cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Kaffa media net work

Well come to kaffa መረጃ ህይወት ነዉ መረጃ ምግብ ነዉ እና ለእያንዳንዱ ዜጋ መረጃ አስፈላጊ ነገር ነዉና እናድርስ የቡና መገኛ ሀገር ከፋ ኢትዮጵያ no woraafo kaffine

Show more
Advertising posts
583Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ተለቀቀ! የፍትህ መፅሔት ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳላኝ በ30 ሺህ ብር ዋስትና በዛሬዉ ዕለት ከእስር መፈታቱ ታወቀ። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ህገ መንግስታዊ ችሎት ትላንት ህዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም. በዋለዉ ችሎት ጋዜጠኛው በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ቢወስንም የቂልንጦ ማረሚያ ቤት ለመልቀቅ ፍቃደኛ ሳይሆን ማደሩ ይታወቃል። ዛሬ ህዳር 7 ቀን 2015 ዓ.ም ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለ176 ቀናት በእስር ከቆየ በኃላ መፈታቱን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ገልጿል። [Addis Zeybe] @addis_news @addis_news
Show all...
ኢትዮጵያ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሩሲያን በመደገፍ ድምጽ ሰጠች በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ሩሲያ ሩስያ በዩክሬኑ ጦርነት ላደረሰችው ጉዳት ካሳ እንድትከፍል የሚያስገድደው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ኢትዮጵያ የተቃውሞ ድምጽ ሰጥታለች። ኢትዮጵያን ጨምሮ 14 ሀገራት ሩስያ በዩክሬኑ ጦርነት ላደረሰችው ጉዳት ካሳ እንድትከፍል የሚያስገድደውን የውሳኔ ሀሳብ ተቃውመውታል። አረብ ኤሚሬትስን ጨምሮ 73 ሀገራት በድምፀ ተአቅቦ ማለፋቸውን ተከትሎም የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የመንግስታቱ ድርጅት ካወጣቸው አምስት የውሳኔ ሀሳቦች ሁሉ ይሁንታ የተነፈገው ሆኖ ተመዝግቧል። የውሳኔ ሀሳቡ በጦርነቱ ለተገደሉና ለቆሰሉ ዩክሬናውያን ሞስኮ ካሳ እንድትከፍል የሚጠይቅ ነው። በጦርነቱ የጠፋውን የሰው ህይወትና የደረሰውን የንብረት ውድመት የሚያጣራ አለም አቀፍ ቡድን እንዲዋቀርም ተመላክቷል በዚሁ የውሳኔ ሀሳብ። ቻይና፣ ኢራን፣ አንጎላ፣ ቬንዙዌላን ጨምሮ 16 ሀገራት ለሩስያ ድጋፋቸውን በፊርማ ገልፀው፥ ፍትህ በተገቢው የህግ ስርአት እንጂ ምንም አይነት የህግ መሰረት በሌለው የውሳኔ ሃሳብ አይደለም ብለዋል። @addis_news @addis_news
Show all...
''ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ 49 ቢሊየን ብር ቤተመንግስት እየገነቡ ነው እየተባለ ይወራል። አዎ እየገነባን ነው ግን በ49 ቢሊየን ሳይሆን በ 400 እና 500 ቢሊየን ብር ነው። ትንሽ ከተማ ሳተላይት ከተማ ነው የምንገነባው። ጫካ ሲያልቅ በአፍሪካ ደረጃ ጉድ የሚያስብል ፕሮጀክት ነው። ሲያልቅ ታዩታላችሁ። እናንተ ባይገባችሁ የልጅ ልጆቻችሁ ይኮሩበታል።''..... “ልንገነባ ያሰብነው ‘የጫካ ሃውስ’ ይባላል። ልንገነባ ያሰብነው ለኢትዮጵያ፣ ለአፍሪካ ኩራት የሚሆን ‘ሳተላይት ሲቲ’ ነው። ልንገነባ ያሰብነው የኢትዮጵያን ቤት ነው” ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ ንግግር የተወሰደ @addis_news @addis_news
Show all...
ስምምነቱን የጣሰ ማዕቀብ ይጠብቀዋል----አሜሪካ የኢትዮጵያ ፈደራዊ መንግስትና ህወሓት በቅርቡ የተፈራረሙትን ስምምነትን የሚያዉኩ ወገኖችን በማዕቀብ እንደምትቀጣ አንድ የአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን አስጠነቀቁ። የአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን» ከሚለዉ ማዕረግ ሌላ መደበኛ ስምና ማዕረጋቸዉ በሚስጥር የተያዘዉ ባለስልጣን እንዳሉት፣ በአፍሪቃ ሕብረት ሸምጋይነት የተደረገዉን የሁለቱን ወገኖች ድርድር አሜሪካ በቅርብ ስትረዳና ስትተባበር ነበር። ባለስልጣኑ ስለስምምነቱ ማባራሪያ በሰጡበት መግለጫዉ እንዳሉት ሁለቱ ወገኖች እንዲስማሙ ከዋይት ሐዉስ እስከ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር፣ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ በየሐገሩ እስከሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ባለስልጣናት፣ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸዉን ጠቅሰዋል። እንደ ዶቸቨለ ዘገባ ባለስልጣኑ ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ተፈራራሚ ወገኖች የሚሉትና የሚያደርጉት እንቅስቃሴም አበረታች ነዉ ብለዋል፡፡ ባለስልጣኑ «ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ መጣልን ሁል ጊዜ የመርሕዋ መሳሪያ አድርጋ ትጠቀምበታለች።በሰብአዊ መብት ረገጣ የሚጠየቁ ተዋኞችን (ወገኖችን) ተጠያቂ ለማድረግ ወይም ይሕ ስምምነት እንዲከበርና በትክክል ገቢር እንዲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ማዕቀብ ለመጣል አሜሪካ አታመነታም» ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓብይ አሕመድ መንግስታቸዉ ስምምነቱን «በታማኝነት» ገቢር እንደሚያደርግ ማስታወቃቸዉ ይታወሳል። የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የላከዉ መድሐኒትና የሕክምና ቁሳቁስ ትናንት መቀሌ መደረሱ መገለጹ አይዘነጋም። @addis_news @addis_news
Show all...
አዲስ አበባ-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተፈታ የፍትሕ መፅሔት ባለቤትና ማኔጂንግ ኤዲተር ተመስገን ደሳለኝ ከ6 ወራት እስራት በኋላ ዛሬ በ30 ሺሕ ብር ዋስትና ተፈታ።ጋዜጠኛዉ የታሰረዉ "የሐገር መከላከያ ምስጢሮችን ማውጣት ፣ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለሕዝብ ማሰራጨትና እና ለወንጀል ማነሳሳት" በሚሉ ሶስት ጭብጦች ተከስሶ ነዉ። ጋዜጠኛው መጀመሪያ በ10 ሺህ ብር፣ ቀጥሎ በ100 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቅ ፍርድ ቤት ቢወስንም ውሳኔው እስከ ዛሬ ድረስ ተፈፃሚ አልሆነም።ትናንት አዲስ አበባ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት ለሦስተኛ ጊዜ በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጣ አዝዞ ነበር።ይሁንና ትናንትም ሳይፈታ ማረሚያ ቤት አድሮ ዛሬ ከቀትር በኋላ መለቀቁን ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ተናግሯል። ተመስገን ከዚሕ ቀደምም በመጽሔት በሚያትማቸዉ ጽሑፎቹ ምክንያት በተደጋጋሚ ለእሥር ተዳርጓል። ተመስገን የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ሥልጣን ከመያዙ በፊት በነበረዉ የኢሕአዴግ የአስተዳደር ዘመንም በጋዜጠኝነት ሙያው ምክንያት ለረጅም ዓመታት ተፈርዶበት በእሥር ላይ የቆየ ጋዜጠኛ ነው። ትናንት የዋስትና መብቱ በፍርድ ቤት ተከብሮለት ሳለ ታሥሮ የነበረበት የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንደማይፈታው ማሳወቁን ጋዜጠኛ ተመስገን "ፍርድ ቤት ፈትቶኛል፣ ከዚህ በኋላ እኔ ላይ ለሚፈጠረው ነገር ኃላፊነቱን የሚወስደው ማረሚያ ቤቱ ነው።»ማለቱን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለዴቼ ቬለ ተናግሯል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፍርድ ቤቶች በዋስትና ይሁን በነፃ የሚለቋቸው ተከሳሾች ወይም ጠርጣሪዎች አንድም ፖሊስ ፣ አለያም ማረሚያ ቤቶች እንዳሰሩ ሲያቆዩቸዉ ማየት እየተለመደ ነዉ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ትናንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ "የፍትሕ ሥርዓቱ ሥብራት ትልቅ ነው። ፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ሰፊ ችግር
Show all...
ባልደራስ የቄለም ወለጋውን ጭፍጨፋና የአባላቱን እስርና ወከባ አወገዘ ፤ ተቃዋሚው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በአጭሩ ባልደራስ ትናንት ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓም በአሮምያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን የተፈጸመውን ግድያ በጥብቅ እንደሚያወግዝ ዛሬ በማኅበራዊ መገናኛ ገጹ ባስነበበው መግለጫው አስታውቋል። ፓርቲው በመግለጫው ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓም በምዕራብ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ «ንጹሀን አማራዎች» በግፍ ሕይወታቸውን ያጡበትን ግድያ በሰላማዊ መንገድ በተቃወሙ በአዲስ አበባ፣ በባህርዳር፣በጎንደር ደብረ ማርቆስ በደብረ ብርሀን እና በሌሎችም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች ላይ መንግሥት ይፈጽማል ያለውን እስርና ማዋከብም አውግዟል።መንግሥት እየፈጠረ ነው ካለው ኤኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ህልውናዊ ካላቸው ቀውሶች በተጨማሪ የፋኖና የባልደራስ አባላትን ጋዜጠኞችንና ማኅበራዊ አንቂዎችን እንዲሁም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ማዋከብ ከጀመረ ውሎ አድሯል ብሏል ባልደራስ።የባልደራስ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ባህር ዳር ለስራ ጉዳይ በሄዱበት ሕገ ወጥ ባለው መንገድ ከታሰሩ በኋላ በ30 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ መወሰኑን አስታውሶ ሆኖም በዋስትናው መሠረት ከእስር ከተፈቱ በኋላ አዲስ አበባ ዳግም መታሰራቸውን አስታውቋል። ከዚህ ሌላ የፓርቲው አባል አቶ ኢሳያስ ጥጉ እንደታሰሩ፣ሌላው የፓርቲው አባል ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ደግሞ ባህርዳር እንደታሰሩ ገልጿል።የእስር ማዘዣ የወጣባቸው የድርጅቱ አባል ጌጥዬ ያለው ጉዳያቸው በፍርድ እየታየ መሆኑን የጠቀሰው የባልደራስ መግለጫ በ የፓርቲው አባል ድምጻዊ አሌክስ ሸገር ትንንት መታሰሩን የጠቀሰው ባልደራስ ከዚህ ቀደም ታስረው ነበር ያላቸው ሌሎች አባላቱ እስካሁን በዋስ ሊወጡ አልቻሉም ብሏል። በፓርቲው አባላት ላይ ይደርሳል ያለው እስርና አፈና ተጠናክሮ መቀ
Show all...
⭕️ 1 ሰው በእርስዎ ሊንክ አማካኝነት የ 🇪🇹🇪🇹Ethio Birr ቦት ሲቀላቀል 1 ብር ያገኛሉ 🔗የእርስዎ መጋበዣ ሊንክ:👇👇 https://t.me/EthioCard_bot?start=r0530855356
Show all...
⭕️ 1 ሰው በእርስዎ ሊንክ አማካኝነት የ 🇪🇹🇪🇹Ethio Birr ቦት ሲቀላቀል 1 ብር ያገኛሉ 🔗የእርስዎ መጋበዣ ሊንክ:👇👇 https://t.me/EthioCard_bot?start=r0530855356
Show all...