cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopian Daily

News every day

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
186Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በጦርነቱ የወደሙ ቅርሶች መኖራቸውን ለማረጋገጥ ወደ ላሊበላ ባለሞያዎች ሊላኩ ነው በጦርነቱ የወደሙ ቅርሶች መኖራቸውን ለማረጋገጥ ወደ ላሊበላ ባለሞያዎች ሊልክ መሆኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ገለፀ፡፡ ከዚህ ቀደም አክሱም፣ ደሴ እና መቀሌ በነበረው ጦርነት የተጎዱ ቅርሶችን ለይቶ ለማወቅ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በስፍራው ባለሙያ ልኮ እንደነበረ እና በተመሳሳይ ሁኔታም ላሊበላ በተፈጠረው ጦርነት ምን ያህል ቅርሶች እንደወደሙ እና ጥገና ሚደረግላቸውንም ለመለየት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለሙያ ለመላክ ዝግጅት ላይ መሆኑን በቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ነጃት ጀማል ለአሀዱ ራዲዮ ተናግረዋል፡፡
Show all...
በኦሮሚያ ክልል ከ400ሺህ ሕዝብ በላይ ለምግብ እጥረት መጋለጡ ተነገረ። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ሻላ፣ ሲራሮ፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌ እና ወንዶ ተብለው በሚጠሩ አምስት ወረዳዎች ውስጥ ለረጅም ጊዜ በቆየ የዝናብ እጥረት ሳቢያ ከ400 ሺህ በላይ ሕዝብ ለምግብ እጥረት መጋለጡ ተነግሯል። "ከዚህ ቀደም የምግብ እጥረቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች እህል የሚዘራው በበልግ ወቅት ዝናብ ነበር። ይሁን እንጂ ዘንድሮ ከመስከረም እስከ ሰኔ ወር ድረስ ዝናብ አልነበረም። በዚህም ምክንያት የምግብ እጥረቱ ሊከሰት ችሏል" ሲሉ የዞኑ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኃላፊ አቶ ያሲን ጋርጁ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የምግብ እጥረት ካጋጠማቸው ሰዎች መካከል የተወሰኑት ከዚህ ቀደምም ድጋፍ ይደረግላቸው እንደነበር ያስረዱት ኃላፊው ከአምስቱ ወረዳዎች በሁለቱ ማለትም በሻላ እና ሲራሮ ከምግብ እጥረት በተጨማሪ የውሃ እጥረት መኖሩንም ተናግረዋል። በተከሰተው እጥረት ሳቢያ የሞተ ሰው ስለመኖሩ ለቢቢሲ የገለጹ ነዎሪዎች ቢኖሩም የምዕራብ አርሲ ዞን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኃላፊው አቶ ያሲን ጋርጁ የምግብ እጥረቱ ይከሰት እንጂ በምግብ እጥረቱ ሳቢያ እስካሁን ሕይወቱ ያለፈ ሰው ስለመኖሩ ሪፖርት አለመደረጉን ይናገራሉ።
Show all...
መረጃ #Ethiopia : የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ለመጡ ወገኖቻችን ጊዜያዊ ማረፊያ ማዘጋጀቱን አስታወቀ። 1ኛ. ቅዳሜ ገበያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማረፊያ "ጣቢያ አንድ ":- ከወልድያ እና ከጉባላፍቶ አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ። 2ኛ.ዳዉዶ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የማረፊያ "ጣቢያ ሁለት":- ከባላ፡ከራያ አላማጣ እና ከኮረም አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ። 3ኛ. ካራጉቱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማረፊያ "ጣቢያ ሶስት" ከመርሳ እና ከሀብሩ ወረዳ አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ። 4ኛ. አድስ ፋና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ማረፊያ "ጣቢያ አራት" ቆቦ ከተማና ከራያ ቆቦ አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን በክፍለ ከተማና በቀበሌ ደረጃ መላ ህዝባችንና አመራራችን በጎፍቃደኛ ወጣቶቻችን አስፈላጉውን ትብብር ሁሉ እንደሚያደርጉላች በማመን ከላይ በተመለከቱት የማረፊያ ጣቢያዎች በመሄድ እንድትመዘገቡ ጥሪ ቀርባል። ከወቅታዊ ጉዳዮቻችን ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ያለውን የተፈናቃይ ቁጥር በመገንዘብ ልዩ እገዛ ለማድረግ ከወዲሁ ፍቃደኝነታችሁን በመግለፅ ወደተግባር የገባችሁ የንግዱ መሀበረሰብ ከተማ አስተዳደሩ ምስጋናውን ለመግለፅ ይወዳል። የደሴ ከተማ አስተዳደር
Show all...
306 ህጻናት አሳዳጊ አግኝተዋል የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የካቢኔ አባላት እና የተለያዩ ተቋማት "አንድ ቤተሰብ ለአንድ ህጻናት" በሚል 306 ህጻናትን ለማሳደግ ተረክበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ በጉዲፈቻነት የወሰድናቸውን ልጆች ልክ እንደ ቤተሰብ በአካል ፣በአዕምሮና ስነልቦና የተሟላ እድገት እንዲኖራቸው ሃላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡ ነገ ልናጭድ የምንችለው ዛሬ የሰዘራነውን ትውልድ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ይሄ ተግባራችን ዛሬያችንን ብቻ ሳይሆን ነገያችንን ጭምር የሚያሳምር በመሆኑ ትውልድ ግንባታ ላይ ሁሉም ሊረባረብ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብራሃም ታደሰ በበኩላቸው እነዚህን ህጻናት ለመንከባከብ ባለሀብቶች፣ የሴክተር ተቋማት እና የተቋማት አመራሮች በጠቅላላው ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሃዳስ ኪዱ ፤ ቢሮው ወላጅ አልባ ህጻናትን በሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር ጉዲፈቻን እንዲያገኙ የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 1 ሺ 350 ህጻናት በጉዲፈቻ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል። በዛሬው ዕለትም ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የካቢኔ አባላት እና የተለያዩ የሴክተር መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ክፍለ ከተሞች ህጻናትን በጉዲፈቻ ለማሳደግ እና በስፖንሰር ለመንከባከብ ርክክብ መደረጉን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክረታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Show all...
የደሴ ከተማ አስተዳደር ከዛሬ ነሐሴ 4 ቀን፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆን የሰዓት እላፊ አወጀ። «የከተማዋ ነባራዊ ሁኔታ ከወትሮው በተለየ የከተማዋን ነዋሪ ሕዝብ ልዩ ክትትል እና ድጋፍ የሚጠይቅ ነው» ሲል የከተማዋ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት በፌስ ቡክ ገጹ ዐስታውቋል። ወደ ከተማዋ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተፈናቃይ መግባቱን ያመለከተው መግለጫው «ለከተማዋ ሁለንተናዊ ደህንነት ሲባል» የሰዎች እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ በሰዓት መገደቡን ዐስታውቋል። በዚህም ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ከተፈቀደላቸው የጸጥታ እና የጤና ተቋማት ተሽከርካሪዎች በቀር ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ክልከላ መቀመጡን ገልጿል። በሕዝብ ማመላለሻነት የሚያገለግሉ የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 12 ሰአት በኋላ መንቀሳቀስ እንደማይፈቀድላቸው መግለጫው አመልክቷል።
Show all...
"በሀገር ውስጥና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ እናት ሀገራችሁ ጥሪ ታቀርብላችኋለች" የኢትዮጵያ መንግስት የጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል። መንግስት በመግለጫው "ውጊያው የትግራይን ሕዝብ ምሽግ ካደረገው እኩይ ኃይል ጋር እንጂ ከትግራይ ጋር አይደለም፤ እናም ስንፋለም መጠቀሚያ የሆነውን የትግራይ ሕዝብ ብሎም መላዋ ኢትዮጵያን ከአሸባሪው ቡድን ነጻ ለማውጣትና የሀገራችንን ሰላምና አንድነት ለማስከበር ነው።" "ሁሉም ሀገር ወዳድ ሉአላዊነቱን ለማስጠበቅ በሙሉ ልቡ ይሠለፍ፤ እንደ ጥንቱ ዛሬም የሀገሩን ክብር ላለማስደፈር ቆርጦ ይነሳ። " ሲል አስፍሯል።
Show all...
ሰበር ዜና❗️ መንግስት ሽብርተኛ ተብሎ በተፈረጀው በሕወሓት ኃይል ላይ “ብርቱና የማያዳግም” እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ ሰጠ! መንግስት “ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሣ የክህደት ኃይል” ባለው የሕወሐት ኃይል እና የውጭ እጆች ስውር ደባ ለመደምሰስ ብርቱና የማያዳግም እንዲወሰድ አቅጣጫ ሰጠ፡፡የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልል ልዩ ኃይሎች እና ሚሊሻዎች የማያዳግም ክንዳቸውን እንዲያሳርፉ አቅጣጫ አቅጣጫ አስቀምጧል።መንግስት እስካሁን በተናጠል የተኩስ አቁም ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡
Show all...
ዩኒሴፍ፤ በአፋር ክልል የተገደሉ ዜጎች ጉዳይ አስደንጋጭ መሆኑን ገለጸ! በአፋር ክልል በተፈጸመ ጥቃት 107 ህጻናትን ጨምሮ የ240 ተፋናቃዮች መገደል አስደንጋጭ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታወቀ።የዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር ሄንሪታ ፎር በአፋር ክልል በደረሰው ጥቃት ዙሪያ መግለጫ አውጥተዋል።በአፋር ክልል በጤና እና ትምህርት ተቋማት ውስጥ የተጠለሉ 107 ህጻናትን ጨምሮ 240 ዜጎች መገደላቸውን መስማቱን የገለጸው ዩኔስኮ ይህም አስደንጋጭ እንደሆነ ጠቅሷል።ከዚህ ባለፈም ዋነኛ የምግብ ማከማቻ መውደሙ እንዳሳሰበውም ነው ተቋሙ የገለጸው። በአፋር ክልል እና በሌሎች የትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች እየተደረገ ያለው ውጊያ መባባሱ ለህጻናት አስከፊ መሆኑንም የዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር ሄንሪታ ፎር ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።ዩኒሴፍ፤ በአፋር ክልል በተፈጸመ ጥቃት 107 ህጻናትን ጨምሮ የ240 ተፋናቃዮች መገደላቸውን ይግለጽ እንጅ፤ድርጊቱን የፈጸመው አካል የትኛው ወገን እንደሆነ ግን በመግለጫው ላይ አላካተተም።የአፋር ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ አርብ ዕለት ባወጣው መግለጫ የህወሀት ኃይሎችን ባደረሱት ጥቃት 107 ህጻናትን ጨምሮ 240 ተፋናቃዮችን መገደሉን መግለጹ ይታወሳል። የአፋር ክልል ሰላምና አስተዳደር ቢሮ፤ ህወሃት በክልሉ ፈንቲረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በንጹሃን አርብቶ አደሮች ላይ በከፈተዉ ድንገተኛ ጥቃት በሰዉና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ሃምሌ ወር ላይ መግለጹ የሚታወስ ነው።በሰሜን ኢትዮጵያ በተቀሰቀሰው ጦርነት በርካታ ህጻናት ችግር ላይ እንዲወድቁ ማድረጉንም ተቋሙ አስታውቋል። ሁሉም ወገኖች አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ትግበራን እንጀምሩም ጥሪ አቅርቧል። Via Alain
Show all...
ዓለም አቀፉ የህፃናት አድን ድርጅት በአፋርና አማራ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች አስቸኳይ የቁሳቁስ ድጋፍ እያደረኩኝ ነው አለ ዓለም አቀፉ የህፃናት አድን ድርጅት በአፋርና አማራ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች አስቸኳይ የቁሳቁስ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ሴቭ ዘ ችልድረን ለአሻም በላከው መግለጫ እንዳመለከተው በአፋር ክልል አራት ወረዳዎች፣ በያሎ፣ ጉሊና ኡዋና አውራ ከ16 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የመጠለያ፣ የማብሰያ እቃዎች፣ ፍራሽና ብርድ ልብስን የመሳሰሉ የቁሳቁስ ድጋፎችን እደረገ ይገኛል፡፡ የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቃል አቀባይ ህይወት እምሻው ለአሻም እንዳረጋገጡላት በቀጣይ በአማራ ክልል በሰቆጣ፣ ወልዲና ደሴ ለሚገኙ ከ20ሺህ በላይ ተፈናቃዮች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለመስጠት ዝግጅታቸውን አጠናቅቀዋል፡፡ በዚህም ደሴ ከተማን እንደ ማዕከል በመጠቀም ለእያንዳንዱ ቤተሰብ 5 ኪሎ ስንዴ ዱቄት፣ 5 ኪሎ አተር ክክ፣ 5 ኪሎ መኮረኒ እና 5 ሊትር ዘይት በየወሩ ይዳረሳል ተብሏል፡፡ ሴቭ ዘ ችልድረን በሁለቱም ክልሎች ለሚገኙ ዕርዳታ የሚሹ ዜጎች የየአካባቢው የፀጥታ ሁናቴ በፈቀደ መጠን ድጋፉን አስፍቶና አጠናክሮ ለመቀጠል ቁርጠኝነት አለኝ ብሏል፡፡
Show all...
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የፌዴራል መንግሥትን ከሕወሓት አመራሮች ጋር ሊያወያይ ማሰቡን ገለጸ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የተከሰተውን ጦርነት ወደ ሰላማዊ ድርድር ለማምጣት፣ የፌዴራል መንግሥትንና በቅርቡ በፓርላማ በሽብርተኝነት የተፈረጀውን የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ታጣቂዎችን ለማወያየት እንዳሰበ ገለጸ፡፡ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ራሔል ባፌ (ዶ/ር) ምንም እንኳ የምክር ቤቱ ሐሳብ ጅምር ላይ ቢሆንም፣ በቅርቡ እንቅስቃሴ ሲጀምር ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ምክር ቤቱ በአገሪቱ ውስጥ ያጋጠመው ችግር የፌዴራል የመንግሥት ጉዳይ ብቻ ባለመሆኑ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ሁኔታዎችን በአጽንኦት ይከታተል ብለዋል፡፡ Via ሪፖርተር
Show all...