cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍሬ-ሐይማኖት

ተዋህዶ ሐይማኖቴ የጥንት ነሽ የእናት አባቴ ሰላም ለአንቺ ይሁን ቤተ-ክርስቲያን በደሙ ያፀናሽ ኢየሱስ መድህን ➕➕➕

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
966Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር) የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!! †† † † †† ለአባ ሕርያቆስ ፤ ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለአባ ይስሀቅ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!! †† † † †† ከዋክብት የሚያመሰግኑት በስማቸውም የሚጠራቸው: የፀጋው ብዛት የማይታወቅ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!! †† † † †† ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር
Show all...
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። (አብ) የእግዚአብሔር መንፈስ በውኃ ላይ ይረብብ ነበር። (መንፈስ ቅዱስ) ከዚያም እግዚአብሔር ብርሃን ይኹን አለ። (እግዚአብሔር ቃል ተናግሮ ብርሃን ይሁን አለ) “ቃል” ወልድ ነው። ዘፍጥረት [1:1] - - - - - - በዘፍጥረት መግቢያ ላይ ያለችውን ጥቅስ እንዲሁ ከላይ አንብበን ካለፍናት ይህ ኩሉ ሚሥጢር ያልፈናል ማለት ነው። ይህች ጥቅስ ሚሥጢረ ሥላሴን በሚገባ ያስረዳናል። - - - አንድም ስለ ባቢሎን ሰዎች የሚናገረው ምዕራፍ “ኑ እንውረድ ቋንቋቸውንም እንደባልቀው” እያለ ሦስትነትንና አንድነትን ያስረዳል። ዘፍጥረት [11:7] - - - አንድም አበ ብዙሐን አብርሐም የተናገራቸው በዘፍጥረት 18 ሙሉውን የሥላሴን ሚሥጢር የሚያስረዳ አይደለምን? ፤ በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት። ፤ ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፥ እንዲህም አለ። ፤ አቤቱ፥ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ፥ እግራችሁን ታጠቡ፥ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፤ ፤ ቍራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፥ ልባችሁንም ደግፋ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ፤ ስለዚህ ወደ ባሪያችሁ መጥታችኋልና። እነርሱም። እንዳልህ አድርግ አሉት። ፤ አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ገባና። ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፥ ለውሺውም፥ እንጎቻም አድርጊ አላት። ፤ አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፥ እጅግ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴናው ሰጠው፥ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኰለ። ፤ እርጎና ወተትም ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፥ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ነበር፥ እነርሱም በሉ። ፤ እነርሱም። ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? አሉት። እርሱም። በድንኳኑ ውስጥ ናት አላቸው። ፤ እርሱም። የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች አለ። ሣራም በድንኳን ደጃፍ በስተ ኋላው ሳለች ይህንን ሰማች። ፤ አብርሃምና ሣራም በዕድሜአቸው ሸምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር፤ በሴቶች የሚሆነውም ልማድ ከሣራ ተቋርጦ ነበር። ፤ ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች። ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም ፈጽሞ ሸምግሎአል። ፤ እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው። ካረጀሁ በኋላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች? ፤ በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገኛለች። ፤ ሣራም ስለ ፈራች። አልሳቅሁም ስትል ካደች። እርሱም። አይደለም፥ ሳቅሽ እንጂ አላት። ፤ ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶም አቀኑ፤ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ። ፤ እግዚአብሔርም አለ። እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለሁን? (ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 18:17) - - - - - - - አንድም እግዚአብሔር እና መንፈሱ ልከውኛል የሚለው አብንና መንፈስ ቅዱስን አይደለምን? የተላከውስ ወልድ አይደለምን? የእግዚአብሔር መንፈስ ልኮኛል ብሎ አንድ አድርጎ መናገር ሲቻል እግዚአብሔር እና መንፈሱ ብሎ የተናገረው ሚሥጢረ ሥላሴን ሲያስረዳን አይደለምን። ኢሳይያስ [48:16] - - - - - - - አንድም ሚሢጢረ ሥጋዌን ያበሰረ ቅ/ገብርኤል ምን እንዳለ አልሰማንምን። አብሳሬ ድንግል ቅ/ገብርኤል ለእመቤታችን እንዲህ አላት። + የልዑል ኃይል ያጸናሻል (አብ) የእግዚአብሔር መንፈስ ያድርብሻል (መንፈስ ቅዱስ) የምትወልጂውም የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። (ወልድ) - - - አንድም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቁ አላቸው እንጂ በእነዚህ “ስሞች” አጥምቁ አላላቸውም። ይህ አንድነት ሦስትነትን አያሳየንምን። - - - አንድም መንፈስ ቅዱስን የካደ በዚህም ሆነ በወዲያኛው ዓለም ይቅር አይባልም። ማቴዎስ [12:32] ይለናል። አንድም የእግዚአብሔርን ስም የሚሰድብ ማንኛውም ሰው ይገደል የተባለውን አላነበብንምን። ዘሌዋውያን [24:16] - - - - - - - በአትክልት አቅራቢያ ካላችሁ እስኪ ከአጠገባችሁ ያለውን ዛፍ እዩ። ሥር ፤ ግንድ እና ፍሬ አለው። + የዛፉን ሥር ባናየውም ሥሩ እንዳለ ግን እናውቃለን። ሥሩ በግንዱ ይታወቃልና። ሥሩ እንዳለ በፍሬው ይታወቃልና። + የዛፉ ሥር የአብ ምሳሌ ነው። ግንዱ የወልድ ምሳሌ ነው። ፍሬው የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው። + በግንዱ ሥሩን አወቅነው። በወልድ አብን አውቀወናልና። በፍሬው ሥሩን አወቅነው። በመንፈስ ቅዱስ አብን አውቀነዋልና። + + + + + + + በስም ሦስት እንደኾኑ በኣካልም ሦስት ናቸው፡፡ ለአብ ፈጽሞ አካል አለው፡፡ለወልድም ፈጽሞ አካል አለው፡፡ ለመንፈስ ቅዱስም ፈጽሞ አካል አለው፡፡ አካሉ ግን የማይመረመር ምሉዕ ስፍሕ ረቂቅ ነው፡፡ እርሱ ራሱ ቢያውቀው እንጂ ሌላ ኣያውቀውም ፡፡ ፍጥረት ኹሉ በሱ ፊት በቅጠል ላይ እንዳረፈች ጠልና እንደወርቅ ሚዛን ማቅኛ ነው ብሎ ኢሳያስ በትንቢቱ ላይ እንደተናገረ፡፡ረቂቅም እንደኾኑ ኤጲፋንዮስ ስፋሕ ረቂቅ ብሏል፡፡ በስም ሦስት ብቻ ሳይኾኑ በገጽ ሦስት ናቸው ብላም በቅዱሳት መጽሓፍት አስረጂነት ቅድስት ቤተክርስቲያን እንዲ በማለት ትመሠክራለች- በአካል ሦስት እንደኾኑ በገጽም ሦስት ናቸው ለኣብ ፍጹም ገጽአለው፡፡ ለወልድም ፍጹም ገጽ አለው፡፡ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም ገጽ አለው፡፡ አይኹድና ሰባልዮስ ግን አንድ ገጽ ይላሉ፤ እንዲኽም ቢሉ፤'አዳም ኮነ ከመ አሐዱ እምኔነ- እነኾ አዳም ከኛ እንደ አንዱ ኾነ'አሉ ብሎ መጽሐፍ ይመሠክርላቸዋልና ይረታሉ፡፡ ዘፍ. 3÷22ለአብ ፍጹም መልክ አለው ለወልድም ፍጹም መልክ አለው ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም መልክ አለው፡፡ ለመለኮት ሦስት አካል ሦስት ገጽ ሦስት መልክ እንዳለው የተነገረው ኹሉ እናምናለን እንዳለ አትናቴዎስ አንዳንድ ሰዎች ግን ለሥላሴ መልክ የላቸውም ይላሉ፡፡ ምነው ቢሏቸው ኹሉን ሊያዩ ዓይን አላቸው ይላሉ÷ኹሉን ቢሰሙ ጆሮ አላቸው÷በምልዓት ኹነው ቢታዩ ገጽ አላቸው÷ በኹሉ ሊገኙ እግር አላቸው ÷ኹሉን ቢይዙ እጅ አላቸው ተባሉ እንጂ ይኽ ኹሉ የላቸውም ይላሉ እነሱ እንዲህ ቢሉ መጻሕፍት ይመሰክራልና ከሀዲዎች እንደሚሉት አይደለም፡፡ + -አፍንጫ እንዳላቸው 'የአቤልን መስዋዕት አሸተተ' ብሏል -አፍ እንዳላቸው 'እግዚአብሔር ባፉ ጠርቶ ወዲህ ቅረብ አለኝ' ብሏል ኢሳያስም እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረ ብሏል -ዓይን እንዳላቸው 'የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ወዳጆቹ ነው'ብሏል መዝ.33÷15 -ጆሮ እንዳላቸው' ጆሮውም ወደ ልመናቸው ነው'ብሏል መዝ.33÷15 -ፊት እንዳላቸው 'የእግዚአብሔር ፊት ወደሚሠሩት ሰዎች ነው'ብሏል መዝ.33 ÷16 -እግር እንዳላቸው 'የጌታችን የአምላካችን የፈጣሪያችን እግር በቆመበት እንሰግዳለን'ብሏል መዝ.131÷7 -እጅ እንዳላቸው 'እጆችህም ፈጠሩን'ብሏል መዝ.118÷73 - አባ ሕርያቆስም 'ለጴጥሮስ እንዳሳየው ኹሉ በእጁ የተያዘ ነው'ብሏል ኢሳያስም 'ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሮቼ መመላለሻ ናት'ብሏል ኢሳ.86 ÷1 ሐዋ. 7÷49 በዚኽ ኹሉ ሦስትነታቸው ታወቀ ተረዳ - - - + + + + + + + ምንጭ: 81 አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ 21 21 21 ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አይችሏትም ቤተክርስቲያን አትታደስም! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰ
Show all...
ሔር >>>
Show all...
bandsmbratva 25: ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ መስከረም ፲፰ (18) ❖ ✞✞✞ እንኩዋን ለአበው #ቅዱሳን_ኤዎስጣቴዎስ_አኖሬዎስና_ማር_ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +"+ #አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ_ረባን +"+ =>ሐዋርያዊው ጻድቅ ኢትዮዽያዊ (ኤርትራዊ) ሲሆኑ በዓለም ደረጃ የሚታወቅ አገልግሎት ያላቸው አባት ናቸው:: በመካከለኛው ዘመን የኢትዮዽያ ታሪክ የኤወስጣቴዎስንና የተክለ ሃይማኖትን ያህል ስሙ የጐላ ጻድቅ አይገኝም:: +ጻድቁ በ1265 ዓ/ም አካባቢ እንደ ተወለዱ ሲታመን ወላጆቻቸው #ክርስቶስ_ሞዐ እና #ስነ_ሕይወት ይባላሉ:: የጻድቁ የመጀመሪያ ስም #ማዕቀበ_እግዚእ (ለጌታ የተጠበቀ) ነው:: ኤዎስጣቴዎስ የተባሉ በሁዋላ ነው:: +ገና ከልጅነታቸው መንፈሰ እግዚአብሔር አድሮባቸዋልና ለዚህ ዓለም ግድ አልነበራቸውም:: ከመምሕር ዘንድ ገብተው: ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምረው: ዲቁናን ተቀብለው ያገለግሉ ገቡ:: በዲቁና አገልግሎታቸው ስሉጥ በመሆናቸውም የዘመኑ አበው 'ዳግማዊ እስጢፋኖስ' እያሉ ይጠሯቸው ነበር:: +ከዚያ በወጣትነት እድሜአቸው ምናኔን መርጠው: ጾምና ጸሎትን ከስግደት ጋር አዘወተሩ:: እንዲህ ባለ ሕይወት ሳሉ አንድ ቀን ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ዘንድ መጣ:: +በዘባነ ኪሩብ: በግርማው ቢያዩት ደነገጡ:: ጌታ ግን "ወዳጄ ኤዎስጣቴዎስ! ገና ከእናትህ ማሕጸን መርጬሃለሁ:: ከኢትዮዽያ እስከ አርማንያም ሐዋርያ ትሆን ዘንድ ሹሜሃለሁ:: 'ዘኪያከ ሰምዐ: ኪያየ ሰምዐ . . . አንተን የሰማ እኔን ሰማ: አንተን እንቢ ያለ እኔን እንቢ አለ" ብሏቸው: ባርኩዋቸው ዐረገ:: +ጻድቁ ፈጣሪያቸውን ስለ ስጦታው እያመሰገኑ ቅስናን ተቀብለው ስብከትን ጀመሩ:: ስም አጠራራቸውም ፈጥኖ በሃገሪቱ ተሰማ:: በየቦታው እየዞሩ ያላመነውን አሳምነው እያጠመቁ: ያመነውን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እያጸኑ: ሕይወተ ገዳምን እያስፋፉ ኖሩ:: +አሁን ኤርትራ ውስጥ የሚገኘውንና እርሳቸው የመሠረቱትን ገዳም ጨምሮ ለገዳማዊ ሕይወት መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርገዋል:: በገዳማቸውም አባ አብሳዲን ጨምሮ በርካታ አርድእትን አስተምረዋል: አፍርተዋል:: +አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በተለይ የሚታወቁት #ቀዳሚት_ሰንበት እንዳትናቅ (እንድትከበር) ባደረጉት ጥረት ነው:: ደግሞም ተሳክቶላቸዋል:: ቅርብ ጊዜ ከምናየው የድፍረት ሥራ በቀር በሃገራችን 2ቱም ሰንበቶች ክቡር ናቸው:: +አቡነ ኤዎስጣቴዎስ 2 ጊዜ በእግራቸው ተጉዘዋል:: መሔዳቸው ግን ለመሳለም ብቻ አይደለም:: ይልቁኑ የወንጌል ዘርን እየዘሩ: ፍሬውንም እየለቀሙ እንጂ:: እርሳቸው መቼም ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን ቸል አይሉምና:: +በመጨረሻ ሕይወታቸውም በገዳማቸው ላይ ደቀ መዝሙራቸውን አባ አብሳዲን ሹመው ለአዲስ ጉዞ ተነሱ:: እኩሎች ልጆቻቸውን በገዳማቸው ትተው እኩሎችን አስከትለው ጉዞ ወደ አርማንያ ተደረገ:: +በመንገድም ወደ ባሕረ #ኢያሪኮ ሲደርሱ የሚሻገሩበት መርከብ አጡ:: ድንቅ አባት ናቸውና በእምነት አጽፋቸውን (ኩታቸውን) አውልቀው ባሕሩ ላይ ጣሉት:: በላዩ ላይም በትእምርተ መስቀል አማትበው ተቀመጡበት:: +ደቀ መዛሙርቶቻቸውም ባሕሩ ላይ በተነጠፈው ኩታ ላይ ከበው ተቀመጡ:: ከሰማይም ጌታችን ወርዶ በመካከላቸው ቆመ:: #ሚካኤል በቀኝ #ገብርኤልም በግራ ቆሙ:: ጻድቁ ደግሞ ልጆቻቸውን ያስተምሯቸው: ይተረጉሙላቸው ገቡ:: +በመካከል ግን አንዱ (የማነ ብርሃን ይሉታል በቅኔ ቤት) በመጠራጠሩ እርሱ የተቀመጠባት ብቻ ተቀዳ ሰጠመ:: በሁዋላ ግን ጻድቁ ተመልሰው አውጥተው: ከሞት አስነስተውታል:: በዚህም ምክንያት 'ዘአደወ ባሕረ-ማዕበልን የተሻገረ' ይባላሉ:: +አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በአርማንያ ለዘመናት ሰብከው: ሕይወተ ገዳምን አስፋፍተው: ብዙ ተአምራትን ሠርተው: በተወለዱ በ80 ዓመታቸው: በ1345 ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: በብዙ ዝማሬ በመቅደሰ #መርምሕናም ተቀብረዋል:: ዛሬ #በኢትዮዽያ: #ኤርትራ: #ግብጽና #አርማንያ ይከብራሉ:: +"+ #አቡነ_አኖሬዎስ_ጻድቅ +"+ =>እኒህ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ 'ታላቁ አኖሬዎስ' ይባላሉ:: በዚህ ስም ከሚጠሩ አባቶች ዋነኛው እኒህ ናቸው:: ተወልደው ያደጉት #ሙገር አካባቢ ሲሆን ዘመኑም 14ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ወላጆቻቸውም #ሰላማ እና #ክርስቶስ_ዘመዳ ይባላሉ:: +ጻድቁ ከአቡነ #ተክለ_ሃይማኖት ደቀ መዛሙርት አንዱ ናቸው:: በወንጌል ትምሕርት ከመሞላታቸው ባሻገር ፍጹም መናኝ ስለ ነበሩ እጅግ ደፋር ነበሩ:: የትኛውንም ስሕተት ፊት ለፊት ይናገሩም ነበር:: +አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲያርፉ ጌታ "በአንተ ፈንታ አኖሬዎስ ቀሪ ጣዖት አምልኮን ያጠፋል" ብሎ ነግሯቸው ነበር:: ይኸውም አልቀረ ጻድቁ ከ12ቱ ንቡራነ እድ እንደ አንዱ በተመረጡ ጊዜ በደበቡ የሃገራችን አካባቢ ክርስትናን አስፋፍተዋል:: +#ደብረ_ጽጋጋ ገዳምንም የመሠረቱ እርሳቸው ናቸው:: ዛሬ '#ኑራ_ሑሴን' እየተባለ ታሪኩ ጠልሽቶ የሚነገርለት ዋሻ የጻድቁ በዓት ነው:: አቡነ አኖሬዎስ 2ቱን ነገሥታት (#ዓምደ_ጽዮንንና #ሰይፈ_አርእድን) በመገሰጻቸው ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል:: ጻድቁ ብዙ ፍሬ አፍርተው በዚህ ቀን ዐርፈዋል:: +"+ #ማር_ያዕቆብ_ግብጻዊ +"+ =>በግብጽ ገዳማት ውስጥ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ተነስተው ካበሩ ቅዱሳን አንዱ ማር ያዕቆብ ነው:: ቅዱሱ ከተባረከ ቤተሰብ ተወልዶ: በሥርዓቱ አድጐ ገና በልጅነቱ ከመምሕሩ ጋር መንኗል:: ከገድሉ ጽናት የተነሳ ሰይጣን በግልጽ ይፈታተነው ነበር:: +በተለይ ለ7 ዓመታት ያህል ይደበድበው: መሬት ላይ ይጐትተው: በጥፊ ይመታው ነበር:: እርሱ ግን በጸሎቱ መብረቅ አውርዶ አባርሮታል:: በበርሃው ምንም የሚበላ ነገር ባለ መኖሩ የዱር እንስሳትን ወተት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ይጠጣ ነበር:: +ቅዱሱ ሰማዕት ለመሆን ሞክሮም ነበር:: ማር ያዕቆብ ገድሉና ተአምራቱ እጅግ ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ስሙ ከፍ ከፍ ብሏል:: እስኪ ጊዜውና እድሉ ካለዎት #መጽሐፈ_ስንክሳር ላይ የተጻፈውን ገድሉን እንዲያነቡ ልጋብዝዎት:: ጻድቁ ያረፈው በዚሁ ዕለት ነው:: =>አምላከ ቅዱሳን ወዳጆቹ ካሉበት ጉባኤ እንደ ምሕረቱ ታላቀነት ያድርሰን:: በረከታቸውንም ይሙላልን:: =>መስከረም 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ረባን 2.አቡነ አኖሬዎስ ዓቢይ 3.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ 4.ቅዱስ ዕፀ መስቀል 5.ቅድስት እሌኒ ንግሠት 6.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ 7.ቅዱስ መርቆሬዎስ ካልዕ (ሰማዕት) 8.ቅዱስ ቶማስ ሰማዕት 9.ቅዱስ ኤፍሬም ሰማዕት 10.አባ ፊልሞስ 11.ቅዱስ ሰልሖን ሰማዕት 12.ቅዱስ አክሳኤልስ ሰማዕት 13.ቅዱስ ይስሐቅ ሰማዕት 14.ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀሲስ 15.ቅዱስ ነኪጣ ሰማዕት 16.አባ ፊላታውዎስ መንክራዊ 17.አባ ኖብ ባሕታዊ 18.አባ አትናቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት 19."60" ሰማዕታት (ማሕበረ ቅዱስ አቦሊ) =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) =>+"+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም #ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም . . . መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: +"+ (ማቴ. 5:13-16) <<< ወስብሐት ለእግዚአብ
Show all...