cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ማህበረ ቅ/እስጢፋኖስ ዘአረካ

@estifanos_areka ይህ ማህበር መቀመጫውን በአረካ የታላቁ ገዳምና የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ያደረገ የዲያቆናት ማህበር ሲሆን አላማውም ሐይማኖታቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁና የሚያሳውቁ ዲያቆናትን እና ምዕመናንን ማፍራት ነው @estifanos_areka

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
399Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼  ሥርዓተ ማኅሌት ዘዓውደ ዓመት 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼          🌻 ፨ስቡዕ_ከተባለ_በኃላ 🌻          🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 @ermiasyeabolje @ermiasyeabolje      መልክዐ ሥላሴ፦ ሰላም ለገበዋቲክሙ እለ ዕሩቃን እምልብሰ ወርቅ፤ ሥሉስ ቅዱስ ሥርግዋነ መፍርህ መብረቅ፤ መንገለ(ኀበ) ፍኖቱ ምጽዋት ለቆርነሌዎስ ጻድቅ፤ ይምርሐኒ ወንጌልክሙ እግዚአ ፍኖት ረቂቅ፤ ዘጸያሔሁ ዮሐንስ መጥምቅ      ዚቅ፦ ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ፤ እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ።       ዓዲ፦ ወንጌል ቅዱስ ዘሰበከ ዮሐንስ፤ ቃለ ወልደ እግዚአብሔር።      ዘጣዕሙ፦ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።       ዚቅ፦ ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም መሠረተ ጽድቅ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ወአዘዘ ደመና በላዕሉ።      ነግሥ፦ ምስለ ራጉኤል ስዑል በነበልባል ወዮሐንስ ድንግል፤ ወበርተሎሜዎስ ሐዋርያ ሰባኬ ወንጌል፤ ወኢዮብ ዓዲ ተወካፌ ቊስል፤ ዓውደ ዓመት ለባርኮ እምጽርሐ አርያም ጌልጌል፤ ማርያም ንዒ ለምሕረት ወሣህል።      ወረብ፦ ዓውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዓውደ ዓመት/፪/ ንዒ ማርያም ለምሕረት ወሣህል/፪/      ዚቅ፦ ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ዮሐንስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ።      ዓዲ፦ በምድረ ጽዮን ኢይኩን ሐከክ፤ ወበገራኅታ ኢይብቊል ሦክ፤ ጸሊ ኀበ አምላክ ራጉኤል መልአከ፤ ዓውደ ዓመት ከመ ይትባረክ።      መልክዐ ዮሐንስ፦ በስመ እግዚአብሔር እሳት በሐቅለ ኅሊና ነዳዲ፤ ወበስመ ማርያም ድንግል መጥበቢተ ዓለም አባዲ፤ ማኅቶተ ጸዳል ዮሐንስ ጽልመተ አበሳ ሰዳዲ፤ ከመ እዜኑ ኂሩተከ እደ ኃጣውእየ ይፍዲ፤ በአየረ ሰማይ ይጸርሕ ቃልከ ዓዋዲ።      ዚቅ፦ እገኒ ለከ እግዚኦ በኲሉ ልብየ፤ ወእዜኑ ኂሩተ ዚአከ፤ እትፌሣሕ ወእትሐሠይ በአድኅኖትከ።     ወረብ፦ እገኒ ለከ እግዚኦ በኲሉ ልብየ/፪/ እትፌሣሕ ወእትሐሠይ በአድኅኖትከ/፪/      ዓዲ፦ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ማኅቶተ ጥበብ ውስተ አልባቢነ አኅቱ፤ ኀበ አዘዝከነ ኑፈር ወንዕቱ።       መልክዐ ዮሐንስ፦ ሰላም ለሥዕረተ ርእስከ እንተ ደለዎ እኳቴ፤ ወለርእስከ ሰላም ዘተመትረ ከመ ናቡቴ፤ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ፤ መብልዕ ዜና ፍቅርከ ወነገረ ጽድቅከ ስቴ፤ ያስተፌሥሕ መላእክተ ወሰብአ መዋቴ።      ወረብ፦ "ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ"/፪/ ወላዴ መጥቅዕ/፪/ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ ወላዴ መጥቅዕ/፪/      ዚቅ፦ ውስተ ርእሰ ዓውደ ዓመት ተጽሕፈ ተዝካርከ፤ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ።     መልክዐ ዮሐንስ፦ ሰላም ለአዕይንቲከ እለ ሠኑየ ይትኌለቁ፤ ወለአእዛኒከ ሰላም እለ ይትላጸቁ፤ ዮሐንስ ከማከ ሶበ ፈተዉ ወጽሕቁ፤ እሳተ ነዳዴ ኢተክህሎሙ ያጥምቁ፤ ራጉኤል በትጋሁ ወኢዮብ በጽድቁ።     ወረብ፦ "እሳተ ነዳዴ" ኢተክህሎሙ ያጥምቁ/፪/ ዮሐንስ ከማከ ሶበ ፈተዉ ወጽሕቁ/፪/      ዚቅ፦ ሰላማዊ ብእሲሁ፤ ቅዱሳት እደዊሁ  እለ አጥመቃሁ፤ ለመድኃኔዓለም።     መልክዐ ዮሐንስ፦ ሰላም ለአማዑቲከ እግዚአብሔር ዘገብሮ፤ ወለንዋየ ውስጥከ ሰላም መንጦላዕተ ሥጋከ እንተ ሰወሮ፤ ዮሐንስ ልብው መዝገበ ጥበብ ወአእምሮ፤ እፎ ኢያጽራከ ለሀቅለ ገዳማት ፃዕሮ፤ ፍጹመ መኒነከ አብያተ ዘውቅሮ።      ወረብ፦ "አብያተ ዘውቅሮ"/፪/ መኒነከ/፪/ ፍጹመ መኒነከ ዮሐንስ ልብው/፪/      ዚቅ፦ አብያተ ዘውቅሮ መኒነከ፤ በተዘከሮ ማኅደር ዘበሰማያት፤ ፀጒረ ገመል ረሰይከ ዓራዘከ።      መልክዐ ዮሐንስ፦ አምኃ ስብሐት አቅረብኩ ለመልክዕከ በጽዋዔ፤ እንዘ አስተዋድድ ቃለ መጠነ ራብዕ ሱባኤ፤ ተወክፈኒ ዮሐንስ ምስለ በርተሎሜዎስ ቀርነ ጉባኤ፤ ከመ ተወክፈ እግዚእከ ቅድመ ወንጌላዊት ትንሣኤ፤ እምደ አሐቲ ብእሲት ጸራይቀ ክልዔ።     ዚቅ፦ ዮሐንስ እዴከ መጥወኒ፤ ወበርተሎሜዎስ አቡየ ለባርኮ ቅረበኒ።     ወረብ፦ ዮሐንስ እዴከ መጥወኒ/፪/ ወበርተሎሜዎስ አቡየ ለባርኮ ቅረበኒ/፪/     አንገርጋሪ፦ ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ፤ ዓርኩ ለመርዓዊ ትሰመይ፤ ወአዝማዱ በሥጋ ትሰመይ፤ ተፈኖከ ታርኁ አናቅጸ ጽድቅ።      አመላለስ፦ ተፈኖከ ታርኁ/፪/ ታርኁ አናቅጸ ጽድቅ/፬/     ወረብ፦ ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ ነቢየ ልዑል/፪/ ዓርኩ ለመርዓዊ ትሰመይ ነቢየ ልዑል/፪/ እስመ ለዓለም ዘሰንበት ዘመጠነዝ ጸጋ ወጽድቅ ዘተውህበ በገዳም፤ላዕለ ዮሐንስ ካህን ወነብይ፤ ከመ ያጥምቆ በፈለገ ዮርዳኖስ ለዘቀደሳ ለሰንበት፤በከመ ሥምረቱ ንብረቱ ገዳም፤ ማ፦ሑረቱ አዳም፤ ውስተ ሐቋሁ ቅናቱ ዘዓዲም      🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼     🌼መዝሙር ዘዮሐንስ🌼     🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 (በ፭/ን) ዮሐንስ አኅድዓ እምካልአኒሁ አንሐ ወክሐ እንዘ ይብል እምላዕሉ ወረደ ቃለ አብ ወተሐውከ ማየ ዮርዳኖስ እምግርማ መለኮት ወደንገጹ ኵሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር ከማሁ ኮነ በቢታንያ በቤተ ራማ በማዕዶተ ዮርዳኖስ ወሶበ ርእዮ ዮሐንስ ለኢየሱስ ከልሐ ወይቤ ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ይቤሎ ኢየሱስ ለዮሐንስ አጥምቀኒ በማይ ከመ ይትቀደስ ማይ በማዕተበ ሰማይ አጥመቆ ዮሐንስ ለኢየሱስ በፈለገ ዮርዳኖስ እምድኅረ አጥመቀ ለሊሁ ተጠምቀ ምህሮሙ ለሕዝብ ወይቤሎሙ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ።
Show all...
#ደብረ_ዘይት (የዐቢይ ጾም አምሥተኛ ሳምንት) ደብረ ዘይት የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም መምጣት የምናስብበት፣ የመምጫው ምልክት የሆኑትን ነገሮች እየመረመርን ራሳችንን በንስሐ ሕይወት የምናዘጋጅበትና ከዘላለም ፍርድ ኩነኔ ለመዳን እንደ ቃሉ መመላለስ እንዳለብን የምናስብበት ነው። ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁም ተብለናልና ሁልጊዜ ዝግጁና ስንዱ ሆነን እንደቃሉ ለመኖር እስከ መጨረሻው ጸንተን ለመዳን እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ) እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወስ ኲሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኲሎሙ ኃጥአነ ምድር፡፡ ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ ወበ አዕላፍ መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን ዘእም ኀበ እግዚአብሔር ይምሐረነ አብ በይእቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት እስመ ገባሬ ሕይወት ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት፡፡ ትርጉም:- ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ ተዘጋጅታችሁም ኑሩ፤ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እስከ መጨረሻው የጸና እርሱ ይድናል፡፡የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ የሰማያትና የምድር ኃይላት ሁሉ ይናወጣሉ። ያን ጊዜ በምድር ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለቅሳሉ አላቸው፡፡ ጌታችንም ከባሕርይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ በመለከት ድምፅ ከአእላፍ መላእክት ጋር በግርማ መለኮቱ ከሰማይ ወደ ምድር ይወርደል፡፡ #የዕለቱ_ምንባባት 1ኛተሰ.4÷13-ፍጻ፡- ወንድሞቻችን ሆይ÷ ስለ ሞቱ ሰዎች÷ ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ልታውቁ እንወዳለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ እንደ ተነሣ ካመንን እንዲሁ እግዚአብሔር ሙታንን በኢየሱስ ያስነሣቸዋል ከእርሱም ጋር ያመጣቸዋል፡፡ 2ኛ ጴጥ.3÷7-14፡- አሁንም ሰማይና ምድር በዚያ ቃል ለእሳት ተዘጋጅተዋል፤ ኃጥኣን ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀንም ተጠብቀዋል፡፡ነገር ግን ወንድሞቻችን ሆይ÷ ይህን አትርሱ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ አንዲት ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት÷ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን ነውና፡፡ ሐዋ. 24÷1-21፡- በአምስተኛውም ቀን ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከመምህራኑና ጠርጠሉስ ከሚባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳውሎስንም በአገረ ገዢው ዘንድ ከሰሱት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ) #የዕለቱ_ምስባክ መዝ. 49÷2 እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ፡፡ ትርጉም፦ እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፡፡ አምላካችንም ዝም እይልም፤ እሳት በፊቱ ይነድዳል በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ፡፡ #የዕለቱ_ወንጌል ማቴ. 24÷1-25፡- ጌታችን ኢየሱስም ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው የቤተ መቅደሱን የሕንጻ አሠራር አሳዩት፡፡ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፤ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፡፡” (ተጨማሪ ያንብቡ) #የዕለቱ_ቅዳሴ፦ ቅዳሴ አትናቴዎስ
Show all...
#መጻጉዕ #የአብይ_ጾም_፬ተኛ_ሳምንት መጻጉ በዮሐንስ ወንጌል፭ ላይ ታሪኩ የተጻፈው ለ፴፰አመት አልጋ ላይ ተኝቶ የኖረ በቤተ ሳይዳ/በቤተ ዛታ ስፍራ ይዞ የመልአኩ መምጣት የውሃው መባረክ የውሃው መናወጥ እና ድህነቱን በተስፋ የሚጠብቅ ግን ድህነቱ በሳምንት አንዴ እርሱም አንድ ሰው ብቻ ስለሆነ ሚያገኘው ይህን እድል ማግኘት ያቃተው ተሸክሞ ወደ ውሃው የሚያደርሰው በተባረከ ጊዜ እንዲድን የሚያግዘው ሰው አልባ ህመምተኛ ነው። ጌታችንም ወደ ቤተ ሳይዳ መጥቶ የልቡን ሃሳብ ያውቃልና ልትድን ትወዳለህን??? አለው ጌታችን መጻጉ የሚፈልገው ጠፍቶት ሳይሆን መሉ ሰው ነህና መስክር ፍላጎትህ ከአንደበትህ ይውጣ በሚል ነው። ይህም ታማሚ እዛጋ ለብዙ ዘመን ያየው የነበረው በሰዎች ተረድተው ወደ ተቀደሰው ውሃ ገብተው ድነው ሲወጡ ነበርና ብቸኛ መሆኑን መዳን እየቻለ ግን ወደ ውሃው የሚያደርሰው ጎረምሳ ስለፈለገ ሰው የለኝም አለ. አንድም ጌታችን ገና የ፴ አመት ወጣት ነበርና ተሸክሞ ያደርሰኛል ወይም ከርሱ ጋር ብዙ ሰዎች ነበሩና ሰው ቢያዝልኝ በሚል ሰው የለኝም አለ። ብዙዎቻችን ዛሬ ዛሬ የመጻጉ ጥያቄ እናስተናግዳለን ሰው የለኝም የሚለው ብዙ ቦታ ሰጥተነዋል ግን ከሰው በላይ የሆነው የድንግል ልጅ ስላለልን ደስ ይበለን። ጌታችንም ለ፴፰ አመት አልጋህ አንተን ተሸክማለችና አሁን ተነስ አልጋህን ይዘህ ሂድ አባለ ያላሰበው ደስታ አደናግሮት ማን እንደ አዳነው እንኳአን ሳያውቅ ነበረ የተነዳው በዚም ገጠመኝ በሰንበት ስራ አይሰራም የሚሉ አይሁዶች ያዙትና እንዴት በሰንበት አልጋ ትሸከማለህ ብለው ያዙት ፴፰ አመት ሲተኛ ግን ማንም አልጠየቀውም ለዛም ነው ሰው ርቦታለንና ያዳነኝ እርሱ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው ማን ነው ያዳነህ?? ይህ ምላሽ እርሱ ባይመልስም ለነርሱ ግልጽ ነው በዛ ሰአት ከርሱ ከመድኃኒያለም ውጪ እንዲህ አይነት ተግባር የሚሰራ አነበረምና መጻጉ በውስጡ ዘወትር ማን ነው ያዳነኝ የሚለው ጥያቄ አንግቦ ጌታም በመቅደስ አግኝቶት ኃጥያትህ ተሰርዮልኻል ግን ዳግመኛ ከዚ በላይ እንዳያገኝህ ደግመህ አትበድል ሲለው ምስክር አይሉት ፈጥኖ ሄደና ለአይሁድ ያዳነኝ እርሱ ነው ብሎ ተናገረ ሕማማተ መስቀል ላይ አባቶቻችን የጌታ ፊት በጥፊ ጸፍቶታል ይልሉ ያለፋበት የኖሩበት የስቃይ ህይወት መርሳት ያዛይን ጀርባ መንከስ......... ከዚህ በላይ ኃጥያት እንዳታገኝህ???? ከ፴፰ አመት በላይ አልጋ ላይ የነበረው ከዚህ በላይ እንዳያገኝህ......?? ሲል ሲኦል እንዳትገባ ከዚ የከፋ ስቃይ እሳት እንዳያገኝህ ደግመህ አትበድል ሲል ነው። እኛ ስንቶቻችን ነን የእናት ጡት ነካሽ ዳግማዊ መጻጉ በቤቷ ኖረን የስጋችን ፈውስ ከፀበል ከእምነቱ ተደባብሰን ድነን.......ለነፍሳችን ንስኃ ከአባቶች አግኝተን ስጋውንም በልተን ደሙንም ቆርሰን ዛሬ ግን ከርሷ ርቀን በውሸት መስክረን ሁለተኛው ንጉስ ብርን ያነገስን ዳግማዊው መጻጉ ሆነን የተገኘን ዛሬ ካለው መከራ የባሰ የወደፊቱ የቆየው መከራ ሳያገኘን ሮጥ ብለን እንድናመልጥ አምላካችን ይርዳን። መጻጉን ብቻ አይደለም ጌታችን በመዋለ ስጋዌ ዘመን ያዳናቸው ድውያን ሁሉ የታወሳሉ እኛም የስጋ የነፍስ በሽታ አለብንና እርሱ ይታደገን ይፈውሰን አሜን። ድውይ ነኝ አንተ አድነኝ መጻጉን የፈወስክ በልዩ ስልጣንህ/2 የስጋ በሽታ (ባንተ እንደተረታ)/2 እኛም ተይዘናል በነፍስ በሽታ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
#እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡ መጋቢት ፭ በዓለ ዕረፍት ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ #share አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤ * እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤ * እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤ * ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤ * ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤ * በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤ * 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤ * ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ #ላሊበላ፥ ለአቡነ #ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ #አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ) ፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ፤ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ)  ምድረ ከብድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት፤ ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤ *ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡ *ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤ ፠ እንደገና ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ፣ #አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም_ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፡፡ ፠ እድሜያቸው ረዥም እንደመሆኑ፤ ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ላሊበላን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳን ወደ ርሳቸው እየመጡ በረከትን ተቀብለዋል፡፡ ፠#በግብፅ_300_ዓመታት_፥ #በኢትዮጵያ_ምድር_ላይ_262_ዓመታት (በዋነኛነት #በምድረ_ከብድና_በዝቋላ_ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን #ገዘዛ_አቦን_ መጥቀስ ይቻላል) ፠ በድምሩ 562 ዓመታት ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባት ምድረ ከብድ ገዳም ግን ራደች፥ ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከብድ/ ተብለሽ ተጠሪ አላት፤ የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡ ፠ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤ ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ገብረ ሕይወት፡፡ https://t.me/mezmuremahletzorthodox
Show all...
መዝሙረ ማህሌት ዘ ኦርቶዶክስ

https://t.me/mezmuremahletzorthodox