cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Grace

ሮሜ 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³ ወንጌሉም ስለ ልጁ፣ በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ሆነ፣ ⁴ በቅድስና መንፈስ ደግሞ ከሙታን በመነሣቱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በኀይል ስለ ተገለጠው ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

Show more
Advertising posts
1 811
Subscribers
-224 hours
-77 days
-1830 days
Posts Archive
“በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤” ይላል የእግዚአብሔር ቃል። ለመሆኑ የዚህ ፍቅር ተቃራኒው ምንድነው?Anonymous voting
  • ነፃነት
  • ፍርሃት
  • ጥላቻ
  • ዘረኝነት
0 votes
Photo unavailableShow in Telegram
ሮሜ 4 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁴ ነገር ግን እግዚአብሔር ጽድቅ አድርጎ ለሚቈጥርልን፣ ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው በእርሱ ለምናምን ለእኛም ጭምር ነው። ²⁵ እርሱ ስለ ኀጢአታችን እንዲሞት ዐልፎ ተሰጠ፤ እኛን ጻድቅ አድርጎ ለማቅረብም ከሞት ተነሣ። የትንሣኤው መገለጥ አማኞች ለማጽደቅ ነው፤ ትንሣኤ ኢየሱስ ከሙታን ተነስቷል ብለን የምናከብረው በአል ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ በሙታን መነሳት (የትንሣኤ መገለጥ ) አማኞች የእግዚአብሔር ጽድቅ የተደረጉበት ትክክለኛ ማንነታችን ነው። ትንሣኤ አማኞች በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ሆኖ የተገለጠበት ትክክለኛ ማንነታችን ነው። ትንሣኤ አማኞች በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተብለን የተጠራንበት ድንቅ መገለጥ ነው። ትንሣኤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሳት አማኞች ለማጽደቅ ተነሣ እንጂ ኢየሱስ ተነስቷል ብለን የምናከብረው በዓል አይደለም። #ትንሣኤ_በየአመቱ_የሚከበር_መንፈሳዊ_በአል_አይደለም፤ #ትንሣኤ_አማኞች_የእግዚአብሔር_ጽድቅ_ሆኖ_የተገለጡበት_ድንቅ_የምስራች_ነው። አማኞች የእግዚአብሔር ጽድቅ ናቸው ብለን ስንናገር ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት አማኞችን ለማጽደቅ ነው። #Messager_Ephraim_Gebreyesus https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
👍 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
#እግዚአብሔር_ልጆች የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ የሚለው የሐዋርያው ዮሐንስ አባባል በግሪኩ ቋንቋ የተገለጠበት ሐረግ ማነጻጸሪያ በሌለው ባልተለመደ ዓይነት ፍቅር እንደወደደን የሚገልጽ ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር በእግዚአብሔር አባትነት፤ የእግዚአብሔር አባትነት በእግዚአብሔር ፍቅር መጠን እንዲገለጡ እርስ በራሳቸው በእጅጉ የተሳሰሩ ናቸው። የእግዚአብሔር ፍቅር ጥልቀት ኃጢአተኛ፣ ደካማና ጠላቶች የነበርነውን እኛን ዳግም ለመዋጀት በማይመጠነው መልካምነቱ ልጁን ስለ እኛ በመስጠቱ የተገለጠ ነው። እግዚአብሔር ከአምላካችን ባሻገር አባታችንም ነው! (ሮሜ 5፥6) ሬቨረድ. ተዘራ ያሬድ Join and subscribers👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
❤#በሰራነው_ሳይሆን_ክርስቶስ_በሰራው❤ =============================== ✍️በአንዱ አዳም አለመታዘዘ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ (በኢየሱስ) መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ፡፡ (ሮሜ 5፥ 19) ✍️ኃጢአተኞች የተባልነው እኛ በሰራነው ሳይሆን አዳም በሰራው እንደ ሆነ ጻድቃን የተባልነውም እኛ በምሰራው ሳይሆን በክርስቶስ ሥራ ነው፡፡ ✍️ስራችን ኀጢአተኞች ካላደረገን ስራችን ጻድቃን ሊያደርገን አይችልም፡፡ ስለዚህ በአንዱ አዳም ሃጢያተኞች ሆነናል ብለን ለመናገር ካላፈርን በአንዱ በክርስቶስ ጻድቅ ነን ማለት እውነት እንጅ ከንቱ ድፍረት አይደለም ፡፡ (ሮሜ 5፡12-21) 📌 በክርስቶስ ላላችሁ ጸጋና ምህረት ይብዛላችሁ። የወንጌል እውነት Join and subscribers👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
👍 2 1🔥 1
በዚህ የመዝሙር ግብዣዬ ትነካላቹ የተባረኩበት የፀሎት መዝሙር ግብዣ #ፀጋ ይብዛልኝ @SisayAzusaRevivall
Show all...
01:00
Video unavailableShow in Telegram
#ተከፍሏል_ነቢይ_እዩ_ጩፋ_Shorts_(720p).mp4 ሙሉ ስብከቱ ለማግኘት ከዚህ በታች ባለው ሊንክ መሠረት ተጭናችሁ እንድትሰሙ እጠይቃለሁ። ስብከት ርዕስ፦ ተከፍሏል.mp4 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
ስለ 3ኛው የአለም ጦርነት የተነገረ ትንቢት... - Christian Promotion - CP https://www.facebook.com/GospelMusicEthiopia/photos/a.1335101486618309/4729852057143218/?type=3
Show all...
ዛሬ ህልም አለኝ። አንድ ቀን ሸለቆው ሁሉ ይዋጣል፣ ኮረብታውም ከፍ ከፍ ይላል፣ ተራራውም ሁሉ ዝቅ ይላል፣ ሸካራማ ቦታው ሜዳ ይሆናል፣ ጠማማውም ስፍራው ይቃናል፣ የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል የሚል ህልም አለኝ። ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያዩታል። ይህ ንግግር የተናገረው ማነው?Anonymous voting
  • ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒዮር
  • ወንጌላዊ ዶክተር ቢሊ ግርሃም
  • ባራክ ኦባማ
  • ኔልሰን ማንዴላ
0 votes
👍 1 1😁 1🤩 1
Photo unavailableShow in Telegram
“እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 2፥4-5 "አገልጋይ ነኝ።" ባይ ግን በሰዎች ዘንድ ለመወደድ ሲባል ዋጋ ሌለው ውሸት ዋጋ የሚተምን እውነትን ግን የሚሰውር፤ብሎም ለግል ጥቅም የሚያሸረግድ የጌታ አገልጋይ ሊሆን አይችልም። “ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም።” — ገላትያ 1፥10 የዚህ መልዕክት የጸሐፊ Milka Yonatan Join and subscribers👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
07:38
Video unavailableShow in Telegram
በወንድም ዳዊት ፋሲል በማቴዎስ ወንጌል ም.25 ላይ በተመለከተ የሰጠው ማብራሪያ ይመልከቱ። Join in the group👇👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
Salvation/መዳን/ ክፍል አንድ ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ ❤ መዳን በኢየሱስ ክርስቶስ❤❤ ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (ሐዋ. 4፡12) ከላይ ያለው መልዕክት ስለ መዳን የተነገረን አንድ እውነት አለ፤ መዳን የሚገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ ነው። ✍️ “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤” የሚለው ቃል መዳን በሰው ሆነ በመላዕክት ዘንድ ሊገኝ የማይችል በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ የምትቀበለው የዘላለም ድነት ነው። ✍️ “እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” የሚለው ቃል ድነት የተገለጠው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኝው የዘላለም ህይወት ሰዎች ሁሉ አምኖ እንዲድኑ የተሰጠ ስም ሲሆን ከዚህ ስም ውጭ ሌላ የመዳን መንገድ እንደሌለ አስረግጦ ይናገራል። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያዘጋጀው ድነት በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የዘላለም ህይወት እንዲቀበሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። “ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”   — ዮሐንስ 14፥6 (አዲሱ መ.ት) ❤❤❤❤❤❤❤ ❤ ኢየሱስ ያድናል!  ❤ ❤❤❤❤❤❤❤ 📖📖📖ይቀጥላል📖📖📖 Join in the group👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
👍 3 2
ንቧ🐝 ና ሲሳይ ተፋጠጡ😄 #የልፍለፍ ፕሮግራም #ለታዳጊዎች ና #ለወጣቶች #ምክር #አስቂኝ ና ቁም ነገር ከሲሳይ አዙዛ ጋ @SisayAzusaRevivall
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ የሚለው የሐዋርያው ዮሐንስ አባባል በግሪኩ ቋንቋ የተገለጠበት ሐረግ ማነጻጸሪያ በሌለው ባልተለመደ ዓይነት ፍቅር እንደወደደን የሚገልጽ ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር በእግዚአብሔር አባትነት፤ የእግዚአብሔር አባትነት በእግዚአብሔር ፍቅር መጠን እንዲገለጡ እርስ በራሳቸው በእጅጉ የተሳሰሩ ናቸው። የእግዚአብሔር ፍቅር ጥልቀት ኃጢአተኛ፣ ደካማና ጠላቶች የነበርነውን እኛን ዳግም ለመዋጀት በማይመጠነው መልካምነቱ ልጁን ስለ እኛ በመስጠቱ የተገለጠ ነው። እግዚአብሔር ከአምላካችን ባሻገር አባታችንም ነው! (ሮሜ 5፥6) 📌 የእግዚአብሔርን ፍቅር መረዳት ከሚለው አዲስ መጽሐፍ የተወሰደ! ሬቨረድ. ተዘራ ያሬድ https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኤፌሶን 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁸ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ⁹ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ¹⁰ እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ወዳጄህ በኢየሱስ ክርስቶስ ተሰርቶ ያለቀው የመስቀል ስራ በጸጋው እምነት መቀበል ስለቻለን ሀይማኖት አያስፈልግም። ሀይማኖት በመስቀል ላይ የተሰራው ስራ ሳይሆን በአንተ ጥረት እና ትግል እንድትኖር የሚያድርግ ከባድ ቀንበር ነው። ሀይማኖትን መከተል ትተህ የሕይወት ቃል ያለው ኢየሱስ ብትመርጥ ይሻላል። ኢየሱስ ያሳርፋል እንጂ እንደ ሀይማኖት ስርአት ሸክም አትሆንም። ኢየሱስ በጸጋው አካል ስለሆነ ያሳርፋል እንጂ በሀይማኖት ቀንበር ስር አይቀመጥም። https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
02:01
Video unavailableShow in Telegram
#አማራጭ_የሌለው_ምርጫ_ኢየሱስ_ብቻ_ነው_ይሄን_ድንቅ_መልዕክት_ላልሰሙ_አሰሙልኝ_የመዳን_ቀን_ዛሬ_ነው። Join and subscribers👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
👍 2 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
"በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውን ከእንግዲህ አላስብም።" -ዕብራውያን 8:12 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
1
የእግዚአብሔር መለኮታዊ ፍቅር የእግዚአብሔር መለኮታዊ ፍቅር ማለት እግዚአብሔር ሰውን የወደደው መስፈርት አስቀምጦ ሳይሆን አንድያ ልጁን እስከመስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ የወደደው በመለኮታዊ ፍቅሩ ነው። እግዚአብሔር ሰውን የመውደድ ጥጉን ልጁን እስከመስጠት ድረስ ነው፤ ዮሐ.3፥16-17። ዮሐንስ 3 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁶ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ¹⁷ እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር በሰው ልጆች ላይ የተገለጠው አንድያ ልጁን ወደ አለም በመላክ ገደብ የሌለው መለኮታዊ ፍቅሩ የገለጠበት ድንቅ ስጦታ ነው፤ 1ዮሐ.4፥9። እግዚአብሔር እኛን የወደደው ለሀጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን እስከመስጠት ድረስ ነው፤ 1ዮሐ.4፥10። 1ኛ ዮሐንስ 4 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁹ እግዚአብሔር ፍቅሩን በመካከላችን የገለጠው እንዲህ ነው፤ እኛ በእርሱ አማካይነት በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከ። ¹⁰ ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው። እግዚአብሔር እኛን የወደደበት የምህረቱ ባለጠግነት አንድ ልጁን ሳይሳሳ እንዲሁ መውደዱ ነው፤ ሮሜ 8፥32፤ ኤፌ.2፥4-5። ኤፌሶን 2 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴ ነገር ግን በምሕረቱ ባለጠጋ የሆነ እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ፣ ⁵ በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ፣ በክርስቶስ ሕያዋን አደረገን፤ የዳናችሁት በጸጋ ነው። የእግዚአብሔር መለኮታዊ ፍቅር አንድያ ልጁን በመስጠት ገልጧል፤ ሮሜ 5፥8። “ነገር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል።”   — ሮሜ 5፥8 (አዲሱ መ.ት) https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
1
የሰው ማንነት Introduction ❖ሰው/Human/ ሰው፤ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር ዐፈር አበጀው፤ የሕይወትንም እስትንፋስ እፍ አለበት (ዘፍ.2፥7)፤ ስለዚህ ሰው ሥጋ፣ነፍስ እና መንፈስ ነው። ሴትንም ከወንድ ፈጠረ፤ ዘፍ.2፥21:22። መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ሰውን እንዴት እንደ ፈጠረው ከዚህ የበለጠ መግለጫ አይሰጥም። ሰው አስቀድሞ ሕይወት ካለው እንስሳ ሳይሆን ግዑዝ ከሆነው ከዐፈር መፈጠሩን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስተምራል። ሰው ከእንስሳት ፈጽሞ የተለዩ መሆኑ በእግዚአብሔር መልክ እና ምሳሌ በመፈጠሩ ይታያል፤ ዘፍ.1፥26፤ 2፥7፤ 3፥19። ብዙ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ሰውን በአንድ ቀን እንደ ፈጠረ ያምናሉ፤ ሌሎች ግን መጽሐፍ ቅዱስን በዘመናዊ ሳይንስ ከሚገኘው ከአዝጋሚ ለውጥ መላምት ዐሳብ ጋር ለማዛመድ እግዚአብሔር ሰውን በረጅም ጊዜ ውስጥ ፈጠረው ሲሉ ይሰማሉ። ========ይቀጥላል========= Join and subscribers👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ቅርስ  ጠባቂም አስጠባቂም ብቻ መሆን እንዴት ይሰለቻል! "#ሃይማኖት" የቱንም ያህል እድሜው ቢረዝም ምንም አያመጣም!ናፍጣና ቤንዚል የሌለው መኪና ምን መልኩ ቢያምርምንም በአይነቱ ጠንካራ ቢሆንምበዕውቅ ሰዎች የተዋቀረ ቢሆንም በቃ አይሄድም! 😥 ለዚህ አይመስላችሁም ወደ ፊት ከመሄድ ይልቅ ባለህበት ቁም እንደሚል ወታደራዊ ትዕዛዝ ቆመን ያለነው? 😥 የጓደለን ጥቅስ አይደለም! አለም ከጥቅስ በስተቀር ምንም እንደሌለን ክፍተታችን እስክታይ እንደምን እንዲህ ሳትን?😥 የጎደለን ጥቅስ አይደለም የጥቅሱ ባለቤት መንፈሱ እንጂ😥 ክርክር ትችት መከፋፈል መከፋፋት አይደለም የጎደለን - የእግዚአብሔር ጥበብና ኅይል የሆነው ክርስቶስ እንጂ: የጎደለን ስብከትም ዝማሬም ህንፃም የተማሩ ሰዎችም አይደሉም - አላዛርን ጎትቶ የሚያወጣው ክርስቶስ እንጂ: ቤተክርስቲያን ያለክርስቶስ በዶክትሪንና በዶግማ ብርድልብስ ተሸፋፍና ረጅም አመታትን መቆየት ትችላለች: ይሄ ደግሞ በታሪክ የተረጋገጠ ነው:: ቤተክርስቲያን ሌላ ዶግማና ዶክትሪን ሳይሆን የሚያስፈልጋት የሕይወት ምንጭ የሆነው ክርስቶስ ነው: አለም ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያንም ጭምር የክርስቶስ ሕይወት በሙላት ተገልጦ ለማየት ርሃብተኛ ናት😥 ዶሮ ወጥ ምን ምን እንደሚሸት ማወቅ ዶሮ ወጥን መብላት አይደለም:: የሰው ልጅ ሆይ በውኑ እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን? #ጌታ_ሆይ_አንተ_ታውቃለህ:: ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉@biruk351
Show all...
03:43
Video unavailableShow in Telegram
4🤩 1
ዋጋህን ማወቅ ከፈለክ ምትሄድበትን ቦታ እወቅ!    "አንድ ልጅ አባቱን ሄደና 'ዋጋዬ ስንት ነው?' ብሎ ጠየቀው። አባትም አንድ የከበረ ድንጋይ ሰጠውና 'እሄን ይዘህ ሱቅ ሂድና ስንት ነው? ሲልህ ምንም ሳትናገር ሁለት ጣትህን ✌️አሳየው አለው።' ልጅም እንደተባለው የከበረ ድንጋዩን ይዞ ሱቅ ሄደ። ባለሱቁም 'ስንት ነው?' ብሎ ሲጠይቀው ሁለት ጣቱን አሳየው፤ ባለሱቁም '2 ብር' ሲለው ምንም ሳይመልስለት የከበረ ድንጋዩን ይዞ አባቱ ጋ ተመለሰና የሆነውን ነገረው።    "ከዛ አባትየውም እራሱኑ የከበረ ድንጋይ ይዞ ወርቅ ቤት እንዲሄድና ስንት ነው? ሲልህ ለባለሱቁ የሰጠሀውን አይነት መልስ ስጠው' አለው። ልጁም እንደተባለው ወርቅ ቤት ይሄድና 'ስንት ነው?' ሲባል ሁለት ጣቱን አሳየ። የወርቅ ቤቱም ሰውዬ '2ሺ' ብሎ ሲጠይቀው፤ ምንም ሳይመልስ አባቱ ጋ ተመለሰ። ከዛ የሆነውን ነገረው።"   "አባትየውም ለ3ተኛ ጊዜ እራሱኑ የከበረ ድንጋይ ይዞ 'የከበረ ድንጋይ ሚሸጥበት ሂድና ለሁለቱ የመለስክላቸውን አይነት መልስ ስጥ' አለው። ልጅም የከበረ ድንጋይ ሚሸጥበት ቦታ ሄደና 'ስንት ነው?' ሲባል እንደቅድሞቹ ሁለት ጣቱን አሳየ፤ ሰውየውም '200 ሺ' አለው፥ ልጁም ምንም ሳይናገር አባቱ ጋ ተመለሰ እና የገጠመውን ነገረው። አባትም 'አየህ ልጄ ያንተ ዋጋ ሚተመነው ቦታህን ስታውቅ ነው፤ ርካሽ ቦታ ከሄድክ ያረክሱሃል፥ ውድ ቦታ ከሄድክ ውድ ነህ!' ብለው አስተማሩት።"   🗣:- ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ https://t.me/Amazing_Grace_minister
Show all...
👍 3
የሰው ምንድነው?Anonymous voting
  • ሰው መንፈስ፣ ነፍስ እና ሥጋ ነው።
  • ሰው መንፈስ ነው ነፍስ አለው በሥጋ ውስጥ ያድራል።
  • ሰው መንፈስ ብቻ ነው።
0 votes
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በዚህ የቴሌግራም አገልግሎት ስለ እግዚአብሔር ጸጋ በተከታታይ ስናስተምር ቆይተናን አሁን በቅርብ ቀን ስለ ሰው ማንነት በሚል ርዕስ በቅርብ ማስተማር እንጀምራለን። Join and subscribers👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
#ታጥበናል፣ #ተቀድሰናል፣ #ጸድቀናል “ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥11 ታጥበናል፣ ተቀድሰናል፣ ጸድቀናል ስንል በግብዝነት የምንናገረው ቃል ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ በተሠራው ስራ በእኛ ማንነታችን የተደረገንበት እና የተሠራበት መሆኑን ለማሳየት ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ ያመነ አማኞች ከሀጢአት እና ከሞት ነፃ በመሆን ወደ ተቀደሰው የእግዚአብሔር ህይወት እና ማንነት ተካፋይ ሆነናል። ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌ.2፥1-2 በተናገረው መሠረት በበደላችን እና በሀጢአታችን ሙታን እንደነበርን፤ አሁን ግን ዳግመኛ በተወለደነው በክርስቶስ ኢየሱስ በማመናችን በጸጋው እምነት ድነናል (ኤፌ.2፥8-10)። በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩ ሰዎች በየእለቱ ይቀደሱ ነበር፤ አሁን ግን በአዲስ ኪዳን ዘመን የሚኖሩ አማኞች (ቤተክርስቲያን) ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በክርስቶስ ኢየሱስ ተቀድሰናል። #Messager_Ephraim_Gebreyesus https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
👍 1
02:42
Video unavailableShow in Telegram
የተጠራነው ኢየሱስ እንድንመስል ነው። ወንድም ዳዊት ፋሲል Join and subscribers👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
01:25
Video unavailableShow in Telegram
እምነቱ_ፅድቅ_ሆኖ_ተቆጠረለት🙏
በአዲስ ኪዳን የተገለጠ ጽድቅ በእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ነው።
Join and subscribers👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
3🎉 1
ክፍል=ሦስት እግዚአብሔር ልጆች ሮሜ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁹ የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና። ²⁰ ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም፤ ²¹ ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው። የእግዚአብሔር ልጆች መገለጥ የፍጥረት ዋና ናፍቆት ነው። ፍጥረት የእግዚአብሔር ልጆችን መገለጥ በናፍቆት የሚጠባበቀው ከንቱነት እና ከባርነት ነፃ ወጥቶ ወደ እግዚአብሔር ልጅነት ወደሆነው ነፃነት እንዲኖር መፈለጉ ነው። ፍጥረት የእግዚአብሔር ልጆችን መገለጥ አጥብቆ የሚሻ ፍጥረት ነው። የእግዚአብሔር ልጆች መገለጥ ማለት የእግዚአብሔር መለኮታዊ ክብር በህይወቱ ላይ ተገልጦ ለፍጥረት ብርሃን መሆን ነው። የእግዚአብሔር ልጆች በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ድንቅ ልጆች ናቸው፤ ሮሜ 8፥14። ፍጥረት ከመበስበስ ባርነት ወደ ከበረው ነፃነት እንዲመጣ አጥብቆ የሚሻ ነው። የእግዚአብሔር ልጆች ሲገለጡ በሁለት ነገሮች ላይ የተመሠረተ ነው። #1.የምድር ጨው ሆኖ የሚገለጡ ናቸው፤ ማቴ.5፥13፣ #2.የዓለም ብርሃን ሆኖ የሚገለጡ ናቸው፤ ማቴ.5፥14-16። ከላይ ባለው መሠረት የእግዚአብሔር ልጆች በሁለት ነገር ሲገለጡ የፍጥረት ናፍቆት እርካታ የሚሰጡ ይሆናሉ። አማኞች የእግዚአብሔር ልጆች ሆኖ ሲገለጡ በምድር ላይ የሰው ህይወትን ጣፋጭ የሚያደርጉ ድንቅ ልጆች ሲሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ የዓለም ብርሃን ሆኖ ሲገለጡ በጨለማ እስራት የሚገኘው ፍጥረት ወደ ነፃነት ህይወት ይጋብዛል። #ማሳሰቢያ ክፍል ሦስት በዚህ አላበቃም ይቀጥላል። Join and subscribers👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
👍 1
01:16
Video unavailableShow in Telegram
📌የዘላለም ልብሳችን ኢየሱስ ነው! በወንድም ሀብታሙ አዲሱ Join and subscribers👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
01:30
Video unavailableShow in Telegram
#ተፅዕኖ_ፈጣሪ_ህይወት በአዲስ አበባ አዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ-ክርስትያን ከ10፡00 ጀምሮ ከአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ጋር የእግዚአብሔርን ቃል እንማራለን  እግዚአብሔርን በአምልኮ ከፍ እናደርገዋለን!!! አብረዉን የእግዚአብሔርን ፀጋ እንዲካፈሉ ጋብዘኖታል!!! #አድራሻችን_ገርጂ_ከኮሪያ_ሆስፒታል_ወደ_ቦሌ_ሆምስ_እንደታጠፉ_20_ሜትር_ላይ_ያገኙናል። Join and subscribers👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
2
00:54
Video unavailableShow in Telegram
እግዚአብሔር መልካም ነው። የፖስተር ዳዊት ሞላልኝ Join and subscribers👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
👍 1
✍ ሠርገኛ ነህ ወይስ ለቅስተኛ? ******** ወዳጄ፦ ✍ ለአይሁድ ተሰጥቶ የነበረውን የሙሴ ሕግ ካልፈጸምኩ ብሎ መፍጨርጨር ለአሜሪካ መንግሥት ግብር ካልከፈልኩ ብሎ እንደመጨነቅ ነው!! ✍ ለአሜሪካ መንግሥት ግብር ክፈል እንዳልተባልክ ሁሉ የሙሴንም ሕግ ጠብቅ አልተባልክም!! ✍ የሙሴ ሕግ የተሰጠው ለአይሁዳውያን ብቻ እንጂ ለአለም ሁሉ አይደለም!! ✍ የሙሴ ሕግ በራሱ የተመሰረተው የሌዊ ክሕነት ላይ ነው!! ✍ በሙሴ ሕግ ሊቀካሕናቱ አሮን እንጂ ኢየሱስ አይደለም!! ✍ ኢየሱስን ካሕን አድርጎ ያልሾመን የሙሴ ሕግ ጠብቂ የተባለች ቤተክርስቲያን የለችም!! ✍ በሙሴ ሕግ ደመወዝ እንጂ ስጦታ የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ የራስ ጥረት እንጂ የጸጋ እርዳታ የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ መስራት እንጂ ማመን አይቻልም!! ✍ በሙሴ ሕግ ባርነት እንጂ ልጅነት የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ መርከስ እንጂ መጽደቅ አይታወቅም!! ✍ በሙሴ ሕግ ሞት እንጂ ሕይወት የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ ፍርሀት እንጂ ድፍረት የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ መቅሰፍት እንጂ ምህረት አይታወቅም!! ✍ በሙሴ ሕግ ኩነኔ እንጂ ሰላም የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ ሀዘን እንጂ ደስታ የለም!! ✍ በሙሴ ሕግ ለቅሶኛ እንጂ ሠርገኛ የለም!! 📌 ጸጋ የተሰጠው ለአለም ሁሉ እንጂ ለአይሁዳውያን ብቻ አይደለም!! 📌 በጸጋ ሊቀካሕናቱ ኢየሱስ እንጂ አሮን አይደለም!! 📌 በጸጋ ጽድቅ እንጂ ኩነኔ የለም!! 📌 በጸጋ ሰላም እንጂ መታወክ የለም!! 📌 በጸጋ በረከት እንጂ እርግማን የለም!! 📌 በጸጋ ሕይወት እንጂ ሞት የለም!! 📌 በጸጋ ስጦታ እንጂ ደመወዝ የለም!! 📌 በጸጋ እረፍት እንጂ መባከን የለም!! 📌 በጸጋ መቻል እንጂ መዛል የለም!! 📌 በጸጋ መርካት እንጂ መጠማት የለም!! 📌 በጸጋ ልጅነት እንጂ ባርነት የለም!! 📌 በጸጋ ደስታ እንጂ ሀዘን የለም!! 📌 በጸጋ መቀደስ እንጂ መርከስ የለም!! 📌 በጸጋ ድፍረት እንጂ ፍርሀት የለም!! 📌 በጸጋ ድል እንጂ ሽንፈት የለም!! 📌 በጸጋ ሠርገኛ እንጂ ለቅሶኛ የለም!! 👉 እኔ በጸጋው አርፌአለሁና ሠርገኛ ነኝ!! አንተስ.....ሠርገኛ ነህ ወይስ ለቅስተኛ? #ሄኖክ_አሸብር https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
👍 3 2
00:30
Video unavailableShow in Telegram
#የመጀመርያውም_የመጨረሻውም_የአብ_ዜና_ኢየሱስ(360p).mp4
ድንቅ መልዕክት የመልዕክቱ ጸሐፊ እና ገጣሚ Hani Kurabachew https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
🔥 1
00:33
Video unavailableShow in Telegram
አምነዋለሁ-ኤባ_ዳንኤል_Amnewalehu-Ebba_Daniel(720p).mp4 Join and follow👇👇👇👇 Join👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
👍 1
ክፍል ሦስት ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን #ቃልም_ሥጋ_ሆነ። ዮሐንስ 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁴ ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም አደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጅን ክብር አየን። ¹⁵ ዮሐንስም፣ “ ‘ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበረ ከእኔ ይልቃል’ ብዬ የመሰከርሁለት እርሱ ነው” በማለት ጮኾ ስለ እርሱ መሰከረ። ¹⁶ ከእርሱ ሙላት ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋ ተቀብለናል፤ ¹⁷ ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ። ¹⁸ ከቶውንም እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም፤ ነገር ግን በአብ እቅፍ ያለው አንድያ ልጁ የሆነው አምላክ እርሱ ገለጠው። #ቃልም_ሥጋ_ሆነ ማለት የኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም ዘመናት በፊት ከአብ ጋር የነበረ የእግዚአብሔር ልጅ የራሱን ዝቅ በማድረግ ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ ፊል.2፥6-8። ፊልጵስዩስ 2 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም፤ ⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፤ ⁸ ሰው ሆኖ ተገልጦም፣ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ የራሱን በአባቱ ፈቃድ ሰው ሆኖ የተገለጠው እስከ መስቀል ሞት ድረስ በመታዘዝ ቃል ሥጋ ሆኖ ተገለጠ ማለት ነው። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ጋር በክብር ነበር፤ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር በክብር የነበረው የአንድያ ልጁ ወደ አለም ላከ። #ቃልም_ሥጋ_ሆነ ማለት ከእግዚአብሔር አብ ጋር የነበረው የእግዚአብሔር ልጅ ከድንግል ማርያም አማካይነት በመንፈስ ቅዱስ የተጸነሰ ሰው ሆኖ የተገለጠ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ቃል ሥጋ ሆነ የሚለው ድንቅ መገለጥ የእግዚአብሔር የባሕርዩ አምላካዊ ማንነቱ ሳይለወጥ ሰው ሆኖ የተወለደ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር የነበረ፤ የእግዚአብሔር  ትክክለኛ መልክ ይዞ ከድንግል ማርያም ተወለደ። Evangelist Ephraim Grace Man Join and subscribers👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
👍 4
00:43
Video unavailableShow in Telegram
ለመሞት ተዘጋጀተህ ኑር፤ ክርስትና ለመኖር ብቻ ሳይሆን ለመሞት ጭምር ነው። 👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
👍 1
01:23
Video unavailableShow in Telegram
🔖 ክርስቶስ ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ሀጢያተኞችን ለማዳን ነው። እኛ ሁላችን የእግዚአብሔር ወሰን የሌለው ትዕግስት ማሳያ እንሆን ዘንድ ምህረትን አገኘን። 1ኛ ጢሞቴዎስ 1:16 (አ.መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ "‘ክርስቶስ ኢየሱስ ኀጢአተኞችን ለማዳን ወደ ዓለም መጣ’ የሚለው ቃል እውነተኛና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ። ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ በእርሱ ለሚያምኑና የዘላለምን ሕይወት ለሚቀበሉ ወሰን የሌለው ትዕግሥቱን ከኀጢአተኞች ዋና በሆንሁት በእኔ እንደ ምሳሌ አድርጎ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ።" ከእሁድ መደበኛ አምልኮ ፕሮግራም የተወሰደ ፓስተር ጄሪ - ዘጸአት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን - ሳርቤት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
6
03:24
Video unavailableShow in Telegram
#ክርስቶስ_የእግዚአብሔር_መልክ_ነው። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
4
01:17
Video unavailableShow in Telegram
የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ድንቅ አምልኮ ጊዜ በቅርብ ቀን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚል ትምህርት በዚህ ቻናል ላይ ፖስት ይደረጋል። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/abundant_grace_church
Show all...
👍 1