cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Salale University students

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
5 129Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በኦሮሚያ ክልል የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ጥቅምት 16 ትምህርት ይጀምራሉ! የኦሮሚያ ክልል የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ በሰጡት መግለጫ በክልሉ ከጥቅምት 16 ጀምሮ ተማሪዎች በሦስት ዙር ተከፍለው ትምህርት እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል፡፡ በዚህም ፦ ዙር 1 - ጥቅምት 16 የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩ ይሆናል፣ ዙር 2 - ጥቅምት 30/2013 ዓ/ም የዞን በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩ ይሆናል። ዙር 3 - ልዩ ዞኖች እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞች ትምህርት ይጀምራሉ። በኦሮሚያ ክልል ከ33 ሺ በላይ አዳዲስ መማሪያ ክፍሎች መገንባታቸውን ያስታወሱት አቶ አዲሱ አረጋ በዚህ ዓመት ከ11.5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር መታቀዱን ገልጸዋል፡፡ (OBN) @selaleuniversity @selaleuniverity
Show all...
Salele university የመወያያ group ስለተከፈተ ይሄን Link በመንካት @selaleuniversit @Selaleuniversit ገብታችሁ መወያየት ትችላላችሁ Add አድርጉበት የግቢውን ተማሪዎችን በሙሉ
Show all...
" የ2013 የትምህርት ዘመንን ታሳቢ ያደረገ የኮርስ ክለሳ እየተደረገ ነው " ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር እያደረገው ባለው ውይይት የቀጣይ አመት ላይ የኮርስ ክለሳ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ትምህርት ሚኒስቴር በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን ትምህርት ለማስጀመር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ፡፡ የ2013 ትምህርት ዘመን ትምህርት የሚሰጥበት ጊዜ አጭር ስለሆነ ተማሪዎች መማር የሚገባቸውን ታሳቢ ያደረገ የኮርስ ክለሳ እየተሰራ ሲሆን በአጭር ጊዜም ወደ ክልሎች ይላካል ተብሏል፡፡ ትምህርት ቤቶች ትምህርት ሲጀምሩ የ2013 ትምህርት ምዕራፍን ከመጀመራቸው በፊት በ2012 የትምህርት ዘመን ያልተሸፈኑ ዋና ዋና ጉዳዮች በመከለስ እንደሚሆን ተገልጿል ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ በመከላከል ትምህርት መጀመር እንዲችሉ የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት የሚያረጋግጥ አደረጃጀቶችን ፈጥሮ እየሰራ ይገኛል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶችን በ3 ዙር ዳግም ለመክፈት የሚያስችል ምክረ ሃሳብ ማቅረቡ ይታወቃል ።
Show all...
Salele university የመወያያ group ስለተከፈተ ይሄን Link በመንካት @selaleuniversit @Selaleuniversit ገብታችሁ መወያየት ትችላላችሁ Add አድርጉበት የግቢውን ተማሪዎችን በሙሉ
Show all...
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመስቀል በአል አደረሳችሁ❗️ ✝🔥መልካም በአል🔥✝ 🦁• @Selaleuniversity •🦁
Show all...
#UPDATE የከፍተኛ ትምህርት ማስቀጠያ ቅድመዝግጅት እና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በጅማ ዩኒቨርስቲ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በመድረኩ በያዝነዉ አመት ትምህርት ለማስቀጠል እንደ ቅድመ-ሁኔታ የቀረቡ ሃሳቦች በዉይይት እና በግምገማ ተደርጎባቸው በመድረኩ ሃሳብ ተሰጥቶባቸዉ እንደሚፀድቁ ይጠበቃል። በዚህም:- - በክፍል ዉስጥ የተማሪዎችን ቁጥር ከ25 እስከ 30 ማድረግ - የመማሪያ ክፍሎች ከዚህ ቀደም ከሚይዙት የተማሪ ብዛት በግማሽ መቀነስ - በአንድ መኝታ ክፍል ከ4 ያልበለጡ ተማሪዎችን መመደብ - የመማር ማስተማር ሂደቱን በክፍል ዉስጥ ዉስን ግዜ አድርጎ ተማሪዎች አብዛኛዉን ግዜ በመኝታ ክፍላቸዉ እና በቤተ-መፅሐፍት እንዲያደርጉ ማመቻቸት - የአንድ ክፍለ ግዜ ርዝመት እስከ 35 ደቂቃ እንዲሆን ማድረግ - ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲረጋገጥ ከፌደራል እስከ ክልሎች እና ዞኖች ድረስ ካለዉ መዋቅር ጋር በቅንጅት መስራት እንደሀሳብ ቀርበዋል። (MoSHE - Dr Mulu Nega) @selaleuniversit
Show all...
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን መቀበል ከመጀመራቸው አስቀድሞ የተቋማቱ ዝግጁነት እንደሚረጋገጥ ተገልጿል! የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመክፈት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ በጅማ ዩኒቨርስቲ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተከታዩን ብለዋል፦ - ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መች ይከፈቱ  የሚለው ትክክለኛ መልስ እያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ በWHO መለኪያ መስፈርት መሰረት ደረጃውን ጠብቆ በተዘጋጀ ዝርዝር በጥልቀት የዝግጅት መጠኑ ተፈትሾ ዝግጁ ሲሆን ብቻ ነው። በዚያ መሰረት የተቋማት ዝግጅት ይፈተሻል። በዳሰሳውም መሰረት መቀበል እንደሚችሉ ፍቃድ ይሰጣል። - ቅድሚያ ለተመራቂዎች በመስጠት ተማሪዎችን በመከፋፈል በትንሽ ቁጥር ይጀመራል፡፡ ይህም ከሚታዩ ነገሮች ትምህርት እየተወሰደ የተማሪ ቁጥር ለመጨመር እድል ይሰጣል። ዝርዝር አፈጻጸሙ በምን እንደሚመራ ከጤና ሚኒስቴር  ጋር በመሆን ፕሮቶኮል ይዘጋጃል። - የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በማጓጓዝ ሂደት ውስጥ ችግር እንዳያጋጥም ከትራንስፖርት ሚኒስቴርና ጤና ሚኒስቴር  ጋር በትብብር ይሰራበታል። - ዩኒቨርስቲዎች ከአሁኑ ተማሪዎች መልሶ ለመቀበል የሚያስችል እቅድ አዘጋጅተው ከአስተዳደር ሰራተኞች እና መምህራን ጋር በመወያየት የጋራ ሊያደርጉ ይገባል። - አንድ ብሎክ ወይም አንድ ካምፓስ ኮቪድ-19 ቢያጋጥም ምን ይደረጋል ከሚለው ጀምሮ በዝርዝር መስራት እና እያንዳንዱ እቅድ ያለተማሪዎች እገዛ ተፈፃሚ ስለማይሆን ወደተማሪዎች ለማስረፅ መስራት የግድ ይላል። - የመከላከያ ቁሳቁሶችን አስመልክቶ ደግሞ የትኞቹ በዩኒቨርስቲዎች ይቅረቡ የትኞቹ በተማሪዎች ይሟሉ የሚለውን ከተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ተለይቶ መወሰን አስፈላጊ ነው። (MoSHE-Dr Samuel Kifle) @Selaleuniversity
Show all...
💥ሁለተኛ ሴሚስተር ያልጀመሩ ተማሪዎችን በሁለት ወር፣ የሴሚስተሩን 25 በመቶ የተማሩትን ደግሞ በ45 ቀናት ማካካሻ ለማስጨረስም ታሳቢ ተደርጓል። እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ ነባር ተማሪዎችን በሶስት መርሃ ግብር፤ ተመራቂ ተማሪዎችን ደግሞ እስከ ሁለት ወር ለማሰጨረስ ነው የታሰበው። ተመራቂ ያልሆኑ ነባር ተማሪዎች ጉዳይ እየታየ የሚቀጥል ሲሆን ትምህርት ማስቀጠያው ከጥቅምት እንዲጀምርም ታስቧል። በአንድ ክፍል ውስጥ ከ25 እስከ 30 ተማሪዎችን ለማስተማር ታቅዷል፤ ሌሎች መማሪያ ክፍሎች ደግሞ የመያዝ አቅማቸውን ግማሽ ብቻ እንዲይዙ ይደረጋል። @Selaleuniversity @Selaleuniversity
Show all...
💥በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ጉባኤ በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው። በጉባኤው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2012 የስራ ዘመን ኮሮናን ለመከላከል ያከናወኗቸው አበይት ተግባራትና ያስገኙት ውጤት ይገመገማል። ትናንት በተጀመረው በዚሁ ጉባኤ የዘንድሮ ትምህርት በሚጀመርበት ሁኔታ ላይ ጉባኤው እንደሚመክርና መረሃ ግብሩ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል። 📌በቆይታቸው ከዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር በጋራና በጥልቀት በመወያየት ዩኒቨርስቲዎችን መልሶ መክፈት ላይ ስምምነት እንደሚደርሱ ተገልጿል፡፡ @selaleuniversity @Selaleuniversity
Show all...
Salele university የመወያያ group ስለተከፈተ ይሄን Link በመንካት @selaleuniversit @Selaleuniversit ገብታችሁ መወያየት ትችላላችሁ Add አድርጉበት የግቢውን ተማሪዎችን በሙሉ
Show all...