆንም ለኔ አይሰራም፡፡ ደንበኛቸው ስለሆንኩ አንድም ቀን ተናግረውኝ አያውቁም፡፡ ያዘዝኩትን ቡና አጋምሼ ጠረጴዛው ላይ እንዳስቀመጥኩት አንዲት ሴት ወደኔ ተጠግታ ሰላምታ አቀረበችልኝ፡፡ የለመድኩት ፍርሐቴ መጣ፡፡ ለሰላምታዋ ምላሽ ለመስጠት ዘገየሁ፡፡ ወደውስጥ የሳብኩትን የሲጋራ ጭስ ረሳሁት፡፡ ሳንባዬን አስጨንቆት ኖሮ በትንታ ተጣደፍኩ፡፡ ልጅቷ ተደናግጣ ስትመለከተኝ ቆየችና ‹‹ይቅርታ›› አለችኝ፡፡ ከዚያም ከጎኔ ያለውን ወንበር በጣቷ እያመለከተች ‹‹ወንበሩ ሰው አለው?›› ስትል ጠየቀችኝ፡፡ አንገቴን ግራና ቀኝ በማወዛወዝ ሰው እንደሌለው አሳወቅኳት፡፡ ቁጭ አለች፡፡ የተቀባችው ሽቶ አፍንጫዬን አልፎ ወደ ውስጤ ሲገባ አንዳች ልዩ ስሜት ውስጤን አናወጠው፡፡ እንደምንም ቀና ብዬ ለአፍታ አየኋት፡፡ ፀጉሯ አጭር ሲሆን የፊቷ ውበት ግን እንከን አይወጣለትም፡፡ ላነጋግራት ብፈልግም ቃላቶች ለዚያን ሰዓት ያልተፈጠሩ ይመስል አንደበቴ ዝግ ሆነ፡፡ በቃ ዝም-ዝም፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ‹‹መተዋወቅ ጥሩ ነው....እንተዋወቅ የኔ ስም ሮማን ወርቅ ይባላል ›› አለችና እጇን ዘረጋችልኝ፡፡ ፈገግታዋ ልብን ያሸብራል፡፡ እጆቼ እንዳይንቀጠቀጡ በመጠንቀቅ የተዘረጋውን እጇን ጨበጥኩትና የኔንም ስም ነገርኳት፡፡ ከዚያ ስለዓየር ሁኔታው፣ ስለተቀመጥንበት ወንበርና ስለሌሎችም ነገሮች አወራን፡፡ ብዙውን እሷ ናት የምታወራው፡፡ ሮማን ያዘዘችውን ማኪያቶ በማንኪያ እያገላበጠች ሲጋራ የጨበጥኩበትን እጄን ደጋግማ ስታይ ማጨስ የፈለገች መሰለኝና ከተጨማደዱት ሲጋራዎቼ አንዱን አውጥቼ ጋበዝኳት፡፡ ትንሽ ፈገግ ብላ እንደማታጨስ ነገረችኝ፡፡ አላግደረደርኳትም፡፡ ለራሴው አጨስኩት፡፡ ይቀጥላል... JOIN & SHARE @ethio_lebold CONTACT US @typing080 💞የፍቅር ጐጆ❤ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Show all...
💗ሮ💗ማ💗ን💗 ክፍል5⃣ 🖍...ድንጋጤዬን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ ‹‹ ነገ .. ነገ .. ነገ .. እ .. ነገ ስራ የለኝም! ›› አልኳት፡፡ ግን ውሸቴን ነበር፡፡ አያቴን ወደክሊኒክ ለመውሰድ ቀጠሮ ይዤ ነበር፡፡ ‹‹ እንግዲያማ መገናኘት እንችላለን ማለት ነው ›› አለች ሮማን፡፡ ‹‹ እ .. አዎ .. እንችላለን ››አልኩ ፈጠን ብዬ ሀሳቧን እንዳትቀይር የፈራሁ ይመስል፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ሮማን ከመቀመጫዋ ተነስታ እጄን ጨበጠችኝና የጠጣንበትን ሂሳብ ከፍላ የቀጠሮውን ቦታ ነግራኝ ተሰናብታኝ ሄደች፡፡ የካፌው ተሰተናጋጆች ሮማንን ከኋላዋ በአይኖቻቸው አጀቧት፡፡ እንደዚያ አፍጥጠው ሲያዩዋት ተበሳጨሁ፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ጉሮሮአቸውን ፈጥርቄ ከግድግዳው ጋር ባጋጫቸው ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ቅናት ወረረኝ፡፡ ፍቅረኛዬ ላይ አይናቸውን ማፍጠጣቸው አንገበገበኝ፡፡ ሲጋራዬን እያወጣሁ አፌ ላይ መጣድ ጀመርኩ፡፡ ጭሱ በግንባሬ በኩል በቀስታ እየተመመ የካፌውን ጣሪያ ለመንካት ጉዞ ሲጀምር ቀና እያልኩ እመለከተዋለሁ እኔን ይመስለኛል፡፡ የማላውቀውን፣ መቼ እንደጠፋብኝ ያልተገነዘብኩትን ህልም እንደምፈልገው፡፡ በሃሳብ ውስጥ ስናውዝ ድንገት የሞባይል ስልኬ ጠራ፡፡ ደዋዩ ጓደኛዬ ዩሐንስ ነው፡፡ አለቃዬ ሲፈልገኝ እንደነበር ሊነግረኝ ነው የደወለው፡፡ ‹‹እሱን ተወው ባክህ! ይልቅ አንድ ወሬ ልንገርህ›› አልኩት፡፡ ‹‹ምንድነው የምትነግረኝ....ዝም ብለህ ለሰውየው ብትደውልለት ይሻላል›› ሲል መለሰልኝ፡፡ ‹‹በቃ እሺ እደውልለታለሁ... ዛሬ ምን እንደተፈጠረ ልንገርህ?›› ‹‹ምንድነው ምን ተፈጠረ?›› ‹‹ፍቅረኛዬን አገኘኋት!›› ‹‹አገኘኋት?›› ‹‹አዎ አገኘኋት.. ወይም አገኘችኝ! ቆይ አስተዋውቅሃለው... ብታያት በቃ ልዕልት ናት! Princess›› የካፌው ተስተናጋጆች ዘወር ዘወር እያሉ ተመለከቱኝ፡፡ ሳላውቀው በጣም እየጮህኩ ነበር ለካ፡፡ **** ‹‹ዘግይቻለሁ እንዴ ግን?›› ጠየቀችኝ ሮማን ጎን ለጎን ሆነን ወደመናፈሻው እየገባን ሳለን፡፡ ምን ነካት ልጅቷ ስንት ጊዜ ነው የምትጠይቀኝ? መዘግየት ብርቅ መሰላት እንዴ? ‹‹እንዲያውም ፈጥነሽ ነው የመጣሽው›› ስል መለስኩላት ለአፍታ በአይኖቼ እየቃኘኋት፡፡ አለባበሷ እንደነገሩ ነው፡፡ ይቀጥላል.......... JOIN & SHARE @ethio_lebold CONTACT US @typing080 💞የፍቅር ጐጆ❤ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Show all...
💗ሮ💗ማ💗ን💗            (አጭር ልቦለድ) ክፍል1⃣ 📝...የሰማዩ ገጽ ጠቁሯል፡፡ በቁጣ የተሞላ ይመስላል፡፡ ያረገዘውን ዝናብ ወደመሬት ለመጣል ይቁነጠነጣል፡፡ ከአፉ የሚተፋው የመብረቅ ብልጭታ በድምጽ ታጅቦ ከደመናው በታች ይታያል፡፡ ከፊት ለፊቴ ሰዎች ወዲያና ወዲህ ሲሯሯጡ እመለከታለሁ፡፡ ከመጣው መአት ራሳቸውን ለማዳን የሚሸሸጉበት ጥግ ፍለጋ በደመነፍስ ይጓዛሉ፡፡ እኔ ግን እዚህ ቁሜያለሁ፡፡ የመናፈሻውን በር ተደግፌ እሷን በመጠበቅ ላይ እገኛለሁ፡፡ በዚህ ጥቁር ሰማይ ስር ጫፍ አልባ ሩጫ የሚሮጡን ሰዎች በአይኔ እየማተርኩ የቀጠረችኝን ሴት ከነሱ መካከል ለማግኘት እፍጨረጨራለሁ፡፡ ቀይ፣ አፍንጫዋ ጎራዳ፣ አጭር ጸጉርና ረጅም ተክለ ቁመና ያላት ሴት እይታየ ውስጥ እንድትገባ መጸለይ ይዣለሁ፡፡ ቀጠሯችን 12 ሰዓት ነው፡፡ 10 ደቂቃዎች አልፈዋል፡፡ ‹ምነው ዘገየች? የውሸቷን ነበር እንዴ የቀጠረችኝ?› እያልኩ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ይሄን ክፉ ሃሳቤን ልቀጥልበት ስንደረደር ድንገት በትከሻዋ ቦርሳ ያነገበች ረጅም ሴት የመንገዱን ጠርዝ ይዛ እየተጣደፈች ወደእኔ ስትመጣ ተመለከትኩ፡፡ እሷ ናት፡፡ ሮማን፡፡ ልቤ መዝለል ጀመረ፡፡ በሴትና ወንድ ግንኙነት ውስጥ የማላውቃቸው፣ የማይገቡኝ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር በመጀመርያው ቀን ቀጠሮው ሲገናኝ ሰላምታ የሚሰጣት እንዴት ነው? ጉንጯን መሳም? ከንፈሯን መሳም? በትከሻው ትከሻዋን መደለቅ? ወይስ ምን? አላውቅም፡፡ በዚህ ጉዳይ ጓደኞቼን ማማከር ነበረብኝ፡፡ ልደውልላቸው ይሆን? ሞባይል ስልኬን ፍለጋ ኪሶቼን ስፈታትሽ ፊት ለፊቴ መጥታ ቆመችና ‹‹ይቅርታ! ዘገየሁ እንዴ?›› አለች፡፡ ድምጽዋ በጣም ያምራል፡፡ ‹‹ድምጽሽ ያምራል›› አልኳት አፌ ላይ እንደመጣልኝ፡፡ ‹‹ አመሰግናለሁ! ብዙ አስጠበኩህ? ›› እንደገና ጠየቀችኝ፡፡ ‹‹ አይ .. ደህና ነኝ .. ምንም አልል ... ማለቴ ብዙ ጠበቅኩሽ እንዴ? ›› መናገር የፈለኩት ጠፋብኝ፡፡ ተንተባተብኩ፡፡ ይቀጥላል ... JOIN & SHARE @ethio_lebold Contact Us @typing080 💞የፍቅር ጐጆ❤ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Show all...
🙏በፀሎት🔥 #ክፍል1⃣6⃣ #ተከታታይ ልቦለድ የማየውን ማመን አልቻልኩም ማመንም አልፈለኩም እንዴት ብዬ? በሩ መከፈቱን ሲመለከቱ ሁለቱም ከተቀመጡበት ተነሱ ሳግ አፍኖኛል አይኔ በእንባ ጭጋግ ዳምኗል ኤርሚያስ በድንጋጤ ፊቱ አመድ መስሏል በፀሎትን እየሸሸ አንዴ እኔን አንዴ በፀሎትን እያፈራረቀ ግራ በመጋባት ይመለከተናል ከዚ በላይ መቋቋም አልቻልኩም እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ ‹‹ማናችሁ! አንቺ ማነሽ? ምንድነው ነገሩ ቆይ የትኛዋ ናት በፀሎት?›› ኤርሚያስ ይጠይቃል መልስ የሚሰጠው የለም ለካስ ስሜ በፀሎት እንደሆነ ነው የሚያውቀው የእርሱ እንዲህ ግራ መጋባት ደግሞ የበለጠ ነገሮችን ለመረዳት እንዳልችል አወሳሰበብኝ አሁን እርሱም እንደኔ የበፀሎት ወጥመድ ውስጥ እንደወደቀ ገባኝ ወደ በፀሎት ተጠግቶ ‹‹ማነሽ አንቺ ?›› ትከሻዋን ይዞ ሲወዘውዛት ‹‹በፀሎት እኔ ነኝ!!›› አለችው ወደ እኔ ሲመጣ ጭቅጭቃችንን የሰማችው እናቴ ወደ እቤት ገባች ሶስታችንንም እያፈራረቀች ተመለከተችን እና ‹‹በፀሎት!!….. ልጄ… እ›› ብላ ዝልፍልፍ ስትል ልትወድቅ እንደሆነ ቀድሞ የገባው ኤርሚያስ ተንደርድሮ መሬት ከመድረሷ በፊት ተቀበላት ምድር ሰማዩ ዞረብኝ ‹‹ልጄ ነው ያለችው? የምን ልጅ? በፀሎት የእኔ እህት ናት? ሊሆን አይችልም! ቆይ እንዴት መንታ እህት አለኝ ማለት ነው? አንድ ግዜ እንኳን እንደዚ ሊሆን እንደሚችል እንዴት አላሰብኩትም?›› ቁጥር ስፍር የሌላቸው ጥያቄዎች ጭንቅላቴን ወጥረው ሊያሳብዱኝ ደረሱ ‹‹ኸረረረ ኢቺ ሴትዮ ትቀልድ የለ እንዴ የሞተችው እናቴ ተነሳች እኮ!!!›› ብላ ከጣሪያው በላይ ሳቋን ለቀቀችው እና ቦርሳዋን አንስታ ስትወጣ አንዲት የድንጋጤ ወይም የጥርጣሬ ስሜት ሳይታይባት ‹‹ይሄን ቦታ ለቀሽ ካልሄድሽ ልብሽን እንደምሰብረው ነግሬሽ ነበረ አሰታወሽ? ያውልሽ በፍቅርሽ ትንሽ ተደብሬበታው ከአሁን በኋላ ደግሞ አልፈልገውም ያንቺ ነው መልሼልሻለው ›› ብላኝ ወጥታ ሄደች፡፡ ሰዎች ተሰብስበው እናቴን አፋፍሰው ወደ ሀኪም ቤት ሲወስዷት የሚሆነውን እያየው ከመደንገጤ የተነሳ ምንም ማድረግ አልቻልኩም፡፡ በፀሎት ይሄ ሁሉ ሲፈጠር ምንም ሳይመስላት ትንሽ እንኳን ሳትረበሽ መሄዷ ደግሞ ሌላ ተአምር ሆኖብኛል፡፡ ከታማሚነት ወደ አስታማሚነት በሰአታት ልዩነት ውስጥ ሽግግር አደረግኩ ግን እኔም በቂ እረፍት ማድረግ ስለነበረብኝ ከእናቴ አጠገብ ተቀምጬ አይን አይኗን አያታለው እንጂ ሁሉም ቦታ እየተሯሯጠ የእናቴን ሂወት ያተረፈልኝ ኤርሚያስ ነው፡፡ ባየወት ቁጥር ስለ እርሱ ምን እንደሚሰማኝ አላውቅም ትኩር ብሎ አንዳንዴ ሲያየኝ አይን ለአይን እንገጣጠም እና አይኔን እሰብራለው ለእርሱ ይቅርታ ማድረግ ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላውቅም በተለይ እናቴ እንዳለችው በፀሎት እህቴ ሆና ከተገኘች ነገሮችን ለመቀበል ከምገምተው በላይ እንደሚከብደኝ ይሰማኛል እናቴ የደም ግፊት ስለበረባት ነው በፀሎትን ስታይ በድንጋጤ የወደቀችው ኤርሚያስ ሰዎች አስተባብሮ በፍጥነት ሀኪም ቤት ባትሄድ ኖሮ እህን ግዜ አጥቻት ነበረ፡፡ በነጋታው በጠዋት የኤርሚያስ ስልክ ጮኸ እኔንም ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ እርሱ ነው ከዛን ቅፅበት በኋላ እንኳን ልናወራ በሙሉ አይን ተያይተን አናውቅም ነበር የተደወለለትን ስልክ ትንሽ ካወራ በኋላ ‹‹ላንቺ ነው›› ብሎ ሰጠኝ የማን መሆኑን ሳይ የእራሴ ስልክ ቁጥር ነው ‹‹ሄለው ›› አልኩኝ በፀሎት ነበረች አባቷ በሂወት እና በሞት መካከል እያጣጣረ እንዳለ ነገረችኝ እና አንድ ውለታ እንድውልላት ‹‹አባቴ ስላንቺ ሰምቷል እና አንድ ጊዜ አይንሽን ማየት ይፈልጋል እባክሽ አባቴ እንዳደርግለት የጠየቀኝን ነገር አለማድረግ አልችልም አንዴ መጥተሸ እይው ?›› ነበር ያለችኝ አባትዋን እንደምትወደው በአንደበቷ ስትናገር ሰምቻታለው ሆስፒታል መሆኑንም ጭምር ታድያ የእርሷ አባት በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እኔን ማየት ለምን አስፈለገው? እናቴ ያለችው ነገር እውነት ነው ማለት ነው? በአንድ በኩል እንደዚ አስባለው በሌላ በኩል ደግሞ ስንት ጊዜ ትታለያለሽ ቃል ኪዳን እረፊ የጀመረችውን ነፍስሽን የመንጠቅ ስራ ልትጨርሰው ነው! አርፈሽ ተቀመጪ! አላየሽም እንዴ እናትሽ ልጄ ስትላት እንዴት ስቃ እንደሄደች? በዛ ላይ እርሷ ለማንም ነፍስ የምትራራ አይደለችም አትሂጂ ይለኛል፡፡ …..በመጨረሻ ከእራሴ ጋር ብዙ ስጣላ ከቆየው በኋላ አባቴ ተኝቶበታል ወዳለችበት ሆስፒታል ሄድኩ የተኛበት ክፍል በሩ ላይ ስደርስ በፀሎት ብቻዋን ተቀምጣ በግልኮስ እርዳታ ነፍሱ የቆየውን አባቷን ትጠብቃለች እንዳየችኝ ከተቀመጠችበት ተነሳች ፊቷ ላይ የተመለከትኩት የሀዘን እና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ግን እድሜ ልኬን የሚረሳኝ አይመስለኝም ያኔ ዘናቡ ላይ ቆማ ሳያት ተስፋ የቆረጠች የመሰለኝ ትክክል ነው ሁለታችንም ከቃላት በላይ የሆኑ ንግግሮችን በአይኖቻችን ተነጋገርን ተስፋ መቁረጧን በአይኗ ብቻ እንደተረዳውት የአባቷን ፍላጎት ለማሟላት ስለመጣው በአይኗ አመሰገነችኝ ‹‹ አባ አባቴ..እቺውት መጥታለች›› አለችው ቀ ስ ቀ ስ ቀ ስ ቀ ስ እንደማድረግ ብላ የአባቷ አይኖች በቀስታ ተገለጡ ገና ጎልማሳ ነው አባቷ ግን በሽታው ሰውነቱን ጨርሶት አቅም አሳጥቶታል እጆቼን ለመያዝ ሲሞክር አቅም አንሶት ተዝለፈለፈ ሰውነቱ ከመመናመኑ ብዛት እጆቹ እንኳንስ ለመያዝ ሲታይም ያስፈራል እጆቹ መያዝ ሲያቅታቸው እኔ ለመያዝ ስፈራ ተመልክታ እጆቼን ያለ ፍቃዴ ጎትታ የአባቷ እጆች ላይ አሳረፈቻቸው ተሳቀቅኩ እሷ ደግሞ በግልምጫ ከመሬት አንስታ ደባለቀችኝ እጄን ስትጎትተኝ ሙሉ ለሙሉ ያልዳነው ቁስሌ በሀይለኛው አመመኝ እና አቃሰትኩ እሳቸው ሲይዙኝ ግን በቀስታ እና በልስላሴ ስለሆነ የቁስሉ ህመም ቀስ በቀስ እየተወኝ ሄደ ‹‹ ቃል..ኪዳን…ልጄ…››ሲሉኝ ልቤ ለሁለት ተከፈለ እናቴ እስከ ዛሬ አባቴ በህይወት እንዳለ እህትስ እንለኝ ለምን ደበቀችኝ? እውነት ይህ ሰው አባቴ የተንኮል ቋት የሆነቸው በፀሎት ደግሞ እህቴ ናት? ይሄ እውነት ውስጤን ምንኛ ጎዳኝ እንዲህ ያለ አባት ከሚኖረኝስ ዝንት አለም አባት ሳይኖረኝ ቢቀር ይሻለኛል፡፡ ‹‹አ ባ ት ሽ እኔ ነኝ ልጄ ›› አለና ሀይለኛ ሳል ያጣድፈው ጀመር ሳሉ እረፍት አልነበረውም ሲስል በየመሀሉ አክታውን ሲተፋ ሙሉ ለሙሉ ደም ነው ከአፍ የሚወጣው ይህን ማየት ስለዘገነነኝ በፀሎት በማስታጠቢያ አጠገቡ ሆና ስትቀበል ክፍሉን ለቅቄ ወጣው ፡፡ አንድ ማህፀን ያፈራን አንድ ላይ ተቃቅፈን የተረገዝን ልጆች ነን እናቴ እናቷ አባቷ አባቴ ናቸው ግን አንዳችን ለአንዳችን ምንም ስሜት የለንም ከመወለድ በላይ አብሮ በማደግ የምናገኘውን የእህትማማችነት የወላጅ ፍቅር ቤተሰቦቻችን ነጥቀውናል በፀሎት ጠላትነ በሀይል እንዴት ማሸነፍ እንደምትችል ተንኮል ተምራ አደገች እኔ ቃል ኪዳን ከሰው ጋር እንዴት በፍቅር መኖር እንደሚቻል ተምሬ አደኩ ወላጆች ሁሌም የልጆች መሰረት ናቸው እሾህ እየዘሩ ስንዴ መጠበቅ ቂልነት ነው የተዘራ ይበቅላል አውሬ እንኳን ፍቅር ለሰጠው ፍቅር ያውቃል ፡፡ .........ይቀጥላል.........✍ ቀጣዩን#ክፍል1⃣7⃣እንዲቀጥልLike👍ማድረግ እንዳይረሳ ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ 👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Amiryeee አድርሱን 📗📒📕📗📒📕 Join&share @Ethio_leboled 📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚 📖📖📖📖📖📖
Show all...
🙏በፀሎት🔥 #ተከታታይ ልቦለድ #ክፍል1⃣4⃣ አሁን ምንድነው እሺ የማደርገው? በቃ ፍቅረኛ ያዝኩ ማለት ነው? ያውም በዚህ ፍጥነት ነዋ! ስሙ ማነው እሺ? ስሙን እንዴት ነው ማወቅ የምችለው? አይኖቼ በክፍሉ ውስጥ ከዛና ከዚ ሲራወጡ ስሙን የማወቂያ መንገድ ፍለጋ ሱሪውን አየውት አንድ አይነት ነገር ማግኘቴ አይቀርም መቼም ሱሪው ውስጥ ተንደርድሬ ሄጄ ሱሪውን አነሳው እና መፈተሸ ጀመርኩ መታወቂያዎች አገኘው ፈጥኜ መታወቂያውን ከፍቼ ስሙን አነበብኩ ኤልያስ እንግዳየው ይላል ግልግል መታወቂያውን ቦታው መልሼ ወደ አልጋዬ ተመለስኩኝ እያፏጨ ፎጣውን እንደጠቀለለ ታጥቦ ሲመጣ ተረኛ እኔ መሆኔን ተረድቼ ለመታጠብ አንሶላ ተጠቅልዬ ስነሳ ‹‹ኸ ረረረ ቆይ እንዳትወድቂ ደግሞ እኔ ልጠብሽ ›› አለና ደገፈኝ ‹‹ኸረ በፍፁም እኔ ምንም አልሆንም ደና ነኝ ያንተ እርዳታ አያሥፈልገኝም ›› ድጋፉን አስለቅቄ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባው ከመታጠቢያ ቤት ስወጣ ቆንጆ ቁርስ እየሰራ እንደሆነ አፍንጫዬ ነገረኝ ለመብላት ቋመጥኩ ግን ልብሴን ለብሼ እስክጨርስ እንኩዋን ምግቡ አልደረሰም ስላላስቻለኝ ማብሰያ ክፍል ድረስ ስሄድ ቱታ እና ቲሸርት ለብሶ ፓስታ በመቀቀል ስራ ተጠምዷል ‹‹ ቁርስ አይደርስም እንዴ በጣም እርቦኛል›› አልኩኝ ዞር ብሎ አየኝ እና ‹‹ኦ አድካሚ ስራ ላይ ነዋ የነበርሽው….›› ደስ የሚል ሳቁን ለቀቀው ‹‹ሂ ወደ ዛ የሆንክ ሞዛዛ እስቲ የሰራኸውን አቅምሰኝ ባለሙያ ትመስላለክ›› እጄን ዘረጋውለት ማማሰያውን እጄ ላይ ሲያደርገው አቃጠለኝ እና ጮሄ እጄ ላይ ያደረገውውን እንዳለ ደፋውት ቆሞ ይስቅብኛል በጣም ስለተናደድኩ ድብድብ አድርጌ መታውት ምግቡ ደርሶ ስንበላ አብዛኛውን እኔ ነበርኩ የበላውት ስራ አልሄድኩም እሱም አልሄደም ቀኑን ሙሉ አብረን ዋልን ደስ የሚል ቀን ሆነልኝ ፍቅር ግን ሁሌም እንዲህ ከሆነ በጣም ደስ የሚል ነገር ነው ማለት ነው፡፡ በነጋታው ስነቃ ከአልጋው ኮሞዲኖ ላይ የተፃፈ ወረቀት አገኘው አጠገቤ የለም ‹‹ መልካም ቀን እወድሻለው›› ይላል አንብቤ ስጨርስ ፈገግ አልኩኝ ደጋግሜ አነበብኩት ውስጤን ስለ እርሱ ሳስብ የማላውቀው የደስታ ስሜት ያጥለቀልቀዋል ከዘ ቀደም ፍቅር ለሚባለወ ነገር ቦታ ሰጥቼው ስለማላውቅ አዲስ የሆነ የሚያሥደስት ገነት ያለው ያህል እየተሰማኝ ነው፡፡ መስሪያቤት እንደደረስኩ ፊቴ በፈገግታ በርቶ ለሁሉም ላገኘዋቸው ሰራተኞች ሰላምታ እየሰጠው ገባው ዘበኛው ገና ስገባ ኮፍያቸውን አውልቀው የመስገድ ያህል አጎንብሰው ሰላም ሲሉኝ የመጣው ሰሞን የሚያዩኝ አስተያየት እና ስድባቸው ትዝ ብላኝ ፈገግ አልኩኝ፡፡ ቢሮ እንደገባው ምክትል አስተዳደሯ ቢሮዬን አንኳኩታ ገባች ቦርሳ ይዛለች ‹‹ ደና አደርሽ ቃል ኪዳን?›› አለችኝ መኮሳተሯ ትናንት ከመቅረቴ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ገብቶኛል ምን አይነት የፍቅር አለም ውስጥ ሰምጬ እንደዋልኩ ባወቀችልኝ ጭራሽ እዚህ እንዲህ ያለ ጣጣ እንዳለብኝም እረስቼው ነበር ‹‹ደና አደርሽ አበባ?›› ብዬ ወደ ስራዬ… ኦ ኦ ‹‹ትናንት በሰላም ነው? …. ለማንኛውም ትልቅ ሰርፕራይዝ አለኝ ›› ብላ ተሰረቁ የተባሉትን ፋይሎች ከቦርሳዋ አውጥታ ሰጠችኝ መቀበል ፈራው በፀሎት ይሄን አንዳወቀች በቀጥታ እኔ ላይ ነው የምታነጣጥረው ‹‹ይሄን መቀበል አልችልም እዚ ነገር ውስጥ መግባት አልፈልግም እባክሽ ቢሮዬን ለቀሽ ውጪልኝ ችግር አልፈልግም ›› ‹‹ እውነት….. ፈራሽ? ባትፈልጊም እዚህ ነገር ውስጥ አንዴ ገብተሸበታለ መታገል ብቻ ነው ወደ ኋላ ማፈግፈግ ብትፈልጊም አትችይም አዝናለው›› ብላ ፋይሎቹኝ ጠረጴዛዬ ላይ ጥላልኝ ወጣች የሚገርም ነው ሰው እንዴት ሳይፈቅድ እልም ያለ ጥይት አልባ ጦርነት ውስጥ ይገባል? አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ ሂወቴ አደ ጋ ውስጥ እንደሆነ እየተሰማኝ ነው ወደ እዚህ ሀገር ተቀይሬ የመጣሁበትን አጋጣሚ አምርሬ ጠላሁት ሌላ ምንም አማራጭ ስለሌለኝ ፋይሎቹ የያዙትን ሚስጥር ለማጣራት ተስማማው ስራውን ዛሬውኑ መጀመር እንዳለብኝ ስላስጠነቀቀችኝ እነዚህን ሁለት ፋይሎች ሳገላብጥ ሳመሳክር ኦዲት ሳደርግ ዋልኩኝ ግን ምንም አይነት ስህተት ላኝበት አልቻልኩም፡፡ .........ይቀጥላል.........✍ ቀጣዩን#ክፍል1⃣5⃣እንዲቀጥልLike👍ማድረግ እንዳይረሳ ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ 👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Amiryeee አድርሱን 📗📒📕📗📒📕 Join&share @Ethio_leboled 📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚 📖📖📖📖📖📖
Show all...