cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Letenah Ejigu Wale

Show more
Ethiopia2 635Amharic2 389The category is not specified
Advertising posts
4 074Subscribers
No data24 hours
-157 days
-6930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አማራ ባንክ ሃረር ቅርንጫፍ
Show all...
የድሬ ትዝታየ ሲደመር አዲሷ ሃረር ፤ ድሬዳዋ ከ13 አመት በኋላ መጣሁ ፤ ይገርማል ።በፈረንጆች 2010 ወይም በእኛ 2002 ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ድሬ መጣሁ ። በወቅቱ ወደ ድሬ የመጣሁበት ጉዳይ ወዲህ ነበር ። በወቅቱ በህንድ አገር ፓንጃብ ዩኒቨርሲቲ የፒኤቺዲ ተማሪ ነበርኩና በአገር አቀፍ የማይክሮ ፋይናንስ ኮንፈረንስ ላይ የምርምር ወረቀቴን ላቀርብ ወደ ድሬ መጣሁ ። ኮንፈረንሱን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ማህበር ነበር (Association of Ethiopian Microfinance Institutions, AEMFI). በወቅቱ ደግሞ የAEMFI ዳይሬክተር የነበረው ነፍሱን ይማረውና ዶር ወልዳይ አምሃ ነበር ። ዶር ወልዳይ አምሃ ለኢትዮጵያ ማይክሮ ፋይናንስ ዘርፉ እድገት ብዙ አስተዋፅኦ ያደረገ በጣም ትጉህ እና ቅን ሰው ነበር ። ዶር ወልዳይ አምሃ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር (Ethiopian Economics Association, EEA) ፕሬዝዳንትም ነበር ። ከሆኑ አመታት በፊት ነው እጅግ አስደንጋጭ በሆነ የመኪና አደጋ ህይወቱ ያለፈው ። RIP Dr Wolday Amha 😭 እናማ ድሬ የምርምር ወረቀቴን አቅርቤ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የቦርድ አባላትን እና ዋና ስራ አስፈፃሚዎችን አግኝቸ ስለ ዘርፉ ብዙ ሃሳቦች የተቀያየርኩበት ወቅት ነበር ። በነገራችን ላይ የኔ የፒኤቺዲ ትምህርት ፋይናንስ ነው ። እናም ለፒኤቺዲየ ምርምር ርዕስ በወቅቱ ስመርጥ በአእምሮየ የመጣው ጥያቄ እንዴት ነው የኔ ትምህርት ለድህነት ቅነሳ ትግሉ አስተዋፅኦ የሚያደርገው ብየ ማሰብ ጀመርኩ ። ይህንን ሃሳብ ደጋግሜ ሳውጠነጥነው የመጣልኝ ነገር በቃ ስለ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ማጥናት አለብኝ ብየ ነው ። ከዚያ በዚያው ዘርፍ ጥናቴን ሰራሁና ጨረስኩ ። እንደኛ አይነት ድሃ ለሆነ አገር የማይክሮ ፋይናንስ ተቋሞች ለኢኮኖሚው እጅግ ሲበዛ ቁልፍ ተቋማት ናቸው ፤ መደገፍና በጣም ማደግ አለባቸው ። እያንዳንዱ ትምህርት ለለውጥ እና ለፀረ ድህነት ትግሉ ካልዋለ ወይም አስተዋፅኦ ካላደረገ ፋይዳ ቢስ ነው ። ያ የፒኤቺዲ ጥናቴም ትምህርቴን ለህዝብ ጥቅም እንዲውልና በተለይም ለድሃው ማህበረሰብ እንድቆረቆር የገፋኝ ይመስለኛል ። አሁን ላይ ሆኘ ሳስበው ደግሞ የፒኤቺዲ ጥናቴን በድሃ ተኮር ፋይናንስ (ማይክሮ ፋይናንስ) ላይ መስራቴ የህዝብ የፋይናንስ ተቋም የሆነውን አማራ ባንክ እንድንወልድ አስተዋፅኦ አድርጓል ብየ እንዳስብ ያስገድደኛል ። ተመልከቱ የሆነ ጊዜ በሆነ ነገር ከተለከፋችሁ በቃ ተለከፋችሁ ነው ። ብዙ የፋይናንስ የምርምር ዘርፎች ቢኖሩም እኔ ሁሌም የሚመስጠኝ የጥቃቅን እና አነስተኛ ፋይናንስ (Micro and Small Enterprises Finance) ነው ። እኔ የማምነው ልማት የሚመጣው ከታች ያለው ህዝብ ሲነቃነቅ ነው ብየ ነው ። I honestly beleive in grass root movement and bottom up approach to development. አገራችን ድሃ ናት ስለዚህ ሁሉም ሙያ ለፀረ ድህነት ትግሉ አስተዋፅኦ ማበርከት አለበት እላለሁ። ተማርን የምንል ሰዎች ትምህርት ዝም ብሎ ጉራ የምንቸረችርበት ሳይሆን አንተም ተቀይረህ ማህበረሰብ የምትቀይርበት መሆን አለበት ። ይህ የሁልጊዜም ፍልስፍናየ ነው ። ከዚህ ውጭ ከሆነ ለኔ ትምህርት ጉራ ብቻ ነው እለዋለሁ ። የኔ ነገር ወደ ሌላ ነገር ገባሁ ፤ በሉ ወደ ድሬ ትዝታ ልመልሳችሁ ። እናማ በወቅቱ ድሬ ሳምንት ያክል ቆይተን ብዙ ትዝታ ነበረን ። በዛን ጊዜ የድሬዳዋ ከንቲባ የነበሩት በአሁኑ ሰአት የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ሃላፊ የሆኑት ክቡር አቶ አደም ፋራህ ነበሩ ። ገና ወደ ድሬ ስንመጣ እንዴት በክብርና በማርሽ ባንድ እንደተቀበሉን አስታውሳለሁ ። ድሬዎች እንግዳ መቀበል ላይ 1ኛ ናቸው ። በየቀኑ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የኮንፈረንሱ አባላትን በድሬ የተለያዩ ምርጥ ሆቴሎች ከባድ የእራት ግብዣ ከሙሉ የሙዚቃና የመዝናኛ አገልግሎት ጋር ሲያቀርቡልን ነበር ። የምስራቁ ኢትዮጵያን ሙዚቃና ባህል ያየሁት ያኔ ነበር ። ከሰሜኑ ጋር ያለው ልዩነቱ ይገርመኝ ነበር ። ለመጀመሪያ ጊዜ ግመል ያየሁትም ያኔ ነበር ። ኢትዮጵያ ግን ምን ያክል ሰፊና በጣም ብዙ ልዩነቶች (diversity) እንዳላት የተረዳሁበትም ወቅት ነበር ። የድሬ ገብያዎችን ጎብኝተን ብዙ ነገርም (ለምሳሌ የሴቶች ድሪያ) ሸምተን ነበር ። ብቻ ድሬዎች ፍቅራቸው ልዩ ነው ። ዌል እንግዲህ ይህን ሁሉ የድሬ ትዝታ ከ13 አመት በኋላ የመጣብኝ ዛሬ ከአአ ተነስተን ድሬዳዋ ኤርፖርት አርፈን በከተማው ወደ ሃረር ስናልፍ ነው ። አሁን ሃረር ገባን ። ሃረር ለመጀመሪያ ጊዜ መምጣቴ ነው ፤ ዞርዞር ብየ ሃረርን ካየኋት በኋላ ስለ ሃረር ደግሞ አስቃኛችኋለሁ ። ከድሬ ሃረር እንዲህ ቅርብ ነው ለካ ። በመሃል ያሉ ከተሞችን አየኋቸው ። ከድሬ እንደወጣህ ደንገጎን ታገኛለህ ። ደንገጎ ወደ አዲስ አበባ እና ወደ ሃረር የሚሄደው መንገድ የሚገነጥልባት ናት ። ቀጥሎ ሌሎች ትናንሽ ከተሞች አሉ ። ቀጥሎ ሃረምያ ዩኒቨርሲቲ ያለበት የሃረምያ ከተማ እና የሃረምያ ሃይቅን አየሁት ። ደርቋል የተባለው የሃረምያ ሃይቅ መመለሱ ደስ ይላል ። በመጨረሻም ጥያቄ ፤ ውድ አንባቢዎቸ ፤ ከድሬ እስከ ሃረር ያለው አካባቢ ኢኮኖሚው በአብዛኛው የተመሰረተው በምንድን ላይ ነው ? መቸም ይህ ጥያቄ Exit Exam ቢመጣ ማንም ይደፍነዋል ብየ አስባለሁ ። ይህን ጥያቄ ስጠይቅ ግን ለምንድን ነው ሰይፉ ፋንታሁን ትዝ ያለኝ 😁 የጥያቄው መልስ በአረንጓዴ ወርቅ ወይም በርጫ የሚል ይሆናል 😁 አወዳይ የምትባልዋ የቀለጠች ከተማ ደግሞ የበርጫው ኢንዱስትሪ ዋና የአክሲዮን ገብያ ናት ኡዝቢላሂ 😁 ከበርጫ ሚኒስቴር መረጃ ካገኘሁ ስለ በርጫው ኢኮኖሚማ የምዳስሰው ነኝ (ፍላጎት ፤ አቅርቦት ፤ ምርት ፤ ፍጆታ ፤ ሽያጭ ፤ ዋጋ ፤ ትርፍ ፤ ሃብት ፤ እዳ ፤ ካፒታል፤ የፈጠረው የስራ እድል ፤የአካባቢ ተፅእኖ ግምገማ ወዘተ) ፅሁፌን በሙሃሙድ ሙዚቃ ልቋጨው ፤ የድሬ ልጅ ናት የከዚራ ፤ ስለውበቷ ምኑን ላውራ ። የሀረር ልጅ ናት የአዋሽ ማዶ፤ ልቤ ተሠዷል እሧን ወዶ ። ሻሎም ✌️✌️✌️ ለጤናህ ነኝ ከሃኪም ጋራ ስር ፤ ሃረር
Show all...
እርሳቸውም ከእነዚህ አንዱ እንዳልሆኑ እንዲህ መልሰዋል። “እኔ ሚሊዮነር ሆኛለሁ፤ 20 ጊዜ የታተመ መጽሐፍ አለኝ። ሌላ 12 ጊዜ የታተመ መጽሐፍ አለኝ። 6.6 ሚሊዮን ሕብረት ባንክ አክሲዮን አለኝ፤ የማከራየው ቤት አለኝ፤ ገንዘብ መሥራት የጀመረ ዩቲዩብ አለኝ። ምን ትፈልጋለህ?” ስለዚህ ሞቲቬሽን ይሠራል ነው የሚሉኝ? “አዎ! የሰው ልጅ ዋናው ሃብቱ አስተሳሰቡ ነው። የሰው ልጅ ሃብቱ የመሬት ስፋት ቢሆን ሲንጋፖር አትኖርም ነበር። ምቹ መሬት ቢሆን ጃፓን አትኖርም ነበር። ዋናው ነገር ከአንገት በላይ ያለን አካል በአግባቡ መጠቀም ነው። “እኔ ያን ሥልጠና ባልሳተፍ አሁን ጡረታ ወጥቼ ዳማ ስጫወት ነበር የምታገኘኝ። መሠልጠን በመቻሌ ግን ገና የ30 ዓመት ሕልም አለኝ።” የናትናኤል አማራጭ መንገድ ዶ/ር ወሮታው ከሚሉት በተቃራኒው የሚቆመው ናትናኤል እንደ ግለሰብም እንደ አገርም ለገባንበት ቀውስ መፍትሄው የሞቅታ ሞቲቬሽን አይደለም ይላል። ታዲያ መፍትሄው ምንድነው ሲባል “ኮንሽየስ መሆን” ብሎ በድፍኑ ይመልሳል። ከቀልብ መሆን፣ መንቃት፣ ያለንበትን ማወቅ ማለቱ ነው። ሞቲቬሽን ያልነቃ ሕዝብ ኪስ ውስጥ ገብቶ ገንዘብ ለማውጣት ይሰራል። ለፖለቲከኞችም ሕዝብን ለመንዳት ይጠቅማል። ምንጊዜም ያልነቃ ሕዝብ አእምሮ ውስጥ የሞቲቬሽን ጠብታ በመጨመር ማስከር ይቻላል። ለውጥን በሞቲቬሽን ማምጣት ግን ፍጹም አይቻልም ይላል። “ጃፓን ድምጽ የለም፤ ሥራ ግን ይሠራል። እኛ ጋር ግን አገሩ ሁሉ በሞቲቬሽን ቀረርቶ ተሞልቷል። ለምን ይመስልሃል?” ሞቲቬሽን መር ፍልስፍና እንደ አገር አይበጀንም የሚለው ናትናኤል፣ ይህ ያልተጨበጠ ባለጸጋ የመሆን ዲስኩር ከአስተዳደር አልፎ ወደ እምነት ቤቶች መግባቱን ይተቻል። “ብዙ ቸርቾች ውስጥ አሁን አሁን ወንጌል ሳይሆን ሞቲቬሽን ነው የሚሰበከው። ኢየሱስ ምን ሊያመጣልኝ ይችላል እንጂ መቼ ይመጣል የሚል ሰው ከምዕመኑ ዘንድ የለም።” “አገራችን ካለችበት ቀውስ ለመውጣት ሞቲቬሽን አይሠራም። እንችላለን፣ ታላቅ ነበርን፣ ታላቅ ነን በሚል ፉከራ አገር አይለወጥም። ከባድ ቀውስ ውስጥ ነን። ሞቲቬሽን ለዚህ መፍትሄ አያመጣም።” ናትናኤል በተደጋጋሚ አሁን አማራጩ ‘ኮንሺየስነስ’ን መሞከር ነው ሲል አበክሮ ይሞገታል። ምንድነው ኮንሺየስነስ ሲባል ግን የተፍታታ መልስ መስጠትን ገሸሽ ያደርጋል። “መንቃት። በአእምሮ ሰላም ውስጥ መሆን። ከቀልብ መሆን። አሁን ላይ መሆን።” ይህ ማለት ምን ማለት ነው? “አጠገብህ የሚሻክር ነገር አለ?” “አዎ!” “ካለ ስሜቱን በቃላት ግለጽልኝ?” ገለጽኩለት። “አሳምረህ በቃላት ስሜቱን ገልጸኸዋል፤ እኔን ግን አልሻከረኝም።” ለማለት የፈለከው አልገባኝም። “ኮንሺየስነስ እንደዚያ ነው። ትኖረዋለህ እንጂ ቃላት በመደርደር አትገልጸውም። ወሬ ሳይሆን ተግባር ነው።” *** *ይህ ጽሑፍ ባለፈው ዓመት “ሚሊየነር የመሆን ጥበብን የሚሰብኩን ሰዎች ለምን ‘ድሆች’ ሆኑ?” በሚል ርዕስ በቢቢሲ አማርኛ ላይ ወጥቶ የነበረ ሲሆን፣ ከጥቂት ማሻሻያ ጋር በድጋሚ የቀረበ ነው። Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ❤
Show all...
ዛሬ ደግሞ ለቲክቶክ ዘመን በሚስማማ መልኩ በሚጻፉ፣ ቶሎ ተጥደው፣ ቶሎ በሚገነፍሉ፣ ቶሎ ተነበው ቶሎ የሚጣሉ (Use and throw) መጻሕፍት ብቅ ብለዋል። ገበያ የሚወዳቸው ሞቲቬሽኖች የሚገርመው በዓለም የገነኑት የማነቃቂያ መጻሕፍት አብዛኞቹ በሚሊዮኖች ቅጂ የታተሙ ናቸው። ከየትኛውም የመጻሕፍት ዘውግ (Genre) ባልተናነሰ ሁኔታም ወደ አማርኛ ተመልሰዋል። በኢትዮጵያ ገበያ ሌሎች መጻሕፍት 3 ሺህ ቅጂን ለማለፍ ፍዳቸውን በሚያዩበት ጊዜ፣ እነሱ እንደዋዛ በ20 እና 30 ሺህ ቅጂ ይታተሙም ነበር። አሁን ግን መጻሕፍቱ በመድረክ ዲስኩሮች እየተተኩ ይመስላል። ፋይዳቸው ዘላቂ ነው? ብለን ብንጠይቅ አልዘገየንም ለማለት ነው። እውን ናትናኤል እንደሚለው ሞቲቬሽኖች ‘የብድር ደስታ’ መፈልፈያ ፋብሪካዎች ናቸው? ወይስ ዶ/ር ወሮታው እንደሚሉት ሰዎችን ወደላቀ ልዕልና የሚያደርሱ አውራ ጎዳናዎች? በሙግቱ ትንሽ እንግፋበት እና እናገባድ። “በስድስት ዓመት ውስጥ ራሴን አፍርሼ ሠራሁት” ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ያመቻቸላቸው ሥልጠና አዲስ የብርሃን ዘመን የከፈተላቸው ዶ/ር ወሮታው፣ ከዚያ ወዲያ የሞቲቬሽን መጻሕፍትን እያሳደዱ ማንበብ ጀመሩ። እሳቸው ወጣት ሳሉ የቭላድሚር ሌኒን እንጂ የናፖሊዮን ሒል መጻሕፍት አልነበሩም። ስለ ግል ቢዝነስ ማሰብም ነውር ነበር። የወላጅ ዘመድ የመጨረሻ ሕልምም ልጄ ተቀጥሮ ደመወዝ ይበላል ወይስ አይበላም የሚል ነበር። ከ1992 ዓ.ም. ወዲህ ግን እነ ናፖሊዮን ሒል ብቅ አሉ። እሳቸውም "Think and Grow Rich"ን ነበር መጀመሪያ ያነበቡት። ከፍተኛ መነቃቃት ፈጠረላቸው። ከዚያ ወዲያ የሞቲቬሽን መጽሐፍት አደን ውስጥ ገቡ። ዘመኑን መለስ ብለው ሲያስታውሱ “ከዚያች ሥልጠና ወዲህ በነበሩ ስድስት ዓመታት ነበር ራሴን አፍርሼ እንደ አዲስ የሠራሁት” ይላሉ። ሞቲቬሽን የሚሠራው እንዴት ነው? አእምሯችን ከልጅነታችን ጀምሮ የሐሳብ ድር ሲያደራ ነው የኖረው። በቀን በአማካይ ከ60 ሺህ በላይ የሐሳብ ዘለላዎችን ይመዛል፤ ይፈትላል። እያነሳ ይጥላል። ከዚህ ሁሉ ሺህ የሐሳብ ደውር አብዛኛው ፀፀት እና ተስፋ ነው። ትናንት እና ነገ። በሌላ አነጋገር አእምሯችን ወይ ወደ ትናንት ይንሸራተትብናል፤ አሊያ ደግሞ ወደ ነገ ይስፈነጠራል። ዛሬ ላይ፣ አሁን ላይ ሁን ስንለው እሺ አይልም። ለዚህም ነው “ከቀልቡ የሆነ ሰው ማግኘት አስቸጋሪ የሚሆነው” ይላል ናትናኤል። ከቀልብ መሆን ምን ማለት ነው? ክፍል ውስጥ አስተማሪ ስም ሲጠራ በአካል የተገኘውን ተማሪ ለመቁጠር ነው። ከቀልቡ የሆነ ሰውን ‘አቴንዳንስ’ ቢይዝ ግን አስተማሪው ራሱ ‘አብሰንት’ ሊባል ይችላል። ከቀልብ መሆን ቀላል ነገር አይደለም። ሐሳብን ማቆም የዋዛ አይደለም። ሌላ አብነት፤ ሰዎች መለኪያ ውስኪ የሚጎነጩት ኋላ እና ፊት የሚፈነጭን ሐሳብ ለማስቆም ነው። የሆነ መለኪያ ቁጥር ላይ ስንደርስ ይህ ይሳካል። ፊልም የምናየውም ለተመሳሳይ ግብ ነው። ሐሳብን ለማስቆም። በምንወደው ፊልም ውስጥ እጅግ ፍሰሐ የምናደርገው ያ ቀዥቃዣው ሐሳብ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ስለሚቆም ነው። አለበለዚያ በ5 ደቂቃ የ15 ዓመት ፀፀት እያሰብን ሕመም ውስጥ እንገባለን፤ እናረጃለን። ወደ ዋናው ነጥባችን እንምጣ። አነቃቂ (ሞቲቬሽን) ንግር ስንሰማ ወይም ጽሑፍ ስናነብ ከፍታ ላይ እንወጣለን፤ የስሜት ማማ ላይ። ብዙዎቹ በቁማችን ቂቤ ያጠጡናል። ምኞታችንን እንድናመነዥግ ያግዙናል፤ በዲስኩር፣ በመጽሐፍ የሕልም ዓለም ውስጥ ያንሳፍፉናል። ስለዚህ ከፍተኛ የስሜት መነቃቃት ይፈጠርብናል። በዚህ ሂደት ውስጥ ታዲያ ከሰዎች መማር፣ ጥልቅ የንባብ ፍቅር ውስጥ መግባት፣ በራስ ማመን ሊፈጠሩ ይችላሉ። “ሞቲቬሽን ወደ ጠንካራ ዲሲፕሊን የመራቸው ሰዎች አሉ፤ ይህ በጎ ገጽታው ነው” ይላል ናትናኤል። ክፋቱ ግን ሞቲቬሽን በራሱ ሱስ ሊሆን ይችላል። ወደ እውነታው ስንመለስ ስለሚያመን እዚው መቅረት እንመርጣለን። ከሞቲቬሽን ወደ ሞቲቬሽን። በማነቃቂያ መድኃኒት የምንሠራ ከሆነ የዚያ መድኃኒት ጥገኛ መሆናችን አይቀርም። ሞቲቬሽን ሱስ ነው። ሁሉም ሱስ ሃንጎአር አለው፤ ሞቲቬሽንም ቢሆን፣ ይላል። ናትናኤል በሞቲቬሽን አብዮት ጊዜ ብዙ በጎ ነገሮች እንደተፈጠሩ አይክድም። ሰዎች ንባብን ለምደዋል። ከአዲስ ሐሳብ ጋር ተዋውቀዋል። የጊዜ አጠቃቀማቸው ተሸሽሏል። የሞቲቬሽን መሠረታዊ ችግሩ ግን አንድ ነው ይላል፤ “የብድር ደስታን መፍጠሩ።” ሞቲቬሽን የደስታ ወረፋ ውስጥ ያሰልፈናል ይላል። “ወደፊት ይህ ዓይነት መኪና፣ እንዲህ ዓይነት ቤት፣ እንዲያ ዓይነት ትዳር ሲኖረኝ ደስተኛ እሆናለሁ…” ካልን የደስታ ወረፋ ውስጥ ነን ማለት ነው። ከአነቃቂ ንባብ/ዲስኩር በኋላ ሰዎች መጠነኛ ድብርት ውስጥ ይገባሉ የሚለው ናትናኤል ምክንያቱ “የብድር ደስታ ውስጥ ስለነበሩ ነው” ይላል። “እኔም በሞቲቬሽን ሙሉ ጉባኤ ሙሉ ቁጭ ብድግ የማደርግበት ጊዜ ነበረ። ይሄ እኔ ሳልሆን ተማሪዎቼ የሚመሰክሩት ነገር ነው። ስህተት እንደሆነ ለመረዳት ግን ጊዜ ወስዶብኛል።” ታዲያ መፍትሄው ምንድነው? ሃብታም ሳይሆኑ ሃብታም የመሆን ምሥጢርን ማስተማር አይከብድም? በአሜሪካ ብዙዎቹ የብልጽግና ሰባኪዎች፣ የይቻላል አቀንቃኞች ቢያንስ የሃብት ጥያቄያቸውን መልሰዋል። ሚሊዮን ቅጂዎችን ሽጠዋል። ሕዝብ አነቃንቀዋል። በእኛ አገር ይህ ብዙም አይታይም። የሃብትን ምሥጢር፣ የብልጽግናን ቁልፍ እንካችሁ የሚሉን ሰባኪዎች ለራሳቸውም ያወቁ የማይመስሉበት አጋጣሚ አለ። ይህን ጥያቄ ለዶ/ር ወሮታው አንስተንላቸው ነበር። ሁሉንም በአንድ ቅርጫት ማስቀመጥ አግባብ እንዳልሆነ ጠቀሱ። በልምድ እና በሕይወት ተሞክሮ አልፈው የሚያሠለጥኑ አሉ። አዳራሽ ሕዝብ ሰብስበው ያለ ምንም የሕይወት ልምድ፣ ሕዝብ ላይ ቴአትር የሚሠሩም አሉ። “ለምሳሌ ናፖሊዮን ሒል ‘ቲንክ ኤንድ ግሮው ሪች’ን ሲጽፍ 25 ዓመት ነው የወሰደበት።” ስለዚህ እያሉን ያሉት ዶ/ር፣ ችግሩ ከሥልጠናው ሳይሆን ከአሠልጣኞቹ ነው? “አዎ! ለምሳሌ የእኔ አሠልጣኞች ያሰብከውን ስላለምክ ብቻ ትደርስበታለህ አላሉኝም። ለስኬት የምከፍለው ከፍተኛ ዋጋ እንዳለ ነው ያስተማሩኝ።” ባልተፈተነ ሕይወት፣ በጣፈጠ ቋንቋ ብቻ በሰው አእምሮ መጫወት ትክክል አይደለም የሚሉት ዶ/ር ወሮታው “ሙሉ አዳራሽ አስፈንጥዞ ማስወጣት ይቻላል። እኔ ያንን አልከተልም።” ዶ/ር ግን የማነቃቂያ ሥልጠና በመስጠት ሰውን ከድህንት ማውጣት ይቻላል? የምር ይህ ዘዴ ይሠራል ብለው ያምናሉ? “እንዴታ! ሰው ከዋሻ የወጣው ከችግር ለመውጣት ነው። ቁርጠኝነት እና ዓላማ ካለ ምን የማይሠራ ነገር አለ። ደግሞም በኢትዮጵያ። አንድ ሰው 8 ሰዓት ቢሮ ከሠራ ሌላውን 8 ሰዓት ባጃጅ ቢነዳ ምንድነው ችግሩ። የመለወጥ ቁርጠኝነት ካለ ማለቴ ነው።” ዶ/ር ሌላው ጥያቄ ሰዎችን አትቀጠሩ እያላችሁ ለምን በተሳሳተ መንገድ ታበረታታላችሁ? “ተቀጥረህ አትቅር እናለለን እንጂ አትቀጠር አንልም። ሰው ልምድ ማግኘት አለበት እኮ።” የመጨረሻ ጥያቄ ዶ/ር፣ ሃብት እና ብልጽግናን የምትሰብኩ ሰዎች ለራሳችሁም ሃብት አልፈጠራችሁም ይሏችኋል? “ይህ የተሳሳተ ነው። የእነ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ አሰልጣኝ ሯጭ ሳይሆን ለምን ያሰለጥናል ይባላል እንዴ? አዋቂ ያወቀውን ቢያስተምር በቂ ነው።” ዶ/ር ወሮታው ይህን ካሉ በኋላ ግን በልምድ እና በዕውቀት ያልዳበረ ሕይወት ሌላውን ለማብቃት ባይደፍር መልካም እንደሆነ አልሸሸጉም።
Show all...
አነቃቂ ንግግሮች ወዴት ያደርሱናል? * ወደ የማይጨበጥ ተስፋ ወይስ ወደ ስኬት? #Ethiopia | መካሪና ሰባኪ በዝቷል። ከመገናኛ እስከ ኢኒስታግራም፤ ከዩትዩብ እስከ ድልብ መጻሕፍት፣ ከመድረክ እስከ ታክሲ፤ በተለይ አራተኛ ወንበር ላይ። የሁሉም መልዕክት አንድ ነው፤ ‘የብልጽግና ባቡር ቀርባለችና ተሳፈሩ’ የሚል። በየዓመቱ መቶ ሺዎች እየተመረቁ ሥራ ያጣሉ። ‘የሥራ ፍጠሩ’ ሰባኪዎች ይቀበሏቸዋል። በስንት ደጅ ጥናት የተገኘን ሥራ ‘ጥላችሁ ውጡ’ ይላሉ። ዛሬውኑ የራሳችሁ አለቃ ሁኑ እያሉ ያስጎመዣሉ። ከእጅ ወደ አፍ ቀርቶ፣ እንደ ወፍ - ከአፍ ወደ አፍ በሆነ የዛሬ ኑሮ፣ ‘ከቆጠባችሁ ከነገ ወዲያ ሚሊዮነር ትሆናላችሁ’ ይላል። አነቃቂ መጻሕፍት ሕይወት ይለውጣሉ? የመድረክ ዲስኩሮች ያበለጽጋሉ? አንዳንዶች ‘አዎና! እኛን ነው ማየት!’ ይላሉ። ሌሎች ደግሞ በአነቃቂ መጻሕፍት የሚለወጥ ሕይወት ካለ የደራሲው እና የዲስኩረኛው ብቻ ነው ብለው ያፌዛሉ። በሁለቱም ጎራ የካበተ ልምድ ያላቸውን አሰልፈን ጉዳዩን ብናብላላውስ? ዶ/ር ወሮታው፡ “የአንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ሕይወት ለመለወጥ እየሠራሁ ነው” በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ግንኙነት ሦስተኛ ዲግሪ አላቸው። የእርሳቸው ሥራ ግን የሰዎችን አእምሮ ከብልጽግና ጋር ማዋደድ ነው። ወጣቶችን ወደ ሃብት ማማ ማውጣት። የትኛውንም አእምሮ በመግራት ስኬት እና ልዕልናን ማጎናጸፍ ይቻላል ብለው ያምናሉ። እንደተመረቁ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ተቀጠሩ፣ ከዚያም ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ አስተማሪ ሆኑ። ከዕለታት አንድ ቀን “ሕይወቴን የሚለውጥ አጋጣሚ ተፈጠረ” ይላሉ ዶ/ር ወሮታው። ቀን እና ወሩን ሁሉ አይረሱትም። በ1992 ዓ.ም. ነሐሴ ወር ከዩኒቨርስቲው ከጋና በመጡ አሠልጣኞቹ በሚሰጥ ሥልጠና ላይ እንዲሳተፉ ተላኩ። ሥልጠናውን ሲጨርሱ ከባድ የአስተሳሰብ ነውጥ ገጠማቸው። የአስተሳሰብ ነውጡ፣ የሕይወት ለውጥን አስከተለ። “በዚያች ቅጽበት የራሴን ነጻነት አወጅኩ፤ ከዚያ በኋላ በጭራሽ አልተቀጠርኩም፤ በጭራሽ!” ይላሉ። “ተቀጥሮ መሥራት አንገሽግሾዎት ስለነበር ነው ዶ/ር?” “አይደለም፤ በዚያች ቅጽበት የምኖርለትን ሕልሜን ስላገኘሁ ነው።” “የሚኖሩለት ሕልም ምንድን ነበር?” “ማሠልጠን፤ ባለጸጎችን ለኢትዮጵያ ማፍራት።” “የምር ይሳካል ብለው ያምናሉ?” “ያለጥርጥር! አንድ ሚሊዮን ባለጸጎችን ለኢትዮጵያ እናፈራለን።” “መቼ ነው ይህን ሁሉ ሰው ባለጸጋ የሚያደርጉት?” “የዛሬ 20 ዓመት፤ በነሐሴ 2023 ዓ.ም።” ዶ/ር ወሮታው ይህን የሚሉበት እርግጠኝነት የእምነታቸውን ጥንካሬ ያሳብቃል። እንዴት ያለ ሥልጠና ቢሆን ነው? “...በዚያ ሥልጠና ወሮታው ላይ ሳቅኩበት፤ ወሮታውን ነጻ አወጣሁት። ለሕልሜ ታማኝ እንድሆን፣ ሃብቴ አስተሳሰቤ እንደሆነ፣ የማምንበትን እየሠራሁ እንድኖር ያደረገኝ አጋጣሚ ነበር።” የእሳቸው ሕይወት በአንድ ሥልጠና ከተለወጠ የሌሎች ሕይወት ለምን አይለወጥም? ናትናኤል ፋንታ፡ “የሞቲቬሽን ሥልጠና በብድር መደሰት ማለት ነው” ‘ናትናኤል ሜሞሪ’ በሚለው የንግድ ስሙ በርካቶች ያውቁት ይሆናል። የሕይወቱን እኩሌታ በአእምሮ ሥልጠና ላይ አሳልፏል። ናትናኤል በተለይ በማስታወስ ጥበቡ በ90ዎቹ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ እየቀረበ ብዙ ሰዎችን ሲያስደምም አንዳንዶች ዛሬም ድረስ ያስታውሱታል። ናትናኤል ከማስታወስ ጥበብ በኋላ በቀጥታ ወደ ‘ሞቲቬሽን’ [ማነቃቃት] ተሸጋገረ። ብቻ በጥቅሉ ባለፉት በ21 ዓመታት በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ከአእምሮ ጋር በተያያዘ አሠልጥኗል። የእሱን ልብ አንጠልጣይ ‘ሞቲቬሽን’ ቃል ለመስማት ብዙዎች አዲስ አበባ 22 አካባቢ ደጅ ጠንተዋል። እሱም ያንን ዘመን በመለስተኛ ፀፀት እያስታወሰ፣ “...ሙሉ ጉባኤ ቁጭ ብድግ አስደርግ ነበር” ይላል። አሁን ግን ፍጹም በተቃራኒው ቆሟል። የአነቃቂ ንግግሮች አድናቂ አይደለም። እንዲያውም ‘ሞቲቬሽን’ አይሠራም ሲል አውጇል። “ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ ያረጋገጥኩት አንድ ነገር ቢኖር፣ የሰዎችን ሕይወት ለመለወጥ ትክክለኛው መንገድ ያ እንዳልነበረ ነው” ይላል። ለምን? በ21 ዓመት ውስጥ ምን ተፈጠረ? ትክክለኛው መንገድ ያ ካልሆነ ታዲያ የቱ ነው? በዓመታት ጥናት ደረስኩበት የሚለውን ይነግረናል። የአነቃቂ መጻሕፍት አጭር የሕይወት ታሪክ ራስ አገዝ መጻሕፍት፣ የይቻላል ዲስኩሮች እና መሰሎቻቸው በጅምላው ‘ሰልፍ ዴቨሎፕመንት ኢንዱስትሪ’ ውስጥ ይካተታሉ። በአሜሪካ በአንድ ወቅት ከሙዚቃ ኢንዱስትሪው ቀጥሎ ሚሊዮን ዶላር የሚያንቀሳቅስ ዘርፍ ነበር። በተለይ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ወዲህ። የአነቃቂ መጻሕት አባት የሚባለው ቻርልስ ሃናል ነው። ኋላ የመጡት ገናናዎች የእርሱ ደቀ መዛሙርት ናቸው። በዘመኑ የጻፈው ነገር አእምሮን የሚያሸፍት ነበር። “…ኋላ ላይ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያን መጽሐፎቹን ለቅማ አቃጥላበታለች” ይላል ናትናኤል። ከእርሱ በኋላ አብረሃም ማስሎው መጣ። “አእምሮን በመግራት ማንም ሰው ምንም መሆን ይችላል” ብሎ ተነሳ። ቀስ በቀስ ሞቲቬሽን ከቤት እና ከቢሮ ወጥቶ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሰተት ብሎ ገባ። የይቻላል መንፈስ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንቀጾች ጋር ስምም ተደርጎ በሰባኪዎች አንደበት ተነገረ። ሚሊዮኖች በተስፋ ራሳቸውን ሳቱ። ያለስስት ጥሪታቸውን ለሰባኪያን ሸለሙ። ከአፋቸው ማር ጠብ የሚልልላቸው ሰባኪያን መቅደስ ጠበባቸው። በቲቪ መስኮት መጡ። ‘ቴሌቫንጀሊስቶች’ ተወለዱ። በስብከት ጉባኤ መዋጮ የግል ጄት ገዙ። ምዕመናን የታክሲ እያጡ፣ እየነጡ መጡ። ካፒታሊዝም ፋፋ። የገበያ ትንቅንቅ ተፈጠረ። ‘ሞቲቬሽን’ ሽያጭን የሚያስመነድግ ሁነኛ መሣሪያ እንደሆነ ተደረሰበት። ሰዎች የስቶክ ማርኬት የድርሻ ገበያ እንዲገዙ ማሳመን ፈተና ሆኖ ነበር። ለዚያም ነው በሞቲቬሽን አእምሯቸውን ማጦዝ፣ በተስፋ ካውያ ማጋል አስፈላጊ ሆኖ የተገኘው። እንዲህ፣ እንዲያ እያለ በ80ዎቹ እና በ90ዎቹ የሞቲቬሽን ኢንዱስትሪ ጣሪያ ነካ። ደራሲያን መጻሕፍትን በሚሊዮኖች ቅጂ መሸጥ ጀመሩ። በእኛም አገር ‘ኔትዎርክ ማርኬቲንግ’ በስፋት ዘልቆ ገባ። የ’ጎልድ ኩዌስት’ ዘመን፣ የፒራሚድ ገበያን ለማሳለጥ ሁነኛ የ’ሴልስ’ ስትራቴጂ ኾኖ አገለገለ። ሐኪሞች ሆስፒታልን፣ መምህራን አስኳላን ጥለው ወጡ፤ ወደ ሀብት ይወስዳል የተባለው አውራ ጎዳና በሕዝብ ታመቀ፣ ተጨነቀ። ብዙዎች “አይቤን ማን ወሰደው”ን እያነበቡ አይባቸውን ፍለጋ ባዘኑ። አንዳንዶች አገኙት። ብዙዎች አጡት። ናትናኤል ያን ዘመን የነበረውን አስደማሚ መነቃቃት ሲያስታውስ፣ “አዳራሽ ውስጥ ‘I believe I can fly’ የሚል ሙዚቃ ተከፍቶ ሰዎች በተስፋ ብቻ ሲያለቅሱ አይቻለሁ” ይላል። ይህን ነው እሱ “የብድር ደስታ” የሚለው። ምን ማለቱ እንደሆነ ቆየት ብሎ ያስረዳናል። የዴል ካርኒጌ ዘመን እርግጥ በእኛ አገር ብቻም ሳይሆን አሜሪካ ገበያ እነ ዴል ካርንጌ፣ እነ ናፖሊዮን ሒል የጻፏቸው መጻሕፍት ከባድ የአስተሳሰብ አብዮት አስነስተዋል። በተለይ ናፖሊዮን ሒል ለ25 ዓመታት 500 የሚሆኑ እጅግ የናጠጡ ባለጸጎች ላይ ጥናት ሠርቶ “Think and Grow Rich” የሚለውን መጽሐፉን ከጻፈ በኋላ ምድረ አሜሪካ በ‘ይቻላል’ ተነቃንቋል። ከዚያ ወዲያ ‘ሞቲቬሽን ዘርፍ’ ሳይከስም እየጎመራ ነው የቆየው። በርካታ በዓለም ዙሪያ የተሰራጩ የማነቃቂያ መጻሕፍት ታትመው ሚሊዮኖች ጋር ደርሰዋል።
Show all...
የገቢ ስትራቴጅ (Revenue Strategy) 1. በላብህ በደምህ (Active Income) 2. በብርህ (Passive Income)
Show all...
የአንድ ሰው የገቢ ኡደት (Revenue Cycle) ምን ይመስላል? (ለጤናህ እጅጉ ዋለ) የአንድ ሰው የገቢ ኡደቱ እንደሚከተለው ከ ሀ ወደ ፐ ይፈሳል ። ማለቴ ከለፍተህ ጥረህ ግረህ ብላ (Active Income) ወደ ብዙ ሳትለፋ ብላ (Passive Income) የሚቀየረው በሚከተለው ዘዴ ነው ። 1. በመጀመሪያ የሆነ የሚያበላ 😂 ትምህርት ወይም ሙያ ተማሩ ። የሚያበላ ትምህርት ወይም ሙያ ምንድን ነው ከተባለ እንጃ ራሳችሁ ተወያዩበት 😂 እውቀትና ሙያ ነፃ ያወጣል የምንለው ለዚያ ነው ። የአንድ አገር እድገትና ብልፅግና መሰረቷ ትምህርት ነው ። ያልተማረ ሰውኮ ገንዘብ ቢኖረውም እየኖረ አይደለም ። ያልተማረ ሰው በጨለማ ውስጥ የሚኖር ሰው ነው ። በኔ አተያይ ህዝባችን ቢያንስ በዝቅተኛ ደረጃ ወይ ቴክኒክ እና ሙያ ወይም የመጀመሪያ ዲግሪ መያዝ አለበት ። ከዚያ በላይ ያለው እንኳን ለጥቂቶች ብቻ ነው መሆን ያለበት ። አገሪቱ እንዳይን የጠፋችው ሁሉም በግድ ማስተርስና ዶክትሬት ካልያዝኩ ብሎ ገግሞ ነው 😁 2. ቀጥሎ በተማራችሁበት ትምህርት እና ሙያ የሚያበላ ቦታ 😂 ተቀጠሩና ገቢ አግኙ ፤ ይህ በላብ የሚገኘው ገቢ Active Income ይባላል ። አዳም ሆይ ለፍተህ ጥረህ ግረህ ብላ ብሏል ታላቁ እና ቅዱሱ መፅሃፍ ። የሚያበላ መስሪያ ቤት የቱ ነው እንጃ እራሳችሁ ተወያዩበት😂 3. ቀጥሎ ተቀጥራችሁ ከምታገኙት ገቢ ውስጥ ቆጥቡ ሁሉን አታውድሙት ፤ የብዙ ሰው ችግር ይኸ ነው ፤ ሁሉን ማውደም ። በአለም አቀፍ ስታንዳርድ መሰረት ቢያንስ የገቢያችንን 20% መቆጠብ አለብን ይባላል ። እኛ ግን ያለንን ሁሉ አውድመን ከዛ ወይ እንበደራለን ወይ እንለምናለን ። በቁጠባ ላይማ አነቃቂ ስልጠና መስጠት አለብኝ 😂 3. ቀጥሎ ቁጠባችሁን ይዛችሁ ባንክ ሂዱና ተበደሩ ። ብድር አትፍሩ ። ስለብድርም ስልጠና መስጠት አለብኝ 😂 4. ቀጥሎ የራሳችሁን ቁጠባና የባንክ ብድሩን ይዛችሁ ብዙ ሳትለፉ ገቢ የሚያስገኝላችሁ ንብረት ግዙ ። ያ ንብረት የሚከራይ ህንፃ መገንባት ወይም የሚያበላ አክሲዮን መግዛት ሊሆን ይችላል ። Look back again all kind of passive income strategies I wrote. 5. ህንፃውን አከራዩ ወይም አክሲዮን ግዙና ቀስ በቀስ ከመቀጠር ወጡ እና ሳትለፉ ገቢ አግኙ ። ይህ ብዙ ሳትለፉ ገቢ የምታገኙበት ዘዴ Passive Income ይባላል ። ህንፃው ወይም አክሲዮኑ ይሰራል አንተ አትሰራም ግን ትበላለህ 😁 Passive Income ማለት ሳትሰራ መብላት ነው ። በነገራችን ላይ ይህ ህጋዊ እና ታክስ የሚከፈልበት ስራ ነው ። አንዳንዱ እንደ ህገወጥ ስራ ሊያየው ስለሚችል ብየ ነው ይችን ነጥብ የጨመርኳት 😁 በአጠቃላይ ይኸው ነው ፤ እና ግልጥ ነው ጓዶች 😂 ይህን ሁሉ እንድለፈልፍ ያደረገኝ ዶር GM Melaku ከአሜሪካ ህንፃው እንዴት ይሰራል ብሎ ለጠየቀኝ ጥያቄ መልስ ነው ። እግዞ ተው እንጂ ብዙ አታስለፍልፉኝ 😁 ሻሎም ለጤናህ ነኝ ከአባይ ወንዝ ዳር
Show all...
ብዙ ሳንለፋ ገቢ የምናገኝባቸው ዘዴዎች (Passive Income Strategies) (ለጤናህ እጅጉ ዋለ ) 1. ህንፃ ማከራየት 2. የትርፍ ክፍፍል የሚከፍሉ አክሲዮኖችን መግዛት 3. ለጓደኛህ ማበደር (Peer to Peer Lending) 4. በዌብሳይት ምርቶችን ማስተዋወቅ (Affilate Marketing) 5. ዲጂታል ኮርስ ወይም ኮንቴንት መፍጠር 6. ከአእምሮአዊ ንብረት የሚገኝ ሮያሊቲ 7. ከፍተኛ ወለድ የሚያስገኙ የባንክ ቁጠባዎች 8. ንብረት ማከራየት ፤ ለምሳሌ መኪና ፤ ማሽን ሌላም እቃ
Show all...
የማዳበሪያ ስርጭት ምርመራ ይካሄድ !!! በኔ ግምት በማዳበሪያ ስርጭት ጉዳይ ላይ ማዳበሪያው ጥቁር ገብያ ገብቶ አርስአደሩ እንዲበዘበዝ ያደረጉ ማንኛውም ከላይም ሆነ ከታች ያለ አመራር ሆነም ባለሙያ ሆነ ነጋዴ ካለም ነጋዴ በሚመለከታቸው የህግ አካላት (ፀረ ሙስና ፤ አቃቢ ህግ ፤ ፖሊስ ወዘተ) ምርመራ መደረግ አለበት እላለሁ ። ለዚህም በየሶሻል ሚዲያው የህዝብ ተቆርቋሪ ነኝ የሚለው አክቲቪስቱ ወጥሮ መቀስቀስ አለበት እላለሁ ። በማስቀጠል የህዝብ የቴሌቪዢን ጣቢያዎችም (ኢቢሲ ፤ አሚኮ ፤ ፋና ፤ ዋልታ ወዘተ ) serious የሆነ የምርመራ ጋዜጠኝነት (Investigative Journalism) ዘገባ መስራት አለባቸው ። ይህን ካልሰሩ ምን ሊሰሩ ነው ? ዋ ! ባጭሩ ከዚህ በላይ አገርና ህዝብን systematically መግደል የለምና ሁሉም ተረባርቦ አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረግ አለበት እላለሁ !!!
Show all...