cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዳዊት ደስታ ‹‹ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል››

Show more
Advertising posts
359
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailable
የአብርሆት ቤተመፅሀፍት ከዛሬ ጀምሮ የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ‼️ በቀን እስከ 15ሺህ ሰዎችን የሚያስተናግደው ቤተመፅሀፍቱ፤ የ24 ሰዓት አገልግሎት በመጀመር የአንባቢያንን ፍላጎት ለማሟላት እንደሚሰራ ነው የተገለፀው፡፡ የአብርሆት ቤተ መፅሀፍት አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ምሽት 12 ሰዓት፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እስከ ምሽቱ 6 ሰአት አገልግሎት እየሰጠ ቆይቷል:: ይሁንና በበርካታ ሰዎች ጥያቄ እና ፍላጎት መሰረት፤ ቤተ መፅሀፍቱ ከዛሬ ጀምሮ 24 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉን ነው የቤተ መፅሀፍቱ ዳይሬክተር ውባየሁ ማሞ የገለፁት:: ከጊዜ ወደጊዜ የአንባቢያን ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ብሎም የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት፤ ቁጥር ሁለት አብርሆትን ለመገንባት ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቁመዋል: የአብርሆት ቤተ መፅሀፍት ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአጠቃላይ 10 ሚሊዮን አንባቢዎችን አስተናግዷል።
Show all...
Photo unavailable
ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ - ዮሐንስ አድማሱ ገጣሚው ዮሐንስ አድማሱ ስለ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ ሕይወት እና ሥራ የጻፈው እና ዮናስ አድማሱ (ዶ/ር) ባሰናኘው መጽሐፍ ዙሪያ የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም አሰናኞችና ተሳታፊዎች ውይይት ያደርጋሉ።
Show all...
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
አንባቢ ትውልድ ስትሠራ፥ ሀገር እየሠራህ ነው። በአሜሪካ ሀገር "1000 Books Before Kindergarden" የተሰኘ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት አለ። ከወላጆች ጋር በመተባበር፥ ወላጆች ልጆቻቸው ኬጂ ከመግባታቸው በፊት 1000 የሕጻናት መጻሕፍትን እንዲያነቡላቸው ያደርጋል። ልጆቹም ኬጂ ከመግባታቸው አስቀድሞ 1000 አጫጭር የሕጻናት መጻሕፍትን በማንበብ እውቅናን ያገኛሉ። ከሁሉ በላይ ደግሞ የማንበብን ጥቅም እና የንባብ ፍቅርን ከልጅነታቸው በውስጣቸው እንዲሠርጽ ይሆናል። ለትውልድ ስናስብ እንዲህም አይነት በጎ ተግባር ይደረጋል። ምንጭ ከFresenbet GY Adhanom የፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ
Show all...