cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

እንዘምራለን 🎶 Enzemraln🎹🥁

በየግዜው አዲስ የሚለቀቁ ዝማሬዎችን እና ቆየት ያሉ መዝሙሮችን የሚያገኙበት እንዲሁም 👉በዝማሬ 🎵 👉በግጥም 📚 👉በቃል 🎤 📖 👉በሌሎችም ማገልገል ለምትፈልጉ ተቀላቀሉን... @Enzemraln

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
417Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

leyo😘 ይሄን መዝሙር ከሰማችሁት እንኳን ደግማችሁ ስሙት እውነት ትባረኩበታላችሁ ለወዳጆም ያጋሩ 🙏 . #ይታወቅልኝ ሰው እኔን ሲያይ እንደፈወስከኝ ይታወቅልኝ ሰው እኔን ሲያይ እንደማርከኝ ይታወቅልኝ ሰው እኔን ሲያይ እንዳቆምከኝ ይታወቅልኝ ሰው እኔን ሲያይ እንዳፅናናኸኝ ይታወቅልኝ በቃ በተባለው ላይ በቃ እኔ ባልኩት ላይ በቃ ሰዎች ባሉት ላይ እረዳቴ መተህ የለወይ ልጠይቀኝ መተህ የለወይ ልትፈታኝ መተህ የለወይ ልትፈውሰኝ መተህ የለወይ ጠያቂዬ መተህ የለወይ ወንድም ጋሼ መተህ የለወይ የሞተ ነገሬን ጎበዝ ተነስ ያለው ማነው የጠፋ ነገሬን ጠርቶ ያመጣው ማነው ኢየሱስ ነው ኢየሱስ ነው ኢየሱስ ነው ወድሀለው መድሀኒቴ ስለመጣህ ወደ ቤቴ ስለመጣህ ወደ ህይወቴ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ✍TsiOfJesus 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ይታወቅልኝ -||- በረከት ተስፋዬ sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ማርከን ዜማ 💙 @Enzemraln @Enzemraln
Show all...
፨ፍቅርህን አልክድም፨ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ሁኔታው ለኔ ባይገባኝም የማልፍበት ሁሉ ቢከብድም እኔ ግን ፍቅርህን አልክድም ጊዜ ሲያልፍ ጊዜኮ ይተካል እንደአንተ ሁሉ መቼ ይቆያል 🕐9:44 7.3MB #ልዩ_ፕሮግራም_ከዘማሪ_ማክ_ጋር Pianist 🎹 Yoni @Enzemraln
Show all...
ኢየሱስ ይለያል። 📌ሰዎች የሞተ ሰው እሬሳ ብለው ሲጠሩት ኢየሱስ ግን የሞተን ሰው አንተ ጎበዝ ብሎ የጠርቶ ከሞት ያስነሳ ነው። 📌ዛሬ እናተም የሞተ ነገር አላቹ አበቃ የያላቹሁት ነገር ካለ በዛ ነገር ላይ የኢየሱስን ስም ጥሩበት ያኔ መሞተው ነገራቹ ላይ ህይወት ይዘራበለል።🙏
Show all...
. #እንኳን_አደረሳቹ 🇪🇹🇪🇹 ✝ 🇪🇹🇪🇹 (ሮሜ 5) 6 ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና።7 ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል።8 ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።9 ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን።10 ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤11 ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን። ❤✝ ፋሲካ ✝❤ 👉ሐጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለኛ የሞተበት 👉እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅሩን የገለጠበት 👉በደሙ የፀደቅንበት 👉ከቁጣው የምንድንበት 👉ጠላቶች ሳለን በልጁ ሞት ከእግዚአብሔር ጋር የታረቅንበት 👉መታረቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር የምንመካበት በአላችን ነው፡፡ #ሮሜ6፥6_ #መስቀሉ_ትርጉም_አለው፦ ለሐጢአት እንዳንገዛ የሐጢአት ስጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዎችን ተሰቅሎበታልና #ሞቱ_ትርጉም_አለው፦ ለሐጢአት ሕያው ሆነን እንዳንኖር ለሐጢአት ሞተናልና #ትንሳኤው_ትርጉም_አለው፦ በፅድቅ ለመኖር ከእርሱ ጋር አስነስቶናል፡፡ ❤❤ ❤❤ ❤ ❤ ❤ ❤#መልካም_ፋሲካ ❤ ❤ #እንኳን ❤ ❤#አደረሰን ❤ ❤ ❤ ❤ <<ሐጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን እውነትም በእኛ ውስጥ የለም በሐጢአታችን ብንናዘዝ ሐጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመፃም ሁሉ ሊያነፃን ፃድቅና የታመነ ነው የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከሐጢአት ሁሉ ያነፃናል>> 1ኛዮሐ1፥7 Have a nice Holiday and ceremony To all my Friends Happy ✝ Easter @Enzemraln@Enzemraln
Show all...
አርብ ምሽት ማንም አይቀርም 💙 22/08/13 10:00 - 2:00 ድሬ ላይ ካሉ ወጣት ዘማርያን ጋር ልዩ የወጣቶች የአምልኮ ፕሮግራም 🎤 🎹 🎸 አዘጋጅ:- የግንፍሌ ሙሉ ወንጌል ወጣቶች ህብረት... ኑ በመስቀል ላይ ሞቶ ያዳነን ቤዛችንን በጋራ እናምልክ አድራሻ:- ከሼል ወደ አዲስ ከተማ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብሎ God Bless You 🙌 Share and join us @Enzemraln
Show all...
10 አዲስ ክርስቲያን ወዲ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የሚጠቅም ምክር 1. በነገር ሁሉ እግዚኣብሔርን አስቀድሙ (ማቲ 6፥33 / ምሣሌ 3፥5-6 ) በዚህ ምድር ላይ የተጠራነው በዋነኝነት እግዚኣብሔርን ለማክበር እና ከእርሱ ጋር ሰራተኞች ሆነን ልንሠራ ነው:: በእርግጥ አንድ ተማሪ ወደ ግቢ ሲሄድ ዋነኛ አላማው መማር ቢሆንም ለክርስቲያን ግን በህይወት ዘመን ሁሉ እግዚኣብሔርን ማስቀደም አለበት :: ስለዚህ ቃሉን ለማንበብ እና ለማሠላሠል ፣ ለመፀለይ እና እግዚኣብሔርን ማወቅ ማስቀደም አለብን :: ይህ ማለት ግን የትምህርት ሰአትን ተጋፍተን መሆን የለበትም። አንዳንድ ተማሪዎች ክለስ ቀርተው፣ ማጥናት እየኖረባቸው ፌሎ ብለው ይሄዳሉ ይህን ተገቢ አይደለም :: 2. በተቻለ መጠን ኢየሱስን የሚወዱ ጋደኞች ይኑሩን ሠው በተለያየ መልኩ ከእግር ይቀርባል ደግሞሞ ይርቃል :: ከእነዚህ መንገድ መካከል ዋነኛው ጓደኛ ነው:: መጽሃፍ ቅዱስ በ2ተኛ ጢሞ 2፥22 ላይ “ከወጣትነት ክፉ ምኞት ሽሽ፤ በንጹሕ ልብ ጌታን ከሚጠሩት ጋርም ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን ተከታተል።” — 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥22 (አዲሱ መ.ት) በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን በተግባር የሚያደርጉት ጋር አብሮ መሆን ጠቃሚ ነው 3. ስለ መጨናነቅ አታሰቡ የመጀመሪያው አንድ ተማሪ ግቢ ገባ ሲባል ወደ ሁሉም ሀሣብ ሚመጣው "Christmas test " ወይም " የገና ግርግር " የሚባለው ፈተና ነው:: በእርግጥ የመጀመሪያ የማጠቃለያ ፈተና የሚሰጥበት ወቅት ቢሆንም የዩኒቨርሲቲ ውጤት እና ህይወት ማብቂያ ተደርጎ መታሰብ የለበትም :: በዚህ ወቅት ራስን አረጋግቶ ፈተና ላይ በማተኮር አቅም በፈቀድ መጠን መስራት እና ውስጥን ማረጋጋት አስፈላጊ ነው። “እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።” — 1ኛ ጴጥሮስ 5፥7 (አዲሱ መ.ት) 4 ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙ ሌላው በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚስተዋለው ጊዜን በአግባቡ አለመጠቀም ነው፡፡ አንዳንዴ በጣም ብዙ የሚሰራ ነገር ይኖር እና በተማሪ ላይ መጨናነቅ ይታያል። አንዳንዴ ደግሞ ሠፊ የሆነ ነፃ ጊዜ ስለሚኖር ምን ዕንደሚደረግ ይጠፋል። ታዲያ በሁለቱም ወቅት የራስን፣ የውስጥን ስሜት ማረጋጋት እና በእቅድ መመራት ተገቢ ነው። ብዙ አሣይመንቶች በተሠጡ ጊዜ አግባብነት ባለው ወቅት መስራት በተደራረበብን ወቅት ተራ በተራ ለመስራት እና ለመጨረስ መሞከር ተገቢ ነው፡፡ ነፃ ጊዜ በሚገኝበት ወቅት በእቅድ ማሣለፍ መለማመድ ተገቢ ነው። “ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤” — መክብብ 3፥1 (አዲሱ መ.ት) 5. ትምህርታቹን ላይ አተኵሩ ግን አታምርሩ በኢትዮጲያ አብዛኛው የማህበረሠብ ክፍል የወደፊት ህይወቱን በትምህርት ላይ ብቻ የተመሰረት እና የነገው ተስፋ በትምህርት ብቻ ይገኛል ብሎ የሚያምን በተጨማሪ የሀገራችን ስርአት ለዚህ የተጋለጠ ነው፡፡ ትምህርት አንድ የዕውቀት መገቢያ መንገድ ነው:: መጽሃፍ ቅዱስም ትምህርታችን በአግባቡ ዕንድንማር ይመክረናል። “ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥16 ይህ ማለት ግን ትምህርት የህይወታችን መሠረት ነው ፤ ትምህርት ካልተሣካልን የህይወት መጨረሻ ነው ማለት አይደለም፡፡ እግዚኣብሔር በእርግጥ በአንድም በሌላም መልኩ ይሥራል። በዚህ ዘመን የታወቁ ሰዎች ፣ የእግዚኣብሔር አገልጋዮች፣ እና ሌሎች ሠዎች በቀለም ዕውቀታቸው የበለፀጉ ነበሩ ፤ናቸውም፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ፊደል ያልቆጠሩ፣ የቀለም እውቀትን የማያውቁ በእግዚኣብሔር ቤት የኖሩ በአለም በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው ታላቅ ተፅህኖ ያመጡ ሠዎች አሉ። በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ጥበበኞች ብሎ ዳንኤል፣ ሠለሞን ወዘተ ...... ይጠቅሣል። በሌላ በኩል ደግሞ መጽሃፍ ቅዱስ ራሱ ሐዋሪያትን ያልተማሩ እና ማንበብ የማይችሉ ዕንደ ነበሩ ይነግረናል። አስተውሉ! " ትምህርትን አያስፈልግም እያልኩ ሣይሆን ዕንደ ክርስቲያን እግዚኣብሔር ላይ ነው ተስፋችን መሆን ያለበት ፣ ስለዚህ ትምህርታቹ ላይ አተኩሩ ግን አታምርሩ" ይቀጥላል... ©teho #ሼር ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 📩📩 @en_hakkore 🚀🚀 @sozo_purity 🚻🚻 @sozo_family
Show all...