cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Aleazer Melese

የእግዚአብሔርን ቃል መማር

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
211
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ኢየሱስ ዘላለማዊ ነው። ሁላችንም መኖር የጀመርነው ከመጸነሳችን በኋላ ነው።ይህን ማንም አይክድም ። ከመጸነሳችን በፊት አልነበርንም ።በእግዚአብሔር እቅድ ነበርን። አንዱ የእግዚአብሔር የአምላክነቱ መገለጫ #ዘላለማዊነት ነው ። #ያለ___የነበረ___የሚኖር ኢየሱስ አብርሃም ሳይወለድ ያለ ነው ከአብርሃም ዘመንም በኋላ ያለ ነው ። ነገም ልወስደን ይመጣል። ኢየሱስ ዘላለማዊ በመሆኑ ኢየሱስ 100% አምላክ ነው። ዮሐንስ 8 ⁵⁷ አይሁድም፦ ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ⁵⁸ ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ #አብርሃም__ሳይወለድ__እኔ__አለሁ አላቸው። ⁵⁹ ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ። @transformedchristianlife
Show all...
ሻሎም ሻሎም ቅዱሳን በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ክርስቲያኖች አለን።ነገር ግን እንደ ብዛታችን ያክል የምስራቹን ወንጌል ላላመኑ ሰዎች የመመስከር ሁኔታ ያን ያክል ያደገ አይደለም ።ለዚህ ችግር እንደመነሻ የሚጠቀስ ችግር ቢኖር አንዱ #የተለወጠ___ክርስቲያን__ሆኖ__ያለመኖር__ችግር__ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ ስያስተምር አንድ ነገር ብሏል ማቴዎስ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁴ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። ¹⁵ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። ¹⁶ #መልካሙን_ሥራችሁን_አይተው_በሰማያት_ያለውን_አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። ስለዚህ እኛ አማኞች ለዓለም ብርሃን ስለሆንን ሁል ጊዜ አላማኞች አባታችን የሆነውን እግዚአብሔር ያከብሩ ዘንድ ብርሃናችን ሁሌ ይበራ ዘንድ ይገባዋል ። ብርሃናችን በሰው ፍት እንድበራ 1,መጸለይ 2,መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ 3,ከቅዱሳን ጋር ህብረት ማድረግ 4,ለመንፈሳዊ ህይወታችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቀጥሎ የሚጠቅመንን መንፈሳዊ መጽሐፍት ማንበብ አለብን። ጥያቄና ሀሳብ ካላችሁ @aleazer2cj ሼር ማድረጉን አትርሱ @transformedchristianlife
Show all...
ሻሎም ቅዱሳን ኢየሱስ ጌታ መሆኑን በራሱ አፍ ተናግሯል ወይ? ይህ የብዙ ሙስልሞች ጥያቄ ከዚህ በመቀጠል ኢየሱስ ጌታ ወይም አምላክ መሆኑን በራሱ አፍ የተናገረውን ከመጽሐፍ ቅዱስ እናያለን! #ዮሐ 5:17-19 (የዮሐንስ ወንጌል 5 ) ------------ 17፤ ኢየሱስ ግን። አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። 18፤ እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ። እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር። 19፤ ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና። #ማት 22:41-42 (የማቴዎስ ወንጌል 22 ) ------------ 41-42፤ ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ፥ ኢየሱስ። ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው። የዳዊት ልጅ ነው አሉት። 43-44፤ እርሱም። እንኪያስ ዳዊት። ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል? 45፤ ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል? አላቸው። 46፤ አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም፥ ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም። ቢይንስ ለ10 ሰው #ሼር #አድርጉ @transformedchristianlife
Show all...
ሻሎም ሻሎም የጌታ ልጆች #እባካችሁ አጭር ፅሑፍ ናትና ጨርሳችሁ አንብቧት!!! 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✝🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ‹‹የሚናከብረው የተሰቀለዉን ወይስ የተሰቀለበትን?!!?›› "ኃይላችን የመስቀሉ ቃል ወይስ ዕፀ-መስቀል??????" #የመስቀል በዓል # ትውፊት እንድህ ይላል :- "በተአምራዊነቱና በክርስቲያኖች ዘንድ ከፍተኛ ክብር የተሰጠው በመሆኑና ይህን የተመለከቱ አይሁድ ቅዱስ መስቀሉን በአንድ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦታ እንዲቀበር አደረጉ፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በየቀኑ ቆሻሻ ስለሚጥሉበት ቦታው ወደ ተራራነት ተቀየረ፡፡ ምንም እንኳን መስቀሉን ለማውጣት ባይችሉም በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች ቦታውን ያውቁት ነበር፡፡ በሰባ ዓመተ ምሕረት በጥጦስ ወረራ ኢየሩሳሌም ስለጠፋች በዚያ የነበሩ ክርስቲያኖች ተሰደዱ፡፡ የተቀበረበትን ቦታ የሚያውቅ ባለመገኘቱ መስቀሉ ከ300 ዓመታት በላይ ተዳፍኖ /ተቀብሮ/ ኖረ፡፡ በ326 ዓ.ም. የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ ቅዱስ መስቀሉን ለመፈለግ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ አደረገች፡፡ እዚያም ደርሳ ጉብታ የሆነውን ሁሉ ብታስቆፍር መስቀሉ ያለበትን ቦታ ማግኘት አልቻለችም፤ ሰውም ብትጠይቅ የሚያውቅ አልተገኘም፡፡ በመጨረሻም አንድ ይሁድ አረጋዊ የታሪክ አዋቂና ሽማግሌ አግኝታ ቅዱስ መስቀሉ የተቀበረበትንና የተጣለበትን አካባቢ ያውቅ ዘንድ ጠየቀችው፡፡ ሽማግሌውም “አንቺም በከንቱ አትድከሚ ሰውንም አታድክሚ እንጨት አሰብስበሽ እጣን አፍሽበት በእሳትም አያይዢው የእጣኑ ጢስ ወደላይ ወጥቶ ወደታች ሲመለስ አቅጣጫውን አይተሽ አስቆፍሪው በዚህ ምልክት ታገኚዋለሽ” አላት እርሷም ያላትን ሁሉ አደረገች። እንጨት ደምራ በዚያ ላይም ዕጣን ጨምራ በእሳት ለኮሰችው፤ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ መስቀሉ ያለበትን ቦታ በጣት ጠቅሶ እንደማሳየት ያህል አመለከተ፡፡ንግሥት ዕሌኒም ጢሱ ያረፈበት ቦታ ቅዱስ መስቀሉ የተቀበረበት እንደሆነ አመነች፡፡ ይህ ይሁድ አረጋዊ የታሪክ አዋቂና ሽማግሌ በኋላ በክርስቶስ አምኖ ተጠምቋል፤ ስሙም ኪርያኮስ ተብሏል፡፡በዚህም መሠረት #ከመስከረም_17 ቀን አስጀምራ እስከ መጋቢት 10 ቀን ሌሊትና ቀን ለሰባት ወራት ያህል የጉድፍን ኮረብታ ቆፍረው ቆሻሻውንም ካስወገዱ በኋላ ሦስት መስቀሎች ተገኙ ፡፡ የጌታም መስቀል ሙት በማስነሣቱ ተለይቶ ታውቋል፡፡ መስቀሉ የተገኘው መጋቢት 10 ቀን 326 ዓ. ም. ነበር፡፡ ቅድስት ዕሌኒ ይህን ተአምር በማየቷ እጅግ ደስ አላት፡፡ ሕዝቡም ሁሉ መስቀሉን እየዳሰሱ ኪርያላይሶን እያሉም በመዘመር ደስታና ሐሴት አደረጉ፡፡ በኋላም በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕብነ መሠረት ወይም የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦ ለመሰቀሉ መታሰቢያ ቤተክርስቲያን ተሠርቶ ተመርቆ የገባው (ቅዳሴ ቤቱ) የተከበረው መስከረም 17 ቀን 327 ዓ.ም. ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ሁለቱም ዕለታት ይከበራሉ፤ በደማቅ ሁኔታና በመጀመሪያ ደረጃ የሚከበረው ግን መስከረም 17 ነው፡፡ይህም የሆነበት ምክንያት መጋቢት 10 ቀን ሁልጊዜም በዐቢይ ጾም ወቅት የሚውል መሆኑና ለመስቀሉ የተሠራው ቤተ መቅደስ የከበረው መስከረም 17 በመሆኑ ነው፡፡ ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ በኢትዮጵያችን ሌላው የጌታችንን መስቀል ልዩ ሥፍራ እና ክብር የሚሰጠው ጉዳይ ደግሞ በ15 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በ ዓፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በ ቀራንዮ የተሰቀለበት ቀኝ እጁ ያረፈበት ግማደ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ መቀመጡ ነው። ንጉሡ አፄ ዳዊት ግማደ መስቀሉን አስመጥተው በኢትዮጵያ አድባራት ሁሉ በመዞር፣ ሊያሳርፉበት ያልሞከሩበት ቦታ አልነበረም፤ ነገር ግን መሬቱ እየተንቀጠቀጠ አስቸገረ። በመጨረሻ ግን “አንብር መስቀልዬ በዲበ መስቀል። (መስቀሌን በመስቀልያ ሥፍራ አስቀምጠው)” የሚል መለኮታዊ ምሪት ስለደረሳቸው፣ አሁን ግሼ አምባ በሚባለው ሥፍራ ላይ መስከረም 21 ቀን ፲፬፻፵፮ ዓ/ም አሳረፉት። ☦☦☦☦☦☦☦☦☦ በመጀመሪያ በዓሉን ለምታከብሩ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለዉ በመቀጠል በታርኩ ላይ ጥያቄ ላነሳ ነው። 1 መስቀሉ ታምራት በማድረጉ አይሁዶች ቢቀኑ እንዴት ቀለል አድርገዉ ቆሻሻ መጣያ ጣሉት ማቃጠል እየቻሉ ክርስቲያኖቹስ ታምር የሚያደርገዉን መስቀል ለምን መልሰዉ ሳይወስዱ? -> ወይስ የእስራኤል አገር ቆሻሻ ጥበቃ ይደረግለታል? -> መስቀሉ ታምራት ማድረግ እየቻለ እንደት ተጣለ? => ታምራት ባቆመበት ወቅት ነዉ የጣሉት ማለት ነዉ? => ተዉት እሽ አንደ ተጥሎአል እንበል ግን መስቀሉ እንጨት ነዉ አይደለ? መቼም የሁሉም መልስ # አዎ እንደሆነ አምናለሁ ታድያ በአንድ በኩል ቆሻሻ ተከምሮ ወደ አፈር ተቀይሮ ተራራ ሆኔ እየተባለ በሌላ በኩል ደግሞ ሶስቱም መስቀሎች ለ#326 ዓመታት አልበሰበሱም በትሎች፤በብሎች፤በምስጦች አልተበሉም!እንዴት? =>በታምር ነው! ብለን ከተፈላሰፍን እሽ የወንበዴዎችም መስቀል ታምረኛ ሆኖአል ማለት ነዉ:: ሌላዉ የገረመኝ ቆሻሻ እየተጣለ የተፈጠረዉ ተራራ! ኪሎማንጀሮ በለዉ! #7 ወር ሙሉ ቀንና ማታኮ ነዉ የተቆፈረዉ! ወደ ሰዓት ስንቀይረዉኮ 5040 ሰአት #አስቡ ቁፋሮዉ ሀገራዊ ነዉ!ሌላዉ የመስቀሉን አቅጣጫን እንድያሳየቸዉ የጨመሩት እጣን አስማታዊ ነዉ? ወይስ በእግዚ/ር መንፈስ ተመርተዉ ነዉ? አስተዉሉ ይንን ምሪት እየሰጠ ያለዉ ሰዉ ጌታን የማያዉቅ ሰዉ ነዉ፡፡ ገና መች ተገረማችዉ ንጉሥ ዐፀ ዳዊት የመስቀሉን ጉማድ ወደ ኢትዮጵያ ሲያስመጡ እንዴት አስመጡ? ለምን አስመጡ? በምን አስመጡ? ከየት ሀገር አስመጡ? ማነዉ መስቀሉን እየቆረጠ ሲያድል የነበረዉ? ከመጣስ በኋላ በየአድባሩ ለማሳረፍ ሲሞክሩ በአዉሮፕላን ነበር እንዴ? በእግር ከሆኔማ 1ኛ መሬት ላይ ነዉ ያለዉ 2ኛ ኢትዮጵያን በእግር መዞር የአንድ ቀን ስራ አይደለምና ከሰዉም ትከሻ ይወርዳል ስለዚህ እንዴት ነዉ ነገሩ? እናንተ ራሳችሁ አስቡበት እኔ ግን ላጠቃልል ነዉ መስቀሉ ከተቀበረበትም ተገኜ፤ ወደ ኢትዮጵያም መጣ፤ሄደንም አየን፤በእጅም ዳሰስን፤ ህይወት የሚሆኔን ክርስቶስ ብቻ ነዉ ፈልጉ የተባልነዉ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁን ነዉ፤ ስለዚህ በከንቱ ግዜያችንን አናባክን አድርጉ የተባልነዉ ባናደርገዉ እሳት የሚበላን የመጀመሪያና ትልቁ: አንድና አንድ ነገር በክርስቶስ ማመን ነዉ፡፡ #Note ክርስቶስ ህያዉ ነዉ መስቀሉ ግን ግዑዝ ነዉ፡፡ ጳውሎስ "የእግዚአብሔር ኃይል ነው" ያለው የመስቀሉን ቃል እንጂ የመስቀሉን እንጨት አይደለም:: 1ቆሮ 1:18 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ‹‹መስቀሉ ሳይሆን በመስቀሉ ላይ የተሰቀለዉ ክርስቶስ ብቻዉን ያድናል፡፡›› 👆👆👆👆👆👆👆👆 እግዚያብሔር ኢትዮጵያውያን እና ኢትየጵያን ለዘላለም ይባርክ ለወዳጆቻቹ Shear ማድረግ #atrsu….ተባረኩ !! @aleazer2cj @transformedchristianlife
Show all...
ሰላም ይብዛላችሁ ቅዱሳን! ሮሜ 8፥34 የሚለው "ስለ እኛ የሚማልደው" ወይስ "ስለ እኛ የሚፈርደው?" የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “ስለ እኛ የሚማልደው” የሚለውን ሐረግ “ስለ እኛ የሚፈርደው” ብላ ተርጕማ በሥራ ላይ ማዋሏ ይታወቃል። ይህ የትርጉም ለውጥ በመጀመሪያ የተደረገው በ1975 ዓ.ም. በግእዝና በዐማርኛ በታተመውና በአብዛኛው በቅዳሴ ላይ፦ መልእክታተ ሐዋርያት፣ ግብረ ሐዋርያትና ቅዱስ ወንጌል በሚነበብበት ሐዲስ ኪዳን ላይ ነው። ይህም ትርጕም በአብዛኛው በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የተገደበ ነው። ከዚያም በ2000 ዓ.ም. ለራሷ ባሳተመችውና የግእዙን ንባብ መሠረት ያደረገ ነው ባለችው መጽሐፍ ቅዱሷ ላይ፣ ይኸው የግሪኩን ንባብ የጣሰ ትርጕም - “ስለ እኛ የሚፈርደው” የሚለው ይፋ ከኾነ ዐሥራ ሦስት ዓመታት ዐለፉ። አኹንም ድረስ ግን በዚህ ሐረግ ላይ የተደረገው የትርጕም ለውጥ ማከራከሩን ቀጥሏል። ክፍሉ “ስለ እኛ የሚፈርደው ነው የሚለው” ባዮቹ፣ “ይትዋቀሥ በእንቲኣነ” የሚለው መሟገትን፣ መከራከርን ብቻ ሳይኾን መፍረድንም ያሳያል ይላሉ። “ተዋቀሠ” የሚለው የተገብሮ ግስ ግን “በቁሙ (ተዋቀሠ)፣ ተሟገተ፣ ተከራከረ” የሚል ትርጕም ነው ያለው። ከግሱ በተለያየ ቅርጽ በሚወጡ ሌሎች ቃላት በኩል ግን ትርጕሙ ልዩ ልዩ እየኾነና እየሰፋ ይኼዳል። ይህ ደግሞ አንዳንድ ቃላት የፍቺ መጠናቸው ሰፊ ኾኖ ሲገኝ የሚከሠት ነው። የተዋቀሠን “መስም (ስም የሚኾን ቅጽል)” የኾነውን “መስተዋቅሥ” የሚለውን ቃል ትርጕም ከተመለከትን፣ “የሚያዋቅሥ፣ የሚያከራከር፣ ዳኛ። የሚዋቀሥ፣ ተዋቃሽ፣ ተከራካሪ፣ ባላጋራ” ይኾናል (ኪወክ ገጽ 401)። አንዳንዶች “ተዋቀሠ” የሚለውን ተደራራጊ ግስ፣ በአስደራጊው ግስ “አስተዋቀሠ፦ አዋቀሠ፥ አወቃቀሠ፥ አሟገተ፥ አከራከረ” በኩል በመፍታትና በመስም (ስም በሚኾን ቅጽል) “መስተዋቅሥ፦ የሚያዋቅሥ፥ የሚያከራክር፥ ዳኛ። የሚዋቀሥ ተዋቃሽ ተከራካሪ፤ ባላጋራ” የሚለውን በመያዝ ይፈርዳልን ለማምጣት ይሞክራሉ (መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፣ ነገረ ክርስቶስ ክፍል አንድ፣ ገጽ 479)። ይህ በእውነቱ ማምታታት ነው፤ ምክንያቱም ሮሜ 8፥34 የግእዙ ንባብ የተጠቀመው ቃል “ይትዋቀሥ - ይዋቀሣል፤ ይከራከራል፤ ይሟገታል” የሚለውን ቃል ነው እንጂ፣ “መስተዋቅሥ - የሚያዋቅሥ፣ የሚያከራክር ዳኛ።” የሚለውን ቃል አይደለም። ለዚህም ይኾናል ግለሰቡ ይህን ትርጉም በጽሑፉ ዋና አካል ውስጥ ሳይኾን በግርጌ ማስታወሻ በማምታታት መንገድ ያስቀመጠው። ይህም ቢኾን አያስኬድም፤ ምክንያቱም ምንም የግሱ ሥር አንድ ቢኾን የትኛውም ግስ በተደራራጊ ግስ የሚኖረው ትርጕም በአስደራጊ ግስ ከሚኖረው ትርጕም ይለያል። • ተዋቀሠ ሲል ትርጕሙ፦ በቁሙ (ተዋቀሠ)፥ ተሟገተ ተከራከረ ሲኾን፥ አንዱ ለሌላው/ስለ ሌላው የሚያደርገውን ክርክርና ሙግት ያመለክታል። • አስተዋቀሠ ሲል ደግሞ ተከራካሪው ወይም ተሟጋቹ እርሱ አይኾንም፤ ነገር ግን ሌሎች ኹለት አካላትን የሚያዋቅሥ፥ የሚያወቃቅሥ፥ የሚያሟግት፥ የሚያከራክር ይኾናል እንጂ (ኪወክ ገጽ 401)። ሮሜ 8፥34 ላይ ግእዙ የተጠቀመው የተደራራጊውን ግስ ካልኣይ አንቀጽ “ይትዋቀሥ” የሚለውን ነው። ይህም ይሟገታልን፣ ይከራከራልን እንጂ ይፈርዳልን አያስገኝም። ስለዚህ ተደራራጊው ግስ በምንም መንገድ ይፈርዳል የሚል ትርጕም አይሰጥም። አንድምታ ትርጓሜውም “ስለ እኛ ይከራከራል” በሚለው ላይ ተመሥርቶ ማብራሪያውን የሰጠው ግሱ ወደ ይፈርዳል ስለማይሰድ ነው (የሮሜ 8፥34 አንድምታ ትርጓሜውን ተመልከት)። "ስለ እኛ የሚፈርደው" የሚለውን የተሳሳተ ትርጉም የሚሰጡ ሰዎች አንድምታው ሐሳባቸውን ስለሚያፈርስባቸው እሱ የሰጠውን ትርጉም ማየትም፣ መስማትም፣ በጽሑፎቻቸው ውስጥ መጥቀስም አይፈልጉም። ይህም የሚያሳየው “ስለ እኛ የሚፈርደው” የሚለው ትርጕም ከጊዜ በኋላ የመጣ፣ “ኢየሱስ አማላጅ” አይደለም በሚሉ ክፍሎች ግፊት የተሰጠ እንጂ በሊቃውንቱ ዘንድ ቅቡልነት የሌለው መኾኑን ነው። ደግሞም ኢኦተቤክ በ2000 ዓ.ም. ለራሷ ያሳተመችው መጽሐፍ ቅዱስ ትርጕሙን ለውጦ “ስለ እኛ የሚፈርደው” ብሎ ከተረጐመ በኋላ፣ በግርጌ ማስታወሻው ላይ ግን “ግሪኩ የሚማልደው ይላል” ብሏል። የሐዲስ ኪዳን እናት ቋንቋ ወይም በመጀመሪያ የተጻፈበት ቋንቋ ግሪክ ነው። ግእዙ የቅጂ ቅጂ ነው እንጂ ዋናው አይደለም። ግእዙም ቢኾን አስገድደውት እንጂ “ስለ እኛ የሚፈርደው” አይልም። ስለዚህ ይፈርዳል ተብሎ በተሳሳተ መንገድ የተተረጐመው ቃል፣ ሲኾን ሲኾን በግሪኩ፣ ያም ባይኾን በግእዙ መሠረት መታረም አለበት እንጂ፣ ግሪኩም ግእዙም ያላሉትን ማለት የለበትም። ደግሞም የኹለት ሺሑ ዓመተ ምሕረት መጽሐፍ ቅዱሷ ግእዙን መሠረት ያደረገ ትርጕም ነው ከተባለ ይህ ክፍል ለግእዙም ታማኝ መኾኑን ማሳየት ነበረበት፤ እዚህ ላይ ግን ታማኝነቱን አጉድሏል። “ስለ እኛ የሚፈርደው” ተብሎ የተተረጐመው ስሕተት የሆነው አለ ንባቡ በመተርጐሙ ብቻ አይደለም፤ የዐማርኛንም ኾነ የግእዙን ሕገ ሰዋስው ስለሚጥስም ነው እንጂ። በዐማርኛም ኾነ በግእዝ ሰዋስው “የሚፈርደው” ከሚለው ግስ ጋር ዐብሮ የሚኼደው ተውላጠ ስም (እኛ) የሚፈልገው መስተዋድድ “ለ” ወይም “በ” እንጂ “ስለ” አይደለም፤ ምክንያቱም መፍረድ በኹለት ወገን ማለትም ለሚፈረድለትም ለሚፈረድበትም ይነገራል፤ ለሚፈረድለት ወገን ሲነገር፣ “ስሙ” ወይሞ “ቅጽሉ” ላይ “ለ”፣ በሚፈረድበት ወገን ላይ ደግሞ “በ” መስተዋድድ ይወድቃል። በምሳሌ ለማስረዳት የሚከተሉትን መጽሐፍ ቅዱሳውያን ጥቅሶች ላቅርብ፤ • “ለድኻ አደጉና ለመበለቲቱ ይፈርዳል፥” (ዘዳ. 10፥18) • “እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል” (ዘዳ. 32፥36)። • “እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳልና፥ ባሪያዎቹንም ይረዳልና።” (መዝ. 135፥14)። • “እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።” (መዝ. 82፥1) • “በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል፤ ...” (ኢሳ. 2፥4) • “እንዲህ አይኹን፤ እንዲህ ቢኾን እግዚአብሔር በዓለም እንዴት ይፈርዳል?” (ሮሜ 3፥6)። ከዚህ አንጻር “ስለ እኛ የሚፈርደው” የተባለው ሕገ ሰዋስው ተጥሶ የተሰጠ ትርጕም በመኾኑ፣ “የሚፈርደው” የሚለው ትርጕም የገባው አለአግባብ መኾኑን ያመለክታል። በቃሉ ላይ ዐብሮት የማይኼድ ወይም ሕገ ሰዋስው የማይፈቅደው መስተዋድድ ስለ ወደቀበትም፣ በዐማርኛም ኾነ በግእዙ ሰዋስው ስሜት አይሰጥም፤ ለአፍም ለጆሮም ጣዕም የለውም። ይህ ኹሉ ኾኖ “ስለ እኛ የሚፈርደው” የሚል ንባብ በግድ ካልኾነ በቀር “ለእኛ የሚፈርደው” የሚል ትርጕም ሊሰጥ አይችልም። ኢየሱስን ከመካከለኛነቱ ለማንሣት ምን ያኽል የትርጕም በደል እንደ ተፈጸመ አያችሁን? ይቀጥላል
Show all...
#እንዴት ናችሁ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች ጸጋ እና ሰላም ይሁንላችሁ❗     ዛሬ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ስለ የምናገረው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ እንማራለን ❗ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ተጽፎ ያለቀው ኢየሱስ ወደ ምድር ሥጋ ለብሶ ከመምጣቱ ከ400 ዓመት በፊት ነው። ብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ከሚያስተምረን ክፍል አሁን ጥቅቱን እናያለን።      ❶, #ት/#ኢሳ 9:6 "፤ ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። " (ትንቢተ ኢሳይያስ 9: 6) ይህ ስለ መሲሁ ማለትም ስለ ኢየሱስ የተተነበየ ትንቢት ነው። ስለ ኢየሱስ በትንቢቱ ከተነገሩ ነገሮች ውስጥ አንዱ #ኢየሱስ #ኃያል #አምላክ #እንደሆነ #ነው❗ ይህም የሚያሳየን ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ነው❗ምክንያቱም እግዚአብሔር #ኃያል #አምላክ #ተብሏልና ❗ (ትንቢተ ኢሳይያስ 10 ) ------------ 20፤ በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ የእስራኤል ቅሬታ ከያዕቆብም ቤት የዳኑት ከእንግዲህ ወዲህ በመቱአቸው ላይ አይደገፉም፤ ነገር ግን #በእስራኤል #ቅዱስ #በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይደገፋሉ። 21፤ የያዕቆብም ቅሬታ #ወደ #ኃያል #አምላክ #ይምለሳሉ።           ❷, #ት/ኢሳ 7:14 "፤ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም #አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። " (ትንቢተ ኢሳይያስ 7: 14)      #አማኑኤል #ማለት #ምን #ማለት #ነው❓       #አማኑኤል ማለት #እግዚአብሔር #ከእኛ #ጋር #ነው #ማለት #ነው❗ ይህም ማርያም ኢየሱስን ያለ ወንድ እንደምትወልድ መልአኩ ገብርኤል ከነገራት በኋላ ጸንሳ ስትገኝ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ ስናገር እንዲህ አለው❗ (የማቴዎስ ወንጌል 1 ) ----------- 18፤ የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። 19፤ እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ። 20፤ እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ። የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። 21፤ ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። 22፤ በነቢይ ከጌታ ዘንድ። 23፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው። ይህም ስለ ኢየሱስ በነቢያት ከተተነበዩ ትንቢቶች አንዱ ነው።            ❸, #መዝ 110:1 "፤ እግዚአብሔር ጌታዬን። ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው። " (መዝሙረ ዳዊት 110: 1) ይህን ጥቅስ ኢየሱስ ስያስተምር እንዲህ አላቸው። (የማቴዎስ ወንጌል 22 ) ------------ 41-42፤ ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ፥ ኢየሱስ። ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው። የዳዊት ልጅ ነው አሉት። 43-44፤ እርሱም። እንኪያስ ዳዊት። #ጌታ #ጌታዬን። #ጠላቶችህን #የእግርህ #መረገጫ #እስካደርግልህ #ድረስ #በቀኜ #ተቀመጥ #አለው #ሲል #እንዴት #በመንፈስ #ጌታ #ብሎ #ይጠራዋል? 45፤ #ዳዊትስ #ጌታ #ብሎ #ከጠራው፥ #እንዴት #ልጁ #ይሆናል? #አላቸው። 46፤ አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም፥ ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም። ነቢዩ እና ዘማሪው ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ስለ ጌታ ኢየሱስ ጌትነት/አምላክነት የተናገረው ትንቢት በኢየሱስ ተፈጽሟል ❗      #ጌታ(አብ) ጌታዬን(ኢየሱስን)..... አለው❗ ይህን ክፍል በተጨማሪ ኢየሱስ እና አብ በመለኮት አንድ ነገር ግን በአካል የተለያዩ መሆናቸውንም ጭምር ያስተምረናል ❗ #ኢየሱስ #እና #አብ #በአካል #አንድ #አይደሉም #ማለት #ኢየሱስ #አብ #አይደለም #ማለት #ነው❗        ❹, #መዝ 45:6-7 (መዝሙረ ዳዊት 45 ) ------------ 6፤ አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘላለም ነው፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። 7፤ ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፤ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ። እግዚአብሔር አብ በዚህ ክፍል ኢየሱስን #አምላክ #ሆይ #ብሎ #ጠርቶታል❗❗❗ የዕብራውያን ጻፊ ይህን ክፍል ስያስተምር እንድህ አለ። (ወደ ዕብራውያን 1 ) ------------ 7፤ ስለ መላእክትም። መላእክቱን መናፍስት አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ 8፤ ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። 9፤ ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ ይላል። በዚህ የዕብራውያን መጽሐፍ እግዚአብሔር አብ መልአክትን መናፍስት እንዳላቸውና #ኢየሱስን #ልጁን ግን #አምላክ ሆይ ብሎ እንደጠራ በግልጽ ያስተምረናል ❗ኢየሱስ ከመልአክት ይበልጣሉ ❗      ይቀጥላል.... ይህን እውነት በኢየሱስ ክርስቶስ ላላመኑ እና አምነውም ይህን ያውቁ ዘንድ ይገባቸዋል ለሚትሉ ወዳጆቻችሁ      Share አድርጉላቸው ❗ t.me/aleazermelese
Show all...