#እቺን ቃል ንገሯት😂😍
ተፈርዶብኝ እጂ መለየት ተስኖኝ ጥሬውን ከብስል
ሀገሬው ምድር ላይ እሷ ብቻ ቆንጆ የቀረች ይመስል
ዞር ባለች ቁጥር አትራቂኝ እያልኩኝ የምለማመጣት
ልቻለው ብዬ እጂ ምሳሌ ከምሆን አፍቅሮ ከማጣት
#ገደል ግቢ በሏት
ይሄው ደግሞ ዛሬ ገላዋን በሙሉ አወደችው ሎሽን
ፀጉሯን አጎፈረች ደመቀች በሽንሽን
ከንፈሯን ምን ይሆን ደግሞ የቀባችው
የእጇን አይበሉባ በቄንጥ አኮናትራ ሰአቷን አየችው
ገናነው መሰለኝ ጊዜን ታዘበችው
መንቀር አለችና መስታወት ፊት ቆመች
ደግሞ ፈገግ አለች ጥርሷ ይርገፍና
#ማርያምን ታምራለች
ዘከርኳት በወዳች መከርኳት በዘመድ
ቀለበት አይጠቅማት አሰርኳት በገመድ
#ገደል ግቢ በሏት
ልቤን ከጋረደው ወዳጅ ከከለላት ስውር አይነጥላ
እዲህ እዳማረባት መሄድ ከጀመረች አፍቃሪ ሰውጥላ
ልክ እደገላዋ ይለስልስ መንገዱ ፍፁም አይጎርብጣት
አየሩ በሙሉ ፍክት ይበልላት እደ ጥርሷ ንጣት
እያልኩኝ ፎክሬ እደ ገጣሚ ቃል ልቤ አልጀነጅን
የት አባቷን እና በፀበል ካልወጣች ትረሳለች በጅን
#ገደል ግቢ በሏት
የት አባቷን እና እዲህ የሚያምርባት
የት እናቷን እና እዲህ የሚደምቅባት
#ገደል ግቢ በሏት
እስከ መቼ ድረስ ስቀባ እኖራለው ጉድፍ ልቧን ስኩል
#ገደል ግቢ በሏት
እኔ ገደል ስር ነኝ ድንገት ከወደቀች እድቀበላት
https://t.me/fkrleneShow more ...