ch
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
3 632
订阅者
+124 小时
+3977 天
+1 06030 天
帖子存档
አርሲ የሰማዕታት ምድር አሁንም ዕረፍት አላገኘችም  በምስራቅ አርሲ ዞን በመርቲ ወረዳ በፈረቀሳ ቀበሌ በቀን 17/06/2018 ለ18 አጥቢያ  ከአስር ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው በተደጋጋሚ ክርስቲያኖችን በመጨፍጨፍ የሚታወቁት  አክራሪ እስላሞች ብዙ ጥፋትና ውድመት አድርሰዋል። ስምዐ ተዋሕዶ ከአካባቢው ከሞት ያመለጡ ሰዎች የሰጡት መረጃ እንደሚያመለክተው በግምት አስር ሰዓት በጀመረው ግድያ በውል ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸውን ለጊዜው በስም የተለዩት ግን አራት ሰዎች መሆናቸውን እነሱም ሲሳይ ገዛኸኝ፣ታደሰ ገነነ ፣ደሰያለው ዝቄ እና አብቲ ከድር  በመባል የሚታወቁ ኦርቶዶክሳውያን ሰማዕትነት መቀበላቸውን አረጋግጠናል። ጽንፈኛው ቡድን ከግድያው በተጨማሪ ከዚህ በታች በዝርዝር ያስቀመጥናቸውን ክርስቲያኖች ቤት ከነ ሙሉ ንብረት አቃጥለዋል።                1.አልታየ ፀጋዬ                2.እንዳሻው ገነነ                3.ጌታ ወጋየሁ                4.አልማዝ አሰፋ                5.ግርማ ሙሉነህ                6. ኢሳያስ አለሙ                7.አደም እጅጉሁ                 8.ሰይፈ ላቀው                 9. ከበደ ወልዴ                 10. ስንታየሁ ወልዴ                  11. ከተማ አሰፋ እንደረሰን መረጃ ከሆነ የአካባቢው ክርስቲያኖች መከላከያ ከአሁን አሁን ደርሶ ያድነናል ብለው ቢጠብቁም፤ የመንግስት ድጋፍ እንዳለው በሚያሳብቅ ሁኔታ መንገድ ተዘግቶ ምንም እንዳይገባ በማድረግ በአሁኑ ሰዓት ጽንፈኞቹ ከተማው ላይ መትረየስ ማጥመዳቸውን አረጋግጠናል። በዚህ ሳቢያ እስከአሁን የሞቱ ቤተቦቻቸውን አስከሬን ማንሳት እንዳልቻሉ ተናግረዋል። በሌላ በኩል ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ ክርስቲያኖችም ታግተው መወሰዳቸውን ለማወቅ ችለናል። ከግድያው ያመለጡትን አንዳንዶቹን ክርስቲያኖች ደግሞ እግራቸው ወደመራቸው ቦታዎች እየተሰደዱ ነው። ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንመለሳለን። #በሃገራችን_ኢትዮጵያ_እየተፈጸመ_ያለው_የኦርቶዶክሳውያን_እልቂት_የመንግሥት_መዋቅር_የሚያውቀው_የሚደግፈው_ሽፋን_እየሰጠ_የሚያበረታታው_እንጂ_ባልታወቁ_ኃይሎች_የሚፈጸም_ወንጀል_አይደለም ©ስምዓ ተዋሕዶ

ብልፅግና ከየ አቅጣጫው ጦርነት ውስጥ መግባቱን ተከትሎ ሰራዊቱ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ቀጥሏል‼️ በዚህም ሰባት የደቡብ ዕዝ 202ኛ ኮር የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ የነበሩ የሰራዊቱ
+1
ብልፅግና ከየ አቅጣጫው ጦርነት ውስጥ መግባቱን ተከትሎ ሰራዊቱ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ቀጥሏል‼️ በዚህም ሰባት የደቡብ ዕዝ 202ኛ ኮር የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ የነበሩ የሰራዊቱ አባላቶች ህዝባችንን አንወጋም አገራችንንም አናፈርስም በማለት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው አፋብን ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል:: የኮሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብን ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ መ/ር አታሎ ሙሉጌታ የካቲት 18/06/2018ዓ/ም 18/ዐ6/2018 ዓ.ም

የዕድ ውኃ መሀል ከተማ እና በጎይ ቀበሌ ደረቅ ወንዝ አዲሱ ገበያ ላይ ጠላት ሲወቀጥ ውሏል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ የካቲት 18/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ ወረዳ የዕዱውኃ ከተማ መሽጎ የሚገኘው የአገዛዙ ሰራዊት የካቲት 17/2018 ዓ.ም ወደ ጎይ ቀበሌ ደፈጣ ጥሎ በሚጠባበቅበት ሰዓት በወቅቱ መረጃ የደረሳቸው እነ ሞት አይፈሬ የበላይ ትንፋሾች የሽፈራው ግርፎች 64ኛ ክፍለ ጦር አባላት በጎይ ቀበሌ፣ ደርቅ ወንዝ፣ የዕዱውኃ መኃል ከተማ በረንታ ት/ቤተ እና አዲሱ ገብያ ባደረጉት ውጊያ:- 🕳 3(ሶስት) የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ሲወገዱ 🕳 9(ዘጠኝ) የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ መሆናቸው ተረጋግጧል። በሸበል በረንታ የአካባቢውን ነዋሪ ባህል፣ እሴትና ወግ በመጣስ ለሆዱ አድሮ የነበር ሚሊሻ #አቡሽ ሰዋለና ሌሎች በስም ያልጠቀስናቸ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ቅጥረኛ ሚሊሻዎች ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ ሆነው ደብረማርቆስ ሪፈራል ሆሲፒታል መግባታቸውን አረጋግጠናል። የሽፈራው ቀየ መሆኑን ሳያውቁ እንደ እሳት እራቶ እየገቡ አለቁ አዲስ ትውልድ፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ አስተሳሰብ!! የካቲት 18/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

የ12ተኛ ክፍለ ጦር ዙ_23 ተኳሽ ፋኖን ተቀላቀለ ። አስር አለቃ ማሀባው አግማስ አያናው የተባለው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 803 ተኛ ኮር 12ተኛ ክፍለ ጦር ዙ_23 ተኳሽ የነበረው የመከላከያ ሰራዊት
+2
የ12ተኛ  ክፍለ ጦር ዙ_23 ተኳሽ ፋኖን ተቀላቀለ ። አስር አለቃ ማሀባው አግማስ አያናው የተባለው  የሰሜን ምስራቅ  ዕዝ 803 ተኛ ኮር 12ተኛ  ክፍለ ጦር ዙ_23 ተኳሽ የነበረው  የመከላከያ ሰራዊት አባል  በተደጋጋሚ  ከጨፍጫፊው ብልፅግና ስርዓት ጎን ተሰልፎ  ከአፋብን ሀይሎች ጋር በተለዩዪ አውደ ውጊያዎች ሲዋጋ እና በአለቆቹም  ትዛዝም ከሲቪል ዜጎች እስከ ህዝባዊ ተቋማት በዙ-23 ከባድ መሳሪያ ያለ እርህራሄ  እንዲጨፈጭፍና እንዲያወድም ይገደድም እንደነበር ይገልፃል  ። አስር አለቃ ማሀባው መከላከያ ተቋም አሁን ላይ በዘራፊ  እና ባለአዋቂ መሪዎች እጅ መውደቁ  ዜጎች የተለያየ ታልጋ እየተለጠፈባቸው  ገንዘብ ይቀጣሉ ፣ ይታሰራሉ፣ ይደፈራሉ ሀብታቸው እንዲወድም ይደረጋል  ሀገርም አደጋ ላይ ወድቃለች ይህን ክስተት  እያየውና እየሰማው ከተቋሙ ጋር መቀጠልን ትቸ ተቋሙን ለመታገል ወደ ፋኖ መጥቻለሁ ይላል። አስር አለቃ ማሀባው አግማስ  ከመከላከያ ተቋም ወጥቶ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ  (አፋብን ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦርን ተቀላቅሏል ። ክፍለ ጦራችንም አስተማማኝ ዙ-23 ተኳሽ በነፃ አስፈርሟል ። መሳሪያው ከብርሃኑ ጁላ ስለምናገኘው አያሳስበነም ።          ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!! አርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ          የካቲት 18/2018 ዓ/ም

አስረስ ማረ ዳምጤ የአብይ አህመድ አገዛዝ በጎጃም ጃዊ ቀጠና ያሉ ከተሞችን ያለ ምህረት በመደብደብ ላይ ይገኛል። ምንም አይነት ውጊያ በሌለባቸው ትናንሽ ከተሞች ሲቪሊያንን ብቻ ዒላማ ያደረጉ የጀት
+1
አስረስ ማረ ዳምጤ የአብይ አህመድ አገዛዝ በጎጃም ጃዊ ቀጠና ያሉ ከተሞችን ያለ ምህረት በመደብደብ ላይ ይገኛል። ምንም አይነት ውጊያ በሌለባቸው ትናንሽ ከተሞች ሲቪሊያንን ብቻ ዒላማ ያደረጉ የጀት ኤርክራፍት እና የድሮን ድብደባወችን ለቀናት እየፈፀመ ይገኛል። የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም  ሰዋታ፣ ኩንብር፣ ብሔራዊ የሚባሉ ትናንሽ ከተሞች እና አካባቢያቸው ላይ ከጠዋት እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ድብደባወችን ፈፅሟል። አብይ አህመድ ከዩናትድ አረብ ኢምሬት የተበረከቱለትን ቦንቦች እና ሮኬቶች ብቻ ሳይሆን በደርግ ዘመነ መንግስት ከራሽያ የገቡ እስከ 500 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ እንደ ፋብ (FAB) አይነት ቦንቦወችን በብዛት እየጣለ መንደሮችን እያወደመ ነው። አስረስ ማረ ዳምጤ

ዝክር ሰማዕታት የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ነበር። በሸዋ ምድር ላይ ያለው አየር በክብርና በሀዘን ድብልቅ ስሜት የተሞላው። ፀሐይ በድል አድራጊነት ስትወጣ የ7ለ70 ክፍለጦር ዋና መሪ አርበኛ ተስፋዬ ቦጌ ግን ከጠላት ጋር የመጨረሻውን እልህ አስጨራሽ የጨበጣ ውጊያ አድርጎ ወደ ማይቀረው የሰማዕትነት ጉዞ የውንድሞቹን ዬእነ አርበኛ እንዳሻው ጎሽሜ ተከትሎ በበርግቢ ጊወርጊስ ጫፍ ላይ በጃራሞሬ ተራራ ላይ የክብር መስዋዕትነትን ተቀበለ ። ​የጦር መሐንዲሱ ​ተስፋዬ ቦጌ ዝምተኛ ግን እንደ ገደል የሚያስተጋባ የውስጥ ጥንካሬ ያለው ሰው ነበር። በጦር ሜዳ ስትመለከተው የጦር መሐንዲስነቱ ይገለጣል። የጠላትን ስውር ሴራ አስቀድሞ የማንበብ ችሎታው ለጓዶቹ እንደ ጋሻ ነበር። ተስፋዬ ካለ መንገድ አይጠፋም ይባላል። እያንዳንዱን ውጊያ የሚመራው በንዴት ሳይሆን በብልሃት በጭካኔ ሳይሆን ለወገኑ ባለው ጥልቅ ርኅራኄ ነበር። ተስፋዬ ቦጌ ​ለወዳጁ እንደ ማር የጣፈጠ ቅን ለጠላቱ ግን እንደ እሬት የመረረ ራስ ምታት ነበር። ያ የ7ለ70 ክፍለጦር ዋና አዛዥ፣ ዛሬ የዓመት ዝክሩ ሲታሰብ ትላንት በደሙ የፃፈው ታሪክ በጓዶቹ ልብ ወኔና ጀግንነት ቀስቅሶ እንደ ንስር ታድሶ ይኖራል። ​ ያች መራራ ሰዓት ​ያች ቀን መራራ ነበረች። የካቲት 17/2017 ዓ.ም የጥይት ድምፅ ከሸለቆው ማዶ ሲሰማ ተስፋዬ ቦጌ ግንባር ቀደም ነበር። ለአማራ ህዝብ ህልውና መተኪያ የሌላትን አንድ ህይወቴን መስጠት ክብር ነው የሚለው ቃሉ ያደረገው ። ሆኖም ግን ​መሪው ወደቀ ግን አልሞተም። ልክ እንደ ዘር መሬት ውስጥ ተቀበረ እንጂ። ጓዶቹ ስለ ጓድ ወንድም ተስፋዬ ቦጌ ሲያስቡ ሲያለቅሱ በውስጣቸው ግን አንድ ትልቅ እልህ ተወለደ። ያ እልህ የተሰዋለትን ዓላማ ከግብ እናደርሳለን የሚል የቃል ኪዳን መሐላ ነበር። ​ዛሬ የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም አንድ ዓመት ሞላው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የ7ለ70 ክፍለጦር አባላትና አመራሮች በአንድነት ወደ ማይቀርው የነፃነት ጉዟቸው ቃላቸውን በተግባር አፅንተን እየኖርን ነው። ፊታችን ላይ ሀዘን የለም ይልቁንም የአሸናፊነት ወኔ በልባችን ገንብተናል። ​ ​ታጋይ ይሰዋል፣ ትግል ግን ይቀጥላል!!!

የምረት ጥሪውን ተቀብለው ዛሬም እየመጡ ነው ከሁሉም አቅጣጫ በመውጣት 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ .....የካቲት 18/2018 ዓ.ም 1ጀንበሩ ንጉሱ.....
+5
የምረት ጥሪውን ተቀብለው ዛሬም እየመጡ ነው ከሁሉም አቅጣጫ በመውጣት 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ .....የካቲት 18/2018 ዓ.ም 1ጀንበሩ ንጉሱ.......ፓሊስ....ከሰዴ 2 ብርሀን ነገሰ .....ሚሊሻ...ከሞጣ 3 መለሰ ደርቤ..መከላከያ ከ25ኛ ክፍለ ጦር ሲሆን በአማራ ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ ለማስቀረት በቀሪ ጊዜያችን ከህዝባችን ጎን እንሰለፋለን ብለዋል። ( ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም ) አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ትክክለኛ የፊስቡክ መረጃ ያገኛሉ ይወዳጁት!! https://www.facebook.com/share/17DgyenNzP/

የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ እናት ማን ናቸው? የእምዬ እናትኮ ጎጄ ነበሩ አምብብ ወገኔ የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክን እናት በሚመለከት የተለያዩ ሰዎች የተለያዬ ነገር ሲናገሩ ይሰማል። የቁልቢው ልጅ ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ «አጤ ምኒልክ» በሚል ርዕስ አዘጋጅተው በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. ባሳተሙት መጽሐፍ ገጽ 13 ላይ. . . «ብዙ የታሪክ ፀሐፊዎች እንደሚሉት ወይዘሮ እጅጋየሁ ውብና ከደህና ቤተሰብ መወለዳቸውን ይገልፃሉ። የአባታቸውን ስም ግን የሚገልጽ የለም። ለማ አድያሞ ይባላሉ። ይህም ሲተነትኑም አንዳንዶቹ ከጉራጌ አገር የተማረኩ ባሪያ ናቸው ይሏቸዋል። ባርያ ማለት በገንዘብ የሚሸጥ ብቻ ሣይሆን በጦርነት የሚማረክ ሁሉ ባርያ ይባላል። ይህ ሁሉ ይቅርና ዋናው ቁም ነገር ታሪክ መሥራት እንጂ ትውልድ አይደለም። ታላቁ ናፖሊዮን እንደዘመኑ አፃፃፍ ወደላይ የሚቆጠር ዘር አልነበረውምና ታሪኩን የሚጽፈው ፀሐፊ ቀርቦ «የትውልድ ታሪክዎን ከየት ልጀምር?» ቢለው «ያለፈውን ትተህ ከኔ ጀምር አለው እንደሚባለው ነው።» ሲሉ ጽፈዋል። የዐፄ ምኒልክን እናት በሚመለከት ብዙ ሰው ሲጽፍ በአመዛኙ የሚጠቅሰው ወይንም የሚስማማው ከፍ ሲል የቀረበውን የደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞን ትርክት ዋቢ ያደርጋል። ሆኖም ግን ይህ ትርክት ትክክለኛ ታሪክ አይደለም። የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክን እናት በሚመለከ ንጉሰ ነገስቱ በሕይወት ሳሉ የተመዘገበው እውነታ ከዚህ ቀጥሎ የሰፈረውን ይመስላል። “የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ እናት ትክክለኛ ስም እጅጋየሁ ኃይሉ ነው። ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ እንደጻፈው ወይዘሮ እጅጋየሁ ኃይሉ ባርያ አይደሉም። ወይዘሮ እጅጋየሁ ኃይሉ የጎጃም ተወላጅ የጎዛምን ሰው ናቸው። ይህን ታሪክ የሚነግሩን በ1889 ዓ.ም. «የጎጃም ትውልድ በሙሉ ከአባይ እስከ አባይ» በሚል የመዘገቡት አለቃ ተክለ እየሱስ ዋቅጅራ ናቸው። አለቃ ተክለ እየሱ ዋቅጅራ በ1860 ዓ.ም. በዛሬው ወለጋ ክፍለ ሀገር ሆሮ ጉድሩ ቅርብ ከሆነች አልባሳ በሚባል ስፍራ የተወለዱና በንጉሥ ተክለ ሃይማኖት የጎጃም አስተዳደር ዘመን በሰዓሊነትና በጸሓፊነት አገራቸውን ያገለገሉ ስመ ጥር ሊቅ ናቸው። «የጎጃም ትውልድ በሙሉ ከአባይ እስከ አባይ» በሚል ርዕስ ያሰናዱትን የትውልድ መድብል ለመጀመሪያ ጊዜ በ1889 ዓ.ም. ሲጠናቅቁ 11 ዓመታት የፈጀ መረጃ የማሰባሰብ ስራ ሰርተዋል። አለቃ ትክለ እየሱስ የጻፉት የጎጃም ትውልድ መድበል ለህትመት የበቃው ረቂቁ ካዘጋጁት ከ114 ዓመታት በኋላ በ2003 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ አሳታሚነት በግርማ ጌታሁን አዘጋጅነት ነበር። አለቃ ተክለ እየሱ ዋቅጅራ ጽፈውት በግርማ ጌታሁ አዘጋጅተው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ የታተመው የአለቃ መድበል ገጽ 73 ላይ እንደሚታየው የዳግማዊ ምኒልክ እናት ወይዘሮ እጅጋየሁ ኃይሉ ሲሆኑ የትውልድ ክፍለ ሀገራቸው ጎጃም ሲሆኑ ትውልዳቸው ከጎዛምን ነው። አለቃ ተክሌ በጻፉት የጎጃም ትውልድ መድበል መሰረት የዳግማዊ ምኒልክ እናት ወይዘሮ እጅጋየሁ ኃይሉ የጎዛምን 3ኛ ትውልድ የሆነው የተከብጀን የልጅ ልጅ ልጅ ሲሆኑ የሚወለዱት ጎጃም ጎዛምን እነራታ፣ የብራጌ፣ ዳሊገውና የደረት አካባቢ ነው። በነገራችን ላይ እነዚህ የገጠር ቀበሌዎች ደብረ ማርቆስ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ የገበሬ ቀበሌ ማህበራት ናቸው።” የዳግማዊ ምኒልክን እናት ውበትና ቁንጅና በሚመለከት የቁልቢው ልጅ ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ «ወይዘሮ እጅጋየሁ ውብ ናቸው» ሲል የገለጸው ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ። ነፍሱን ይማረውና ድምጻዊ ተስፋዬ ወርቅነህ የወደዳት የጎጃም ቆንጆ «ስዕለ ማርያም» እንደምትመስል የዳሊገው ጊዮርጊሷን ቆንጆ «ዉቢቱ ጎጃሜ» በሚለው ዘፈኑ”አልጋ ላይ ስትጥይ ቀበቶ አስፈትተሽ፣ ማሩኝ ታሰኛለሽ ወንድ ልጅ አስተሽ፤ ሲል ይገልጻታል። የሆነው ሆኖ የወይዘሮ እጅጋየሁ ኃይሉ ሙሉ የቤተሰብ ሀረግ እንደሚከተለው ነው። የጎጃም እነራታ፣ የብራጌ፣ ዳሊገውና የደረት አካባቢ ተወላጅ የሆኑት ተከበጀን ታላቅ ቤትን ወለዱ፤ ታላቅ ቤት ዮሐንስን ወለዱ፤ ዮሐንስ ማሮን ወለዱ፤ ማሮ ኃይሉን ወለዱ፤ ኃይሉ እጅጋየሁን ወለዱ፤ እጅጋየሁ ዳግማዊ ምኒልን ወለዱ። ልብ በሉ ይህ ታሪክ የተመዘገበው ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ በሕይወት እያሉ በ1889 ዓ.ም. ነው። ስለዚህ የዳግማዊ ምኒልክ እናት በተለምዶ እንደሚባለው እጅጋየሁ አድያሞ ሳይሆን እጅጋየሁ ኃይሉ ነው። የትውልድ ሀረጋቸውም ጎጃም ደብረ ማርቆስ ከተማ ዙሪያ ባሉ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ነው። አበበ ኃረገ ወይን

ንጋቱ ገና ነው። በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎና በሸዋ ተራራዎች ላይ የሚንቀሳቀሰው ጭጋግ ገና አልተገፈፈም። በድንጋያማው ገደል አፋፍ ላይ፣ በዝናብ የራሰ የክላሽንኮቭ ጠመንጃውን ደግፎ የቆመው ወጣት ፋ
ንጋቱ ገና ነው። በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎና በሸዋ ተራራዎች ላይ የሚንቀሳቀሰው ጭጋግ ገና አልተገፈፈም። በድንጋያማው ገደል አፋፍ ላይ፣ በዝናብ የራሰ የክላሽንኮቭ ጠመንጃውን ደግፎ የቆመው ወጣት ፋኖ፣ አይኑን ወደ አድማሱ ሰድቧል። ከበስተጀርባው፣ በሸራ ድንኳን ውስጥ አንዲት አነስተኛ የሬዲዮ መገናኛ ብልጭ ድርግም ትላለች። ​የ"ፍኖተ አማራ ሚዲያ ዘጋቢ የሆኑት እነዚያ ብርቱ ድምፆች፣ በዱርና በበረሃው መካከል ሆነው ታሪኩን ለዓለም ለማድረስ ብዕርና ካሜራቸውን እንደ ነፍጥ አንግበዋል። ​ ድምፁ በብርድ ቢንቀጠቀጥም ወኔው ግን እንደ ረመጥ ይፋፋል። "እዚህ የምናየው ተራራና ገደል ብቻ አይደለም፤ እዚህ የምናየው የአማራን የቁርጥ ቀን ልጆች ጽናት ነው። እሳቱ ሲነድ አብረን እንሞቃለን፣ ጥይቱ ሲዘንብ አብረን እንቆማለን። በአራቱም ማዕዘናት፣ ከነዚያ እንደ እሳት በሚፈተኑ ጀግኖች ጋር አብረን እየተዋደቅን፣ የነፃነትን ንጋት እንጠባበቃለን።" ​ዘጋቢው ወደ ካሜራው ጠጋ ብሎ፣ በቁርጠኝነት አይን አይኑን እያየ ንግግሩን ቀጠለ፦ ​"ወገኖቻችን... እኛ እዚህ በግንባር ዋጋ እየከፈልን ቢሆንም፣ የእናንተ ድምፅ ካልታከለበት ትግላችን ጎባጣ ይሆናል። ይህ 'ፍኖተ አማራ' የእናንተም ድምፅ ነው። ሚዲያችን የሁላችሁም የትግል አውድማ እንድትሆን፣ ክንዳችሁን አቀብሉን። እንድናድግ፣ እንድንሰማና የጀግኖቹን ድምፅ በዓለም ዙሪያ እንድናስተጋባ የእናንተ ትብብር ወሳኝ ምዕራፍ ነው። አብራችሁን ቁሙ፣ ከእኛ ጋር ተወዳጁ!"

አንድ ታላቅ አርበኛ ላሰተዋውቃችሁ በርግጥ ታቁት ይሆናል! አማረ ታዘዘ ይባላል የአሳምነው እዝ የአፄ ዘረአይቆብ ኮር የህዝብ ግንኙነት ነው ። በትምርቱም የድግሪ ምሩቅ ነው። እጅግ ሲበዛ ታታሪና ቆራ
አንድ ታላቅ አርበኛ ላሰተዋውቃችሁ በርግጥ ታቁት ይሆናል! አማረ ታዘዘ ይባላል የአሳምነው እዝ የአፄ ዘረአይቆብ ኮር የህዝብ ግንኙነት ነው ። በትምርቱም የድግሪ ምሩቅ ነው። እጅግ ሲበዛ ታታሪና ቆራጥ ጀግናም ነው ብዙ ጀግንነቶችን የፈፀመ ታላቅ አርበኛ ነው ሴራ ቀድሞ የሚገባው እነዛን ሴራዎች እንዴት በብለሀት ማለፍ እንዳለበት ቀደሞ የሚረዳ ጀግና አርበኛ ነው። ይህ አርበኛ አንድ ትልቅ ታሪክ የሰራ ነው ሁለት ልጆቹን አንድ ወንድና ሴት ልጆቹ በአንድ ወቅት በብልፅግና ሰራዊት ታግተው ተወስደው ነበር እነዛ ላይ የሚሳሱ ልጆቹን ወስዶ እንደ ማስፈራሪያ ተጠቅሞበት ነበር ብልፅግና እሱ ግን መልሱ ልጆቼ ከህዝቤ አይበልጡም ነበር የፈለጋችሁን ማድረግ ትችላላችሁ ነበር መልሱ! ቆራጡ አርበኛ የአባቶቹ ልጅነው።እንዲህ ያሉ አርበኛ ያለበት ነው የሸዋ ምድር✊ Amare Tazeze አማረ ታዘዘ አርበኛው በርታ የሸዋው አለኝታ✊

'' በማንነታቸው ታፍነው የሞት ፍርድ የሚጠብቃቸው 4ቱ ጋዜጠኞች! በአስቸኳይ ፍትህ ይሻሉ ተባለ #ሸር በማድረግ አንሸራሽሩት አለም አቀፉ የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው የሞት ወይም የዕድሜ ልክ እስራት ሊፈረድባቸው የሚችሉ አራት ጋዜጠኞች ጉዳይ በግልጽነትና በፍትሃዊነት እንዲታይ ጥሪ አቀረበ። ዛሬ የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ፌብሩዋሪ 24 ቀን 2026) ባወጣው መግለጫ፣ ድርጅቱ በጋዜጠኞቹ ላይ እየተካሄደ ያለው የፍርድ ሂደት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሕግ ጥበቃ እንዲደረግለት አሳስቧል። ለሦስት ዓመታት ገደማ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት አስማማው እና ዳዊት በጋሻው ሲሆኑ፤ የታሰሩትም በአማራ ክልል በነበረው አለመረጋጋት ዙሪያ በሰሩት ዘገባዎች ምክንያት መሆኑን መግለጫው ያስረዳል። "የአማራ ድምፅ"  ጋዜጠኛ የሆነው ጎበዜ ሲሳይ ግንቦት 2015 ዓ.ም በጅቡቲ በቁጥጥር ሥር ውሎ ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ተላልፎ መሰጠቱ የሚታወስ ነው። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም (ፌብሩዋሪ 4 ቀን 2025) ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ማስረጃ ጋዜጠኞቹን የሚያስከስስ ነው ብሎ በመወሰኑ፣ ተከሳሾቹ በመጪው ግንቦት ወር የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ያሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል። የ"ኢትዮ ንቃት" መስራች መስከረም አበራ፣ የ"የኛ ሚዲያ" ዘጋቢ ገነት አስማማው እና የ"አራት ኪሎ" ሚዲያ አዘጋጅ ዳዊት በጋሻው ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዝያ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል። የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) ጋዜጠኞቹ ለረጅም ጊዜ በእስር ላይ መቆየታቸውና የተመሰረተባቸው ክስ ከባድነት በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት እና በፍትህ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ስጋት እንደሚፈጥር ገልጿል። በመሆኑም ባለሥልጣናት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን በማክበር ጋዜጠኞቹ የሚገባቸውን ፍትህ እንዲያገኙ እንዲያደርጉ በጥብቅ አሳስቧል። CPJ Africa - Committee to Protect Journalists

#ለዩንቨርስቲ_ተማሪዎችና_ለሚመለከተው‼️ አሸባሪው የብልፅግና ቡድን በአማራ ህዝብ ላይ ይፋዊ ጦርነት ከፍቶ እንዲሁም የነቁ አማራዎችንና ተወካዬቻችንን በዬ እስር ቤት አጉሮ ምርጫ የሚል ዲስኩር አማራ ምድር ላይ ለማድረግ እንቅስቃሴ የጀመረና በዛሬው ዕለት #ምልምል_የመስክ_አሰልጣኞች ወደ ስልጠና ማስገባቱን ንስር አማራ በደረሳት መረጃ አረጋግጣለች። ሰልጣኞች የተላከላቸው መልዕክት ከታች አስቀምጠነዋል👇 "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአማራ ክልል የመስክ አሰልጣኞች ምልመላ ያለፉ ስለሆነ በ telegram group ላይ ባለው ስልጠና ማእከል ተገኘተው ከየካቲት 17-18 እንድከታተሉ እናሳስባለን። የስልጠና ቦታ የምናሳውቅ የሆናል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ"""" ☝️☝️☝️☝️ #ማሳሰቢያ:- በአማራ ህዝብ ላይ ይፋዊ ጦርነት ተከፍቶብን ባለበት ሰዓት ምርጫ ይካሄዳል ብሎ ማሰብ ዘበት ነውና ይህንን ምርጫ ሂደት ለማሳለጥና ገንዘብ ለማግኘት ብላችሁ ከሽብር ቡድኑ የብልፅግና ተቋማት ተሰልፋችሁ የምትንቀሳቀሱ ወጣቶችና የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ታሪካዊ ተወቃሾች መሆናችሁን እያስገነዘብን ለሚወሰድባችሁ ማንኛውም እርምጃ ኃላፊነት ራሳችሁ እንደምትወስዱ ከወዲሁ እናሳውቃለን‼️ 17/ዐ6/2018 ዓ.ም

ሞተ አሉት እንጅ ጀግናኮ አይሞትም የአማራይቱ ልጅ እጁን አይሰጥም!! 💪💪💪 አርበኛ ማንዴላ የወንዶቹ ወንድ አንዳንተ ጀግና ሽህ ይወለድ። መሀል ላይገብቶ በለው እያለ ያን ባንዳ ሁላ ሲያምሰው ዋ
+1
ሞተ አሉት እንጅ ጀግናኮ አይሞትም የአማራይቱ ልጅ እጁን አይሰጥም!! 💪💪💪 አርበኛ ማንዴላ የወንዶቹ ወንድ አንዳንተ ጀግና ሽህ ይወለድ። መሀል ላይገብቶ በለው እያለ ያን ባንዳ ሁላ ሲያምሰው ዋለ። መሄዱን ይሂድ ጀግና ስስት ነው እሱን ሚተካ አምሳያው ማነው። ይህንም ስላልኩ ሙቷል አትበሉ የጀግና ዘሩ ብዙ ነው በሉ። ሞተ አሉት እንጂ ጀግናኮ አይሞትም የአማራይቱ ልጅ እጁን አይሰጥም!! ክብር ለጀግና ሰማዕታት ጓዶቻችን ይሁን!!🙏🙏🙏

እዚህ ሰፈር እየወጡ በቲክታክ እና facebook ላይ እየወጡ ታጋይ ታጋይ ስለተጫወቱ እና በመሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ስም ስለማሉ ብቻ ታጋይ ይመስሉን የነበሩ ግን መሬት ላይ አንድም ጠብ እሚል ስ
እዚህ ሰፈር እየወጡ በቲክታክ እና facebook ላይ እየወጡ ታጋይ ታጋይ ስለተጫወቱ እና በመሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ስም ስለማሉ ብቻ ታጋይ ይመስሉን የነበሩ ግን መሬት ላይ አንድም ጠብ እሚል ስራ ሰርተው እማያቁ አደናጋሪወች ለጠላት እጅ ሰተዋል። እንደነዚህ አይነት ሌባ እና አደናጋሪ የፋኖ አባላትን መቆጣጠር እሚቻለው ጠንካራ ወታደራዊ መዋቅር በመስራት ጠንካራ መጠይቅ ያለው ተቋም ሲመሰረት ነው። ይሄንን ለማድረግ ድርጅታችን አደረጃጀቶችን ለማዘመን ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ጠናካራ እዝ እና ሰንሰለት ያለው ሰራዊት ለምገንባት ቀን ከሌት እየተጋ ባለበት ሰአት ላይ ቅርብ ወራጆች ወርደዋል። መሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ እንጦጦ ስንደርስም ሚከዳ ይኖራል ብሎ የለ? አበጀ በለው ገርዬ

በቅንነት፣በታማኝነት እና በፅናት አለን በቦታችን‼️ በዚህ ትግል ውስጥ ቅርብ ወራጆችን እያስተዋልን ነው።ቅርብ ወራጅ ድሮም ነበር ፣አሁንም አለ ፣ወደ ፊትም ይኖራል ። "እንጦጦ ስንደርስም የሚከዳ አለ !" አይደል ያለው አብዮታዊው መሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ .... ሽኮኮዎች ለምን ቅርብ ይወርዳሉ? ምን አይነት ሰዎች ናቸው ቅርብ እየወረዱ የሚገኙት? ለሚሉት ቁልፍ ጥያቄዎች መልስ የሚሆኑ የቅርብ ወራጆች ጠባይ መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፦ 1ኛ.ትግሉ የወራት ብቻ እድሜ ያለው የመሰላቸው ግለሰቦች፦አብዮታዊ ትግሉ በአጭር ተቋጭቶ እነሱም የድሉ ተካፋይ ለመሆን በስሜት የተቀላቀሉ ፤ትግል መውጣት መውረድ፣መራብ መጠማት ፣ስሜትን ከፋና ዝቅ የሚያደርግ ተቀያያሪ እንቅስቃሴና ተግባር የሚታይበት በአጠቃላይ የከበረ መሰዕዋትነት የሚከፈልበት መራር መሆኑን በደንብ ያልተገነዘቡ ግለሰቦች ቅርብ ወራጆች ሆነው ይገኛሉ። 2ኛ.አብዮታዊ ትግሉ ነፃ ያወጣቸው ታጋዮች፣መሪዎች፦የአማራው አብዮታዊ ትግል ነፃ ያወጣቸው ታጋዮች እንዲሁም መሪ የሆኑ ግለሰቦች መኖራቸው እሙን ነው ።እነዚህ ግለሰቦች ከቤታቸው ቁጭ ባሉበት ትውልዱ ነፃ አውጥቷቸው የትግሉ አካልና የትግሉ መሪ ያደረጋቸው አሉ።አብዛኞቹ የህልውና ትግሉን በደንብ ተገንዝበው የሚጠበቅባቸውን ታላቅ ሃላፊነት በቆራጥነትና በፅናት እየተወጡ የሚገኙ ሲሆን ጥቂቶች ደግሞ በታሪክ አጋጣሚ ያገኙትን እድል ለአልተገባ ድብቅ አላማና ፍላጎት ሲያውሉ ይገኛሉ።ይህ ከህልውና ትግሉ በተቃራኒ የሚያስሄድ ሴራና ተንኮል ሲነቃባቸው በአጋጣሚ ያገኙትን "የታጋይነት ፥የመሪነት ካባ" ለጠላት መደራደሪያነት እንዲሁም እጅ መነሻነት በመጠቀም ወደ ጠላት ካምፕ ሲገቡ ይታያል። 3ኛ.ታዋቂነት፣ዝና እና አድናቆት በመሻት ብቻ የተቀላቀሉ ግለሰቦች፦በዚህ ውሰጥ የሚገኙ ግለሰቦች በትግሉ ውሰጥ ካደረጉት በላይ እንዲመሰገኑ፣አንዲታወቁ ይፈልጋሉ።ከልክ ያለፈ ክብርና አድናቆት ይሻሉ።የሚፈልጉትን ክብር፣አድናቆት እና ዝና ያጡ የመሰላቸው ወቅት ከትግሉ ገለል ይላል።ለጠላት ርካሽ ፓለቲካ መጠቀሚያ ይሆናሉ። 4ኛ.ትግሉን ለግል ጥቅም ለማዋል የሚፈልጉ ግለሰቦች፦የተሰጣቸውን ታላቅ የህዝብ አደራ ለራስ ጥቅም፣የገንዘብ ማካባቻ እና መዘነጫ ማዋል።ለህዝብ እታገላለሁ እያሉ ህዝብን መዝረፍ፣ማገት እና የራስን ጥቅም ብቻ ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴ ማድረግ።ይህንን አጉል ተግባራቸውን በመረጃ ፣ በማስረጃ በግምገማ ሲገኙ እና ተጠየቅ ሲመጣ ያለምንም ርህራሄ ጥቅማቸው በመነካቱ እየከዱ ወደ ጠላት ካምፕ ይገባል። ............. መታወቅ ያለበት፦ይህ ትግል የአማራ ህዝብ ፥ የህዝባችን ትግል ነው ።አብዮታዊ ትግሉ ሃዲዱን ጠብቆ ከድል ማማ ላይ እንዲደርስ በንስር አይን የሚከታተል፣በቆቅ ንቃት የሚጠብቅ እዩኝ እዩኝ የማይል፣ራሱን ለትግሉ አሳልፎ የሰጠ ንቁ እና ብቁ ያደፈጠ በርካታ ትውልድ አለ።ሚዲያ ካገነነው፣ ከሚታየው እና ከሚታወቀው ቅርብ ወራጅ ከሆኑ የዘመን ሽኮኮዎች በላይ እልፍ ብርቱ ታጋይና መሪዎች አሉ። እንፅና! የፀና ትውልድ የድሉን ዋንጫ በድል አደባባይ ከፍ ያደርጋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ! Hailemichael Bayeh