cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ተዋህዶ ሀይማኖቴ💚💛💓

እሴብህ ጸጋኪ ኦ እግዝትነ ማሪያም🙏 ፅዮን ሆይ ስምሽን ለልጅ ልጅ እናሳስባለን 🙏 "የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሏቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው። ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ.." [ዕብ 13፡7-9

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
254Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

" ጨዋ ሰው በሌሎች ሰዎች መጎሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምቾት ይረሳልና " #ብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ሺኖዳ ⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇ 🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ ~ሼር~🟩🟨🟥 @TewahidooHaymanote > <@TewahidooHaymanote 🟩🟨🟥 ~~~~ተቀላቀሉ ~~
Show all...
💗 "ቅድስት ድንግል ማርያምን መውደድ ከሚገባኝ መጠን በላይ አልፌ ወድጄያት ይሆን? ብለህ ሥጋት አይግባህ። ኢየሱስ ክርስቶስ ከወደዳት በላይ ልትወዳት አትችልምና" 💗 ቅዱስ ማክሲሚሊያን ኮልብ ⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇ 🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ ~ሼር~🟩🟨🟥 @TewahidooHaymanote > <@TewahidooHaymanote 🟩🟨🟥 ~~~~ተቀላቀሉ ~~
Show all...
የእመቤታችን_አማላጅነት_በአጭሩ‼️ 👉 አማላጅ ማለት ወደዋናው ባለሙሉ ሥልጣን ሊያቀርብ የሚችል ባለሟል ነው። አማለደ ማለት ለመነ፣ ጸለየ ማለት ነው። ዋናው ባለሥልጣን እርሱ አንድ አምላክ የሆነ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሥልጣኑ አምላክነቱ የባሕርዩ ነው። ባለሟሎቹ ደግሞ መረጥኳችሁ፣ ጠራኋችሁ፣ አጸደኳችሁ፣ አከብርኳችሁ ያላቸው ቅዱሳን ናቸው። ይህ የባለሟልነት ሥልጣን የተሰጣቸውም በሰማይና በምድር ንጉሥ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህን እውነት በተመለከተ በመጽሐፍ ቅዱስ እጅግ በጣም በሰፊው የተጻፈ ቢሆንም ከብሉይና ከሐዲስ ኪዳን ትንሽ ጥቅሶች እንመልከት:- #በብሉይ_ኪዳን 1, ዘፍ 20÷7 "ነቢይ ነው ስለ አንተም ይጸልያል ትድናለህም 2, ዘጸ 8÷8 "ፈርኦንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ ጓጉንቸሮቹን ከኔ ከሕዝቤም እንዲያርቅ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ" 3, ኢዮ 42÷8 "ባርያዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል እኔም እንደ ስንፍናችሁ እንዳላደርግባችሁ ፊቱን እቀበላለሁ።" #በሐዲስ_ኪዳን 1, ያዕ.5÷16 "የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።" 2, 2ቆሮ5÷20 "በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን።" ማንኛውም ሰው ታድያ ቀጥታ ወደ አምላኩ መጸለይ ይችላል ዳሩ ግን አማላጅ የሚያስፈልገው:- 1, እግዚአብሔር የማማለድን እና የማስታረቅን ቃልኪዳን ለቅዱሳን ስለሰጠ/2ቆሮ5÷20/ 2, በቅድስና ሕይወት ቅዱሳን ጻድቃን ከእኛ ስለሚበልጡ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማድረግ ለእግዚአብሔር ቅርብ ስለሆኑ/መዝ33(34)÷15/ 3, ሁሉን ትተው ስለተከተሉት ማማለድ ብቻ አይደለም ይፈርዱ ዘንድ ሥልጣንን ሰቷቸዋልና/ማቴ19÷27-29/ 🔴 ሁሉን ትተው ለተከተሉት ለ 3ዓመት ደቀመዛሙርቱ ለሐዋርያት የመፍረድን ሥልጣን ከሰጣቸው አምላካችን ክርስቶስ ታድያ እድሜ ልኳን ከጌታ ያልተለየችው፣ 9ወር ከ5ቀን በማኅጸኗ ለተሸከመችው፣ ለአራት ዓመታት ሙሉ ጡቶቿን ላጠባችው፣ ሄሮድስ በምቀኝነት ሊገድለው በፈለገ ጊዜ በጀርባዋ አዝላ አራት ዓመት ከአንዱ ሀገር ወደ አንዱ ሀገር አብራው ለተሰደደችው፣ ከውልደቱ እስከ ትንሣኤው ላልተለየችው ታማኝ እናቱ እውነት ምን ዐይነት ሥልጣን ሰቷት ይሆን?!?! እውነት ለእኛ ማማለድስ(መጸለይስ) ወደልጇ እውነት ለእመቤታችን ቁምነገር ሆኖ ነው?! ስለዚህ ከላይ ባየናቸው ነጥብ መሠረት ለዛውም ጸጋ የሞላብሽ ተብላ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደ እመቤታችን የተነገረለት ማን አለና? ምንስ ይጎድላታል? ንጽህና ነው ወይስ ቅድስና? ለእኛ ወደ ልጇ ለመጸለይ?! ክብር ለመድኃኔዓለም እና እሱ ላጸደቃቸው እና ለመረጣቸው ለቅዱሳኑ ይሁንልኝ! አሜን!! ⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇ 🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ ~ሼር~🟩🟨🟥 @TewahidooHaymanote > <@TewahidooHaymanote 🟩🟨🟥 ~~~~ተቀላቀሉ ~~
Show all...
" ሕዝቤ፥ ስማኝ፥ ልንገርህ፤ እስራኤልም፥ ስማኝ፥ልመስክርብህ፤ አምላክስ እኔ አምላክህ ነኝ።" (መዝ 50: 7) የኢትዮጵያ ህዝብ አምላክህ እግዚአብሔር ነው። እኛ ብትክደውም እርሱ ግን አምላካችን እንደሆነ በብዙ መንገድ ይመሰክርብናል። (መዝ 50 ) ------------ 14 ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፤ 15 በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተ ታከብረኛለህና 19 አፍህ ክፋትን አበዛ፥ አንደበትህም ሽንገላን ተበተበ። 20 ተቀምጠህ ወንድምህን አማኸው፥ ለእናትህም ልጅ ዕንቅፋት አኖርህ። 21 ይህን አድርገህ ዝም አልሁህ፤ እኔ እንደ አንተ እሆን ዘንድ ጠረጠርህ፤ እዘልፍሃለሁ በፊትህም እቆማለሁ። 22 እግዚአብሔርን የምትረሱ እናንተ፥ ይህን አስተውሉ፤ አለዚያ ግን ይነጥቃል የሚያድንም የለም። 23 ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። (የእስራኤል አምላክ የታመነ ነው) ⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇ 🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ ~ሼር~🟩🟨🟥 @TewahidooHaymanote > <@TewahidooHaymanote 🟩🟨🟥 ~~~~ተቀላቀሉ ~~
Show all...
ሞትን ሳያይ በእሳት ሰረገላ የተነጠቀው ነብይ ማነው?Anonymous voting
  • ሙሴ
  • ኤልያስ
  • ሄኖክ
  • ኤልሳዕ
0 votes
ማርያም እና የመናፍቃን ተደጋጋሚ ጥያቄዎቻቸው "ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ "1 ጴጥ 3:16 👉 ጥያቄ 3 ነገረ ማርያም ላይ ነፍሳት እንዲድኑ አንቺ ሙቺ ሲላት እንኳን አንዴ ሰባት ጊዜም ቢሆን ልሙት አለችው በምልጃዋ ሲገርመን እንዴት በሞቷ ልታድን ትችላለች?? 👉 መልስ ሰባት ጊዜ ልሙት ማለቷ በምልጃዋ እንጂ በሞቷ ታድናለች ? ለሚለው ሞትዋን የምልጃእጅ መንሻ አድርጋ ነው ያማለደችው እኛ እንዲህ ካደረክልን ብለን የምንሳለው ስእለት አይነትይህ ደግሞ የቅዱሳን ልማድ ነው " አሁን ይህን ኃጥያታቸው ይቅር በላቸው ያለዚያ ግን ከጻፍከው መፅሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ "ዘፀ 32:32 እመቤታችን ከተቀስናቸው ቅዱሳን ሁሉ ብትበልጥ እንጂ አታንስምና አምነን እንቀበላለን!! ©ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇ 🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ ~ሼር~🟩🟨🟥 @TewahidooHaymanote > <@TewahidooHaymanote 🟩🟨🟥 ~~~~ተቀላቀሉ ~~
Show all...
"ይረባኛል፣ይጠቅመኛል ብለህ የመናፍቃንን መጽሐፍ አትመልከት፡፡ ከመመልከትህ የተነሳ ጸጋ ክብር ታጣለህ፡፡ አንድም የነቢያትን የሐዋርያትን መጽሐፍ በመመልከት ከሚገኘው እውቀት ተለይተህ ትጎዳለህ፡፡” ማር ይስሐቅ 🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ ~ሼር~🟩🟨🟥 @TewahidooHaymanote > <@TewahidooHaymanote 🟩🟨🟥 ~~~~ተቀላቀሉ ~~
Show all...
ገብረመንፈስ ቅዱስ የአለም ብርሃን ናቸው ይኸው ለዘላለም ያበራል ስራቸው🙏🙏🙏
Show all...
ማርያም እና የመናፍቃን ተደጋጋሚ ጥያቄዎቻቸው "ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ "1 ጴጥ 3:16 👉 ጥያቄ 2 ክርስቶስ ከሙታንመካከል ሲነሳና እንዲሁም ሲያርግ መግነዙን እዛው መቃብር ነበር የተወው ማርያም ግን ስታርግ መግነዟን ይዛ ነበር ለምንድነው?? ለቶማስ ልትሰጠው ነወ ከሚለው ሌላ የተሻለ መልስ አላችሁ 👉 መልስ እመቤታችን ለቶማስ ልትሰጠው ሳይሆን መታጠቅያዋ ስለሆነ ነው ከነ መታጠቅያዋ ስለተነጠቀች ነው (Ascention በራስ ወደላይ መውጣት ሲሆን Assumption መወሰድ መነጠቅ ነው ።) ለቶማስ መሥጠቷ ደግሞ የቅዱሳን ልማድ ነው ኤልያስ ሲያርግ መጎናፀፍያውን ትቶለት ሄዷል ለኤልሳ በዚህም መጎናፀፍያ ባሕር ከፍሎበታል ።2 ነገ 2:12 የእርሷ ልብስ ምን ያደርጋል? ቢሉ ከላይ እነሱ በሰጡን ፎርሙላ ተጠቅመን " እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎችም መናፍስት ይወጡ ነበር ።" ሐዋ 19: 22 ። ይህን ያሰነበበ የእመቤታችን ልብስ ምን እንደሚያደርግ አየይጠፋውም።ጌታ መግነዙን የተወው ትንሣኤውን የማያምኑ ሰዎች አውሬ በላው ሌባ ሰረቀው ብለው ያሶሩትን ወሬ ከንቱ ለማድረግ ነው አውሬ መግነዝ ፈቶ አይበላም ሌባም ውድ በፍታ ትቶ ሥጋ ብቻ አይሰርቅም በዚህ ጉዳይ የዲያቆን ኅብረት የሺጥላን "መግነዙን ትቶ ለምን ተነሣ? " የሚል ትምህርት google አድርጎ መመልከት ይቻላል ይህ መግነዝዋ ነው carbon dating አርኪዮሎጂስቶችም ለሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዘመኑን አረጋግጠው የምስክር ወረቀት ሰጥተዋታል። 🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ ~ሼር~🟩🟨🟥 @TewahidooHaymanote > <@TewahidooHaymanote 🟩🟨🟥 ~~~~ተቀላቀሉ ~~
Show all...
❖ መልካም አዲስ አመት አትበሉን!!!!!!! የ ፳፻፲፩ (2011) ዓ.ም የመልካም ምኞት መግለጫ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ማኅበራዊ ሚዲያዎች 'መልካም አዲስ አመት' ሲሉ "መልካም አዲስ ገረድ' ማለታቸው መሆኑን ያውቃሉ...... ♦ "አመት" ተብሎ በአልፋው "አ" ሲጻፍ ሴት አገልጋይ ገረድን ይገልጻል። ለምሳሌ፦ "ተፈሥሒ ኦ አመት ወእም ድንግል ወሰማይ ሰማያዌ..." /ውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ/ ሲል ገረድ(ሴት አገልጋይ) ና እናት፤ ድንግልና ሰማይ ሆይ ደስ ይበልሽ ማለት ነው። ♦ "ዓመት" ሲሆን ዘመን ይሆናል። "...ርእሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ።..."/መልክአ ዮሐንስ መጥምቅ፤ ለሥእርተ ርእስከ(ለራስ ጸጉርህ)/ ሲል ደግሞ "የመጥቅዕና የአበቅቴ መጀመሪያ ርእሰ ዓመት ዮሐንስ ሆይ..." ማለት ነው። ✍ አመት የሚለው በብዙ ቁጥር አእማት ይሆናል። በዕብራይስጥ አማህ፤ በሱሪስት አምታ፤ በዐረብኛ ደግሞ አመት ይለዋል። ትርጓሜውም ሴት ባሪያ፤ ገረድ፤ ደንገጥር ማለት ነው። "...በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ ባሪያይቱ..." ዘፀ.11፥5 የሚለውን ግዕዙ "አመት እንተ ትነብር ዲበ ማሕረጽ።" ይለዋል። በዚህ አገባብ አማርኛው "ባሪያይቱ" የሚለውን ግዕዙ "አመት" ይላታል። ✔ ወንዶች ባሪያዎችን "አግብርት" ሲላቸው ሴቶች ባሪያዎችን ደግሞ "አእማት" ይላቸዋል። [ዘፍ.32፥5 ግዕዙን ንባብ ተመልከት] ♦ ዓመት የሚለው ደግሞ በብዙ ቁጥር "ዓመታት" ሲባል ዘመን፥ ዘመናት፥ ብዙ ቀን፥ የዕለታት ድምር ማለት ነው። "በባቢሎን ንጉሥ በብልጣሶር በመጀመሪያው ዓመት" ዳን.7፥1 የሚለውን ግዕዙ "በቀዳሚ ዓመተ መንግሥቱ።" ይለዋል። "የዕድሜህም ቁጥር ብዙ ነውና፥" ኢዮ.38፥21 የሚለውን ግዕዙ "ኊልቆ ዓመታቲከ፥" ይለዋል። ✍ ስለሆነም አንድ ሰው 'እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሰን' ሲል 'እንኳን ለአዲሷ ገረድ አደረሰን' አለ ማለት ነው። ይኼ ደሞ ጸያፍ ነው። ♦ "እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን" ሲል "እንኳን ለአዲሱ ዘመን አደረሰን ማለቱ ነው። ይኸውም የተገባ ነው። ✔ መልካም ምኞታችሁን የገለጻችሁ መስሏችሁ 'መልካም አዲስ አመት' አትበሉን!!!!! በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ 🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ ~ሼር~🟩🟨🟥 @TewahidooHaymanote > <@TewahidooHaymanote 🟩🟨🟥 ~~~~ተቀላቀሉ ~~
Show all...