cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መልካም አስተሳሰብ እና አመለካከት - Positive Thinking and Attitude

እንኳን በደህና መጡ ወደ ጥበብ ገበታ ቤተሰብ:: ቀኖን በጥሩ መንፈስ ማሳለፍ ይፈልጋሉ # እንግዲያውስ ትክክለኛ ቦታ መተዋል በኛ ቻናል 1.የቀኑ ማነቃቅያ የዕውቀት ምግቦች: ድብርትን የሚያጠፉ ሀሳቦች:አውንታዊ አመለካከት 2.የራስ ጤና በራስ ለማከም የምረዱ ጥበቦች 3.የውስጣዊ ዓይን እይታ ማከምያ ሰነልቦናዊ ጥበቦች የመሳሰሉት ሀሳቦችን ያገኛሉhttps://t.me/PThinkingAttitude100

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#የህይወት_ወርቃማ_ህጎች #1 #ማድረግ_የምትፈልገውን_አድርግ በሙያህ ላይ፥ በእድገትህ ላይ፥ በባህሪህ ላይና በራስህ ላይ ትኩረት አድርግ፨ በመካከል ሌሎች ምኞቶች እንዲገቡ አትፍቀድ፨ በራስ የመተማመን መንፈስ ይኑርህ። #አካላዊ_እና_አእምሯዊ_ጤንነትህን_እንደ_ውድ_ሀብት_ቁጠር። የአእምሮ ጤንንት ልክ እንደ አካላዊ ጤንነት አስፈላጊ ነው። ስለዚህ፥ የአእምሮ ጤንነትህን ተንከባከብ፤ ውጥረትና ጭንቀት ካጋጠመህ፣ እርዳታ አግኝ፣ ወይም የአዕምሮ ጭንቀትህን ለመቆጣጠር አንዳንድ የራስ አገዝ መጽሃፎችን አንብብ። #ለራስህ_ታማኝ_ሁን_እና_እራስህን_በደንብ_ተንከባከብ ራስህን በጥሩ ሁኔታ ለመንከባከብ፥ ለትክክለኛ ጉዳዮችህ እውቅና መስጠትና በእነሱ ላይ መስራት ያስፈልግሃል፨ #በየጊዜው_ከምታገኛቸው_ሰዎች_ሁሉ_ጥሩ_ልማዶችን_ተማር በየቀኑ በጠዋቱ በእግርህ ስትጓዝ፥ ጂምናዚየም ስትሄድ፣ አውቶብስ ላይ፥ በስራ ቦታ፣ በኮሌጅ፣ በካፌና በሬስቶራንት ከብዙ ሰዎች ጋር ትገናኛለህ። የምታገኘው እያንዳንዱ ሰው ልንማርበት የምንችለው ቢያንስ አንድ ልዩ ጥሩ ልማድ ወይም ባህሪ አለው። ስለዚህ ከሁሉም ሰው ለመማር ሞክር፨ #ለሌሎች_እና_ለራስህ_ደግ_ሁን የምንቀበለው የምንሰጠውን ነው ስለዚህ ለምታገኛቸው ሰዎች ሁሉ ደግ ሁን። ለሌሎች ደግ ስትሆን ግን ለራስህ ደግ መሆንን አትርሳ። አንድ ነገር ባሳካህ ወይም ጥሩ ነገር በሰራህ ጊዜ ራስህን አመስግን ወይም ለጥሩ ስራህ ራስህን አድንቅ። ምንጭ:ወርቃማ_ሕጎች መጽሐፍ
Show all...
ፅናት ይኑርህ! ፨፨፨////፨፨፨ ሰሚ ባጣህ፣ ጆሮ በተነፈክ ሰዓት ፅናት ይኑርህ፤ ትኩረት ባልተሰጠህ፣ ተመልከች ባጣህ ጊዜ ፅናት ይኑርህ። አዎ! ለሰዎች እየለፋህ፣ ለሰዎች እየጣርክ፣ እየደከምክ ሰዎች ችላ ሊሉህ ይችላሉ፣ ሰሚ፣ አዳማጭ ላታገኝ ትችላለህ፣ አንድም አስታዋሽ፣ አንድም ተመልካች በሌለበት በብዙ እጥፍ ልትደክም ትችላለህ። አበረታች ስትፈልግ አታገኝም፤ አጋዥ ስትመኝ አይኖርህም፤ ከጎንህ የሚቆም፣ በሃሳብህ የሚስማማ ባንተ የሚተማመን ሰው ፈልገህ ልታጣ ትችላለህ። አዎ! ጀግናዬ..! ፅናትህ የሚፈተነው በዚህ ሰዓት ነውና ፅናት ይኑርህ፤ ታግሽ ሁን፤ በቶሎ እጅ አትስጥ፤ አትረበሽ፤ አትታወክ፣ ተስፋ አትቁረጥ። በብቸኝነት ስሜት ከመዋጥ እራስህን አውጣ፤ ማንም የለኝም አትበል። አጋዥ ብታገኝ፣ ረዳት ቢኖርህ መልካም ነበር ነገር ግን ባይኖርህም እርሱ ከመንገድህ አያስቀርህም። ያሰብከው ብቻህን መሆኑን እንዳትዘነጋ። አዕምሮህ ሲጠግብ፣ ሲመቸው፣ በእራስ መተማመን ሲኖረው፣ የነገውን መልካም ውጤት መመልከት ሲችል ፅናት ይኖርሃል፤ ቢደክምህም ትለፋለህ፤ ቢያምህም ትችለዋለህ፤ ቢሰለችህም ትጋፈጠዋለህ፤ ቢከብድህም ታደርገዋለህ። አዎ! የማይሆኑ ተስፋ አስቆራጭ ቃላት በሰማህ ቁጥር ውስጥህን አትረብሸው፤ ትረትህን የሚጎዳ አላስፈላጊ ሃሳብ ቢሰጥህም ያለእርሱ ማደግ እንደማትችል አስብ። ሳትተች ሙገሳ ላይ አትደርስም፤ ሳትነቀፍ ለአድናቆት አትበቃም፤ ሳትሰደብ ከበሬታን አታገኝም፤ ሳትዘለፍ ብርቱ ወዳጅ አታፈራም፤ አዎ! የሚደርስብህን አሉታዊ ጫና ሁሉ ዋጥ አድርገው፣ ተቀበለው፤ ቅስምህን ከመስበሩ በፊት አንተ እዛው ሰብረህ አስቀረው፤ ተስፋህን ከማጨለሙ፣ ራዕይህንም ከማደብዘዙ በፊት ተስፋህን አግዝፍበት፤ ራዕይህን አርቅቅበት። ማንም ቢያወራ ግድ አይኖርህም፤ ሰው ውስጡ ያለውን፣ እራሱ ያመነበትን ብቻ ያወራልና ማንም አለመቻልህን ቢነግርህ ያንተን ሳይሆን የእራሱን አለመቻል በሚገባ ተረዳው። ብዙ ጅምር ስራዎች ከነበሩት አንተም እንዲሁ ትመስለዋለህ፤ ያንተን ፅናትና ጥረት በእራሱ ልምድ ሊለካ ይሞክራል። አንተ ግን እርሱ እንደማይሆን፣ እንደማይሰራ አረጋግጥለት። አንገትህን ደፍተህ ስራ፤ አቀርቅረህ ለህልምህ ኑር፤ በጊዜው እርሱ ያሳልፍልሃል፤ እርሱ ቀና ያደርግሃል፤ በንቀት ላይ ያረማምድሃል፤ በሳቅ፣ በስላቅ ላይ ያሻግርሃል፤ ትቺት፣ ዘለፋን ሰብስቦ ያስወግድልሃል፤ ያንቋሸሹህን ያዋርድልሃል፤ ያበረቱህን ያኮራቸዋል። አዎ! በፅናት ታገል፤ ጠንክረህ ስራ፤ ውስጥህን ለማርካት፣ ፍላጎትህን ለመሞላት ተፋለም፤ ብትመታም፣ ብትጎዳም፣ ብታዝንም፣ ብትሰበርም ከአሸናፊነት ዞር አትበል፤ ፅናት ይኑርህ፣ ድልም አድርግ።. ✍️ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! መልካም ቀን ይሁንልን!😍❤🙏
Show all...
በሀዘን ውስጥ ፈገግታ 😭😍🤔😍🤐💏🧑‍🤝‍🧑🤭🤦‍♂️😍 የምትበላው መኖር ስላለብህ፣ የምትለብሰው አበደ እንዳይሉህ፣ የምታፈቅረው ስለሚያሳዝኑህ፣ የምትረዳው ሕሊና ፀጥ እንዲልልህ ሊሆን ይችላል። እንደ ማሽላ እያረሩ መሳቅ ውስጥህን ጎድቶት ይሆናል። ምስጥ እንደበላው እንጨት ላይህ ገዝፎ ትንሽ ሲነኩህ የምትወድቅ ሆነህ ይሆናል። ስለገባው ገቢ እንጂ ስለወጣው የማያውቁ ምቀኛ ጎረቤቶች ያበሳጩህ ፣ ሁሉም ነገር አልጥም ብሎህ በግድ የምትኖር ሰው ሆነህ ይሆናል። እንዲህ የምሆነው የመረጥኩትና የሰለጠንኩበት ትምህርቴ አሊያም በቀደመ አስተሳሰቤ ያገቧኋት ሚስቴ ትክክለኛ ምርጫዬ ስላልሆኑ ነው እያልክ ትታመስ ይሆናል። ዛሬ ስታገኝ የድህነት ሚስትህና ጓደኞችህ ያን ክፉ ቀን መስለውህ ይሆናል። በምትኩ ደግሞ በሽንገላ ፍቅር አብደህ ይሆናል። ሲገባ ሰፊ ሲወጣ ጠባብ በሆነው ፣ ማላመጥ እንጂ መዋጥ በሌለበት ፖለቲካ ውስጥ ገብተህ በሩ ጠፍቶህ እየተቆለጨለጭክ ይሆናል። አርፍበታለሁ ብለህ የገነባኸው ቤትህ ነገር የተጣደበት ምድጃ ሆኖብህ አሊያም የምትወደው ልጅህ በሕመም የሚንገላታበት ሆኖ ወደ ቤትህ የሚወስደውን ጎዳና ስትጀምር እግርህ እያጠረብህ ተቸግረህ ይሆናል። የሞቀው ትዳርህን ስታስብ ከመሐል አንዳችን ብንቀነስ ልጆቹ ምን ይሆናሉ? የሚል ፍርሃት እየወዘወዘህ ሊሆን ይችላል። ብር ካለ በሰማይ መንገድ አለ በሚል ፈሊጥ ተይዘህ ገንዘብ የሁሉም ነገር መልስ መስሎህ ፍቅርን እየገፋህ ገንዘብ ታከማች ይሆናል። የአገሬ ሰው የሚያከብረው ሲወፍሩ ነው ብለህ ጭንቀትህን በምግብ እየተወጣኸው ይሆናል። ገንዘብ ሲመጣ ሰላሜ በየትኛው በር እንደ ወጣ አላውቅም እያልክ ይሆናል። ብዙ ሕዝብ እየወደደህ ይህ ሁሉ ተከታይ ቢከዳኝስ እያልክ ተጨንቀህ ይሆን? ወይስ አመስግና በምትራገመው ዓለም ተራው ደርሶህ ያመሰገነህ ሁሉ ሰድቦ እስኪጨርስ ወረፋው ረዝሞብህ ይሆን? ከክብርህና ከሥልጣንህ የተነሣ እንኳን ጠላቶችህን ወዳጆችህን ማመን ተስኖህ ጥላህን እየፈራህ የምትኖር ሆነሃል? በማያስተማምን ፖለቲካ ቤት ሠርቶ ከባድ ማሽን ተክሎ መኖር እያስጨነቀህ ያላረፈ ልብ ይዘህ ሊሆን ይችላል። ወይም መብራት ጠፍቶ ፣ ጉንዳን ገብቶ ፣ እርሱ ታሞ፣ ሚስቱ ምጥ እንደመጣበት ሰው ሆነሃል? ለነገ የሚሆን በጎተራህ ስለ ሌለ ዕረፍት አጥተህ ይሆን? ብቻህን ለምታወራው፤ ጭር ባሉ መንገዶች ለምታለቅስ ፣ በሰው ልቅሶ ለራስህ ኑሮ ለምታላዝን፣ በወዳጅና በትዳር መካከል ብቸኝነት ለፈጀህ፣ ቋንቋህ ሰሚ ላጣው፣ ከዚህ ሁሉ በላይ በነገ ፍርሃት ለተያዝከው ወገን ዋስትናህ ማን ነው? በሰለጠነው ምድር ኢንሹራንስ ያልተገባለት ማንኛውም ተንቀሳቃሽ ንብረት መንቀሳቀስ አይችልም። የጤናና የሕይወት ዋስትና ያልገቡ ሰዎችን መቅጠርም ባለ ሀብቶች ይፈራሉ። በከፍተኛ በጀት የሚንቀሳቀሱ የዋስትና ተቋማትም መኪና ለወደመበት ያንኑ የሚያህል መኪና ፣ ቤት ለተቃጠለበት ተካካይ ቤት ይሰጣሉ። ምንም እንኳ የሕይወት ኢንሹራንስ ቢያስገቡም ሕይወት ላጣ ሕይወትን ሰጥተው አያውቅም። በለማ ከተማ ፍርሃት ለሚንጠው ፣ የውስጥ ጥያቄ ለወጠረው ፣ ጣራ ሲቆጥር ለሚያድረው እንቅልፍ ብርቁ ፣ ትዳሩ አክሲዮን ለሆነበት ፣ ነገ ጨለማ ሆኖ ለሚታየው ዋስትና የሚሰጥ የኢንሹራንስ ተቋም የለም። እንዲህ ያለውን ዋስትና ሰጪ ቢያገኙ የኢንሹራንስ ተቋማት ራሳቸውም ይፈልጉት ነበር። ታዲያ የኑሮ ዋስትናህ ማን ነው? ይህን ሁሉ ሕመማችሁን የነካካሁት እየቆነጠጡ ማስለቀስ እንደሚወዱ ሰዎች ሆኜ አይደለም። ስለ ኑሮ ሳነሣም ጆሮን ለመማረክ ብዬም አይደለም። ለእናንተ እንደምናገር ባስብ ኖሮ ብዕሬን አስቀምጥ ነበር። ከድካሜና ከሩጫዬ በኋላ እፎይ የምልበት ቃል ለራሴ እያዘጋጀሁ እንደ ሆነ ግን አውቃለሁ። ይህን የምጽፈው ቃለ መጠይቅ አድርጌ ሳይሆን ራሴን አይቼ ነው። እኔም ለእኔ ያለሁት እኔ ብቻ እየመሰለኝ የባዘንኩበትን ዘመን አውቃለሁ። ሰዎች በሕይወቴ ወሳኝ የሆኑ እየመሰለኝ ሲወዱኝ የምኖር ፣ ሲጠሉኝ የምጠፋ ይመስለኝ ነበር። የትልልቅ ሰዎችን ስልክ መያዝ እንደ ቡዳና መጋኛ መድሀኒት የኪሴ መሣሪያ ይመስለኝ ነበር። የእግዚአብሔርን ሳይሆን የሰውን ፊት እያየሁ ያገለገልኩበት ዘመን ብዙ ነው። ጊዜዬን እንጂ ሕይወቴንና ክብሬን አስቀምጬ ማገልገል ባለ መቻሌ ሩጫዬ ሁሉ የብቻ ሩጫ እንደ ነበር ተገንዝቤያለሁ። ስህተትን በስህተት ለማጥራት በመሞከር አእምሮዬን ለብዙ ዘመን እንዳቆሰልኩ እግዚአብሔር በሰጠኝ የፀጥታ ጊዜዎች አውቄአለሁ። ምድር ለተሸከመችኝ እነርሱ ከብዷቸው ብዙ ያሉኝ ወገኖች አሉ። ለመወደድም ለመጠላትም ጊዜ አለውና ሁለቱንም አይቼ ሕይወት እንዲህ ነው? ያልኩበት ጊዜ ብዙ ነው። መርዝ የተቀላቀለበት ሰላምታ ብዙ ጊዜ ተቀብዬአለሁ። እየወጉ "ይማርህ" የሚሉ የከበቡኝ ጊዜ ጥቂት አይደለም። ስለ ከዱኝ ባልንጀሮቼ ሰዎች ሲጠይቁኝ ውስጤ እያረረ ደህና ናቸው ስል መልሰው "አቤት የእናንተ ፍቅር" ሲሉኝ ደግሞ ራሴን ጠይቄአለሁ። በዚህ ሁሉ ወጀብ ውስጥ ግን የተረዳሁት ፈጣሪ ቁም ሳይል ሕይወትን የሚያቆማት እንደ ሌለ ነው። በርግጥም የምኖሬ ዋስትና ፈጣሪ ነው። ሌሎችም ሼር በማድረግ ለሰው ልጅ ሰላም እንስጥ ✍️ Bini Girmachew መልካም ቀን ይሁንልን 😍❤🙏
Show all...
ሁላችንም የምንኖርለትን ምክንያት እስክናውቀው ድረስ ሙሉ አቅማችንን አንጠቀምም፤ ስለዚህ ሌሎች ድክመታችንን አይተው እሱ እኮ ሰነፍ ነው ይሉናል፤ እሷ እኮ ግድየለሽ ናት ይሉናል። ወዳጄ የምትኖርለትን ምክንያት ሳታውቀው ቀርተህ እንጂ ከማንም አንሰህ ወይ ሰነፍ ሆነህ ተፈጥረህ አይደለም! እህቴ የሚያበረታሽን ጉልበት | የሚሰጥሽን ምክንያት አተሽ እንጂ የሚገርም አቅም ነው ያለሽ! አላማህን ያወከው እለት ምንም ነገር አያቆምህም! መልካም ቀን ይሁንልን😍❤🙏
Show all...
“ዉድድርህ ከሰዎች ጋር አይደለም! ዉድድርህ:- ✓ ከገደልከዉ ሰአት ✓ ከፈጠርከዉ በሽታ ✓ መማር እያለብህ ችላ ካልከዉ እዉቀት ✓ መስዋእት ካረከዉ ጤናህ ✓ አዲስ ሃሳብን አልቀበልም ካልከዉ ማንነት ✓ ያንተን መጣር ከማይወዱ ሰዎች ✓ እድለ ቢስ እንደሆንክ ከሚነግርህ ሰይጣን ጋር ነዉ” -ጀምስ አልሸር 🙌መልካም ቀን 😍❤ቸር ያውለን🙌
Show all...
ማንን እያዳመጥክ ነው? ፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨፨ የእራስ ግንዛቤን ለማሳደግ እንዲሁም እራስን አብልጦ ለማወቅ ውጫዊውን ጫጫታ ከመስማት ይልቅ ውስጥን ማዳመጥ ተመራጭ ነው። ዘወትር ለአካባቢያችን ድምፅ ተጋላጭ በሆንን ቁጥር ለእራስ መሰጠት ያለበትን ውድ ጊዜ እንዘነጋለን። በውጫዊው ሁካታና ወከባ እንዘናጋለን። አዎ! ጀግናዬ..! ማንን እያዳመጥክ ነው? ማንን አብዝተህ ትሰማለህ? እራስህን፣ ፍላጎትህን፣ ህልምህን፣ ራዕይህን ወይስ ወቅታዊውን የአለም ጫጫታ? ውስጥህ የሚመላለስ ብዙ ሃሳብ አለ፣ ትኩረትህን የሚሻ ከፍ ያለና ሊቀይርህ የሚችል ግሩም አመለካከት አለ፤ አንተንም ሆነ ሌሎችን ሊያሻግር የሚችል ድንቅ እሳቤ አለህ። አዎ! ውጪውን ለመስማት ሞክር፤ ውስጥህን ግን በጥልቀት አዳምጠው። ከገዛ ሃሳብህ እየሸሸህ ፍቱን እረፍትን አትመኝ፤ በሌሎች አስተያየት ውስጥ እርካታን አትፈልግ፤ በሌሎች ሩጫ አንተ አታሸንፍም፤ በሌሎች ትጋት አንተ አታድግም፤ አትለወጥም። የሌሎችን ብርታት ማውራት በህይወትህ የሚያመጣው ለውጥ የለም። የምትቀየረው፣ የምታድገው በእራስህ ጥረትና ልፋት ብቻ ነው። ደስታና እርካታህ እራስን ባወክ፣ ውስጥህን ባዳመጥክ ልክ ነው። አዎ! አንዳንዴ ውጪ ላይ የሚወራው፣ የሚተነተነው፣ አብዝቶ የሚነገረው ሃሳብ ከጭንቀት የሚያሳርፍ ሊመስለን ይችላል፤ ለጊዜውም ያረፍን ሊመስለን ይችላል። እውነተኛው እረፍትና ሰላም ግን እራስን ለማዳመጥና እራስን ለመሆን ዝግጁ በሆንን ልክ ነው። እየገፋሀው፣ እየሸሸሀው፣ እየጠላሀው የምትቀይረው አስተሳሰብም ሆነ ማንነት የለም። በቅድሚያ እራስህን ተቀበል፤ ውስጣዊ ሽኩቻህን፣ ሹክሹክታህን በጥሞና አዳምጥ፤ ወደ እራስህ ተመልክ፤ ደረጃህን ያለህበትን ስፍራ፤ ፍላጎትህን ለይ። የሚያስደስትህን ለማድረግ ማንም እስኪነግርህ አትጠብቅ። አንተ እራስህ ስለራስህ የምታውቀው ሌሎች ከሚነግሩህ በእጅጉ ይበልጣልና። መልካም ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 ✍️ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
Show all...
ሰውነትን አክብር! ፨፨፨፨/////፨፨፨፨ ሰውን ሰው የሚያሰኘው ተክለ ቁመናው ሳይሆን ሰዋዊ ባህሪው፣ ሰውነቱ ነው። ሰውነቱም ርህራሄው፣ ሃዘኔታውና አሳቢነቱ ነው። ሰው ሆኖ ለሰው ካላሰበ፣ የሰው ህመም ካልተሰማው፣ ካላመመው ሰውነቱ ጥያቄ ውስጥ ነው። እሱ ምንም ባይመስለው ውስጡ ያለው የአምላክ መንፈስ ይታገለዋል። የሚታገለውን መንፈስ ላለመስማት ግን ብዙ አማራጮችን ሊጠቀም ይችላል። ይህም ማለት ሰውነቱን ለመሸሽና ለመፋቅ የሚያደርገው ትግል ተደርጎ ይቆጠራል። አዎ! ጀግናዬ..! ሰውነትን አክብር፤ ሰው ለሆነ ሁሉ ቦታ ይኑርህ። ሃሳብህ ሰውኛ ነው፣ እይታህ፣ አረዳድህ ሰውኛ ነው፤ ስራህ ሁሉ የሰውነትህ ነፀብራቅ ነው። ሰው ያለሆነ፣ አንተ የምታደርገውን ሊያደርግ አይችልም። ከባዱ የሰውነት ፈተና ሰው ሆኖ እንደሰው መኖር አለመቻል ነው። አዎ! ማናችንም ብንሆን እኛ ነፃ ሆነን፣ እኛ ደህና ሆነን ለሌላው የማዘን እድሉን የምናገኘው እኛ ከጉዳቱ ውጪ ስንሆን ነው። አንተ ብትጎዳ ሃዘኔታው ለእራስህ ይሆናል፤ ደህና ሆነህ ግን አለማዘን፣ አለመራራት አትችልም። የምታየው ተግባር ሁሉ ከሰው የማይጠበቅ፣ የማይመጥነው፣ የማይገልፀው ቢሆንብህ አንተም በእርሱ ማዘን ካቆምክ፣ ምንአይነት ሰው እየሆንክ እንደሆነ እራስህን ጠይቅ። ምንም ማድረግ ባትችል ማዘን ትችል ዘንድ ሰውነትህ ያስገድድሃል፤ ነገሮች እንዳልነበሩ በሆኑ ሰዓት ምንም እንዳልተፈጠረ የመሆን ባህሪ የለህም። አዎ! ሰውነትህን የሚገልፁ ባህሪያትን ተላበስ፤ በእነርሱ ተመላለስ። እራስህን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከልብህ ውደድ፣ አክብር፤ ሌላውንም እንዲሁ ውድድ፣ አክብር፣ ቦታ ስጥ። ለሃዘኔታም ይሁን ለርህራሔ ጊዜ እስክታጣ አትጠብቅ። የአምሳያህ ሰው ሁሉ ህመም ይስማህ፤ የማንንም ጉዳት እንደቀላል አትመልከት። የተገኘሀው ከሰው ነው፤ የምትኖረውም ከሰው ጋር ነው፤ ውሎ አዳርህ፣ ስራህ፣ እንቅስቃሴህ ሁሉ ከሰው ጋር ነውና ሰውነትን አክብር፤ የአምላክ አምሳል መሆኑ ይሰማህ፤ በሰውነትህም እዘንለት፤ በቻልከው መጠን ከሃሳብ ጀምሮ የእርዳታ እጅህን ዘርጋለት። መልካም ቀን ይሁንልን! ✍️ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
Show all...
🩸አጥፍቻለው!🙋‍♀ 👇👇 በፍቅር ግኑኙነት👫 ውስጥ አልፎም በትዳር አለም አለመስማማት አለመግባባት ያለ ነው አዲስ አይደለም🤷‍♂ በአንዳንድ ሁኔታዎን ላትግባቡ፣ ሃሳባችሁ ሊለያይ፣ የአንዳችሁ ፍላጎት ከአንደኛችሁ ላይጥም ወይም ላይሄድ ይችላል🤔 ለምን አትበሉ ሰዎች ናችሁና ነገር ግን ይህ ሲፈጠር እሺ በቃ ይሁን ብሎ ማለፍ ሳይሆን ቶሎ ለዛ ነው እርምጃ ወስቶ ማለፍ ፍቱን መድሃኒት ነው💊 ታዲያ በመካከላችሁ ይህ አይነቱ ክስተት ሲፈጠር በሰከነ መንፈስ "በመነጋገር" መፍታት አዝላቂው መንገድ ነው🙏 ለዛሬ ግን ይህ አይነቱ ጉዳይ አለመግባበቱ ብሎም አለመስማማት በመካከላችሁ ሲፈጠር🤷‍♂ አንድ እጅግ ጠቃሚና መፍትሄ የሚያመጣን ነገር ላካፍላችሁ በጥሞና ተከታተሉኝ ልባሞች👇 አለመግባባት የሚመጣው በብዙ ጉዳዮች ቢሆንም ነገር ግን ያን ነገር ለማብረድ👉 "ጥፋተኛ" ሆኖ መቅረብ ተገቢና ምርጡ መንገድ ነው😳 ምናልባት አንቺ ጋር ጥፋት የለም አዎን የለም❌ ምናልባት አንቺ ልክ ሆነሽ ይሆናል አዎን ይሆናል👍 ነገር ግን ልክ ነኝ ማለት አንዳንድ ጊዜ ያለመግባባታችሁን ጊዜ ያረዝማል ልክ ብትሆኚም👉 "አዎን ጥፋቱ እኔ ጋር ነው ይቅርታ!" ብለሽ ማብረድና የፍቅር ግኑኙነትሽን አልያም ትዳርሽን ማስከን ትችያለሽ🙋‍♀ እሳትን ማጥፊያው እሳት ሳይሆን ውሃ እንደሆነ🤔 አንቺም አለመግባባት ጥፋተኛ እንደሆንሽ አድርገሽ ወደ መግባባት አምጪው👍 ይህን ስታደርጊ ሊያም ይችላል አዎን ያማል🤷‍♂ ግን ይህን በማድረግሽ 1⃣ ልባምና አስተዋይ መሆንሽ እጅጉን ይጎላል ለነገም ስንቅ ይሆንሻል 2⃣ ለፍቅረኛሽ/ለባልሽ ትምህርትን ትሰጪዋለሽ አዎን አጥፍቻለው ስትይ አዕምሮው ይወቅሰዋል ስለዚህ "ሳታጠፊም አጥፍቻለው ማለት ውርደት አልያም ክብርን ማጣት ሳይሆን ክብርን ማግኘትና አስተዋይነትም ጭምር ነው"🙏 መልካም ቀን ይሁንልን😍❤🙏🙏
Show all...
ብርጭቆ ከእጃችሁ ላይ ወድቆ መሰበሩ ብቻ ሳይሆን ጥፋት🤔 ይልቅ የተሰበረው የብርጭቆው ስብርባሪ በእጆቻችሁ ለማንሳት ስትጥሩ ጉዳት እንዳያደርስባችሁ ተጠንቀቁ⚠️ አስከፊው ያ ነውና😳 "ችላ ስል" አልያም "ድንገት" ነው ከእጄ ወድቆ የተሰበረው ማለት ሰበብ እንጂ ምክንያት አይሆንም❌ ም/ቱም ብርጭቆ ስስ ስለሆነ አስቀድሞውኑ ጥንቃቄ ይሻልና ሃላፊነቱን ሙሉ ለሙሉ አንቺው ትወስጃለሽ🤷‍♂ ልብ በይ 👉 " ሃጥያት መስራትህን ብቻ ሳይሆን ያ የሰራሃው ሃጥያት የሚወልደው ክፉ ዘር በቀጣይ ህይወትሽ የሚያመጣብሽን ነገር ፍሪ!😳" እንዲሁ ባለማስተዋል በግድ የለሽነት ብሎም በድፍራት☹️ ዛሬ ላይ የምትሰሪው ሃጥያት ነገ ትልቅ ዋጋን እንደሚያስከፍልህ አትዘንጊ የዘራሽውን ማጨድ አይቀርምና😰 ለምትኖሪለት ህይወት ጥንቁቅ ሁኚ መቆሚያ እንደሌለው ንፋስ ወዲህ ወዲያም አትበይ❌ ደግሞም አስተውይ ቅድስና ሁሌም የበላይህ ይሁን🙏 ለነገሮች ችላ አትበይ ንቂም ዘመኑንም መርምሪ🤔 ያለበለዚያ የዘርሽ ውጤት መጨረሻ ስቃይ ብሎም ሞት ነውና 😔 🤷‍♂ ✍️ከወንድማችሁ ቦና🐆
Show all...
❤️‹ለምትወዷቸው ሠዎች ይበሩ ዘንድ ክንፍ ስጧቸው፤ ተመልሠው ይመጡ ዘንድ ስር አስይዟቸው፤ ከናንተ ጋር ይቆዩ ዘንድ ምክንያት አኑሩላቸው፡፡›› ቅድሚያ ለሰብዓዊነት!! Priority for Humanity! ፈጣሪ ማሰተዋል ይስጤን ሰላም ጤና ፍቅር & አንድነት ለእናት ሀገር ኢትዮጵያ ይሁንልን 😍❤🥰🙏🙏🙏
Show all...