ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多4 039
订阅者
+6824 小时
+3957 天
+1 39230 天
帖子存档
➧ እኛ ለርስቶቻችን "ለወሰን እና ማንነቶቻችን" እምንታገለዉ በብአዴን - ብልፅግና በፈለገዉ ልክ ሳይሆን እኛ ባቀድነዉ ነዉ፡፡
➧ የህልዉና ትግሉ እና የማንነት ጉዳዮች ለእኛ የማይለያዩ የሳንቲም ገፅታዎቸ ናቸዉ፡፡
ነገሩ አሁን ጥርት እያለ ነው። የታሉ ፋኖዎች? የሚል አጀንዳ ዛሬ ደምቆ እየተሰማ ነው። ዲጂታል ሰራዊቱ ፎርሙላውን ተከትሎ እየሰራ ነው። ከአንድ ምንጭ የሚቀዳላቸውን አጀንዳ የቃላትም ሆነ የስርዓተ ነጥብ ልዩነት ሳያደርጉ መድረኩን እንዲያጠለቀልቁ ታዘዋል። ቅደም ተከተሉ እንዲህ ነው፥
ጠለምት ላይ የህወሀት ሰራዊት እንዲገባ ግብዣ ይደረግለት፥ በራያም የመንግስት ሰራዊት እንዲወጣና ህወሀት እንዲረከበው መንገዱ ይጠረግለት፥ ከዚያም ህወሀት ገደሉን ሳያይ ሳሩን ብቻ አይቶ ሲገባ ጠብቆ ተኩስ ይከፈትበት፥ ይህ ክስተት 'ህወሀት ጦርነት ከፈተ' የሚል ርዕስ ተሰጥቶት ለሚዲያ ሰራዊቱ ይላክለት፥ የሚዲያ ሰራዊቱም ትንፋሽ የሚያሳጣ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በመክፈት አጀንዳውን ከፍ ያድርገው፥ ህዝቡ 'ፋኖ የታለ?' የሚል ጥያቄ እስኪያነሳ ድረስ የህወሀት ወረራ በሚገባ ይራገብ፥ ህዝቡ ጥያቄውን የማያነሳ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ዲጂታል ሰራዊቱ 'ህወሀት ወረራ ከፈተ- የሚለውን ቀነስ አድርጎ ፋኖዎች የታሉ?' የሚል ጥያቄ በየገጾቻቸውና በየዩቲብና ቲክቶክ መድረካቸው በማንሳት ወደ ምንፈልገው መስመር አጀንዳውን ማምጣት አለብን።
.....ይህ ነው - ፎርሙላው። እስከአሁን አልተዛነፈም። ዛሬ ይኸው ጥያቄ በዲጂታል ሰራዊቱ ተነስቶ ''ፋኖን የበላ ጅብ አልጮህ አለ'' እያሉ ነው።
በአጭሩ የፋኖ አፈሙዝ ብልጽግና ላይ አነጣጥሯል። የፋኖ አይኖች ከብልጽግና ላይ ተተክለዋል። በብልጽግና ዜማ የሚደንስ ፋኖ የለም።
#የብልጽግና "#የህልውና_ስጋት" እና #የፋኖን_አንድነት_የመበተን_ስልት
የብልጽግና መንግስት አሁን ያለውን የጦርነት ድባብ የፈለገበት ምክንያት ከድንበር ጥበቃ ባለፈ፣ በቀጥታ የፋኖን መጠናከርና የአንድነት ጉዞ ለማደናቀፍ የታለመ ነው። ትንታኔው በሚከተሉት ቁልፍ ነጥቦች ይጠቃለላል፦
#፩. #የፋኖ_አንድነት የፈጠረው "የመንግስት መውደቅ" ስጋት
በቅርቡ የታየው የፋኖ ዕዞች መጠናከርና ወደ አንድ አመራር የመምጣት ሂደት ለመንግስት ትልቅ ድንጋጤ ፈጥሯል። ፋኖ በክልሉ ያለውን የህዝብ ተቀባይነት ይዞ በአንድነት ከገፋ፣ መንግስትን ከመቀመጫው የመንቀል አቅም እንዳለው ብልጽግና በሚገባ ተረድቷል። ስለዚህ ይህ ኃይል ሳይቀናጅና ወደ መሃል አገር ሳይገፋ ባለበት እንዲገታ ማድረግ የመንግስት ቀዳሚ አጀንዳ ነው።
፪. "#የትብብር_ስጋት" (The Fear of Alliance)
መንግስት በውስጥ በኩል ትልቅ ስጋት አለው፤ ይህም "ፋኖና ህወሃት የጋራ ጠላታቸው ብልጽግና መሆኑን ተረድተው ቢተባበሩስ?" የሚል ነው። ይህ እንዳይሆንና ሁለቱ ኃይሎች በጥርጣሬና በጠላትነት ተፋጥጠው እንዲቀጥሉ፣ ሆን ተብሎ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ የድንበር አካባቢዎችን ክፍት በማድረግ "የማይጠፋ የእሳት ቃጠሎ" በመሃላቸው መለኮስን መርጧል።
፫. #የፋኖን_አንድነት_በሃሳብ_የመከፋፈል_ሴራ (Internal Fragmentation)
ይህ ጦርነት ቢቀሰቀስ መንግስት በፋኖ ውስጥ ሁለት ተቃራኒ ጎራዎች እንዲፈጠሩ ይጠብቃል፦
"#እንዋጋ" የሚለው ወገን፦ የአማራ ህዝብ ለዳግም ወረራ መጋለጥ የለበትም፣ የህልውና ጦርነት ነው በሚል ስሜት ኃይሉን ወደ ድንበር እንዲያፈስ ይገፋፋል።
"#ወጥመድ_ነው_አንግባ" የሚለው ወገን፦ ይህ የመንግስት ሴራ ነው፣ ዋናው ትግላችን አዲስ አበባ ነው በሚል ጦርነቱን የሚሸሽ ጎራ።
#ውጤቱ፦ በእነዚህ ሁለት ሃሳቦች መካከል የሚፈጠር የጦርነት ስትራቴጂ ልዩነት፣ በቅርቡ የተመሰረተውን የፋኖ አንድነት በውይይት ሳይሆን በውዝግብ እንዲበተን ያደርገዋል።
፬. #የፋኖን_የኃይል_ሚዛን_ማስቀየስ
ፋኖ አሁን ባለው ቁመና መንግስትን ለመጣል የሚያስችል ወታደራዊ ዝግጅት ላይ ነው። መንግስት ግን ይህንን ኃይል "ተፈላጊነቱ በድንበር ጥበቃ ላይ ብቻ እንዲሆን" (Regional containment) ይፈልጋል። ፋኖ በድንበር ጦርነት ከተጠመደ፣ የመንግስትን ስልጣን የሚገዳደርበት ጊዜና ኃይል አይኖረውም፤ ይህም ለብልጽግና የትንፋሽ ጊዜ ይሰጠዋል።
#ማጠቃለያ
ብልጽግና ጦርነቱን የፈለገው ፋኖን በወታደራዊ ጥቃት ብቻ ሳይሆን፣ "በአንድነትና በሃሳብ ልዩነት" ለመምታት ነው። የፋኖ አንድነት በመንግስት የጦር መሳሪያ ሳይሆን በመንግስት "ተንኮልና ሴራ" እንዲፈርስ የታለመ ስልታዊ ቁማር ነው።
ሰበር...ከአላማጣ ከተማ ሸሽተው ወደ ቆቦ ከተማ ከገቡት የአገዛዙ ወታደሮች መካከል በርካቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው መኮብለላቸው ተሰማ!
ይሄንን ተከትሎ በቆቦ ከተማ በአንዳአንድ ሰፈሮች ቤት ለቤት ፍተሻ ሲካሄድ አምሽቷል።
ወታደሮቹ ከትናንት ምሽት ጀምሮ እስከ ንጋት ባለው ቆቦ ከተማ ከገቡ በኋላ ነው ደብዛቸው የጠፋው።
ወታደሮቹ ብዛታቸው ከሁለት ጋንታ በላይ እንደሚሆንና ከነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያ ጀምሮ ሙሉ ትጥቃቸውን እንደያዙ ነው የጠፉት።
የወታደሮቹን መጥፋት ተከትሎ በቆቦ ከተማ መግቢያና መውጫ አከባቢዎች ላይ ብርቱ ቁጥጥር እየተደረገ ሲሆን፡ በአንዳንድ የከተማዋ አከባቢዎች ላይ የቤተ ለቤት ፍተሻ ሲደረግ ማምሸቱን ምንጮች ገልፀዋል።
በተጨማሪም በቆቦ ከተማ ወታደሮቹ ሰፍረውባቸው በሚገኙ ካምፖች ተጨማሪ ወታደር እንዳይከዳ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ከዕዝ መምሪያዎች አስቸኳይ ትዕዛዝ ወርዷል።
ከፋኖ ጋር እየተካሄደ በሚገኘው ውጊያ አከርካሪው የተሰበረው መከላከያ ሰራዊቱ፡ ይህን በድል ሳይወጣ ሌላ አዲስ ጦርነት በመጀመሩ ለመማረክ እንኳን እድል እንደማያገኝ ስለተረዳ በተስፋ መቁረጥ ስሜት ተሞልቶ እየተበተነ ይገኛል።
ለአገዛዙ እጅ የሠጠው ፋኖ ተረሸነ‼
ይህ ከዚህ በታች የሚታየው ግለሰብ ሻንበል ውበቴ ( ገደፋየ) የሚባል ሲሆን በበፊቱ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ጉና ክፍለ ጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ ከእነ ልጁ የፋኖ አባል ነበር። እነ በለጠ አንዳርጌ (ቆራጡ) ከቀጠናው ተባረው ወደ እነ እያሱ ሲሄዱ ከእነ ቆራጡም ከብርጌዷም ሳይሆን አውላላ ሜዳ የነበረ ሠው ነው። መጨረሻ ላይ ብርጌዷ ቀጠናውን ከሌባ እና ከሰርጎ ገብ ለማፅዳት እንቅስቃሴ ስታደርግ ወደ እነ ( በለጠ አንዳርጌ ( ቆራጡ ) ይቅርታ ቆራጡ የተባለ ቆርጦ ወደ አገዛዙ ስለሄደ ነው😂 ተቀላቀለ። በመጨረሻም በእነ አያሌው የድለላ ፕሮጀክት ተሳታፊ ሁኖ ከእነ ቆራጡ ጋር ለአገዛዙ እጁን ሠጠ። ልጁ ግን አሁንም በብርጌዷ ስር ይገኛል።
በፎቶው እንደምታዩት ፀዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተሀዲሶ በሚል አገዛዙ ሰብስቧቸው እያለ ለአሚኮ ቃሉን እየሠጠ በነበረበት ሰዓት የተነሳው ፎቶ ነው። አገዛዙ በሚፈልገው መንገድ ፕሮፖጋንዳ አሠርቶታል። ከታሀድሶ በኃላ በእነ በለጠ አንዳርጌ ጥርናፍ እስቴ ወረዳ በሚሊሻነት ተመደበ። በተደጋጋሚ ከፋኖ ጋር ውጊያ ገጥመው ብዙ በፋኖ ሀይሎች የበለጠ አንዳርጌን አጃቢዎች ጨምሮ ተደምስሰዋል።
አገዛዙ ሰሞኑን ፋኖን ለማጥቃት ሰኞ ለማክሰኞ ሌሊት ጉዞ እያደረጉ እያለ " ለፅንፈኛው መረጃ ትሠጣለህ" በማለት መከላከያ ረሽኖታል። ሌላም ከእሱ ጋር አብሮ የነበረ ግለሰብ ተረሽኗል።
በሉ እናንተም ሂዱ እኛም ወደዛው ነን!
የቁስ ሰቀቀናም የአብይ አማራዎችና የወረሙማው የዳልጋ ከብቶች በዚህ ወቅት እያሉን ያሉት "አፈሙዛችሁን ከብልጽግና አገዛዝ ላይ አንስታችሁ፣ ወደ ሰሜን ጠላቶቻችን (ህውሃትና ኤርትራ አዙሩልን" እያሉን ነው።
ለወዶገብ የቁስ ሰቀቀናም ብአዴናውያን ማለት የምንፈልገው "እናንተ አድማ መከልከል እና ሚሊሽያን ይዛችሁ ወደ ወልቃይት ዝመቱ፤ እኛ ደግሞ ወልቃይትና ራያን ላለፉት 3 ዓመታት በጀት የከለከለውን አማራውን በቀየው ሁሉ መኖሪያ ያሳጣውንና ህልውና አደጋ ውስጥ የከተተውን አገዛዝ ለመርሰስ ዘመቻችንን እንቀጥላለን"።
እናላችሁ እንዲያ ከሆነ መንገዳችን ይለያይ እንጅ፣ ሁለታችንም የምንዘምተው ለወልቃይት ይሆናል ማለት ነው 😉። እናላችሁ እናንተ ማዘዝ የምትችሉት የእራሳችሁን አፈሙዝ ብቻ ነው ለማለት እና በሉ እናንተም ሂዱ እኛም ወደዛው ነነ ለማለት ነው። አይ ካላችሁ ግን የመነፋረቅ ይቅርና፣ የመታነቅ መብታችሁም የተከበረ ነው።
አፋብን|ቴዎድሮስ ዕዝ
ጥር 21/2018ዓ.ም
_፩
74ኛ ክፍለጦር በደፈጣ ጥቃት ጠላትን ደመሰስ።
ከደብረወቅ እና ፈለገ ብርሃን በመሰባሰብ የማህበረሰብን ንብረት ለመዝረፍ ሲንቀሳቀስ በነበረ የአረመኔው ሰራዊት ላይ በግዶ እና መጣያ መገንጠያ ላይ ደፈጣ በመጣል በረካታ ሰራዊት መደምሰስ ተችሏል።
201ኛ ኮር 74ኛ ክፍለጦር ባደረሰው ድንገተኛ ጥቃት ተደናግጦ ወደ ፈለገ ብርሃን በመሸሽ ላይ እያለ በተመሳሳይ ደፈጣ በመያዝ በቦምብ ተጨማሪ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።
____፪
ጠላት በተከታታይ አፋብንን እየተቀላቀለ ይገኛል።
በርካታ የምሊሻ አባላት ፣የአድማ ብተና አባላትና የመከላከያ አባላት በየቀኑ እየፈረሱ ፋኖን እየተቀላቀሉ ነው። በዛሬው እለትም 6 የአረመኔው ሰራዊት አባላት በራሳቸው ፍቃድ ከጠላት ካንፕ በመክዳት ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል።
የአንድነቱ መበሰር ለዚህ እንደገፋፋቸው በሰጡት ቃለ መጠይቅ አብራርተዋል።
___፫
ከ86 በላይ ንፁሀን አማራዎች መራዊ ከተማ ላይ በፋሽቱ አብይ አህመድ አረመኔ ሰራዊት የተጨፈጨፉት 2ኛ ዓመት በፋኖ ተዘክሮ ውሏል።
___፬
በ6 ቀበሌዎች ሕዝባዊ ውይይት ተደረገ።
፪ እጁ እነሴ ወረዳ አጋም-ውሃ ፣ ደብረ-ማርያም፣ ደብር-ሚካኤል ፣መቃ፣የጭቃ እና ጓትራን ቀበሌ 54 ክፍለ ጦር ህዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል።
ከሕዝብ ጋር የምናደርገው መምከር ትግሉን መጠበቅ ነው።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ጥር 21/2018 ዓ.ም
ሰበር...በራያ ቆቦ ወረዳ ካድሬዎች መካከል ከባድ ሽብርና ጭንቀት ተፈጥሯል!
ከአመራሮቹ መካከል አንዳንዶች ከተማዋን ለቀው ለመውጣት እንቅስቃሴ የጀመሩ ቢሆንም ነገር ግን ከበላይ አመራሮቻቸው በመጣ ትዕዛዝ ታግደዋል።
በአሁን ሰዓት ቆቦ ከተማ ከአላማጣና ኮረም ሸሽተው በመጡ ወታደሮችና ሜካናይዝድ መሣሪያዎች የተጥለቀለቀች ሲሆን፡ በከተማዋ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን ካድሬዎቹ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በከተማዋ እየዞሩ መናገራቸውን ነዋሪዎቹ ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።
የሰዓት እላፊ ገደቡ ከዛሬ ጥር 21/2018 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፡ ማንኛውም ተሽከርካሪ ከምሽት 12:00 በኋላ እንቅስቃሴ ታግዷል፡ በተመሳሳይ እግረኞች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ አይችሉም ተብሏል።
የብልፅግናው አገዛዝ በከተማዋ የሚገኙ ባንኮች ገነዘባቸውን እንዲያሸሹ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩም ተሰምቷል።
የአገዛዙን የክፋትና የተንኮል እጆች እየተከታተሉ ለህዝብ ማድረስና እንዲጠነቀቅ ማድረግ ያስፈልጋል!
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ቆቦ ከተማና አካባቢው ላይ ከነ ጌታቸው ረዳ ታጣቂዎች የተመለመሉ ጥቂት ሃይሎች አስገብቶ ንፁሃን ላይ ጥቃት እንዲፈፅሙ በማድረግ ''ህወሓት አጠቃችሁ'' የሚል ተለምዷዊውን ተራና ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ለመስራት ዝግጅት ማድረጋቸውንና ተልዕኮ መውሰዳቸውን ውስጥ አርበኞች መረጃ አድርሰውናል::
ጀምበር የጠለቀችበት ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ለፖለቲካ ትርፍና ለስልጣኑ ሲል ዛሬም እንደ ትላንቱ ንፁሃን አማራዎችን ከማስጨፍጨፍ ወደኋላ አይልምና መላው ህዝባችን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲወስድ መልክታችንን እናስተላልፋለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 21/5/2018 ዓ.ም
74ኛ ክ/ጦር በደፈጣ በግዶ እና መጣያ መገንጠያ ላይ ጠላት ተረፍርፏል ።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
ጥር 20/2018 ዓ.ም
መነሻውን ደብረወርቅ እና ፈለገብርሃን አድርጎ መጠያ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መረጃው የደረሰው ፋኖ ደያጠባ፣ጎል ውቅማ እና መጠያ መገንጠያ ላይ ደፈጣ በመጣል እልህ አስጨራሽ ውጊያ በማካሄድ 14 ሙት እና ከ11በላይ ጠላት ቁስለኛ በማድረግ አሳፍሮ መመለስ ተችሏል።
ቁስለኞችን ይዞ ወደ ፈለገብርሃን ከተማ በመገዝ ላይ እያለ በቦንብ ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን ከ5 በላይ መከላከያ እና ምኒሻ በማቁሰል ምሽታቸውን የሃዘን ካባ በማልበስ በሃፍረት እንዲከናነቡ ማድረግ ተችሏል።
ጥር 21/2018 ዓ.ም
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
የአፋብን የቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኘነት
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር ህዝባዊ ውይይት መድረክ አደረገ!!
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ፣ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር በሚያስተዳድሯቸው ቀጣናዎች ሰፊ ህዝባዊ ውይይት እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም በአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ሥር የሚገኙ ከፍተኛ የዕዝ የኮር እና የክፍለ ጦር አመራሮች በተገኙበት ከሞረትና ጅሩ ወረዳ ላም ዋሻ ቀበሌ ህዝብ ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችና ለትግሉ ጠቃሚ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ጥልቅ ምክክር የተደረገበት መድረክ ነበር። በተለይም የአማራ ህዝብ ሲናፍቀው የነበረውና አንድ ሁኑልኝ በማለት ሲያደርገው የነበረው ግፊት እውን መሆኑ የተበሰረበት መድረክ ሆኗል። የጋራ ጠላትን ለመመከት የሚያስችል አማራዊ የአንድነት ድርጅት መፈጠሩን ተከትሎ፣ የህዝቡን ደስታና ድጋፍ ተሳታፊዎቹ በተለያዩ ሃሳቦች ገልጸዋል።
ህዝቡም እንኳን አንድ ሆናችሁልን፤ ከአሁን በኋላ በሙሉ ልብና በ24 ሰዓት ከጎናችሁ ተሰልፈን ይህንን ቅዱስ ትግል ከዳር ለማድረስ እንሰራለን በማለት ደስታቸውንገልፀውልናል። በመጨረሻም በመድረኩ የፋኖ አሁናዊ የወታደራዊ አቋም ባለፈ፣ በህዝብና በአመራሩ መካከል የነበረውን የመተማመን ድልድይ ይበልጥ ያጠናከረ ነው። ድላችን በተባበረ ክንዳችን የሚበሰርበት በተግባር ደግሞ የሚፈታበት የመጀመሪያው ምዕራፍ የሚሆንበት ቀን ቅርብ ነው።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
አርበኛ አማረ ታዘዘ
ጥረ 21/05/2018 ዓ.ም
የወረዳውን ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች እርምጃ ተወሰደባቸው!
ጥር:-21/2018 ዓ/ም
በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ስር የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ኢንጅነር ለዓለም ብርሐኑ እና ላሊበላ ከተማ ሰፍሮ የሚገኘው የብልፅግና ፓርቲ ተላላኪ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ሆቴል አዘግተው አስረሽ ምችው በሚሉበት ጊዜ ላሊበላ ከተማ ላይ ሰርገው በገቡ ባልታወቁ ኃይሎች በደረሰባቸው የእጅ ቦምብ ጥቃት ከፍተኛ አመራሮቹ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደዋል።
ጉዳቱ የደረሰው ጥር 20/2018 ዓ/ም ከምሽቱ 4:30 ገደማ ላሊበላ ከተማ ለውዝ መገንጠያ ሀብትዬ መዝናኛ ካፌ ሲሆን በደረሰባቸው የእጅ ቦምብ ጥቃት አንድ ከፍተኛ የመከላከያ አመራር ወዲያውኑ ህይወቱ ሲያልፍ ተጨማሪ ሰባት የመከላከያ አመራሮችና አባላት ከባድ አካላዊ ጉዳት አስተናግደዋል።
የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ኢንጅነር ለዓለም ብርሐኑም የጉዳቱ ሰለባ ሲሆኑ ጉዳቱ እንደደረሰ ወዲያውኑ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን የመተንፈሻ ሳንባቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንደተጎዳና ሰው ሰራሽ መተንፈሻ ተሰርቶላቸው እንዳሉ፣ጀርባቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንደደቀቀና ራሳቸውን ስተው ኮማ ውስጥ እንዳሉ አሁንም በሞትና በህይወት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ በውስጥ መረጃዎቻችን በኩል ተረጋግጧል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር:-21/2018 ዓ/ም
ቤተ-ክርስቲያን አገልጋዩ የሐይማኖት አባት በብልፅግና ሰራዊት በግፍ ተረሸኑ!
ጥር:-21/2018 ዓ/ም
በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ቡግና ወረዳ 09 ጉልሐ ቀበሌ ነዋሪ እና የጀርጀንቦይ መድሐኒአለም ቤተ-ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት የ58 አመት ዕድሜ ያላቸው መርጌታ ጌጡ በላይ የብልፅግና አገልጋይ በሆኑት መከላከያ ሰራዊት አባላት ጥር 20/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ገደማ በግፍ ተረሽነዋል።
የቤተ-ክርስቲያኑ አገልጋይ አባት መርጌታ ጌጡ በላይ አይና እየሱስ ከተማ እህል በወፍጮ አስፈጭተው በመመለስ ላይ እንዳሉ እየሱስ ቤተ-ክርስቲያን ጫካ ውስጥ አራት ጥይት አከታትለው በመተኮስ እንደረሸኗቸው ታውቋል።
የተረሸኑበት ምክኒያትም ሰሞኑን ከፋኖ ኃይሎች ጋር አስታርቁን በሚል ሽፋን ከተመለመሉት የሐይማኖት አባቶች አንዱ ሲሆኑ ራሳችሁ ባጠፋችሁት ጥፋት፣መነኩሴን ለሚደፍር፣የቆሎ ተማሪን ለሚረሽን፣ቤተ-ክርስቲያንን ለሚያረክስ ስርዓት አልላክም በማለታቸው በቡግና ወረዳ ብልፅግና አመራሮች ሴራ ጠንሳሽነትና አስተባባሪነት በብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ትዕዛዝ ፈፃሚነት የሐይማኖት አባቱ እንደተረሸኑ የውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጀግኖች ለአላማቸው ይሰዋሉ! ትግላቸውና አላማቸው ይቀጥላል!
ጥር 20/2018 ዓ/ም ጀግናው መኩሪያ ፈንቴ ለአላማውና የህልውና አደጋ ላይ ላለው ህዝቡ አንድያ ህይወቱን ለግሷል!
አርበኛ መኩሪያ ፈንቴ የመጀመሪያ ዲግሪውን በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የተመረቀ ሲሆን፤ሁለተኛ ድግሪውን በወልድያ ዩኒቨርስቲ ተመርቋል:: በ2013 ዓ/ም የአማራ ፋኖ ንቅናቄንና ምስረታዎችን በመቀላቀል የአርበኝነቱን ህይዎት ያኔ ጀመረ። የአርበኝነት ጅማሮው ከአምስት አመታቶች በላይ በጫካና በዱር ያሳለፈ በፅናትና በታማኝነት ለአማራ ህዝብ የቆመ ነበር።
አርበኛ መኩሪያ የደጋው መብረቅ ኮር ህዝብ አደረጃጀት መምሪያ እና በሚኒሊክ ዕዝ ማህበራዊ ዘርፍ ም/ሃላፊ ነበር። አርበኛው ከአዋጊነት እስከ ተዋጊነት የተዋጣለት መሪም ነበር። ጥር 20/2018 ዓ/ም ከማለዳው12:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 7:00 ሰዓት በዘለቀው አውደ ውጊያ በርካታ የፋሽስቱን ሰራዊት ዶግ አመድ በማድረግ፤በርካታዎችን ምርኮኛና ቁስለኛም በማድረግ ጀግናው ፊት ለፊት ከጥላት ጋር አንገት ለአገት ተናንቆ በጀግንነት ተሰውቷል።
አርበኛ መኩሪያ ፈንቴ ከአማራ ህዝብ በፊት እኔ እሞታለሁ ብሎ ደረቱን ለጥላት የሰጠ የቁርጥ ቀን አርበኛ ነበር። ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦርን ከጓዶቹ ጋር በመመስረትና ለአማራ ህዝብ የነፃነት ሀይል አድርጎ በመገባት ትልቅ ሚና ነበረው። አርበኛው አንድያ ህይዎቱን ለአማራ ህዝብ በአውደ ውጊያ ሜዳ ላይ የሰጠ ሲሆን የአርበኞች መሰዋዕትነት የአማራ ፋኖ ትግል መራር ዋጋ የሚከፈልበት ህያው ዋጋ መሆኑ ሲሆን ለዚህ ትልቅ የታሪክ ህያው ምስክር ሆኖ አርበኛ መኩሪያ ፈንቴ ለአላማውና ለህዝቡ ተሰውቷል።
#ኑረን ለምናገለግለው ሞተን ለምናሻግረው ህዝባችን ምንስ የማንሆንለት ይኖራልና!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ!
ጥር 21/5/2018 ዓ.ም
