cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Wolaita Sodo Mehal ketema Kale Heywet Church

በወንጌል አናፍርም #ወንጌል_ኢየሱስ_ነው፡፡ Join us @WolaitasodoMKHC @WolaitasodoMKHC @WolaitasodoMKHC @WolaitasodoMKHC እየሱስ ጌታ ነው ✞✞✞✞✞ ♥♥♥♥

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
150
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በድጋሚ መልካም ጋብቻ
Show all...
መልካም ገብቻ🤴👸
Show all...
ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።      ደስ ብሎናል ደስ ይላችሁ!!! ዛሬ በቀን 15/9/2013 በወላይታ ሶዶ መሀል ከተማ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን የጋብቻ ስነ ስርዓት በአቶ ጳውሎስ ዮሀንስ እና በ ወ/ሪት ቤዛዊት በርገነ ተፈፅመዋል. እኛም ከወዲሁ ጋብቻው የሰላም የፍቅር የመተሳሰብ እንዲሆን እንመኛለን። -ከአባት መሪዎች -ከወጣት መሪዎች -ከልጆች መሪዎች እና -ከአጥቢያው ወጣቶች የተላለፈ መልዕክት መልካም ጋብቻ Therefore a man leaves his father and mother,and he will protected by his wife,both will become the same flesh. We are happy are you happy!!!! Today on 15/9/2013 in Wolaita sodo city Kale Hiowet Church, marrige ceremony was held by Ato paulus and mrs Bezawit bergene We also Wish the Marriage to be peaceful and caring. -from the leaders of the fathers -from a leaders of children and -A message from the church, youth.            Happy married life to you
Show all...
"14 The grace of the Lord Jesus Christ, and the love of God, and the communion of the Holy Ghost, [be] with you all. Amen." (2Corinthians 13:14)
Show all...
#ዋጋህ_እንደ_ቦታህ_ነው!! ከእለታት ባንዱ ቀን አንድ ታዳጊ አባቱን፤ “የህይወት ዋጋው ስንት ነው?” ሲል ጠየቀው፡፡ አባትም መልስ በመስጠት ፈንታ ልጁን እንዲህ ሲል አዘዘው፡፡ “እንካ ይህንን የድንጋይ ቁራጭ...ወደ ገበያ ውሰደው " "ሰዎችም ዋጋውን ከጠየቁህ በጣቶችህ ሁለት ቁጥርን ብቻ አሳያቸው እንጂ ምንም አትናገር” አለው፡፡ ልጁም ድንጋዩን ወሰደ፡፡ ወጥቶም በገበያ መሃል ቆመ፡፡ አንዲት ሴትም መጣች፡፡ “ይህ ድንጋይ ዋጋው ስንት ነው? ብትሸጥልኝ ወስጄ ግቢዬ ውስጥ አስቀምጠዋለሁ” አለችው፡፡ ልጁም እንደታዘዘው ምንም ሳይናገር ሁለት ጣቶቹን አሳያት፡፡ እሷም አለች “ሁለት ብር? እወስደዋለሁ!!” ልጁም ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ በገበያ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡ አባትየውም አለው “አሁን ደግሞ ድንጋዩን ይዘህ ወደ ሙዚየም ሂድ ዋጋውን ሲጠይቁህም ሁለት ጣቶችህን አሳይ” ልጁም ወደ ሙዚየም ወጣ፡፡ ገዢም መጥቶ ዋጋ በጠየቀው ጊዜ ሁለት ጣቶቹን አሳየው፡፡ ገዢውም “ሁለት መቶ ብር? እወስደዋለሁ!” አለው፡፡ ልጁም በድንጋጤ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡ አባትየውም ተናገረ፡፡ “አሁን ደግሞ በመጨረሻ ድንጋዩን ይዘህ ወደ የከበሩ ማዕድናት መሸጫ ሂድ ለባለቤቱም አሳየው” አለው፡፡ ልጁም ሄደ ለሱቁም ባለቤት አሳየው፡፡ የሱቁ ባለቤት በመገረም “ይህ እኮ አለም ላይ እጅግ ውድ ከሆኑ የከበሩ ድንጋዮች አንዱ ነው” አለ፡፡ “ከየት አገኘኸው? ስንትስ ትሸጠዋለህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም ምንም ሳይናገር ሁለት ጣቶቹን አሳየ፡፡ የሱቁም ባለቤት አለ.... “ይህንን ድንጋይ በሁለት መቶ ሺህ ብር እወስደዋለሁ፡፡” ልጁም በመገረም እየሮጠ ወደ ቤቱ ተመልሶ ያጋጠመውን ለአባቱ ነገረው፡፡ አባትየውም “ልጄ አሁን የህይወትህ ዋጋ ተገልጦልሃል” አለው፡፡ አየህ የመጣህበት ቦታ፣ ዘርህ፣ ሃይማኖትህ፣ የቤተሰቦችህ ሃብት፣ የተወለድክበት ቦታ ልዩነት አይፈጥርም፡፡ ዋናው ራስህን የምታስቀምጥበት ቦታ፣ ራስህን የምታገኝበት የሰዎች ስብስብ ነው፡፡ ልዩነቱ ያለው ራስህን ለመሸከም በምትመርጥበት መንገድ ነው፡፡ ህይወትህን ሙሉ የሁለት ብር ድንጋይ ዋጋ ስትሰጠው ኖረህ ይሆናል፡፡ ህይወትህን ሙሉ የኖርከው ዋጋህ ሁለት ብር ብቻ እንደሆነ በሚያስቡ ሰዎች ተከበህ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ውድ የሆነ የከበረ ድንጋይ በውስጡ ይዟል፡፡ ልዩነቱም ያለው ውስጣችን ያለውን የከበረ ድንጋይ አይተው ዋጋ በሚሰጡን ሰዎች መሃል መገኘትን ስንመርጥ ነው፡፡ ራሳችንን በገበያ ወይም በከበሩ ማዕድናት ሱቅ የማስቀመጥ ምርጫው አለን፡፡ በሌሎች ሰዎች ውስጥ ያለውንም ውድ ዋጋ ለማየት ምርጫው የኛው ነው፡፡ ሌሎች ሰዎችም የከበረ ዋጋቸውን እንዲረዱ ማድረግ እንችላለን፡፡ አብረህ የምትውላቸውን ሰዎች በጥንቃቄ ምረጥ፡፡ ይህ በህይወትህ ልዩነትን ይፈጥራልና !! ቦታችሁን ምረጡ Join our sister channal @gospel_talk @gospel_talk
Show all...
እውነተኛ የክርስትና ህይወት መለኪያዎች (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ 3) የክርስትና ህይወት መለኪያዎች ጳውሎስ መልዕክቱን በ3መንገድ ከፍሎታል 1. ቆጥራለወ 1-11 (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ 3) ---------- 1፤ በቀረውስ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ። ስለ አንድ ነገር መልሼ ልጽፍላችሁ እኔን አይታክተኝም ለእናንተ ግን ደኅና ነው። 2፤ ከውሾች ተጠበቁ፥ ከክፉዎችም ሠራተኞች ተጠበቁ፥ ከሐሰተኛም መገረዝ ተጠበቁ። 3፤ እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና። 4፤ እኔ ግን በሥጋ ደግሞ የምታመንበት አለኝ። ሌላ ሰው ማንም ቢሆን በሥጋ የሚታመንበት እንዳለው ቢመስለው፥ እኔ እበልጠዋለሁ። 5፤ በስምንተኛው ቀን የተገረዝሁ፥ ከእስራኤል ትውልድ፥ ከብንያም ወገን፥ ከዕብራውያን ዕብራዊ ነኝ፤ ስለ ሕግ ብትጠይቁ፥ ፈሪሳዊ ነበርሁ፤ 6፤ ስለ ቅንዓት ብትጠይቁ፥ ቤተ ክርስቲያንን አሳዳጅ ነበርሁ፤ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ብትጠይቁ፥ ያለ ነቀፋ ነበርሁ። 7፤ ነገር ግን ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቈጥሬዋለሁ። 8-9፤ አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤ 10-11፤ እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። 2. እይዛለው 12-13 (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ 3) ---------- 12፤ አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ። 13፤ ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ 3. እፈጥናለው 14-21 (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ 3) ---------- 14፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ። 15፤ እንግዲህ ፍጹማን የሆንን ሁላችን ይህን እናስብ፤ በአንዳች ነገርም ልዩ አሳብ ቢኖራችሁ፥ እግዚአብሔር ይህን ደግሞ ይገልጥላችኋል፤ 16፤ ሆኖም በደረስንበት በዚያ እንመላለስ። 17፤ ወንድሞች ሆይ፥ እኔን የምትመስሉ ሁኑ፥ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ፥ እንዲሁ የሚመላለሱትን ተመልከቱ። 18፤ ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ። 19፤ መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። 20፤ እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ 21፤ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል። እውነተኛ የክርስትና ህይወት መለኪያዎች ፩. እግዚያብሔርን በመንፈስና በእውነት ማምለክ ፪. በክርስቶስ ኢየሱስ ደስ መሰኘት ፫. በስጋ የማይታመን ፬. ምድራዊ ነገሮችን በእግዚያብሔር እይታ ማየት             8/9/2013E.C                             Sunday Program© @WOLAITA SODO MEHAL KETEMA   KALE HEYWEY CHURCH
Show all...
     የደቀመዝሙር ባህርያት 1. ራሱን የካደ እርሱ ደቀመዝሙር ነው። 23፤ ለሁሉም እንዲህ አላቸው። በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ። 24፤ ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፤ ስለ እኔ ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን እርሱ ያድናታል። (የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 9) 2. በእግዚአብሔር ፊት በትጋት መመላለስ " ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች።" (የዮሐንስ ወንጌል 9:4) 3. ክርስቶስን መምሰል " እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ።" (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-2) 4. አገልጋይ መሆን " ስለዚህ ወንድሞችን ብታሳስብ፥ በእምነትና በተከተልኸው በመልካም ትምህርት ቃል የምትመገብ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ።" (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:6) 5.የክርስቶስን ምፃት ነቅቶ መጠበቅ (የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25) ---------- 1፤ በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች። 2፤ ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ። 3፤ ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤ 4፤ ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ። 5፤ ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። 6፤ እኩል ሌሊትም ሲሆን። እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ። 7፤ በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ። 8፤ ሰነፎቹም ልባሞቹን። መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው። 9፤ ልባሞቹ ግን መልሰው። ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው። 10፤ ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ። 11፤ በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና። ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ። 12፤ እርሱ ግን መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ። 13፤ ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።                                በወንጌላዊት ሁለአገረሽ
Show all...