cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

በአይነቱ ልዩ እና ኦርቶዶክሳዊ ለዛና አስተምህሮ የጠበቁ ቀደም ያሉ ዝማሬዎች እምያገኙብት እንዲሁም ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን እሚያገኙበት

Show more
Advertising posts
1 901Subscribers
No data24 hours
-27 days
-2230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

📢 : ጳጉሜ ማለት ምን ማለት ነው ? 📢 : የጳጉሜን ጾም ለምን እንጾማለን ? በ ኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ጳጉሜ የምትባልአምስት(ስድስት)ቀን አለች።ይቺ ጳጉሜን ወር እንዳንላት 25 ቀን ይጎላታል።ሳምንትም እንዳንላት 2 ቀን ያንሳታል። ለወርም ለሳምንትም አቅም የሚያንሳት ጳጉሜ በአመቱ መጨረሿ ላይ ትገኛለች። ጳጉሜ የሚለው ስያሜ '' ኤፓጉሜኔ ''ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጓሜው "ተጨማሪ" ማለት ነው። በመሆኑም ጳጉሜ የአመቱ ምራቂ ቀናት እንጂ ወር ወይም ሳምንት አትባልም። አውሮፓውያን በአመቱ ወራ ት ውስጥ በታትነዋታል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ሊቃው ንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የአመት ተጨማሪ በማድረግ የአመቱን ቀን 365 ወይም 366 ቀን ብለው ደምረውታል። ጳጉሜ በየአመቱ አምስት ወይም ስድስት ቀን ሆና የም ትመጣ ናት።በአራት አመት አንዴ ጳጉሜ ስድስት ሆና ት መጣለች በዚህም የአመቱ በዓላት ቀናትን ትቀይረዋለች ለምሳሌ የገና በዓል በአራት አመት አንዴ ታህሳስ 28 ቀን ሲውል ሌላውን ግን 29ኝን አይለቅም። በዚህም ኢ ትዮጵያ የ 13ወር ፀጋ ባለቤት እና ከአፍሪካም ከአለም ም ብቸኛ የሯሷ አቆጣጠር ያላት ሀገር ያደርጋታል። እስካሁን ሳይንስ ያልደረሰበት ነገርግን የቤተክርስቲያን ሊቃውንት በሚገባ የሚያውቁት ጳጉሜ በ 700 አመት አንዴ ሰባት ትሆናለች።ለዚህም ብቸኛዋ ማስረጃ ተዋህ ዶ ሐይማኖትና ስንዱዋ እመቤት ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት። የጳጉሜ ፆም(ፆመ ዮዲት) ይህች ፆም ከሁለቱ የፈቃድ ፆም አንዷ ናት አንዱ ፆመ ፅጌ ሲሆን ሁለተኛዋ ይህች የጳጉሜ ፆም ናት።በብዙ ሀን ዘንድ ባትታወቅም ታላቅ የበረከት እና እራስን የም ናድስባት ጾም ነች። የጰጉሜ ጾም ጾመ ዮዲት በመባልም ትታወቃለች ይህም ዮዲት እረሷ ስለፆመችው ነው። ዮዲት ስላችሁ የቤተክር ስቲያን አጥፊየሆነችው የዲት ጉዲት እንዳልሆነ አሰምሩ ልኝ። ታሪኩም እንዲህ ነው። የፋርስ ንጉስ ናቡከደነ ፆር በሰራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀ በልክ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለ ሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ መ ዮዲት 2:2-7። እርሱም እንደታዘዘው በሀይላቸው የሚመኩትን 12ሺ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡትን 12ሺ ጦረኞችን እየ መራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሄድ ከ አይሁድ ከተ ማ ደረሰ በዚያም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ል ጆች አለቀሱ። ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ እርቃ ንፅህናዋን ጠብቃ በፆም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች።በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራሷ ላይ ትቢያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች።የፍጥረ ቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር ህዝቡን የሚያድንበት ን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሶስተኛው ቀን መለሰላት ዮዲ 8 :2 ከዚህም በሁዋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤልያዊያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋ ቸዋል። ዮዲት ጠላቷን ማጥፋት የቻለችው በፆም እና በፀሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ሀይልን አግኝታ ነው። ጳጉሜ የአመቱ መገባደጃና መሸጋገሪያ እንመሆኗ መጠን እጅግ ድንቅ ቀናት ናት።ይህች ወር የዳግም ም ፃት መታሰቢያ ናት,የዘመነ ፍዳ መገባደጃ ከ ቁር ብርዱ መላቀቂያ በመሆኗ ብዙ እና አያሌ ጥቅም አላት። ስለዚህ ምዕመና በየ አመቱ ጳጉሜን የቻለ በመፆም በ በመፀለይ መጪውን አመት የተሻለ እንዲሆን እራስን በ ማዘጋጀት ፀበል በመጠመቅ በልዩ ዝግጅት ያሳልፋሉ። አሜን
Show all...
ወቅቱን በደንብ የሚገልፅ ስዕል፤ ይህ ስዕል ከተቻለ በደንብ ተስሎ ለታሪክም ለትውልድም በየ ቤተክርስቲያናቱ መቀመጥ ያለበት የጥበብ ስራ ነው። እስኪ የገባው? በኮሜንት፤
Show all...
የአራቱ ኪሩቤልን ስም ቅዱስ ያሬድ እንዲህ ይላቸዋል ፩) ባራማራ ፪) እግረማጣ ፫) ሱርትዮን ፬) መሊጦን ይላቸዋል። ሃይማኖተ አበው ላይ ስለዚህ ኪሩቤል ሲናገር መናብርት ነባብያን ይላቸዋል። የሚናገሩ መናብርት ይላቸዋል። ከሱራፌል ነገድና ከኪሩቤል ነገድ ሁለት ሁለት ተመርጠው በጠቅላላው አራት ኪሩቤል አሉ። እንደገና በኢዮር ከሚገኙት አርባ ነገዶች አሥሩ ነገድ ኪሩቤል ይባላል። ሰአሉ ለነ ኀበ እግዚአብሔር ጸባዖት___ቅ. ያሬድ (ኪሩቤል ሆይ ወደአሸናፊ እግዚአብሔር ለምኑልን)
Show all...
ከጲላጦስ ወደ ሔሮድስ ፥ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ ፥ ከሔሮድስ ወደ ቀያፋ አመላለሱት፨ ሥርዓቱን ፥ ቀኖናውን ፥ ዶግማውን የሚያውቁትም የማያውቁትም ጮኾበት፥ በሩን ዘጉበት ፨ በየጊዜው የሚፈስሰው የአረጋዊ አባት ዕንባ ምን ያመጣ ይኹን? ብጹዕ አባታችን በረከትዎ ትድረሰን፨
Show all...
ከጲላጦስ ወደ ሔሮድስ ፥ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ ፥ ከሔሮድስ ወደ ቀያፋ አመላለሱት፨ ሥርዓቱን ፥ ቀኖናውን ፥ ዶግማውን የሚያውቁትም የማያውቁትም ጮኾበት፥ በሩን ዘጉበት ፨ በየጊዜው የሚፈስሰው የአረጋዊ አባት ዕንባ ምን ያመጣ ይኹን? ብጹዕ አባታችን በረከትዎ ትድረሰን፨
Show all...
👉👉የቅዱስ አባታችን ጉዞ (ሁሉም ያየው ሀቅ ) በህገ ቤተክርስቲያን እንኳን ፓትርያርክ? አንድ ሊቀጳጳስ ሲመጣ ቄሰገበዙ የቤተመቅደሱን በር ይከፍታል ሊቀጳጳሱ ገብቶ ቅዱስ ብሎ ጸሎት አድርጎ ባርኮ ተከትለው የመጡትን አባታዊ ምክር ሰጥቶ ያሰናብታል ❓ዛሬ ግን ያየነው ይህን አይደለም በየትኛውም ቦታ በስርዓት በህግ በምንም ቤተክርስቲያን አሐቲ ናት የእነገሌ የምትባል ቤተክርስቲያን የለችም አሁን ግን በአንዳንድ ግለሰቦች የእኛ የእነሱ የሚል ነገር ሲያነሱ ይሰማሉ ይህ ትክክል አይደለም እንኳን በአንድ ሲኖዶስ ስር ያለች ቤተክርስቲያን በባለፈው ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የቀኖና ጥሰት ተፈጸመ ሲባል የግብጽ ሲኖዶስ መግለጫ አውጥቷል የህንድ ሲኖዶስ ትክክል አይደለም እኛ ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ይህን አንጠብቅም ወደነበራችሁበት ክብር ተመለሱ በማለት መግለጫ አውጥቷል ጉዳዩን ተቃውመዋል ይህ የሚያሳየው ቤተክርስቲያን አሐቲ መሆንዋን ነው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የምትገለገለው የግብጽ እና የግሪክ የእስክንድር ሊቃነ ጳጳሳት ባወጡት ህግ በሰሩት ስርዓት ነው የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጳጳሳት ካልሆኑ አልፈልግም አላለችም ሃይማኖተ አበው የእነሱ ነው ቅዳሴው የእነሱ ነው ቀኖናው ዶክማው የእነሱ ነው ስርዓተ ምንኩስናው የእነሱ ነው ይህን ተቀብላ የምትገለገለው በቤተክርስቲያን የእኛ የእነሱ የሚባል ስሌለለ ነው ❓እንዲያውም እንናገር ካልንማ ግብጻዊው ሊቀጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስን አባቴ ትላለች ዮሐንስ አፈወርቅ አባቴ ቅዱስ አትናቴዎስ አባቴ ትላለች ከዚህ በላይ ምን ትምህርት አለ 👉👉ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ የበለጠ በሊቃውንቶችዋ በቅዱስ ያሬድ ዜማ አብባ አሸብርቃ በዓለም ከፍ ብላ ትታያለች ተብሎ ሲጠበቅ እየሆነ ያለው ተቃራኒ ነው ❓ሊቃነ ጳጳሳትን በጎጥ መሾም ጀምራለች ወዘተ ሌላም ሌላም ሐምሌ ሁለት ቀን ቅዱስ አባታችን ለተፈጠረው ክፍተት ሽማግሌ አልክም እራሴ መሄድ አለብኝ ብለው ሊቃነጳጳሳት አስከትለው ልጆቻቸውን ለመባረክ ይቅርታ ለመጠየቅ መሄዳቸው ይታወቃል አሁን በፎቶ አስደግፌ የላኩላችሁ ፎቶ ላይ እንደምናየው ከኤርፖርት ጀምሮ የክፍሉ ጳጳሳት አልነበሩም ካህናት አልተገኙም ሲቀጥል አካባቢው ወደአለው ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ዝግ ነው እንደማንኛውም በውጭ ተሳልመው ፓትርያርኩ ሲመለሱ አየን ይህ ትልቅ ስህተት ነው ከዚህ በላይ ስህተት የለም ❓በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የነውር ነውር ነው በፓትርያርኩ ላይ በርዋን የዘጋጅ ቤተክርስቲያን ለማን እንደምትከፈት አላውቅም በመግቢያዬ ላይ እንደተናገርኩት በትግራይ ያሉ አቢያተ ክርስቲያናት ችግር ደርሶባቸዋል አወ በሚገባ ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው ነገር ግን ይህ ችግር በትግራይ ብቻ ያቆመ አይደለም ወደ ወሎ ሂዱ የወደሙ አቢያተ ክርስቲያናት በአቡነ ኤርምያስ በዝርዝር ተነግሯል በሺዎች የሚቆጠሩ አቢያተ ክርስቲያናት ወድመዋል ጎንደርም እንደዚያም ባይሆን በተመሳሳይ ነገር ግን የትኛውን ሲኖዶስ አኮረፉ በየትኛው ጳጳስ ላይ በር ዘጉ ለቤተክርስቲያን ከሲኖዶስ ከፓትርያርኩ በላይ እኔን ይመለከተኛል ማለት ጉም መጨበጥ አይሆንም ወይ እንደማይመለከተን እያየን እየሰማን ዝም ያልናቸው ብዙ ነገሮች አሉ በሲኖዶስ አድርጎ ስርዓቱን ጠብቆ ይምጣ ብለን ዝም ያልናቸው ብዙ ናቸው እረ ስንቱ ❓❓❓❓❓ አሁንም በእውነት እግዚአብሔር ያስተካክለን 🙏🙏🙏
Show all...
ሰንበተ ክርስቲያን " ወዮ ይህች ዕለት አብ የቀደሳት ወልደ የባረካት መንፈስ ቅዱስ ከፍ ከፍ ያደረጋት ናት፡፡ በርሷ ደስ ይበለን፡፡ በርስዋም ኀሤት እናደርጋግ ትከብሩባት ዘንድ አክብሯት ዘመን ወር ለመባል በርሷ የታወቃችሁ ሌሎች ዕለታት ሆይ የበዓላትን በኩር ኑ አመስግኗት ይህችውም የከበረች ሰንበተ ክርስቲያን ናት፡፡ "      ቅዳሴ አትናቴዎስ             https://t.me/mzmur_ortodox  
Show all...
ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

በአይነቱ ልዩ እና ኦርቶዶክሳዊ ለዛና አስተምህሮ የጠበቁ ቀደም ያሉ ዝማሬዎች እምያገኙብት እንዲሁም ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን እሚያገኙበት

‹‹ወይእዜኒ አንትሙ ከመዝ ግበሩ፤ ከእንግዲህ እናንተም እንዲሁ አድርጉ›› (መጽሐፈ ስንክሳር) የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕንጸተ ቤታ እና ቅዳሴ ቤታ የሚዘከርባቸው ሰኔ ሃያ እና ሃያ አንድ ቀን የከበሩ በዓላት ናቸው፡፡ እመቤታችን ባረገች በአራኛው ዓመት ጳውሎስና በርናባስ በፊልጵስዩስ ወንጌልን እያስተማሩ ነበር፡፡ ሕዝቡም አምነው ተጠመቁ፤ ነገር ግን ከእንግዲህ ጣዖት እንዳያመልኩና ወደ ጣዖት ቤትም እንዳይሄዱ ቢከለክሏቸው ‹‹የለመድነውን ከከለከላችሁንማ መካነ ጸሎት ስጡን›› ብለው አስገደዷቸው፡፡ ይህንንም ለመንገር ወደ ቅዱስ ጴጥሮስና ዮሐንስ ‹‹አልቦ ዘትገብሩ ወኢምንተኒ ዘእንበለ ትእዛዙ ወምክሩ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ያለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባም፤ እናንተም ጸልዩ፤ እኛም እንጸልያለን›› ብለው መልእክት ላኩባቸው፡፡ ሱባኤያቸውንም ሲጨርሱ ክብር ይግባውና ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ (ስንክሳሩ በሀገረ ቂሳርያ ዘኬልቄዶን ይላል መዝገበ ታሪክ ደግሞ በፊልጵስዩስ ይላል) ሰበሰባቸው፡፡ ዮሐንስ ‹‹ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን?›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹በእናቴ ስም ጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፋቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላሳያችሁና ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው›› አለው፡፡ ይህንን ብሎ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው፤ ተራርቀው የነበሩ ሦስት ደንጊያዎች ነበሩ፤ በገቢረ ተአምራቱም አቀራርቦ ቁመቱንና ወርዱን መጥኖ ሰጣቸው፡፡ እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ /እየተሳቡ/ ቁመቱን ፳፬ ወርዱን ፲፪ ክንድ አድርገው ሠርተውታል፡፡ ‹‹ወአዕባንኒ ይለመልሙ በእዴሆሙ፤ ደንጊያዎችም በእጆቻቸው ይለመልሙ ነበር›› እንዲል፤ ከዚያም ‹‹ወይእዜኒ አንትሙ ከመዝ ግበሩ፤ ከእንግዲህ እናንተም እንዲሁ አድርጉ›› ብሏቸው ዐርጓል፤ ይህ የሆነው ሰኔ ፳ ቀን በ፶፫ ዓመተ ምሕረት ነው፡፡ በማግሥቱ ሰኔ ፳፩ ቀንም ጌታ እመቤታችንን ታቦት፣ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡ ዳግመኛም እጁን ጭኖ ቅዱስ ጴጥሮስን ፓትርያሪክ አድርጎ የሾመውም በዚህች ዕለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜም የሰማይ መላእክትና የምድር ሰዎች (ሐዋርያት) አንድ ሆነው አመስግነዋል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር! https://t.me/mzmur_ortodox
Show all...
ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

በአይነቱ ልዩ እና ኦርቶዶክሳዊ ለዛና አስተምህሮ የጠበቁ ቀደም ያሉ ዝማሬዎች እምያገኙብት እንዲሁም ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን እሚያገኙበት