cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

@youthforchrist

ወጣቶች የሚንቀሳቀሱ🔥 እሳቶች🔥 የሚያምሩ🌹 አበቦች🌹 የጉልበት💪ባለቤቶች💪ናቸዉ። admin; @Bini_boy ቻናላችንን ተ🀄ላ🀄ሉን @youthforchrist1 FB channel https://m.facebook.com/youthforchrist12/

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
242Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
በፎርጅድ ብር እንዳይሸወዱ እንዴት መለየት እንችላለን ethiopian money change |fake money |addis guday

የቻናላችን ቤተሰብ በመሆን በየጊዜው የምንለቃቸውን ቪዲዮዎች ለማየት ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን subscribe ያድርጉ በመቀጠልም የደውል ምልክቱን አንድ ጊዜ ይጫኑየቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን!!!ethiopian news | addis...

“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።” — ራእይ 5፥9-10 በደሙ #ከነገድ_ሁሉ #ከቋንቋ_ሁሉ #ከህዝብም_ሁሉ በክርስቶስ #ደም_ታጥበህ "ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 2 ቆሮ 5÷17"እንደሚል መጽሐፉ #አዲስ_ማንነት_አግኝተን ለእግዚአብሔር መንግስት ካህናት ከሆንበት ከዛ ክብር ያወረደን ማነው? ወይስ የክርስትና እውነት አልገባንም?ወይስ አንድ የሀይማኖት ተቋም ውስጥ መግባት ስላለብን ብቻ ነው? ክርስትና ስም አይደለም ህይወት ነው ክርስትና የክብር ህይወት ነው ክርስትና ከዘር አስተሳሰብ ወተን ለፍጥረት ሁሉ ምናስብበት ነው ክርስትና የዘላለምን ህይወት ምናስብበት እንጂ ምድር ላይ በሚሰፉን ነገራት ላይ ምናተኩርበት አይደለም ይቅር ይበለን ወዴት እየሄድን ነው?አባቶቻችን ያወረሱን እውነት ይሄ ነው? @Grace_Worship
Show all...
መዝሙር 118 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ናትና። ² ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘላለም እንደ ሆነች የእስራኤል ቤት አሁን ይንገሩ። ³ ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘላለም እንደ ሆነች የአሮን ቤት አሁን ይንገሩ። ⁴ ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘላለም እንደ ሆነች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ አሁን ይንገሩ። ⁵ በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ ሰማኝ አሰፋልኝም።እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል? ⁷ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ እኔም በጠላቶቼ ላይ አያለሁ። ⁸ በሰው ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል። ⁹ በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ ይሻላል። ¹⁰ አሕዛብ ሁሉ ከበቡኝ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤ ¹¹ መክበቡንስ ከበቡኝ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤ ¹² ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ፥ እሳትም በእሾህ ውስጥ እንዲነድድ ነደዱ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው። ¹³ ገፋኸኝ፥ ለመውደቅም ተንገዳገድሁ፤ እግዚአብሔር ግን አገዘኝ። ¹⁴ ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፥ እርሱም መድኃኒት ሆነልኝ። ¹⁵ የእልልታና የመድኃኒት ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው፤ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች። ¹⁶ የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ፤ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች። ¹⁷ አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ። ¹⁸ መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ፤ ለሞት ግን አልሰጠኝም። ¹⁹ የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤ ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ²⁰ ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት፤ ወደ እርስዋ ጻድቃን ይገባሉ። ²¹ ሰምተኸኛልና፥ መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ። ²² ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ²³ ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆነች፥ ለዓይናችንም ድንቅ ናት። ²⁴ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን። ²⁵ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፤ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና። ²⁶ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤ ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ። ²⁷ እግዚአብሔር አምላክ ነው፥ ለእኛም በራልን እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ የበዓሉን መሥዋዕት በገመድ እሰሩት። ²⁸ አንተ አምላኬ ነህ አመሰግንህማለሁ። አንተ አምላኬ ነህ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ሰምተኸኛልና፥ መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ። ²⁹ እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ናትና። @Grace_Worship
Show all...
ሕይወት ተገለጠ በዶ/ር ማሙሻ ፈንታ ተከታታይ የዩሐንስ ወንጌል ትምህርት ነው፡፡ ይህንንም ትምህርት በ @Grace_Worship በተከታታይነት ይዘንላቹ የምንመጣ ይሆናል፡፡ ለሌሎችም እንዲደርስ #Share አድርጉ #መልካም_ትምህርት
Show all...
ስድብስ ሀጢያት አይደለም? ሶፍያ ሽባባው ሰሞኑን በለቀቀችው አገራዊ አንድነት፣እርቅ ፣ ሰላምን የሚሰብክ ዜማ ላይ ብዙ ክርስቲያኖች አስተያየት ሲሰጡ ተመለከትኩ ይህም አስተያየት አስተማሪ ሳይሆን ስድብ ፣ ዘለፋ ለዛውም በክርስቶስ ደም የተሰረዘ ታሪኳን በማምጣት መሳደብ ይሄ ዳግመኛ መዳናችንን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ጉዳይ ነው አጥፍታ ከሆነ እንኳን መምከርን እንጂ ስድብን ምን አመጣው ስለመምከርም ቢሆን ቃሉ እንዲ ነው ሚለው ማቴዎስ 18 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵ ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ ¹⁶ ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤ ¹⁷ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ። አሁን እያረግን ያለው ግን ክርስቲያኒያዊ ባህሪም ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊም አይደለም አንደውም ይበልጥ ልዩነታችንን የሚያርቅ ነው ሚሆነው ስለ ስድብ ቃሉ ብዙ ቦታ ቢናገርም አንድ ክፍል እንመልከት እና ልጨርስ “አሁን ግን እናንተ ደግሞ ቍጣንና ንዴትን ክፋትንም፥ ከአፋችሁም ስድብን የሚያሳፍርንም ንግግር እነዚህን ሁሉ አስወግዱ፤” — ቆላስይስ 3፥8 ሰው ያስተካከልን መስሎን እራሳችን አናጥፋ ተባረኩ እወዳቹሀለው @Grace_Worship
Show all...
Comments – 1
✍ወንጌል በሐዋሪያዎች ተጀምሮ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ በተቀጣጠለ ሁኔታ በመቀጠል ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ወንጌል ማለት የምስራች ማለት ሲሆን ይሄም የምስራች ስለ ልጁ እየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የወንጌል ተናጋሪዎች እውነቱ ገብቶአቸውና እራሳቸውን ለዚህ እውነት ያስገዙ ስለሆኑ በሚናገሩበት ወቅት አብዛኛዎቹ ተደራሲያን እብዶች ፣ መናፍቅ ፣ ሀሰተኛና ሌሎችንም በዚህ ጽሑፌ መግለጽ የሌለብኝን ለነርሱ ስድብ ለእኛ ደሞ በሰማይ አክሊል ሊሆን የሚችልን ነገር ጀባ ይሉናል፡፡ “እብዶች ብንሆን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን፥ ለእናንተ ነው።” 📖 2ኛ ቆሮ 5፥13📖 ✍ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ሲያስር ፣ ሲያሳድድ ብሎም እስጢፋኖስ ተወግሮ ሲሞት ተባባሪ ሆኖ ሲመለከት እብድ ያላሉት ክርስቲያን ሆኖ ክርስቶስን ሲሰብክ ይሄን ስም አወጡለት በጣም የሚገርም ነገር ነው፡፡ 10፤ ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። 📖2 ቆሮንቶስ 12 📖 ✍ስለዚህ በዚህ አሁን በምናልፈው ስድብና ነቀፋ ውስጥ ስናልፍ ደስ ይለናል አብልጠንም እንጠነክራለን፡፡የምንሳደብ ሰዎች ግን ሀጢያቱ መልሶ ይጠምደናል እና እንጠንቀቅ፡፡ ✝የክርስቶስ ወንጌል አለምን ይሸፍናል✝ ❤️ተባረኩ እወዳቹሀለው❤️ @Grace_Worship
Show all...
“በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው፤” — ምሳሌ 27፥15 😁😁😁😁😁😁😁😁😁😁 ምሳሌ 27 ሳነበው እንደ ጅል ሲያስቀኝ ነበር፡፡ ሙሉ ምራፉን እንድታነቡት በጣም አስተማሪ ነው፡፡ @Grace_Worship
Show all...
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ " በሄሰን የሰላም ሽልማት" ያገኙትን 25,000 (ሀያ አምስት ሺህ) ዩሮ ለመልካም ወጣት ማዕከል ግንባታ ለመስጠት ቃል መግባታቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ዛሬ ከሰዓት አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በመገኘት ተረክበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወርሀ ጳጉሜ መልካም ወጣት ለኢትዮጵያ አንድነት 2011 የመዝጊያ ፕሮግራም በሚሊኒየም አዳራሽ ተገኝተው አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በወጣቶች የመልካም ስብዕና ግንባታ ላይ እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀው የኢትዮጵያ ወጣቶችን ለመደገፍ እየሠራ ላለው የላቀ ሥራ እውቅና መስጠታቸው የሚታወስ ነው። @Grace_Worship
Show all...