cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Nile Tech News& Apps

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ቴክኖሎጅ ነክ ነገሮችን እንዲሁም አፖችን ያገኛሉ። Group @Grapetechsgroup

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
173Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በብዝሓ ሕይወት ጥበቃ በቀጣዮቹ አስር ዓመታት የብዝሓ ሕይወት ጥበቃን በማዘመን ረገድ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኢንቫይሮሜንታል ዲ.ኤን.ኤ እና ኔትዎርክድ ሴንሰር የተባሉ ቴክኖሎጂዎች ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸው ተጠቆመ፡፡ በተለይም ማሽን ለርኒንግ እና ኮምፒዩተር ቪዥን ከሌሎቹ ቴክኖሎጂዎች ጋር ተጣምረው ዘርፉን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያዘምኑት ይጠበቃል ሲል ዎርልድ ዋይልድ ላይፍ ድረ-ገፅ አስነብቧል፡፡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ከካሜራ እና ከሳተላይት የሚሰበሰቡ መረጃዎችን በመጠቀም ብርቅዬ ዝርያዎችን ለመለየት፣ ክስተቶችን በመተንተን በተለየ ሁኔታ አደጋ ላይ የወደቁ ዝርያዎችን ለማወቅ፣ በብዝሓ ሕይወት ውስጥ የሚገኙ ዝርያዎችን ቁጥር እና ሁኔታ ለመገንዘብ አገልግሎት ላይ ይውላል፡፡ የዘርፉን ሁኔታዎች በመመርመር ለመረዳት እና አስጊ ለሆኑ ከባቢያዊ ተግዳሮቶች መፍትሔ ለመሻት የቴክኖሎጂዎቹ አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ዋይልድ ላብስ የተባለው ተቋም ከኮሎራዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በማይክሮሶፍት እና አርም በተባሉ የቴክኖሎጂ ተቋማት ድጋፍ ባደረጉት የዳሰሳ ጥናትም ቴክኖሎጂዎቹ ለዘርፉ ስላላቸው አበርክቶ ተብራርቷል፡፡ ከሰላሳ ሰባት ሀገራት የተውጣጡ ሁለት መቶ አርባ ስምንት የዘርፉ ባለሞያዎች በዳሰሳው ተሳትፈዋል፡፡ ከተሳታፊዎቹ ዘጠና በመቶ በላይ የሚሆኑት ሦስቱ ቴክኖሎጂዎች በጣም ጠቃሚ ስለመሆናቸው እና የዘርፉን አጠቃላይ ገፅታ የመቀየር አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
Show all...
​​✳️ ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ ብዙዎቻችንን የሚያሳስበንን የBattry Life ጉዳይ አንስተን እንወያያለን። እንደሚታወቀው የስልካችን፣ የታብሌቶቻችን እና ላፕቶፖቻችን ባትሪ ወሳኝ ነገር ሲሆን በሚደክምበት ጊዜ ግን በጣም ችግር ያሳየናል፤ Full እስከሚል አድርገነው እራሱ ብዙም ሳንጠቀምበት ይዘጋል። ግን ለምን? የስልክዎ Battery Life ባትሪ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይበት 5 መንገዶች እንይ፡ 🔺 ባትሪዎ ወደ 0% ወይም 100% እንዳይሄድ ያድርጉት. ◽️ አንዳንዶቻችን የባትሪ ጤንነት ለመጠበቅ ምርጡ መንገድ ሙሉ ለሙሉ ማለትም 100% ቻርጅ ለማድረግ እና ሙሉ ሳይጨርስ አለመሰካት ነው ብለን እናስባለን። ነገር ግን ይህ የአጠቃቀም ዘዴ ለአዲስ ባትሪዎች ይህ መንገድ አይሰራም እናም የባትሪዎን የሙቀት መጠን በመጨመር ዕድሜውን በግማሽ ሊቀንስ ይችላል። ስለዚህ ከፍ ካለ 85% ዝቅ ካለ ደግሞ 25% ቢሆን ይመረጣል። ምክንያቱም የሊቲየም-አዮን ባትሪዎች ሙሉ በሙሉ ሲሞሉ ውጥረት ውስጥ ስለሚገቡ ምርጡ አካሄድ በከፊል መሙላት ነው። 🔺 ከቻሉ ባትሪዎን ቀስ ብለው ይሙሉ ◽️ Fast Charger ቴክኖሎጂዎች ጊዜ ቆጣቢ ናቸው ብንል ማንም አይከራከርም። ነገር ግን የባትሪያችንን ዕድሜ ከፍ ለማድረግ ካሰብን ምናልባት ስንቸኩል ብቻ ብንጠቀምባቸው ይመከራል። ምክንያቱም እነዚህ ቻርጀሮች ስልኮቻችን ከሚፈልጉት በላይ ሀይል በመስጠት ባትሪዎቻችንን ያስጨንቃሉ ይህም የባትሪያችንን እድሜ ያሳጥራል። በሌላ በኩል ባትሪዎን ተመጣጣኝ ሀይል ባለው ቻርጀር በዝግታ መሙላት ጥሩ ነው። 🔺 ቻርጅ የምናደርግበትን ቦታ መምረጥ ◽️ ቅድም ሲል ለማሳየት እንደሞከርነው የስልክ ባትሪዎች ምርትን ጭንቀት አይችልም ስለዚህ ስልካችን ቻርጅ በሚደረግበት ጊዜ ለመጋል ቅርብ ስለሆነ ቀዝቀዝ የሚል ቦታ አስቀምጠን ቻርጅ ማድረግ ይመረጣል። ምክንያቱም ባትሪ በሚግልበት ወቅት ስለሚጎዳ እድሜው ይቀንሳል። 🔺 የማይጠቀሙትን መተግበሪያ መዝጋት ◽️ የሞባይል መተግበሪያዎች ወይም አፖች በምንጠምበት ግዛት እንደስራቸው ቢወሰንም ሁሉም ባትሪ ይጠቀማሉ። ነገር ግን እንዳንድ አፖች የዘጋናቸው ቢመስለንም Background ለይ በመሆን የስልካችንን ባትሪ ብቻ ሳይሆን ራም ይጠቀማሉ ይህ ደግሞ ለስልካችን ባትሪ እድሜ ብቻ ሳይሆን ለስልካችን ፍጥነት ጎጂ ነው። ስለዚህ የማንጠቀምበትን መተግበሪያ በማጥፋት ባትሪ መቆጠብ እንችላለን። 🔺ስልክን ለተወሰነ ጊዜ ማጥፋት፦ ◽️ ሰው ሰርቶ ማረፍ እንደሚፈልገው ሁሉ ስልክን ማጥፋትም ለባትሪው መልካም እንደሆነ ነው ባለሙያዎች የሚገልጹት። ለዚህ ደግሞ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን በተለይም ወደ መኝታ ሲያመሩ በማጥፋት እረፍት መስጠት። ይህ ሲሆን ደግሞ የስልኩ ባትሪ እድሜ እንዳያጥርና ረዘም ላለ ጊዜ እንዲያገለግልዎ ይረዳናል። ◽️ ለተጨማሪ ድጋፍ ምርጥ Battery Saver አፖችን @Habeshan_Apps ለይ ለቀናል አፖቹ በዋናነት Background የሚሰሩ አፖችን በማጥፋት ባትሪ ይቆጥቡልናል በተጨማሪም ሌሎች ወሳኝ ስራዎችን ይሰራሉ አውርዳችሁ ተጠቀሙ። 🏷 ጥያቄ ወይም አስተያየትዎን 👥: @Habeshan_Techs 🤖: @Habeshan_Robot
Show all...

የሰው ልጆች ለኤልያኖች የላኩተ የድምፅ እና የምስል መረጃ። ከ44 ዓመት በፊት የኛ ዩንቨረስ ማለቂያ የለሽ መሆኑን የተረዱት ሳይንቲስቶች ሁለት እስፔስ ክራፍቶችን ዝንብለው እስከመጨረሻ ድረስ እንዲሄዱ በማሰብ ቮያጀር አንድ እና ቮያጀር ሁለት የተሰኙ እስፔስክራፍቶችን ዲዛይን አደረጉ ነገረ ግን ዝንብለው እንዲሄዱ አልፈለጉም ነበር እስፔስክራፍቶቹም ሰለ ሰው ልጆች እንዲውም ሰለኛ አለም ሙሉ መረጃን ይዘው እንዲቀሳቀሱ አድርገዋቸዋል የሳይንቲስቶቹ ሀሳብ እንዚህ እስፔስ ክራፍቶች ዝንብለው ሲሄዱ ባጋጣሚ ኤልያኖችን ካገኟቸው ስለኛ መኖር መረጃ እንዲሰጧቸው በማሰብ ነበር። እስፔስክራፍቶቹ ሰለኛ አለም የያዙት መረጃ ምንድነው ሚሞሪው ወይም ዲስኩስ ከምን ተሰራ? መረጃው የተቀመጠው እስፔስክራፍቶቹ ላይ ከተገጠመ የድሮ ዲስክ ላይ ነው ዲስኩ መያዝ የሚችለው ወይም ጠቅላላ የመያዝ አቅሙ 65.5kb ቢሆንም 155 ምስሎችን እና ከ55 በላይ የድምፅ ቅጂዎችን ይዟል ወደ አሰራሩ ስንመጣ ኮፐር ላይ ወርቅን በማቅለጠ ከላይ የሚታየውን አካላ በወርቀ በመቀባት ነው ወይም በእንግልዘኛው አጠራር "gold-plated copper" የምንለው አይነት ዲስክ ነው። ዲስኩ ከጫፍ ጫፍ 30cm ስፍት አለው ሌላው ቅጂው እንዲሸፈን (cover) የተደረገው በአልሙንዬም እና ዪራኒዬም-238(uranium-238) በሚባሉ ማሀድኖች ነው ይሄም ማለተ ቅጂው ምንም ሳይሆን ቢልዬን አመታትን መቆየተ ይችላል። ይሄ ዲስክ ሰለኛ አለም ቁልፍ ቁልፍ ነገሮችን ይዟል ይሄም መረጃውን ከፍቶ ማየት የሚችል ፍጡር(aliens) እንዲያገኙት እና መረጃውን እንዲረዱት ሳይናሳዊ በሆነ መንገድ የተሰራ ነው። ምክንያቱም ሳይንስ በየትኛውም ቦታ ላይ ተመሳሳይ ነው እንዲውም የፒዚክስ ሕጎች በዚህ ዩንቨረስ ውስጥ በሁሉም ቦታ ላይ ተመሳሳይነት አላቸው ሰለዚህ የኛን ያክል የሰለጠኑ ከሆኑ በቀላሉ ይረዱታል ተብሎ ይታሰባል። በውስጡ ምን ምን ነገሮችን ይዟል የድምፅ ቅጂው የእንስሳት የአዋፍትን እንዲውም የእፃን ልጅን ድምፅ ይዟል ሊላው ደግሞ በ55 ቋንቋዎች የሰው ልጆች መልክት ለኤልያኖች ያስተላልፉበት ቅጂም ተካቷል በተመሳሳይ በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት ጀሚ ካርተረም መልክት ያስተላለፉበት ቅጂም ተካቷል የምስል መረጃዎቹ ደግሞ የመሬትን ገፅታ የሚያሳይ እንዲውም የሰው ልጆችን እና እንስሳዎችን ገፅታ የሚያሳይ ሲሆን በአጠቃላይ የኛን መሬት ገፅታ የሚያሳይ ከ115 በላይ ምስሎች ተካተዋል። እንዚህ ሰለኛ አለም መረጃን ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት እስፔስ ክራፍቶች እስካሁን ድረስ 45 ዓመት ተጉዘዋል በዚህ ጉዙዋቸው ደግሞ ከ20 ቢልዬን በላይ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠዋል እስካሁን ባለውም በሰላም እየተጓዙ ነው የሰው ልጅ ከምድረገፅ ቢጠፍ እንኳን እንዚህ እስፔስክራፍቶች ሰለኛ መኖር ብቸኛ መረጃዎች ሁነው እስከመጨረሻው በዚህ ዩንቨረስ ውስጥ ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል። እንዚህ እስፔስ ክራፍቶች ይዘዋቸው እየተንቀሳቀሱ ያሉትን መረጃ ማየት እና ማዳመጥ ለምትፈልጉ የተወሰኑት ምስሎች እና ቅጂዎች እኛ ጋር ስላሉ እንለቃለን እስከዛው ግን "like" እና "subscribe"👇👇👇 https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1
Show all...

ብዙ ሳተላይቶች ያሏቸው አገሮች ስም ዝርዝር አገር የሳተላይት ብዛት 1. አሜሪካ 1897 2. ቻይና 412 3. ሩሲያ 176 # ቀሪ አገሮች ያሏቸው ሳተላይቶች አንድ ላይ ሲደመር 887 ይሆናል። ከአፍሪካ ግብፅ በአንድኝነት ስትመራ ዘጠኝ ሳተላይቶች አሏት አገራችን ኢትዮጵያ ሁለት ሳተላይት ያላት ሲሆን ይሄም ከአፍሪካ 6 ኛ ላይ ያስቀምጣታል ከአፍሪካ አህጉር ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ12 አገሮች በላይ ሳተላይቶች ያሏቸው ሲሆን ቀሪዎች 35 አገራት እና ከዛ በላይ የሚሆኑት አገራት ደግሞ ምንም አይነት ሳተላይት ጠፈረ ላይ የሏቸውም የዩቲውብ ቻናላችንን subscribe ለማድረግ ወይም የለቀቅናቸውን ቪዲዮዎች ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ👇👇👇👇👇👇👇 https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1
Show all...
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለ ካርድ ከ ኤቲኤም ገንዘብ ማውጣት የሚያስችል አገልግሎት መስጠት ጀመረ ።
Show all...
የግል ዳታ ጥበቃ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው። በየአመቱ ጥር 20 የግል ዳታ ጥበቃ ቀን የሚከበር ሲሆን በግል ዳታ ጥበቃና ደህንነት ዙሪያ ለግለሰቦች፣ ድርጅቶች እና የንግድ ተቋማት ግንዛቤ ለማስጨበት ታልሞ የተዘጋጀ ነው። የዲጂታል ቴክኖሎጂ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ ሰዎች የመረጃ ልውውጣቸውንና የገንዘብ ዝውውራቸውን በዲጂታል መልኩ እያደረጉ ነው። የግል ዳታ አቀናባሪዎችና ተቆጣጣሪዎች ደግሞ የግል ዳታን ይሰበስባሉ፣ ይመዘግባሉ፣ ያደራጃሉ፣ ያዋቅራሉ፣ ያከማቻሉ፣ ይጠቀማሉ፣ በተለያዩ መንገዶ እነዚህን ዳታዎች ለሶስተኛ ወገኖች ይፋ ያደርጋሉ። እነዚህ አካላት የግል መረጃን ሲያቀናብሩ የግል ዳታ ማቀናበር መርሆዎችን ባከበረና የባለቤቶቹን መብት በጠበቀ መልኩ መሆን ይገባል። ኢትዮጵያም የዜጎቿን የግል ዳታ ለማስጠበቅ ይረዳት ዘንድ ጠንካራ የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ እያረቀቀች ትገኛለች። ጠንካራ የግል ዳታ ጥበቃ ስርዓት መኖር ለጤና፣ ለትምህርት፣ ለፋይናንስ፣ ለትራንስፖርት ዘርፍ መጎልበት ትልቅ ጠቀሜታ አለው። መንግሥት ለዜጎች የሚያቀርባቸውን አገልግሎቶች ተደራሽነት ያሰፋል፤ ዕንግልትን ይቀንሳል፣ በሂደትም ያስቀራል፣ ተዓማኒነቱንም ከፍ ያደርጋል። በአደጉ ሀገራት ያሉ የዳታ ተቆጣጣሪዎች የያዟቸውን የግል ዳታዎች በኢትዮጵያ እንዲቀናበር ሁኔታዎችን በማመቻቸት ኢንቨስትመንትን ያበረታታትል፣ የሥራ ዕድልንም ይፈጥራል። ኢትዮጵያ የግል ዳታ ጥበቃ ሥርዓት በመፍጠር፣ ለግል ዳታ ጥበቃ የነቃ ዜጋን በማፍራት፣ የግል ዳታ ጥበቃን የሚያረጋግጡ ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀምን ባህል በማጎልበትና ዓለም አቀፍ ትስስርን በመገንባትና በማስፋት የዲጂታል ኢኮኖሚን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም እየሰራች ትገኛለች። ©በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው።
Show all...
በOpera mini ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ኮኔክሽኑ በጣም ቀርፋፋ ሆኖ ተቸግረዋል? እንዴት በopera mini ላይ የኢንተርኔት ፍጥነቱን መጨመር እንችላለን የሚለውን እናያለን። ከታች የተጠቀሱትን 9 እስቴፓች በመከተል ፈጣን ኢንተርኔት በopera mini ላይ መጠቀም ይችላሉ። step1. በመጀመሪያ Opera miniውን ይክፈቱ። step2. በመቀጠልም Address Bar ውስጥ ገብተው www. የሚለውን ያጥፉ። step3. ከዛም Address Bar ውስጥ opera:config ብለው ይፃፉ። step4. ከዛም Power Settings ይመጣሎታል። step5. የመጀመሪያውን Option "Large placeholders for images" የሚለውን YES ከሆነ NO አድርጉት። step6. ከዚያም ሁለተኛውን Option "Fit text to screen" የሚለውን YES ከነበረ NO ያድርጉት። step7. በመቀጠልም ሶስተኛውን Option 'Loading timeout' የሚለውን 20 ያድርጉት። step8. ከዛም Save የሚለውን በመጫን ይጨርሱ። step9. ከዛም Operaዎትን ዘግተው እንደገና መልሰው በመክፈት ፈጣን የሆነውን ኢንተርኔት ይጠቀሙ። ከተመቾት ለወዳጆት ያጋሩት።
Show all...
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ !!!
Show all...