cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Mekdela Amba University Registrar and Alumni Directorate Office

This channel is the official telegram ch of the registrar of MAU, and its purpose is to provide students, teachers and staff with accurate information such as university admission, registration dates, exam programs, academic calendar etc....

Show more
Ethiopia4 625The language is not specifiedEducation33 816
Advertising posts
1 642Subscribers
-224 hours
+27 days
+1530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ለክረምት ነባር ተማሪዎች በሙሉ:-
Show all...
👉#ይህ_የመቅደላ_አምባ_ዩኒቨርስቲ_ሬጅስትራር_ኦፊሻል_ቻናል_ነው! 👉 ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ! 👉 ሌሎች ተማሪዎችን እዚህ ቻናል ላይ Add አድርጉ (የአባላት ቁጥር ቢያንስ 2.5K መድረስ አለበት በዚህ ሳምንት)! 👉ሪመድያልን በተመለከተ አዲስ ነገር ሲኖር በዚህ ቻናል ብቻ እናሳውቃለን! 👉https://t.me/MAUREG1
Show all...
Mekdela Amba University Registrar and Alumni Directorate Office

This channel is the official telegram ch of the registrar of MAU, and its purpose is to provide students, teachers and staff with accurate information such as university admission, registration dates, exam programs, academic calendar etc....

ማህበራዊ ሚዲያዎች ያለ VPN መስራት ጀመሩ። ለወራት ያህል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ መነሳቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ ለማረጋገጥ ችሏል። #ቴሌግራም ፣ ዩትዩብ ፣ ፌስቡክ ፣ ቲክቶክ መሰል የማህበራዊ ሚዲያዎች ከወራት በፊት (የካቲት ወር 2015 ዓ/ም) በተጣለባቸው ገደብ ያለ VPN መስራት እንዳቆሙ ይታወቃል። ዛሬ ሰኞ ከሰዓታት በፊት ግን እነዚህ የማህበራዊ ሚዲያዎች #ያለ_VPN_እየሰሩ እንደሚገኙ እና ገደቡም መነሳቱን #ማረጋገጥ ችለናል
Show all...
👉#ይህ_የመቅደላ_አምባ_ዩኒቨርስቲ_ሬጅስትራር_ኦፊሻል_ቻናል_ነው! 👉  ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ! 👉 ሌሎች ተማሪዎችን እዚህ ቻናል ላይ Add አድርጉ (የአባላት ቁጥር ቢያንስ 2.5K መድረስ አለበት በዚህ ሳምንት)! 👉ሪመድያልን በተመለከተ አዲስ ነገር ሲኖር በዚህ ቻናል ብቻ እናሳውቃለን! 👉https://t.me/MAUREG1
Show all...
Mekdela Amba University Registrar and Alumni Directorate Office

This channel is the official telegram ch of the registrar of MAU, and its purpose is to provide students, teachers and staff with accurate information such as university admission, registration dates, exam programs, academic calendar etc....

ውጤት የሚታይበት website ይሰራ እየገባችሁ ማየት ትችላላችሁ!
Show all...
ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከተቀመጡት ተማሪዎች ውስጥ 40.65 በመቶዎቹ የማለፊያ ነጥብ አስመዘገቡ! ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከተቀመጡት ተማሪዎች ውስጥ 40 ነጥብ 65 በመቶዎቹ የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገባቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ከሰኔ 30 ቀን ጀምሮ ለስድስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የዩኒቨርሲቲ ትምህርት መውጫ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ገልፀዋል። ለመውጫ ፈተና ሊቀመጡ ይችላሉ ተብሎ ተገምቶ ከነበረው 240 ሺህ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን 194 ሺህ 239 ተማሪዎች ብቁ ሆነው ለፈተና መመዝገባቸውንም ነው የተናገሩት። ከዚህ ውስጥ ከ48 የመንግስት ተቋማት 84 ሺህ 627 ተማሪዎች እና ከ171 የግል ተቋማት 109 ሺህ 612 ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውም ነው የገለጹት። የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡት ውስጥ ከመንግስት ተቋማት 77 ሺህ 981 ተማሪዎች እንዲሁም ከግል ተቋማት 72 ሺህ 203 ተማሪዎች በድምሩ 150 ሺህ 184 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 61 ሺህ 54 ተማሪዎች ወይም 40 ነጥብ 65 በመቶ የማለፊያውን ነጥብ አስመዝገበዋል ነው የተባለው፡፡ ለተቋማትም የተማሪዎቻቸውን ውጤት የመላክ ሥራ መጀመሩንም ጠቁመዋል።
Show all...
#Update ዩኒቨርሲቲዎች ላለፉት አምስት ቀናት ሲሰጡት የቆየው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቁን አሳውቀዋል። ከ44 የመንግሥት እና ከ161 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ዕጩ ተመራቂዎች ከሐምሌ 03/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየውን ፈተና መውሰዳቸው ተገልጿል። ከ168 ሺህ በላይ ዕጩ ተመራቂዎች ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተናውን ይወስዳሉ መባሉ ይታወሳል። ምን ያህል ተማሪዎች በኦንላይን የተሰጠውን ፈተና እንደወሰዱ መንግሥት በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ከሐምሌ 08/2015 ዓ.ም ጀምሮ ውጤት ይገለጻል መባሉ አይዘነጋም። በሌላ በኩል ፥ የመውጫ ፈተና ከሰጡ ተቋማት አንዱ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የፈተናው ውጤት ዛሬ ይፋ መሆኑን ገልጿል። ተቋሙ በ41 ፕሮግራሞች ካስፈተናቸው 1604 ተፈታኞች  ፡- - በ13 ፕሮግራሞች 100% - በ7 ፕሮግራሞች ከ90-99% - በ11 ፕሮግራሞች ከ80-89% በአጠቃላይ በ31 ፕሮግራሞች 80% እንዲሁም እንደ ዩኒቨርሲቲ 81% ተማሪዎቹ ማለፋቸውን በይፋ አሳውቋል። ዩኒቨርሲቲው ካስፈተናቸው 1604 ተማሪዎች 1289 ተማሪዎች ከ50% በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውንም ገልጿል። በተጨማሪ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን  የመውጫ ፈተና (EXIT EXAM) ካስፈተናቸው 1450 ተማሪዎች መካከል 78.5% ተማሪዎችን በብቃት ማሳለፍ ማቻሉን ገልጿል። ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ካስፈተነባቸው 43 ፕሮግራሞች መካከል፡- 👉 100% ያሳለፉት 11 የትምህርት ክፍሎች/ፕሮግራሞች 👉 ከ90% በላይ ያሳለፉ 21 የትምህርት ክፍሎች/ፕሮግራሞች 👉 ከ80% በላይ ያሳለፉ 27የትምህርት ክፍሎች/ፕሮግራሞች 👉 ከ70% በላይ ያሳለፉ 32  የትምህርት ክፍሎች/ፕሮግራሞች መሆናቸውን ገልጿል።
Show all...
#Update ሁሉም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች በተቋማቸው የምርቃት መርሃ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ተገለጸ። መንግሥት ከዚህ ቀደም ወስዶት በነበረው ውሳኔ ላይ ማሻሻያ በማድረግ፤ “የመውጫ ፈተናን #ያላለፉ ተማሪዎችም በተቋማቸው የምርቃት ፕሮግራም ላይ እንደሚሳተፉ” የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አሳውቋል። ከዚህ ቀደም ከግማሽ በላይ ጠቅላላ ድምር ውጤት (CGPA 2.00>) ያላቸው ተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ ይሳተፉ የነበረ መሆኑን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አስታውሷል። አሁንም በተመሳሳይ የመውጫ ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ የሚሳተፉ ሲሆን ዲግሪ ለመውሰድ መሟላት የሚገባቸውን እንዲያሟሉ ይጠበቃል ብሏል። የመውጫ ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች ለምዘና ብቁ ሲሆኑ በየሦስት ወሩ መፈተን እንደሚችሉም ህብረቱ ገልጿል። ያለገደብ ድጋሚ የመፈተን ፍላጎት የሌላቸው ዕጩ ምሩቃን በደረጃ ዝቅ ያለ የትምህርት ማስረጃ መውሰድ እንደሚችሉ በመመሪያ መቀመጡን ህብረቱ የላከልን መግለጫ ያሳያል። የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች በትምህርት ማስረጃቸው ላይ ከ100 ያመጡት ውጤት የሚገለፀው በጊዜያዊው ማስረጃቸው ላይ ሳይሆን በትራንስክሪፕት ላይ እንደሆነም ህብረቱ ጠቁሟል።
Show all...