cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopian student text book in pdf🇪🇹

https://t.me/Best_book_for_students

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
3 648Subscribers
No data24 hours
-157 days
-7430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

" ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016  የማካካሻ (Remedial) ትምህርት ፈተና ይሰጣል " - ትምህርት ሚኒስቴር   ትምህርት ሚኒስቴር የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016 እንደሚሰጥ ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል። ፈተናው በ30 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚከናወን ይሆናል። የሚሰጠው ፈተና የማካካሻ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም የተሰጠውን የማዕከል ፈተና ላልወሰዱ  ተማሪዎች መሆኑ ተገልጿል። ሚኒስቴሩ ፤ ከመስከረም 7- 10/2016 ዓ.ም ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና #በወረቀት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል። በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከ50 % በታች ሆኖ ወደከፍተኛ ትምህርት መግባት ያልቻሉ እና በአንጻራዊነት የተሻለ ውጤት የነበራቸው ወደ 200ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአንድ ሴሚስተር የማካካሻ ትምህርት መውሰዳቸው ይታወቃል። የማካካሻ  (ሬሜዲያል) ፈተና የሚሰጠው ተማሪዎቹ በተቋማት እና በማዕከል የሚሰጠውን ምዘና ወስደው በሚያስመዘግቡት ውጤት መሠረት ከ2016 ዓ.ም ፍሬሽማን ተማሪዎች ጋር የከፍተኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ነው። #MoE
Show all...
👍 5
#Update የሬሜዲያል ተማሪዎች ፈተና ከመስከረም 07 እስከ 10/2016 ዓ.ም ይሰጣል። የሬሜዲያል/ማካካሻ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም የተሰጠውን የማዕከል ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናው እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም ፈተናው በ30 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 07 እስከ 10/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል። ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም ተገልጿል። #MoE ለጥቆማ 👉
Show all...
#ለመፈተን_ዝግጁ_ነኝ በፀጥታ ችግርና በሌሎች ምክንያቶች ፈተና ያልወሰዱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ለመፈተን መዘጋጀቱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡ የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በሁለት ዙር መሰጠቱን አገልግሎቱ አስታውሷል፡፡ ይሁንና በጎንደርና በጋምቤላ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ እና በከፊል 14 ሺህ 891 ተማሪዎች እንዲሁም በሕህ ግ ጥላ ስር በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ 419 ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን ሳይወስዱ መቅረታቸው ተጠቅሷል፡፡ ተፈታኞችን  ከመጪው መስከረም 8 እስከ መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡ መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተነዎች አገልግሎት ነው ለጥቆማ 👉
Show all...
የሬሜዲያል ፈተና በቅርቡ ስለሚሰጥ ተፈታኞች ዝግጅት እንዲያደርጉ ተጠየቀ ከነሐሴ 23 እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ሊሰጥ የነበረው የሬሜዲያል ፈተና የተራዘመው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ስላልተጠናቀቁ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ መጠናቀቅ ያለባቸው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በአግባቡ ለማጠናቀቅ ሲባል የፈተናውን ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘም አስፈልጓል፡፡ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንደተጠናቀቁም በቅርቡ ተፈታኞች ለፈተና ስለሚጠሩ ዝግጅት እያደረጉ እንዲጠብቁ አሳስበዋል፡፡ ባለፈው ጊዜ ፈተና ያልወሰዱ እና የማካካሻ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ 46 ሺህ የሚጠጉ የመንግሥትና የግል ተማሪዎች በቅርቡ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ አረጋግጠዋል፡፡ በቅርቡ ፈተናቸውን የሚወስዱ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ የሚያመጡ የሬሜዲያል ተፈታኞችም ቀደም ብለው የሬሜዲያል ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ካመጡ ተማሪዎች ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበት ጊዜ ተመሳሳይ ስለሆነ ስጋት እንዳይገባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ለጥቆማ 👉
Show all...
👍 2
#JimmaUniversity ጅማ ዩኒቨርሲቲ የሬሚዲያል ተማሪዎችን ውጤት ይፋ አድርጓል። በጅማ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (ሬሚዲያል) ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የቆያችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁን በተቋሙ ድረ-ገጽ ላይ በመግባት ማየት ትችላላችሁ፡፡ ውጤት ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://portal.ju.edu.et/
Show all...
#EAES የ2015 ዓ.ም ቀጣይ ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል። በኢትዮጵያ ውስጥ በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ እንዲሁም በውጭ ሀገር ሆነው በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት ለተማሩ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በነሐሴ ወር መጨረሻ የመልቀቂያ ፈተና ይሰጣል። በተመሳሳይ በትግራይ ክልል ለሚገኙ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም የመልቀቂያ ፈተናው እንደሚሰጥ አገልግሎቱ ጠቁሟል። ለጥቆማ 👉
Show all...
#Haramaya University Remedial Result ለጥቆማ 👉 q
Show all...
#ArbaminchUniversity አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial) ውጤት ይፋ አደረገ። የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial) ማጠቃለያ ውጤት በመረጃ መረብ (Online) መለቀቁን አሳውቋል። ተማሪዎች ከታች የቀረበውን ሊንክ በመጫን (ወይም ሊንኩን በዌብ ፔጅ ላይ ኮፒ-ፔስት በማድረግ)፣ መለያ ቁጥር (ID Number) በማስገባት፣ Search እና View Result በመጫን ማየት ይችላሉ ተብሏል። በውጤቱ ላይ ቅሬታ ያለው ተማሪ ካለ ከሰኞ እስከ ረቡዕ (ከነሐሴ 1 እስከ 3/ 2015 ዓ.ም) ባለው ጊዜ ውስጥ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር ቢሮ (የአምዩ አስተዳደር ሕንጻ 2ኛ ፎቅ) ማመልከት ይችላል ተብሏል። https://survey.amu.edu.et/remedial/ ተቋሙ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርብ የቅሬታ ማመልከቻ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አሳውቋል። መረጃው ፦ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ነው።
Show all...
ለወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ሬሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ ውድ የሬሚዲያል ተማሪዎች ውጤት መገለፁን ተከትሎ ተማሪዎች ቅሬታ እንዳላችሁ እየገለፃችሁ ስለሆነ በሚከተለውን የኢሜል አድራሻ እስከ ዕለተ አርብ ቀን 28/11/2015 ዓ.ም ብቻ ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። ቅሬታ ማቅረቢያ የኢሜል አድራሻ👇 [email protected]
Show all...
#AASTU የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለ1ኛ እና 2ኛ አመት መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ አደረገ። የአንደኛ እና ሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች በክረምቱ ወቀት ትምህርት ተጀምሮ በ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ምክንያት ትምህርት ተቋርጦ ነበር። በዚሁ መሰረት በጊዚያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስቀጠል ለ1ኛ እና 2ኛ አመት መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መመለሻ ጊዜ ነሃሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል። ተማሪዎች በእለቱ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ የተሰጠ ሲሆን ከነሀሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ተቋሙ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ አሳውቋል። ለጥቆማ 👉
Show all...