cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

𝙞𝙢𝙖𝙜𝙞𝙣𝙖𝙩𝙞𝙤𝙣

∂ α я к 🌃 % S u n s e t 🌇 . 🔇 ሞገስ ዘአምድ °FB @thoughts_painting

Show more
Advertising posts
1 756Subscribers
+1224 hours
+1027 days
+31730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ተመሳሳይ ቀን ፥ ብቸኝነት ፥ ጸጸት  ፥ እንባ ፥ ሀዘንና መሰልቸት፤ እኚህ ሁሉ ከተሰማሽ ከልብሽ ሁኚ ልቤ ላይ ነሽ..!።
Show all...
«አስማት ላሳይህ» አለችኝ... ድሮ... ድድድድድድሮ «እሺ» አልኩ «አንድ ቁጥር ያዝ በጭንቅላትህ» «ያዝኩኝ» «በል የያዝከውን ቁጥር እርሳው» «ኧኸ? እንዴት?» «እርሳው ብያለሁ እርሳው!» «ሆሆይ... እሺ ረሳሁት!» «ሰባት ነበር የያዝከው አይደል?» «ኧረ ተበላሽ! ሶስት ነበር!» «እርሳው አላልኩህም? እንዴት አስታወስከው!?» እኔ... ዝም! (ትዝ አለሽ?) የረሳሁሽ ልክ እንዳሳየሽኝ አስማት ነው። እንጂማ እንዴት በ«ቃል» የያዙትን መርሳት ይቻላል!? ፦red-8
Show all...
°ሙሉ ነሽ ፥ ምሉዕ በኩለሄ!! በእውነተኛ ሳቆቻችን በማይሰበሩ ፥ ዐለት ልቦቻችን ስለሰሩን ድርብ ፍቅር ስለቸሩን ፥ እኚያ ደግ ሃዘናት መስቀል ተሸክመን ፥ ስለዋልንባቸው የመከራ ቀናት በጠኣም...በምሬት በመካ... በናዝሬት እምልልሻለሁ! በሰማይና በመሬት ፤ በሚመጣው ኣለም ባደግንበት ቀዬ ...ሙሉ ነሽ ፥ ምሉዕ በኩለሄ! እንዳ'ምላክ ምናብ ከሕልም በላይ እንደተዋበ እንደ ዶፍ ዝናብ ምድረበዳ ላይ እንደዘነበ እንደ ውብ ቀለም እንደ ሩቅ ዓለም የሰነፍ ኣሳብ እንደ'ማያውቀው እንደ ጽኑዕ ዕምነት ልክ እንደ ገነት ማርና ወተት እንደሚያፈልቀው ፤ እንደረቀቀው... እንደ ልብ ምት ፥ እንደ እስትንፋስ የሽቱ ጠረን ፥ እንዳ'ለው ነፋስ እንደ ገነት አልባብ እንዳ'ውዳመት ድባብ እንዳ'ምላክ ልደት ሰማይ ከምድር እንዳስታረቀ እንደዮርዳኖስ ማይ በእሳት በመንፈስ እንዳጠመቀ። እንደልደት እንደጥምቀት እንደ ሕማማት እንደመስቀል እንደቡሄ ምሉዕ ነሽ ፥ ምሉዕ በኩለሄ። ሳይጋጌጡ ፥ እንደመቆንጀት እንደሩህሩኋ ፥ እንደ እናት አንጀት ሁሉን እንደመብለጥ ከሞት ደብዳቤ ፥ ሕይወት እንደመግለጥ እንደአብርሖተ ልብ ፥ እንደመገለጥ የሊቅ ብራኄ ሙሉ ነሽ ፤ ምሉዕ በኩለሄ! ከአማልክት ወገን እንደመሰለፍ በሞት ጥላ ስር ፥ ተራምዶ እንደማለፍ እንደ አያት ግሳጼ ፥ እንደሕጻን ልጅ ሳቅ እንደሚወነጨፍ ፥ የዕኩለ ቀን ብራቅ እንደዋሻ መብራት እንዳርበኛ ኩራት እንደአበባ ሰሞን ፥ እንደጸደይ ወራት ጦሙን ለዋለ አንጀት ፥ እንደሚደርስ እራት ሙሉ ነሽ እንደሊቁ ቅኔ እንደ ስነግጥም ምሉዕ ነሽ ለእኔ ሳቅና ለቅሶ ፤ እርካታና ጥም! ብንጠራራ : ብጎናበስም ብጣራ : የአማልክትን ስም ከአንቺ አልፌ አልሄድም ከአንቺ አልፌ አላይም ሁሉን ነሽ በእኔ አለም ጸሐይም ሰማይም። ከራስ መዋደጃ ወደራስ መሄጃ ...እስከዘላለም ጽንፍ ሁሉን ነሽ ፥ ምሉዕ ነሽ የልጅ ብካይና ፥ የእናት ብሩክ ዕቅፍ። ሙሉ ነሽ ፥ ምሉዕ ነሽ! የበረሐ ሀሩሩን ፥ የምታበርድ ጠል የድውይ ንዳዱን ፥ የምትሽር ቅጠል ሙሉ ነሽ እንደግዚሀር እንደቃሉ እንደኪዳን እንደውሉ። ሙሉነሽ ፍጹም ውበት ፥ ንጹህ እውነት እኖርልሽ ተስፋ ፥ እጸድቅብሽ እምነት ሙሉ ነሽ ሳይስቱ ድሕነት ፥ ሳይሞቱ ውብ ገነት። ['ርግማንሽ' ፍቅር አለበት ፥ ጅልነትሽ አሪፍነት።] ሙሉ ነሽ ተምኔትም ትንቢትም ሕልምም እውንም አንቺን እያየን ፥ በእግዜር አናምንም። ሙሉ ነሽ ምሉዕ ነሽ ከነፋስ ከነፍስ ከመልኣክ ከአምላክ ገጽሽ ይረቃል ሳቅሽን ያየ መልክሽን ያየ ፥ ለጽድቅ ይበቃል። ሙሉ ነሽ ፥ ምሉዕ በኩለሄ! -Tewdros Takele
Show all...
~                «ካ'ለም ሁሉ ተለይቼ    ለእሷ ብቆም ሁሉን ትቼ      ቂልነቷ ፡ ሞኝነቷ ከእሷ መሸሽ እንደማልችል ነገረችኝ እንኳን እሷን እኔን ትቼው እያየችኝ!Âť
Show all...
`` ሁልጊዜ ህይወቴን እያባከንኩ ነው በሚል ኣሳብ ከራሴ ጋር እጣላለሁ..! ``                      -ቻክ ቡላኔክ
Show all...
`` እንዴት አመስጋኝ ልሁን? ማንንስ ላመስግን? መጥፎ ጊዜዎቼን ለብቻዬ ኖሪያለሁ! ``                      -ዶይስቶቭስኪ
Show all...
መርሳት የምችለውን ያህል ኖሪያለው፤ ከዛ በኋላ የተፈጠረውን አላስታውስም..።
Show all...
“But In the end, Love is blind, friendship closes its eyes..” `` ግን በመጨረሻም ፍቅር እውር ነው፤  ጓደኝነትም አይኑን ይጨፍናል!።``                                    -Friedrich Nietzsche            ፦Beyond Good and Evil 📖
Show all...
    “But In the end, Love is blind, friendship closes its eyes..” `` ግን በመጨረሻም ፍቅር እውር ነው፤  ጓደኝነትም አይኑን ይጨፍናል!።``                                    -Friedrich Nietzsche           ፦Beyond Good and Evil 📖
Show all...