cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ISLAM IS UNIVERSITY

⭐️ሰው የሚገነዘብ አእምሮና የሚያፈቅር ልቦና ባለቤት ነው።እነዚህ ሁለቱ ካልተመጣጠኑ ስብእናው አደጋ ውስጥ ነው።የሚያገናዝበው አዕምሮው፣የሚያፈቅረው ልቡ፣የሚንቀሳቀሰው አካሉናወደ ሰማይ የሚወነጨፈው መንፈሱ በውህደት ካልተንቀሳቀሱ ሰውየው ላይ ችግር አለ ማለት ነው 📨የፍቅር እና የጥላቻ ስሜቱ፣የፍላጎት እናየፍርሃት መንፈሱ በአዕምሮ ብስለት ካልተገራ አስቸጋሪ ነው አስተያየት👇 T.me/Aisuu_bot

Show more
Advertising posts
19 079
Subscribers
-1124 hours
-437 days
-19430 days
Posts Archive
🔰 #እየሩስ_አሌምን_ለገና_ስጦታ_አድርስልኝ 🔰   #ክፍል ☞ አንድ 1⃣ ✍ አሚር ሰይድ እየሩሳሌምን (ቁድስ) ለገና ስጦታ አቅርብልኝ ባለው የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊዮድ ጆርጅ ትዕዛዝ መሰረት እየሩሳሌም ከሰባት መቶ ዓመታት የሙስሊሞች አገዛዝ በኋላ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የአዉሮፓዊያን ንበረት የሆነችበት ሂደት እንዳስሳለን፡፡ ቁድስ በእስራኤል እጅ ስትሆን ከ700,000 በላይ ሙስሊሞች ከቁድስ ተፈናቅለዋል፡፡  የዓረቡ ዓለም ከእምነቱ ይልቅ ብሄሩን ያስቀደመበት አስከፊ የጃሂሊያ አመፅ መነሻ ሚስጢርና ያስከተለው አሁን ድረስ ያልበረደ ጠባሳ ለጋዛ ሰዎች እምባ ለቅሶ ምክንያት ምን እንደሆነ በዚህ ፁሁፍ እንዳስሳለን አብራችሁኝ ሁኑ፡፡በዚህ ፁሁፍ ዋቢ ያደረኩት ከሙሀመድ አሊ ቡርሀንና ከኡስታዝ አደም ካሚል ከተናገሯቸዉ ከፃፏቸዉና ከተለያዩ ታማኝ ምንጮች አዘጋጅቻለሁ፡፡ ይህ በተከታታይ የሚቀርብ ፁሁፍ በአንድ ቀን ቀንም ለሊትም ብየ ያዘጋጀሁት ስለሆነ Edit ለማድረግ ጊዜ የለም የቃላት ስህተት ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ እነሆ ወደ ፁሁፉ    ቸይም ሀይዝማን የተባለ ሳይንቲስቲት አሞኒያን በመጠቀም አሴቶን የተባለ ኬሚካል ፈለሰፈ፡፡ አሴቶን ለቦምብ ማምረቻ ይዉላል፡፡ እንግሊዝ ኬሚካሉን እጅግ ትፈልገው ነበር፡፡ ጦርነቱ በታሪክ የመጀመሪያው የኬሚካል ጦር መሳሪያዎች ለዉጊያ ተግባር አገልግለውበታል፡፡ ሀይዝማን የታወቀ የአይሁድ ጽዮናዊያን ንቅናቄ ተሳታፊ ነበር፡፡ለዚህ አይሁድ ለሰራዉ ቦንብ ሲባል ለእንግሊዝ ያቀሰበዉ ጥያቄ ለእስራኤል የሚሆን ሀገር ይሰጠን ቦንቡን በብዛት እንዳመርት የሚል ነበር ታዳ እንግሊዝ እስራኤልን ሀገር ለመመስረት እንቅስቃሴ ጀመረች የዓረቦችና የእንግሊዝ ግንኙነት ከ18ኛው ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ጀምሮ የተፀነሰ ነው፡፡ በተለይ ህንድን በቅኝ ግዛት ከተቆጣጠረች በኋላ ወደ ዓረቦች የምታደርገው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማደግ ጀመረ፡፡ ከሸይህ ሙሃመድ አብዱል ወሃብ  እንቅስቃሴ መወለድ በኋላም ያቆጠቆጠው ዲፕሎማሲዋ ተጠናከረ፡፡ ዓረቦች የራሳቸውን የዓረብ ኃያል መንግስት ለመፍጠር ሲነሳሱም ከጎናቸው ሆነች:: 1882 የዓረቦች ልብ የምትባለውን ግብፅ በቅኝ ግዛት ያዙ፡፡ ይህም የተጀመረውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በከፍተኛ መጠን አጠናከሮ ፖለቲካዊ መሰረት እንድታስይዘው አስቻላት:: በተለይ ግብጽን በቅኝ ግዛት ስትቆጣጠር ለንደን በካይሮ ለሚገኘው እንደራሴው የሰጠው ኻላፊነት ጉልህ ሚና እንዲጫወተ አደረገች፡፡ በሂጃዝ ቀጠና የሚገኘውን የአረቦች ኃይል እንዲከታተልና በቅርበት እንዲጎራበተዉ የሚያደርግ አቅጣጫ ተቀበለ፡፡ ሂጃዝ ማለት መካና መዲማን ጨምሮ በቀይ ባህር በኩል የሚያገናኘዉ የአረብያ ክፍል ነዉ፡፡ 1902 ላይ ሚከማህን የተባለው በግብፅ የእንግሊዝ ተወካይ ዓረቦችን ይበልጥ ወደሱ ዓላማ አቀረባቸው፡፡ አንድ የሀያ ስምንት አመት ወጣት ለስለላ ተግባር እንዲሰራም ወደ ዓረቢያ ላከው፡፡ ይህ ወጣት ቲ.ኢ.ሎረንስ ይባላል፡፡ በአንደኛው ዓለም ጦርነት የዓረቦች እንቅስቃሴ ጉልህ ስፍራ ያለው ወጣት ነው፡፡ በመጀመሪያ ዓረቦች በራሳቸው አንድነት ላይ እከል ውስጥ ነበሩ፡፡ ከሌሎች ሙስሊሞች ጋር ብቻ ሳይሆን በራሳቸውም መሃል ከፍተኛ ልዩነት ፈጥረው ነበር፡፡ በነገድና በጎሳ በመከፋፈል ተበታትነው እየኖሩ ነበር፡፡ ይህም ከነብዩ በፊት እንደነበረው የጃሂሊያ ዘመን ማለት ነው፡፡ በትናንሽ ጎሳ ተመዳድበው በየጊዜው ደም እየተፋሰሱ የሚኖሩ ኋላ ቀርነት ያጠመቃቸው ነገዶች ሆነዋል፡፡ ሁኔታው ለእንግሊዝ አዲስ ዓላማና አካባቢውን የመቆጣጠር ፍላጎት ወሳኝ ከፍተት ነበር፡፡ ሎረንስ ወደ ዓረቢያ ሄዶ እስልምናን እንደተቀበለ በመግለፅ በዓረቦች ልብ ውስጥ ጥልቅ ብሎ ገባ፡፡ ዓረባዊያኑ ሹሞች ሳይቀሩ ከርስቲያን ከሆነችው እንግሊዝ መሰሊም ይሆናል ብለው የሚጡበቁት ፈረንጅ ስላልነበረ በሎረንስ ሰለምኩ ማለት በጣም ተደሰቱ ተፍነከነኩ፡፡ እሱ ግን ከልቡ ሰልሞ አልነበረም፡፡ ሰዎችም በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነናል» የሚሉ አልሉ፤ እነርሱም አማኞች አይደሉም:: አላህንና እነዚያን ያመኑትን (ሰዎች) ያታልላሉ፤ የማያውቁ ሲኾኑ ነፍሶቻቸዉን እንጅ ሌላን አያታልሉም(2:8-9)አላህ ብሎን ነበር ግን ሙስሊሞችን ሸወዳቸዉ፡፡ ዓላማውን ለማሳካት ምክኒያቱ ሙስሊም ነኝ ብሎ መናገሩ እንደነበር በሚገባ ተገንዝቧል፡፡ አማኞች ብዙ ጊዜ የተከበረ ሰው ወይም በሰዎች ዘንድ እውቅና ያለው ሰው እምነታቸውን እንደተቀበለ ሲሰሙ ይደሰታል፡፡ ቅን ይሆኑለታል፣ ያምኑታልም፡፡ ይሄ በተለይ በሙስሊም ሱልጣኔቶች በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡ ሎረንስ ወጣት ቢሆንም ዓረቦች የሰጡት ከብር ከራሳቸው በላይ ነበር፡፡ ይህን እድል ተጠቅሞ ወደ እንድነት እመጣቸው፤ አሰለጠናቸው፤ በዘመናዊ የእንግሊዝ ጦርም አስታጠቃቸው፡፡ ከሱ ጋር የተገናኘው የዓረቦች መሪ ሸሪፍ ሁሴን ነበር፡፡ የሐሺማዊያን የዘር ግንድ ውስጥ በመሆኑ በዓረቦችም በሙስሊሞችም ዘንድ የላቀ ክብር አለው፡፡ የሀሽምይ ዓረቦች ከነብዩ ሰዐወ የዘር ግንድ ጋር የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ለዚህ ነው ሸሪፍ ሀሴን ኢብን ዓሊ የላቀ ቦታ የተሰጠው፡፡ በመካ ዓረቦች የተሰጠው ቦታ በሌሎች አካባቢ የሚኖሩ ዓረቦችም እንዲቀበሉት አስቻለው፡፡ አዲስ የፖለቲካ ዓላማም በዉስጡ ተወለደ፡፡ ኪታላቁ የሙስሊሞች ኻሊፌት(ቱርኮች ኡስማኖች) ተገንጥሎ ዓረቦችን ብቻ በማሳመፅ የዓረብ ስርወ- መንግስት የመፍጠር ከፍተኛ ጉጉት አደረበት፡፡ ይህ ከኸሊፋው የመገንጠል አመፅ በዓረቦች ዘንድ ወሬው ተዛመተ፡፡ ሸሪፍ ሁሴንም ብዙ ተከታይ የዓረብ ነገዶች ማግኘት ቻለ፡፡ ሆኖም ኺላፋው አካባቢውን ለመቆጣጠር የነበረው ብልጫ አመፁን በቀላሉ እንደሚቀለብሰው የታወቀው ሸሪፍ ሁሴን ለአመፁ የሚረዳውን የአቶማን ሱልጣኔቶች ጠላት ያሰላስል ጀመር፡፡ እንግሊዝና ፈረንሳይ ከበፊት ጀምሮ የሙስሊም ኺላፋዎችን ለማፈራርስ ተግተው ሲጥሩ እንደኖሩ ይታወቃል፡፡ አሁንም ኦቶማንን ለመጣል በዝግጅት ላይ በነበሩበት ሰዓት ሸሪፍ ሁሴን ከነሱ ጋር ለማበር ወሰነ፡፡ ሙስሊሞችን ለመምራት ስለፈለገ ቀድሞ የነበረውን የሙስሊሞች መሪ ለመጣል ልቡ ቋመጠ፡፡ ይህ ታሪካዊ የሙስሊሞች ዓረቦች ስህተት ለእንግሊዝ ከሎተሪ በላይ ሎተሪ ሆነላት፡፡ ከሰማይ እንደወረደ አስጎመዣት፡፡ የሙስሊም መሪ ሆኖ በሌላኛው የሙስሊም መሪ ላይ ለማመጽ ስለፈለገ እርዳታዋን እንድትቸረው ሲጠይቅ ለንደን ደንግጣለች ብንል ግነት አይሆንም፡፡ ይሄንን ወሬ ሲሰሙ ተሰምቷቸዉ የማያቅ ደስታ ተሰማቸዉ ፍጹም ያልጠበቀችው ብስራት ነበር፡፡ የኦቶማን ኺላፋ ታላቅነት ድባብ ያልጠፋበት ወቅት ላይ በተደጋጋሚ የሞከረችው ጥቃት ሳይበግረው ኻያልነቱን ጠብቆ የኖረ መንግስት ከዉስጥ አማጺያን ተነስተው ደግፉን ሲሉ እንደማየት ያለ ወሳኝ ዜና አልነበረዎ ለለንደን ሹማምንት፡፡ ጉዳዩን በጥንቃቄ ተከታትሎ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲሰጣቸው እንግሊዝን ወከሎ የግብጽ ሙስሊሞችን ለሚገዛው ሄንሪ ሚከ ማህን ኃላፊነት ተሰጠው፡፡ ከላይ እንዳነሳነው ሚክ ማህንም ቲኢ ሎረንስን ወደ ቀጠናው የጀመረውን የስለላና የዲፕሎማሲ ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ሁኔታዎችን አመቻቸለት፡፡ እንግሊዝ ለሸሪፍ ሁሴን እኛ እንግሊዞች አብረህ የምትዋጋ ከሆነ ከትግሉ ቡሀላ ሙሉ የአረቦችን ቀጠና እንዲመራ እንደምታደርግለት በሀምሌ ወር በ1915 በሚስጥር ተፈራረሙ፡፡
Show all...
በስምምነቱ መሰረት ሸሪፍ ሁሴን በኸሊፋው ላይ አመፅ እንዲያነሳ የሚለው ሀሳብ ይገኝበታል፡፡ አሳዛኝ የሙስሊም መሪነት አስተሳሰብ ነበር፡፡ ሙስሊሞች በስልጣን ጥም ተሸንግለው በራሳቸው መሪ ላይ አመፅ ለማንሳት የቋመጡበት የታሪከ አብነት፡፡ በሚስጢር የተደረገው ስምምነት ዶሴ ሙሉ በሙሉ ግልፅ ባልሆኑ ሀሳቦች የተሞሉ ነበሩ፡፡ ሸሪፍ ሁሴን ይህን ጉዳይ ሳያዉቀው እንዳልቀረ ብዙ ምሁራን ያምናሉ፡፡ የሸሪፉ ፍላጎት ስምምነቱ የሚሰጠውን ዉጤት ብቻ መጠበቅ አልነበረም፡፡ ዋና ግቡ ከእንግሊዛዊያኑ በቂ የጦርና ሎጂስቲክስ እርዳታ ማግኘት ነበር፡፡ ዉላቸው ላይፀና ቢችል የራሱን መንገድ እንደሚከተል ያስተዋለ ይመስላል ይላሉ ምሁራኑ፡፡ እንግሊዛዊያኑ ያሉትን ተቀብሎ ለፈረመላቸው ሸሪፍ ታዲያ መሳሪያዎችን ከመስጠት ጀምሮ በቂ የጦር ስልጠና ጭምር በመስጠት አልደከሙም፡፡ የኦቶማንን መንግስት ለመጣል ወሳኝ እድል ያገኙት በሙስሊም ዓረቦች በኩል መሆኑን አስረግጠው ይረዳሉና፡፡ እነሱም ለትግል አጋርነት ካልሆነ ለዓረቦች የገቡትን ቃል እንደማይቀጠሉበት ይገባቸዋል፡፡ እንግሊዝ ከዓረቢያ አንድ ጥግ (የፐርሺያ ሰላጤ አባዳን መንደር) የፈለቀውን ነዳጅ መቆጣጠር ችላለች፡፡ በዚያ ላይ በቀጠናው በተከታታይ ነዳጅ እንደሚፈልቅ እየተነገረ መሆኑን ዊንስተን ቸርችል አስተዉሏል፡፡ ከሁሉም የአዉሮፓ መሪዎች ቀድሞ ይህን በማስተዋሉ አካባቢውን በበላይነት መቆጣጠር የእንግሊዝ ብቻ እድል እንዲሆን ጥልቅ ዓላማ ይዟል፡፡ ስለዚህ ሁሉም በየስሜቱ የያዘውን ይዞ ሱልጣኑን መጣል ስለሚቀድም ብቻ ተግባብተው አለፉ፡፡ ክፍል ➋ ይቀጥላል......
Show all...
እየሩሳሌምን(ቁድስን) ለገና ስጦታ አድርስልኝ ዳታ እኛ ጋር ከተቋረጠ 6ወራትን አለፈ እናም የምንጠቀመዉ ከሌላ ቦታ በሚመጣ ዳታ ስለሆነ ተከታታይ ዳታ የመጠቀም ቻንስ ካገኘሁ ለገና ስጦታ ተብሎ በእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስተር ሊዮድ ጆርጅ ትዕዛዝ ለአንድ ኢሴቶ ለሚባል ቦንብ ለሰራዉ የሁዳ ሰዉ ዉለታ ሲል የየሁዳ ሀገር ለመመስረት ሲል ሙስሊም አለም ትልቁ ሶስተኛ መስጊዳችንን  ያጣነዉን ቁድስ በእኛዉ በሙስሊሞች ችግር እንዴት ቁድስ ከእጃችን እንደወጣች  ☞ቁድስ ከእጃችን ሲነጠቅ አረቦች ተሸዉደዉ አብረዉ ቁድስን እንዴት እንዳስረከቡ ☞አሁንስ ያለዉ ሁኔታ የአረቦች ዉድቀት ☞ እስራኤል የአሜሪካንን አስተሳሰብ ፓርላማ እንዴት ለእሷ ብቻ እንደሚያደሉ በሰፊዉ ሰፋ ባለ ፁሁፍ አዘጋጃለሁ ከተወሰኑ ቀናት ቡሀላ እንደምንም ዳታ አመቻቼ አቀርባለሁ ይጠብቁኝ፡፡ ✍ አሚር ሰይድ
Show all...
እየሩሳሌምን(ቁድስን) ለገና ስጦታ አድርስልኝ ዳታ እኛ ጋር ከተቋረጠ 6ወራትን አለፈ እናም የምንጠቀመዉ ከሌላ ቦታ በሚመጣ ዳታ ስለሆነ ተከታታይ ዳታ የመጠቀም ቻንስ ካገኘሁ ለገና ስጦታ ተብሎ በእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስተር ሊዮድ ጆርጅ ትዕዛዝ ለአንድ ኢሴቶ ለሚባል ቦንብ ለሰራዉ የሁዳ ሰዉ ዉለታ ሲል ሙስሊሞች ያጣነዉን ቁድስ በእኛዉ በሙስሊሞች ችግር እንዴት ቁድስ ከእጃችን እንደወጣች ☞ቁድስ ከእጃችን ሲነጠቅ አረቦች ተሸዉደዉ አብረዉ ቁድስን እንዴት እንዳስረከቡ ☞አሁንስ ያለዉ ሁኔታ የአረቦች ዉድቀት ☞ እስራኤል የአሜሪካንን አስተሳሰብ ፓርላማ እንዴት ለእሷ ብቻ እንደሚያደሉ በሰፊዉ ሰፋ ባለ ፁሁፍ አዘጋጃለሁ ከተወሰኑ ቀናት ቡሀላ እንደምንም ዳታ አመቻቼ አቀርባለሁ ይጠብቁኝ፡፡ ✍ አሚር ሰይድ
Show all...
ከመፅሀፍ ገፅ ➊➊ #ወንድም_መተኪያ_የለውም ✍አሚር ሰይድ አንዲት ሴት ናት። የራሷ ባሏ፣ ልጇና ወንድሟ የአገር መሪውን አል-ሙንተሲር ቢላህን ለመግደል አሲረዋል ብላ ታስወነጅላቸዋለች፡፡ ባለሥልጣናትም እሷው ባቀበለቻቸው መረጃ ላይ ተመርኩዘው ሦስቱን ሰዎች እስር ቤት አስገቧቸው፡፡ ጉዳያቸው ከተጣራ በኋላ አልሙንተሲር ቢላህ ሦስቱ ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ ትዕዛዝ ሰጡ፡፡ ሴትየዋ ይህን ውሳኔ ስትሰማ ግን ሮጣ ወደ መሪው ቤት በመሄድ በእግራቸው ላይ ወደቀች። ለቤተሰቧ አባላት ምሕረት እንዲያደርጉ ወይም እሷንም ከነርሱ ጋር እንዲገድሏት ተማፀነቻቸው አልሙንተሲር ቢላህ የሴትየዋ ሁኔታ ስላሳዘናቸው ጥቂት ካሰቡ በኋላ “አንቺ ሴት ምልጃሽን ተቀብዬአለሁ፡፡ ምሕረት የማደርገው ግን ከሦስቱ ሰዎች ለአንዱ ብቻ ይሆናል:: የትኛውን ከቅጣቱ እንዲተርፍልሽ እንደምትፈልጊ መወሰን ያንቺ ፈንታ ነው አሏት፡፡ ሶስቱንም ስለምትወዳቸው ማንን እንደምትመርጥ ግራ የገባት ሴት ከብዙ ማሰብ በኋላ እንዲህ የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰች። >ሌላ ባል ማግባት ይቻላል፣ >ሌላ ልጅም መውለድ ይቻላል፣ ወንድሜን ግን መልሼ ላገኘው አልችልምı እሱ ከተገደለብኝ በምንም ልተካው አልችልም ስለዚህ እሱ እንዲተርፍልኝ እመርጣለሁ* በሴትየዋ ብልሀነትና አርቆ አስተዋይነት የተደነቁት አልሙንተሲር ቢላህ ሶስቱንም አሰናበቷት ዘመዶችሽን ምሬልሻለሁ ይዘሻቸው ሂጂ በማለት አሰናበታት፡፡ ወንድም መተኪያ ያለዉም!!! join👇👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group
Show all...
ከመፅሀፍ ገፅ 10 #የኪስራው_ሚስትና_አሳ_አጥማጅ ✍አሚር ሰይድ የፋርስ ንጉስ የነበረው ኪስራ ኢብኑ ፐርቬዝ ዓሣ መመገብ የሚወድ ንጉስ እንደነበር ይነገራል። አንድ ቀን ኪስራ ከሚስቱ ሺሪን ጋር ተቀምጦ ሳለ የሆነ ዓሣ አጥማጅ ያጠመደውን ግዙፍ ዓሣ ወደ ቤተ-መንግሥቱ በማምጣት በሽልማት መልክ ለንጉሱ አበረከተለት። ንጉሡም በዓሣው ትልቅነት በመገረሙ ለአምጪው 4 ሺ ዲርሃም ሸለመው፡፡ ዓሣ አጥማጁ ልክ እንደሄደ የንጉሱ ሚስት የባሏን አድራጐት በማውገዝ፦ “ይህን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለአንድ ዘመድህ ብትሰጥ ዘመድህ ለአንድ ተራ አጥማጅ የሸለምከውን ገንዘብ እንዴት ትሰጠኛለህ ብሎ ሊወቅስህ ይችላል' አለችው፡፡ ኪስራ፦ -ያልሽው ነገር እውነት ሊሆን ይችላል፡፡ አስቀድሜ የሸለምኩትን ገንዘብ እንዴት መልሼ እቀበለዋለሁ?” ሲላት፥ ,,,,,,ሺሪን- “እኔ ይህን የማደርግበት ዘዴ አውቃለሁ፡፡፨ ዓሣ አጥማጁን አስጠራው' አለችው፡፡ 'ሲመጣ ዓሣው ወንድ ነው ወይንስ ሴት? ብለህ ጠይቀው፡፡ ፆታው ወንድ ነው ካለህ አይ እኔ እንኳ የፈለግኩት ሴት ነበር ትለዋለህ። ሴት ናት ካለህ ደግሞ እኔ የፈለጉት ፆታው ወንድ የሆነ ዓሣ ነበር ትለዋለህ” በማለት መከረችው፡፡ ዓሣ አጥማጁ ርቆ ስላልሄደ ተጠርቶ ሲመጣ የሆነ ችግር እንዳለ ስለጠረጠረና በተፈጥሮውም ብልህ ሰው ስለነበር ገንዘቡን መልስ ቢሉት የማምለጫ ዘዴ እያሰላሰለ ንጉሱ ፊት ቀረበ፡፡ .....ንጉሡ “ቅድም ያመጣህልን ዓሣ ወንድ ዓሣ ነው ወይንስ ሴት?” ሲሉትም የዓሣ አጥማጁ ምላሽ -ንጉስ ሆይ ዓሣው እንኳን ሁለቱም ፆታ አለው፡፡ ወንድም ሴትም ነው˚ የሚል ሆነ፡፡ ዓሣ አጥማጁ ከጥያቄው በስተጀርባ ያለውን ዓላማ ተረድቶ የማምለጫ ዘዴ በማበጀቱ የተደነቀው ንጉስ ለፈጣን ብልህነቱ ተጨማሪ 4 ሺ ዲርሃም ሸለመው፡፡ ዓሣ አጥማጁ አንድ ላይ 8 ሺ ዲርሃም ተሸክሞ ቤተ-መንሥቱን ለቆ ሊወጣ ሲል ከተሸከመው ገንዘብ ውስጥ አንዲት ድርሃም ስለወደቀችበት ሌላውን ገንዘብ መሬት አስቀምጦ ያቺን ዲርሃም ሊያነሣ አጐነበሰ። ይህን ሲያደርግ ንጉሱና ሚስቱ ይመልከቱት ነበር ድርጊት ያናደዳት ሺሪን ለንጉሱ 'የዚህን ስግብግብና ወራዳ ሰው አድራጐቱ ተመልከት! አንዲት ዲርሃም ስለወደቀችበት እርሷን ለማንሣት ብቻ ሌሎቹን ዲርሃሞች ከትከሻው አውርዶ መሬት ሲያስቀምጥ ያቺን ዲርሃም ከአሽከሮችህ አንደኛው እንኳን እንዲወስዳት እዚያው ትቷት አይሄድም ነበር? ስትለው .... ንጉሱ “እውነትሽን ነው ካላት በኋላ ዓሣ አጥማጁን አስጠርቶ “ለራስህ ምንም ክብር የለህምን? አንዲት ዲርሃም ለማንሳት ብለህ እንዴት በገንዘብ የተሞላ ቦርሣህን ከትከሻህ አውርደህ ታጐነብሳለህ? አንዲቷን ዲርሃም እዚያው ትተሃት አትሄድም ነበር? ....ሲለው ዓሣ አጥማጁ-ንጉስ ሆይ! አላህ ዕድሜዎን ያርዝምልዎ፧ እኔ ያቺን ዲርሃም ከወደቀችበት ያነሣሁት ትጠቅመኛለች ብዬ ሣይሆን በዚህች ዲርሃም ላይ ባንድ ጐኗ የእርስዎ ምስል በሌላው ጐኗ ደግሞ ስምዎ ተፅፎ ይገኛል፡፡ እዚያ ትቼያት ቢሄድ በቦታው የሚተላለፍ ሰው የርስዎ ስምና ምስል ያለባትን ያቺን ዲርሃም በድንገት ቢረግጥ የእርስዎን ክብር እንደመንካት ይቆጠራል የሚል ስጋት ስላደረብኝ ነው፡፡ አያድርገውና ይህ ቢከሰት ደግሞ እኔ የዚያ ወንጀል መንስዔ ሆንኩ ማለት ነው አላቸው በዓሣ አጥማጁ አስተሳሰብ የተማረኩት ንጉስ እንደገና ሌላ 4000 ዲርሃም ሸለሙት፡፡ ዓሣ አጥማጁ የተሸለመውን 12 ሺ ዲርሃም ተሸክሞ ከቤተ-መንግስቱ ሲወጣ ንጉሱ ባለሟሎቹን በመሰብሰብ “ከእንግዲህ በሴት ምክር ላይ ተመርኩዛችሁ ምንም ዓይነት ውሳኔ አታስተላልፉ:: ይህን ካደረጋችሁ እንደኔ ዲርሀሞቻችሁን ልታጡ ትችላላችሁ" በማለት ፈገግ😃😁 አስባላቸዉ፡፡ join👇👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group
Show all...
👍 1
ከመፅሀፍ ገፅ ➒ #የተበደለ_ሰው_ዱዓ_መሬት_ጠብ_አይልም ✍አሚር ሰይድ ነቢዩ ሰዐወ በእርሱና በአላህ መሃከል ምንም ዓይነት ግርዶ የለምና የተበደለን ሰው ዱዓ ፍሩ” ማለታቸውን ኢብኑ ዐብባስ አውርተዋል፡፡ ስለዚህ ሰዎች ሲበድሉን መፍትሔው መበሳጨት ወይም ለሌሎች ሰዎች መናገር ሳይሆን የአላህን እገዛ በነርሱ ላይ መሻት ነዉ፡፡ አርዋ ቢንት ዑወይስ ከእርሻ መሬቷ የተወሰነው በሰዒድ ኢብኑ ዓምር ኢብኑ ኑፈይል ተወስዶብኛል በማለት ለአሚር ሙሐመድ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ ሐዝም አቤቱታ አቀረበች፡በአላህ ይሁንብኝ የነጠቀኝን መሬት በአስቸኳይ የማይመልስልኝ ከሆነ በነቢዩ ሰዐወ መስጂድ ውስጥ ጀመዓው ፊት አዋርደዋለው በማለትም ዛተች፡፡ ሙሐመድ ግን- "እባክሽን የአላህ መልዕክተኛ ባልደረባ የሆኑትን (ሰዒድ ኢብኑ ዐምር) አትጉጂኣቸው፡፡ ሰዒድ የሚበድልሽ ወይም መብትሽንም የሚነካ ሰው አይደለም የሚል ምክር ሰጧት፡፡ አርዋ በዚህ ምላሽ ባለመርካቷ ወደ ዑመይራህ እና ዐብደላህ ኢብኑ ሰላማህ በመሄድ ተመሣሣይ አቤቱታና ዛቻ ሰነዘረች: ዑመይራና ዐብደላህ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ሰዒድ ዘንድ ሄዱ፡፡ ሰዒድ በእርሻ ቦታው ላይ ሆነው ወደሳቸው የመጡትን ሁለት ሰዎች ሲመለከቱ- 'ምን ጉዳይ ገጥሞኣችሁ ነው ወደኔ ልትመጡ የቻላችሁት?" በማለት ሲጠይቁ ....አርዋ ስለሳቸው የምታቀርበውን ክስ ለማጣራት መሆኑን ነገሯቸው፡፡ ሰዒድ ኢብኑ ዓምር በሰሙት ነገር በማዘን “የአላህ መልዕክተኛ ሰዐወ የሌላ ሰው ሐቅ የሆነችን የእጅ መዳፍ የምታክል መሬት እንኳን ብትሆን በሕገ-ወጥ መንገድ የወሰደ ሰው በቂያማ ቀን ከሰባቱ መሬቶች የዚያችን ቦታ የሚያክል ሸክም ይንጠለጠልበታል ማለታቸውን ስለሰማሁ ትምጣና የኔ ሐቅ ነው የምትለውን መሬት ትውሰድ” ካሉ በኋላ " #አላህ_ሆይ! ይህች ሴት በሐሰት ወንጅላኝ ከሆነ ሳትሞት የዓይኗን ብርሃን ነስተሃት የሞቷንም መንስዔ ዓይነስውርነቷ እንድታደርግ እጠይቅሃለሁ የሚል ዱዓ አደረጉ፡፡ ለሰዎቹም ያደረጉትን ዱዓ ለሴትየዋ እንዲነግሯት ጠየቁ። .... አርዋ ያሸነፈች መስሏት ሰዒድ በመሬቱ ላይ የነበረን ጎጆ በማፍረስ በምትኩ የራሷን ቤት ሠራች። ይሁን እንጂ ይህን እንዳደረገች ብዙም ሳትቆይ ዓይኖቿ ጠፉ፡፡ የምትንቀሣቀሰውም በአገልጋይዋ ድጋፍ ሆነ፡፡ አንድ ቀን ውኃ ለመቅዳት ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ብቻዋን በመሄዷ ጉድጓዱ ውስጥ ገብታ ሕይወቷ አለፈ፡ የተበደለ ሰው ዱዓ በአላህ ዘንድ ይህን ያህል ተቀባይነት አለው፡፡ ሰዉን ከበደል አደራ አደራ እንጠንቀቅ!!! join👇👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group
Show all...
ከመፅሀፍ ገፅ ➑ #የኢብን_ቀይም_ወርቃማ_አባባሎች ✍አሚር ሰይድ ኢብን ቀይም እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል- “አንድ የአላህ ባሪያ ከእንቅልፉ ሲነቃ ብቸኛው ምኞቱ አላህን ለማስደሰትና እርሱን ለመገዛት ከሆነ አላህ ወዲያው የዚህን ሰው ፍላጐቶች ሊያሟላለትና የሚያበሳጩትን ነገሮች ሊያስወግድለት ይወስናል። ይህ ብቻ አይደለም፨ አላህ የዚህ ሰው ልብ እርሱን ብቻ እንዲያፈቅር፣ ምላሱ እርሱን ብቻ እንዲዘክር፣ ሰውነቱ እርሱን ብቻ እንዲገዛ ያደርጋል፡ ባሪያው ሲነጋ ጭንቀቱ ሁሉ የዚህ ዓለም ጉዳይ ከሆነ አላህ የሰውየውን ጭንቀቶችና ሸክሞች ለራሱ (ለሰውየው) ይተወዋል። ልቡን በጭንቀት፣ ውሎውን በመከራና በብስጭት ይሞላል፡፡ ፍቅሩን ከዚህ ዓይነት ሰው ስለሚያርቀው የሰውየው ፍቅር ለምድራዊ ነገሮች ብቻ ይሆናል። ምላሱ ስለሌሎች ሰዎችና ሌሎች ነገሮች በማውራት ይገደባል። ሰውነቱ ያምጻል፡ ለተለያዩ ስሜቶችና ፍላጐቶች ተገዢ ይሆናል። ልፋቱ የአህያ ዓይነት ልፋት ይሆናል፡፡ ፊቱን ከአላህ ፍቅር፡ ዒባዳና ታዛዥነት ያዞረ ሰው ደግሞ ሕይወቱ በምድራዊ ደስታዎችና ፈንጠዚያዎች፣ ለፍጡራን በመገዛትና በማጐብደድ የተሞላች ትሆናለች- አላህ ﷽ “አር-ረሕማንን ከማውሳት ራሱን ያገለለ ሰይጣንን የቅርብ ወዳጁ ይሆን ዘንድ እናዘጋጅለታለን" (ቁርኣን 43:36) ብሏልና፡፡ ኢብን ቀይም ይህ እንዳይከሰት የሚከተለውን እንድናደርግ ይመክሩናል- “በሦስት ሁኔታዎች ውስጥ ስትሆኑ ልቦቻችሁን ፈልጉ ➊ ቁርኣንን ስታደምጡ፣ ➋ ዚክር ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል ስትቀመጡና ➌ ለብቻችሁ ስትሆኑ˚ በእነዚህ ሦስት ሁኔታዎች ውስጥ ሆናችሁ ልባችሁን ለመግዛት (ለመሰብሰብ) ካልቻላችሁ አላህ ልብ ይስጣችሁ* join👇👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group
Show all...
ከመፅሀፍ ገፅ ➐ #ሙእሚኑ_ሲፈተን! ✍አሚር ሰይድ አንድ ካፊር ለሙእሚን እንዲህ አለው፡፡ “አላህ ከከተበብኝ (ከጻፈብኝ) በስተቀር ሌላ ጉዳት አይነካኝም ብለህ አልነበረም? ሙእሚኑም “አዎ ብያለሁ አለው፡፡ ካፊሩ መልሶ “እንደሱ ከሆነ በል አሁን ከዚህ ተራራ ጫፍ ላይ ዝለል። አላህ ሊያድንህ ወስኖ ከሆነ ያድንሃል” አለው፡፡ ሙእሚኑም “ይህን ያልከኝን እፈጽም ነበር። ግን ደግሞ አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር ባሮቹን የሚፈትነው አላህ ነው እንጅ ባሮች አላህን አይፈትኑትም በማለት የካፊሩን ተንኮል ውድቅ አደረገበት፡፡ join👇👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group
Show all...
ስግብግብነት ሲበዛ ሙሐመድ አደ-ዳሪ የሚከተለውን አስተላልፈዋል- “ከእኛ መሃከል አንድ ስግብግብ ሰው ነበር። ይህ ሰው ያለውን ዐሥር አህዮች እየነዳ የዳር ከተማን ለቅቆ ወጣ፡ በመጓዝ ላይ እያለም አንደኛይቷን አህያ ተቀመጠባት፡፡ አህያዋ ላይ ተቀምጦ እያለ የተቀሩትን አህዮች ሲቆጥር ዘጠኝ አህዮች ብቻ ሆኑበት፨ አህዮቹን ደጋግሞ ቢቆጥርም ቁጥራቸው ያው ዘጠኝ ሆነ። ከዚያ ከተቀመጠው አህያ በመውረድ ·ተቀምጨያት ከማገኘው ጥቅም ከአንዲት አህያ ቁጥር የማገኘው ትርፍ እመርጣለሁ🙄 በማለት በእግር መጓዙን መረጠ። መኖሪያ ቀየው ሲደርስ ረጅም ርቀት በእግሩ ተጉዞ ስለነበር ተዝለፍልፎ ሊወድቅ ደርሶ ነበር፡፡ join👇👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group
Show all...
ከመፅሀፍ ገፅ ➎ #ሙእሚን_ከአንድ_ጉድጓድ_ሁለቴ_አይነደፍም ✍አሚር ሰይድ የበድር ጦርነት ወቅት አቡ ዐዝዛህ አል-ጁመሂ የተባለ ባለቅኔ በምርኮነት ሙስሊሞች እጅ ወደቀ፡፡ አቡ ዐዝዛህ የግጥም ተሰጥኦውን ተጠቅሞ በሙስሊሞች ላይ ቁረይሾችን ሲያነሣሣ የነበረ ሰው ነበር። ከተማረክ በኋላ ወደ ነቢዩ ሙሐመድ ሰዐወ ዘንድ ቀርቦ “እኔ ብዙ የቤተሰብ አባላትን የማስተዳድር ደሃ ስለሆንኩ ምሕረት አድርገውልኝ ይልቀቁኝ, ይዘኑልኝ• በማለት ተማፀናቸው፡፡ ነቢዩም ሰዐወ አዝነውለት እንዲለቀቅ አዘዙ፡፡ ሌላ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ግን ከቁረይሽ መሪዎች አንዱ የሆኑት ሶፍዋን ኢብኑ ኡመያህ ለአቡ ዐዝዛህ 'ያ አቡ ዐዝዛህ አንተ ትልቅ የግጥም ችሎታ አለህ  ይህን ችሎታህን ተጠቅመህ ተከታዮቻችን ሙስሊሞችን በመውጋት ላይ ጽናት እንዲኖራቸው ቀስቅስልን∶ በማለት ተማፀነው፡፡ አቡ ዐዝዛህ ነቢዩ ሰዐወ እሱን በመልቀቅ የዋሉለት ውለታ ስላለ ውለታቸውን ውድቅ በማድረግ የሚጐዳቸው ነገር ላይ ለመሳተፍ እንደማይፈልግ ቢነግረውም ሶፍዋን ኢብኑ ኡመያህ አቡ ዐዝዛህ በቅስቀሣው ዘመቻ የሚረዳቸው ከሆነ- “ከጦርነቱ በሰላም ከተመለስክ ከሃብቴ አካፍዬህ ሃብታም አደርገሃለሁ፡፡ በጦርነቱ ላይ ከተገደልክ ሴቶች ልጆችህን ከእኔ ሴቶች ልጆች ጋር የተቀማጠለ ኑሮ እንደማኖራቸው ቃል እገባልሃለሁ ብሎት አሳመነው፡ በተገባለት ቃል የጓጓው አቡ ዐዝዛህ ወደተባለው ጦርነት ሄደ። ለሁለተኛ ጊዜም የሙስሊሞች ምርኮ ሆነ፡፡ እንደ በፊቱም ነቢዩ ሰዐወ ፊት ቀርቦ ምሕረት እንዲያደርጉለት ጠየቃቸው፡፡ ነቢዩ  ግን “በአላህ ይሁንብኝ ከእንግዲህ ጉንጮችህ ዳግም መካን አይነኩም። በርግጥ ሙሐመድን ሁለቴ አታለሃል፡፡ አንድ ሙእሚን ደግሞ ከአንድ ጉድጓድ ሁለቴ አይነደፍም፡ ካሉት በኋላ ወደ ዙበይር ዞር ብለው ዝብይር ሆይ! ይህን ሰው ሰይፈው አሉት፡፡ ሁለቴ ለማታለል የሞከረው አቡ ዐዝዛህ በገዛ ቅጥፈቱ ምክንያት ሕይወቱን አጣ፡፡
Show all...
ከመፅሀፍ ገፅ ➍ #አላህ_እንዲህም_ያድናል! ✍ አሚር ሰይድ ከምዕተ ዓመታት በፊት የኖረው መሪ ሱልጣን ሱቀይላ እንቅልፍ ቶሎ የሚጥለው ሰው ነበር። ከምሽቶቹ በአንዱ ግን እንቅልፍ ሸሸው፡፡ ቢገላበጥ ሊወስደው አልቻለም። እንቅልፍ እንደሸሸው የተረዳው ሱቀይላህ 'መንቃቴ ካልቀረ ሥራ ልሥራ በማለት የባሕር ኃይሉን ጀነራል በመቀስቀስ “ከመርከቦቻችን አንዱን ወደ አፍሪካ ላክ፡፡ ምን እየተከናወነ እንደሆነም መልዕክት እንዲልኩ አድርግ የሚል ትዕዛዝ ሰጠው፡፡ ጄነራሱም እንደታዘዘው አደረገ፡ እንቅልፍ በማጣቱ በለሊት የሚንሸራሸረው ሱልጣን ቆየት ብሎ ወደ ባሕር ዳርቻው ወርዶ መርከቦቹን ሲቃኝ ወደብ የለቀቀ አንድም መርከብ አለመኖሩን ስላየ ጀነራሉን ተቆጣዉ:: ጀነራሉ የታዘዘዉን መፈፀሙን እሱ በማያቀዉ ምክንያት ተመልሶ መልህቅ መጣሉን ነገረዉ፡፡ መርከቡ ከጉዞው ለምን እንደተመለሰ የመርከቡን ካፒቴን ለመጠየቅ ተያይዘው ወደ ካፒቴኑ ሄዱ፡፡ ካፒቴኑም ለምን ከጉዞው እንደተገታ እንዲህ ሲል ነገራቸው፡፡ 'የባሕር ጉዞውን ስንጀምር ድቅድቅ ጨለማ ስለነበር ምንም ነገር ለመመልከት አልቻልንም፡፡ ትንሽ እንደተጓዝን ግን ከጭለማው ውስጥ ከባሕር ላይ “አላህ ሆይ አንተ ለእርዳታ ሲጠሩት ለጠሪው የምትደርስለት አምላክ እርዳኝ" የሚል የሰው ድምፅ ስለሰማን ድምፁን ወደሰማንበት አቅጣጫ አመራን፡፡ ስንደርስ የሆነ ሰው ከመስመጥ ለመዳን የሞት ሽረት ትግል ላይ ነበር፡፡ ከባሕሩ ውስጥ ጐትተን ካወጣነው በኋላ የገጠመውን ስንጠይቀው ይቀዝፍበት የነበረው ጀልባ እንደሰጠመችበትና እኛ እስከደረስንለት ጊዜ ድረስ እርዳታ ፍለጋ ሲጮህ ውሉ እንዳመሸ ነገረን ከዚህ ታሪክ አላህ የአንድ ግለሰብ ሕይወት ለማዳን ሲል የአገሩን መሪ እንቅልፍ መንሳቱን እንገነዘባለን፡፡ አላህ ሱወ ጥበቡ የላቀ አሠራሩ የረቀቀ እርዳታው ከማይጠበቅበት አቅጣጫ የሚደርስ አምላክ ነው፡፡
Show all...
ከመፅሀፍ ገፅ ➌ #የዱዓ_ዕምቅ_ኃይል ✍ አሚር ሰይድ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት አንዲት ሴት የኢማም ማሊክ ደረሳ የነበሩ ኢስማዒል የሚባሉ ዓሊም ታገባለች የዚህ የተቀደሰ ጋብቻ ትሩፋት ሙሐመድ የሚባል ልጅ ማግኘታቸው ነበር ኢስማዒል ብዙም ሳይቆዩ አረፉ። ከበስተኋላቸው ግን ለሚስታቸውና ለሕፃን ልጃቸው ማሳደጊያ የሚሆን ብዙ ሃብት ትተው ነበር፨ እናት ልጇን ሙሐመድን በጥሩ ኢስላማዊ ሥነ-ምግባር ኮትኩታ አሳደገች በቂ የዲን ዕውቀትም እንዲቀስም አደረገችው ልጃ, አድጐና በዕውቀት ፋፍቶ ታላቅ ዓሊም እንዲሆንላት ምኞት ቢኖራትም ይህ ልጅ አንድ ችግር ነበረበት ዓይነስውርነት። በዘመኑ ደግሞ ለዓይነስውር ታዳጊ በዕዉቀት ለመግፋት ምቹ ሁኔታ አልነበረም፨ የዲን ዕውቀት የሚፈልጉ ሰዎች ከአገር አገር፣ ከዓሊም ዓሊም መሄድ የግድ ስለነበር ይህ ልጅ ይህን ለማድረግ ዕድል አልነበረውም፡፡እናቱ ግን ተስፋ አልቆረጠችም በየዕለቱ ዱዓ ማድረግ ጀመረች በዚህ ሁኔታ እያለች ከዕለታት አንድ ቀን በእንቅልፋ ለየት ያለ ህልም አየች። በህልሙ ውስጥ ነቢዩላህ ኢብራሂም  ወደ እሷ መጥተው “ከዱዓዎችሽ ብዛት የተነሣ አላህ ሰምቶሽ ለልጅሽ የአይኑን ብርሀን መልሶለታል አሏት እናት እስኪነጋ ለመጠበቅ አልቻለችም፨ ተነስታ ልጁ, ወደተኛበት ክፍል ገብታ ከእንቅልፉ ስትቀሰቅሰው የሙሐመድ ዓይኖቹ በርግጥም በርተዋል አላህ የሚሳነው ነገር የለም፡፡ በታላቅ ጭንቀት ላይ ያሉና ለእርዳታ ወደርሱ የተመለሱትን ባሮች ከመርዳት ወደኋላ አይልምና አላህ የልጇን ዓይነስውርነት በመፈወሱ እጅግ የተደሰተችው እናት ልጇ ለትምህርት ያለውን ጉጉት ያብልጥ እንዲገፋበት በርትታ አዝዘችው በዚህ የዒልም ዘርፍ ከፍተኛ የተባለ ዕውቀቶችንም እንዲቀስም ረዳችው፡፡ በሕይወት ዘመኑ አጋማሽ ላይ ይህ ልጅ ከቁርኣን ቀጥሉ ታላቅ ተቀባይነት ያለውን መጽሐፍ ለማዘጋጀት የበቃው የሶሒሕ ቡኻሪ አጠናቃሪ –በሙሉ ስማቸው ሙሐመድ ኢብኑ ኢስማኢል አል- ቡኻሪ ናቸው፡፡ ቡኻሪ አላህ በዲናዊ ዕውቀት ያበለፀጋቸው እጅግ ብሩህ አስተዋይና አስታዋሽ አዕምሮ የሰጣቸው ታላቅ ዓሊም ነበሩ።
Show all...
ከመፅሀፍ ገፅ ➋ #ነፍስያውን_ያሸነፈው_ወጣት   🤞✍አሚር ሰይድ ኢብን ሐዝም በጣም ይዋደዱ ስለነበሩ ሁለት ጓደኛሞች ታሪክ አስተላልፈውልናል፡፡ ሁለቱ ጓደኛሞች ከመዋደዳቸው የተነሣ በመካከላቸው ምንም ገደብ አልነበራቸውም። ከዕለታት አንድ ቀን ጓደኛሞቹ በአንደኛው ቤት ተቀምጠው ሳለ መሸ። ከጓደኛው ጋር ሲጫወት የነበረውና የቤቱ ባለቤት የሆነው በድንገት ለአስቸኳይ ሥራ ወጥቶ ለመመለስ ባለመቻሉ በቤቱ የቀረው ጓደኛው እዚያው የማደሩ ነገር እርግጥ ሆነ። በቤቱ ውስጥ እሱና የጓደኛው ሚስት ብቻ ቀሩ፡፡የሁለቱን ጥብቅ ጓደኝነት የማታውቀው ሚስት እኩለ ለሊት ሲደርስ ከባሏ ጓደኛ ጋር የመተኛት ፍላጐት ስላየለባት እሱ ወደተኛበት ክፍል ዘልቃ በመግባት እንዲገናኛት ወተወተችው፡ በመጀመሪያ ላይ የጠየቀችውን ለማድረግ ልቡ ቢነሣሣም የጓደኛው አመኔታ ሲታወሰው ስሜቱን ለመግታት ያልተለመደ እርምጃ ለመውሰድ ተነሣ፡፡ የጓደኛው ሚስት ስታስቸግረውና የእሱም ስሜት ሲነሣሣ አንደኛውን የእጁን ጣት አጠገቡ በነበረው ኩራዝ ላይ እያስቀመጠ “ከጀሃነም እሳት ይህ ይሻልሃል' ይል ጀመር፡፡ ሴትየዋ ይህንንም እያየች ወጣቱን ለወሲብ መፈለጓን አልተወችም፡፡ እሱም እሷ ባስቸገረችውና ስሜቱ በተቀሰቀሰበት ቅፅበት የእጆቹን ጣቶች በኩራዝ መለብለቡን ቀጠለ። ሲነጋ ከእጆቹ ጣቶች አንደኛው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኖ ነበር፡፡ ጓደኝነት ይህ ነው
Show all...
👍 1
ከመፅሀፍ ገፅ #የነብዩ ሰዐወ መቃብር ቁፈራ የተጋለጠበት!! #አዘጋጅ ☞አሚር ሰይድ የታሪክ መጻሕፍት በ557 ዓ.ሂ የተከሰተን አንድ አስገራሚ ጉዳይ ሳይጠቅሱ አያልፉም፡፡ ያ ዘመን የዐብባሳውያን ሥርወ-መንግሥት በመንኮታኮት ላይ የነበረበት ዘመን ነበር፡፡ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በአጐራባች አገራት ይኖሩ የነበሩ ክርስቲያን መንግሥታት አንድ ከባድ ሴራ ጠነሰሱ። ሴራቸው የሙስሊሞችን መዳከም ተገን አድርገው የነቢዩን አስከሬን ከነበረበት በመስረቅ ወደ ራሳቸው ግዛት መውሰድ ነበር፡፡ ይህን በማድረግም በሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ሞራላዊ ጉዳት ለማድረስ አሰቡ:: ስለዚህ ይህን ረቂቅ ተንኮል ለማስፈፀም ሁለት የተመረጡ ሰላዮችን የሞሮኮ ኢስላማዊ አለባበስ በማልበስ ወደ መዲና ከተማ ሰደዱ ሰዎቹም ለነዋሪዎቿ ለፀሎት ወደ ቅድስቲቷ ከተማ የመጡ ሐጃጆች መሆናቸውን እንዲናገሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጣቸው፡፡ ሁለቱ ሰዎች ተልዕኮኣቸውን ለመወጣት እንዲችሉ መስጂደል ነበዊ (የነቢዩ መስጂድ) አጠገብ ባለ ቤት ውስጥ መኖር ጀመሩ፡፡ በጐረቤቶቻቸውም ዘንድ ለመታመን ሲሉ መስጂድ ማዘውተርና የዒባዳ ተግባራትን በጥልቀት ማከናወን የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ሆነ፡፡ ዋናው ጉዳያቸው ግን የተላኩበትን ዓላማ ማስፈፀም እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ይህን ተልዕኮ ለማከናወን የመጀመሪያ ሥራቸውንም ከነበሩበት ቤት አንስተው ወደ ነቢዩ መቃብር ለመድረስ ውስጥ ለውስጥ በመቆፈር መሿለኪያ ለማበጀት ቁፋሮ ጀመሩ፡፡ እንዳይነቃባቸውም በየቀኑ ትንሽ ትንሽ ብቻ እየቆፈሩ የሚያወጡትን አፈር በትናንሽ መያዣዎች አድርገው ጀለቢያቸው ሥር በማንጠልጠል አል-በቂፅ ወደሚባለው የመዲና    የቀብር ስፍራ እየወሰዱ ይደፉ ነበር። ሌሎቹ ነዋሪዎች ሰዎቹ በየዕለቱ ወደ ቀብር ሥፍራ የሚሄዱት የሞቱትን በመዘየር ሞትና አኼራን ለማሰብ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ ሰዎቹ አንዳንዴ ሲደክማቸው መሿለኪያ ለማበጀት የሚቆፍሩትን አፈር ከሚኖሩበት ቤት አጠገብ ወዳለ ጉድጓድም ይደፉ ነበር። እንዲህ እያደረጉ በመጨረሻ መሿለኪያውን ከነቢዩ ሰዐወ ቀብር ጋር ሊያገናኙ ደረሱ፡፡ እዚህ ደረጃ ሲደርሱ ተልዕኮኣቸው ለመሳካቱ እርግጠኛ ስለነበሩ የትኩረት አቅጣጫቸው የነቢዩን አስከሬን ካወጡ በኋላ በምን መንገድ ወደ መጡበት ግዛት እንደሚያጓጉዙ ማቀድ ነበር፡ የተለያዩ ዘዴዎችን አውጥተው አወረዱ፡፡ በዚያው ወቅት አላህ የራሱን ሴራ እያሴረባቸው እንደሆነ ግን አላወቁም፡፡ የዘመኑ የሙስሊሞች መሪ የነበሩትና ከመዲና ብዙ ርቀው የሚኖሩት ኑረዲን ሙሐመድ ኢብኑ ዘንጂ በዚያው ሰሞን አንድ ለየት ያለ ሕልም እዩ፡፡ በሕልማቸው ውስጥ ነቢዩ ሰዐወ ነበር የታዩዋቸው፡ ነቢዩ ወደ ሁለት ቀያይ ፀጉረ ልውጥ ሰዎች እያመለከቱ ከእነርሱ እንዲያድኗቸው ኑረዲንን ይማፀናሉ ይህን ከባድ ሕልም ሲመለከቱ ኑረዲን በድንጋጤ እየተንቀጠቀጡ ከእንቅልፋቸው ነቁ። ራሳቸውንም ለማረጋጋት ሶላት ከሰገዱ በኋላ ተመልሰው ወደ መኝታቸው ቢሄዳም አሁንም ያው ሕልም ተመልሶ መጣባቸው:: ሕልሙ ለሦስተኛ ጊዜ ሊመጣባቸው ከእንቅልፋቸው በመነሣት ከሚንስትሮቻቸው መካከል ሷሊሕና ብልህ የነበረውን ጀማሉዲን አል ሙሲሊ የተባለውን አስጠሩ፡፡ ያዩትን ሕልም ለጀማሉዲን ሲነግሩት ሕልማቸው በመዲና ውስጥ የሆነ እንግዳ ነገር እየተከናወነ መሆኑን እንደሚጠቁም አስረዳቸው፡፡ በአስቸኳይም ወደ ነቢዩ ከተማ በመሄድ ስለ ሕልሙ ለማንም ሳይናገሩ ሁኔታዎችን እንዲከታተሉ አሳሰባቸው፡፡ ኑረዲን ከለሊቱ የቀረውን ክፍል ለጉዞው ዝግጅት ሲያደርጉ አደሩ፡፡ ጀማሉዲንን ጨምሮ ሃያ ጭነት ከሃያ ሰዎች ጋር እንዲዘጋጅ አዘዙ፡ ከሻም(ሶሪያ) ተነስተው መዲና ለመድረስ የፈጀባቸው ዐሥራ ስድስት ቀናት ብቻ ነበር። መዲና ሲደርሱ በፍጥነት የሄዱት በመስጂደል ነበዊ ውስጥ ወደሚገኘው አልረውዳ ልዩ የሶላት ስፍራ ነበር፡፡ እዚያ በመሄድም ዱዓ አደረጉ:: ይሁን እንጂ ሕልሙን በተመለከተ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሊያውቁ አልቻሉም፡፡ አማካሪያቸው ጃማሉዲን በሕልማቸው ውስጥ ያዩዋቸው ሁለት ሰዎች ምን ዓይነት እንደሆኑ እንዲነግሩት ሲጠይቃቸው ኑረዲን የሰዎቹን መልክና አለባበስ እንደሚያስታውሱና ቢያገኙዋቸው መለየት እንደሚችሉ ነገሩት፡፡ ጀማሉዲን ሰዎቹን ለመያዝና ሴራቸውን ለማክሸፍ ቆርጠው በመነሳታቸው ፈጣን እርምጃዎችን መውሰድ ጀመሩ፡፡ የመዲና ነዋሪዎች በመስጂዱ ውስጥ ሲሰበሰቡም እንዲህ የሚል ማስታወቂያ አስነገሩ፡፡ 'መሪያችን በሶደቃ ለመስጠት ነይተው ያመጡት ብዙ ሃብት አለ፡፡ ሶደቃውን ለማከፋፈል እንዲመቸን በችግር ውስጥ ያላችሁ ሰዎች ሁሉ እየመጣችሁ ስሞቻችሁን እንድታስመዘግቡ እንጠይቃለን የሚል፡፡ ይህን ማሳሰቢያ እንዳስነገሩ ሰዎች ሶደቃውን ፍለጋ ተንጋግተው መምጣት ሲጀምሩ ኑረዲን በሕልማቸው ውስጥ ያዩዋቸውን ሰዎች ለመለየት ዳር ቆመው እያንዳንዱን ሰው ይቃኙ ነበር። ብዙ ሰዎች መጥተው የድርሻቸውን እያነሱ ቢሄዱም ኑረዲን ተፈላጊዎቹን ሁለት ሰዎች ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻም ከሶደቃው ድርሻውን ያልወሰደ ሰው እንዳለ ሲጠይቁ የሆነ ሰው ·ከሞሮኮ የመጡ ሁለት ሰዎች አሉ፡፡ ሰዎቹ በጣም ሷሊሕ ሰዎች ስለሆኑ ሶደቃውን ለመቀበል አልፈለጉም አላቸው፡፡ ኑረዲን ይህን እንደሰሙ ሁለቱን ሰዎች በአስቸኳይ እንዲያመጧቸው አዘዙ፡፡ ኑረዲን ሁለቱ ሰዎች እፊታቸው እንደቀረቡ ሰዎቹ ነቢዩ ሰዐወ በሕልማቸው ያመለከቷቸው ሰዎች መሆናቸውን በቀላሉ አወቁ። ሰዎቹንም “ለመሆኑ ከየት ነው የመጣችሁት? በማለት ጠየቁ፡፡ እነርሱም የመጣነው ከመግሪብ ነው፣ አመጣጣችን ለሐጅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ዓመት እዚሁ ለማሳለፍ ወስነናል' አሏቸው:: ኑረዲን ሰዎቹ የሆነ ያቀዱት ሴራ መኖሩን ቢጠረጥሩም ምን እንደሆነ በእርግጠኝነት ለመለየት ስላልቻሉ ድብቅ ሴራቸውን ይፋ እንዲያወጡ በማሰብ የተለያዩ ጥያቄዎችን አከታትለው ቢጠይቁም ምንም ፍንጭ ሳያገኙ ቀሩ፡፡ በዚህም የተነሣ ምንም እርምጃ ሊወስዱባቸው አልተቻላቸውም:: ኑረዲን ቀጥለው ያዘዙት ቤታቸው ይፈተሽ የሚል ነበር፡፡ ቤታቸው ሲፈተሽም በቤቱ ውስጥ ካስቀመጡት በርካታ ገንዘብ ውጭ ሊያስጠረጥራቸውና ሊያስወነጅላቸው የሚችል ምንም ነገር ሳይገኝ ቀረ፡፡ ለፍተሻ ወደ ቤታቸው የገባ ሰው አንድ በአንድ መውጣት ሲጀምር ኑረዲንም ምንም ምልክት በማጣታቸው ቤቱን ለቀው ሊወጡ ሆነ: በዚያች ቅፅበት ነበር አላህ የሙስሊሞቹ መሪ አንዳች ነገር አትኩረው እንዲመለከቱ ያደረገው ኑረዲን ወለሉን ሲቃኙ በወለሉ ላይ ከተነጠፉት ጣውላዎች ው አጥብቆ እንዳልያዘ አስተዋሉ፡፡ ይህን እንዳዩ ጐንበስ በማለት ጣውላውን ሲያነሱ የመዲናን ነዋሪዎች ጉድ ያሰኘ ክስተት ተስተዋለ። በወለሉ መሿለኪያ መቆፈሩን ነዋሪዎቹ ግን ይበልጥ የተደናገጡት መሿለኪያው ወዴት እንደሚያመራ ሲረዱ ነበር፨ መሿለኪያውን የቆፈሩት በከተማይቷ ውስጥ በሷሊሕነታቸው ይታወቁ የነበሩት ሁለቱ የሩቅ አገር እንግዶች መሆናቸው ሌላው ግርምታ የፈጠረ ጉዳይ ሆነ፡ እስከዚያን ጊዜ ድረስ ሁለቱ ሞሮኮኣውያን የሚታወቁት በጥልቅ ዒባዳቸውና በላቀ ኢስላማዊ ሥነ-ምግባራቸው ነበር፡፡ እጅግ የተናደዱት መሪ ኑረዲን ሁለቱን ሰዎች መግረፍ ሲጀምሩ ሰዎቹ በርግጥ ከመግሪብ (ሞሮኮ) አንዳልመጡና በመሪያቸው ከፍተኛ ገንዘብ ተከፍሏቸው የተላኩ ክርስቲያኖች መሆናቸውን የመጡትም የነቢዩን አጽም ቆፍረው በማውጣት በድብቅ ወደ አገራቸው ለመውሰድ መሆኑን አመኑ፡፡ ኑረዲን ሁለቱ ሰዎች በሞት እንዲቀጡ አዝዘው የተቆፈረው መተላለፈያም በአስተማማኝ መልኩ በአለት እንዲደፈን አደረጉ፡፡ ሴራውንም እንዳከሸፉ ወደ ሻም (ሶሪያ) ተመለሱ፡፡
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ንጉስ ፈይሰል አሸዋ ላይ በተዘረጋው ምንጣፍ ላይ ተቀምጦ የአሜሪካ ቴፕላይን ካምፓኒ ሃላፊን አስጠራ "አንዲት የነዳጅ ጠብታ ወደ እስራኤል እንዳይላክ" ሲልም አዘዘ። Mahi Mahisho አሜሪካ ትዕዛዙን ጥሳ ለእስራኤል እርዳታ እንደላከች ሲሰማ ከአሜሪካ ጋር የነበረውን የነዳጅ ሽያጭ ውሉን አቋረጠ። በሀገረ አሜሪካ ሰላማዊ ሰልፍ ነገሰ ሰዎች በነዳጅ ማደያዎች ፊት ተሰልፈው ነዳጅ እንጂ እስራኤልን አንፈልግም የሚለውን መፈክር አስተጋቡ። በዚህ ጊዜ ንጉስ ፋይሰል ታዋቂ ንግግሩን አደረገ "ነዳጅ ከቁድስ ክብር አይበልጥብንም። አያቶቻችን በተምርና በወተት ኖረዋል እኛም ወደዛው ህይወት እንመለሳለን" አላህ ይዘንልህ ዛሬስ አረቦች ዛሬስ የአለም ሙስለሞች?? በቀን ይሄን ያህል ንፁሀን ሞቱ ቆጣሪ ሁነናል
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ጎልማሳ አባቱ በህይወት እስካለ የሚወዳትን ሴት አግብቶ መኖር በነፍሱ ላይ እርም አደረገ። ለዘመናት ብቸኝነትን መርጦ አባቱን እየተንከባከበ ለመኖር በመወሰኑ የተደነቁ ምክንያቱን ማወቅ ፈለጉ። ለምን ሲሉም ጠየቁ። "ለሊት ሲተኛ...." በማለት ንግግሩን እንደጀመረ ሳግ ተናነቀውና አለቀሰ "አባቴ ሲተኛ በጎኑ መገላበጥ አይችልም። ከቀኝ ወደ ግራ የማዟዙረው፣ ገላውን አጥቤ ምግብም የማበላው እኔ ነኝ። ሚስት አግብቼ እሷን አቅፌ ስተኛ ባባስ?! ነጥቶ ገርጥቶ፣ ከስቶ ኮስምኖ፣ ጀርባው በሀዘን ጎብጦ፣ ሸክም ጫንቃው ላይ ተደራርቦ ያሳደገኝን አባቴን በዚህ መልኩ ትቼ እንዴት ለአንድ ቀን ከርሱ ርቄ ማደር ይቻለኛል?!" አለ። ሊላሂ ደሩክ ይህ ደግሞ እስር ቤት ነው ቁርአን መኽሉቅ ነው የሚለውን መርህ ያልተቀበሉት ታላቁ ዓሊም የህየል ቡርሙኪ በዘመኑ መንግስት ተቀፍድደው ከነልጃቸው ዘብጥያ ወረዱ። አካላቸው የደከመ በመሆኑ ለሊት በቀዝቃዛ ውሀ ውዱዕ ማድረግ እየከበዳቸው ብርዱም ሰውነታቸውን ለህመም እያጋለጠ ጤና ራቃቸው። ይህን ያስተዋለው ልጅ ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ በመጋባት ውስጥ ተውጦ እየዋለለ በድንገት አንድ መላን ዘየደ። አባት አይናቸው ተከድኖ ረፍት እስኪወስዱ ይጠብቅና ግርግዳውን ተደግፎ ውሀውን በማንቆርቆርያ ይዞ ሆዱ ላይ ይለጥፈዋል። ከሰውነቱ የሚመነጨው ሙቀት ውሀውን ያሞቅለት ዘንድ ለሊቱን ቆሞ ያነጋል። አባት ከዕንቅልፋቸው ሲነቁ "አባቴ ሆይ በዚህ ውዱእ አርጉ" በማለት ማንቆርቆሪያውን ያቀብላቸዋል። በመልካምነታቸው አትገረሙንምን?!! Mahi Mahisho
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ኡጋንዳ 🇺🇬 ተይዟል ለፍቅረኛው ሲል እንደ ሴት * ጡት መያዣ አድርጎ * ሜካብ ተሰርቶ * ፁጉር ተሰርቶ በፍቅረኛው ስም ፈተና ሲፈተን የነበረው ግለሰብ ሙሳ ሴሞጎሮሬ ይባላል:: ኡጋንዳዊ ሲሆን በኡጋንዳ ሀገር የአንድ አውራጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ነው ይህ ምስኪን የህግ ሰው ኢሬኔ ሙቶኒዪ የምትባል የሴት ፍቅረኛ አለችው:: ኢሬኔ በኡጋንዳ የህግ ጥናት ማእከል የህግ ተማሪ ስትሆን ሀምሌ 29 ላይ የማጠቃለያ ፈተና ነበረባት መቼም የዚህ ጾታ መከራ አያልቅም አይደል?🤗😝 ሙሳ ሶሞጎሮሬ :- * ሹሩባ ተሰርቶ * ጡት መያዣ አድርጎ * ቀሚስ ለብሶ * ታኮ ጫማ አድርጎ እና ሜካፕ ተሰርቶ እንደ ሴት ቂን ቂን እያለ ለሴት ፍቅረኛው ፈተና ሊፈተን ይገባል በፈተናው መሀል ግን የሴት ፍቅረኛው ኢሬኔን ጠንቅቆ የሚያውቅ አንድ መምህር (በመልክ ይሁን በሽታ ያወቃት አልታወቀም እስካሁን😝) ጥርጣሬውን ወደ ፍተሻ ሲቀይረው ወንድ ሆኖ ተገኝቷል ወዲያው የኡጋንዳ ፖሊስም ሙሳን ከሴት ወደ ወንድ ቀይሮት በማጭበርበር እና ፎርጂድ ሙከራ ከሶት ፍርድ ቤት ገትሮታል:: Via Zemelak Endrias የዚስ ከፋ 😎😎 🌴🌴🌴
Show all...
......, #ፍቅር ...,       ✍አሚር ሰይድ 🔰አንዲት እህቴ ፍቅር ይዞኛል ግን ፍቅር ምንድን ነዉ ብላ ጠይቃኝ የዛሬ 2አመት በፊት የመለስኩላት ነዉ እናንተ ስለፍቅር ምን ትላላችሁ⁉️❓ ☞ፍቅር ህልም ነዉ ስትነሺ የማታገኚዉ ☞ፍቅር ንፋስ ነዉ ከየት በኩል እንደመጣ የማታየዉ ☞ፍቅር ዉሀ ነዉ ጨብጠሽ ይዘሽ የማታስቀምጪዉ ☞ፍቅር የእሳት እረመጥ ነዉ አንዴ የእሳት ረመጥ በእግርሽ ከረገጥሽዉ እግርሽ እንደመግል ሁኖ ያመረቅዛል በዛ እግርሽ መሬት መንካት አትችይም ሳታነክሽ ብዙ ወር ትቆያለሽ ከዛ በስንት ድካም ይሻልሻል ☞ፍቅር የማያገኙትን ሰዉ በዉንም በህልምም አብሮ እሱ ጋር እየኖሩ አብረዉ ልጅ ሲወልዱ ተከባብረዉ ሲኖሩ የሚያሳይ የህይወት ስዕል ነዉ ...ስዕል ደግሞ እዉነት አይደለም ያዉ ስዕል ነዉ...,ፍቅር የማያገኙትን ሰዉ ልብሽ ላይ ስለሽ ያንን ስዕል እንዳይጠፋብኝ እያሉ የመጨነቅ የመጠበብ ኑሮ ነዉ..ስዕሉ እንዳይጠፋ የመታገል ህይወት ነዉ ☞ፍቅር ተራራ ነዉ ይላሉ ግን ፍቅር ተራራ አይደለም ሜዳ ነዉ ..ግን የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ...ተራራ ስትወጪ ይደክምሻል ግን በግድም ቢሆን ወጥተሽ ትጨርሻለሽ ከተራራዉ ጫፍ ላይ ደርሻለሁ በስንት ድካም ብለሽ  ራስሽን ታደንቂያለሽ ደክመሽም ቢሆንከተራራዉ ጫፍ በመድረስሽ ...ፍቅር ግን የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ሂደሽ ሂደሽ አጨርሽዉም ጫፉ ላይ የማይደረስ ነዉ...ለምን ብትይ ተራራ ወጥተሽ ከጫፍ ትሆኛለሽ...የወጣሽዉን ተራራ ደግሞ መዉረድ አያቅትም ተራራ የሚከብደዉ መዉጣቱ ነዉና ሜዳ ግን ብትሄጅ ብትሄጅ ብትሄጅ አያልቅም....ለምሳሌ ከደሴ አዲስ አበባ 401 km ነዉ ያንን በእግርሽ ሂደሽ ትጨርሽዋለሽ?በጭራሽ አጨርሺዉም ግን ጠንካራ ነኝ ብለሽ ካሰብሽ አያቶቻችን መኪና በሌለበት ዘመን ሂደዋል እኔም በእግሬ እሄዳለሁ ብለሽ ከተሳካልሽ ☺️ አአ  ከሄድሽ😉 ከአአ አሶሳ ሱዳን ድንበር 660 km አለ እሱን በእግርሽ ሂደሽ ትጨርሺዋለሽ?በጭራሽ አሞክሪዉም ...አይታወቅም የሰዉ አቅሙ☺️ ጠንካራ ከሆንሽ ሄድሽ እንበል አሶሳ ደረሽ ምድር ታበቃለች?ምድር ተሂዶ አያልቅም ከሱዳን ጀምሮ ስንት ሀገር አለ...በእግርሽ በመኪና በአየር ሂደሽ የማጨርሺዉ....በእግርሽ ሱዳንን አልፈሽ ብትሄጅ ስትሄጅ ስትሄጅ ዉቅያኖስ ወይ ባህር ታገኛለሽ በእግርሽ ከሞከርሽ ሰምጠሽ ትቀሪያለሽ ...ወደ ጀመርሽበት አትመለሽ ሩቅ ነዉ ባለሽበት ቀባሪ ሳትገኝ ትሞቻለሽ ማለት ነዉ☺️ ፍቅርም ሂደዉ ሂደዉ የማይመለሱበት የቁም ሞት መሞቿ ህይወት ነዉ ፍቅር ተራራ ሳይሆን ሂደሽ ሂደሽ የማጨርሺዉ የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ... እናም ይሄን ረጅም መንገድ ሂደሽ የማጨርሽዉ አለም ...በእግሬ እሄዳለሁ ብለሽ ማሳመን ነዉ ፍቅርም እወጠዋለሁ ብለሽ ሂደሽ የማጨርሽዉን ጉዞ መጀመር ነዉ...ከጀመርሽም ይሄን የማይጨረስ አለም አንድ እርምጃ ሳትረመጅ ሀሳብሽ ተበታትኖ እግርሽ ተሳስሮ ሳትሄጅ ትመለሻለሽ ..,ፍቅር አሰቡበት ሳይደርሱ ወደ ፊት የሆዱ መስሎ በማያቁት መንገድ ወደ ሆላ መመለስ ነዉ.. ግን ወደ ሆላ መመለስሽ የሚገባሽ ቡሀላ ሳትሄጅ ከተመለሽ ቡሀላ ነዉ ☞ፍቅር ካልተሳካ ከህይወት ተስፋ መቁረጥ ነዉ ...ደግሞም ሴት ነሽ ይከብዳል ወንዱ ሌላ ሊኖረዉ ይችላልና ....እሱ ካልተረዳሽ ስቃይ ነዉ ☞ፍቅር ያለዉ አማረኛ ፊልም እና ዘፈን ላይ ነዉ...አማረኛ ፊልም ስናይ ዘፈን ስናዳምጥ ያንን ያየነዉ ያዳመጥነዉ ሙዚቃ ወደ ዉስጣችን ገብቶ ያንን ለማዋሀድ እኔስ የለኝም ወይ? ብለን በአየነዉ ፊልም ሙዚቃ ፍቅርን እየሳልን የምንረበሽበት የሙዚቃዉ የፊልሙ አይነት አፍቃሪ ሳናገኝበት የምንኖርበት የፊልምና የሙዚቃ ኑሮ ነዉ ☞ፍቅር ጥልቀት ያለዉ ክብ ዲንጋይ  ነዉ...ያንን ዲንጋይ ለማዉጣት ብቻሽን ብትቆፍሪም ሰዉ ቢረባረብ የማይወጣ ነዉ...ፍቅርም ጥልቀት ያለዉ ከልብ የማይወጣ ክብ ዲንጋይ ነዉ ☞እኔ የምልሽ ፍቅር ከሚይዝሽ ኮረንቲ ያዝ አርጎ ቢለቅሽ ይሻላል...ለምን ኮረንቲ አስደንግጦ ይተዉሻል ፍቅር ግን ያፈቀርሺዉ የኔ ይሆን በሚል እልክ ....እራስሽን በራስሽ አሳምነሽ የምትኖሪበት ህይወት ነዉ፡፡ ☞ፍቅር ያፈቀሩትን ሰዉ የማያገኙበት ህይወት ነዉ...ትዋጀሻለሽ ግን አብሮ ለመሆን የምትሰቃይበት ኑሮ ነዉ.   የማይረዳሽ ለትዳር የማይሆን ከሆነ የወደድሽዉ አደራ አደራ ፍቅርሽን አፍነሽ አላህ እንዲያነሳልሽ ዱአ አርጊ ካልሆነ እሱ በፍቅር ልብሽ ላይ ይጫወትብሻል ሀራም ያሰራሻል...የሴት ልጅ ፍቅር ከባድ ነዉ ፡እኔ ይሻላል የምለዉ ወንድ ቢያፈቅር ነዉ ወንድ ከወደደ ይታገሳል ተስፋ ቆርጦም ይነሳል...ሴትግን ብታፈቅር ትጎዳለች በተለይ የማይረዳ ለትዳር የማይሆንሽ ከሆነ ✅ ደግሞ ማወቅ ያለብሽ በፍቅር መለየት አለ ምክንያቱን ሳታቂ የኔ ነዉ ያልሽዉ ሊከዳሽ ይችላል.....ወይም በቤተሰብ ወይ በእትህት ወንድም ወይ በተሳሳተ መረጃ ልብ ላይ ያርፍና የሆነ ጊዜ ይቆረፍዳል የዛን ጊዜ ከወዳጅ ከምወጂዉ ትለያለሽ የዛን ጊዜ ማፍቀርሽን ትጠያለሽ ፍቅር ልብሽ ላይ ተቀምጦ ትሰቃያለሽ ከሰዉ በታች ልትሆኝ ትችያለሽ....ከሚወዱት መለየት ከባድ ነዉ እምባስ ይወጣል የልብ እምባ ግን እዛዉ አልቅሶ ይቀራል😔...የማይወጣ ነገር የቀረ ደግሞ ለዉስጥ በሽታ ነዉ መቼም ጤነኛ አትሆኝም.... አሏህ በተከበረ ቁርአኑ እንኳን ከወዳጅ መለያየት ሀዘኑ በጣም ጥልቅ እንደሆነ ይናገራል የአይን ብርሃን እስከማጣት ( وتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَٰٓأَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَٱبْيَضَّتْ عَيْنَاهُ مِنَ ٱلْحُزْنِ فَهُوَ كَظِيمٌۭ ) " ከእነሱም ዘወር አለና ኣ«በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ ፡፡ ዓይኖቹም ከሐዘን (ለቅሶ) የተነሳ ነጡ ፡፡ እርሱም በትካዜ የተሞላ ነው ፡፡" _....የየሱፍ አባት ወደዉ አልቅሰዉ አይናቸዉን ያጡት ነብይን ነዉ..እኛ ግን አላህ ለፈጠረዉ ተራ ሰዉ አልቅሰን አይናችንን ታመን ልባችንን ማድማት የለብንም ሆነም ቀረ ...የሰዉ ልጅ ለራሱ ሳያቅ የራሴ ህይወት ሳይገባኝ  በሰዉ እፈርዳለሁ ... ✔በጥላቻ ድልድይ መረማመድ ቁልቁለት ነው። ✔ፍቅርን በተግባር ማረጋገጥ ዳገት ነው። ✔ስለ በደል ማውራት ተራ ነው። ✔ የተበዳይን እንባ ማበስ ከባድ ነዉ😔። ✔መፍረድ ቀላል ነው። ✔ፍትሀዊ መሆን ምጥ ነው። ✔መለያየት ቀላል ነው። አንድ መሆን ፈተና ነው። ✔ትልልቅ ነገሮችን ማሰብ ቀላል ነው። ትንንሽ ነገሮችን ማድረግ ከባድ ነዉ። ✔በምኞት መኖር ቀላል ነው። እውነትን መቀበል መራር ነው። ✔ተስፋ ማድረግ ቀላል ነው። አማኝ መሆን ፅናት ነው። ብቻ አሏህ ከሁላችንም ጋር ይሁን ከፍቅር የዉሸት ኑሮ ይሰዉረን እናም እኔ የምለዉ ልብን አትዉደድ አይባልም ግን መጀመሪያ ለይል ተነስተሽ አልቅሰሽ ዱአ አርጊበት ይቅርታ ግን እኔ ለፍቅር ጥሩ አመለካከት የለኝም😊 እኔ ለአንቺ የምረዳሽ ቢኖር ከፍቅር ተስፋ ማስቆሮጥ....የምወጂዉን እንደማታገቢ ተስፋ ማስቆረጥ ...ፍቅር በሌለበት አለም አፍቃሪ እንዳትሆኝ አእምሮሽን እንድትጠርጥሪ ማድረግ...የፍቅር ህይወትሽ እንዲጨልም ማረግ ብቻ ነዉ😂 ለፍቅር ጥሩ አመለካከት ያላቸዉ በፍቅር ያተረፉ ካሉ እነሱን ብትጠይቂ ጥሩ ነዉ ባይ ነኝ☺️ ⚠️ Warning ፍቅርን በተግባር ማረጋገጥ ዳገት ነዉ መለያየየት ቀላል ነዉ አንድ መሆን ግን ፈተና ነዉ ጨርሻለሁ ከአጠፋሁ አዉፍ በይ 😊 እርስዎ ስለፍቅር ምን ይላሉ
Show all...
Show all...
Show all...
......, #ፍቅር ...,       ✍አሚር ሰይድ የሆነ አንዲት እህቴ ፍቅር ይዞኛል ግን ፍቅር ምንድን ነዉ ብላ ጠይቃኝ የዛሬ 2አመት በፊት የመለስኩላት ነዉ እናንተ ስለፍቅር ምን ትላላችሁ⁉️❓ ☞ፍቅር ህልም ነዉ ስትነሺ የማታገኚዉ ☞ፍቅር ንፋስ ነዉ ከየት በኩል እንደመጣ የማታየዉ ☞ፍቅር ዉሀ ነዉ ጨብጠሽ ይዘሽ የማታስቀምጪዉ ☞ፍቅር የእሳት እረመጥ ነዉ አንዴ የእሳት ረመጥ በእግርሽ ከረገጥሽዉ እግርሽ እንደመግል ሁኖ ያመረቅዛል በዛ እግርሽ መሬት መንካት አትችይም ሳታነክሽ ብዙ ወር ትቆያለሽ ከዛ በስንት ድካም ይሻልሻል ☞ፍቅር የማያገኙትን ሰዉ በዉንም በህልምም አብሮ እሱ ጋር እየኖሩ አብረዉ ልጅ ሲወልዱ ተከባብረዉ ሲኖሩ የሚያሳይ የህይወት ስዕል ነዉ ...ስዕል ደግሞ እዉነት አይደለም ያዉ ስዕል ነዉ...,ፍቅር የማያገኙትን ሰዉ ልብሽ ላይ ስለሽ ያንን ስዕል እንዳይጠፋብኝ እያሉ የመጨነቅ የመጠበብ ኑሮ ነዉ..ስዕሉ እንዳይጠፋ የመታገል ህይወት ነዉ ☞ፍቅር ተራራ ነዉ ይላሉ ግን ፍቅር ተራራ አይደለም ሜዳ ነዉ ..ግን የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ...ተራራ ስትወጪ ይደክምሻል ግን በግድም ቢሆን ወጥተሽ ትጨርሻለሽ ከተራራዉ ጫፍ ላይ ደርሻለሁ በስንት ድካም ብለሽ  ራስሽን ታደንቂያለሽ ደክመሽም ቢሆንከተራራዉ ጫፍ በመድረስሽ ...ፍቅር ግን የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ሂደሽ ሂደሽ አጨርሽዉም ጫፉ ላይ የማይደረስ ነዉ...ለምን ብትይ ተራራ ወጥተሽ ከጫፍ ትሆኛለሽ...የወጣሽዉን ተራራ ደግሞ መዉረድ አያቅትም ተራራ የሚከብደዉ መዉጣቱ ነዉና ሜዳ ግን ብትሄጅ ብትሄጅ ብትሄጅ አያልቅም....ለምሳሌ ከደሴ አዲስ አበባ 401 km ነዉ ያንን በእግርሽ ሂደሽ ትጨርሽዋለሽ?በጭራሽ አጨርሺዉም ግን ጠንካራ ነኝ ብለሽ ካሰብሽ አያቶቻችን መኪና በሌለበት ዘመን ሂደዋል እኔም በእግሬ እሄዳለሁ ብለሽ ከተሳካልሽ ☺️ አአ  ከሄድሽ😉 ከአአ አሶሳ ሱዳን ድንበር 660 km አለ እሱን በእግርሽ ሂደሽ ትጨርሺዋለሽ?በጭራሽ አሞክሪዉም ...አይታወቅም የሰዉ አቅሙ☺️ ጠንካራ ከሆንሽ ሄድሽ እንበል አሶሳ ደረሽ ምድር ታበቃለች?ምድር ተሂዶ አያልቅም ከሱዳን ጀምሮ ስንት ሀገር አለ...በእግርሽ በመኪና በአየር ሂደሽ የማጨርሺዉ....በእግርሽ ሱዳንን አልፈሽ ብትሄጅ ስትሄጅ ስትሄጅ ዉቅያኖስ ወይ ባህር ታገኛለሽ በእግርሽ ከሞከርሽ ሰምጠሽ ትቀሪያለሽ ...ወደ ጀመርሽበት አትመለሽ ሩቅ ነዉ ባለሽበት ቀባሪ ሳትገኝ ትሞቻለሽ ማለት ነዉ☺️ ፍቅርም ሂደዉ ሂደዉ የማይመለሱበት የቁም ሞት መሞቿ ህይወት ነዉ ፍቅር ተራራ ሳይሆን ሂደሽ ሂደሽ የማጨርሺዉ የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ... እናም ይሄን ረጅም መንገድ ሂደሽ የማጨርሽዉ አለም ...በእግሬ እሄዳለሁ ብለሽ ማሳመን ነዉ ፍቅርም እወጠዋለሁ ብለሽ ሂደሽ የማጨርሽዉን ጉዞ መጀመር ነዉ...ከጀመርሽም ይሄን የማይጨረስ አለም አንድ እርምጃ ሳትረመጅ ሀሳብሽ ተበታትኖ እግርሽ ተሳስሮ ሳትሄጅ ትመለሻለሽ ..,ፍቅር አሰቡበት ሳይደርሱ ወደ ፊት የሆዱ መስሎ በማያቁት መንገድ ወደ ሆላ መመለስ ነዉ.. ግን ወደ ሆላ መመለስሽ የሚገባሽ ቡሀላ ሳትሄጅ ከተመለሽ ቡሀላ ነዉ ☞ፍቅር ካልተሳካ ከህይወት ተስፋ መቁረጥ ነዉ ...ደግሞም ሴት ነሽ ይከብዳል ወንዱ ሌላ ሊኖረዉ ይችላልና ....እሱ ካልተረዳሽ ስቃይ ነዉ ☞ፍቅር ያለዉ አማረኛ ፊልም እና ዘፈን ላይ ነዉ...አማረኛ ፊልም ስናይ ዘፈን ስናዳምጥ ያንን ያየነዉ ያዳመጥነዉ ሙዚቃ ወደ ዉስጣችን ገብቶ ያንን ለማዋሀድ እኔስ የለኝም ወይ? ብለን በአየነዉ ፊልም ሙዚቃ ፍቅርን እየሳልን የምንረበሽበት የሙዚቃዉ የፊልሙ አይነት አፍቃሪ ሳናገኝበት የምንኖርበት የፊልምና የሙዚቃ ኑሮ ነዉ ☞ፍቅር ጥልቀት ያለዉ ክብ ዲንጋይ  ነዉ...ያንን ዲንጋይ ለማዉጣት ብቻሽን ብትቆፍሪም ሰዉ ቢረባረብ የማይወጣ ነዉ...ፍቅርም ጥልቀት ያለዉ ከልብ የማይወጣ ክብ ዲንጋይ ነዉ ☞እኔ የምልሽ ፍቅር ከሚይዝሽ ኮረንቲ ያዝ አርጎ ቢለቅሽ ይሻላል...ለምን ኮረንቲ አስደንግጦ ይተዉሻል ፍቅር ግን ያፈቀርሺዉ የኔ ይሆን በሚል እልክ ....እራስሽን በራስሽ አሳምነሽ የምትኖሪበት ህይወት ነዉ፡፡ ☞ፍቅር ያፈቀሩትን ሰዉ የማያገኙበት ህይወት ነዉ...ትዋጀሻለሽ ግን አብሮ ለመሆን የምትሰቃይበት ኑሮ ነዉ.   የማይረዳሽ ለትዳር የማይሆን ከሆነ የወደድሽዉ አደራ አደራ ፍቅርሽን አፍነሽ አላህ እንዲያነሳልሽ ዱአ አርጊ ካልሆነ እሱ በፍቅር ልብሽ ላይ ይጫወትብሻል ሀራም ያሰራሻል...የሴት ልጅ ፍቅር ከባድ ነዉ ፡እኔ ይሻላል የምለዉ ወንድ ቢያፈቅር ነዉ ወንድ ከወደደ ይታገሳል ተስፋ ቆርጦም ይነሳል...ሴትግን ብታፈቅር ትጎዳለች በተለይ የማይረዳ ለትዳር የማይሆንሽ ከሆነ ✅ ደግሞ ማወቅ ያለብሽ በፍቅር መለየት አለ ምክንያቱን ሳታቂ የኔ ነዉ ያልሽዉ ሊከዳሽ ይችላል.....ወይም በቤተሰብ ወይ በእትህት ወንድም ወይ በተሳሳተ መረጃ ልብ ላይ ያርፍና የሆነ ጊዜ ይቆረፍዳል የዛን ጊዜ ከወዳጅ ከምወጂዉ ትለያለሽ የዛን ጊዜ ማፍቀርሽን ትጠያለሽ ፍቅር ልብሽ ላይ ተቀምጦ ትሰቃያለሽ ከሰዉ በታች ልትሆኝ ትችያለሽ....ከሚወዱት መለየት ከባድ ነዉ እምባስ ይወጣል የልብ እምባ ግን እዛዉ አልቅሶ ይቀራል😔...የማይወጣ ነገር የቀረ ደግሞ ለዉስጥ በሽታ ነዉ መቼም ጤነኛ አትሆኝም.... አሏህ በተከበረ ቁርአኑ እንኳን ከወዳጅ መለያየት ሀዘኑ በጣም ጥልቅ እንደሆነ ይናገራል የአይን ብርሃን እስከማጣት ( وتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَٰٓأَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَٱبْيَضَّتْ عَيْنَاهُ مِنَ ٱلْحُزْنِ فَهُوَ كَظِيمٌۭ ) " ከእነሱም ዘወር አለና ኣ«በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ ፡፡ ዓይኖቹም ከሐዘን (ለቅሶ) የተነሳ ነጡ ፡፡ እርሱም በትካዜ የተሞላ ነው ፡፡" _....የየሱፍ አባት ወደዉ አልቅሰዉ አይናቸዉን ያጡት ነብይን ነዉ..እኛ ግን አላህ ለፈጠረዉ ተራ ሰዉ አልቅሰን አይናችንን ታመን ልባችንን ማድማት የለብንም ሆነም ቀረ ...የሰዉ ልጅ ለራሱ ሳያቅ የራሴ ህይወት ሳይገባኝ  በሰዉ እፈርዳለሁ ... ✔በጥላቻ ድልድይ መረማመድ ቁልቁለት ነው። ✔ፍቅርን በተግባር ማረጋገጥ ዳገት ነው። ✔ስለ በደል ማውራት ተራ ነው። ✔ የተበዳይን እንባ ማበስ ከባድ ነዉ😔። ✔መፍረድ ቀላል ነው። ✔ፍትሀዊ መሆን ምጥ ነው። ✔መለያየት ቀላል ነው። አንድ መሆን ፈተና ነው። ✔ትልልቅ ነገሮችን ማሰብ ቀላል ነው። ትንንሽ ነገሮችን ማድረግ ከባድ ነዉ። ✔በምኞት መኖር ቀላል ነው። እውነትን መቀበል መራር ነው። ✔ተስፋ ማድረግ ቀላል ነው። አማኝ መሆን ፅናት ነው። ብቻ አሏህ ከሁላችንም ጋር ይሁን ከፍቅር የዉሸት ኑሮ ይሰዉረን እናም እኔ የምለዉ ልብን አትዉደድ አይባልም ግን መጀመሪያ ለይል ተነስተሽ አልቅሰሽ ዱአ አርጊበት ይቅርታ ግን እኔ ለፍቅር ጥሩ አመለካከት የለኝም😊 እኔ ለአንቺ የምረዳሽ ቢኖር ከፍቅር ተስፋ ማስቆሮጥ....የምወጂዉን እንደማታገቢ ተስፋ ማስቆረጥ ...ፍቅር በሌለበት አለም አፍቃሪ እንዳትሆኝ አእምሮሽን እንድትጠርጥሪ ማድረግ...የፍቅር ህይወትሽ እንዲጨልም ማረግ ብቻ ነዉ😂 ለፍቅር ጥሩ አመለካከት ያላቸዉ በፍቅር ያተረፉ ካሉ እነሱን ብትጠይቂ ጥሩ ነዉ ባይ ነኝ☺️ ⚠️ Warning ፍቅርን በተግባር ማረጋገጥ ዳገት ነዉ መለያየየት ቀላል ነዉ አንድ መሆን ግን ፈተና ነዉ ጨርሻለሁ ከአጠፋሁ አዉፍ በይ 😊 እርስዎ ስለፍቅር ምን ይላሉ
Show all...
00:19
Video unavailableShow in Telegram
Repost from Islam mindset
"የአላህ ደጋግ ባሮች በኢባዳ ላይ ሆነው ስለ ወንጀላቸው እያስታወሱ ያለቅሳሉ፤ አንተ በወንጀል ላይ ሆነህ ትስቃለህ!" ኢብኑል ጀውዚይ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ሀያሉ የጂንጊስ ኻን ጦር አለምን ሊቆጣጠር ከምስራቅ የሞንጎሊያ ኦቶኬን ተራሮች ተነስቶ ወደ ምእራብ እየገሰገሰ ነው ። እናም በርካታ ከተሞችን ተቆጣጥሮ ከውቧ የኢማም አልቡኻሪ ከተማ ቡኻራ ደጅ ደርሷል ። ጂንጊስ ኻን ከቡኻራ ከፍተኛ መከላከል እንደሚገጥመው ስለገመተ አንድ መላ ዘየደ - የከተማዋን ህ ለሁለት መክፈል ! ስለሆነም ለከተማዋ ህዝብ እንደዚህ የሚል ደብዳቤ ላከ " ከኛ ጋር የምትሰለፉ ከሆነ እናንተ ነፃ ናችሁ " የሚል ። በዚህ ጊዜ የከተማዋ ህዝብ ለሁለት ተሰነጠቀ ግማሹ ከጂንጊስ ኻን ጎን እንሰለፍ ሲል ግማሹ እርሱን እንዋጋለን እንጅ አንሰለፍም አለ ። የጅንጊስ ኻን እቅድ የመጀመሪያ ግቡን መታ ። በመቀጠል ጂንጊስ ከእርሱ ጎን እንሰለፋለን ላሉት ሌላ ደብዳቤ ላከ " ከእኛ ጋር ሆናችሁ እምቢ ያሉትን የምትዋጉ ከሆነ ከተማዋን ለናንተ አስረክባችሗለሁ " አላችሁ ። እነርሱም " ታድያ ምን ገዶን " በማለት የገዛ ወንድሞቻቼውን ተጋደሉና አሸነፏቸው ። በዚህ ጊዜ ጅንጊስ ኻን ለጦሩ እነዚህን ከነርሱ ጋር የተሰለፉትን እንዲገድሉ አዘዘ ። ለምን ? ተብሎ ሲጠየቅም " እነዚህ ህዝቦች ጥሩ ሆነው በነበሩ ለእኛ ለማያውቁን ህዝቦች ብለው የገዛ ወገኖቻቼውን ባልተጋደሉ ነበረ ስለዚህ ግደሏቸው " አለና አስጨፈጨፋቸው ። ቡኻራም በቀላሉ ካለብዙ መስዋዕትነት በእጁ ገባች ። እዚህ ጋር ዋናው ትምህርት ምን መሰላችሁ ዛሬ አንዱን ከድቶ ካንተ ጋር የተሰለፈ ነገ አንተንም ይከዳሀል ! አንዴ የከዳ ሁሌም ይከዳልና ! እናም በህይወታችሁ ውስጥ የሆነን አካል ሲከዳን ያያችሁትን ሰው በፍፁም በጭራሽ እንዳታቀርቡት ለዚህ ለክ*ህደቱ ሚሊዮን ምክንያት ቢደረድር እንኳ ! #Seid_Mohammed_Alhabeshiy
Show all...