cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Www.መዘምር ድ/ን ባዘዘው ተስፋዬ.com

ድል አለ በስም ድል አለ በቃል ተራራው ይናቃል አማኑኤል ስል፡፡ ዘማር ድያቆን ባዘዘው ተስፋዬ channel ፡ Enem twulid negn bits it ilishalewu ende abatoche simshini anesalewu Phone + 0901613959 Asab kale commet kale bezi litxeyiqu tichilalachiu አምላክ ይባርካችው

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
220Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ጾመ_ፍልሰታ <ፍልሰታ > የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት ይነገራል። ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን መነሣቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙ ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዐዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው። #ሃይማኖታዊ_መሠረት እመቤታችን ከአባቷ ከኢያቄም እና ከናቷ ከሐና ነሐሴ ፯ ቀን ተፀንሳ ግንቦት ፩ ቀን በሊባኖስ ተወልዳለች። <እምሊባኖስ ትወጽዕ መርአት ፦ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች > እንደተባለ ። እመቤታችን በእናት አባቷ ቤት ሦስት ዓመት፤ በቤተ መቅደስ አሥራ ኹለት ዓመት፤ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ፡ ከዮሐንስ ወልደዘብዴዎስ ዘንድ አሥራ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወር ቆይታ በ ፷፬ ዓመት ዕድሜዋ በ፵፱ ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። የእመቤታችንን ስም የሚገልጹ የውዳሴ ጽሑፎችም በዕድሜዋ ልክ ተደርሰዋል። ለምሳሌ የውዳሴ ማርያም ቁጥር ፷፬ ነው፤ የመልክዐ ማርያም ቁጥርም ፷፬ ነው።[1] ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ተሰባስበው አስከሬኗን ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መቃብር ለማሳረፍ ሲሄዱ አይሁድ ለተንኮል አያርፉምና ተተናኮሏቸው። ቀድሞ ልጇ ሞቶ ተነሣ፣ ዐረገ እያሉ ሲያስቸግሩን ይኖራሉ: ደግሞ አሁን እሷም ተነሣች፣ ዐረገች ሊሉ አይደል በማለት አይሁድ ተሰባስበው አስከሬኗን ለማቃጠል ሲተናኮሉ እግዚአብሔር በተአምር ከነዚያ አይሁዶች አድኗቸዋል ። የእመቤታችንንም አስከሬን ነጥቆ ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አኑሮታል። ከዚያ በኋላ ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩት ዘንድ በዐረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ ፩ ጀምሮ እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ድረስ ኹለት ሱባዔ ይዘው በአሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና በምህላ በፍጹም ደስታ በጌቴሰማኔ አሳረፉት ። በሦስተኛውም ቀን ተነሥታ ስታርግ ከሰኡቃዊያን ወገን የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አያት። እርሱም በቀብር ሥርዓቱ ጊዜም አልነበረም። ሀገረ ስብከቱ ህንድ ስለነበር ሊያስተምር ወደዛው ሂዶ ነበርና። በዚያም ሲያስተምር ሰንብቶ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ያገኛታል። ትንሣኤዋን ከርሱ ሰውራ ያደረገች መስሎት አዝኖ «ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀርቼ ነውን ?» ብሎ ቢያዝንባት እመቤታችንም ከርሱ በቀር ማንም ትንሣኤዋን እንዳላየ ነግራ አጽናናችው። ለሌሎቹ ሐዋርያትም እንዲነግራቸው ለምልክትም /ለምስክርም እንዲሆነው ሰበኗን /መግነዟን ሰጥታው ዐረገች። ቶማስም ኢየሩሳሌም ደርሶ ሐዋርያትን «የእመቤታችን ነገርስ እንደምን ሆነ?» ሲል ቢጠይቅ «አግኝተን ቀበርናት እኮ» አሉት። እርሱ ምስጢሩን አዉቆ ደብቆ «ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር» እንዴት ይሆናል ? አይደረግም ይላቸዋል። ሊያሳያቸውም መቃብሩ ዘንድ ሂደው ቢከፍቱት አጧት። እርሱም «አታምኑኝም ብዬ እንጂ እርሷስ ተነሥታ ዐርጋለች» በማለት ኹኔታውን ተረከላቸውና ለምስክር ይሁንህ ብላ የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው። ከዚህ በኋላ ለበረከት ይሆናቸው ዘንድ ሰበኑን ተካፍለው ወደየአህጉረ ስብከታቸው ሄዱ። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ በሚይዘው የመጾር መስቀል ላይ በሁለት ቀዳዳዎች አልፎ ተጠምጥሞ የምናየው መቀነት መሰል ጨርቅ የዚያ ሰበን ምሳሌ ነው። በዓመቱ ሐዋርያት ከያሉበት ተሰባስበው ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ እኛስ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምርው ሱባዔ ቢይዙ ከኹለት ሱባዔ በኋላ እንደገና ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ለማየት በቅተዋል። ሐዋርያዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናም ምእመኖቿ ከእመቤታችን በረከትን እንዲያገኙ ይጾሙ ዘንድ ይህን ሐዋርያት የጾሙትን ጾም እንዲጾሙ ዐዉጃለች። ምእመናንም በተለየ መልኩ በጾም በጸሎት በሱባዔ ጽሙድ ሆነው ይህን ወቅት ያሳልፋሉ። የእመቤታችን ትንሣኤ ድንገት እንደእንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ ነቢያት የተገለጸ ነው። ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር ፻፴፩ ቁጥር ፲ ላይ «አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦትም» ይላል። በዚህም ምእመናንን ወደ ምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ አለ። ታቦት የጽላት ማደርያ እንደሆነ ሁሉ እመቤታችንም ለክርስቶስ ማደርያ በመሆኗ አማናዊት ታቦት ትባላለች። ንጉሥ ሰሎሞንም በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲ ላይ «ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፤ ወዳጄ ሆይ ተነሽ፡ ውበቴ ሆይ ነይ» ብሏል። እዚህ ላይ «ወዳጄ ...ውበቴ»" የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ። ክቡር ዳዊት መዝሙር ፵፬ ቁጥር ፱ ላይ «በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች» እንደሚል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነቱን ከፈጸመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንዳረገ እመቤታችን ቅድስት ድንገል ማርያምም በቀኙ ትቀመጥ ዘንድ «ተነሽ ነይ» አላት ። እንግዲህ ይህንና የመሰለዉን ሁሉ ይዘን የእናታችንን ዕረፍቷንና ትንሣኤዋን እንዘክራለን እንመሰክራለንም። @dnbaze💚💚❤️ @dnbaze❤️❤️💚💛 @dnbaze💜💚💛❤️
Show all...
""ሚስጥረ ስላሴ " ምስጢረ ሥላሴ፦ስለ ስላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው። እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ ነው። <= >የእግዚአብሔር ሦስትነት ስንል፦ እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው። የእግዚአብሔር ሦስትነት በስም በግብር በአካል ነው። <= >እግዚአብሔር በስም ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው። እነዚህም፦ #አብ #ወልድ መንፈስ ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም፤ አንዱ በሌላው ስም አይጠራም። "ዘፍጥረት1፡ 2 " "ምሳሌ30፡4" ። >እግዚአብሔር በግብር ሦስት ነው፦ ስንል ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው። እነሱም፦ መውለድና ፤ማስረጽ የአብ መወለድ፡ የወልድ መስረጽ፡ የመንፈስ ቅዱስ ፤ የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ። "መዝሙር2፡7" <=>እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ ለአብ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው። ለወልድ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ። #ለመንፈስቅዱስ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው። <=>የሦስቱ የእግዚአብሔር ስሞችትርጉም #አብ፦ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸነው። #ወልድ፦ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው። "መዝሙር2፡7" #መንፈስቅዱስ፦ ረቂቅ፤ ልዩ፤ ንፁህ; ከፍጡራን ሁሉ የተለየ ማለት ነው።
Show all...
# ይድረስ_ለሴቶች_እህቶቼ_አንብቡት ወንዶችም አንብባችሁ ለእህቶቻችን ሼር ሼር ሼር በማድረግ አጋሩ አዲስ ተች ስልክ የገዛችውን ልጅ አባቷ ሲያያት . . . . . . . ›› አባት ፡ “”ስልኩን ስትገዢ በመጀመሪያ ያደረግሽው ምንድነው ? “” ብሎ ጠየቃት፡፡ ልጅ ፡ “”በመጀመሪያ ያደረኩት . . . ስክሪኑ እንዳይጫጫር መከላከያ ስቲከር ለጠፍኩበት . . . “” አባት ፡ “” እንደዚ እንድታደርጊው የገፋፋሽ ሰው እለ ?”” ልጅ ፡ “” የለም ! ! ! “” አባት ፡ “”ያመረቱትን እንደ ማንቋሸሽ አይሆንም ግን . . .”” ልጅ ፡ “”ኧረ አባዬ ! እንደውም የሚመክሩን እንድንለጥፍበት ነው ! ”” አባት ፡ “” የሸፈንሽው ግን ርካሽ ስለሆነ ወይም ስለሚያስጠላ ነው ??? “” ልጅ ፡ “”” በነገራችን ላይ የሸፈንኩት . . . እንዳይበላሽብኝ እና ብዙ ግዜ እንዲያገለግለኝ ስለምፈልግ ነው ! “” አባት ፡ “”” ስትሸፍኝው . . . ውበቱን አልቀነሰውም “” ልጅ ፡ “”” እንደውም በጣም አምሮበታል በዛ ላይ እንዳይበላሽ ይከላከልልኛል “” አባት ፡ በአባትነት ዓይን እያያት “”” አንድ ጥያቄ ብጠይቅሽስ. . . ከስልክሽ የሚበልጠውን ገላሽን እንድትሸፍኝው . . . እሺ ትይኛለሽ ወይ ??? `` ሁሌም አባታችን እግዚአብሔር ይጠይቀናል በሰው ላይ አድሮ . . . . ብቻ በብዙ ነገር ራሳችንን እንድንሸፍን ይጠይቀናል ! ☞የምናስተውል ካለን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል"፤ ፨ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸፍኑ (1 ኛ ጢሞ 2፥9) ፠ በሚሞት ስጋችሁ ሐጢያት አይንገስ ብልቶቻችሁን የፅድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ (ሮሜ 6፥12-14) ፠ ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው ካልተቻለ ዝሙትን ለመከላከል በአንድ ይፅና ከዚህ ውጭ ጉዞ ወደ እሳት ነው (1ኛ ቆሮ 7፥1) ፠ ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱ ያፈርሰዋል ቤተ መቅደሱም እናንተው ናችሁ (1ኛ ቆሮ 3፥17) ፠ የወንድ ልብስ የለበሰች ሴት በአምላክ ዘንድ የተጠላች ናት (ዘዳ 22፥5; ዘፀ 39፥28) ፠ ፀጉሯን ሳትሸፍን የምትፀልይ ሴት እራሷን ያዋረደች ናት(1ኛ ቆሮ 11፥5) እንድናስተውል እና እንደ እግዚአብሔር ቃል እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን አሜን (ለምታውቁት ሰው እና መንፈሳዊ ግሩፕ ትልኩ ዘንድ በእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም አበክሬ እጠይቃችኋለሁ አደራ) @dnbaze @dnbaze join it
Show all...
በጣም አስተማሪ ታሪክ ይነበብ ♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️ አንድ በሥራው ታታሪ የሆነ ዓሳ አጥማጅ ነበር።ይህ አጥማጅ በየቀኑ ዓሳ ያጠምድና አስከሚያልቅ ድረስ ይጠቀማል። ልክ ሲያልቅ ወደ ባህር ዳርቻ በመሄድ ሌላ ያጠምዳል። ከእለታት አንድ ቀን የዓሳ አጥማጁ ሚስት ባሏ ያመጣላትን ዓሳ በመቆራረጥ ላይ ሳለች አሰገራሚ ነገር ታያለች። ይህች ሰው የተመለከተችው እጅግ የከበረ ሉል ነው ። በጣም እየተገረመች በዓሳ ሆድ ውስጥ ሉል ...? አያለች ባሌ... ባሌ... ባሌ... እያለች ባሏን መጥራት ጀመረች ከዚያም "ምን እንዳገኘሁ ተመልከት ሉል እኮ ነው!! ሉል ... ከዓሳው ሆድ ውስጥ " አለችው ። እሱም " እንዴት አሰደሳች ሚስት ነሽ እስኪ አቅርቢው ለዛሬ ለቤት ቀለባችን መግዣ ትሆነናለች ..... ከዓሳ ሌላ ምግብ እንበላለን!!" አላት..... ይህ ዓሳ አጥማጅ ሉሉን በመያዝ ወደ ሉል ገዢና ሻጭ በመሄድ ያሳየዋል። ገዢውም "እኔ ይህንን ሉል የመግዛት አቅሙ የለኝም፤ ዋጋው ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ይህንን ሱቄንና መኖሪያ ቤቴን ብሸጠው እንኳን ልገዛህ አልችልም። ይልቁንስ እከሌ የሚባል ሀብታም ነጋዴ አለ እርሱ ሊገዛህ ይችላልና ወደርሱ ሂድ። አለው ። ዓሳ አጥማጁ ሉሉን በመያዝ ወደ ተባለው ሀብታም ሰው በመሄድ ጉዳዩን ነገረው። ይህ ታላቅ ነጋዴም "እኔ አልችልም ይህ የያዝከው ሉል በገንዘብ የሚተመን አይደለምና እኔ መፍትሔ ብዬ የማስበው ወደ ከተማው አስተዳዳሪ ሄደህ ብታሳየው ነው እንደዚህ አይነት ውድ ሉል ከርሱ ውጭ የመግዛት አቅም አለው ብዬ የማስበው ሰው የለም " አለው። ጉዞውን ወደ ተባለው አስተዳዳሪ በማድረግ ቤቱ እንደደረሰ ወደ ህንፃው ለመግባት ፈቃድ እስኪያገኝ ድረስ መጠበቅ ጀመረ። (እንደገባም) ለአስተዳዳሪው የያዘውን ሉል ሲያሳየው አጅግ ተገረመ። "እንደዚህ አይነት ሉል ስፈልገው የነበረ ነው… እንዴት ተመኑን እንደምከፍልህ አላውቅም… ነገር ግን ለየት ወዳለው ካዝናዬ እንድትገባ እፈቅድልሃለሁ። እዛ ውስጥም ለስድስት ሰዓታት በመቆየት የቻልከውንና የፈለከውን ንብረት ተሸክመህ መውጣት ትችላለህ። ይህ እንግዲህ የሉልህ ክፍያ ነው።" በማለት ወደ ካዝናው እንዲገባ ጋበዘው። ዓሳ አጥማጁም "አለቃዬ ሆይ! ስድስት ሰዓት…!! እንደኔ ላለ ዓሳ አጥማጅ በጣም ብዙ ነው እንደው ሁለት ሰዓት ብታደርግልኝ " ሲል ጠየቀው። አስተዳዳሪውም "በጭራሽ አይሆንም ስድስት ሰዓት ሙሉ ከካዝናዬ የፈለከውንና የምትችለውን ያህል ይዘህ መውጣት አለብህ " አለው። ዓሳ አጥማጁ ወደ ካዝናው ሲገባ በጣም የሚያስደንቅ ሁኔታን ተመለከተ። በሦስት የተከፈለ ሰፊ ክፍል ☞ አንደኛው ክፍል በአልማዝ፣ በወርቅና በተለያዩ ጌጣጌጦች የተሞላ ክፍል ነው። ☞ሁለተኛው ክፍል ለመተኛት ምቹ የሆኑ ለየት ያሉ ፍራሾች ያሉበት ክፍል ነው። ☞ ሦስተኛው ክፍል አጠቃላይ በሚፈለጉና ውድ በሆኑ የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች የተሞላ ነው። ዓሳ አጥማጁ ከራሱ ጋር መነጋገር ጀመረ። "ስድስት ሰዓት!! እንደኔ ላለው ድሃ ዓሳ አጥማጅ በጣም ብዙ ነው በዚህ ስድስት ሰዓት ምን ማድረግ አለብኝ? ጥሩ! በሦስተኛው ክፍል ባሉት ምግብና መጠጥ መጀመር አለብኝ ምክንያቱም ብዙ ወርቅ ለመሸከም የሚያስችለኝን ኃይል አገኝበታለሁ። " በማለት ወደ ሦስተኛው ክፍል በመሄድ መብላት ጀመረ። ይበላል… ይበላል… ይጠጣል… ከስድስቱ ሰዓታት በመብላት ሁለቱን ሰዓት ተጠቀመ። ልክ ሲጨርስ ወርቁንና ጌጣጌጡን ለመሸከም ወደ አንደኛው ክፍል በመሄድ ላይ ሳለ በሁለተኛው ክፍል ያለውን ያማረ ምቹ ፍራሽ ተመለከተና እራሱን ማናገር ጀመረ። "አሁን በጣም ጠግቤያለሁ ለምን ትንሽ በመተኛት በደንብ ለመሸከም የሚያስችለኝን እረፍት አልወስድም? ይህንን እድል ደግሜ አላገኘውምና ለምን አበላሸዋለሁ?" በማለት ወደ ፍራሹ በመሄድ በጀርባው ተዘረጋ በጣም ጭልጥ ያለ እንቅልፍም ወሰደው። ከተወሰነ ሰዓታት በኃላ "ተነስ ተነስ ቁም አንተ ጠባብ የሆንክ ዓሳ አጥማጅ ተነስ… ቁም...... ጊዜው አልቋል " አለው። ዓሳ አጥማጁም " እ እ እንዴ ምንድነው...?" አለ። ሰውዬውም " አዎ! ወደ ውጭ ውጣ " አለው። አጥማጁም "ኧረ ምንም በቂ ዕድል አላገኘሁም " አለ። ሰውዬውም "ስድስት ሰዓታት ሙሉ በዚህ ካዝና ውስጥ ሆነህ ጊዜህን ሳትጠቀም ቀርተህ አሁን ትባንናለህ? ከዚያም ሰዓት እንዲጨመርልህ ትጠይቃለህ? እነዚህን አልማዝና ወርቆች በፍጥነት ሰብስበህ በመውጣት የፈለከውን ምግብና መጠጥ እንዲሁም ያሰኘህን አይነት የመኝታ ፍራሽ መግዛት ትችል ነበር። ነገር ግን አንተ ዝንጉና ጠባብ በመሆንህ በዙሪያህ ያለውን እንጂ ሩቅ ያለውን ነገር አታስብም።" በማለት "ወደ ውጭ አስወጡት! " አለ። አጥማጁም "ኧረ ባካችሁ!! ኧረ!… እባካችሁ አንድ እድል ይሠጠኝ " ቢልም ሊሆንለት አልቻለም። ታሪካችን አለቀ በውስጡ ያለው ትምህርት ግን አላለቀም...... ♻️🔆♻️🔆♻️🔆♻️♻️🔆♻️ ልብ በሉ ይህ ሰውዬ እጅግ የከበረ ጸጋ ተሰጥቶት አልተጠቀመበትም ባለችው ጊዜያዊ ምግብና መኝታ ተታሎ ጥቅሙን አጣ እኛም ምድራዊ ነገር አታሎን ጥርስ ማፏጨትና ልቅሶ ወዳለበት እንዳንጣል በጊዜ ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን ልንኖር ግድ ነው። 👇👇👇👇👇👇@dnbaze Join and share
Show all...
#ስለኛ_የሚማልደው_ለምን_አለ ? መናፍቃን ክርስቶስን አማላጅ አድርገው ከሚያቀርቡበት ውስጥ አንዱ ጥቅስ ይሄ ነው ፦ "የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው ? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞም ስለኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው " ሮሜ 8:34 ከላይ እንደ ተገለጠው #ኮነነ የሚለው ቃል የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ፈረደ ገዛ ማለት ነው ። የሚኮንን ማነው ? ሲል የሚገዛ የሚፈርድ ማነው ? ማለት ነው ። ምላሹም በጥቅሱ እንደተገለጸው #ክርስቶስ_ኢየሱስ ነው ። መጻሕፍት እንደሚመሰክሩት እኛም እንደምናምነው መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛው አስታራቂ መሆኑ አማላጅ አያሰኘውም አይደለምም የእርሱ የማስታረቅ ስራ ከአማላጅነት ጋር የሚነጻጸር አይደለም ። ሁልጊዜ ስለ ክርስቶስ ስናስብ ከአብና ከመንፈስቅዱስ ጋር ያለውን አንድነት መዘንጋት የለብንም ። እንግዲህ ይሄ ጥቅስ መናፍቃን እንደሚሉት የክርስቶስን አማላጅነት የሚገልጥ ሳይሆን የክርስቶስን ፈራጅነት የሚያሳይ ነው ። ጌታችን ኃጢአትን ይቅር የሚል ፣ በደልን የሚደመስስ ፣ ምሕረትን የሚሰጥ ከራሱ ጋር ያስታረቀን አስታራቂያችን ፣ የታረቅንበት መታረቂያችን ፣ የታረቅንበት ታራቂያችን ነው እንጂ አማላጃችን አይደለም ። " እርሱ ክርስቶስ ገዢ ነው ፈራጅ ነው " ሮሜ 14:10 እንግዲህ ጌታ ፈራጅ ከሆነ እንዴት አማላጅ ሊሆን ይችላል ? ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ መባሉ እግዚአብሔር ስለሆነ ሲሆን እግዚአብሔር ከሆነ እንዴትና ከማን ይማልዳል ? #ቀኝ የሚለው ቃል ሥልጣንን፣ ክብርን፣ ሃይልን የሚያሳይ ነው ከአብ ጋር ያማልደናል እንዳንልም "እኔና አብ አንድ ነን "ዮሐ10:30 ብሏል ። ታዲያ ስለኛ የሚማልደው የሚለው እንዴት ነው ቢሉ መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠነቀቀው ከዘይቤ ይልቅ ለምስጢር ነው ። ለምሳሌ ቅዱስ ጳውሎስ የሚማልደው ሲል ጌታችን ከመወለዱ ከ700 ዓመት በፊት የነበረው ኢሳያስ ደግሞ ስለ አመፀኞች ማለደ ብሎአል ። ኢሳ 53:12 ኢሳያስ ገና ወደ ፊት የሚፈፀመውን እንደተፈፀመ አድርጎ ሲናገር ጳውሎስ ደግሞ የተፈፀመውን ገና ወደፊት እንደሚፈፀም አርጎ ተናገረ። ያውም በቃላት ሳይሆን እራሱን አሳልፎ በመስጠት አንዴ ለዘላለም የተፈፀመ ስለሆነ ማለደ ብሎ ደመደመው "ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይሄን አንድ ጊዜ ፈፅሞ አድርጓልና " ዕብ7:27 ይህም በመስቀሉ ከራሱ ጋር ከባህርይ አባቱ ከአብ ጋር ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሱ ቤዛነት ፣ በሱ ካሳነት ለዘልዓለም መዳናችንን ለመግለፅ እንጂ መናፍቃን እንደሚሉት እሱ ከአብ አንሶ ስለኛ ምህረትና ይቅርታ የሚጠይቅ አማላጅ አይደለም በሌላ መልኩ ደግሞ ከ1938 ዓ.ም የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለኛ #ይፈርዳል በማለት ነበር የተቀመጠው ። በ1980 የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ግን ስለኛ #የሚማልደው ይላል ። የ1938 ፈረደ የሚለውን ኀላ ቀላል አማርኛ በማለት ማለደ ተብሎ ሆን ተብሎ የተቀየረ ነው እንግዲህ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 8:34 ያሰፈረውን ፍሬ ሃሳብ ለመረዳት እስቲ ኢየሱስ አማላጅ ነው ለሚሉት ጥቂት ጥያቄዎችን እናንሳ የሚያጸድቅ መኮነን አይችልም ? የሚኮንንስ ለማጽደቅ ምን ይሳነዋል ? በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጥስ የሚችል ማነው ? ክርስቶስ በሞቱ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ እኛን የሚያድንበት ስልጣን አጥቶ ነው ስለኛ የሚማልደው ? ክርስቶስ ሁሉን የሚችል ኤልሻዳይ ነው ። ለሰውም እንደየስራው መክፈል የሚቻለው ፤ የሁሉ ዋጋ በእጁ ያለ የሚተካከለው የሌለ ባለ ጸጋ እውነተኛ ፈራጅ ዳኛም ነው ። እስቲ በመጽሐፍ ጥቅስ እናስደግፈው "እነሆ በቶሎ እመጣለው ለእያንዳንዱም እንደ ስራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ " ራዕ 22:12 ሌላ እንጨምር "እነሆ ዋጋው ከእርሱ ጋር ደሞዙም በፊቱ ነው "ኢሳ 40:10 ክርስቶስ ፈራጅ ከሆነ ታዲያ የሚለምን የሚያማልድ ማነው ? ከተባለ ከተለማኙ ጋር በቅርብ የሚተዋወቅ እውነቱን ለማስረዳት ይቅርታን ሊያሰጥ የታመነ ከተማላጁም ባለሟልነትን ያገኘ ነው ። ይሄንንም ስራ የሚሰሩት ከእግዚአብሔር በጸጋ የከበሩ ቅዱሳን ናቸው Comment@dnbaze 0901613959 💚 @dnbaze💚 💛@dnbaze 💛 ❤️ @dnbaze❤️
Show all...
1❤ ሮሜ 8 ፥26-27ሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል አንዴት እንድንጸልይ አንደሚገባን አናውቅምና ነገርግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ያማልድልናል ልብንም የሚመረምር የመንፈስ አሳብ ምን እንደሆነ ያውቃል እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ስለ ቅዱሳን ያማልዳልና።" 😳😳መንፈስ ቅዱስ ያማልዳል ይላላል 😳😳 2❤ሮሜ8፥34 "የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለእኛ የሚማልደው ክርስቶስ እየሱስ ነው።"😳😳እየሱስ ያማልዳል 😳😳 3❤ ኤር23፥25"ነገር ግን ቃሌን ስሙ እኔም አምላክ እሆናቹኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ መልካምም ይሆንላቹህ ዘንድ ባዘዝኋቹሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ ብዬ በዚህ ነገር አዘዝኋቸው። ነገር ግን በክፉ ልብሳቸው አሳብና እልከኝነት ሄዱ ወደ ፊትም ሳይሆን ወደኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም። አባቶቻቹህ ከግብፅ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በእየለቱ እየማለድሁ ባሪያወቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባቸው ነበር።"😳😳እግዚአብሔርም ይማልዳል 😳😳 እና (((ማነው አማላጅ እየሱስ መንፈስቅዱስ ወይስ እግዚአብሔር ))) ?????ለምንድንነው ይማልዳል ያለው?? @dnbaze
Show all...
✝ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ እነሆ🙏🙏🙏 1️⃣: ስለ ሥላሴ የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት:- ዘፍ 1:26 ዘፍ 3:22 ዘፍ 11:18 ዘፍ 18:1-2 ኢሳ 48:26 ማቴ 3:16-17 ማቴ 28:19 ሉቃ 1:35 ዮሐ 7:28-29 ዮሐ 14:25-26 ሐዋ 3:14 1ኛ ቆሮ 12:4-7 2ኛ ቆሮ 13:14 ኤፌ 4:4-7 2️⃣ስለ እመቤታችን ቅድስናዋ ፣ ክብሯ ፣ ድንግልናዋና አማላጅነቷ:- መዝ 9:11 መዝ 13:10 መዝ 44:9 መዝ 86:5 መዝ 131:13 መዝ 44:2 መኃ 4:12 ኢሳ 7:14 ኢሳ 49:23 ኢሳ 60:14 ማቴ 1:23 ሉቃ 1:28 ሉቃ 1:42 ዮሐ 2:1-11 ዮሐ 19:16 ሮሜ 11:26-27 2ኛ ቆሮ 11:2 ራዕ 12:16 3️⃣ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ እንጂ አማላጅ አይደለም፡- ዘፍ 3:22 1ኛ ሳሙ 16:1 ኢሳ 9:6 ዳን 7:14 ሆሴ 13:4 ዘካ 9:9-10 ሚክ 5:2 ሉቃ 1:32-33 ዮሐ 10:30 ሉቃ 2:12 ዮሐ 14:7 ሮሜ 9:5 ቆላ 2:9-10 ቲቶ 2:11-13 ዕብ 1:3-4 ዕብ 1:10-11 1ኛ ጴጥ 3:23 1ኛ ዮሐ 2:23 ራእ 3:22 ራእ 22:12-13 4️⃣ስለ ታቦትና ጽላት ዘፀ 24:12 ዘፀ 25:10 ዘፀ 25:21 ዘፀ 26:34 ዘፀ 31:18 ዘፀ 32:15 ዘፀ 34:1 ዘፀ 34:28 ዘፀ 37:1 ዘፀ 40:20 መኃ 7:89 ኢያ 3:3 ኢያ 7:6 2ኛ ቆሮ 6:16 5️⃣ስለ ጾም የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ:- ዘፀ 34:28 ዘፀ 9:9 ሳሙ 20:26 1ሳሙ 7:6 1ሳሙ 31:13 2ኛ ሳሙ 1:12 2ኛ ሳሙ12:16 ዕዝ 8:21 ዕዝ 68:10 ዕዝ 108:24 ኢሳ 48:3 ኤር 36:9 ዳን 9:3 ዳን 20:2-3 ኢዩኤ 2:14 ኢዩኤ 2:12 ዮና 3:5 ማቴ 4:2 ማቴ 6:16:18 ማቴ 9:14-15 ማቴ 17:21 ማር 2:18 ማር 9:29 ሉቃ 2:37 ሉቃ 18:12 የሐ.ስራ 13:3 ሐዋ 14:23 2ኛ ቆሮ 11:17 6️⃣ ስለ መስቀል በመጽሐፍ ቅዱስ:- ማቴ 10:38 ማቴ 16:20 ማር 8:34 ሐዋ 5:30 1ኛ ቆሮ 1:18 ገላ 3:13 ገላ 6:13 ፊል 2:8 ፊል 3:18 7️⃣ጥምቀትን በተመለከተ:- ሕዝ 36:25 ማቴ 3:5-6 ማቴ 26:19-20 ማር 1:4-5 ማር 16:16 ሉቃ 3:21 ዮሐ 3:5 ዮሐ 3:22 ኤፌ 4:5 ገላ 3:26-27 ሐዋ 19:4 ሐዋ 18:8 ሐዋ 13:24 ሐዋ 10:47 የሐዋ 9:18 1ኛ ቆሮ 1:16 1ኛ ቆሮ 10 :2 1ኛ ቆሮ 12:13 8️⃣ስእለትን በተመለከተ:- ዘኁ 28:20 ዘኁ 21:2 ዘፀ 23:21 መሳ 11:30 መዝ 49:14 መዝ 75:11 1ኛ ሳሙ 1:11 መክ 5:4-5 ዮና 2:10 ናሆ 1:15 ሐዋ 18:18 9️⃣ጻድቃን ሰማዕታት ያማልዳሉ:- ዘፍ 18:17-18 ዘፍ 18:23:24 ዘፍ 20:7 ዘፍ 33:3 ዘፍ 42:6 1ኛ ሳሙ 28 :14 2ኛ ሳሙ 1:2 2ኛ ነገ 1:13 2ኛ ነገ 2:15 2ኛ ነገ 4:9 2ኛ ነገ 4:32-35 መዝ 88:34 ማቴ 18:18 ዮሐ 20:23 ሐዋ 10:25 ሐዋ 16 :29 1ቆሮ 6:1-2 ፊሊ 4:6 1ኛጢሞ 5:17 ያዕ 5:14 ራእ 14:13 🔟መላእክት ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ:- መዝ 148:2 ኢሳ 6:3 ማቴ 4:12 ማቴ 18:10 ማቴ 25:31 ማር 8:38 ራእ 1:11 ሉቃ 1:19 1️⃣1️⃣መላእክት ጸሎታችንን ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ:- ጦቢ 12:15 ሉቃ 15:10 የሐዋ 10:4 ኢዮ 25:3 ኤር 33:22 ዳን 7:10 ሄኖ 10:1 ራእ 5:11 1️⃣2️⃣ለመላእክት የአክብሮት ስግደት ይገባል:- ዘፍ 19:1 ዘኁ 22:31 ኢያ 5:14 ዳን 8:16-17 1️⃣3️⃣መላእክት አብሣሪያን ናቸው:- ዘፍ 16:11 ሉቃ 1:13 ሉቃ 1:19 ሉቃ 1:30-31 ሉቃ 2:10-11 1️⃣4️⃣መላእክት በአደጋ ጊዜ ፈጥነው ይደረሳሉ:- ዘፍ 22:11-12 መዝ 90:11-12 ዳን 6:22 ዳን 10:13 ማቴ 2:13 ሐዋ 5:19-20 ሐዋ 12:7 1️⃣5️⃣ ፀበል መርጨት ያስፈልጋል ዘኁ 19:20 ለመቀላቀል lela yemenafiqan xiyaqehochin lemagignet join share this link👇👇 @dnbaze @dnbaze join 0901613959 🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
Show all...
የቅዱሳን አማላጅነት በሐዲስ ኪዳን፦ 1,ማቴ.18፥18፣ማቴ.16፥19፣ዮሀ.21፥15-17 የምዕመናን ህይወት አደራ ሰጥቷቸዋል ። 2,ሐዋ.4፥31፣8፥6 በዲያቆኑ ፊልጶስ አማላጅነት ብዙ ሰዎች ተፈውሰዋል። 3,ቅዱስ ጴጥሮስ በአማላጅነቱ 8 አመት ከአልጋ ተጣብቆ የነበረውን ኤንያን ፈውሶታል። የሐዋ .9፥33 4, የሐዋ,9፥36 በኢዮጴም ጣቢያን ከሞት አስነስቷል ። 5, የሐዋ.14፥8 ሀዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በልስጥራን እግሩም የሰለለውን ሰው በጸሎቱ ቀጥ አንዲል አድርጓታል ። 6, ፊልጵስዮስ የሟርተኝነት መንፈስ የነበራትን ሴት በፀሎቱ ፈውሷታል።የሐዋ,16፥16 ያዕ.5፥14-16 ለዚህ ነው የጻድቅ ሠው ፀሎት በስራዋ እጅግ ሀይል ታደርጋለች። ይላል እኛም አምነን የሠሩትን ብንሠራ አይደለም የሚማለድለት ሠው ነውና አማላጅ መሆን እንችላለን ። ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን! @dnbaze @dnbaze⛪️⛪️
Show all...
የቅዱሳን አማላጅነት በሐዲስ ኪዳን፦ 1,ማቴ.18፥18፣ማቴ.16፥19፣ዮሀ.21፥15-17 የምዕመናን ህይወት አደራ ሰጥቷቸዋል ። 2,ሐዋ.4፥31፣8፥6 በዲያቆኑ ፊልጶስ አማላጅነት ብዙ ሰዎች ተፈውሰዋል። 3,ቅዱስ ጴጥሮስ በአማላጅነቱ 8 አመት ከአልጋ ተጣብቆ የነበረውን ኤንያን ፈውሶታል። የሐዋ .9፥33 4, የሐዋ,9፥36 በኢዮጴም ጣቢያን ከሞት አስነስቷል ። 5, የሐዋ.14፥8 ሀዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በልስጥራን እግሩም የሰለለውን ሰው በጸሎቱ ቀጥ አንዲል አድርጓታል ። 6, ፊልጵስዮስ የሟርተኝነት መንፈስ የነበራትን ሴት በፀሎቱ ፈውሷታል።የሐዋ,16፥16 ያዕ.5፥14-16 ለዚህ ነው የጻድቅ ሠው ፀሎት በስራዋ እጅግ ሀይል ታደርጋለች። ይላል እኛም አምነን የሠሩትን ብንሠራ አይደለም የሚማለድለት ሠው ነውና አማላጅ መሆን እንችላለን ። ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን! @dnbaze @dnbaze
Show all...
በተሳፋሪዎች የተሞላዉ አዉቶብስ ጉዞ ላይ ነዉ ወዲያዉ የአካባቢዉ የአየር ሁኔታ ተቀያየረና አስፈሪ የነጎድጓድ ድምፅ የመብረቅ ብልጭታ መታየት ጀመረ፡፡ ተሳፋሪዎቹ አዉቶብሱ ከአሁን አሁን በመብረቅ ተመታ እያሉ መጨነቅ ጀመሩ መብረቁ ግን መኪናዉን እያለፈ ይወድቅ ነበር፡፡ እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ ሁለት ሶስቴ እንደቀጠለ ሾፌሩ አዉቶብሱን ከአንድ ዛፍ ሃምሳ ጫማ ርቀት ሲቀረዉ አቆመና ተሳፋሪወቹን "ከእናንተ መሃል ዛሬ መሞቱ ግዴታ የሆነ ሰዉ አለ ከአሁን በኋላ አብሮን ከተጓዘ በእሱ ምክንያት ሌሎቻችንም አብረን ልንጠፋ እንችላለን። ስለዚህ ሁላችሁም በየተራ እየወጣችሁ ያንን ዛፍ እየነካችሁ እንድትመለሱ እፈልጋለሁ መሞት ያለበት ሰዉ ካለም ዛፉን የነካ ጊዜ በመብረቅ ይመታል ሌሎቻችን ግን እንተርፍለን ማለት ነዉ!!" አለ ሁሉም የመጀመሪያዉን ተሳፋሪ ሄዶ ዛፍን እንዲነካ መጎትጎት ጀመሩ እሱም እየጨነቀዉና በፍርሃት ተዉጦ ሄዶ ዛፍን ነክቶ በሰላም ተመለሰ ምንም ሳይሆን በመመለሱም ልቡ በደስታ ጮቤ ረገጠች፡፡ መጨረሻ ላይ የነበረዉ ተሣፋሪ ተራ እንደደረሰ ሁሉም ሟቹ እሱ እንደሆነ በማሰብ ዐይኑን እያዩት እንዲሄድ ገፋፉት እሱም በመሞት ፍራቻ ተዉጦ ከአዉቶብሱ ወረደ። ከዛፉ ደርሶ እንደነካዉም ኃይለኛ ድምፅ ተሠማ አስፈሪ የመብረቅ ብልጭታም ሆነ... መብረቁ ግን የመታዉ አዉቶብሱን ነበር። ውስጡ የነበሩት ተሳፋሪዎችም ሞቱ፡፡ እነዚያ ቀደም ብሎ አዉቶብሱን ያለፉት አደጋዎች ሁሉ ያለፉትም ለመጨረሻዉ ተሣፋሪ ንጽህና ነበር፡፡ ራሳችንን ሁልጊዜ እንደ ንጹህ እናያለን [ግን ለምን?] @dnbaze @dnbaze
Show all...