cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Hule Geb Tube ሁለ ገብ ቲዩብ

ያውቁትን ማሳወቅ ነው የኛ ሰራ !! https://youtu.be/xFfev2KDxV0

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
189Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ለእናቱ ብቻ በእጇ እንዲሰጣት የተነገረውን ከትምህርት ቤቱ የተቀበለውን በፖስታ የታሸገ ደብዳቤ ይዞ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ 💡ከቤቱም ሲደርስ ለእናቱ ለአንቺ በእጅሽ እንድሰጥሽ ከትምህርት ቤት ተሰጥቶኝ ነው ብሎ ሰጣት፡፡ እናቱም ፖስታውን ከፍታ የተላከላትን ደብዳቤ ስታነበው ዓይኗ በእንባ ተሞላ፤ እንዲህም ብላ ድምጿን ከፍ አድርጋ አነበበችለት "ልጅሽ እጅግ በጣም ጓበዝ ተማሪ ስለሆነ እሱን ለማስተማር ብቁ የሆነ መምህር በትምህርት ቤታችን ስለሌለን ራስሽ በቤትሽ አስተምሪው፡፡" በማለት አነበበችለት፡፡ 💡ከአመታት በኋላ የዚህ ወጣት እናት ሞተች፡፡ ይህም ወጣት ከጊዜ በኋላ ቤተሰቦቹ ይኖሩበት ወደ ነበረበት ቤት በማቅናት ያደገበትን ቤት ይጎበኝ ጀመረ፡፡ ከዚያም መሳቢያ ውስጥ ፖስታ ያያል ፖስታውንም ሲከፍተው አንዲት ደብዳቤ አገኘ፡፡ 💡ደብዳቤውን ሲያነበው እንዲህ ይላል "ልጅሽ የተቃወሰ ተማሪ ስለሆነ ከዚህ በኋላ ወደ እዚህ ትምህርት ቤት መቼም እንዲመጣ አንፈልግም፡፡ "ወጣቱ ልጅም ደብዳቤውን ካነበበ በኋላ ለረጅም ሰዓት ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ ፤ የግል ማስታወሻው (Diary) ላይም እንዲህ ብሎ አሰፈረ "ቶማስ ኤዲሶን የሚባል ቀዉስ ልጅ በእናቱ ምክንያት የዘመኑ ጀግና ሰዉ ሆነ።" በትምህርት ቤት መምህራኖቹ የተቃወሰ ነው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይመጣ ብለው ያሉት ወጣቱ ልጅ ቶማስ ኤዲሶን የተነገረበትን ክፉ ንግርት በማፍረስ በእናቱ መልካም አስተሳሰብና አበረታችነት የመብራት ኃይል፣ አምፑል፣ ቴሌግራፍ  እና የፊልም ካሜራ ፈጣሪ በመሆን በዓለም ሁሉ እውቅ የአሜሪካ ሳይንቲስት ሆነ። 💡በምንናገረው መልካም ንግግር በሰዎች ውስጥ የተቀመጠን ለሰዉ ሁሉ የሚጠቅም እምቅ አቅምን  በማንቀሳቀስ እንዲወጣ በማድረግ ለዓለም ሁሉ እንዲተርፍ ማድረግ እንችላለን፡፡ ••• ምንጭ (Source):- "የእውቀት መንገድ" በአንተነህ ጌታቸው #ይሸመት… #ይነበብ…
Show all...
ጆራም ቫን ካቨርን . "ኢስላም መታገድ አለበት " በሆላንድ የአክራሪ የኢስላም ጠል ቀኝ ክንፍ አባል በሀገሪቱ ፀረ ኢስላም ሰልፎችን በማስተባበር እና በመምራት ወደር የማይገኝለት " ኢስላም በአውሮፓ ቦታ ሊኖረው አይገባም " እስልምና ለማህበረሰብ ስጋት እና ጠንቅ በመሆኑ በአውሮፓ ህብረት ሀገራት ሊታገድ ይገባል " የሚል አስተሳሰብ አንግቦ በሰፊው የሚንቀሳቀስ እና በሚሊዮኖች ተከታይ በመላው አውሮፓ ማፍራት የቻለ ፖለቲከኛ በአውሮፓ በተለይ በዴንማርክ ፣ ሆላንድ እና ፈረንሳይ የኢስለም መልእክተኛ በሚል በተሰራጨ የካርቱን ምስል በመላው አለም በሚገኙ ሙስሊሞችን ባስቆጣበት ወቅት እንዲሁም በስላቅ ካርቱን ምስል ተሳትፈዋል በተባሉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መወሰድ ሲጀምር ጃራም ለሚያካሂደው ፀረ ኢስላም አብዮት ትልቅ ዕድል ይከፍታል "ጃራም ትክክል ነበር " ኢስላም ከአውሮፓ ማህበረሰብ የኑሮ ዘይቤ ጋር ሊቆራኝ የማይችል በንግግር ነፃነት የማያምን እና ትዕግስት የለሽ በጭካኔ የተሞላ እምነት ነው በአውሮፖ ሊታገድ ይገባል " የሚሉ ድምፆች ይበራከታሉ ጃራም በካርቱን ምስል ተሳትፈዋል ተብለው የተገደሉ የመፅሄት እትመት ጋዜጠኞች በመላው አውሮፓ እልህ እና ጥላቻን በማጫሩ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሞ የኢስላም ዕገዳን ጥሪውን አጠናክሮ ቀጠለ " ትክክለኛ የኢስላም ገፅታ እና የመልእክተኛው ሴጣናዊ ተልእኮ " የሚል መፅሃፍ ለማሳተም እና በመላው አውሮፓ ለማሰራጨት እንቅስቃሴ ይጀምራል ለእትመት ያቀደውን መፅሃፍ በማስረጃ ለማስደገፍ ቁርአን እንዲሁም "አረመኔ ያለውን መልእክተኛ " የህይወት ታሪክ የሚያሳይ በደች ቋንቋ ትርጉም ማንበብ ይጀምራል " ሰይጣናዊ ተልእኮ " ርዕሱን ፅፏል ርዕሱን ሊያጠናክርለት የሚችል ማስረጃ ይኸው ከእርሳቸው መፅሀፍ የተወሰደ " ብሎ በዝርዝር ሊያስቀምጥ ተዘጋጅቷል ከገፅ ወደ ገፅ ይገልጣል ያነባል ነገርግን በማስታውፕሻ ደብተሩ ላይ ከርዕሱ በቀር የእርሱን አመለካከት ሊያጠናክርለት የሚችል አንዳችም ነገር ያጣል መፅሃፍ ስለ ማሳተም እቅዱ በአደባባይ ነበር ለህዝብ የገለፀው ብዙዎቹ የመፅሃፍ እትመቱ ተጠናቆ ለማንበብ ያላቸውን ጉጉት በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲገልፁ ተሰምተዋል ቀናት አልፎ ወራቶች ተቆጥፕሩ ለአውሮፓ ገበያ ይቀርባል የተባለው የመፅሃፍ ህትመት የውሃ ሽታ ሆኖ ይቀራል በጃሪም ዝምታ ግራ የተጋቡት ጥያቄ ማንሳት ጀመሩ የመፅሃፉ ህትመት መች ይጠናቀቃል ? መፅሃፉ በምን ደረጃ ላይ ነው ያለው ? በማለት ጥያቄ ያቀርቡለታል ጃሪም ሲመልስ መፅሃፉ በርዕስ ደረጃ ነው ያለው ፣ ስራዬን ያጠናክርልኛል ብዬ ባነበብኳቸው ቁርአን እና ሀዲስ ውስጥ የኢስላም መልእክተኛ በመልካም ስነምግባር የታነፁ እና ልባቸው በእዝነት የተሞላ ግለሰብ መሄናቸውን እንድገነዘብ ነው ያደረገኝ ብሎ ንግግሩን የቋጨበት መንገድ በምክትል ሊቀመንበርነት የሚመራው የአክራሪ ቀኝ ክንፍ PVV ፓርቲ ደጋፊዎች እና የአውሮፓ ፀረ ኢስላም አቀንቃኞችን ክፉኛ ያስደነገጠ ነበር " በኢስላም የመጨረሻው ነብይ በእርግጥም ከፈጣሪ የተላከ ለመሆኑ ከሰው ልጆች የተለየ ፍፁም በሆነው ስብዕናው መረዳት ችያለሁ " ፀረ ኢስላም መፅሃፍ ለማሳተም ለማስረጃነት ይሆነኝ ብዬ ማንበብ የጀመርኩት ቁርአን እና ሀዲስ አይኔን እንድገልፅ ረድቶኛል በጭፍን ጥላቻ ታውሬ በመልካም ሙስሊሞች ላይ ጥላቻ ስዘራ ኖሪያለሁ ፣ ከጥፋት ተመልሶ ለተፀፀተ አላህ ይቅር ባይ መሆኑንም ካነበብኩት ቅዱስ መፅሀፍ አግኝቻለሁ ከእንግዲህ የአክራሪ ቀኝ ክንፍ የፖለቱካ ፓርቲ አባል ሆኜ በአመራር ላይ መቀጠል አልችልም በፈቃደነት ስልጣን ለቅቄያለሁ የሚታተም ፀረ ኢስላም መፅሃፍም አይኖርም ሳወግዘው እና ስጠላው ወደ ነበረው የእስልምና ኃይማኖት ለመግባት ወስኛለሁ " ነበር ያለው ጃሪም ይህንን አስተያየት መስጠቱን ተከትሎ ከሦስት ሺህ በላይ የእንገድልሃለን ማስፈራሪያዎች እንደ ደረሱት ነገርግን ድንፋታ እና ማስፈራሪያ የቱንም ያህል ቢበራከት እውነትን መቀየር እንደማይቻል ገልጿል ጆራም ቫን ካቨርን እስልምናን ተቀብሎ የኡምራ ጉዞ ያደረገ ሲሆን የእስልምና ጥላቻን ሲቀሰቅስ እና ብዙ ያልተገቡ ቃላቶችን ስሰነዝር የኖርኩ በመሆኔ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እኔን ለነቀበል ጊዜ ይወስድበታል ብዬ አስቤ ነበር ነገርግን ሸሀዳ ከያዝኩበት ደቂቃ ጀምሮ ፍፁም ወንድማዊ በሆነ አቀባበል የቀረበኝ በመሆኑ የዚህ እምነት አንዱ አካል በመሆኔ ይበልጥ እንድኮራ አድርገውኛል*
Show all...
📲ስልኮ ላይ ያሉ ስልክ ቁጥሮች(contacts) ባጣውስ ብለው ይሰጋሉ⁉️ ❍✰✰✰✰✰◉⚇◉✰✰✰✰✰❍ ✍እንግድያውስ የሚቀጥለውን መረጃ ያንብቡ። ✏️ስልክ ቁጥሮች ከሲም ካርዶ ወይም ሰልኮ በተጨማሪ በኢሜል በማስቀመጥ ስልኮ ሲጠፈ ፣ ሲበላሽ፣ በቫይረስ ሲጠቃ ከሚገጥሞት የመረጃ መጥፋት መካላከል እንችላለን። ከዚህም በተጨማሪ አዲስ ሲም ብንገዛ የስልክ ቁጥሮችን አንድ በአንድ ሴቭ በማድረግ ከኢሜላችን ጋር በማገናኘት በአንዴ ወደ ስልካችን ማምጣት ያስችለናል። ለዚህም የሚከተለውን ስቴፕ ይመልከቱ። 1⃣ የስልኮን menu button መጫን ከዛም “Settings.” 2⃣ “Accounts and sync.” መጫን 3⃣ “Add account” button መጫን 4⃣ “Google.” የሚለው አማራጭ መጫን 5⃣ “Next” button መጫን 6⃣ የGmail login መረጃ በማስገባት “Sign in” በመጫን (ይህ ግን ከዚ በፊት አካውን ከነበሮት ነው Gmail አካውን ት ከሌሎዎት “Create” button የሚለው መጫን ከዛ አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት አካውን መፍጠር። 7⃣ “Sign in” button ስንጫን ስልካችን Gmail ላይ ያሉት የስልክ ቁጥር መረጃዎችን ያወርዳል። 8⃣ “Sync Contacts/Sync now” አማራጭ መጫን 9⃣ “Finish” button መጫን ✏️ ከላይ ያሉትን ስቴፖች በመከተል የስልክ ቁጥሮን ማስቀመጥ ይችላሉ። 🖇🖇🖇🖇🖇🖇🖇🖇🖇🖇🖇🖇 ══════❁✿❁ ══════
Show all...
ትረፊ ያላት ነፍስ “የከፈኑ ተሸካሚ” በመባል ይታወቃል ይህ ሰው ሞተና ታጥቦ፣ ተከፍኖ፣ ተሰገደበትና ተቀበረ፡፡ ሌሊት ላይ ከፈን በመስረቅ የሚታወቅ አንድ ሌባ መጣና ከፈኑን ሊሰርቅ መቃብሩን ቆፍሮ ከፈተው፡፡ አስከሬኑ የተጠቀለለበትን ከፈን ሲፈታው አቡ ሰዒድ ከእስር እንደተፈታ ታሳሪ ተነስቶ ቁጭ አለ፡፡ ሌባዉም ባየው ሁኔታ ደንግጦ ሸሸ፡፡ ተከፍኖ የተቀበረው አቡ ሰኢድ ከፈኑን ይዞ ከመቃብሩ ተነሳ፡፡ የቤተሰቦቹን በር አንኳኳ፡፡ በሩ ሲከፈትና ሲያዩት በእጅጉ ደነገጡ ግራም ተጋቡ፡፡ ስለመቃብር ቆፋሪውና ገጠመኙ ነገራቸው፡፡ ሰውዬው ሞቷል ብለው አፈር አልብሰው ቀበሩት ግና በትክክል አልሞተም ነበር፡፡ ቀኑ ያልደረሰው ሰውዬ አላህ በብልሃቱና በኃይሉ የመቃብር ቆፋሪ ሌባ አመጣለትና እንዲከፍት አደረገው፡፡ ከፈኑንም ፈታለት፡፡ አቡ ሰዒድ ከዚያ በኋላ ለዓመታት እንደኖረ ይነገራል፡፡ የሞተው በሁለት መቶ ዘጠና ዘጠኝ አመተ ሂጅራ ነበር፡፡ ኢብኑ ከሢር “አል-ቢዳያ ወን-ኒሃያ” በተሠኘው መጽሐፋቸው ዉስጥ ያሠፈሩት እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡ እባክዎ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼርና ፎርዋርድ በማድረግ ያዳርሱ የሰዎች የተውበት ሰበብ በር ይሁኑ በቻናላችን በሚሰጡ ትምህርቶች ተሳታፊ ለመሆን ይህን ይጫኑና ጆይን ይበሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/sj67633
Show all...
Hule Geb Tube ሁለ ገብ ቲዩብ

ያውቁትን ማሳወቅ ነው የኛ ሰራ !!

https://youtu.be/xFfev2KDxV0

#እውነተኛአጭርታሪክ አንድ ሰውየ በመኪና🚙 እየሄደ እያለ መንገድ ዳር የቆመች ሴት አየ ሲያያት እርዳታ የምትፈልግ ስለመሰለው መኪናውን አቁሞ ወደ እርስዎ ሄደ …… እርዳታ ትፈልግ እንደሆነም ጠየቃት እርስዎ ግን ለረጅም ሰአታት ማንም አቁሞ ስላልጠየቃት እና ሰውየውን ስታየው አለባበሱ የድሃ🥺 ስለሚመስል እርዳታውን አልፈለገቺም እንደፈራች የተረዳው ሰውየ ስሙን ከነገራት በሃላ ሊረዳት እንደሆነ በመንገር ልያረጋጋት ሞከረ.. ከዛም የተበላሸውን መኪናዋን ከአድካሚ ሙከራ ቦሃላ ሰራላት ሴትዮዋም ላደረገላት ነገር ስንት ልክፈልህ ብላ ጠየቀቺው እርሱም የእውነት ልትከፍይኝ ካሰብሽ ሌላ ግዜ እርዳታ ሚፈልግ ሰው ስታዪ እርጂ ከዛም እኔን አስታውሺኝ😇 አላት.…… ከ 2 ቀናቶች ቦሃላ ሴትዮዋ ወደ አንዲት አነስተኛ ካፌ ሄደች , እዛ የነበረቺዉ አስተናጋጅ የ 8 ወር 🤰እርጉዝ ነበረች ,ምታስተናግደው ብቻዋን ሲሆን በጣም እንደተዳከመች ያስታውቃል. ሴትዮዋም ተስተናግዳ ከጨረሰች ቦሃላ ለአስተናጋጅዋ ገንዘብ አስቀምጣላት ወጣች.…… አስተናጋጅዋም ብሩን ስታይ አላመነችም ነበር ,ሴትዮዋ ያስቀመጠችላት የ 1 አመት ዶሞዝዋ የሚሆን ገንዘብ ነበር ከ ብሩ ጋር ሌላ ወረቀት ተቀምጠዋል እንዲህም ይላል " ውለታየ የለብሺም አሁን አንቺን እንደረዳሁሽ እኔንም አንድ ቀን ሰው እረድቶኝ ነበር ልትከፍይኝ ከፈለግሽ አንቺም ሌላ ሰው እርጂ " አስተናጋጅዋም ስራዋን ከጨረሰች ቦሃላ ለባልዋ ደስታዋን ለማካፈል በችኮላ ወጣች የቤት ኪራይ የሚከፍሉት አልነበረባቸውም ነበር ልጅም ልትወልድ ስለነበር ገንዘቡ ያስፈልጋቸው ነበር እቤት ገብታ የሆነውን ለባልዋ ስትነግረው ማመን አቃተው ከሳምንት በፊት አልቀበልም ያለው ክፍያ እቤቱ ድረስ መምጣቱ አስገረመው😏። ➸የዛሬው መልዕክታችን ➸ ''መልካምነት ራሱ ይከፍለናል'' ምንጭ▸▸ ምርጥ መጣጥፎች
Show all...
📱ስልካችንን ስንጠቀም ማድረግ የሌለብን ነገሮች❌ ⚠ በዝናብ ሰዓት Networking የሆኑ ነገሮችን ማጥፋት (Airplane Mode ላይ ማድረግ) (ምክንያቱም ራዲየሽኑ መብረቅ ይስባል) | off wi-fi | Bluetooth | Main Network ⚠ FM(ኤፍ.ኤም) በEarphone አለማዳመጥ | ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ስማርት ስልኮች FM Antenna ስለሌላቸው ኢርፎኑን እንደ አንቴና ነው የሚጠቀሙት - ስለዚህ በኢርፎን ስናዳማጥ Eectromagnetic ራዲየሽኑ ጭንቅላታችን ላይ ጉዳት ያደርሳል። ⚠ ስልክን Charge እያደረጉ ማንኛውንም ነገር አለመጠቀም በተለይም | አለመደዋወል - Calling | Wifi አለመጠቀም | Gaming - ጌም አለመጫወት። ⚠ በEarphone ሙዚቃ ስናዳምጥ Equalizer በመጠቀም ድምፁን Bass ላይ ማድረግ (ምክንያቱም በNormal ድምፅ ስንጠቀም ያለው ለጆሯችን ቀጭን ድምፅ ስለሚያወጣ ያሳምመናል - የHz አለመጣጣም። ⚠ ትልልቅ Magnet (Magnetic field) ያላቸው ነገሮች አቅራቢያ ስልካችሁን አታስቀምጡ። ⚠️ የስልክ ስክሪን Blue Light የሚባል አደገኛ ጨረር ይለቃል በተቻለ መጠን የስልካችንን Brightness መቀነስ / Blue Light Filter App መጠቀም። ⚠ የባትሪ ቻርጅ በጣም Low ሲሆን ወይም ሲቀንስ ስልኩን ያለመጠቀም ልማድ ይኑርዎ | ምክንያቱም ቻርጅ ሲቀንስ የሚረጨው የጨረር መጠን ይጨምራል። ⚠ ሞባይል ተጠቃሚ ከሆኑ ሲነጋገሩ ወደ ጆሮዎ እና ጭንቅላትዎ እጅግ በጣም አያስጠጉ | ቢያንስ ከ5 Centimetre በላይ ራቅ ማድረግ Electromagnetic Radiation ከተባለው አደገኛ ጨረር ራስዎን ይጠብቃሉ፡፡ ⚠ የሞባይል ስልኮን ታቅፈው አይተኙ | በእንቅልፍ ወቅት ባትሪውን ያጥፉ ወይም ከአልጋዎ 1.8 metre በማራቅ ማታ ሲደወል ከሚለቀቀው Electromagnetic ራስዎን በተቻለ መጠን አያጋልጡ፡፡ ⚠ ነፍሰጡር እናቶች ሞባይል ሲይዙና ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ | የጽንሱ ሕዋሳት ለElectromagnetic radiation እጅግ በጣም አለርጂክ ናቸው | ስለዚህ አቀማመጡንም ሆነ አጠቃቀሙን ከጽንሱ ራቅ ባለ ሥፍራ ይሁን | አላስፈላጊ አጠቃቀምን ለምሳሌ ረጅም ሰዓት ማውራት እና ቶሎ ቶሎ መደዋወል መቀነስ አለበዎት፡፡ ⚠ ብረት ነክ ነገሮች ባሉበት ሥፍራ ሞባይል አይጠቀሙ | ብረት የኤሌክትሮማግኔቲክ ራድየሽኑን ወይም የጨረሩን ጉልበት ያጠነክረዋል | ስለዚህ መኪና ውስጥ፣ አውሮፕላን ውስጥ፣ ሊፍት ውስጥ፣ ባቡር ውስጥ፣ ብረት አጥር ወይም በር አካባቢ፣ የብረታብረት ወርክሾፕ ውስጥ፣ ጋራዥ ውስጥ ወዘተ አስቸኳይ ወይም አጣዳፊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በተቻለ መጠን ሞባይል አይጠቀሙ | የሚጠቀሙም ከሆነ ለአጭር ደቂቃ ብቻ ይሁን፡፡ ⚠ በተለይ!!! በተለይ!!! ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ወጣት ልጆች ሞባይልን ባይጠቀሙ ወይም ባያዘወትሩ ይሻላል | ጨረሩ የጭንቅላት ሴሎቻቸውን እጅግ በጣም ይጎዳዋል፤ ለካንሰርም ያጋልጣቸዋል፡፡ ⚠ በበለጸጉት አገሮች ከ15 ዓመት በታች ባሉ ልጆች ውስጥ ለሚከሰተው ሞት በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ምክንያት የጭንቅላት እጢ ነው | ወላጆች ይህንን እውነታ በመገንዘብ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ሞባይል መጠቀምን በመደበኛነት ልጆች አዘውትረው እንዳይለምዱት ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ⚠ አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ሕፃናት ዕድሜያቸው ከ2 ዓመት በታች የሆኑት ሁሉ የጭንቅላታቸው ራስ ቅል በጣም ስስ ነው | ስለዚህ ጨረሩ ሙሉ ለሙሉ በስሱ አጥንት በኩል ወደ አንጎላቸው ሰርፆ ስለሚገባ ጥንቃቄ አድርጉ፡፡ ⚠ ጨቅላ ሕፃናትና ትናንሽ ልጆች አጠገብ ሁነው ሞባይል አዘውትረው የሚነጋገሩ ከሆነ ለአደጋ ስለሚያጋልጣቸው አጠቃቀሙንና አቀማመጡ ከእነርሱ ራቅ ባለ ሁኔታ ላይ ያድርጉት፡፡ ⚠Smartphone አብዝተን ስንጠቀም የሚመጣው በሽታ -Premature Death -Diabetes -Heart disease -የተለያዩ የCancer በሽታዎች -Discomfort -Musculoskeletal Symptoms ‼️ቴክኖሎጂ የራሱ የሆነ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ሁሉ የራሱም የሆነ ከፍተኛ ጉዳት አለው ስለዚህ ዛሬ ያወቃችሁም ሆነ ከዚህ በፊት የምታውቁ በተቻለን መጠን የSmartphone አጠቃቀማችንን እናስተካክል የዛሬው መልዕክቴ ነው። ══════════════════
Show all...
9 ቁጥር 8 ቁጥርን በጥፊ መታው 8 ለምን ትመታኛለህ ብሎ ሲጠይቀው ከኔ በታች ስለሆንክ ብሎት እርፍ። ይሄን የሰማ 8 ቁጥር 7 ቁጥርን በጥፊ ይመታዋል ምን አደረኩኝ ቢለው ከኔ በታች ስለ ሆንክ ይለዋል። ሰባትም በተራው ስድስትን ስድስትም አምስትን አምስት ኣራትን ኣራት ሶስትን ሶስት ሁለትን ሁለት አንድን የበታቼ ነህ እያሉ ይመቱ ጀመር። ከሁለት ቁጥር የመመታት አደጋ የደረሰበት አንድ ቁጥር 0 ሊመታ አሰበና ለምን በፍቅር አላሸንፈውም ብሎ ና ከጎኔ ቁም ሲለው 10 ሆኑና ልቀው ታዩ። ልቀን ከፍ ብለን እንታይ መደቋቆስ ይብቃን ወደፊት!! 💚💛❤️ከፍቅር የማይገኝ ትርፍ የለም ምንጭ ካነበብኩት
Show all...
እንኳን ወደ 2015 ዓ.ም አዲስ አመት በሰላም አሸጋገረን፡፡ አዲሱ አመት የሰላም፣ የጤናና የስኬት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን! መልካም አዲስ አመት!
Show all...
#ድንቅ ጥናት በአንድ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆነ ፕሮፌሰር አንድ ድንቅ ይፋ አደረገ። ጥናቱም የእንግሊዝኛ ፊደላትን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው በቅደም ተከተል አስቀመጠ። ABCDEFG.....YZ የነዚህን ፊደላት አሃዳዊ ቅደም ተከተል አስቀመጠ 123456789.....26። በጥናቱም የእያንዳንዱ ፊደላት በቁጥር ቅደም ተከተል ሚዛን ሰጠ ''A''=1 ''B''=2 ''C''=3.....''Z';=26ን ሰጠ። በመጨረሻም የቃላትን ደረጃ መመዘን ያዘ።(h+a+r+d+w+o+r+k)(8+1+18+4+23+15+18+11)=98% እዉቀት (k+n+o+w+l+e+d+g+e) (11+14+15+23+12+5+4+7+5)=96% ፍቅር(love)=54% እድል (luck)=47% በዚህም መሠረት ከላይ የጠቀስናቸዉ አንዳቸውም አንዳቸውም ለዉጥ 100% ሊሰጡ እንደማይችሉ አስቀመጠ። ታዲያ 100% ሊሰጠን የሚችለው ጉዳይ ምንድን ነው? ገንዘብ ይሆን አንዴ? (m+o+n+e+y) (13+15+14+5+25)=72% አይደለም ምናልባት አመራር ይሆን? (l+e+a+d+e+r+s+h+i+p) (15+5+1+4+5+18+19+8+9+16)=97% አሁንም አይደለም። ለሁሉም ነገር መፍትሄ አለው። አስተሳሰብ፣ አካሄድ፣አኳኋናችንን ስንቀይር ይቀየራል። ስለዚህ የአስተሳሰብ ሁኔታን ሞከረ። (a+t+t+i+t+u+d+e) (1+20+20+9+20+21+4+5)=100% ስለዚህ ዉጤትና 100% ለዉጥ ሊያመጣልን የሚችለው የአስተሳሰብ ለዉጥ ነዉ መሆኑን አረጋገጠ።
Show all...
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለአንድ ደቂቃ 50 ሳንቲም የአገልግሎት በማስከፈል ላይ ይገኛል ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ በ25 ከተሞች አገልግሎት እጀምራለሁ አለ። ከሁለት ዓመት በፊት በወጣ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ጨረታ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያውን የደንበኞች የቴሌኮም አገልግሎቱን በድሬዳዋ አስጀምሯል። ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ከነሀሴ ጀምሮ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ ኩባንያው በመነሻ ኮዱ 07 በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች አካሂዷል። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮች ለድሬዳዋ ደንበኞቹ በመሸጫ ሱቆች ይፋ ያደረገ ሲሆን ኔትወርኩን ለአንድ ወር የሚቆይ የሙከራ አገልግሎት ተጀምሯል። ድርጅቱ የድምጽ አገልግሎቱን በደቂቃ ከሳፋሪ ኮም ስልክ ቁጥሮች ወደ ሳፋሪኮም እና ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርዶች በደቂቃ 50 ሳንቲም የሚያስከፍል ሲሆን ለኢንተርኔት ደግሞ በ10 ብር 120 ሜጋ ባይት፣ 900 ሜጋ ባይቱን በ50 ብር እንዲሁም ሁለት ጌጋ ባይት መጠን ያለውን ኢንተርኔት ደግሞ በ100 ብር ለ30 ቀናት በመደበኛነት በመሸጥ ላይ ነው። ኩባንያው አክሎም እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ 2015 ድረስ ባሉት ስምንት ወራት ውስጥ በ25 የኢትዮጵያ ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደሚጀምር ለአልዓይን አስታውቋል። አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ ኮምቦልቻ፣ ሀረር፣ አዳማ፣ ሀዋሳ፣ጅማ፣ ጅግጅጋ እና ሌሎች ከተሞች በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ አገልግሎቶቹ ከሚጀመርባቸው አካባቢዎች ዋነኞቹ ናቸውም ተብሏል። በኢትዮጵያ ከ126 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው የግል የቴሌኮም ፈቃድ ተሰጠ በፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር እስከ 2023 ድረስ ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ 25 በመቶ፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለግማሹ ህዝብ እንዲሁም በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ውስጥ ደግሞ 98 በመቶ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የቴሌኮም አገልግሎት የመስጠት እቅድ አለኝም ብሏል። ሳፋሪኮም ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕ፣ ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽንና ሲዲሲ ግሩፕን ያካተተ ነው። ተቋሙ ዓለም አቀፍ አጋርነት ለኢትዮጵያ በሚል በሰኔ ወር 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ህጋዊ ፍቃድ መቀበሉ ይታወሳል። ምንጭ አል-ዐይን
Show all...