cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ălŵåýš smile 😊😊 😊

Is peace life insurance Life is short so always smile 😊😊😊😊😊 Always smile 😊😊 😊 😊😊 Always smile 😊😊 😊😊 😊😊 Smile 😊😊😊 Smile 😊😊😊

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
229Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
​​ሁሌም ማስታወስ ያለብን! ▸ ያለፈው መቼም አይመስልም ▸ አስተያየቶች አንተን ሊገልፁህ አይችሉም ▸ የሁሉም ሰው መንገድ የተለያየ ነው ▸ ፍርጃዎች ስለአንተ አይደሉም ▸ አብዝቶ ማሰብ መከፋትን ያመጣል ▸ ደስታ ሁሌም በውስጥህ ነው ▸ አስተሳሰብህ ሙድህን ይወስናል ▸ ፈገግታ ከሰው ወደሰው ይተላለፋል ▸ መልካምነት ምንም ክፍያ የለውም ▸ አስፈላጊ ሲሆን መተው እና ወደ ፊት መራመድ ስህተት የለበትም ▸ በጊዜ ሂደት ነገሮች ሁሉ መልካም መሆናቸው አይቀርም። 😉👍
Show all...
#ከሳይኮሎጂስቶች_ጋር_አትሳፈጥ ! • የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰሩ ወደ ክፍል ገብቶ የእለቱን ወሳኝ ትምርት ለመጀመር ወደ ቦርድ እንደዞረ ፉጨት ሰማ። ወደ ተማሪዎቹ ዞሮ ማን እንዳፏጨ ጠየቀቃቸው ፣ሁሉም ዝም አሉ። ፕሮፊሰሩ ተረጋግቶ ፣ እስክሪቢቶውን ወደ ኪሱ እየከተተ ፣ የዛሬው ሌክቸር እዚ ላይ ያበቃል፣ አለና ፈገግ ብሎ ነገር ግን መጀመሪያ አንድ ታሪክ እነግራችኋለው አላቸው። ሁሉም በጉጉት መጠበቅ ጀመረ "ትላንት ቤቴ እንቅልፍ ስላስቸገረኝ ፣ዝም ብዬ ተነስቼ ነዳጅ ሞልቼ በዛውም ልናፈስ ለዛሬም ጊዜ ለመቆጠብ ከመሽ ወጣሁ ነዳጅ ከሞላሁ በኋላ ከትራፌክ ነጻ የሆነው መንገድ ላይ እየተንሸራሸርኩ ከሆነ ድግስ ቦታ የወጣች የምትመስል ቆንጂዬ ወጣት አየሁ። መኪናዬን አዙሬ እርዳታ እንደምትፈልግ ጠየኳት "ታክሲ እንዳጣች እና ቤቷ እንዳደርሳት ጠየቀችኝ" ጋቢና ገባች ... ማውራት ጀመርን ... ውበት ብቻ ሳይሆን ባወራነው ርእስ ሁሉ በጣም ስማርት ጭንቅላት እንዳላት ከምታወራው መገመት ቻልኩ። ቤቷ እንደደረስን ፣በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንኩ ነገረችኝ ፣እኔም ጥሩ አስተሳሰብ እንዳላት ነግሬያት በሌላ ጊዜ ተገናኝተን ሻይ ቡና እንድንል ጠየኳት በሀሳቤም ተስማማች ፣ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር እንደሆንኩ አውርተን ፣ስልክ ተለዋወጥን። ልንለያይ ስንል አንድ ነገር ላስቸግርህ ስትለኝ ፣ምንም ችግር የለውም አልኳት።"ወንድሜ አንተ የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ውስጥ ተማሪ ነው፣ በኛ ግንኙነት እንዳይጎዳ ቃል ግባልኝ" አለችኝ ...ችግር የለም ብዬ ስሙን ጠየኳት ስሙንም ነገረችኝ። ምናልባት ብዙ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ ስለሚማሩና ተመሳሳይ ስም ሊኖራቸው ስለሚችል ወንድምሽን እንዴት ልለየው እችላለሁ ? ስል ጠየኳት። እሷም:- ወንድሜ አንድ መለያ ባህሪ አለው በሱ ታውቀዋለህ፣ ፉጨት ማፏጨት ያዘወትራል አለችኝ። ከዛ ሁሉም ተማሪ ወደ አፏጨው ልጅ ዞሮ ማየት ጀመረ። ፕሮፌሰሩም :- "የሳይኮሎጂ PHDዬን ተምሬ እንጂ ገዝቼ አይደለም ያገኘውት ና ውጣ ብሎ ጆሮውን ይዞ ከክፍል አስወጣው • #ምንጭ :- ፍትህ ገፅ
Show all...
ቬሎና ቦሎ (አሌክስ አብረሃም) የዮርዳኖስ የሰርግ ቪዲዮ ከሌሎች የሰርግ ቪዲዮወች የሚለየው ሰርጉ ላይ የትራፊክ ፖሊስ አጭር ትእይንት ስለተካተተበት ነበር እንዴት ማለት ጥሩ ነው ለዮርዳኖስ ሰርግ ጊዜ አጃቢ ሁነን ለምሳ ወደሙሽሪት ቤት እየሄድን ነበር ድንገት ከሰማይ ዱብ ያለ የሚመስል የትራፊክ ፖሊስ የሙሽራውን መኪና ከነሙሽሮቹ አስቆመና ‹‹መንጃ ፈቃድ ›› አለ ኮስተር ብሎ ፍጥነቱና መኮሳተሩን ለተመለከተው በሙሽሮቹ መኪና ጥንዶቹ ሳይሆኑ ጥንድ ፈንጅወች ተጭነዋል የሚል ጥቆማ የደረሰው ነበር የሚመስለው ‹‹ምን አጠፋሁ ሙሽራ እኮ ነው የጫንኩት ›› አለ ሹፌሩ ‹‹ እሱን ማን ጠየቀህ የመኪናው ቦሎ አልታደሰም ›› ብሎ ሹፌሩ ጋር ክርክር ገጠመ :: ድፍን ሚዜ ወርዶ ትራፊክ ፖሊሱን መለመን ጀመረ ‹‹ኧረ በናትህ ሙድ የለውም ሰርግና ሞት አንድ ነው ሲባል አልሰማህም ምናለ ብታልፈን ለዛሬ ›› አለች አንዷ ግማሽ ጀርባዋ የተራቆተ መዘነጥ ያለመደባት የምትመስል ዘናጭ በያዘችው አበባ የትራፊክ ፖሊሱን አይን ልትመነቁለው ደርሳ ነበር ‹‹እኮ ...ይሄ መኪና ‹ቴክኒካል› ችግር ቢኖርበትስ በሰርጋችሁ ቀን ሃዘን ሆነ ማለት አይደል ...ሰርግና ሞት አንድ ነው ማለት ያነው አደጋ ሙድ የለውም ብሎ አያልፍም አለ ሙሽሪትን በአይኑ እየቃኘ ‹‹እሱማ ልክ ነህ ግን አሁን ሙሽሮቹን ጭነን ወደምርመራ እንሂድ እንዴ ›› አለ አንዱ ሞቅ ያለው ሹፌር በማሾፍ ‹‹ ሙሽራ ጭነህ እንጦሮጦስ ከመውረድ ይሻላል ›› አለና ኩም አደረገው የሙሽራው ንስሃ አባት ወርደው ትራፊክ ፖሊሱን ለመኑት ‹‹የኔ ልጅ ቃሉ እንደሚል እ.....ጋብቻ ቅዱስ ... ምኝታውም ንፁህ ነውና ማበረታታት ነው ያለብን ›› እያሉ ስብከት ጀመሩ ‹‹አባቴ እኔ መች መኝታቸውን ህገወጥ ነው አልኩ መኪናቸውን እንጅ ›› አለ ትራፊኩ ቀዝቀዝ ብሎ ነበር በብዙ ልመና ትራፊክ ፖሊሱ የሙሽሮቹን መኪና ከለቀቀ በኋላ አንዷ ከጎኔ የተቀመጠች በጣም ቆንጆ እና ነብሷን እስክትስት የዘነጠች ወጣት (ለሰርግ አጃቢነት የተፈጠረች የምትመስል ) እንዲህ አለች ‹‹....ትራፊክ ፖሊሱ ሙሽሪት ሰፈር ነበር በፊት ጠይቋት እንቢ ብለዋለች ወ.......ይ ወንዶች ! ›› አሙቁልኙ እንዲህ አለ በዜማ ‹‹የኛ ሙሽራ ባለቬሎ አስቆማት ባለቦሎ አስቆማት ባለ ቦሎ .... እልልልልልልልልል ቦሎው ያልታደሰ መኪና ተከትለን ወደሰርጉ ቤት .... ይሄ ሁሉ ሲሆን ካሜራ ማኑ እየቀረፀ ነበር ፡፡ የሰርግ ቪዲዮውን ስናየው ታዲያ የትራፊክ ፖሊሱና የሰርገኛው ንትርክ አጠቃላይ ሰርጉን ‹ቬሎና ቦሎ› የሚል ‹ከሆሊውድ የመጡ ባለሙያወች › የተሳተፉበት የፍቅር ኮሜዲ ፊልም አስመስሎት ነበር ፡፡ (የሰርግ ኮሜዲ የሚባል የለም ብየ ነው ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show all...
"በምድር ላይ እጅግ ውድ የሆነውን ንብረት ተቀብሮ የምናገኘው የት ነው? የአልማዝ ወይም የወርቅ ማዕድናት የሚገኙበት ስፍራ? አይደለም! ከፍተኛ የነዳጅ ድፍድፍ ያለበት ምድር? በፍጹም! እጅግ ውድ የሆነውን ንብረት የምናገኘው በመቃብር ስፍራዎች ነው:: ማድረግ የሚችሉትን ሣያደርጉና ያላቸውን እምቅ ሀይል ሣያወጡ ያሸለቡ ሠዎች ናቸው ውዱን ንብረት እንደያዙ እንደተቀበሩ የሚቆጠሩት " ሬቨረንድ ማይልስ ሙንሮ
Show all...
"ካደኩ በኋላ የተማርኩት ትልቁ የህይወት ትምህርት ሁልጊዜም ለራሴ ቃል መታመን እንዳለብኝ እና ሰዎች ከአላማዬ ሊያቆሙኝ ሲሞክሩ መደንገጥ እንደሌለብኝ ነው" ትለናለች ሚሸል ኦባማ። ከምትፈልገው ነገር የሚያቆምህ አመለካከትህ ነው! ሰዎችና ሁኔታዎች ጠንካራ ከሆንክ ከጎንህ ይቆማሉ፤ በአላማህ የማትፀና ወይ ልፍስፍስ ከሆነክ ግን ሁሉም ይጠቀምብሀል፤ ለራሳቸው ፍላጎት መረማመጃ ያደርጉሀል። አላማህን አስቀድም ወዳጄ!
Show all...
✨✨✨ አንድ ሰውዬ ከጥርሶቹ መሀል አንዲት የበሰበሰች ጥርስ ነበረችው ፡፡ ይህቺ ጥርሱ ሌት ከእንቅልፉ እያነቃች በጣም ታሰቃየው ነበር ፡፡ ወደ አንድ ሀኪም ሄደና እንዲነቅልለት ጠየቀው ፡፡ ሀኪሙም የተሻለ መፍትሄ እያለ ለምን ትነቅለዋለህ ብሎ ጥርሱን እየበሳ ካከመው በሃላ በወርቅ ፍቅፉቂ ሞልቶ አሁን ይሻልሀል ብሎ ሸኘው ፡፡ ነገር ግን የበሰበሰው ጥርስ ሳምንት ሳይሞላው ክፉኛ ያሰቃየው ጀመር ፡፡ በዚህ ትእግስት ያጣው ሰውዬው ወደ ሌላ ሀኪም ሄዶ ምንም ሳትለኝ ይህን ጥርስ ነቅለህ ጣልልኝ አለው ፡፡ ሀኪሙም የበሰበሰውን ጥርስ ነቀለለት ሰውዬውም ጤናው ተመለሰ ፡፡ በማህበረሰብም አፍ ውስጥ ብዙ የበሰበሱ ጥርሶች አሉ ፡፡ የበሰበሱ አመለካከቶች ንግርቶችና ሰዎች በጤናማው መሀል ገብተው ያምሱታል፡፡ ህመም ስቃዩ ይሆናሉ ፡፡ ሀኪም ነን ባዮች ደግሞ የበሰበሰን ነቅሎ እንደመጣል ፤ ህመምን ለማስታገስ የወርቅ ፍቅፋቂ እየሞሉ ያስታምማሉ ፡፡እነሱ ግባቸው ጤና ሳይሆን የተሻለ ህመም መፍጠር ነው ፡፡ በህይወታችንም ውስጥ እንደዚህ የበሰበሱ ጥርሶች አሉ፡፡ በሽተኛ ጥርስ በሽተኛ ጨጓራ እንደሚፈጥረው ሁሉ አንዳንድ ሰዎች በሂወታችን ላለ የስቃይ ህይወት መነሻ ይሆናሉ ፡፡ ታዲያ ይህ ጥርስ እስካልተነቀለ ድረስ ጤነኝነት የለም ፡፡ ከህይወታችን መውጣት ያለባቸውን ነገሮች በወርቅ ፍቅፋቂ ከመሙላት ይልቅ ብናስወግዳቸው ትክክለኛ መፍትሄ ይሆናል ፡፡ ካህሊል ጂብራን ❥❥________⚘_______❥❥
Show all...
Me : ይሄ ጫማ ስንት ነው? The ባለ ሱቅ: 3500birr ብቻ Me who went out with 1000birr : ዋጋውስ ጥሩ ነበር ቀለሙ አልተመቸኝም እንጂ👀👀 Him :በፈለግሺው ቀለም አለኝ👀👀 Me :ቁጥሩ አይበቃኝም👀👀👀 Him :በፈለግሺው ቁጥር አለኝ👀👀👀 Me : እግር የለኝም👀👀😂😂
Show all...
°•.• ከመጣክ አትሂድ ከሄድክ ደግሞ እባክህ አትምጣ💔
Show all...
ፍቅር በርህን ሲያንኳኳ ቶሎ አትክፈትለት ምክንያቱም አንዳንድ ሠዎች እንደ ልጅ አንኳኩተው መሮጥ ይወዳሉ🏃‍♂
Show all...
🥀😢🥀😢 ...........መተዋወቅ + ........... መላመድ + ...........ፍቅር + ..........ክፉ ቀን + ..........መለያየት + ..........መናፈቅ + ?????? 😰😨🤢😖 is deep😘🥀
Show all...
በሚወዱክ ሰዎች ልብ ላይ እና በሚጠሉክ ሰዎች ጨጓራ ላይ እንደመቀመጥ ደስ ሚል ነገር የለም💃🏾
Show all...
አንዲት ልጅ ከኋላዬ እየሮጠች ሳይ ዞር አልኩላት ባንተ ውስጥ ውበት እና ወንድነትን አየሁ ወደድኩህም አለችኝ ☺️እኔም ፈገግ አልኩና ከኔ በላይ ቆንጆ ና በወንድነቱም ከእኔ የተሻለ ጓደኛዬ ከኋላዬ ነው ስላት ዞራ መፈለግ ጀመረች ምንም አላገኘችም የታለ ብላም ጠየቀችኝ ☺️ አሁንም ፈገግ አልኩና ወደሺኝ ቢሆን ኖሮ ሌላ ባልፈለግሽ ነበረ...ብያት መንገዴን ቀጠልኩ!!🚶‍♂ አያችሁ አይደለ🤷‍♂ በአንድ ምክንያት የሚወዳችሁ ሰው በሌላ ምክንያት ይጠሏችኋል ለምን እንደሚወዳችሁ የማያውቀው ግን ሁሌም ቢሆን ይወዳችኋል። ✍️
Show all...
ትላንት ማታ እንባ እየተናነቃት የነገረችኝ ታሪኳ ነዉ ። "ufff ሰዉ እንዴት በዚህ ደረጃ ሰዉን ይጎዳል....?" ....ጎበዟ ተማሪ ፀደኒያ... ፀባይ ሰናይዋ ፀደኒያ በአሰላ ከተማ ተወልዳ አደገች። .... የስምንተኛ ክፍልን የሚኒስትሪ ፈተና ወስዳ በከፍተኛ ዉጤት አጠናቀቀች። እስከዚህ ድረስ ምንም እክል አልገጠማትም ነበር ። ባላት ነገር ደስተኛ ነበረች .. ቤተሰቦቿ ከጎኗ ስለሆኑ መኖር ለእሷ ቀላል ነበር።...ሁልግዜም ቢሆን በጨቅላ አእምሮዋ አንድ ነገርን ብቻ ታስባለች ...የሚኮራባትን አባቷን በጉብዝናዋ ስሙን ማስጠራት...ኩራቱን ከፍ ማድረግን ትመኛለች ። ጠንክራ እየተማረች የአባቷን እምነት አግኝታለች። "ልጅማ ፀዲን ወልደናል" የሚለዉ የቤተሰቦቿ ስሜት ለሰፈሩ ሰዎችም ተጋብቶባቸዋል። "ልጅማ ፀዲ ናት...አንተ እዚህ ተጋድመህ ዋል" ጎረቤቶች ምሳሌ የሚያደርጓት ልጅ ነበረች ። .... እድሜዋ እየጨመረ ግን ዝናቡም ማካፋት...ማእበሉም መስገምገም ጀመረ ። ከእራሷ አንደበት ታሪኩ እንዲህ ይጀምራል ።... በህይወቴ ወንድ ተላክፌ አላዉቅም ነበር ። ቀናም ብዬ አይቼ አላዉቅም ። በወቅቱ የስምንተኛ ክፍል ትምህርታችንን ስላጠናቀቅን የሽኝት ፕሮግራም እያሰናዳን ነበር ። የሚያስፈልጉንን እቃዎች ለማሟላት ጓደኛዬ ቤት ሄድን..እየተመለስን ሳለ "እይዉ እስኪ አያምርም!!" አለችኝ ጓደኛዬ.. በአይኖቿ ሳታስነቃ እየጠቆመችኝ...ግማሽ ፊቱ ነበር እንደነገሩ የታየኝ..እንዳለችዉ በጣም ቆንጆ ይመስላል ። ምን እንደነካኝ አላዉቅም ...ብቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ተላከፍኩ "ሸበላዉ ከኋላህ እቃ ጣልክ" አልኩት ጮኽ ብዬ ...ጓደኛዬ ደነገጠች... የምታዉቀኝ አጎንብሼ ነዉና አዲስ ነገር ሆነባት። እኔም ምን አይነት ሀይል ድፍረቱን እንደሰጠኝ አላዉቅም ። ልጁን ያየሁት ከፓርቲዉ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ነበር። ፓርቲያችን ደግሞ እንደነገ ነዉ ። ሰኔ 27/2011 ላይ የተሳተፍንበት ፓርቲያችን ላይ ተገኝቻለሁ። ነገር ግን አካሌ ነዉ እንጂ ነፍሴ የት እንደሄደች አላዉቅም ነበር ። ድግሱ ምንም ሳይጥመኝ ተጠናቀቀ። ከአራት ቀን በኋላ መልሼ ከቤት ወጣሁ...ሰኔ 30 የእህቴ ምርቃት ስለነበር ለታላቅ እህቴ ስጦታ መግዛት ነበረብኝ።... በመንገዴ ዳር ላይ ብዛት ያላቸዉ ወንዶች ተሰብስበዉ ተቀምጠዋል ። በአጠጋባቸዉ ብቻዬን ማለፍን አስፈራኝ...ግን ደግሞ ተመልሼ በሌላ አቅጣጫ መንገዴን ከቀየስኩ የምፈልገዉ ቦታ በቶሎ አልደርስም። እየተርበተበትኩ መንገዴን ቀጠልኩ...ከዉስጣቸዉ አንዱ ተስፈንጥሮ ወጣና እንተዋወቅ አለኝ... ዝም አልኩት... "ስምሽ ማን ነዉ..? አለኝ "ሰላም እባላለሁ" ብዬ ዋሸሁት... "አንተስ ?" አልኩት በተራዬ ... "ኤልያስ " አለኝ... ትዉዉቃችን ላይ ቀና ብዬ በደንብ አላየሁትም ነበር ። "ለከፋ ላይ በጣም ጎበዝ ነሽ " አለኝ ... በድንጋጤ ልሮጥ ደርሼ ነበር...እየተርበተበትኩ ቀና ብዬ አየሁት. ..እራሱ ነዉ ከፓርቲዉ ቀደም ብሎ የለከፍኩት ቆንጅዬዉ ልጅ ነዉ። "ጓደኛሞች መሆን እንችላለን..?" አለኝ.. "እሺታዬን" ገለፅኩለት... በቆምንበት ብዙ ጥያቄዎችን ጠየቀኝ.. በመጨረሻም "ፍቅረኛ አለሽ እንዴ?" አለኝ.. "እንኳን ፍቅረኛ ሊኖረኝ ፍቅር እራሱ ምን እንደሆነ አልገባኝም" አልኩት .. "በቃ እኔ አስረዳሻለሁ" ሳቅኩ እና ዝም አልኩት... "ማታ እንገናኝ...በራችሁ ላይ ልጠብቅሽ...?" ፍቃዴን ጠየቀኝ... እንደማይፈቀድልኝ እያወቅኩ "እሺ" አልኩት ... ማታ ተደብቄ ወጣሁ...አገኘሁት...ትንሽ አወራንና ተመለስኩ። የእህቴ ምርቃት ቀንም ተቀጣጥረን ነበርና ከምሽቱ 1:30 ላይ ላገኘዉ ወጣሁ። "ወድጄሃለሁ" መሰል አልኩት..ከአንደበቴ አምልጦ የወጣ ቃል እንጂ እንደዛ ለማለት አልፈለኩም ነበር። ምን እየሆንኩ እንደሆነ ለእኔም ግራ ነዉ ። "እኔም ወድጄሻለሁ" በቅፅበት ከንፈሬን ሳመኝ..የመጀመሪያዬ ነበር ስሳም። በጣም ደነገጥኩ..የከንፈሬን ድንግልና ወሰደዉ። ... ዝም ተባብለን ቆየን.... "ሰአት ስንት ነዉ" አልኩት... "4 ሰአት" ቤት እንደሚገሉኝ አዉቃለሁ...ጥዬዉ የመሮጥ ያህል እየተቻኮልኩ ወደ ቤት አመራሁ ። የፈራሁት ሆነ ..አባቴ በሩን ይዞ እየጠበቀኝ ነበር ። "ከወንድ ጋር ቁመሽ አይቼሻለሁ...ዝም በይ.. ምንም አይነት ዉሸት እንዳትጀምሪ..ስኮራብሽ ከወንድ ጋር መንዘላዘል ጀመርሽ..? ያዉም በጨለማ!!" ቁጣዉ ያስፈራ ነበር...በያዘዉ ዱላ እና ቀበቶ ሰዉነቴ እስኪዝል ቀጠቀጠኝ። ስልክ እንዳልደዋወልም ተቀማሁ... እንዲህ ተቀጥቅጬም ለኤልያስ ያለኝ ፍቅር ጨመረ እንጂ አልቀነሰም...ፍርሃት አይሰማኝም ነበር። ቤቱ ባዶ ሲሆንልኝ ተደብቄ እየወጣሁ አይቼዉ እመለስ ነበር ። 2012 ዓ.ም 9ኛ ክፍል ገባሁ...ትምህርት ተጀመረ ። አሁን እንደፈለግን እንሆናለን ብዬ ተስፋ አደረግኩ ። ግን ኤልያስ ጥሎኝ ጠፋ ። የት እንደሄደ እንኳን ማወቅ ሳልችል ተሰወረብኝ ። ትምህርቴን መማር አልቻልኩም ። እሱን አለማየት ጎዳኝ..ናፍቆቱ አሰቃየኝ ። ሁሉ ነገሬን ትቼ እሱን ማሰብ ሆነ ስራዬ ። ከall ትመራለች ብዬ ስጠበቅ ከ72 ተማሪ 24ተኛ ወጣሁ ። ይሄ ቤተሰቤን አስደነገጠ .. ቀጣይ ሴሚስተር አስተካክላለሁ ብዬ ቃሌን ሰጠሁ። ትምህርቴን መማር ጀመርኩ...ትምህርቴ ላይ አተኮርኩ... እየረሳሁት መጣሁ ። የኮቪድ ወረርሽኝ ስለተከሰተ ትምህርት መልሶ ተዘጋ ። ኤልያስ ወደ ሰፈር ተመለሰ ...መልሼ አየሁት ...አልቻልኩም ሩጬ ጉያዉ ዉስጥ ገባሁ ። አቀፍኩት ። "የት ጠፍተህብኝ ነዉ? " አልኩት "ትምህርት ሸገር ነዉ የምማረዉ" አለኝ "ለምን አልነገርከኝም...?" "ስልክሽን ተቀምተሻል...ከቤት መዉጣት አትችይም ..በየት ብዬ ልንገርሽ...? ምን ላርግ?" አለኝ "በሌላ ስልክ ስደዉልልህ ብታነሳልኝ ምን አለበት...አባቴ አያፍርብኝም ነበር። ከትምህርቴ ባንተ ምክንያት ወረድኩ... ረሳሁህ ስል ለምን መጣህብኝ?" በሰጠኝ ተራ ምክንያት እየተናደድኩ ጥዬዉ ሄድኩ። ለእኔ እሱን መተዉ ከባድ ነበር... እራሴን መግታት አልቻልኩም.. በቀጣዩ ቀን አብሬዉ ድጋሜ ፍቅር ጀመርኩ። አብረን ብዙ የማይረሱ ጊዜዎችን አሳለፍን። ቆይተን ወሲብ እንድናደርግ ጠየቀኝ ። "አይሆንም" ነበር መልሴ.. "አንቺ ስትፈቅጂ ይደርሳል" ብሎ ተስማማን... ጥቂት ቀን ቆይቶ "አንድ ለሊት አብረን እናሳልፍ ...ምንም አይፈጠርም" አለኝ.. ባንገራግርም ተስማማሁ ። ጓደኛዬ እነሱ ቤት እንድናድር አባቴን ለምና አስፈቀደችልኝ ። የኤልያስ ጓደኛ ተከራይቶ የሚኖረበት ቤት ነበር ። ወደዛዉ ልናድር ሄድን ...ስገባ አቅሌን ሳትኩ ። በደስታ የልብ ምቴ እየፈጠነች ነበር ። ቤቱ ተዉቦ ነበር..ፊልም ላይ እንዳየሁት አይነት ነበር። በሻማ ተሽቆጥቁጧል ። "እራት ስሪልኝ..ለዛሬ ህጋዊ ሚስቴ ነሽ" አለኝ እየሳቀ... ፍርፍር ልሰራ ተነሳሁ ግን አልተሳካልኝም ሁለት ጌዜም አረረብኝ... "እስኪ እኔ ልሞክር..የዘመኑ ሴቶችኮ " እየሳቀብኝ ፍርፍሩን አዘጋጀዉ ። እራት በልተን እንደጨረስን መጠጣት አለብሽ ብሎ ሻይም አፈላ...ባልፈልግም ጠጣሁለት ። ከጠጣሁ በኋላ ወዲያዉ ነበር እንቅልፌ የመጣዉ... ተቃቅፈን ተኛን...ለደቂቃዎች ዝም አልን። "ፀዲ sex እናርግ?" የባለፈዉን ጊዜ ጥያቄ መልሶ አነሳዉ... "ደስ ካለህ እሺ " ...ቤት ከገባሁ ጀምሮ የነበረዉ ሁኔታ ዉስጤን ተቆጣጥሮት ስለነበር ይመስለኛል የፈቀድኩለት ።... በፍጥነት ልብሱን አወላልቆ ከላዬ ላይ ወጣብኝ ።
Show all...
የሆነዉን በደንብ ማስታወስ ይከብደኛል ። ጠዋት ስነሳ አልጋዉ በደም ተጨማልቋል ። እንዴት እንደሆነ የማስታዉሰዉ ነገር አልነበረም። ለቤተሰቦቼ ዘንድሮ አጎቴ ጋር ነዉ መማር የምፈልገዉ አልኳቸዉ ። አጎቴ የሚኖረዉ አዲስ አበባ ሰሚት አከባቢ ነዉ። ይሄ ሁሉ ከኤልያስ እንዳልለይ ነዉ ። በኤልያስ ፍቅር ሰክሬያለሁ ። ከእሱ ለአፍታም ልርቅ አልፈልግም ። ወደ አዲስ አበባ ሄድኩ ። ኑሮዬ እዛዉ ሊሆን ...ኤልያስ የሚማርበት ትምህርት ቤት ልገባ ነበር ሃሳቤ። ግን ሞልቷል ተብዬ ገርጂ ያለዉ eto parent ትምህርት ቤት ገባሁ። ከዛች ምሽት በኋላ ሁሉ ነገሩ ቀዘቀዘብኝ ። አምስት ጊዜ ብደዉል አንዴ ቢያነሳ ነዉ ። ጆሮዬ ላይ የሚዘጋብኝም ቀናቶች ጥቂት አልነበሩም ። አለም ጨለመብኝ...ግዜያቸዉ ያለፉ መድሀኒቶችን ሰበስቤ በብዛት ወሰድኳቸዉ ። እራሴን ለማጥፋት ሞከርኩ ። ሆስፒታል ገብቼ ግን በ3ተኛ ቀኔ ተሽሎኝ ወጣሁ። መሞትም አልቻልኩም መኖርም አልቻልኩም ። ሆስፒታል ሁኜ የአጎቴ ልጅ ለጓደኛዉ ደወለችለት... "ጎደኛህን እንደገደላት ንገረዉ ..ገላሃታል በለዉ" አለችዉ... ኤልያስ በኔ ስልክ ደወለ "ምን ሆንሽ "አለኝ "ካላንተ ከምኖር ብሞት ይሻለኛል " አልኩት... "ሙቺ ከፈለግሽ" አለኝና ስልኩን ጠረቀመብኝ... ምድር እና ሰማይ ተገለባበጠብኝ..መኖር አቆምኩ። ከአጎቴ ቤት ጎን የምትኖር በእምነት የምትባል ልጅ ነበረች ። "በእነዚህ ትረሺዋለሽ " እያለች ሲጋራ ፤ ጫት እና መጠጥ አስለመደችኝ ። ትምህርት እያልኩ እየወጣሁ ዉሎዬ ሺሻ ቤት ሆነ ። ቀስ እያልኩ ትምህርቴን ጨርሶ አቋረጥኩት ። ወደ አሰላ ተመለስኩ ። የሚያዉቀኝ ሰዉ ሁሉ አዘነ ። የምፈራዉ ቤተሰብ እንኳን እኔን ማስቆም አቃታቸዉ ። ሰክሬ ከአገኘሁት ወንድ ጋር እጋደማለሁ ። ቴሌግራም ላይ ያወራኝ የነበረ ሳሙኤል የሚባል ልጅ ነበር። እንደሚያፈቅረኝ ሲነግረኝ "እኔም አፈቅርሃለሁ " አልኩት... ተገናኘን..ግን የሲጋራ ሱሴን መታገስ አልቻልኩም ። አንዴ መጣሁ ብዬዉ ማጨስ ጀመርኩ ። ተከትሎኝ ነበርና አየኝ ። "በኤልያስ ምክንያት ነዋ እንዲህ የሆንሽዉ? እሱ የቀጣሽን በመሉ እኔ እክስሻለሁ ..እባክሽ ማጨስ አቁሚ" እያለቀሰ ለመነኝ ። እንደዚህ ሲለኝ ልጁን ጠላሁት። ጥዬዉ ሄድኩ ። በዛዉ ምሽት ጭፈራ ቤት ገባሁ ። አብሮኝ ይማር የነበረ ልጅ አገኘሁ ። አብረን መጠጣት ጀመርን...ያለኮንዶም ወሲብ አደረግን ። ከቀናት በኋላ ሱስ ያስጀመረችኝ ልጅ ደወለች "ሸገር ነይ ...ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ቤት ተከራይተን እየኖርን ነዉ። ተቀላቀይን " አለችኝ ደስ እያለኝ ሄድኩ ..ብር አይቸግረንም ። እኔ ጫት ቤት ሻይ ቡና ተቀጥሬ እሰራለሁ ። አንደኛዋ ደግሞ ካፌ መስተንግዶ መስራት ጀመረች። ቀሪዎቹጨሁለቱ ከወንዶች ብር ይቀፍላሉ ። በዚህ ሁኔታ ኑሮን መግፋት ጀመርን ። ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ግን ፔሬዴ ቀረ ። ተመርምሬ እርጉዝ መሆኔን አወቅኩ ። ማስወረድ አልፈለኩም..እኔ እንጂ ልጄ ጥፋተኛ አልነበረምና በሆዴ ተሸከምኩት ። 3ተኛ ወሬን እንደያዝኩ አያቴ ታመመችና ወደ አሰላ ተመለስኩ። "እዚሁ ትወልጂዋለሽ ..የትም አትሂጂ" አለችኝ... "እኔ ሱሰኛ ስለሆንኩ እዚህ መሆን አልፈልግም" አልኳት ... ብዙ ስትለምነኝ ከአጠገቧ ሆንኩ ። ያኔ አታጭሽ እያለ ሲለምነኝ የነበረዉ ኤልያስ ፈልጎ አገኘኝ... ሆዴን አይቶትም "አትዝጊኝ...አትራቂኝ" አለኝ...በጣም ተገረምኩ..እንዴት እንዲህ ሁኜም ተቀበለኝ...? እሱስ ወንድ አይደል..እንዴት አይርቀኝም...? ቴሌግራም ላይ መልሰን ማዉራት ጀመርን ። "እኔ ስጋሽን አይደለም ያፈቀርኩት..እባክሽ አብረን እንሁን" አለኝ... "አይሆንም ሳም...በሁለት ልቦች ዉስጥ ፍቅር ከሌለ ሊሆን አይችልም..ሲቀጥል እኔ እናት ልሆን ነዉ ።" አልኩት... "ልጅ ስላለሽ ፍቅሬ አይቀንስም እባክሽ" እያለ በተደጋጋሚ ሲጠይቀኝ ባላምንበትም አብረን ሆንን። ልሞክረዉ ብዬ ተቀበልኩት ። ጉንጬን እንኳን ስሞኝ አያዉቅም ። ዝግጁ ስትሆኚ ይደርሳል ይለኛል ። ቀስ በቀስ ልቤ ኤልያስን እያስወጣዉ በምትኩ ሳምን እያፈቀረዉ መጣ ። ሱሴንም እየቀነስኩ መጣሁ ግን ማቆም ከብዶኝ ነበር ። ... "ሱስሽን ካላቆምሽ ልጁ ይሞታል" አሉኝ ሀኪሞች... ከእራሴ ጋር እየታገልኩም ቢሆን ለልጄ ስል ለማቆም ሞከርኩ ። ከሳም እገዛ ጋር ለማቆም ቻልኩ ። 8ተኛ ወሬን እንደያዝኩ ግን ሲጋራ ሲጨስ ሸተተኝና ሳላጨስ ቀረሁ ። ሱሱ ከመሬት ጣለኝ ። በቆምኩበት አዙሮኝ ወደቅኩ ። ሆስፒታል ገባሁ ። ህፃኑ ከማህፀኗ በቀዶ ጥገና መዉጣት አለበት ። ካልፈጠን ሁለቱም ይሞታሉ" አሉ ሀኪሞች... ተቀድጄ በሰላም ወለድኳት ። የምታምር ሴት ልጅ ተገላገልኩ ። ሳም "እኔ አባቷ እሆናለሁ " አለኝ ። ከዚህ ሁሉ በኋላ ኤልያስ ተመልሶ መጣ...ይለምነኝ ጀመር "አፈቅርሻለሁም" ይለኛል ። ግን እስካሁን ቢለምነኝም ልመናዉ ከንቱ ሆኗል። የሳም እንክብካቤ ኋላዬን እንዳላይ ረድቶኛል ። ሳም በየዋህነቱ እና በእዉነት ፍቅሩ ከኤልያስ ነጥቆ የእራሱ አርጎኛል ። ልቡ ዉስጥ ሸሽጎኛል ። አሁን አያቴ ቤት እየኖርኩ ነዉ ። ልጄም በጤና እያደገችልኝ ነዉ ። ከተቀላቀለችን 3ተኛ ወሯን ይዛለች ። እናቴ እየተመላለሰች ታየኛለች ። አባቴ ግን ይቅር አላለኝም..ይቅር እንደሚለኝ መልሶ ልጄ ብሎ እንደሚጠራኝ ተስፋ አደርጋለሁ ። ክብሬን የሰጠሁት ሰዉ ክብሬን ካለቦታዉ አስቀምጦት ቢያቆሽሸኝም..ቤተሰቤን ፤ ጓደኞቼን ትቼ አዲስ አበባ የጓደንኩለት ሰዉ በሰዉ ሀገር ባይተዋር አርጎኝ ህይወቴን ቢነጥቀኝም ፈጣሪ በሳም እና በልጄ ህይወቴን መለሰልኝ ። ተመስገን!! .. ያካፈልኳችሁ ሴት እህቶቼ ከእኔ እንድትማሩ ነዉ ። ልታፈቅሩ ትችላላችሁ ። ግን ስሜታችሁን ብቻ አትከተሉት .. አስተወሉ .. ጓደኛችሁን መርምሩት ። "አፈቅርሻለሁ " ያለሽ ሁላ ከልቡ ላይሆን ይችላል ። እስኪጠቀምሽ በኋላም እንደ እቃ አዉጥቶ ሊወረዉርሽ ፈልጎ ይሆናል ። ስጋሽን እንጂ ነፍስሽን ላይሆን ይችላል ያፈቀረዉ። እባክሽ ራስሽን የምትሰዊለትን ሰዉ ምረጪ ። በእኔ የደረሰ አይድረስብሽ!! አመሰግናለሁ ፀልዩልኝ ። 🙏 🔎 ከባለታሪኳ አንደበት በእናቱ ልጅ ተፃፈ። የተሰማችሁን ግሩፑ ላይ በመግባት ፃፉሏት ታነበዋለች ። አይዞሽ ከጎንሽ ነን በሏት !! እሷ ይሄን ለማካፈል ታሪኳን ወደሆላዋ ተመልሳ ለመናገር ታግላለች ። እሷ ስታወራኝ አይኖቼ እንባ ቋጥረዉ ነበር ። ድምጿ ዉስጥ የታፈነ ሳግ ይሰማኝ ነበር ። ጥልቅ ህመሟ ተጋብቶብኝ ዉስጤ ታዉኮ ነበር ። የሚስፈነጠሩት ቃላቶቿ ዉስጥ የታፈኑ ጩኸቶች ነበሩ። ቁስሏን እያስታመመች ነዉ ያወጋችልኝ ። ለኔ ጀግናዬ ናት ። ለእናንተ ስትል ከእራሷ ታሪክ ጋር እየታገለች ነበር ስትነግረኝ የነበረዉ ። እንወድሻለን❤️ ብሩህ ወደፊትም እንደሚገጥምሽ አናምናለን። 💫💥 ግሩፑ ዉስጥ መልካም ምኞታችሁን አስቀምጡላት....👇👇 https://t.me/lovestorey1 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══
Show all...
እስኪ ያለምንም ምክንያት አምላካችንን እናመስግነው ሰንት #አካል ጉዳተኛ ስንት #በልቶ ማደር ያልቻለ አለና ቢያንስም ቢበዛም እስኪ ተመስገን እንበል ምንም አይነት ክፉ ነገር ቢገጥማችሁ ቢመቻችሁም ባይመቻችሁም ሁሉም ነገር #ተመስገን ብሎ ማሳለፍ ትልቅነት ነውና ካለን ለሌላቸው አካፍለን ተሳስበን በፍቅር በደስታ እናመስግን!!
Show all...
መጎዳትህ በአንተ ስህተት ባይሆንም . . . . ከስብራትህ መዳን ግን የአንተ ሃላፊነት ነው!😊👍👍
Show all...
መሳሳት አይደለም የሰው ልጅ ድክመቱ አለመማሩ ነው ካለፈው ስተቱ😉👍
Show all...
' አዲሱ የትምህርት ስርዓት ' በዘንድሮ 2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን በሙከራ ደረጃ እንዲሁም በ2015 ዓ/ም ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ የሚገባው አዲሱ የኢትዮጵያ 🇪🇹 የትምህርት ስርዓት ምን ምን ጉዳዮችን አካቷል ? - አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለሀገር በቀል እውቀት ትኩረት የሰጠ ነው። - ከመዋለ ህፃናት አንስቶ የግብረገብ ትምህርት መስጠት የሚያስገድድ ነው። - በብቃት ላይ የተመሰረተ ፣ የሞያ እና የቀለም ትምህርትንም አብሮ በሚያስኬድ መልኩ የተቀረፀ ነው። - ከምርት እና ከተግባር ጋር የተሳሰረ ብቃትን 21ኛው ክ/ዘመን የሚፈልገውን እውቀት የሚያስጨብጥ ፣ በቴክኖሊጂ ተደግፎ እንዲሰጥ የሚያስችል ነው። አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተማሪዎች ከቅድመ መደበኛ እስከ 6ኛ የግብረገብ ትምህርት አይነት፣ ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ የስነዜጋ ትምህርት እንዲወስዱ ያስገድዳል። ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ይሰጥ የነበረው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትምህርት ከ7ኛ ክፍል እንዲጀመር ያደርጋል። የጤና፣ የግብርና ትምህርት አይነቶችም ተካተዋል። 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ ተማሪ በመለስተኛ ባለሞያነት በዲፕሎማ ተመርቆ ወደስራ እንዲገባም ያስችለል። ለዚህም ከ11ኛ ክፍል ጀምሮ ከመደበኛ ትምህርቶች በተጨማሪ ተማሪዎች በመረጡት የትምህርት መስክ በተግባር የተደገፈ ስልጠና የሚያገኙበት እንድል ተመቻችቷል። 11ኛ እና 12ኛ ክፍል በሁለት ይከፈላሉ የማህበራዊ (ሶሻል) እና የተፈጠሮ (ናቹራል) ሳይንስ በሚል። ተፈጥሮ ሳይንስ (ናቹራል) የመረጠ ተማሪ ሰባት (7) ትምህርቶችን ለአካዳሚክስ ይጠቀምበታል፤ ይህም ለ12ኛ ክፍል ፈተና የሚቀመጥበት ነው። እነዚህም የትምህርት አይነቶች ፦ - እንግሊዘኛ - ሂሳብ - ፊዚክስ - ኬሚስትሪ - ባይሎጂ - ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ - #ግብርና ናቸው። " ግብርና " 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲማሩ ይደረጋል ፤ በብሄራዊ ፈተናም (የ12ኛ ክፍል ፈተና) እንዲመጣም ይደረጋል። ከ7ቱ ውጭ ደግሞ በምርጫ ተማሪዎች 5 የትምህርት መስኮችን መምረጥ ይችላሉ፤ እነዚህ መርጠው የሚማሩት ሲሆን ፤ የትምህርት መስኮቹ ፦ - ማኑፋክቸሪንግ - ኮንስትራክሽን - ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ - ጤና ሳይንስ እና ግብርና ሳይንስ ናቸው። ከአምስቱ አንዱን መርጠው ይማራሉ። የማህበራዊ (ሶሻል) ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ 6 የጋራ ትምህርቶች አላቸው ለ12ኛ ክፍል ፈተና የሚያቀመጡበት / ጥሩ ነጥብ ካላቸው ወደዩኒቨርሲቲ የሚገቡበት ነው። ከዚህ ውጭ ሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ፦ - ከቋንቋ እና ማህበራዊ ሳይንስ - ቢዝነስ - ስነ ጥበባት መካከል አንዱን መርጠው ይማራሉ። ከላይ የተገለፁት ኮርሶች የሁሉም ሞጁሎች ተዘጋጅተው አልቀዋል። በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠነ 12ኛ ክፍልን ያጠናቀቀ ተማሪ ለማፍራት ትምህርት ሚኒስቴር ከተለያዩ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነትን ተፈራርሟል። ሰባቱ ተቋማት የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በመረጡት የትምህርት መስክ ተግባራዊ ትምህርት እንዲያገኙ ማመቻቸት ይጠበቅባቸዋል። አዲሱ የኢትዮጵያ ትምህርት ስርዓት በዘንድሮው ዓመት 2014 ዓ/ም እስከ ስምንተኛ ለሙከራ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ፣ 11ኛ ክፍል በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ባሉ ትምህርት ቤቶች ስራ ይጀምራል። የ8ኛ ክፍል እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለክልላዊ እና ብሄራዊ ፈተና የሚዘጋጁበት ዓመት ስለሆነ እነሱ ላይ ተፈፃሚ አይሆንም። በ2015 ሙሉ በሙሉ በመላው ሀገሪቱ በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች ተግባራዊ ይደረጋል። #NB : ከላይ ያለው መረጃ ሙሉ በሙሉ የተገኘው ከ30ኛው የሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ ነው። "በ2014 #በሙከራ ደረጃ ይትገበራል " ማለት ምን ማለት ነው ? በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ላይ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ይደረጋል ማለት ነው። ለምሳሌ ፦ አንደኛ ደረጃ ከ40 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች አሉ ከነዛ ውስጥ የተወሰኑ (በሺዎች የሚቆጠሩ) ተመርጠው ሙሉ ትግበራ ይደረግባቸዋል። አንድ ትምህርት ቤት ከ1 እስከ 12ኛ ክፍል ቢኖረው ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ውጭ በትምህርት ቤቱ ሙሉ ትግበራ ይደረጋል። በዚህም ሙከራ ተብሎ የተገለፀው በሁሉም የሀገሪቱ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለማይተገበር ነው። ነገር ግን በተመረጡት ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይተገበራል። ሙከራ ይደረግባቸዋል በተባሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ደግሞ ለተወሰኑ ክፍሎች የድሮው ለተወሰኑ ክፍሎች አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይተገበራል ማለትም አይደለም ፤ በትምህርት ቤቱ ሙሉ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይተገበራል። (11ኛ ክፍል ግን በመላው ሀገሪቱ ተግባራዊ ይደረጋል) - ይህን መረጃ ከቀድሞው የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ነው ያገኘነው) በስርዓተ ትምህርቱ ዝግጅት ላይ ፦ - በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ - በመቐለ ዩኒቨርሲቲ (መጀመሪያ አካባቢ-ከግጭቱ በፊት) - በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ - በጅማ ዩኒቨርሲቲ - በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ከ200 በላይ ምሁራን ተሳትፈውበታል። #TikvahFamily @tikvahethiopia
Show all...
#ገንዘብ:- እኔን አግኝና ሁሉንም ተዋቸው ይልሀል! #ጊዜ:- ሁሉንም ተውና እኔን ተከተለኝ ይልሀል! #ፍላጎትህ:- ሁሉንም ተውና ለኔ ብቻ ተጋደል ይልሀል! #ፈጣሪ_ግን:- እኔን አስታውሰኝ ሁሉንም እሰጥሀለው ይልሀል☝️❤️❤️😍😍
Show all...
ወ/ሮ ሎሚ በዶ የ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ በመሆን ተምርጣለች፡፡ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በከፍተኛ የመንግስት ሀላፊነት ሲሰሩ ነበር፡፡በ7 ድምፀ ታዕክቦ እና በአብላጫ ድምፅ ተመርጠዋል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
#መፍራት_ስትጀምሩ_መኖር_ታቆማላችሁ!! የናዚ ተጽእኖ በከፋባቸው ዓመታት ጃኔዝ (Janez Rus) የተባለ አንድ ሰው በናዚ ዘመን በነበረው አቋም ምክንያት በቀልን በመፍራት ለ32 ዓመታት ከአንድ ስፍራ ሳይወጣ እንደተደበቀ ይነገራል፡፡ ይህ ወጣት በፍርሃት ከመደበቁ በፊት የጫማ ስራ ባለሞያ ነበር፡፡ ፍርሃቱ ከነገሰበት በኋላ ግን የቀረውን የወጣትነቱን ዘመን በመደበቅ ነበር ያስበላው፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በJune, 1945 ይህ ወጣት በእህቱ እርሻ ውስጥ በሚገኝ ቤት (Farmhouse) ውስጥ ለ32 ዓመታት ተደብቆ ሲኖር የእናቱን ቀብር እንኳን ለመካፈል አልወጣም፡፡ ከዚህ ስፍራ ከወጣ በኋላ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣ “ከተደበኩበት ቦታ ሆኜ ውጪ የሚገኙ ሰዎች ሲደሰቱና ሲስቁ ስሰማ ምርር ብዬ አለቅስ ነበር”፡፡ ይህ ወጣት በእነዚያ አመታት ውስጥ ያገኘውን ነገር እየበላ ከላይ ሆኖ ወደታች ያለውን መንደር ከማየት ውጪ ምንም ነገር አላደረገም፡፡ ፍርሃት እንዲህ ይልሃል … • አትመልከት - አንድ ነገር እንዳታይ! • አታድምጥ - አንድን ነገር እንዳትሰማ! • አታስብ - አንድ ድምዳሜ ላይ እንዳትደረስ! • አትወስን - ስህተት እንዳትሰራ! • አትራመድ - እንዳትወድቅ! • አትኑር - እንዳትሞት! • አትማር - ፈተና እንዳትወድቅ! • አትውደድ - እንዳትጎዳ! በሕይወትህ ልታነግሱ የምትችሉት ስሜት አንዱን ብቻ ነው - የፍርሃትን ወይም የመኖር ድፍረትን፡፡ አንዱ እንዲነግስ ስትፈቅድለት ለሌላኛው የባርነት ትእዛዝን እያስተላለፍክ ነው፡፡ ፍርሃት ሲነግስ የመኖር ጣእም ይጠፋል፡፡ ተነሱና ፈጣሪን ተማምናችሁ ቀና ብላች ኑሩ! ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
Show all...
የማትፈፅመውን ነገር ቃል አትግባ! በአንድ ቀዝቃዛ ምሽት አንድ ቢሊየነር ጎዳና ላይ ሲዘዋወር ከአንድ ደሀ ሰው ጋር ይገናኛል ቢሊየነሩም ''በዚህ ቀዝቃዛ ምሽት ሙቀት የሚፈጥር ኮት ሳትለብስ ስትዞር አይበርድህም'' በማለት ደሀውን ሰውዬ ይጠይቀዋል ''የለኝም እንጂ ቢኖረኝ እለብስ ነበር'' በማለት ደሀው ሰውዬ ይመልስለታል ቢሊየነሩም ''ትንሽ ታገሰኝ ከቤት አንዱን አመጣልሀለሁ'' በማለት ውጭ እንዲጠብቀው ነግሮ ወደ ውስጥ የገባል ደሀው ሰውየም ''በጣም ተደስቶ እንደሚጠብቀው ይነግረዋል'' ቢሊየነሩ ወደ ውስጥ እንደገባ የሱን ምላሽ የሚፈልጉ ጥሪዎችን በመመለስ እና በሌሎች ጉዳዮች ይጠመድ እና ሰውየውን ረስቶት ያድራል። ጠዋት እንደነቃ የማታው ሰውየ ትዝ ይለውና ከቤቱ ወጥቶ ሰውየውን ሲፈልገው ሰውየው በቅዝቃዜ ህይወቱ አልፎ ያገኘዋል ቢሊየነሩም ሀዘን ተሰምቶት ዙሪያውን ሲመለከት ደሀው ሰውየ ከመሞቱ በፊት የፃፈውን ማስታወሻ ያገኛል አንስቶ ሲመለከተው ''ሞቃት ልብሶች ባልነበሩኝ ግዚያት ሁሉ ሁሌም እንደማደርገው ቅዝቃዜውን የመቋቋም አቅም ነበረኝ ነገር ግን አንተ እንደምትረዳኝ ቃል ስትገባልኝ በቃልህ ስለተማመንኩ እና ስለጓጓሁ እንደ በፊቱ ብርዱን መቋቋም አልቻልኩም'' Source: Psychology in our lives የታሪኩ ፍሬ ነገር! 🔹 ልትፈፅመው የማትችለዉን ቃል አትግባ። ቃልህን ከሰጠህ ግን ጠብቅ። አደርጋለው ያልከዉን አድርግ። የማትችለዉ ነገር ከሆነ እውነቱን ተናገር። ምክንያቱም በራስህ ያለህን እምነት ቀስ በቀስ እየሸረሽ ስለሚያጠፋ እንዲሁም በሰዎች ዘንድም እምነት ሰለሚያሳጣ ነው። melkam_enaseb
Show all...
Demera Night ✝️🌼✝️🌼✝️🌼✝️🌼
Show all...
✝️🌼🌼✝️🌼🌼✝️🌼🌼✝️ መስቀል ሀይላችን ነው የሚያፀናን መስቀል ነው መስቀል ቤዛችን ነው መስቀል የነብሳችን መዳኛ ነው አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን ያመንነው እኛም #በመስቀሉ_እንድናለን_ድነናልም! ✝️🌼🌼✝️🌼🌼✝️🌼🌼✝️
Show all...
እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ✝️🌼✝️🌼✝️🌼✝️🌼
Show all...
እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ✝️🌼✝️🌼✝️🌼✝️🌼
Show all...
እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ✝️🌼✝️🌼✝️🌼✝️🌼
Show all...
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ለመላው የክርሥትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሠላም አደረሣችሁ አደረሠን #መልካም_በዓል ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
Show all...
Ela picture Elias s 11 +251 962 083 473 https://t.me/elapictuer
Show all...
በራስህ ህይወት ውስጥ ሹፌር እንጂ ተሳፋሪ አትሁን እራስህን ማንም እዲመራው አትፍቀድ 💚
Show all...
#ዳኛ፦ ለምንድነው ፍቺ የፈለከው? #አበደ፦ ከጫት ቤት ጫት ቤት ከመዞር ሌላ ስራ የላትም..! #ዳኛ፦ ምን ልሁን ብላ.. #አበደ፦ #እኔን_ፍለጋ 😜😜
Show all...
#ሳይፀልዩ_ማደር የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ ሚዳቋ ፀለየች.... "አውጣኝ አውጣኝ" አለች - ለፈጠራት ጌታ ነብሩም ተርቦ ወደ አምላኩ ቀርቦ ሚዳቆዋን አይቶ - አንጀቱ ከሆዱ እንደጠጣበቀ ፈቅዶ እንዲሰጠው - አምላኩን ጠየቀ የሁለቱን ማብላት - የሁላችን ሰሪ ፀሎታቸውንም - ሰማቸው ፈጣሪ አምላክም በድምፁ - ሚዳቆዋን አላት "እሩጠሽ አምልጪ - ከበረታ ጠላት" ነብሩንም አለው - "እሩጥ ተከተላት ምግብህ አርገህ ብላት" ሚዳቆዋ ስትሮጥ ከነብር ለማምለጥ ነብሩም ሲከተላት ሆዱን ሊሞላባት ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ ሆዱን ብትረግጠው የተኛው ከርከሮ ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነብር አውጣኝ ያለው ወቶ - አብላኝ ያለው በላ ሳይፀልይ ያደረው - ከርከሮ ተበላ
Show all...
ታክሲ ውስጥ ከጎኔ ያለው ልጅ እምፅፈውን ቴክስት እያጮለቀ ሲያስቸረኝ #በቃ_ቦንቡን_ታክሲ_ውስጥ ትቼው ልወርድ ነው እሚል ስፅፍ አይቶኝ ወራጅ ሳይል መኪናው እየሄደ በመስኮት ዘሎ ወጣ 😆😂🤣
Show all...
እርሳስ የሆነ ነፍስ ይስጠን ከእለታት አንድ ቀን አንድ ህፃን አያቱ ደብዳቤ ስትፅፍ ይመለከታል። እናም አያቱን እንዲህ ሲል ይጠይቃታል “አያቴ ይህ የምትፅፊው ደብዳቤ ስለኛ ነው? እኔ እና አንቺ ስላደረግነው ነገር?” አያቱም መልሰው “አዎ ልጄ የምፅፈው ስለ አንተ ነው፣ ነገር ግን ከምፅፈው ፅሁፍ ይበልጥ የምፅፍበት እርሳስ ትልቅ ትርጉም አለው፤ አንተም ስታድግ እና ትልቅ ሰው ስትሆን እንደዚህ እርሳስ እንድትሆንልኝ እመኛለው “ አሉት የልጅ ልጃቸውን ቁልቁል እየተመለከቱት። ህፃኑም አያቱ በጨበጡት እርሳስ ላይ ምንም አዲስ ነገር ባለማየቱ ግራ ተጋብቶ “አያቴ አሁን የያዝሽው እርሳስ ከሌላው እርሳስ በምን ይለያል” አላቸው፤ አያቱም ቀጥለው “አየህ ልጄ፤ ሁሉም ነገር እንዳመለካከትህ ይለያል፤ ይህ እርሳስ አምስት ድንቅ ባህሪዎች አሉት አንደኛው ይህ እርሳስ ያለ እጅ መፃፍ አይችልም፤ አንተም ምንም ድንቅ ተዓምር መስራት እና መከወን የምትችል ሰው ብትሆንም እጅ የሚሆንህ ፈጣሪ ከሌለ ወጋ የለውም።ስለዚህ ፈጣሪን ፍራ የእጁን ፍጥረቶች አክብር። ሁለተኛው እንደምታየኝ እፅፍ እፅፍና እርሳሱ ሲዶለዱም አረፍ እልና በመቅረጫ እቀርፀዋለው፤አካሉን ያጣል ግን ይበልጥም ሹል ይሆናል። ሰውም ቢሆን በህይወቱ ብዙ ውጣ ውረዶች ያጋጥሙታል፤መሳልም መውደቅ መነሳቱም ህመም አለው ግን ፈተናውም ሲያልፍ ይበልጥ ሹል ይሆናል ማለት ነው። ሶስተኛው ደግሞ ልጄ….. ይህ እርሳስ በማንኛውም ሰዓት የምሰራውን ስህተት በላጲስ አጥፍቼ እንዳስተካክል እድል ይሰጠኛል። ይህ ማለት በህይወታችን የምንፈፅማቸውን ስህተቶች ማስተካካል ነውር አይደለም፤አንድ ውድቀት ሲጋጥመን ከሱ ተምረን የተሻለ ድንቅ ሰው ማድረግ፤ ይልቁንም እራሳችንን እያረምን እረጅም መንገድ እንድንጓዝ ይረዳናል። አራተኛው ድንቅ ባህሪ ደግሞ፤ የዚህ እርሳስ ታላቅነት ያለው የውጪ አካሉ ላይ ማለትም አንጨቱ ላይ ሳይሆን፤ ውስጡ የተቀበረው ቀጭን ነገር ላይ ነው። ሰውም ቢሆን እንደዛው፤ሁሌም ቢሆን ታላቅ ነገር የሚሰራው ውስጣችን ያለው ነገር ነው። ውስጣችን ልዩ ሃይል አለው ታምር መስራት ያልታየውን የመፍጠር ድንቅ ብቃት አለው። እናም ልጄ ለውስጥህ ሰላም እና ደስታ ትኩረት ስጥ።ሁሌም የአሸናፊነት መንፈስ ይኑርህ። ውስጥህ መልካም ነገር ከሌለ መልካም ነገር ማድረግ ይሳንሃል። አምስተኛው ምን መሰለህ ልጄ….. ይህ እርሳስ በተፃፈበት ቁጥር ምልክት ይተዋል። አንተም እንደዛው…..በህይወት ጎዳና ስትጓዝ ምልክትህን መተውህ አይቀርምና በኑሮህ የምትወስናቸውን ነገሮች ሁሉ አስተውል።የሰው ልጅ ሁሉ አሻራ የተለያየ ነው አንተስ ምንድነው አሻራህ?ምን ምልክት ዘላለም የአንተ የሆነ ምን አለህ?.ሁሌም ይሄን መልስ። የመጨረሻው አየህ ልጄ እስራሱ ሲዶለዱም ይቀረፃል በዚህም ሂደት ቁመቱ እያጠረ እያጠረ ያልቃል ስለዚህ እርሳሱ ጥሩም ፃፈ መጥፎ ማለቁ አይቀርም እኛ ሰዎችም ከዚች አለም ማለፋችን አይቀርም መልካም ሰርተን እንለፍ እኔ አርጅቻለሁ አንተም እንደኔ አርጅተህ ማለፍህ ስለማይቀር ሁሌም መልካም ሰርተህ እለፍ።አሻራህን በድንቅ መልካም መሬት ላይ አንፅ።
Show all...
#15_ምርጥ_አባባሎች! : 1. ዝቅተኛ እውቀት ባለህ ቁጥር የምትተኛው እንቅልፍ ከፍተኛ ይሆናል፡፡ 2. የሰው ልጅ ከደስታው ይልቅ የሀዘኑን ጊዜያት መቁጠር ይወዳል፡፡ 3. በአብዛኛው ጊዜ ሴቶች የፍቅርን ትርጉም የሚጠፋባቸው በውበታቸው ማምለክ ሲጀምሩ ሲሆን ወንዶች ደግሞ በገንዘባቸው ማምለክ ሲጀምሩ ነው፡፡ 4. መጀመሪያ ለራስህ ራስህ መሆን ስትጀምር ለማን ምን መሆን እንዳለብህ ትገነዘባለህ፡፡ 5. የሰው ልጅ የማሰብ ችሎታው ሲጨምር የጓደኞቹን ብዛት ይቀንሳል፡፡ 6. ከሰዎች ጋር ሮጠህ ያልደረስክበት ነገር ካለ ወደ ተነሳህበት ተመልሰህ ከፈጣሪህ ጋር መሮጥ ጀምር፣ ያኔ ካሰብክበት ሳይሆን ካሰበልህ ቦታ ትደርሳለህ፡፡ 7. ጓደኛን አለማመን ከመካድ የከፋ ነው፡፡ 8. የራስህን ትኩስ እንጀራ ለመጋገር ስትል የሌላውን ቂጣ አትርገጥ፡፡ 9. አንዳንድ ሰዎች የሚወድቁት ሌሎችን በሁለት እግሮቻቸው ለመርገጥ ሲጣጣሩ ነው፡፡ 10. ሰው ከጊዜ እና ከማጣት ብዙ ይማራል፡፡ 11. አንዳንዴ ሽንፈትም ከድል የበለጠ ዋጋ አለው/ ከማሸነፍ ይልቅ በመሸነፍ ውስጥ ብዙ እውቀት አለ፡፡ 12. ሠው የበለጠ እያገኘ በሄደ ቁጥር የበለጠ ስግብግብ እየሆነ ይሄዳል፡፡ 13. ሠዎች ትርጉም ያለው ሥራ መስራት ካልቻሉ የመኖር ትርጉምም ይጠፋባቸዋል፡፡ 14. ባንኮች ዝናብ ሳይኖር ዣንጥላ ያበድሩህና መዝነብ ሲጀምር ግን ዣንጥላውን ይነጥቁሃል፡፡ 15. አዋቂ ሆኖ ለመታየት የምናደርገው ጥረትና ከንቱ ድካም አላዋቂ አድርጎ ያስቀረናል፡፡
Show all...