cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኑ በጌታ ደስ ይበለን!🎧🎤..🎸.🎵..

እዚህ ቻናል ላይ :- 👉አዳዲስና ዘመን የማይሽራቸዉ ዝማሬዎች 👉አምልኮዎችን(Live Songs) 👉 ስብከቶች፣ የመ.ቅ ጥቅሶችን 👉ልዩ መልዕክት ያላቸውን ፒክቸሮችን ያገኛሉ! ይ🀄️ላ🀄️ሉን 👉ለ አስታያየት አና ማገልገል ለምትፈልጉ @Wendi4th @bibi_son

Show more
Advertising posts
188
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 60) ---------- 16፤ የአሕዛብንም ወተት ትጠጫለሽ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ እኔም እግዚአብሔር የያዕቆብ ኃይል፥ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ። 17፤ በናስ ፋንታ ወርቅን፥ በብረትም ፋንታ ብርን፥ በእንጨትም ፋንታ ናስን፥ በድንጋይም ፋንታ ብረትን አመጣለሁ። አለቆችሽንም ሰላም፥ የበላይ ገዢዎችሽንም ጽድቅ አደርጋለሁ፤ 18፤ ከዚያ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳርቻሽም ውስጥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥርሽን መዳን በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያለሽ 19፤ ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም፥ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አይበራልሽም። 20፤ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናልና፥ የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም ጨረቃሽም አይቋረጥም። 🙏🙏🙏 Amen amen amen🙏🙏🙏 @Mercyyy23
Show all...
የራቀህ ሲመስልህ! #ህይወት በፈተና የተሞላች ናት ለአንደኛው ሙሉ ለሌላኛው ጎዶሎ ለአንዱ ሲጨልም በተቃራኒው ደግሞ ለሌላው ይነጋል በአጠቃላይ ለእያንዳንዱ ሰው ትንሽም ሆነ ትልቅ እንደየአቅሙ ፈተና ይፈተናል ሆኖም ይህ ፈተና የመጣው በራሳችን ምኞት ስንጠመድ እንደሆነ ቅዱስ መፅሐፍ ይገልፅልናል (የያዕቆብ መልእክት 1፥13-14) " ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።" #በየትኛውም አይነት ከባድ ፈተና ውስጥ ብታልፉ የእግዚአብሔር ህልውና እና እግዚአብሔር እንደራቀህ ከተሰማህ ያኔ ትልቁ ፈተና እየተፈተንክ እንዳለህ ላረጋግጥልህ እወዳለሁ ምክኒያቱም በጣም ወሳኝ፣አንገብጋቢ ፣አስፈላጊ ከምንላቸው እንዱና ዋና የእግዚአብሔር ህልውና ነው። ሳኦል በዚህ ፈተና ውስጥ አልፏል ባለመታዘዙ ምክንያት የእግዚአብሔር ህልውና ከሱ እርቆታል " የእግዚአብሔርም መንፈስ ከሳኦል ራቀ፥ " (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16: 14) #የእኛም ህይወት ብፌ ላይ እንደተደረደረ ምግብ ነው የምንፈልገውን እና የሚመችህን ታነሳለህ እንጂ የተደረደረውን ምግብ ሀሉ አታነሳም ስለዚህ እንደ ሳኦል መጥፎን ሀሳብ አስወግደን መልካም ከሆነው ከእግዚአብሔር ሀሳብ ጋር ተስማምተን የእርሱ ህልውና እንዳይጠፋብን የራሳችንን ሀላፊነት እንወጣ። #በመጨረሻም የራቀህ ቢመስልም እንኳ እስክታገኘው ድረስ አጥብቀህ.........አጥብቀህ.......አጥብቀህ ከልብህ ፈልገው ታገኘዋለህ ያን ጊዜ ጌታ ከአንተ ጋር እንዳለህ ይሰማሃል። #አንድ ነገር አስብ " እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።" (መዝሙረ ዳዊት 34: 18) ✍ Meron ተባረኩ! 👐 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
Show all...
ዙረያዬ ሲጨልምብኝ መሄጃው ግራ ሲገባኝ አይኖቼን ወዳንተ አነሳው ረዳቴ ፍጠንልኝ አልኩኝ አንተም አንጎዳጎድክና ጠላቴን መከትክና ዳግም አፅንተ አቆምከኝ እንደ ጦረኛም አረከኝ በሀዘን ችግሬ ግዜ አይዞ ባይ ደራሽ አጋዤ ስጠራህ ፈጥነህ የምደርስ ሳነባ እምባዬን ምታብስ አቤቱ እንዳንተ ማነው ወዳጄ እንዳንተ ማነው አቤቱ እንዳንተ ማነው አጋዤ እንዳንተ ማነው እየሱሴ እየሱሴ እየሱሴ እንዳንተ ማነው
Show all...
አላየሁም አልሰማሁም እንዳንተ ያለ ፍቅር የሆነውን አንተ ፍቅር ነህ ፍቅር አንተ ፍቅር ነህ ፍቅር አንተ ፍቅር ነህ ፍቅር አንተ ፍቅር ነህ ፍቅር ፍቅር ነህ ፍቅር ፍቅር ነህ ፍቅር ፍቅር ነህ ፍቅር ደከመኝ ሰለቸኝ አቃተኝ አልልም ወዳደባባይህ መግባትን አልተውም የኔ ጥሩ ወዳጅ የኔ ሊቀካህን ዘመኔ ይለቅ አንተን ሳገለግልህ ፍቅር ነህ ፍቅር ፍቅር ነህ ፍቅር ፍቅር ነህ ፍቅር ፍቅር ነህ ፍቅር ግኡዝ አይደለሁም ስታግዘኝ ምላሽ የማልሰጠው ካደረክልኝ ጋራ ባይመጥንም ስምክን ልባርከው ፍጥረት ይታዘበኝ ያላንተማ የት ነበርኩ ይሄኔ ሞገስ ሆነኅኛል ቆመህልኝ በደካማ ጎኔ ተመስገን እንጂ ሌላ ምን እላለሁ ስትረዳኝ ባይኖቼ ስላየሁ ተባረክ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ ስታግዘኝ ባይኖቼ ስላየሁ ተመስገን እንጂ ሌላ ምን እላለሁ ስትረዳኝ ባይኖቼ ስላየሁ ተባረክ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ ስታግዘኝ ባይኖቼ ስላየሁ singer kaleab teklil
Show all...
“በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤” — ገላትያ 3፥13
Show all...
🗣 ስቀለው? ስቀለው? በማን ሀጥያት ማንን? በእኛ መተላለፍ እርሱን? አይሁዱ ካህኑ አለቆች በሙሉ በአንድነት ሲጮኹ ስቀለው እያሉ እርሱን ስቀልና በርባንን ፍታልን ወንበዴውን ለቀህ ጨዋውን አጥፋልን እያሉ ሲከሱት ዝም አለ እንደ በግ ጠላትነት ቀርቶ ወዳጅነት ሊያደርግ ተበዳይ ነዉ እሱ አይደል በደለኛ ተበድሎ ወዳጅ ይሞታል ስለእኛ . . ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው ➥ @CHRIST_TUBE@CHRISTFAMILY
Show all...
❤️#የኢየሱስ_መስቀል_እና_ትንሳኤ❤️ ================================= ✍️የኢየሱስ መስቀል አሮጌው ነገር እና ለእግዚአብሔር የማይታዘዘው አመጸኛው የሕይወት ስርዓት ፍጻሜ ያገኘበት ሲሆን፣ የበክርስቶስ ትንሳኤ ደግሞ የእግዚአብሔርን ሕይወት የተካፈለው አዲሱ ፍጥረት ከሕይወት ስርዓቱ ጋር ወደ ሕልውና የመጣበት ነው። ✍️2 ቆሮንቶስ 5፡17 ስለዚህ ማንም #በክርስቶስ ቢሆን #አዲስ ፍጥረት ነው፤ #አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 📌ኢየሱስ ለማርታ ትንሣኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ ብሏል ዮሐ 11:25 ስለዚህ ትንሣኤ አመት ጠብቀን የምናከብረው ቀን ሳይሆን ማንነት ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ♦️የኢየሱስ #መስቀል የአሮጌው ፍጥረት መጨረሻ ሲሆን ✍️የክርስቶስ #ትንሳኤ የአዲሱ ፍጥረት መጀመሪያ ነው። 2ቆሮ 5፡17. ♦️የኢየሱስ #መስቀል ከአሮጌው አዳም ጋር ላንገናኝ በሞት የተለያየንበት ሲሆን ✍️የክርስቶስ #ትንሳኤ ከክርስቶስ ጋር አንድ የሆንበት ነው።ሮሜ 6, ሮሜ 7፡1-4, አፌ 2፡4-, ♦️የኢየሱስ መስቀል ከሙሴ ህግ ጋር ላንገናኝ በሞት የተለያየንበት ሲሆን። ✍️የክርስቶስ #ትንሳኤ የህይወት መንፈስ ህግ ከሆነው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተገናኘንበት ነው።ሮሜ 7:4-6 ♦️የኢየሱስ #መስቀል ሃጥያት የተቀጣበት ሲሆን ✍️የክርስቶስ #ትንሳኤ ፅድቃችን የተረጋገጠበት እና በእግዚአብሔር ፊት ሃጢአት አልባ የሆንበት ነው።2ቆሮ 5፡21 ♦️የኢየሱስ #መስቀል እርግማን የተወገደበት ሲሆን ✍️የክርስቶስ #ትንሳኤ በመንፈስ እና በስጋ የተባረክንበት ነው። ገላ 3፡13 , ኤፌ 1፡4 ♦️የኢየሱስ #መስቀል በሽታ የተወገደበት ሲሆን ✍️የክርስቶስ #ትንሳኤ የክርስቶስ ጤና ለኛ የተቆጠረበት ነው።ኢሳ53 , 1ጴጥ 2፡24-25. ♦️ የኢየሱስ #መስቀል ከዲያብሎስ የጭቆና አገዛዝ ነፃ የወጣንበት ሲሆን ✍️የክርስቶስ #ትንሳኤ ነጻነታችን የታወጀበትና ብርሃን ወደሆነው ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት የፈለስንበት ነው። ቆላ 1:13-,1ጴጥ 2:9 ♦️የኢየሱስ #መስቀል አለቅነት እና ስልጣናት የተሻሩበት ሲሆን። ቆላስይስ 2፡15 ✍️የክርስቶስ #ትንሳኤ በጠላት ሀይል ሁሉ ላይ ባለስልጣን ለመሆን ስልጣን የተቀበልንበት ነው። ማቴ 28፡18-20,ሉቃ 10፡19 ♦️የኢየሱስ #መስቀል አባት ከልጁ ከኢየሱስ ፊቱን ያዞረበት የተወው ሲሆን። መዝ 22፡1 ✍️የክርስቶስ #ትንሳኤ አባት እኛን የተቀበለበት እና አለቅህም ከቶም አልተውህም ያለበት ነው። ዕብ 13፡5 ♦️ የኢየሱስ #መስቀል ኢየሱስ አምላኬ አምላኬ ብሎ የጮኅበት ሲሆን። መዝ 22፡1 ✍️የክርስቶስ #ትንሳኤ አባ አባት ብለን የምንጮህበት የልጅነት መንፈስ የተቀበልንበት ነው። ሮሜ 8፡14-17 ገላ 4፡5-7 ♦️የኢየሱስ #መስቀል የዘር፣ የነገድ እና የቋንቋ ልዩነት የጠፋበት ሲሆን ✍️የክርስቶስ #ትንሳኤ አማኝ ሁሉ አዲስ ፍጥረት እና ሰማያዊ ዜጋ የሆንበት ነው። ራዕ 5፡10-, ፊሊ 3፡20 ኤፌሶን 1 (Ephesians) 20-21፤ ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤ 1 ጴጥሮስ 1 (1 Peter) 3-5፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ፀጋ እና ሰላም ለሁላችን ይብዛ። የወንጌል እውነት አገልግሎት ጅማ Gospel Truth Ministry Jimma. https://scontent.fadd1-1.fna.fbcdn.net/v/t39.30808-6/278773344_5002124786569728_8268231661799014791_n.jpg?stp=dst-jpg_p526x296&_nc_cat=104&ccb=1-5&_nc_sid=8bfeb9&_nc_ohc=Tled4QVv2ewAX-qH6_w&_nc_ht=scontent.fadd1-1.fna&oh=00_AT8PrdaXDFA9mvkqjsFuFWtwBlCDzw9vTxDVFHoQIaxmdg&oe=6265C6A3
Show all...
““ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንደሚሆን ታውቃላችሁ፤ የሰው ልጅም ሊሰቀል አልፎ ይሰጣል” አላቸው።” — ማቴዎስ 26፥2 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
“ልባቸው ንጹሕ የሆነ ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና።” — ማቴዎስ 5፥8 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
ደስታ፦ ያሰቡት ሲሳካ፣ የፈለጉትና የሚሹት ሲሆን፣ ፀሎታችን ሲሰማና ምላሹን ስናይ አይደለም ለደስታችን ምክንያቶች ናቸው እንጂ ደስታ አይደሉም።#ደስታ አንድ ቀን ብቅ ብሎ የሚጠፋ፣ በሁኔታዎች መሳካት የሚመጣ ባለመሳካት ደግሞ የሚጠፋ ሳይሆን በእኛ ውስጥ ለሁሌና ለዘላለም የሚቀመጥ የሁኔታዎች መሳካትም ሆነ አለመሳካት ሊሽረው የማይችል ከሁለንተናችን ጋር ተቆራኝቶ ተጣብቆ የሚኖር የሚጠፋ ሳይሆን ይልቁንስ እየጨመረ የሚኖር #ከጌታ_የተሰጠን😍#እራሱ_ክርስቶስ_እየሱስ_ነው_ደስታችን!!!! #ደስታ፦የክርስቶስ እየሱስ መኖር እና መገኘት ነው። ደስታችን ሰላማችን ጌታ በእኛ ዘንድ መኖሩና የእርሱ መኖር ነው። “ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።” — ፊልጵስዩስ 4፥4
Show all...
“ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?” — መዝሙር 139፥7 (አዲሱ መ.ት) “Whither shall I go from thy spirit? or whither shall I flee from thy presence?” — Psalms 139:7 (KJV) መዓዛህን ከሚያስናፍቀኝ፣ ከአንተ የሆነውን ከሚያሳውቀኝ ፣ ስለ አንተ ከሚያወራኝ፣ ወደ እውነት ሁሉ ከሚመራኝ፣ ከአንተ መልካም መንፈስ #መንፈስ_ቅዱስ_ከአንተ_ወዴት_እሔዳለሁ?!
Show all...
ፀልዩ በዚች ምድር ላይ ስትኖሩ በየእለቱ አንድ ነገር ማድረግ ይኖርባቿል እርሱም መፀለይ ነው፤ ኢየሱስ ቀኑን ሙሉ ካገለገለ በኋላ ደከመኝ ሳይል ለሊቱን ደግሞ ብቻውን ወደ ተራራ ወጥቶ አብዝቶ ይፀልይ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፤ አብዝቶ መፀለይን ያስተማረን ኢየሱስ ነው፤ የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች ሴጣን የተሳካለት እናንተን ፀሎት ያስቆማቹ እለት ነው፣ ስለዚህ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ መፀለይን የሚያክል ትልቁን ሀብታቹን በፍፁም በጠላት እንዳታሰርቁት ፤ ብቻ ዝም ብላቹ በብርቱ ፀልዩ ድንገት ሳታውቁት የአምላካቹ የእግዚአብሔር ፊት በእናንተ ላይ ማብራት ይጀምራል። ጌታ ዘመናቹን ይባርክ @winnerswaytv
Show all...
“በድነታችሁ እንድታድጉ፣ አዲስ እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹሑን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤” — 1ኛ ጴጥሮስ 2፥2 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
ዘዳግም 4 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁹ ነገር ግን እዚያም ሆናችሁ አምላካችሁን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ብትፈልጉት ታገኙታላችሁ። ³⁰ ስትጨነቅና ይህ ሁሉ ነገር ሲደርስብህ ያን ጊዜ፣ በኋለኞቹ ዘመናት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ትመለሳለህ፤ ትታዘዝለታለህም። ³¹ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) መሓሪ አምላክ (ኤሎሂም) ነውና፣ አይተውህም ወይም አያጠፋህም፤ ወይም ደግሞ ለአባቶችህ በመሐላ ያጸናላቸውን ቃል ኪዳን አይረሳም።
Show all...
እግዚአብሔር እንደ ልቤ ይበላችሁ ፤ አንደ ልቡም የሚመላለስ ልብን ይስጣችሁ!!!አሜን። እንደ ልብህ አርገን። አሜን “ሳኦልንም ከሻረው በኋላ፣ ዳዊትን አነገሠላቸው፤ ስለ እርሱም፣ ‘እንደ ልቤ የሆነና እኔ የምሻውን ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ’ ሲል መሰከረለት።” — ሐዋርያት 13፥22 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
“አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።” — ኢሳይያስ 61፥10
Show all...
የዕለት ስንቅ የመንፈስ ሰይፍ ( Sword of the spirit) “የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ ፣ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።”( ኤፌ 6 ፥¹⁷) ። በኤፌሶን ምዕራፍ 6 ውስጥ ከተዘረዘሩት መንፈሳዊ የጦር እቃዎች መካከል የመንፈስ ሰይፍ የተባለው የጦር ዕቃ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ በግልጽ ተነግሮናል ። በዚህ ክፍል ላይ: - " ቃል " ተብሎ የተጠቀሰው በግሪኩ :- " ሬማ ፣ rhema " ተብሎ ተቀምጧል። ይህ በአዲስ ኪዳን በተደጋጋሚ የተወሳ እጅግ መልካሙ አሳብ ነው። ይህ ቃል:- የተጻፈ ቃል ወይም ሎጎስ ( written word or logos) ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ የጊዜው ቃል ወይም quickened word ነው። ቃሉ ከመንፈስ ድምጽ ስለሚሰጠን ጥርጥርን፣ ስህተትን ፣ ጥያቄን በማያስተናግድ እርግጠኝነት ለመንፈሳችን ይቀርባል። የመንፈስ ሰይፍ የሚለው ይህንን ነው። " ያዙ !" የሚለው አሳብ መንፈስ ቅዱስ ሬማን ሲሰጠን ከመተላለፍ ይልቅ ቶሎ መያዝ እንደሚገባን ያመለክተናል ። ይህ: የእግዚአብሔር ቃል ( ሬማ) : - “ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤” ተብሎ የተነገረለት ብርቱ ነው። ( ዕብ 4፥¹² ) በሬማ ወቅት የእኛ ሁለንተናችን በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ስለሚሆን ጠላት የማይቋቋመን እንሆናለን። ዮሐንስም ስለሬማ ቃል እንዲህ በማለት ጽፏል: - " ጐበዞች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።” ( 1ኛ ዮሐ 2፥14) ። ሬማ ቃል:- በተወሰነ ጊዜና ለተወሰነ ዓላማ በመንፈስ ቅዱስ ለልባችን( ለመንፈሳችን) የሚሰጥና እንዲህ ነው ተብሎ ሊነገር የማይችል አስደናቂ ለውጥን የሚያመጣ ነው። ስለሆነም ጌታ ራሳችን ላይ በሚከናወን መንፈሳዊ ጉብኝት እና አቅም የጠላትን ጉልበት ስለሚያፈርስ ሬማ በእጃችን ላይ እንዳለ የመንፈስ ሰይፍ ሆኖ ታውጇል። ሬማ ቃል ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንዳለን ጠንካራ ሕብረት ልንቀበለው የምንችለው ቃል ሲሆን ተጽእኖውም ሁለንተናዊ :- ማለትም መንፈሳዊ ፣ አእምሮአዊ፣ አካላዊ ውጤትን ይዞ ሊመጣ የሚችል ነው። ሬማ ቃል ደማቅ ብርሃንን ስለሚያካፍለን የጠላትን ምክር በመግለጥ ምን ማድረግና ወደየት መሄድ እንዳለብን በማሳየት ምሪትን ይሰጠናል። ድልና ምሪት ከሬማ ቃል የምናገኘው ነው። ይሁን እንጂ ሬማ ራሱን የሚገልጠው ከሎጎስ ( ከተጻፈው ቃል) ውስጥ ነው። ያለ ሎጎስ ሬማን መጠበቅ ከቶ ሊታሰብ የሚችል ነገር አይደለም። ያለንበት የሕይወት ውጣ ውረድና መንፈሳዊው ጦርነት ምንም ያህል ሊሆን ይችላል።እውነተኛ መንፈሳዊ ሰው ከሆንን ያለበትን ሁኔታ ሁሉ የምናልፍበትና ድል የምንነሳበት ሬማ ቃል ሲሰጠን እኛ ራሳችን በመንፈሳችን እናውቀዋለን። ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን! አገልጋይ ቃለአብ ካሳዬ
Show all...
✨ በእንግድነት በምንኖርባት በዚህ ዓለም በእንግድነት እንኖር ዘንድ ፍቃዱ ለሆነው ለእርሱ የእሱን ነገር ለእርሱ አሳልፈን የምንሰጥበት ግዜው ነው። #እግዚአብሔር በመጀመሪያም በመጨረሻም እንሰጠው ዘንድ የሚፈልገው እራስህን/ሽን እንሰጥ ዘንድ ነው። ✨ልጅነትህን ✨ወጣትነትህን ✨ጎልማሳነትህን አሳልፈ ትሰጠው ዘንድ ጌታ ይፈልጋል !!! “ወጣትነትህን ማንም አይናቅ፤ ነገር ግን ለሚያምኑት በንግግርና በኑሮ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ሁንላቸው።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥12 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
“ራሳችሁን እንደ ባሪያ አድርጋችሁ ስታቀርቡ፣ ለምት ታዘዙት ለእርሱ፣ ይኸውም ወደ ሞት ለሚወስደው ለኀጢአት ወይም ወደ ጽድቅ ለሚያደርሰው ለመታዘዝ ባሮች እንደሆናችሁ አታውቁምን?” — ሮሜ 6፥16 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
“መልካም ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ነገር በጎ ነገር ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ካከማቸው ክፉ ነገር መጥፎ ነገር ያወጣል።” — ማቴዎስ 12፥35 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
መዝሙር 36 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁷ አቤቱ፥ ምሕረትህን እንዴት አበዛህ! የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ። ⁸ ከቤትህ ጠል ይጠጣሉ፥ ከተድላም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ። ⁹ የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን። ¹⁰ ምሕረትህን በሚያውቁህ ላይ፥ ጽድቅህንም ልባቸው በቀና ላይ ዘርጋ።
Show all...
ኤፌሶን 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³ በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን። ⁴ ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ⁵ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥
Show all...
ኤፌሶን 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ⁴ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በእርሱ መርጦናልና። በፍቅር፣ ⁵ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን፤ ⁶ ይኸውም፣ በሚወደው በእርሱ በኩል በነጻ የተሰጠን ክቡር የሆነው ጸጋው እንዲመሰገን ነው። ⁷ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ባለጠግነት መጠን፣ በደሙ በተደረገ ቤዛነት፣ የኀጢአትን ይቅርታ አገኘን፤ ⁸ ጸጋውንም በጥበብና በማስተዋል ሁሉ አበዛልን። ⁹ በክርስቶስ ያቀደውንም የፈቃዱን ምስጢር እንደ በጎ ሐሳቡ እንድናውቅ አደረገ። ¹⁰ በዘመን ፍጻሜ ይሆን ዘንድ ያለው ሐሳቡ በሰማይም በምድርም ያሉትን ነገሮች ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ ሥር ለመጠቅለል ነው። ¹¹ ሁሉን በፈቃዱ ምክር መሠረት እንደሚሠራው እንደ እርሱ ዕቅድ አስቀድሞ የተወሰንን እኛ ደግሞ በእርሱ ተመርጠናል፤ ¹² ይኸውም በክርስቶስ ተስፋ በማድረግ የመጀመሪያ የሆንነው እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው። ¹³ እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል ይህም የድነታችሁን ወንጌል በሰማችሁ ጊዜ ወደ ክርስቶስ ተጨምራችኋል፤ አምናችሁም፣ በእርሱ በመሆን ተስፋ ሆኖ በተሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ማኅተም ታትማችኋል። ¹⁴ ለክብሩ ምስጋና ለመሆን የእግዚአብሔር የሆኑት እስኪዋጁ ድረስ፣ እርሱ ለርስታችን ዋስትና የሚሆን መያዣ ነው።
Show all...
ማርቆስ 13 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፣ “መምህር ሆይ፤ ድንጋዮቹ እንዴት እንደሆኑ፣ ሕንጻውም እንዴት ውብ እንደሆነ እይ” አለው። ² ኢየሱስም መልሶ፣ “እነዚህን ታላላቅ ሕንጻዎች ታያለህን? አንዱ ድንጋይ በሌላው ላይ እንደሆነ አይቀርም፤ ሁሉም ፈራሽ ነው” አለው። ³ ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ትይዩ፣ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስና እንድርያስ እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤ ⁴ “ይህ መቼ እንደሚሆን ንገረን፤ የዚህስ ሁሉ ፍጻሜ ምልክቱ ምንድን ነው?” ⁵ ኢየሱስም እንዲህ ይላቸው ጀመር፤ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ ⁶ ብዙዎች፣ ‘እኔ እርሱ ነኝ’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። ⁷ ስለ ጦርነትና ስለ ጦርነት ወሬ በምትሰሙበት ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህማ መሆን አለበት፤ ፍጻሜው ግን ገና ነው። ⁸ ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ በብዙ ቦታም የመሬት መንቀጥቀጥና ራብ ይሆናል፤ እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። ⁹ “ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ለአካባቢ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ በምኵራብ ይገርፏችኋል፤ ምስክር ትሆኑም ዘንድ በእኔ ምክንያት በገዦችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ። ¹⁰ አስቀድሞ ግን ወንጌል ለሕዝብ ሁሉ መሰበክ አለበት። ¹¹ ተይዛችሁ ለፍርድ በምትቀርቡበት ጊዜ፣ በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ እንጂ ምን እንናገራለን በማለት አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ እንጂ እናንተ አይደላችሁምና። ¹² “ወንድም ወንድሙን፣ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆች በወላጆቻቸው ላይ ያምፃሉ፤ ይገድሏቸዋልም። ¹³ በእኔ ምክንያት በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን ይድናል። ¹⁴ “ ‘የጥፋት ርኵሰት’ ስፍራው ባልሆነ ቦታ ቆሞ በምታዩት ጊዜ አንባቢው ያስተውል፤ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤ ¹⁵ በቤቱ ጣራ ላይ ያለ አይውረድ፤ ንብረቱንም ለማውጣት ወደ ቤቱ አይግባ፤ ¹⁶ በእርሻ ቦታ ያለ ልብሱን ለመውሰድ አይመለስ። ¹⁷ በእነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው! ¹⁸ ይህም በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፤ ¹⁹ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ፍጥረትን ከፈጠረበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ፣ እንዲሁ ደግሞም ወደ ፊት አቻ የሌለው ታላቅ መከራ ይሆናልና። ²⁰ ጌታ ቀኖቹን ባያሳጥራቸው ኖሮ ማንም ባልዳነ ነበር፤ ስለ መረጣቸው ስለ ምርጦቹ ሲል ግን ቀኖቹን አሳጥሮአል። ²¹ በዚያን ጊዜ ማንም፣ ‘እነሆ፤ ክርስቶስ እዚህ ነው?’ ቢላችሁ ወይም፣ ‘እነሆ፤ እዚያ ነው’ ቢላችሁ አትመኑ። ²² ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ተነሥተው፣ ምልክቶችንና ድንቆችን በማድረግ፣ ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ ያስታሉ። ²³ ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ጊዜው ሳይደርስ ሁሉን ነግሬአችኋለሁ። ²⁴ “በዚያን ጊዜ፣ ከመከራው በኋላ ‘ፀሓይ ትጨልማለች፣ “ ‘ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ²⁵ ከዋክብት ከሰማይ ይረግፋሉ፤ የሰማይ ኀይላትም ይናወጣሉ።’ ²⁶ “በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በታላቅ ኀይልና ግርማ በደመና ሲመጣ ያዩታል። ²⁷ እርሱም መላእክቱን ልኮ ከአራቱ ነፋሳት፣ ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማያት ዳርቻ ምርጦቹን ይሰበስባል። ²⁸ “ምሳሌውን ከበለስ ተማሩ፤ ቅርንጫፏ ሲለመልም፣ ቅጠሏ ሲያቈጠቍጥ በጋ እንደ ተቃረበ ታውቃላችሁ፤ ²⁹ እንዲሁ ደግሞ እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸውን ስታዩ እንደ ቀረበ፣ በደጅም እንደሆነ ዕወቁ። ³⁰ እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች እስከሚፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም፤ ³¹ ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም። … ³² “ነገር ግን ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያችም ሰዓት ከአብ በቀር፣ የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ፣ ወልድም ቢሆን፣ ማንም አያውቅም። ³³ ስለዚህ ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፣ ጸልዩም። ³⁴ ይህም ቤቱን ለአገልጋዮቹ ትቶ፣ እያንዳንዱን አገልጋይ በየሥራ ድርሻው ላይ አሰማርቶ፣ በረኛው ነቅቶ እንዲጠብቅ አዝዞ የሄደውን ሰው ይመስላል። ³⁵ እንግዲህ የቤቱ ባለቤት በምሽት ወይም በውድቅት፣ በዶሮ ጩኸት ወይም ጎሕ ሲቀድ እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ፤ ³⁶ ድንገት ሲመጣ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ፤ ³⁷ ለእናንተ የምነግራችሁን ለሰው ሁሉ እናገራለሁ፤ ተግታችሁ ጠብቁ!”
Show all...
ዕብራውያን 7 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁴ ኢየሱስ ግን ለዘላለም የሚኖር በመሆኑ፣ ክህነቱ የማይሻር ነው። ²⁵ ስለዚህ ስለ እነርሱ እየማለደ ሁል ጊዜ በሕይወት ስለሚኖር፣ በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። ²⁶ እንግዲህ ለእኛ የሚያስፈልገን፣ ቅዱስ፣ ነቀፋ የሌለበት፣ ንጹሕ፣ ከኀጢአተኞች የተለየና ከሰማያት በላይ የከበረ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ነው። ²⁷ እርሱም እንደ ሌሎቹ ሊቃነ ካህናት፣ መጀመሪያ ስለ ራሱ ኀጢአት ከዚያም ስለ ሕዝቡ ኀጢአት በየቀኑ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ራሱን በሰጠ ጊዜ፣ ስለ ኀጢአታቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት አቅርቦአልና። ²⁸ ሕጉ ደካማ የሆኑትን ሰዎች ሊቃነ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣው መሐላ ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ሾሞአል።
Show all...
If u like it share it today
Show all...
Join us @Nubegetadesyibelen #if u like it share it today
Show all...
“እናንተ ወደ እግዚአብሔር ብትመለሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቸርና ርኅሩኅ ስለ ሆነ ወንድሞቻችሁና ልጆቻችሁን በማረኳቸው ዘንድ ምሕረትን ያገኛሉ፤ ወደዚህች ምድር ይመለሳሉ። እናንተ ወደ እርሱ ብትመለሱ፣ እርሱም ፊቱን ከእናንተ አይመልስም።” — 2 ዜና 30፥9 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
ኢዮብ 28 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁸ ስለ ዛጐልና ስለ አልማዝ አይነገርም። የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍ ይልቅ ይበልጣል። ¹⁹ የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን አይተካከላትም፥ በጥሩም ወርቅ አትገመትም። ²⁰ እንግዲያሳ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው? ²¹ ከሕያዋን ሁሉ ዓይን ተሰውራለች፥ ከሰማይ ወፎች ተሸሽጋለች። ²² ጥፋትና ሞት፦ ወሬዋን በጆሮቻችን ሰማን ብለዋል። ²³ እግዚአብሔር መንገድዋን ያስተውላል፥ እርሱም ስፍራዋን ያውቃል።
Show all...
ውሻ ቢነክስህ መልሰህ ውሻውን አትነክሰውም። በህይወትህ የሚያጋጥሙህን መጥፎ ሰዎች እንዲሁ እለፋቸው። ዝም በላቸውና አንተ ከነሱ የተሻልክ መሆንህን አሳያቸው። #ደግ_ደጉን_የምንሰማበት መልካም ቀን ይሁንልን
Show all...
ክርስትና በማካፈል ሳይሆን በመስጠት ውስጥ ያለ ህይወት ነው።
Show all...
“የሕይወት መገኛ የሆነውን ገደላችሁት፤ እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው፤ እኛም ለዚህ ምስክሮች ነን።” — ሐዋርያት 3፥15 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
“እናንተም የደከማች ሁበትን ዋጋ እንዳታጡ፣ ነገር ግን ሙሉ ሽልማት እንድትቀበሉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።” — 2ኛ ዮሐንስ 1፥8 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
መዝሙር 118 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁸ አንተ አምላኬ ነህ፤ አመሰግንሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ። ²⁹ ቸር ነውና፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ምሕረቱም ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።
Show all...
“ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥11-12 1 Timothy 4 (KJV) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹¹ These things command and teach. ¹² Let no man despise thy youth; but be thou an example of the believers, in word, in conversation, in charity, in spirit, in faith, in purity.
Show all...
በቶሎ ይነበብ ልንነቃ ይገባል ለማንበብ 15 ደቅቃ ብቻ ስጥ ህይወትን ይቀየራል አትሳሳት ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ዓለም ወዴት እየሄደች ነው? 1. - መጽሐፍ ቅዱስን ማቃጠል በኡጋንዳ በይፋ ተረጋግጦአል * በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ፣ ወንድ ወይም ሴት በዝሙት ምክንያት ሌላውን የመክሰስ መብት የለውም *በአሜሪካ እየታየ ያለው የወንድ ለወንድና የሴት ለሴት ጋብቻ *ጀርመን ወንድም እህቱን ማግባት እንደሚችል ፣ አባት ልጁን:እናት ልጆአን የማግባት ፍቃድን መስጠቱ ፡፡ *የmiami ከተማበመንገድ ላይ ፣ በቤተ ክርስቲያን ፣ በገቢያ ፣ በእግር ኳስ ሜዳ ወዘተ ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነት በማንኛውም መንገድ ማግኘት እንዲችሉ መፍቀዶአ .*ካናዳ (ከእንስሳት ጋር የ sexታ ግንኙነትን መፍቀዶአ * በስፔን ውስጥ-የወሲብ ፊልሞች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በዩኒቨርሲቲዎች መፈቀዱ *- ለአካለ መጠን ያልደረሱ ዝሙት አዳሪዎች ፈቃድ ማሪ ሉክ በህግ መፈቀዱ *በመጨረሻም ዩኤስ አሜሪካ የሰይጣንን ቤተ ክርስቲያን ከፍታለች ፡፡ በይፋ። የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች ፣ መጨረሻው ተቃርቧል ፣ ጌታ ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል! ማርታናታ!!! ክርስትያኖች ትኩረታቸው እየተከፋፈሉ ሲሆን ዲያቢሎስ መለኮታዊውን ምህረት ለማስቆም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ነፍሳት ከእርሱ ጋር ሊወስድ ይፈልጋል ፡፡ ደቂቃ ካለዎት ... ይህንን መልእክት ያጋሩ ፡፡ ለምን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንተኛለን ? ስለ እግዚአብሔር ማውራት ከባድ የሆነው ለምንድነው ሐሜት ለመናገር በጣም ቀላል የሆነው ለምንድነው? የእግዚአብሔርን መልእክት ችላ ማለት ለምን ቀላል ሆነ? ይህንን መልእክት ለጓደኞችዎ ይልካሉ ወይም ችላ ይላሉ? እግዚያበሔር “በሰዎች ፊት ብትክዱኝ በአባቴ ፊት እክድዳችሁአለሁ” አለ ፡፡ እግዚያበሔር ከወደዱ ይህንን መልእክት ለምርጥ ጓደኞችዎ እና በቡድን በ 60 ሴኮንድ ውስጥ ያጋሩ ፡፡ እግዚአብሔር ይባርኮት. ኣሜን የአለም መጨረሻ ተቃርቧል አትዘናጉ አሁን ያለንበት 2013 ዓም + 5500 ዘመን=7513 ስለዚህ ከ 8ኛው ሽ ላይ ቀንሱት ። 8000 – 7513= 487 ዓም ይቀራል። ነገር ግን ሰምታችሁ ከሆነ ዘንዶ 400 ዓመት ገዝቷል ይባላል እስኪ ጠይቁ። እና የዘንዶው ሲቆጠር 487 – 400 =87 አመት ቀረው።ትንቢቱም እየተፈፀመ ነው። ሌላው ይህ በንዲህ እንዳለ ደሞ 666 አሁን እዚህ በደጃችን ነው፡፡ አጠንክረን እንፀልይ፡፡ የአውሬው ቁጥር 6 6 6 የሚፈፀምበት የትንቢት ጊዜ አልቋል/ተፈፅሟል፡፡ የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ባስተላለፈው የኦባማን የጤና ሽፋን ረቂቅ በህግ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ የህግ ተግባሩ በቅርቡ ይጀምራል፡፡ ይህን የጤና ሽፋን ረቂቅ በእያንዳንዱ የአሜሪካ ዜጋ የሰውነት ክፍል ላይ ግላዊ የሬዲዬ ፍሪኩዌንሲ ቺፕስ መልክ (RFID CHIPS) እንዲተከል ታዟል፡፡ ይህ ቺፕስ በግንባር ወይም በክንድ ላይ ይደረጋል፡፡ ይህ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው በራዕይ 13 : 15 -18 የተቀመጠውን የአውሬው ምልክት ይፈፀም ዘንድ ነው፡፡ እና አሁንም ስለ ፍፃሜው ትጠራጠራለህ? ታውቃለህ ለኦባማ የተለየ መኪና እንደተሰራ አውሬው የሚባል? ተዘጋጅ ንጥቀት አሁን ይጀምራል፡፡ ራዕይ 13ን ቀድመው ተጫውተውታል፡፡ ብዙዎች ግን ይህን አልተገነዘቡትም፡፡ 1. ለምንድን ነው ይህ ችፕስ ከባንክ አካውንት ጋር የተቆራኘው ወይም የተገናኘው? አስታውሱ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ካለ አውሬው ቁጥር 666 ልትገዙም ወይም ልትሸጡም አትችሉም ስለሚል፡፡ እስኪ ገምቱ ይህ ቺፕስ ከገንዘብ ዝርዝር መረጃ ጋር ለምን ተገናኘ? እንዲያውም በጣም ያሳዘነኝ በቤተክርስቲያን ያሉ ብዙዎች ሰዎች ጌታ ሲመጣ ይህን ሁኔታ ሊያልፉት አይችሉም፡፡ ደግሞም ብዙዎቹ መጨረሻው እንደቀረበ አያውቁም፡፡ የቴክኖሎጂ በጣም መራቀቅ ምክንያት ነው ብላችሁ መልስ እንዳትሰጡኝ፡፡ በማንኛውም የህይወት ጎዳናችሁ ከእግዚአብሔር ጋር ካልተስማማ አሁኑኑ ንሰሀ ግቡና ተለወጡ፡፡ ካለበለዚያ መንግስተ ሰማያትን ካጣችሁት ገሀነምን አታጡትም፡፡ ስለዚህ አስቡበት፡፡ ገሀነም መልካም ስፍራ አይደለም በጣም አስከፊው ክፍሉ እንደ መንግስተ ሰማያት ዘላለማዊነት እንዳለበት እዚህም እንደዛው ነው፡፡ ጆሮ ያለው ይስማ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ይስማ፡፡ ጠቃሚ ያልሆነ ነገር ከምትልኩ ይህን ለሌላው ብታስተላልፉ መልካም ነው፡፡ ለምታውቋቸው ቅርብ ለሆኗችሁ ሰዎች ላኩላቸው፡፡ እስኪ የወንጌላዊ ስራ እንስራ፡፡ እባካችሁ ለምታውቋቸው ለእያንዳንዳቸው በየስማቸው ላኩላቸው፡፡ ለሞባይል እንደምንጠነቀቅ ያክል ለእግዚአብሔር ቃል ብንጠነቀቅ ምን እንደሚሆን ልትገምቱ ትችላላችሁ፡፡ ከዚህ ደግሞ በጭራሽ ልንላቀቅ ነፃ ልንሆን አንችል፡፡ ስለዚህ የቻልነውን ያክል እንትጋ እንጋደል፡፡ 7% የሚሆኑቱ ናቸው መልዕክቱን የላኩት በድጋሚ 93%ቱ ግን አልላኩም አላወቁም ስለዚህ ጠንክረን እንስራ፡፡ ሰይጣን እንዲህ ይላል፡- " የሚገርመኝ ሰው እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ አይታዘዝም እኔን ይጠላኛል ግን ይታዘዘኛል፡፡" ይህን መልዕክት በኋላ እንዳትልኩት አሁኑኑ ላኩት!!! ቢያንስ ለ #15 ሰው እባካችሁ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Show all...