cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ISLAMIC SCHOOL

✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..! ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤ የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡ 🎖For any comment T.me/Aisuu_bot 💠Another channal @IslamisUniverstiy_public_group

Show more
Advertising posts
15 658Subscribers
+224 hours
-367 days
-12530 days
Posts Archive
ኒቃብ ለባሾች እና ሐፊዞች ይህን እድል ተጠቀሙበት!
Show all...
ኒቃብ ለባሾች እና ሐፊዞች ይህ እድል እንዳያመልጣችሁ!
Show all...
ኑር የቁርአን ንባብ እና ኢስላማዊ ጥናት ማዕከል - የስራ መደብ፦ የቁርኣን እና ተርቢያ ኡስታዝ/ዛ - ፆታ:- ወንድ ሴት - ብዛት፦ 5 ሴት  3 ወንድ መስፈርት :- - ቁረኣን በተጅዊድ መቅራት መቻል - መሰረታዊ ኢስላማዊ ኪታቦችን የቀራ/ች - የትምህርት ደረጃ:- 12+... - በ 24 ሰዓት ውስጥ ለሚሰጠው የስራ ሰዓት ዝግጁ መሆን - ያለበት ቦታ የኔትዎርክ ችግር የሌለው መሆን ደመዎዝ:- በስምምነት #ማስታወሻ፦ ለኒቃብ ለባሽ እና ሓፊዝ ቅድሚያ እንሰጣለን ለማመልከት፦ @nur_qurean_2 ስልክ :- +251901 77 55 11 +251934993686 #ለእርስዎ_ካልሆነ_ለሌሎች_ያጋሩ! === Halal Jobs ቴሌግራም👉 t.me/HalalJobsEth
Show all...
👍 1
የረመዳን ተአምራት እና ዮሺኖሪ ************************* በ አውሮፓያኑ አቆጣጣር 2016 የ አለማችንን ትልቁን ሽልማት Nobel Prize in Physiology or Medicine ሽልማት ያሸነፈው ፊዚዮሎጂስት Yoshinori Ohsumi ነው። ያሸነፈውም የ ሰውነትን controlled autophagy “የጽዳት ዘመቻ” ሳይንስ በድንቅ ምርምር ከደረሰበት በኋላ ነው። ታድያ ይህ ድንቅ ሰው የሰራው ስራ ስለ ረመዳን ጾም የተለየ ግንዛቤን የፈጠረ ነበር። እናብራራው... የሰው ልጅ ለ 12 ሰአትና ከዚያም በላይ ብቻ ከጾመ "ኦቶፋጂ" (autophagy) በመባል የሚታወቀውን የሴል ሂደት ለመጀመር ያስችለዋል። ይህን ሂደት "የ ሰውነት የጽዳት ዘመቻ" በማለት ልንጠራው እንችላለን። እናም በዚህ የ "ኦቶፋጂ ጽዳት ዘመቻ በ ሰውነት በየቦታው የወዳደቀ ፕሮቲን (Damaged protein) የተበላሹ ሴሎችን ሳይቀር በሙሉ ጠራርጎ በማቃጠል ያስወግዳል። በተፈጥሮ ያረጁ ሴሎች በ ህይወት እያሉ በምትካቸው ወጣት ሴል አይመረትም። ለምሳሌ ይህንን ሁኔታ በ መከላከያ ሴሎች (Immune system) አንጻር ብናይ የሰውነት ባረጁ ሴሎች መሞላት ተጸኖው ቀላል አይደለም። ሽማግሌ ፖሊስ ከሌባ እንደማያስጥለው ሁሉ ሽማግሌ የ መከላከያ ሴልም ከ በሽታ አያድንም። አንድ ሰው 12 ሰአት ጾም ሲጾም ሰውነት የ ምግብ ጉድለቱን ለመሙላት ሲል ሽማግሌ ሴሎችን ገድሎ ለምግብነት ይጠቀማቸዋል (ይበላቸዋል) (ሰው በተፈጥሮ የሚከሳው የራሱን አካል በልቶ ነው)። ሆኖም ስናፈጥር (ስንበላ) አዲስ ንቃት ያለው ወጣት ሴል እንዲፈጠር እድል ይሰጣል (immune cell recycling) ። በዚህም ሂደት ሁሉም ሴል ሲታደስ በዛውም የመከላከያ ሚኒስተር ታደሰ ማለት ነው። ያማለት የበሽታ መከላከል አቅም በ ጾም ምክኒያት ተሻሻለ ማለት ነው። ይህ ሂደት ሴሎች የራሳቸውን ክፍሎች የሚያድሱበትና እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያደርግም የተፈጥሮ አሠራር ነው።ይህ ሂደት በተለይ ኒውሮዲጀነሬቲቭ ሁኔታዎችን ካንሰርን ጨምሮ ገዳይ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት ስለሚችል ለሰው ልጅ እጅጉን አስፈላጊ ነው ።ይህም ሴሎችን ለመጠገንና ለማጽዳት የሚረዳ ከመሆኑም በላይ ለረጅም ዕድሜና እርጅናንም ለመከላከል ተጽእኖ አለው። እጅግ የሚገርመው ሰውነት autophagyን ለመጀመር በትንሹ ለ12 ሰዓት እና በላይ ያህል ይፈልጋል። ከሃይማኖት ጾም አንጻር ስናየው ከእስልምና ጾም ጋር ብቻ ትይዩ ነው (ፊጥራ)። ዛሬ ላይ ፈረንጆች እንደ ጤናማ ባህል promote እያደረጉት ነው።ዩሽነሪ በሽልማቱ ለጋዜጠኞች ስለ autophagy ሲያብራራ ጾሙ ለ4 ሳምንት ሲተገበር እጅግ የተዋጣለት ይሆናል። እናም አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በጤና እንድንከርም በ ፊጥራ ይህንንም ሲስተም በዓመት አንድ ጊዜ ሰውነት ላይ ለአንድ ወር እንዲካሄድ የወሰነለት ሀቅ ይሆን እያልን ተገረምነ 😍😍😍 “ተባረከላሁ አህሰኑል ካሊቂን” አልን። ፎቶው የ ፕሮፌሰር Yoshinori Ohsumi ነው።
Show all...
24👍 10
👍 7
ምናልባት Telegram ላይ እና Facebook ላይ ከሚሊየን በላይ ተከታይና ጓደኛ ሊኖሩህ ይችላል። አላህን የማያስታውሱህ ከሆነ ምንም አይጠቅሙህም።
Show all...
👍 31
ልባችን ""ሁሉም ነገር በ አላህ እጅ እንደሆነ ሲያውቅ በጣም ይረጋጋል
Show all...
🥰 12👍 3
🍎እስከዛሬ ካነበብኩት  በጣ ደስ የሚለኝ . ሰውዬው ከ ኢሻ ሰላት ብሃላ ወደ ቤቱ ሲገባ ልጆቹን ተኝቶ አገኛቸው ባለቤቱን ሰላት ሰግደዋሉ ወይስ አልሰገዱም በማለት ጠየቃት? እሷም : እንዲ አለቺው...ቤት ውስጥ ምንም ምግብ አልነበረምና አታልዬ ሳይሰግዱ አስተኘዋቸው ብላ መለሰችለት ባለቤቷም:እንዲሰግዱ ቀስቅሲያቸው አላት እሷም:እንዳያስቸግሯት በመስጋት አሁን ከቀሰቀስኳቸው በራብ ብዛት ያለቅሳሉ ቤት ውስጥ ደግሞ ምንም ሚበላ ነገር የለም አለቺው እሱም እንዲ አላት :አንቺ ሴት ሆይ አላህ እኔን ያዘዘኝ በሰላት እንዳዛቸው ነው የሪዝቃቸው ጉዳይ በኔ ላይ አይደለም...ቀስቅሺያቸው ሪዝቃቸው በ አላህ ላይ ነው አላት!! አላህም እንዲህ ብሏል :-👇👇 {وَأْمُرْ أَهْلَكَ بِالصَّلَاةِ وَاصطبرْ عَلَيْهَا ۖ لَا نَسْأَلُكَ رِزْقًا ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُكَ ۗ وَالْعَاقِبَةُ لِلتَّقْوَىٰ} ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፡፡ በእርሷም ላይ ዘውትር፤(ጽና)፡፡ ሲሳይን አንጠይቅህም፡፡ እኛ እንሰጥሃለን፡፡ መልካሚቱ መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት፡፡    ጣሃ 20፦13 እናቲቱም እጅ ሰጥታ እንዲሰግዱ ቀሰቀሰቻቸው ከዛም ሰገድው እንደጨረሱ የቤታቸው በር ተንኳኳ!...በሩን ሲከፍቱት አከባቢያቸው ላይ የሚኖር አንድ ባለ ሀብት በተለያዩ ምግቦችች የተሞላ ከረጢት ኢዞ ነበር ከዛ ሰውዬውን ይሄን ለቤተሰብህ ውሰድና ስጣቸው አለው🎈 ሰውዬም ደንግጦ እንዴት ልትመጣ ቻልክ አለው ...ባለሀብቱም አመጣጡን እንዲህ ሲል ተረከለት : አንድ የተከበረ ባለስልጣን እኔ ዘንድ በእንግድነት መጥቶ ነበረ አነዚህ ምግቦችም ለሱ የተዘጋጁ ነበሩ ግን ከመመገቡ በፊት  በሆነ ጉዳይ ላይ ትንሽ ተከራክረን ምግቡን አልበላም ብሎ በመማል ጥሎ ወጣ ከዛም እኔ  የቀረበውን ምግብ ያዝኩና እግሮቼ በቆሙበት ስፍራ ላለ ሰው እሰጣለሁ ብዬ ከቤት ወጣሁኝ ግን ወላሂ ልክ አንተ በር ከመድረሴ በፊት አንድም አልቆምኩኝም በ አላህ ይሁንብኝ እናንተ ዘንድ ምን እንዳመጣኝ አላውቅም በማለት ነገረው ...በዚህ ግዜ የቤቱ አባወራ እጁን ወደላይ ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ 👇👇👇 : رَبِّ اجْعَلْنِي مُقِيمَ الصَّلَاةِ وَمِن ذُرِّيَّتِي ۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَاءِ. «ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ። አለ!! ሱረቱ ኢብራሂም -40: .
Show all...
👍 27 12🥰 4
ልክ ሚሽነሪዎች መጥተው በጥቅማ ጥቅም ሙሥሊሙን ሲያከፍር ዋይ ዋይ ከማለት ይልቅ ተምሮ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉ አያዋጣምን? "ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ" የሚል አገሪኛ ብሒል አለ። ቀድመን አለመንቃታችን ዋጋ ያስከፍለናል። ከአፋር ክልል ከሱማሌ ክልል ከትግራይ ክልል መማር የምትፈልጉ ሙሥሊሞች እባካችሁ ገብታችሁ ተማሩ! ለመግባት ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ! ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa እኅት አበባ፦ http://t.me/selemtewa
Show all...
👍 5 1
"የስራ ዋጋ በሚከፈልበት ቀንና የስራን ዋጋ በሚከፍለው አምላክ ያመነ ሰው መልካም ነገር ለማድረግ  ቀስቃሽ አይጠብቅም፡፡"
Show all...
11👍 4
ተፈኩር አሏህ ምንምን ያሸነፈ ጌታ ነው፡፡ የሰው ልጅ አዲስ ነገር ሲሰራ የነበረን ነገር በማየት ወይም ምሳሌ በማድረግ ነው፡፡ ለምሳሌ ሰው አውሮፕላን ለመስራት አእዋፋትን አጠና፡፡ አሏህ ግን ከምንም ተነስቶ ያደርጋል፡፡ ካልነበረ ነገር ተነስቶ ይፈጥራል፡፡ 👌👌👌አል-ኻሊቅ 👌👌👌
Show all...
👍 34
ربي اجعلني من يصلي الصلاه ليرتاح بها لا ليرتاح منها🤍🤲🏻
Show all...
👍 8🔥 2
🌤የጧት☀️☀️አዝካር🌤                       اصْبَحْنَا وَ أصْبَحَ المُلْكُ لِلَّهِ، وَ الحَمْدُ لِلَّهِ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ المُلْكُ، وَ لَهُ الحَمْدُ، وَ هُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، رَبِّ أسْألُكَ خَيْرَ مَا في هَذَا اليَوْمِ وَ خَيْرَ مَا بَعْدَهُ، وَ أعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا في هَذَا اليَوْمِ وَ شَرِّ مَا بَعْدَهُ، رَبِّ أعُوذُ بِكَ مِنَ الكَسَلِ، وَ سُوءِ الكِبَرِ، رَبِّ أعُوذُ بِكَ مِنْ عَذَابٍ في النَّارِ وَ عَذَابٍ في القَبْرِ. ማለዳ ላይ ለመድረስ ነቅተናል፡፡ በዚህ ሰዓት ሉዓላልነት የዓላማት ጌታ የሆነው አላህ ነው፡፡ ምስጋና ከአላህ ነው፡፡ ከአላህ ውጭ ሌላ\አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፡፡ አገር የለውም፡፡ ሉዓላዊነት የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም የርሱ ብቻ ነው፡፡ ጌታዬ ሆይ የዚህን\ቅና የቀጠዩን የሌሊቱን መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፡፡ ከዚህ ቀንና ከቀጣዩ ከሌሊቱ ክፉ ነገር በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ጌታዬ\ሆይ ከእሳት ቅጣት ከቀብር ውስጥ ቅጣትም በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ازكار الصباح
Show all...
🥰 7👍 4
☞ *�የጠዋት ዚክር* _اَلْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِيْ أَحْيَانَا بَعْدَ مَا أَمَاتَنَا وَإِلَيْهِ النُّشُوْر_ِ                     *ትርጉሙ*⇓� � _▲ሕይወታችንን በከፊል ከገደለ በኋላ ነፋስ ለዘራብን  ላደረገን አላህ ምስጋና ይገባው መመለሻም ወደርሱ ነው።_ _اَلْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِيْ عَافَانِيْ فِيْ جَسَدِيْ، وَرَدَّ عَلَيَّ رُوْحِيْ، وَأَذِنَ لِيْ بِذِكْرِه_ِ               *ትርጉሙ*⇓� _▲አካላዊ ጤንነት ለለገሠኝ ነፍሴንም ለመለሰልኝ እንዳወሳውም ለፈቀደልኝ አላህ ምስጋና ይገባው_
Show all...
ስለ "Halal Jobs" ሰምተዋል? ይህ ፕላትፎርም የተከፈተው ሐላል የሆኑ የስራ ማስታወቂያዎችን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ለማድረስ ሲሆን፥ አዲስ ስራ ለሚፈልጉ፣ ስራ መቀየር ላሰቡና እንዲሁም ቀጣሪዎች የስራ ማስታወቂያቸውን በነፃ እንዲለቁበት በማሰብ የተዘጋጀ ፕላትፎርም ነው!። ይወዳጁን! ይከታተሉን! ወዳጅዎንም ይጋብዙ! ያተርፉበታል! እርስዎም ለወዳጅዎ በማጋራት የአላማችን ተካፋይ ይሁኑ። ቻናል👉https://t.me/HalalJobsEth
Show all...
👍 3
🔴 ዘርን የሚያወድስ አንድ አንቀፅ አይገኝም ‏قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله: "ولهذا ليس في كتاب الله آية واحدة يمدح فيها أحدًا بنسبه ولا يذم أحدًا بنسبه ለዚህማ ሲባል ቁርኣን ውስጥ አንድን ሰው በዘሩ ሚያወድስ ወይም በዘሩ ሚኮንን አንድ አንቀፅ እንኳ የለም وإنما يمدح بالإيمان والتقوى ويذم بالكفر والفسوق والعصيان ሚያሞግሰው በእምነትና አላህን በመፍራት ብቻ ነው የሚኮንነውም በክህደት በጋጠ ወጥነትና በወንጀል ብቻ ነው فجعل الفخر بالأحساب من أمور الجاهلية".. በክብር መፎከረን ከመሃይማን አጀንዳዎች አድርጎታል التفسير الكبير (٤٢/٤)
Show all...
👍 9
فَنَادَىٰ فِي الظُّلُمَاتِ أَن لَّا إِلَٰهَ إِلَّا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمين በጨለማዎችም ውስጥ ኾኖ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ፡፡😢
Show all...
👍 7😢 3
ሰው ሆኖ ያልጎደለው የለም መቸስ። የአደም ልጅ ሆኖ እንከን የሌለበት የለም። ከፊሉ ቁጡ ነው። አንዳንዱ ቸልተኛ ነው። ሌላው ሰነፍ ነው። ሌላው ቀናተኛ ነው። በመጥፎ ቃላት የተፈተተነ አለ። ክፉ ጥርጣሬ የነገሰበት አለ። እኔ  ያልኩት ብቻ ካልሆነ ብሎ ድርቅ የሚል አለ። በየቀኑ እራሳችንን ለማረም መትጋት አለብን። ለመለወጥና ለመሻሻል መጣር ይኖርብናል። አላህ ሆይ ጠዋት ከወጣንበት ሁኔታ የተሻልን አድርገህ ማታ ላይ መልሰን። ሶባሐል ኸይር ☺️ abx
Show all...
21👍 7😢 1
﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللهَ وَابْتَغُوا إِلَيْهِ الْوَسِيلَةَ وَجَاهِدُوا فِي سَبِيلِهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ﴾. «اللَّهُمَّ آتِ نُفُوسَنَا تَقْوَاهَا ، وَزَكِّهَا أنْتَ خَيْرُ مَنْ زَكَّاهَا ، أنْتَ وَلِيُّهَا وَمَوْلَاهَا».
Show all...
👍 6
Repost from ISLAM IS UNIVERSITY
ሰመአት የሆነ ልጇን እንዴት እንደምሸኝ ያረብ ምን ያህል ወኔ ነዉ ግን? እናትነት!!! የፍልስጤም እናቶች ሴቶች ልዩ ናቸዉ t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group
Show all...
5💔 4
☞ሙነሺዶች የዲን አለቃ ሁነዋል፡፡ ☞ሙስሊሞች ቀርአን ከመቅራት ሀዲስ ከመቅራት ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ሁነዋል፡፡ ሞዴልህ ማን ነዉ ቢባል ነብዩ ሰዐወ ማለት ትተዉ ቲክቶክ ፎሎዉ ያደረጓቸዉን የሚጠሩ ይመስላሉ ☞ሴቶች ቁርአን ከመቅራት ሙነሺድ ማየት...ዲኗን ከመማማር ዋሪዳ ሚንበር እያለች ፊቷን ድልቀለም ፋብሪካ ቀለም ሳምፕል መስላ በቲቪ ለመታየት..ነብዩ ሲጠሩ ሰዉ ክብር  ነበረዉ አሁን ግን ነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ የመድረክ ላይ መጨፈሪያ አድርገዋል፡፡ ሴት ትዳር ስታስብ የምታስበዉ ታዋቂ ሰዉ ሆነ..በተለይ የመድረክ ወረርሽኞችን ሆነ ..ነብዬ ትዝ እያልኩን አንበላም አንጠጣም እራበን እያሉ ለሚቀልዱ ሙነሺዶች ሆነ የሴቶች ዌናያቸዉ  ህልማቸዉ ሁሉ የተትረከከ ሆነ...ሴቶች ህዝብ መሀል ካለ ንብ መድረክ ላይ የሚዘል ዝንብ ወዳድ ሁነዋል፡፡ አንዱ ወዶ አይደለም ይህን ሙስሊም ማህበረሰብ በየአቅጣጫዉ ሲመለከት በtiktok በሚዲያ የሚከተዉን ሲያይ ደጃል ቢመጣ ምንም የሚቸገረዉ የሚያስቸግረዉ የለም ያለዉ ..... ብቻ ኡመር ኢብኑል ኸጧብ ካሊድ ኢብኑ ወሊዲን የሚደግም የሴት መሀፀን ጠፋ ያሉት ወደዉ አይደለም፡፡ ግን ለምዕራባዉያን መቼም ቢሆን የማይረታ በተንኮል የማይታለሉ ሁሉም ጀግና ለዲነል ኢስላም ለነፃት የሚዋደቁ አሉ ፍልስጤም ጋዛ ነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ ከ1400 በፊት የመሰከሩላቸዉ ከህዝቦቼ ጠላቶቻቸዉ ላይ የበላይና አሸናፊ የሆኑ አንዲት ጭፍራ ሀቅ ላይ ከመሆን አይወገዱም፡ከሚያገኛቸዉ የኑሮ መከራ ዉጭ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆነዉ የአላህን ትዕዛዝ እንዲመጣላቸዉ ድረስ የተቃረናቸዉ አይጎዳቸዉ፡ ....አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ የት ነዉ ያሉት?ብለዉ ሱሀባዎቹ ጠየቋቸዉ ...በይተል መቅዲስ በበይተል መቅደስ ዙሪያ ብለዉ መለሱላቸዉ፡፡(ሀዲሱን አህመድ ዘግበዉታል) ነብዩ ሰዐወ ከ1400 አመት በፊት ይመጣል ብለዉ የተነበዩት ትንቢት ምንያህላችን እናቃለን??? ሙስሊሞች አይሁዳዉያንን እንደሚጋደሉ ነግረዉናል:: ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ እንዲህ ብለዉናል ሙስሊሞች አይሁዳዉያን ጋር ሳይጋጠሙ በፊት ቂያማ አትቆምም ሙስሊሞች አይሁዳዉያንን እስኪገሏቸዉ ድረስ የዚህን ጊዜ አይሁዳዉያን ሞትሽን ሽሽት ለመደበቅ ከዛፍና ከዲንጋይ ሆላ ይሸሸጋሉ ግን ዛፉና ድንጋዩ አንተ ሙስሊም የአብደሏህ ከኔ ሆላ የተሸሸገ የሁዲ አለ መጥተህ ግደለዉ ይላሉ፡፡ሁሉም ዛፎች ይናገራሉ ከገርቀት ዛፍ በቀር ብለዋል ነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ(ሀዲሱን ቡሀሪና ሙስሊም ዘግበዉታል፡፡ እናም እኛም ኢንሻ አላህ የነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ ትንቢት አላህ ያሳየናል ..ከላይ ካለዉ ሀዲስ ገርቀት የሚበለዉ ቅጠል አሁን ያለዉ እስራኤልሀ ሀገር ዉስጥ በብዛት አለ...በዚህ ጦርነት ከተበታተኑበት ከተለያየ ሀገር ወደ እስራኤል ተሰባስበዋል አሁን ለራሱ ሙሉ የእስራኤል ጦሯን 360,000 በላይ በቀጥታ የጋዛን ሙስሊሞች ለማጥፋት ከአለም ግፈኞች መንግስት ጋር ተባብራ ትደበድብ ይዛለች ግን አላሸነፈችሞ አታሸንፍም እነዛ በአላህ የሚታገዙ ጭቁን ከሰዉ ምንም የማይከጅሉ በአላህ 100% መተማመን ያላቸዉ ኢስላም ሲደፈር የማይወዱ የጋዛ የሀማስ የፍልስጤም ህዝቦች ወደዳችሁም ጠላችሁም ነብዩ ሰዐወ ነግረዉናል አሸናፊ ናቸዉ..እስራኤላዉያን መግቢያ ያጣሉ...አይታወቅም ይሄን ስታነቡ ከ25,000 በላይ ንፁሀን ሙተዉ ከቤት ከንብረታቸዉ ተፈናቅለዉ አረብ ሙስሊም ሀገሮች ከድተዋቸዉ እንዴት ያሸንፋሉ??ብላችሁ ታስቡ ይሆናል መልሱ አዎ 100% አሸናፊ ፍልስጤም ናቸዉ መቼ ላላችሁት አይታወቅም ገና ከዚህ በላይም አላህ ሊፈትናቸዉ ይችላል በዚሁም በቃችሁ ብሏቸዉም ይሆናል ቀናት ሳምንታት ወራት አመታት ብዙ አመታት ሊፈጅ ይችላል ጀሊሉ ነዉ የሚያቀዉ ፡፡ የሰባት ቀን የአረብ ጦርነት ከእስራኤል ጋር አረቦች ተጋጥመዉ እነ ግብፅ ሶርያ ወዘተ በሰባት ቀን ዉስጥ እስራኤል አሸንፋ አሁንድ ድረስ በዛ ድል ታስፈራቸዋለች...ግን አሁን ጦርነት የገጠመችዉ ፈሪ የስልጣን ወንበር ፈላጊ በነዳጅ ብር ልቦናቸዉን ያጡ አረቦችን ሳይሆን ፍልስጤሞችን ነዉ...ፍልስጤምን እስራኤል መቼቼቼቼምምምም ቢሆንንንንን አአአአአታታታታታታሸሸሸሸሸንንንንንፍፍፍፍፍፍምምምምምምም አረብ ሀገር ከድተዋቸዉ ላላችሁ ዛሬ አይደለም የከዷቸዉ በተለያየ ክፍል እንዳየነዉ በፊት እንግሊዝ ጋር ተባብረዉ ለስልጣን ብለዉ ነበር የከዷቸዉ... አሏህ ለአረብ ሀገራት በተለይ ለስዑድ አረብያ ልቦና ማስተዋልን  ይስጣቸዉ ብዙ ጠባሳ ቢኖርም የሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ የተወዱባት ሀገር መካን ይዛለችና ከዱአ ዉጭ አማራጭ የለም ...ግን አለች የመን ነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ የመሰከሩላቸዉ አልኢማኑ የማኒ (ኢማን ከየመኖች ነዉ)ብለዋል ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ በተጨማሪ ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ የዉመል ቂያማ ዉሀ ጥሙ ሲጠና እኔ የማጠጣችሁ ሀዉድ አለ መጀመሪያ የምሰጠዉ #ለየመን ህዝቦች ነዉ ብለዉ መስከረዉላቸዋል፡፡ አሁን እንደምናየዉ እንደ የመን እና በጎን እንደ ኢራን መሬት ወርደዉ ሲያግዟቸዉ እያየን ነዉ፡፡ሁሉንም ለአላህ ብለዉ የሚሰሩትን አላህ ይገዛቸዉ፡፡ ያረብ ከ99 ስሞች ዉስጥ አንዱ ስምህ አዚዝ(አሸናፊ) የሆነዉ  ጌታየ ሆይ በአላህ በሙስሊም ጥላቶች ላይ አሸናፊነትህን አሳየን..ነብዩ ሰዐወ እንደነገሩን ከህዝቦቼ ጠላቶቻቸዉ ላይ የበላይና አሸናፊ የሆኑ አንዲት ጭፍራ ሀቅ ላይ ከመሆን አይወገዱም፡ከሚያገኛቸዉ የኑሮ መከራ ዉጭ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆነዉ የአላህን ትዕዛዝ እንዲመጣላቸዉ ድረስ የተቃረናቸዉ አይጎዳቸዉ ያሉትም በይተል መቅዲስ ነዉ እንዳሉን ጀግነነታችዉን ፅናታቸዉን እያየን ስለሆነ በተጨማሪ በሀዲሰል ቁድስ ነብዩ እንዳሉን ሙስሊሞች ሳያሸንፉ ቂያማ አትቆምም እንዳልከን በህይወት ዘመናችን የምናይ አድርገን ያረብ... ያኢላሂ የሞቱትን ጀነተል ፊርዶስ ..ሀዘን ላይ ያዩትን ሶብር...ችግር ላይ ያሉትን እርዳታህን..ጭንቀት ላይ ያሉትን ፈረጃህን..ጦርነት ላይ ያሉትን አሸናፊነትህን ለአለም ህዝብ አሳየን ያረብ፡፡ የሙስሊም መሳሪያዉ ዱአ ነዉ...እኛ ከፍልስጤሞች እነሱ ጋር በጀግንነት በቆራጥነት ከእግራቸዉ እጣቢ አንድርስም ብቻ 100% እርግጥ ነዉ ይሄን ሁሉ ፈተና አልፈዉ እንደሚያሸንፉ ምንም ቅንጣት ያህል ጥርጥር የለም ብቻ ፈተናዉን ቀላል ከአሁን በፊት ከተፈጠረ የቀለለ ያድርግላቸዉ... ፁሁፉ ዛሬ ተፈፀመ በ7ክፍል ያቀረብኩት ፁሁፍ በአንድ ቀን በ24ሰአታት ብቻ የተዘጋጀ ነዉ በመሀል የተሳሳኩት የቃላት ስህተት ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ ፁሁፉ ዛሬ ተፈፀመ...የፍልስጤምን ሰቆቆ ሀዘን እምባ አላህ ይፈፅምልን አንተም አንቺም እሱም እሷም እናንተም በዱአ እንበርታ ብቻ ሁላቾንም 100% እንሁን ፍልስጤም ያሸንፋሉ እስራኤል የአለም ግፈኞች ቢረዷት ቢተባበሯት በቦንብ ብደበድብ በፈለገችዉ መሳሪያ ብትጠቀም የፍልስጤም ሙጃሂዶችን 1000% ማሸነፍ አትችልም፡፡ አሸናፊዉ ፍልስጤም ፍልስጤም ብቻና ብቻ ናቸዉ እድሜ ይስጠን እናያለን....., 06/06/2016 #ተ....... #ፈ.......... #ፀ...........መ ፁሁፉ ላይ ስህተት ካለ የሚስተካከል ካለ ቶሎ ያሳዉቁኝ edit ማድረግ ስለሚቻል👇👇 T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot join👇👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group
Show all...
6
🔰 #እየሩስ_አሌምን_ለገና_ስጦታ_አድርስልኝ 🔰               #የመጨረሻዉ_ክፍል                  ✍ አሚር ሰይድ #በሙስሊሙ_ወጣት_ላይ_የስነምግባር_ብልሹነትን_ማስፋፋት የሙስሊም ወጣቶችን ባሕሪ ለማበላሸት አውሮፓውያን እና አሜሪካዉያን በህብረት እኢአ ከ200 ጀምሮ 57 ቢሊየን ዶላር መድበዋል፡፡ ✏️ከዚህ ውስጥ 12 ቢሊየን ዶላር ስሜት ማራኪ ስልቶች ለመጠቀም፣ ✏️ 20 ቢሊየን ዶላር የቪዲዮ ፈልም ማምረቻ! ✏️11 ቢሊየን ዶላር ቅምጥ ሴቶችን ማዘጋጃ፣ ✏️ 7.5 ቢሊየን ዶላር የብልግና መጽሄቶች ማዘጋጀት እና ማሰራጨት፣ ✏️ አምስት ቢሊደን ዶላር መሽታ ቤት ማዘጋጀት ✏️2.5 ቢሊየን ዶላር የብልግና ማሰራጫ ጣቢያዎች ✏️ 1.5 ቢሊየን ዶላር ሲዲዎች ማዘጋጃ፣ ✏️ 1 ቢሊየን ዶላር የስልከ መስሮች ማዘጋጃ፣ ✏️ 1.5 ቢሊየን ዶላር የተለያዩ የወሲብ ቀስቃሽ መልእክቶች ማዘጋጃ ላይ ይውላል፡፡ #የሙስሊሙን_ህብረተሰብ_የሚያበላሹ_የብዙሀን_መገናኛዎች ሙስሊሙ ህብረተሰብ በተለይ ወጣቱ ከእስልምና እንዲዘናጋ የተሊያዩ የብዙሃን መገናኛ ጣቢያዎችም ፈጥረዋል፡፡ አሜሪካ በሚገኘው ሆሊውድ ማእከል እስከዛሬ ድረስ ከዘጠኝ መቶ ያላነሱ ዓረብ እና ሙስሊሞችን እሚያንቋሸሹ ፊልሞች ተሠርተዋል፡፡ በ1942 የተመሰረተው የአሜሪካ ድምፅ የሬድዮ ጣቢያ የዓረብኛ ቋንቋን ሶስተኛ ቋንቋ አድርጎ በመጠቀም ረጅም ሰአትን ባሕል በራዥ እምነት ከላሽ ፕሮግራሞችን ያቀርባል፡፡ ☞ ሳዋ የሚባለው የሬድዮ ጣቢያ ዝግጅቱም ከ30 አመት በታች ላሉ ሙስሊም ወጣቶች የተዘጋጀ ነዉ፡፡በስርጭቱም 80% ዘፈንና ድራማ ይጠቀማል፡፡ የሚጠቀምባቸውም የአረብኛ ቋንቋ ዘዬዎች የግብፅን የዒራቅን የሱዳንን የገልፎችን አካባቢ የዓረብኛ ቋንቋ ነው። 🟢 #ሐይ... በመባል የምትታወቀው ወርሃዊ መፅሄት ለተመሳሳይ ዓላማ የተመሰረተች ናት፡፡ የተመደበላትም ዓመታዊ በጀት በአሁኑ 4 ሚሊየን ዶላር ደርሶዋል፡፡ 70 ገጽ ያላት ሲሆን ከ28 እስከ 35 እድሜ ላላቸው ሙስሊም ወጣቶችን ስሜት የሚቀሰቅሱ ፁሁፎችን ታወጣለች፡፡ በአምዱዋም ጭፈራን፣ ስፖርትን አቅፋለች፡፡ በአንድ ጊዜ ከ50 ሺ ያላነሰ ኮፒ ታትሞ በነፃ ለሙስሊም ወጣቶች እንድትደርስ ይደረጋል፡፡                      🟢  #አልሁራ_ቲቪ እኤአ በ2004 የተመሰረተ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር በቀን 14 ሰዓት ብቻ ስርጭት ነበረው፡፡ ይህንን በማሳደግ ወደ 24 ሰአት ስርጭት እንዲኖረው ተደረገ፡፡ በዚህ ጣቢያ ውስጥ ከ200 ያላነሱ ዓረብኛ ተናጋሪ ወጣቶች እንዲሳተፉ ተደረገ፡፡ በዓመት 63 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተመድቦለታል፡፡ ስርጭቱም በዓረቡ ዓለም እና በሙስሊሙ ዓለም እንዲደርስ ተደርጓል፡፡ በዒራቅ ለተከፈተው ቅርንጫፍ 40 ሚሊየን ዶላር በጀት ተመድቦለታል፡፡ ከላይ የዘረዘርናቸው የተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ሁሉም እሚያተኩሩት አሜሪካን በማሞገስና በማወደስ፣ እስልምና እና ሙስሊሞችን ማንቋሸሽ ነው:: ሙስሊሞች ማለት ሰይፈኞች፣ አሸባሪዎች፣ ተዋጊዎች፣ ፅንፈኞች፣ ዘራፊዎች፣ ሴቶችን በዳዮች፣ አውሮፕላን የሚያጋዩ፣ አይሁዶችን ባህር ውስጥ ለመወርወር ያቀዱ ተደርገው በድራማዎችና ፊልሞች ሲሳሉ፤ ዓረብ ማለት ደግሞ ማሰብ የማይችል፣ የመጠጥ ሱሰኛ፣ ከነዳጅ ገቢ ባገኘው ገቢ በዶላር የተሞላ፣ እውቀት አልባ የሆነ ጨካኝ፣ ራሱን የሚወድ ነጭ ሴቶችን እሚያድን ማለት ነው የሚለውን ነው የሚያንፀባርቁት፡፡ >> በተጨማሪም _ በአውሮፓ _ እና _ በአሜሪካ _ ለሚመረቱ የብልግና ፊልሞች በዓረቡ ዓለም የሚያሰራጩ አጋሮች በመፍጠር ከ510 ያላነሱ የዘፈን ቻናሎች በአረቡ ዓለም እንዲሰራጩ አደረጉ፡፡ ለዚህም የተመደበው በጀት ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ሆኖዋል፡፡ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ያሉትን ዘመን ያፈራቸውን ዘፋኞች እስፖርተኞች ጨፋሪዎችን በመጋበዝ በተለያዩ ዓረብ ከተማዎች መሸታ ቤቶች እንዲከፈቱ አደረጉ፡፡ ✍ አሜሪካ በአፍጋኒስታን ላይ ባደረገችው ወረራ እና ዘመቻ የተቃውሞ ሰልፍ የወጣው ወጣቱ ሙስሊም ከ4 ሚሊየን አይበልጥም #ዲያና_ከራዞን የምትባለውን ዘፋኝ ለመቀበል ከ50 ሚሊየን ያላነሰ ሙስሊም ወጣት ወጥቷል፡፡ ልክ ህንድን ለከፈተው ሙሀመድ አልቃሲም ወይም ቁስጠንጢኒያን ለከፈተው ሙሀመድ አልፋቲህ አቀባበል የሚያደርጉ ነበር የሚመስለው፡፡ ☞ 78% ዘፈንን የሚመለከት ☞7% የሀይማኖት ቻናሎችን የሚመለከት ☞ 80% ጭፈራን ስፖርትን የሚመለከት ሆኖዋል፡፡ ቀደም ሲል የረጅም ጊዜ የሙስሊም ታሪክ ፈጣሪን እሚያስከፋ አንድ ወንጀል ብቻ ነበር የሚታየው:: በአሁኑ ጊዜ ግን የተበላሸ ወጣት፣ የተበላሸ ህብረተሰብ፣ የተበላሸ ፖለቲካ፣ የተበላሸ ኢኮኖሚ፣ የተበላሸ ማህበራዊ ኑሮ ሁሉም የተበላሸ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለፈጣሪ አጋር መፍጠር፣ ጥንቆላ፣ በዲን ላይ ፈጠራ፣ ኹራፋት ተንሰራፍቶ እናገኛለን፡፡ 🟢#የዓረቡ_አለም_ወጣት_ሙስሊሙ_ስለ_ትምህርት_ያለው_ግንዛቤ በአረቡ ዓለም 325 ሚሊየን አረብ ሲኖር የዩንቨርስቲዎቻቸው ብዛት ግን 400 ብቻ ነው:: 300 ሚሊየን የሚሆኑ አሜሪካውያን 3400 ዩኒቨርስቲ አላቸው:: 130 ሺ የሚሆኑ የሳውዲ ወጣቶች በተለያዩ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ዘመናዊ እውቀት ለመቅሰም በእስኮላርሺፕ ሽፋን ተሳትፈው ይገኛሉ፡፡ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች እውቀትን ከማስተማር ይልቅ ትኩረት የሚያደርጉት የሚከፍሉትን ገንዘብ ግምት በማስገባት በነፃነት እንዲማግጡ ይለቋቸዋል፡፡ ✍ የሳውዲ ወጣቶች ለትምህርት በሚል በአሜሪካ ዩንቨርስቲ ውስጥ በአመት ከአርባ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ያወጣሉ፡፡ተማሪዎቹ ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በከፍተኛ ማእረግ እንደተመረቁ ተደርገው ይሸኛሉ፡፡ ምክኒያቱም ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በከፍተኛ እርከን እና ሀላፊነት ስለሚመደቡ ተገዢነታቸውም ለቆዩበት ሀገር እና ዩኒቨርስቲ ይሆናል፡፡ የገልፍ ነዋሪዎች ለልጆቻቸው አረብኛ ቋንቋን ከመማር ይልቅ እንግሊዘኛን መማር ያስቀድማሉ፡፡ በዚህም የተነሳ በየዓመቱ ልጆቻቸውን ወደ አውሮፓ ሀገራት በመላክ ከዛም የአውሮፓውያን ቤተሰቦች እንዲቀበሉዋቸው እና በቤታቸው እንዲያሳርፉዋቸው አስፈላጊውን ማረፊያ በማዘጋጀት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቻ የሚያናግሩዋቸው ወጣት ሴቶችን በመመልመል ጓደኛቸው እንዲሆኑ አጋጣሚዎችን ያመቻቻሉ፡፡ ለዚህም ከፍተኛ ክፍያን ይጠይቃሉ እነኚህም፡፡ የሙስሊም ወጣት ቤተሰቦችም ክፍያውን ይፈፅማሉ፡፡ ያም ለጋ ሙስሊም ወጣት በቆይታው ቋንቋ መቅሰም ብቻ ሳይሆን ካረፈባቸው ቤተሰቦች ባህላቸውን ወጋቸውን ልምዳቸውን ብልግናውንም ጭምር እንዲያውም አንዳንዶቹ እምነታቸውን ሳይቀር ቀስመው ይመለሳሉ፡፡ እስልምና ሀይማኖቱን እና ቅርሱን ታሪኩን ያፍሩበታል፡፡ ምዕራባዊያን በቢሊየን የሚመደብ ብር በጅተዉ እንዲበላሹ ጀለብያ ለብሰዉ አምሮባቸዉ ዉስጣቸዉ ግን ለሙስሊም የማይጠቅም የማይጎዳ ትዉልድ ሁነዋል፡፡ ⚡️⚡️ዛሬም በእኛ ኢትዮጲያ አረቦች ከዲናቸዉ እንዳስወጧቸዉ በእኛም አሁን ባለንበት ዘመን እየተንሸራተትን እንገኛለን👇👇
Show all...
👍 3
🔰 #እየሩስ_አሌምን_ለገና_ስጦታ_አድርስልኝ 🔰                 #ክፍል ☞ስድስት 6⃣                  ✍ አሚር ሰይድ #አረቦች_ቁድስን_ካስረከቡ_ቡሀላ_ምዕራባዉያንና_እስራኤል ብዙ ጥቃት አድርሰዉባቸዋል፡፡ ምእራባውያን የአረቡ ዓለምን ከመልቀቃቸው በፊት የፍልስጤምን መሬት ለአይሁድ እምነት ተከታዮች በማስረከብ እና ድጋፍ በመስጠት ላለፉት 73 ዓመታት ያልቆመ ጦርነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ የ1948፣ የ1956፣ የ1967፣ የ1973 እና 1982 ቀጥሎም የገልፍ የመጀመሪያው ጦርነት በዒራቅ እና በኢራን መካከል በ1980 የተደረገው ጦርነት ከአንድ ትሪሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት እና ከሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ነብስ የጠፋበት ጦርነት ነበር፡፡ ☞ የገልፍ ሁለተኛው ጦርነት በመባል የሚታወቀው (ኩዌትን ነጻ ማውጣት) በሚል በ1991 የተካሄደው ከ 100 ቢሊየን ዶላር በላይ ወጭ ያስከተለው ጦርነት ነው:: ☞ በመቀጠልም በ2001 በአፍጋኒስታን ላይ የተካሄደውን ዘመቻ እናገኛለን፡፡ ☞በመቀጠልም  እስራኤል በገዛ ላይ ያከሄደችው ዘመቻ 2008 /2009/ 2012 የተካሄዱትን ጦርነቶች እናገኛለን፡፡ በ23 ቀን ብቻ እስራኤል ባካሄደችው ዘመቻ >>5 ሚሊየን ፈንጅ አርከፍከፋለች >> በ3 ሰከንድ ብቻ 120 ቶን ሚሳኤሎችን አውርዳለች፡ ፡>> አሜሪካ በዒራቅ ላይ በ2002 ባደረገችው ዘመቻ ሁለት ትሪሊየን ዶላር ወጪ አስከትሎባታል፡፡ እስራኤል በ2006 በሊባኖስ ላይ የከፈተችው ዘመቻ 7 ዓመት እንዲፈጅባት ያደረገ ሲሆን አሜሪካ በሶሪያ ላይ ጦርነት ካወጀች ሶስት ዓመት አሳልፋለች፡፡ ዛሬም ድረስ ጦርነቱ አልበረደም፡፡ ☞ በየመን ላይ የሚካሄደው ዘመቻ ለሚሊዮኖች ሞት፣ስደት፣ችግር  የዳረገ ነው፡፡ ሁሉንም ስንመለከት በሙስሊሙ እና በዓረቡ ዓለም ላይ ሆን ተብሎ የሚካሄዱ ዘመቻዎች ሁነው እናገኛቸዋለን፡፡ በዚህም የተነሳ ሙስሊሙ ዓለም እና ዓረቡ ዓለም የመረጋጋት የሰላም ንፋስ እንዲተነፍስ እድል አላገኘም፡፡ ለውድመት ለመበታተን ለስቃይ የተጋለጠ ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ ጦርነት ትርፍ ያገኙት ምእራባውያን የመሳሪያ አምራች ኩባንያዎች ሁነው እናገኛቸዋለን፡፡ >> ዓለም በዓመት1324 ቢሊየን ዶላር ለመሳሪያ ግዢ ያውላል፡፡ >> 8 ቢሊየን ዶላር መሀይምነትን ለመዋጋት ለትምህርት ይመድባል፣ >> ዓረቡ አለም በየዓመቱ ከ100 ቢሊየን ዶላር በላይ መሳሪያ ለመግዛት ወጪ ያደርጋል፡፡ ሳውዲ ብቻዋን 33 ቢሊየን ዶላር ለመሳርያ ግዢ ያወጣሉ፡፡ >> ዓለማችን ረሀብን ለመዋጋት 20 ቢሊየን ዶላር ይመድባሉ፡፡ 🔸 እኤአ በ2006 የአሜሪካ የመሳሪያ ሽያጭ ገቢ 18 ቢሊየን ዶላር ሲሆን 🔹 ሩሲያ 8 ቢሊየን ዶላር፣ 🔸 እንግሊዝ 4 ቢሊየን ዶላር ደርሶ ነበር፡፡ ሁሉም የመካከለኛው ምስራቅ አገራትን ጦርነት ምክኒያት በማድረግ እንደ ገቢ ምንጭ ቆጥረው ነበር የቸበቸቡት፡፡ በአንደበታቸው ስለ ሰላም ያወራሉ በድርጊት ግን የጦር መሳርያ ሽያጫቸው እንዳይቋረጥ አንዳቸው አንደኛዋን አገር ሌላው ሌላኛውን አገር ደግፈው እሳት ያቀጣጥላሉ፡፡ ገልፍ የነዳጅ አምራች ሀገር ከመሆናቸው አንጻር በ5 ዓመት ብቻ ከ3 ትሪሊየን ዶላር በላይ ገቢ አግኝተዋል፡፡ >>>> የዓረቡ ዓለም የሙስሊሙ ችግር የፍልስጤም እና የቁድስ ጉዳይ ሆና እናገኘዋለን፡፡ በአሁኑ ጊዜ የዓረቡ ዓለም የህዝብ ብዛት 325 ሚሊየን ደርሷል፡፡ በ2006 በተሰራ ዘገባ የዓረቡ ዓለም መለዮ ለባሽ ወታደር 8 ሚሊየን ደርሶ ነበር፡፡ በሌላ በኩል እስራኤሎች አምስት ነጥብ ሶስት ሚሊየን ነዋሪ ሲኖራቸው መለዮ ለባሹ (ሰራዊት) ከግማሽ ሚሊየን አይበልጥም፡፡ ያም ሁኖ ግን በሚሊዮን የሚቆጠር ወታደር ያላቸው ዓረቦች ከእስራኤል ጋር በተለየየ ጊዜ ባካሄዱት ጦርነት ድልን ተጎናጽፈው እያውቁም:: #አሜሪካ_በዒራቅ_ላይ_ባካሄደችው_ጦርነት >> አራት ነጥብ አራት ትሪሊየን ዶላር ወጪ አድርጋለች፡፡ >> ሁለት መቶ ሀምሳ ስምንት ሺ ዒራቃውያን ሲገደሉ >> 15 ሚሊየን የሚሆኑ ህጻናት እርዳታ ፈላጊ ሆነዋል፡፡ >> አንድ ሚሊዮን ሴቶች ባል አልባ ሆነዋል፡፡ >> አምስት ሚሊየን ህጻናት ወላጅ አጥ ሆነዋል፡፡ >>12500 ዒራቂያውያን ሲቪሎች ተገድለዋል፣ >> 365 ሺህ ቁስለኞች ሲኖሩ >> ሰባት ነጥብ ስምንት ሚሊየን ዒራቂያውያን ቤታቸውን እና ንብረታቸውን ትተው ተሰደዋል፡፡ >> ዒራቅ በቴምር ዛፍ አምራችነትዋ የታወቀች ሀገር ነበረች:: 53ሚሊየን የተምር ዛፍ ነበራት፡፡ ከዚህ ውስጥ 42 ሚሊየኑ በጦርነቱ ወደመ:: >> የዒራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ የቅርስ እና የታሪክ ባለቤት ነበር፣ ከ170 ሺ ያላነሱ ቅርስ እና ታሪከዋ ለመዘረፍ በቅተዋል፡፡ >>በዒራቅ የሚገኘው አቡ ገሪብ የሚባለው የሰቆቃ እስር ቤት! በአፍጋኒስታን ባግራም፣ በኩባ የሚገኘው ጎንታናሞ በነኚህ ሶስት እስር ቤቶች ውስጥ በሙስሊም አስረኞች ላይ ሲካሄድ የነበረው ግፍና ሰቆቃ ለመገመት የሚከብድ ነው፡፡ 🟢 ከአንዳንድ የአሜሪካ እና እንግሊዝ ዪኒቨርስቲዎች እና የምርምር ማእከሎች ተማሪዎቻቸው የማስተርስ እና የ ዶክትሬት ጥናታቸውን ለመስራት ወደ እነኚህ እስር ቤቶች በመጉዋዝ እስረኞቹ በሚሰቃዩበት ጊዜ የሰው ልጅ በውስጥ አካሉም ሆነ በውጩ ምን ያህል ስቃይን እንደሚሸከም ለመገንዘብ ችለዋል፡፡ ኢራቃውያን የደረሰባቸው በደል በቀላሉ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ >> ከሁሉም የከፋ የነበረው ትልቁ የፈንጅ ተሸካሚ ቢ 52 የሚባለው አውሮፕላን በየትኛውም ሀገር አየር ማረፊያ ማረፍ የማይችል፣ ከለንደን ወጣ ብሎ ግላስኮ በሚባል አየር ማረፊያ እንዲያርፍ ተደርጎ የተሰራ ነው::ዘጠኝ ቶን ፈንጅ ከጫነ በኋላ ከቀኑ አስር ሰአት ጉዞውን በመጀመር ወደ ዒራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ከምሽቱ ሁለት ሰአት በመድረስ በአካባቢው ገና ሲደርስ በከፍተኛ ድምፅ የባግዳድን ነዋሪዎች በነፍስ ውጪ እና ግቢ ጭንቀት እንዲደናገጡ እና ሁሉም  ነዋሪዎች ቤታቸውን በመተው ወደ መስጂዶች በመጠለል የመጨረሻ ፀሎታቸውን ያካሄዱ ነበር፡፡ ጭኖ የመጣውን ዘጠኝ ቶን ፈንጅ በንፁሀን የባግዳድ ነዋሪዎች ያለርህራሄ በማዝነብ ሙትና ቁስለኛ ያደርጋቸው ነበር፡፡ ታላቋንና የቀደምት ሥልጣኔ ባለቤት የሆነችውን ባግዳድ ከተማ ዶግ አመድ የማድረግ ተልእኮውንም ይወጣ ነበር፡፡ ይህም ዘመቻ ለስምንት ቀን ያህል ቆይታ ያደረገ ሲሆን አንድ የሰውን ልጅ ነብስ ለማጥፋት 250 ግራም ፈንጅ በቂ ሆኖ ሳለ የዘጠኝ ቶኑ ፈንጅ ምን ያህል እልቂት እንደፈጠረ መገመት አያቅትም፡፡ >> በሌላ መልኩ አሜሪካንም ሆነ አውሮፓውያን የመሳሪያ አምራች ኩባንያዎች በዒራቅም ሆነ በሌላው የዓረቡ ዓለም በተካሄደው እና በሚካሄደው ጦርነት የአዳዲስ መሳሪያ ሙከራ መድረክ አድርገዋቸዋል፡፡ በገልፍ በተካሄደው ጦርነት በህዝቡ ላይ ያስከተለው ቀውስ ብዙ ነበር፡፡ ጤናማ አየር፣ ውሀ፣ ምግብ እንዳይኖር አድርጎታል፡፡ ስለዚህ በአሁኑ ጊዜ የኢራቅ ነዋሪዎች የሚመገቡት ምግብም ሆነ የሚጠጡት ውሃ፣ የሚበሉት አሳም ሆነ የዛፉ ፍሬ የእርሻው ሰብል ውጤት በሙሉ በኬሚካል የተበከለ ሆኗል፡፡ ተረግዘው የሚወለዱ ህጻናትም የአስተሳሰብ እና የአካላዊ ጉድለት ይታይባቸዋል፡፡ በቀጣይ ክፍል ቢኢዝኒላህ ምዕራባዉያን በአረብ ሙስሊሙ ወጣት ላይ የስነምግባር ብልሹነትን እንዴት እንዳስፋፉ እና ከዲን እንዴት እንደዋጧቸዉ እንዳስሳለን #የመጨረሻዉ_ክፍል ይቀጥላል......
Show all...
👍 2
🔰 #እየሩስ_አሌምን_ለገና_ስጦታ_አድርስልኝ 🔰                 #ክፍል ☞አምስት 5⃣                  ✍ አሚር ሰይድ #አሜሪካ_እስራኤልን_ለምን_መጠቀም_ፈለገች! ዓረቡ ዓለም ምዕራባዊያን እያደረሱበት ያለውን በደል 80 አመት ዘግይቶም ቢሆን ማወቅ ቻሉ፡፡ እስራኤልን ለፖለቲካ ፍላጎታቸው መሳሪያነት ተጠቅመው የዓረቡ ዓለም ጠንካራ ኃይል ሆኖ እንዳይወጣ እያደረጉ መሆኑን አስተዋሉ፡፡ በጉዳዩ ላይ ህብረት ፈጥረውም መከሩ፡፡ ትልቅ ዉሳኔም ላይ ደረሱ፡፡ በከፍተኛ መጠን እየፈለቀ ያለውን የተፈጥሮ ነዳጅ እንደመሳሪያ ለመጠቀም ተስማሙ:: የገልፍ ሀገራትን ጨምሮ የዘይት አምራች ሀገራት ኦፔከ የተሰኘ ድርጅት መሰረቱ፡፡ የድርጅቱ ዓላማ ነዳጅን በራሳቸው ዉሳኔና ቁጥጥር ስር ማዋል ነበር፡፡ ዉሳኔው ትልቅ አማራጭ ነዉ፡፡ ለረዥም ዘመናት በቅኝ ግዛት ፖሊሲ የዓረቡ ዓለም ጀግንነትና በራስ የመተማመን መንፈስ ተሰልቧል፡፡ የኦፔክ ምስረታና ዉሳኔ ምዕራቡን ዓለም እግር ከወርች አሰረ፡፡ #በአሜሪካ_የቤት_መኪኖች_በነዳጅ_እጦት_በፈረስ_ተጎትተው_ወደ_ማረፊያቸው_ተወሰዱ፡ : በወቅቱ መሪ ለነበረው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ኒክሶን ከባድ ቁጣ የፈጠረ አደጋም ነበር፡፡ ኒከሶን ሳኡዲ ዓረቢያን ጨምሮ ብዙ የዓረብ ሀገሮችን ለመዉረር ዉሳኔ ላይ ደረሰ፡፡ ይሁን እንጂ በአሜሪካ የዉጪ ጉዳይ ፖሊሲና የደህንነት እሳቤ ላይ ቀዳሚ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነው ሄንሪ ኪሲንጀር አንዳች ዲፕሎማሲያዊ ቁማር መጫወት እንደሚችል ኒከሶንን አሳምኖ ከሳኡዲ ዓረቢያ ቤተ መንግስት አቀና፡፡ የወቅቱ ገዢ ከነበረው ንጉስ ፈይሰል ጋም ረዥም ሰዓታት የፈጀ ዉይይት አደረገ፡፡በዛ በዚህ ብሎ ፈይሰልን አሳመነ፡፡ የአፍ የማሳመን ጦርነቱንም የአሜሪካን ዓላማ በሚያሳካ መልኩ ቀመረ፡፡ ኪሲንጀር ስልቱ ተሳካለት፡፡ ኒከሶን ያቀደው ወረራም ሳይሳካ ቀረ፡፡ በተቃራኒው #ሳዑዲ_ዓረቢያ_ከዓረቡ_ዓለም_ጋር_የነበራትን_ህብረት_አፍርሳ_የአሜሪካ_ወዳጅ_ሆነች፡፡ በስምምነቱ አሜሪካ ከፍተኛ ድል አግኝታለች፡፡ ከፈይሰል ጋር በነበረው ዉይይት ነዳጅን በአሜረካ ዶላር ብቻ ለመሸጥ ተስማሙ:: ለሙስሊሙ ዓለም ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም ከባድ ቀውስ የፈጠረ ስምምነት ሆነ፡፡ የፔትሮ ዶላር መፈጠርም እውን ሆነ፡፡ የዓረቡ ዓለም ከባዱ ኪሳራ የሚጀምረው እንግዲህ ከዚህ በኋላ ነው፡፡ ለወዲያው ነዳጅ አምራች አረቦች ከፍተኛ ገንዘብ ማጋበስ ቻሉ፡፡ የፖለቲካና የአስተሳሰብ የበላይነታቸውን ግን ፍፁም አሳልፈው ሰጡ፡፡ዛሬ ድረስ አሜሪካ አለምን የምትቆጣጠረዉ የአለም 60% ኢኮኖሚ በእጇ ስለሆነ ነዉ የኢኮኖሚዋ ማደለቢያ ከሳዉዲ አረብያ ነዳጅ ትርፍ ያገኘችዉ ከእሷ በዶላር ገዝታ ለአለም በዶላር ስትሸጥ ዶላር አሁን ድረስ የአለም መገበበያያ ሆነ እነዚህ ከላይ ከጠቆምናቸው ምሳሌዎች ሁለት ቁልፍ ሚስጢሮች ይገልጡልናል፡፡ ➊. የእስራኤል ምስረታ ኃይማኖታዊ ሳይሆን ኢምፔሪያል ፖሊሲ (በአካባቢው የምዕራቡን ዓለም ፍላጎት ለማስፈጸም የሚያስችል መሳሪያ በማስፈለጉ የተፈጠረ ነዉ)!!!!!!!! ➋. በዓረቦችና በእስራኤል መሃል የሚፈጠሩ ጦርነቶች የሙስሊሙ ዓለም የሽብር ባህሪ ዉጤት ነው ብሎ ዓለምን ለማሳመን የሚያስችል የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ ለማድረግ ነው!!!!!   #የአይሁድ_በአሜሪካ_ላይ_ተጽእኖ_ፈጣሪነት ዛሬ ድረስ አሜሪካ እና እስራኤል የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸዉ፡፡እስራኤል ስትነካ አሜሪካ የተነካች ያህል አሜሪካ እስራኤልን በጦር በዲፕሎማሲ ከእስራኤል ጎን ስትሆን እናያታለን ለምን ይሆን ምክንያቱ?? እስኪ ከታች ያለዉን ምክንያት ያንብቡ ሳይሞር ሌስት እና ኢራፕ የተባሉት አሜሪካውያን ፀሀፊዎች እንደገለፁት አይሁዳውያን በአሜሪካ 3%ብቻ ናቸው:: 50% ከነሱ የተማሩ የተከበሩ 200 አሜሪካውያን ተብለው ባለፉት 40 ዓመታት ተሰይመዋል፡፡ ♦️ 20% ከነሱ በአሜሪካ በሚገኙት ዩኒቨርስቲዎች መምህራን ናቸው:: ♦️ በአሜሪካ ካሉት ኩባንያዎች የህግ አማካሪዎች በተለይ በኒዮርክ እና በዋሺንግተን 40% አይሁዶች ናቸው:: ♦️በአሜሪካ ታዋቂ እና ታላላቅ ፊልም አዘጋጆች በገበያም ትልቅ ገቢን ያካበቱ 59% አይሁዶች ናቸው:: ♦️ በአሜሪካ የፊልምና የስነ ፁሁፍ ታዋቂ አዘጋጆች 58% አይሁዶች ናቸው:: ♦️ በአሜሪካ ከ6ሺ በላይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከ 1600 በላይ በየቀኑ የሚታተሙ ጋዜጦች በብዛት በባለቤትነት የያዙት አይሁዶች ናቸው:: እነኚህን ሚዲያዎች በአሜሪካ የፓርላማው፣ የሲ አይ ኤ ፣ የመከላከያው ምላስ ሆነው ይገኛሉ፡፡ #በአሜሪካ_ታዋቂ_ጋዜጦች_ለምሳሌ >> ኒውዮርክ ታይምስ ፥ >> ዋሽንግተን ፖስት፣ >> ዎል እስትሬት ጆርናል ባለቤቶቻቸው አይሁዶች ናቸው፡፡ ✔ ጥቁሮች በአሜሪካ ብዛታቸው 33 ሚሊየን ደርሶዋል ሆኖም አንድ ሴናተር ብቻ ነው ያላቸው፡፡ 3% የሆኑት አይሁዶች ግን 17 ሴናተሮች አሉዋቸው::ቁጥራቸው አናሳ ቢሆንም ተፅእኖ የመፍጠር አቅማቸው ከፍተኛ ነው:: ✔ 15% ከፍተኛ ስልጣንንን የያዙት እነዚሁ አይሁዶች ናቸው፡፡ 17% መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚመሩትም ጭምር፡፡ ✔ በአሜሪካ 25% ታዋቂ ፁሁፎችም ሆኑ ስርጭታቸው በአይሁዶች እጅ ነው ያለው:፡ 3% የሚሆኑት አይሁዶች ከአሜሪካ ህዝብ ግማሽ ቢሊየነሮች ተብለው ይቆጠራሉ፡፡ ✔ የአሜሪካ ኩባንያዎችም የአከሲዮን ንብረት የነሱ ነው፡፡ ✔ ከታላላቅ የቴሌቪዥን ኩባንያዎች በአሜሪካ ሶስቱ የአይሁዶች ናቸው፡፡ ✔ ከታላላቅ የሲኒማ ኩባንያዎች አራቱ የአይሁዶች ሲሆኑ ✔ታላላቅ የመፅሄት እና የጋዜጣ ስርጭቶች በአይሁዶች እጅ ይገኛል፡፡ የአሜሪካ ፓርላማም ሆነ ኋይት ሀውስ የፖለቲካ ውሳኔ ለመስጠት የአይሁዶችን ፍቃድ የሚጠይቅ መሆኑን እናያለን፡፡ ቁልፍ ቦታ ላይ ያሉ ባለስልጣናት አይሁዶች ናቸዉ እናም አሜሪካ ማለት የእስራኤልን ፓሊሲ አስፈፃሚ ናቸዉ ማለት ነዉ በቀጣይ ክፍል አረቦች እስራኤል ካስረከቡ ቡሀላ ምዕራባዉያንና እስራኤል ምን ያህል የጦር ጥቃት እንዳደረሱባቸዉ እናያለን #ክፍል ➏ ይቀጥላል...... ለአስተያየት🔽 T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot join👇👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group
Show all...
አሜሪካ በሁለቱም የዓለም ጦርነቶች ባደረገቻቸው ተሳትፎዎች ሁለቱም ጦርነቶች ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል፡፡ የዚህ አስረጂ እንዲህ ነው፡፡ ሁለቱም ጦርነቶች በዋናነት የአዉሮፓዊያን ጦርነቶች ናቸው:: አሜሪካ እንደሶስተኛ ወገን ዳኛ ሆና እንድትቀርብ ነበር የተፈለገው:: የመጀመሪያው ጦርነት ላይ በቀጥታ እርዳታዋን በማግኘታቸው እንግሊዝና አጋሮቿ ለድል በቅተዋል፡፡ በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ደግሞ ራሷን ወደ ኃያልነት ጎራ ማሳደግ ችላለች፡፡ ዛሬም ስለመካለኛው ምስራቅ ቀውስ ወይም ስለእየሩሳሌም ከተማ ቅድስና የሚሰማንን ስናስብ ማስተዋል የሚገቡን ጉዳዮች አሉ፡፡ ከተማዋ የሶስት ታላላቅ ኃይማኖቶች ማዕከል ናት፡፡ ይሁን እንጂ ከሙስሊሞች አስተዳደር ተወስዳ ወደ አይሁዶች መንግስት እንድትገባ በተደረገውና በሚደረገው ጥረት ላይ በዓለም ያሉ አይሁዶች፣ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች አመለካት ብዙ ያልጠሩ መረጃዎችን ያማከሉ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል፡፡ በቅርቡ ዶናልድ ትራምፕ እየሩስአሌም የአይሁዶች ከተማ እንድትሆን የነበረውን አቋም ሲናገር ብዙ ከርስቲያኖች ደግፈዉታል፡፡ እውን ሊደግፉት ይገባ ነበር? የምናየው ዓለም ብዙ ያልተነገሩ ታሪኮች ዉጤት ሆኗል፡፡ ከእውነቱ ይልቅ ፖለቲካዊ ፈጠራዎች በዓለም ማህበረሰብ ላይ ፍጹም እውነት መስለው ቀርበዋል፡፡ በእየሩሳሌም አስተዳደር ሙስሊሞች፣ አይሁዶችና ክርስቲያኖች በአንድነት በየራሳቸው ቅዱስ መንደሮች እንደየእምነቶቻቸው ይኖሩ የነበረው ሙስሊሞች ባስተዳደሩባቸው ዘመናት እንደነበር ብዙ ማሳያዎች ማቅረብ ይቻላል፡፡ በሌላም በኩል ዛሬ የተመሰረተው የአይሁዶች ከተማ ከሙስሊሞች በመነጠቁ አብዛኛው የዓለም (አይሁድና ክርስቲያን) ማህበረሰብ ከተማዋ ከአህዛቦች ነፃ እንደወጣች ያስባሉ፡፡ ሙስሊሞች በተለይ ከ1970ዎቹ ወዲህ በዓለም የተሳሉበት ሁኔታ አሉታዊ ጭብጥ ያዘለ በመሆኑ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች በየቀኑ ያላቸው ጥላቻ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ኢስላሞፎቢያ የተሰኘ አመለካከትም ተወልዷል፡፡ ከ9ኛው ክፍለ ዘመን ማበቂያ ጀምሮ አንቲሴሜቲዝም የተሰኘ አይሁዶችን የመጥላት አባዜ ተፈጥሮ እንደነበረው ይኼው ከአንድ ክፍለ ዘመን በኋላ አስተሳሰቡ በሙስሊሞች ላይ አማከለ፡፡ ባንፃሩ ከዚያው ከ1970 በኋላ የክርስቲያን መብትና በእግዚያብሄር የተመረጠ ህዝብ የሚል አስተሳሰብ በአሜረካ ወንጌላዊ ጽዮናዊያን ተጀመረ። በሙስሊሞች ላይ የተወለደውን ጥላቻ ጣሪያ ለማስነካት የነዚህ ቡድኖች ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው፡፡ በእስልምና የ14 ክፍለ ዘመን ታሪክ ያልታየ ፕሮፖጋንዳ በሰፈው ተሰራጨ:: ዛሬ ያለውን በሙስሊሙና የክርስትና ሀገራት መሃል የተፈጠረ የግንኙነት መሻከር ምን እንዳመጣው ለማወቅ የምናነሳቸው ጉዳዮች ቢኖሩም ከ1970ዎቹ ወዲህ የምዕራቡ ዓለም ኃያል ሀገራት የተከተሉትን የዉጪ ጉዳይ ፖሊሲ ተከትሎ የተፈጠሩ የሚዲያና የአስተሳሰብ ተዛንፎሾች ማየት ቁልፍ ሚስጢሮችን ይገልጣል፡፡ ወደ ኋለኛው ምዕራፎቻችን የምናያቸው ተጨባጭ ማሳያዎች ስላሉን ይህም ጥናት የሚሰጠው ጠቃሚ መረጃ ይኖራል፡፡ የእስራኤል ምስረታም ሆነ የእየሩሳሌም ዉሳኔ ፍፁም ከኃይማኖት ፍላጎት ዉጪ መሆኑን ባጭሩ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡ ምከኒያታችን አንድ ነው፡፡ አንድ አይና (አክራሪ የአንድ ክንፍ) አመለካከቶች በስፋት ከተስፋፉበት ዘመን ላይ እንደመሆናችን ያልተነገሩ ሌላኛ ከንፎችን ማሳየት የሚኖረውን ዋጋ ማሰብ አይከብድም፡፡ እስራላዊ ፕሮፌሰር አቪ ሽሌይም እንዳሉት“የእስራኤል ምስረታ የእንግሊዝ ኢምፓየር የሀኛው ክፍለ ዘመን ፍጹም ስኬታማ የዉጪ ጉዳይ ፖሊሲ ዉጤት ነው፤ በሌላ በኩል የአይሁዶችን የቆየ ዓላማቸውን የማሳመን ኪሂሎትም ማሳያ ነው፡፡" ብለዋል፡፡ በቀጣይ ክፍል #አሜሪካ_ለምን_እስራኤልን_ለፓለቲካዋ_መጠቀም_ፈለገች??? በኢዝኒላህ ነገ ይጠብቁኝ... #ክፍል ➎ ይቀጥላል...... ለአስተያየት🔽 T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot join👇👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group
Show all...
🔰 #እየሩስ_አሌምን_ለገና_ስጦታ_አድርስልኝ 🔰                 #ክፍል ☞አራት 4⃣                  ✍ አሚር ሰይድ #የአይሁድ_ፅዮናዊነትና_የእንግሊዝ_ድጋፍ አይሁዶችን ከእንግሊዝ ጎን ማድረግ ቀላል አይሆንም፡፡ በወቅቱ አይሁዶች የጀርመን ደጋፊዎች ናቸው:: ሌላው ቀርቶ ዋናው የፅዮናዊያን ቢሮ የሚገኘው በርሊን ነው:: አሸከናዚ ተብለው የሚታወቁት አይሁዶች ጀርመናዊያን ናቸው፡፡ ስለዚህ በሁሉም መስክ የእንግሊዝ ወዳጅ የሚሆኑበት ምክኒያት የለም፡፡ ይህን ግን እንግሊዝ ልትቀበለው አልፈቀደችም፡፡ በተዓምርም ቢሆን አይሁዶች ለእንግሊዝ ጥሩ ስሜት እንዲይዙ መደረግ አለበት፡፡ በተለይ ዴቪድ ሊዮድ ጆርጅ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከሆነ በኋላ ጦርነቱን በፍጥነት ማሸነፍ ስለሚችልበት ዘዴ ነበር የሚያሰላስለው፡፡ አይሁዶች ከጀርመን ጋር ይበልጥ ቁርኝት ስላላቸው ደጋፊዎቹ ለማድረግ ፈታኝ ሆነበት፡፡ ስለዚህ በቀላል ፕሮፖጋንዳ ማሳመን አይችልም፡፡ በወቅቱ የላቀ አመለካከትና አስተሳሰብ የነበራቸው አይሁዶች የዘር ግንዳቸው አካል ከሆነችው ጀርመን ተነጥለው ለጠላት ያብራሉ ማለት ከባድ ነው፡፡ ከብዙ አጢኖት በኋላ አይሁዶችን አብዝቶ የሚያስጨንቃቸው ጉዳይ ተገኘ፡፡ በ1897 ኸርዝል የተባለ አይሁድ በዓለም የተሰደዱ የአይሁድ ዜጎች በአንድነት ከሁለት ሺህ አመታት በፊት ከተሰደዱበት ጥንታዊ መኖሪያቸው እንዲሰባሰቡ የሚያነቃቃ ጥራዝ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ ይህን ተከትሎም በአዉሮፓ ከፍተኛ የሆነ የአይሁድ ፅዮናዊያን ንቅናቄ የተሰኘ እንቅስቃሴ ይታወቃል፡፡ ከአዉሮፓ ወደ ፍልስጤም የሚደረግ ከፍተኛ ስደትም ተመዝግቧል፡፡ በርካታ አይሁዶች በበርሊን ዓላማቸውን ለማሳካት ተግተው እየሰሩ መሆኑም ለእንግሊዝ ራስ ምታት ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው፡፡ ነገሩን ለማጤን የሚያስችል ሌላ ከስተት ተፈጠረ፡፡ #ቸይም_ሀይዝማን_የተባለ_ሳይንቲስቲት_አሞኒያን_በመጠቀም_አሴቶን_የተባለ_ኬሚካል_ፈለሰፈ፡፡ አሴቶን ለቦምብ ማምረቻ ይዉላል፡፡ እንግሊዝ ኬሚካሉን እጅግ ትፈልገው ነበር፡፡ ጦርነቱ በታሪክ የመጀመሪያው የኬሚካል ጦር መሳሪያዎች ለዉጊያ ተግባር አገልግለውበታል፡፡ ሀይዝማን የታወቀ የአይሁድ ጽዮናዊያን ንቅናቄ ተሳታፊ ነበር፡፡ የራሺያ አይሁድ ነው፡፡ በራሺያ አይሁዶችን በማስተባበር ወደ ፅዮን (እየሩሳሌም) ሄደው እንዲሰፍሩ የሚደረገውን ጥረት ሲያስተባብር ቆይቷል፡፡ ሳይንቲስትነቱ ለንደን ከመጣ በኋላ ብዙ ስራዎች ሰርቷል፡፡ አሴቶንን በመፍጠሩም የኖቤል ተሸላሚ ሆኗል፡፡ አይሁዶች ወደ ፍልስጤም ምድር የሚያደርጉትን የገፍ ጉዞ የሚያግዛቸው ወይም ፅዮናዊነትን የሚደግፍላቸው አጋር ይፈልጉ ነበር፡፡ ቸይም ሀይዝማን ለኬሚካል ግኝቱ ሲባል በእንግሊዝ መንግስት ተፈላጊ ሆነ። ይህም በእንግሊዝ መንግስት ፅዮናዊነትን ድጋፍ ለማስገኘት ወሳኝ አጋጣሚ ነበር፡፡ በእንግሊዝ መንግስትና በፅዮናዊያን መሃል ሚስጢራዊ ድርድሮች እንዲደረጉም ሀይዝማን አስደናቂ ሚና ይጫወት ጀመር፡፡ ፅዮናዊያን በፍልስጤም ምድር የአይሁድ ሀገር ለመፍጠር ያለሙትን እንቅስቃሴ እውን ለማድረግ የእንግሊዝን ድጋፍ ማግኘት ከቻሉ ህልማቸው ከቅዠት ያለፈ እንደሚሆን ያምናሉ፡፡እንግሊዝ በዓለም ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ የዓለም ገዢ ነበረችና በጊዜው፡፡ ይሁን እንጂ ቀደም ብሎ በስካይስ-ፒኮት ስምምነት እንግሊዝ ከፈረንሳይ ጋር የተስማማችው የሚስጢር ሰነድ ስለነበር የፅዮናዊያኑን ፍላጎት በቀላሉ መቀበል ከባድ ነበርና እንግሊዝ ፈረንሳይን ልታማከር ቀጠሮ ያዘች፡፡ ናሆም ሶኮሎቭ የተባለ የፈረንሳይ ዲፕሎማት ጉዳዩን ሊማከር ተመረጠ፡፡ የአይሁድ ፅዮናዊያን የላቀ የአእምሮና የዲፕሎማሲ ልምዳቸው ይታወቃል፡፡ በዉይይታቸው ወቅት አዉሮፓዊያኑን ኃያላን ያምታቱ ሀሳቦችና ሰነድ ላይ የሰፈሩ ቃሎች በመጠቀም መንገዳቸውን ጠረጉ፡፡ #ለምሳሌ በመጀመሪያው ሰነድ ላይ የአይሁድ መንግስት መፍጠር አይልም፡፡ ለአይሁዶች ማረፊያ የሚሆን ብሄራዊ መኖሪያ ቤት እንዲኖር የሚል ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ይኼው ቃል ብሄራዊው መኖሪያ ቤት እንዲባል ሆነ፡፡ የተጨመረችውን አንድ ፊደል ልብ እንበል፤ ብሄራዊና ብሄራዊው በሚሉት ቃላት መሃል ያለው ልዩነት አንድ ነው:: የመጀመሪያው የትኛውም ቦታ ሊሆን ይችላል፤ የትኛውንም አካባቢ ይገልጻል፡፡ አዲስ ሀገር ለመግለፅም ያስኬዳል፡፡ እንግሊዝ ለአይሁዶች መኖሪያ እንዲሆን ኡጋንዳን እንደሀገር መርጣላቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ብሄራዊ መኖሪያ ቤት እንፈልጋለን እስካሉ ድረስ የትኛውም የዓለም ጥግ ላይ ቢኖሩ ያስኬዳል፡፡ ብሄራዊው የሚለውን ቃል ከወሰድን ግን ከዚህ በፊት የሚታወቅ ቦታ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ምን ያህል የተራቀቀ አካሄድ እንደተጠቀሙ የሚነገር ምሳሌ ነው፡፡ ☞ ጀርመንም በሌላ በኩል በፍልስጤም ለአይሁዶች መኖሪያ እንዲኖራቸው እንቅስቃሴ ጀምራ ነበር፡፡ ወሬውን የሰማው ባልፎር ጉዳዩን ለማጣራት ተንቀሳቀሰ፡፡ ሆኖም የጀርመን ደጋፊነት ወዲያው በጦርነቱ ተሸናፊ ስለሆነች ብዙ ሳይራመድ መከነ፡ ፡ በእንግሊዝ ሹማምንት ላይ የተፈጠረው የአይሁዶች ሎቢ ግን የባልፈር አዋጅ እንዲፀድቅ አድርጓል፡፡ አዋጁ እንግሊዝ አይሁዶች በፍልስጤም ምድር እንዲሰፍሩን ድጋፍ የሚሰጥ ነበር፡፡ አዋጁ ከመፅደቁ በፊት በእንግሊዝ ፓርላማ #ሞንቴጊው_የተባለ_አይሁድ_ረቂቁን_አጥብቆ_የተቃወመ_ብቸኛ_አባል_ሆነ፡፡ በታሪከ ዓረቦች (ሙስሊሞች) እና አይሁዶች የተጣሉባቸው ዘመናት እምብዛም ናቸው፡፡ >>>>አሁን እንደሚባለው የአይሁድ መንግስት ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ወደፊት በዓረቦችና አይሁዶች መሀል የከረረ ጥል ይፈጥራል፡፡ ስለዚህ አዋጁ ከቶም መፅደቅ የለበትም የሚል አቋም ወሰደ፡፡ የሰማው ግን አልነበረም፡፡ አስተያየቱ ግን እንዳለው ይኼው የባልፈር አዋጅ ከፀደቀበት አመት ጀምሮ ዛሬ ድረስ በዓረቦችና እስራኤል መሃል እጅግ የከረረ ጦርነት መፈጠሩ ነው:: #የባልፈር_አዋጅ እንዲፀድቅ እንግሊዝ ድጋፍ የሰጠተችባቸው አብይ ምክኒያቶች:- ➊ አሜሪካንን ወደ ዓለም ጦርነቱ ለማስገባት የአይሁዶችን የሎቢ ሚና ለመጠቀም፡፡ በወቅቱ ከፍተኛ ቁጥር የነበራቸው አይሁዶች የሚኖሩት በፍልስጤም አይደለም፡፡ በአሜሪካ ኒዮርክ ነው፡፡ በአሜሪካ አጠቃላይ የዉጪ ጉዳይም ሆነ የዉስጥ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም ስለነበራቸው እንግሊዝ ለአይሁዶች በምትዉለው ዉለታና ድጋፍ መጠን እሷም ከነሱ የምትፈልገውን አጀንዳ ለማሳለጥ በማሰብ ነው፡፡ ➋ አሴቶን የተሰኘውን የቦምብ ጥሬ እቃ ያገኘው ሳይንቲስት ምርቱን ለእንግሊዝ ጥቅም እንዲዉል ስለማድረግ ሲጠየቅ በፍልስጤም የአይሁድ መንግስት እንዲኖር ድጋፍ መፈለጉን አብከሮ በመግለፁ ለዚህ ሳይንሳዊ ግኝት ጠቀሜታ ስትል የከፈለችው ዋጋ ነው፡፡ የአይሁድ መንግስት ፍልስጤም ላይ እንዲፈጠር የሚፈልጉ የክርስቲያን ዕዮናዊያን ንቅናቄ ቀደም ብሎ ተፈጣሮ ነበር:: በርካታ የወንጌል ሚሲዮናዊያን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ከበፊቱ በላቀ ቁጥር በመጓዝ አይሁዶችን መደገፍ ቀጠሉ፡፡ ይህን ለማድረግ የራሳቸው ኃይማኖታዊ ምክኒያት ነበራቸው፡፡ ዛሬም ድረስ በመካከለኛው ምስራቅ ታላቁ ጦርነት ወይም አርማጌዶን የሚሉት ጦር እንዲመጣ የሚፈልጉ አክራሪ ወንጌላዊያን ናቸው::👇👇👇
Show all...
ይህ በአንድ ቤተሰብ መሃል የተፈጠረ የስልጣን ጥም የሙስሊሙ ዑማ ላይ ያሳደረው ጠባሳ ቀላል አይደለም፡፡ ዛሬ ድረስ አካባቢው በፈታኝ ቀውስ ውስጥ እንዲገባ ካደረጉ ምክኒያቶች አንዱ ነው:: በእንግሊዝ እከፋፋይነት ሶስቱ የቤተሰብ አባላት እየተቆረሰ የተሰጣቸውን የዓረብ መሬት ማስተዳደር ጀመሩ፡፡ በዚህ ልባቸው ረጋ፡፡ ሀሴት አደረጉ፡፡ ለነሱ ያገኙት በረከት የቋመጡለት ዓላማ ቢሆንም ለእንግሊዝ ግን ጊዜያዊ ስጦታ መሆኑን ታዉቋለች:: ከሶስቱ ቀጠናዎች በተለይ ሂጃዝ በሀሺማይቶች መያዝ እንደማይኖርበት አስምራለች፡፡ የሀሺማይት ነገዶች ከነብዩ (ሰዐወ) የዘር ግንድ ጋር ትስስር ስላላቸው የሙስሊሙ ዓለም አመራራቸውን ሊቀበል ይችላል:: መሪዎቹ እንግሊዝ ቃሏን እርግጥ ሆኗል፡፡ ስለዚህ መካና መዲናን የሚያጠቃለው የሂጃዝ ዓረቢያ ፍጹም ከሀሺም ነገዶች ቁጥጥር ዉጪ መሆን እንዳለበት አስምራ መስራት ጀምራለች:: የዒብን ስዑድ ቤተሰብ የአረብ መንግስት ፈጠራ ለዚህ አላማ የታለመ የእንግሊዝ ስራ ነዉ፡፡ ዓረብያ በሁለት ፍፁም የማይግባቡ መንግስት እንድትከፈል የእንግሊዝ የስለላ መረቧ የተለየ ተፅእኖ ፈጥረዋል፡፡ ቀጠናው ለአመራር አስቸጋሪነት ባላቸው ጎሳዎች የታጨቀ መሆኑ ለጥቃት እንዲያመች ቢያደርገውም ለዘመናት በኢስላማዊ ኺላፋ በአንድነት መኖሩ ይታወቃል፡ ፡ ከእንግሊዝ መምጣት በኋላ ግን ያ የረዥም ዘመን አንድነት ዉሀበ ላይ እንደተጣለ ጨው ሟሙቷል:: የዛሬ መቶ አመት መለስ ብለው አካባቢውን ላጠና ሰው ቀጠናው ዓረብ የሚለውን የአካባቢ ስያሜ አያገኝም፡፡ መካከለኛው ምስራቅ፣ ዓረቢያ፣ ☞ዒራቅ፣ ☞ ስዑድ ዓረቢያና መሰል ስያሜዎች ከመቶ አመት ወዲህ የተፈጠሩ ስያሜዎች ናቸው:: ለዚህ ከስተት መጉላት ታዲያ ከሀሺማዊ መንግስት ጋር የተናቆረችው እንግሊዝ ሌላ የዓረብ ጠላት በመፍጠር አንዱ በሌላኛው ላይ ጦር እንዲያነሳ ማድረጓ ነው:: የኢብን ስዑድ መንግስትን በጦር፣ በማቴሪያልና በገንዘብ ከፍተኛ ድጋፍ አደረገችለት፡፡ ይህም ዓረቦች ጆሮ እንዳይደርስ በከፍተኛ ሚስጢር ተፈፀመ፡፡ ልብ እንበል ወራሪውም ሆነ ተወራሪው የዓረብ ቀጠና ከአንድ ሀገር ድጋፍ የተደረገላቸው ናቸው፡፡ በ1924 ሸሪፍ ሀሴን ራሱን የሂጃዝ ኸሊፋ ብሎ ሰየመ፡፡ ቀደም ብሎ ከ7 አመት በፊት ራሱን ከእንግሊዝ ፈቃድ ዉጪ የአካባቢው ገዢ ለማድረግ በመንቀሳቀሱ የተፈጠረ ቅራኔ እንደነበር አዉስተናል፡፡ ይህኛው የኺላፋ ዉሳኔው ግን አንዳች እርምጃ ለመዉሰድ ወሳኝ ምከኒያት ተደረገ፡፡ ከሌላኛው የዓረብ ግዛት ኃይሉን እንዲያጠናከር በቂ ድጋፍ የተደረገለት የኢብን ስዑድ መንግስት በሸሪፍ ሁሴን ላይ ከባድ ጥቃት አደረገ፡፡ የሀሺማዊ አገዛዝም ከሂጃዝ ምድር እንዲወገድ ሆነ፡፡ ባንፃሩ የኢብን ስዑድ ቤተሰብ የመሰረተው የዳሪያ መንግስት ሂጃዝን ጭምር መቆጣጠር ቻለ፡፡ ሸሪፍ ሁሴን ታላቁን ኺላፋ (ኣቶማን) እንዲወድቅ ለጠላት ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉ ያሰበውን መሪነት እንዳሰበው ሳያላከለት ቀ८::እሱም በእንግሊዝ ተንኮል በራሱ ወገን አረቦች ህልሙ መከነ፡፡ የኢብን ስዑድ ቤተሰብ በዚህ መንገድ በዓረቢያ ከፍተኛ የበላይነት ተጎናፀፈ፡፡ይኼው ዛሬ ድረስ ይኼው ዘዉዳዊ መንግስት ቀጠናዉን እየመራ ይገኛል፡፡ ስዑዲ አረቢያ ከተመሰረችበት አመት 1933 ጀምሮ ዛሬ ድረስ ያለዉን የስዑድ አረብያ ታሪክ ልብ ብለን ካጠናን በዓለም ያለዉን የሙስሊም ማህበረሰብ የጎዱ ብዙ ታሪኮች ተፈፅሞ እናያለን፡፡ ይህ ሁሉ ጉዳት በሳዉዲ አረቢያ መንግሰት ከእስልምና አስበልጦ የስልጣን ጥማቸዉ ምክንያት ነዉ፡፡ይሄዉ ዛሬም ድረስ ባለዉ መንግስት ስዑዲ አረቢያ ለሙስሊሞች መከታ ጋሻ መሆን አቅቷት የምዕራባዉያን እቅድ ማስፈፀሚያ ሁናለች፡፡ ከዛም በመቀጠል የስልጣን ጥም ያሰከራቸዉ አረቦች ሶስተኛው የእንግሊዝ ከህደት በዓረቦች ላይ ተደገመ ፍልስጤም ከእስራኤል ምስረታ በፊት ለሶስት አካሎች እንድትሆን ዉሎች ተፈፅመዉባታል፡፡ ➊ በስካይስ ፒኮት ስምምነት መሰረት ፍልስጤም የእንግሊዝ መሬት ናት፧ ➋ በባልፎር ስምምነት መሰረት ደግሞ ለአይሁዶች በስጦታ የምትበረከት ሆናለች፡፡ ➌ ሚከማህንና ሸሪፍ ሁሴን ባደረጉት ስምምነት ደግሞ ፍልስጤም የዓረቢያ ከፍል ሆና ተቆያለች፡፡ ሶስቱም ስምምነቶች በእንግሊዝና በጦርነት ድል ለመጎናጸፍ ያስችሉኛል ካለቻቸው ወገኖች ጋር የተደረጉ ናቸው፡፡ በቀጣይ ክፍል አይሁዳዉያን ለእንግሊዛዉያን ምን ድጋፍ እንዳደረጉና እንደተባበሩ እናያለን.... #ክፍል ➍ ይቀጥላል...... ለአስተያየት🔽 T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot join👇👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group
Show all...
🔰 #እየሩስ_አሌምን_ለገና_ስጦታ_አድርስልኝ 🔰                 #ክፍል ☞ ሶስት 3⃣                  ✍ አሚር ሰይድ #በለንደን_ይደረግ_የነበረው_ፕሮፖጋንዳ_በጣም_ከባድ_ነዉ እየሩስ አሌም ከሰለሀዲን አል አዩብ ድል ቡሀላ ከሙስሊሞች እጅ ተነጥቃ ስለማትታወቅ ይሄ ድል ያደረገ የገነት ነዉ እስከማለት ደርሰዋል..... በለንደን የነበሩ አብያተ ከርስቲያናት ጀነራል አለንቢ ወደ እየሩሳሌም ያደረገውን ወረራ በከፍተኛ ጉጉትና ቅስቅሳ አድምቀውት እንደነበር ይነገራል፡፡ ጦርነቱ የመጨረሻው የመስቀል ጦር ዘመቻ እንደሚሆንም በስፋት ይነሳ ነበር፡፡ ከታላቁ የሙስሊም ሱልጣን ሰልሃዲን አልአዩብ በኋላ እየሩሳሌምን ማሸነፍ የቻለ የአውሮፓ ጦር አልነበረም፡፡ ጀነራል አለንቢ ይህን ያዉቃል፡፡ እየሩሳሌምን በሱ አመራር ከሙስሊሞች መንጠቅ ከቻለ በታሪከ ድፍን የክርስትናው ዓለም ሲያወድሰው እንደሚኖርም ልቡ ያዉቃል፡፡ ቅዱስ ተግባር ለመፈፀሙም በሰማይ ገነት ሽልማት እንደሚያገኝ አይጠራጠርም፡፡ ሙስሊሞችም በተመሳሳይ ዓላማ እንደሚታገሉ ሁሉ የየሩሳሌም ዘመቻ በልዩነት ኃይማኖታዊ ዘይቤ እንዲላበስ ተደርጓል፡፡ በዚህ ሽፋን መሰረት በአዉሮፓ የነበሩ መንግስታትም ለእንግሊዝ የቻሉትን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ሎርድ ጆርጅ አዲስ የተቀየረው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ለአቶማን ሱልጣኔት ፍፁም ጥላቻ የነበረው ነው፡፡ ቱርክ ስለሚባል ቃል ፍፁም መስማት የማይፈልግና በየትኛውም መልኩ ቢሆን ሱልጣኔቱን ለመጣል የሚታሰብን እቅድ ሁሉ የሚደግፍ መሪ ነበር፡፡ ጀነራል አለንቢ ወዲያ ወደሀገሩ ሲመለስ የሚጠብቀውን ህዝብ ስሜት ለማርካትና በመሪዎቹ ቅድስቷን ከተማ ለገና እንዲያደርስ የተሰጠውን ትዕዛዝ ለመፍፀም የሞት ሽረት ትግል ማድረግ ነበረበት፡፡ ለሙስሊሞችም ቢሆን ቁድስ ሶስተኛዋ ቅዱስ ከተማቸው እንደመሆኗ ተመሳሳይ የግዳጅ አቋም መንፈስ ውስጥ ናቸው:: ጦርነቱ እንዲሁ ከዉጪ ሲታይ የኢምፔሪያሊዝም አካል ይምሰል እንጂ እውነቱ ጦርነቱ ኃይማኖታዊ መልክ መኖሩ ነው:: በለንደን ከፍተኛ ደስታ ሲሆን በጦር ግንባር የመካከለኛው ምስራቅም ተመሳሳይ ደስታ ይንፀባረቅ ነበር፡፡ በለንደን ስለመስቀል ጦርነት ሲሰበከ፤ በምስራቅ ግንባር  አረቦቹ ከእንግሊዝ ጎን አብረዉ በሚዋጉበት ግን ወሬው ተደብቋል፡፡ ጀነራል አለንቢ በሳል የጦር መሪ በመሆኑ ዘመቻውን እንደመስቀል ጦርነት እንዲያስቡት ለወታደሮቹ በቀጥታ መናገር አልፈለገም፡፡ #አብዛኞቹ_ወታደሮች_ሙስሊሞች_ነበሩ፡፡ ነገሩን ካስተዋሉት ጦርነቱን በራሱ ላይ እንደሚያዞሩት እርግጥ ነበር፡፡ ስለዚህ የቁድስ ዘመቻ በጀነራሎቹና በክርስቲያን ወታደሮች ዘንድ ቢታወቅም ከጎናቸው ሲዋጉ የነበሩ ሙስሊም ታጋዮች ግን አያዉቁትም ነበር፡፡ #ከአራት_መቶ_ሺህ_በላይ_አረብ_ሙስሊሞች በዚህ እልህ አስጨራሽ ዘመቻ ተካፍለዋል፡፡ ለሙስሊሞች የእየሩሳሌም ዉድቀት እጅግ አሳማሚ የሆነውም በዚህ ነው:: ሙስሊሞች ባለማወቅም በግዳጅም በጦርነቱ ተሳትፈው የከተማዋ ተከላካይ በነበሩ የኦተማን ቱርክ ሙስሊሞች ላይ ተኩሰዋል፡፡ ጦር ከፍተዋል፡፡ የሸሪፍ ሀሴን ልጅ ፋይሰል ኢብን ሁሴን በርካታ የዓረብ ጦር ይዞ ደማስቆን መቆጣጠር ቻለ፡፡ በተመሳሳይ ወዳጅ የሆነቻቸው እንግሊዝ ደግሞ በፍልስጤም የሚገኘውን የቁድስ ግዛት የዛሬዋ እስራኤልን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በጊዜዉ በነበሩ አረቦች ጦር ተጠቅማ ተቆጣጠረች ከዛም ለእስራኤላዊያን ሀገር እንድትሆን ማመቻቸት ጀመረች ፡፡ ስልጣን ፈላጊ ዓረቦች ደማስቆን ይቆጣጠሩ እንጂ ቀደም ብሎ በአዉሮፓ ኃይሎች በተደረገው ስምምነት መሰረት መቀማታቸው የማይቀር ነዉ፡፡ በስካይስ ፒኮት ስምምነት መሰረት ፈረንሳይ ወደ ሶሪያ ዘመቻ ጀመረች፡፡ ዘመቻውን ተከትሎ ዓረቦች ለእንግሊዝ ጉዳዩን አቤት አሉ፡፡ እንግሊዝ ግን ከዓረብ አቤቱታ ይልቅ የፈረንሳይ ጉዳይ ስለበለጠባት ዓረቦችን አፍንጫችሁን ላሱ አለች፡፡ በልቧ ያለው እውነት ይሄ ቢሆንም ፊት ለፊት በቀጥታ ስሜቷን መግለፅ አልፈለገችም: : በዓረብ ምድር ላይ የምትፈልጋቸው ብዙ ጉዳዮች ይቀሯታል፡፡ ዋናው ነገር ነዳጅ ዘይት ነው:: ስለዚህ የመጀመሪያ ቃሏ የነበረውን የሸሪፍሁሴንና ሄንሪ ሚከማህን ስምምነት ብትክድም ወደፊት ነገሩን በለዘብታ ማለፍ ፈለገች፡፡ ይሁን እንጂ በዓረቢያ ላይ ሰፊ የዓረብ መንግስት መመስረት የፈለጉት የሀሺማይት ነገዶች ለዓላማቸው ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ሸሪፍ ሁሴንና ልጁ ፈይሰል በአንድነት በአመፃቸው ቀጠሉ፡፡ የሁለቱም ዓረብ መሪዎች በወጣቱ ሰላይ ቲ.ኢ.ሎረንስ መሪነት ጠንካራ ስልጠና ወስደዋል፡፡ በዚህም የአቶማንን ጦር በከፍተኛ ሁኔታ በማዳካም የአለንቢ ጦር እየሩሳሌምን እንዲቆጣጠር አድርገዋል፡፡ ንጉስ ፈይሰል በተደጋጋሚ ለንደን በማቅናት ቀድመው የፈፀሙትን ስምምነት እንድትጠብቅና ከፈረንሳይ ጥቃት ነፃ እንድታወጣቸው ጠየቀ፡፡ ለንደን ጉዳዩን እሺም እምቢም ሳትል ቆየች፡፡ በሚስጢር ግን ይህን አመፅ ለማስቆም እንዲቻል የራሷን የዓረቢያ ጉዳይ ፖሊሲ ቀረፀች፡፡ የፖሊሲው አብይ ዓላማ የፈይሰልና የሸሪፍ ሁሴንን ጦር ለማስወገድ የሚያስችል ነው፡፡ #አብረው_ለመታገል_የተስማሙትን_ቃል_በአንድ_አመት_ዉስጥ_ነበር_የጣሰችው፡፡ ሸሪፍ ሁሴንም ነገሩን ስላወቀ ምንም ማማከር ሳያስፈልገው ከኦቶማን ድል በኋላ የዓረብ መንግስት መመስረቱን አዉጇል፡፡ ይህ አዋጁ እንግሊዝን እጅግ አበሳጫት፡፡ በተስማማችው ውል መሰረት የዓረብ መንግስት መፈጠሩ የሚጠበቅ ቢሆንም ዉሉን በመጣሷ ግንኙነታቸው አደጋ ዉስጥ ገባ፡፡ ዓረቦችም ቀጣዩን ከባድ ፍልሚያ ብቻቸውን መጋፈጥ ግድ ሆነባቸው:: ከአቶማን ኃይል አንጻር ዓረቦች እዚህ ግባ የሚባል ኃይል የላቸውም፡፡ በዚያ ላይ የሰለጠኑት በእንግሊዝ ነው:: ስለዚህ እንግሊዝ በፈለገችው ቅፅበት ልትጥላቸው ትችላለች፡፡ በዚህ የተነሳ እንግሊዝ በአረብ ሀገሮች መሪዎች ላይ ሁለተኛው የእንግሊዝ ደባ ለማካሄድ አቀደች፡፡ የሂጃዝ ቀጠና በሸሪፍ ሁሴንና በፈይሰል አመራር ለእንግሊዝ በሚጠቅም መልኩ መስመር ይዟል፡፡ ከዚህ በኋላ አያስፈልጉም፡፡ ሆኖም ራሳቸውን የዓረብ መንግስት ብለው በመጥራት ጠንካራ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ማስቆም አለባት፡፡ ያ ካልሆነ እንግሊዝ የምትቋምጥለት የዓረብ ቅኝ ግዛት ሀሳብ አይሳካም፡፡ ስለዚህ መፍትሄውን እንደሚከተለው አሴረች፡፡ ወንድም በወንድሙ ላይ እንዲሉ በሂጃዝ የዓረብ መንግስት ላይ ወረራ የሚያነሳ ሌላ የዓረብ ነገድ ተመረጠ፡፡ ምርጫው የእንግሊዝ ነው:: ቀድመው አብረዋት የተሰለፉ ወዳጆቿን ማስወገድ የግድ መሆኑን ስላመነች በሌላ የሚስጢር ተልዕኮ ጠንካራ የዓረብ ወራሪ መንግስት አደራጀች፡፡ ይህ ታሪክ ብዙ ጊዜ ሙስሊሞች ካልደረሳቸው ሴራ መሃል ነው:: የኢብን ስዑድ ነገድ የሸሪፍ ሁሴንን ሀሺማዊ መንግስት እንዲወር ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ተሰሩ፡፡ ስራዎቹ በጥንቃቄ እስኪፈጸሙ ድረስ የሀሺም ዓረብ መሪዎችን ዝም ለማሰኘት ጊዜያዊ አስተዳደር ተሰጣቸው:: ለሸሪፍ ሁሴን ኢብን ዓሊ የሂጃዝ ቀጠና ያንተ ነው ተባለ፣ ለልጁ ለፈይሰል ደግሞ ከሜሶፖታሚያ ግዛት ተቆርሶ ዒራቅ የሚል ስም የወጣለት የዓረብ መሬት ተሰጠው:: ሌላኛው የሸሪፍ ሁሴን ልጅ ደግሞ ከታላቋ ፍልስጠየም የተወሰነ መሬት ተቆርሶ ተሰጠው የዛሬዋ ጆርዳን ንጉስም ሆነ፡፡👇👇👇
Show all...