cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

True Gospel

የ እውነት ወንጌል በ ቻናላችን በየ ዕለቱ #መለኮታዊ ትምዕርቶች #ትንቢታዊ መልዕክት #ወቅታዊ ምክር #የፀሎት ጊዜ #መዝሙር ለማነኛውም ሀሳብ እና አስተያየት @Mnasie #JOIN OUR QUOTE CHANNEL @christians_profile https://vm.tiktok.com/ZMdTx2Nqx/

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
960Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

https://vm.tiktok.com/ZMLgaxvgK/ #ለኔ ነው መንከራተትህ follow me on tiktok 🙏
Show all...
Servant Mnasie on TikTok

Servant Mnasie's short video with ♬ original sound

የፍቅር #ጥግ CHANNEL CHRISTIANS PROFILE CREATOR MINASIE
Show all...
#በሞቱ ነፍሴን ከሞት መለሳት CHANNEL CHRISTIANS PROFILE CREATOR MINASIE
Show all...
CHANNEL CHRISTIANS PROFILE CREATOR MINASIE
Show all...
ርዕስ፦ የክርስቶስ ፍቅሩ ሰማይ ምድር ሳይኖር ሳይፈጠር ሁሉ ምንም ሳይገነባ ከአፍ ሳይወጣ ቃሉ በሰማይ በምድር በባህር ውስጥ ያሉ ሳይመጡ ወደምድር ሁኑ ሳይባሉ ህያዋን ፍጥረታት በህይወት ሳይኖሩ ወፎች ከየጎጆ መዝሙር ሳይዘምሩ ወንዞች ከምንጫቸው ሳይፈልቁ ሳይወጡ ሰዎችም መስዋዕት ለእርሱ ሳይሰጡ ክብር ሳያመጡ ማንም ሳያከብረው ክብር የተረፈው ሞገስና ዝና የተትረፈረፈው ሆኖ ሳለ ጻድቅ በዝቶ ሳለ ክብሩ ወደምድር አመጣው አሸነፈው ፍቅሩ በመካከል ኖረ በእጆቹ ስራ የባሪያን መልክ ያዘ ቆመ በሰው ስፍራ ከወንበዴ መሀል እርሱም ተካተተ ስለሰው ልጅ ኖረ ስለሰው ልጅ ሞተ ከፍ ሊያደርገን ወርዶ ሊያከብረን ተዋርዶ ከውርደት ጀመረ በበረት ተወልዶ እምባዬን ሊያብሰው ደሙን አፈሰሰ ፍቅሩን ሊገልፅልኝ መከራን ቀመሰ በክብሩ ሊያከብረኝ ውርደትን ለበሰ በግርግም ጀምሮ በመስቀል ጨረሰ ✍ ምናሴ @true_gospel
Show all...
ዲያጎን የተባለ ፈላስፋ በመንገድ ሲያልፍ አንድ በጣም ውብ የሆነ ሁለመናው የተዋበ ግን ተንኮለኛ ሰው ተመለከተና "ቤቱስ ያምራል ያደረበት ግን የማይረባ ነው አለ። የውጭ ሰውነታችን የውስጠኛው ሰውነታችን አገልጋይ፣ባርያ እና ስራ አስፈፃሚ ነው። የውጭ ሰውነታችን የራሱ ፈቃድ የለውም። አፍ (አንደበት) አእምሮ ሲያዘው ይረግማል አእምሮ ሲያዘው ይመርቃል አእምሮ ሲያዘው ይዘምራል አእምሮ ሲያዘው ይዘፍናል አእምሮ ሲያዘው ያሞግሳል አእምሮ ሲያዘው ይሰድባል። በውጭ የምናያቸው የሰውነታችን ክፍሎች ምንም የሆነ የራሳቸው ፈቃድ የላቸውም። በእግዚአብሔር ፊት የሚያምር መልበስም የማይረባ መልበስም ታጥቦ መቆምም ቆሽሾ መታየትም ዋጋ የለውም። ሰው ወደሚታየው ፊትና ሰውነት ልብስ ይመለከታል። እግዚአብሔር ግን የማይታየውን እና የተሰወረውን ልቦናችንን ያያል። የሚያምር ልብስ ንፁህና ውድ ጫማ ማራኪ ፊት ደስ የሚል ሽቶ ብዙ መባና መስዋዕት የእግዚአብሔር የህይወት መስፈርት አይደሉም። እግዚአብሔር በእኔ ደስ የሚሰኘው ልብሴን ሳጥብ ኪሴን ሳሳብጥ ፊቴን ሳሳምር ሳይሆን ልቦናዬን ሳነፃለት ውስጤን በእምነት ስሞላው ነው። ኤፌሶን 3፥16-17 "በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር..." ይላል። ስለዚህ እግዚአብሔር የውስጥን ሰውነት መጠንከር እና የልብን እምነት ይመለከታል። "ልብን እና ኩላሊትን" የሚለው ቃሉ እነሱን ያያቸዋል ሳይሆን ለሰው የተሰወረውን የሰውን ማንነት ይመረምራል ማለት ነው። አንዳንድ ጊዜ እከሌ ሞተ ሲባል አሁን አይቼው ነበር እኮ ትናንት እኮ አብረን ነበርን.....ምናምን ይባላል። ሰውየው ድንገት አልሞተም ቆሞ ሄደ እንጂ ውስጥ አልቆ ነበር ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር "አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ" ነው የሚለው ሰው ግን ጥፍሩን ፀጉሩን ፊቱን ነው የሚጠብቀው። ፊታችን ቢበላሽ አንሞትም ጥፍራችን ቢነቀልም እንኖራለን ፀጉራችንም ባያምር ምንም ላይቀርብን ይችላል ልባችን ውስጣችን የተበላሸ ቀን ግን ብዙ ነገሮች ይበላሻሉ። እግዚአብሔር የሚባርከው መጀመሪያ ልብን ነው በእግዚአብሔር በረከት የልቡ ዕይታ የተስተካከለ ሰው ምንም ነገሮች ውበት ባይኖራቸው የነገሮችን መልካም ጎን እያየ ይደሰታል። ሰው ዕይታው ካልተስተካከለ ባለው 99 ብር መደሰት ትቶ በጉደለው 1 ብር ያለቅሳል። ሰውነትህን ልብስህን ጠረንህን እና ውበትህን ለራስህ እና ለሰዎች ጠብቅ የውስጥህን ነገር ደግሞ ለእግዚአብሔር አስውብለት። ውስጣችን የሚገነባው በእግዚአብሔር መንፈስ እና በክርስቶስ ላይ ባለን የእምነት ልክ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር የውስጣችንን ጥንካሬ እና በልባችን ያለውን ክርስቶስ ይመለከታል ይመረምራል ይመዝናል። በውስጡ ያልጠነከረ ሰው የውጩ መጠንከር የትም አያደርሰውም። ✍ አገልጋይ ምናሴ #ተባርካችኋል #SHARE_SHARE_SHARE #JOIN 👇👇👇👇👇 @CHRISTIANS_PROFILE @TRUE_GOSPEL
Show all...
ይገርማል ●ከሚያስፈልገን ይልቅ የምንፈልገውን እንመርጣለን ●ከሚናገሩን ይልቅ የሚሰሙንን እንፈልጋለን ●እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ እርሱ እንዲሰማን እንፈልጋለን ●ከመማር ማስተማርን እንመርጣለን ●ከምናገኘው ይልቅ የምናጣው ጎልቶ ይታየናል ●አጠገባችን ያለው ከሩቅ ይታየናል ◈እስኪ የሚያስፈልገንን እንምረጥ ◈ያልሰማነውን ለመናገር ከምንቸኩል መስማትን እናዳብር ◈ፀሎታችን ሁሉ ይሰማል ሁሉም ግን ስኬትን አያገኝምና ለምን ብለን ከምንጮህ እግዚአብሔርን እንስማ ◈ያልተማረ ማስተማር ስለማይችል አስተማሪ ለመሆን ተማሪ እንሁን ◈በምድር ላይ የሚያጣን እንጂ የምናጣው ምንም ነገር የለምና ምንም ነገር ያጣን አይምሰለን ◈ሁሉንም ነገር በቅርበት ለማየት እንሞክር። ➱እርግጠኛ ነኝ እንዲ ካደረግን በትክክለኛው መንገድ ወደ ትክክለኛው ቦታ እንደርሳለን አምላካችን አግዚአብሔር ይረዳናል ✞✞ ◄●●◦ @True_Gospel ◦●●►
Show all...
#የእግዚአብሔር ቃል ስለኛ "እናንተ የምድር ጨው ናችሁ" (ማቴ 5፥13) አዳም የተሰራው በጭቃ ነው መኖርያውም መጨረሻው ከጭቃ ጋር የተቆራኘ ነው ስለዚህ የአዳም ዋጋ ጭቃ ነው። ልክ እንደዚሁ ለአዳማዊ ህይወቱ ብቻ የሚኖር ሰው ከጭቃ የዘለለ ዋጋ አይኖረውም። ክርስቲያን በክርስቶስ ደም ተዋጅቷል ዋናው የክርስቶስ ደም ነው የተገዛበት ነውና። ለዚህ ዋጋው መኖር ያልቻለ ክርስቲያን ግን ራሱን ብቻ ሳይሆን የተገዛበትን ዋጋ እያረከሰ እንደሆነ ሊገባው ይገባል። ክርስቶስ "የምድር ጨው ናችሁ" ሲል ጨውነት ዋጋችን ሳይሆን ማንነታችን ብቻ ነው። በእርግጥ ጨው ርካሽ ነው ከመሬት ላይ ነው የሚታፈሰው ግን ለሰው ወሳኝ ነገር ነው። ጨው በራሱ ጣዕም የለውም ወይ ብቻውን ሊበላ የሚቻል ነገር አይደለም። ነገሮችን ግን ጣዕም ይሰጣቸዋል። ሰዎች ምግብ በራሱ ጣዕም ቢኖረው ጨውን አይፈልጉም ነበር። ነገር ግን ጨው ለሰው ልጆች የግድ ያስፈልጋቸዋል። ምክንያቱም በውስጡ "iodine" የሚባል ንጥረነገር አለ እሱም ለጤና እጅግ ጠቃሚ ነው። ፕሮቲንን ከስጋ ባናገኝ ከባቄላ እናገኛለን የሚል አማራጭ ይኖራል አይዲንን ለማግኘት ግን የግድ ጨውን ማግኘት ያስፈልጋል። ክርስቶስ "ጨው ናችሁ " ሲል በውስጣችን አዮዲን እንዳለብን እና ለሰዎች ጤንነት እጅግ አስፈላጊ መሆናችንንም ጭምር እየነገረን ነው። ጨው በምግብ ውስጥ ከበዛ ወይም ካነሰ ምግብ የመበላት ዕድሉ ይቀንሳል ስለዚህ በልክ እና በመጠን በምግብ ውስጥ መገኘት አለበት ክርስቲያንም በልክ ካልኖረ ብዙ ነገሮችን ሊያበላሽ ይችላል። ጨው መቀመጥ ያለበት ስፍራ አለ ድንገት ውሃ ውስጥ ቢገኝ ይሟሟና ከጥቅም ውጭ ይሆናል። ክርስቲያንም ከብዙ ነገሮች ተጠብቆ ጨውነቱን ጠብቆ ሊኖር ግድ ነው አለዚያ ከጥቅም ውጭ ሊሆን ይችላል። ✍ አገልጋይ ምናሴ #ተባርካችኋል #SHARE_SHARE_SHARE @TRUE_GOSPEL @CHRISTIANS_PROFILE
Show all...
በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ መቆየት ሉቃስ 10፥30 ላይ ያ ሰው ከ ኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴም ተደብድቦ ወደቀ ➥ ኢየሩሳሌም እግዚአብሔር የሚመለክበት ለእግዚአብሔር የሚሰገድበት ስፍራ ነው በዚያ የእግዚአብሔር ህልውና አለ ኢያሪኮ ከእግዚአብሔር ህልውና ውጭ ነው ከእግዚአብሔር ህልውና ውጭ ብዙ ሊደበድቡንና ሊያቆስሉን የሚችሉ ወንበዴዎች አሉ የእግዚአብሔር ህልውና የደህንነታችን #ዋስትና ነው ከህልውናው ውጭ ስንሆን ደህንነት አይሰማንም በህልውናው ውስጥ መቆየት መቻል አለብን ሩት ምዕራፍ 1 ላይ ሩት ከባሏና ከልጆቿጋ ወደ ሌላ ከተማ ለመሄድ ከእግዚአብሔር ህዝብ ምድር ወጣች እንጀራ አገኘች ግን የባሏንና የልጆቿን ህይወት ሊያቆይላት አልቻለም ረሀብ ቢኖርም ባይሞላና ባይሳካም በህልውናው ውስጥ መቆየት መቻል አለብን በህልውናው ውስጥ ከመቆየት በላይ በረከትና ስኬታ የትም አናገኝም በፖሊስ ተከበን ሊሰማን የማይችል ሰላም በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ አለ በመታከም የተመጣጠነ በመመገብ የማናገኘው ጤንነት በአባታችን ህልውና ውስጥ አለ ደህንነታችን ህልውናው ነው ከህልውናው ውጭ ብዙ ወደእኛ የተቀሰሩ ቀስቶች አሉ በደህንነት ለመቆየት በህልውናው ውስጥ መቆየት መቻል አለብን ✍ Mnasie #ተባርካችኋል #SHARE_SHARE_SHARE @CHRISTIANS_PROFILE
Show all...