ch
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
3 534
订阅者
+24824 小时
+5847 天
+97230 天
帖子存档
ሰበር ዜና! አፋብን ምኒልክ ዕዝ እና ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ ታላቅ ድል አስመዘገቡ:: የአፋብን ሁለቱ ዕዞች ምኒልክ ዕዝ እና ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ በርካታ የጠላት ሰራዊት በመደምሰስና በመማረክ እንዲሁም የነፍስ ወከፍ መሳርያ እና ተተኳሽ በመማረክ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል:: መጋቢት 21/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ እስከ ምሽት በነበረው ተጋድሎ በርካታ የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ የተደረገ እንዲሁም የተማረከ ሲሆን በምኒልክ ዕዝ በኩል 104ኛ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር ከ106ኛ ኮር 31ኛ ክፍለ ጦር እና 105ኛ ኮር አሃዶችም የተሳተፉ ሲሆን ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት የመሃመድ ቢሆነኝ ኮር እና አፄ አምደ ፅዮን ኮር አሃድ አባላቶች በጥምረት በመዋጋት ታላቅ ድል አስመዝግበዋል:: በዚህ ታላቅ ድል በተመዘገበበት ተጋድሎ 15 የጠላት ሰራዊት የተማረከ ሲሆን 25 ክላሽ፣ ከ1200 በላይ የድሽቃ ተተኳሽ፣ በርካታ ቁጥር ያለው የብሬን እና የክላሽ ተተኳሽ እንዲሁም ወታደራዊ ቁሳቁስ ከጠላት ተማርኳል::   መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም

በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ያለው ፋሽሽቱ አገዛዝ ፋኖን አገኛለሁ በሚል እውር፣ድንብሩን በተኮሰው ድሮን እና የጦር ሚግ ጀት ንፁሃን አማሮች እና በርካታ ሀብት፣ንብረት መውደሙ ተሰማ። በእግረኛ ሰራዊት ላለፉት ሶስት ዓመታት በአማራ ክልል እና ፋኖ ይገኝባቸዋል ባላቸው የኢትዮጵያ ክፍሎች በሙሉ ንፁሃን ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ሲፈፅም የቆየው ፋሽሽቱ አገዛዝ አሁን ደግሞ ደረጃውን ከፍ በማድረግ ከእግረኛ እና ድሮን ጥቃቶች በተጠማሪ በጦር ሚግ ጀት በአማሮች ላይ የሚፈፅመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል አጠናክሮ መቀጠሉን በተለያዩ ቦታዎች የሚወጡ መረጃዎች አረጋገጠዋል። ትላንት እና ዛሬ ከተፈፀሙ ጥቃቶች መካከል👇🏾 1ኛ) በትናንትናው ዕለት፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን፤ አቤደንጎሮ ወረዳ፣ ጎርቴ ቀበሌ፣ ውባንጭ (ከራ ዱርባ) አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአገዛዙ የጦር ሚግ ጀት ወድሟል። 2ኛ) በተመሳሳይ በደቡብ ጎንደር ዞን፣ ደራና እስቴ ወረዳ፣ ሰኔ ማሪያም አካባቢ በዛሬው ዕለት በጦር ሚግ ጀት በተፈፀመ ከፍተኛ ጥቃት ንፁሃን መገደላቸውን መረጃዎች እየተሰራጩ ነው። 3ኛ) ዛሬ ረፋድ ደግሞ በጎጃም ጎዛምን ወረዳ፣በቀኝ አቦና በየቦቅላ ቢጠቀም፣ የተባለ አካባቢ በጦር የሚግ ጀት እና ድሮን ከ8 ጊዜ በላይ በተፈፀመ ጥቃት የንፁሃን ቤት ተደብድቧል። አገዛዙ የአየር ጥቃቱን በስፋት የቀጠለው በአማራ ህዝብ ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ለማጠናከር ቢሆንም፣በእግረኛ ሰራዊት የፋኖን ክንድ መቋቋም ባለመቻሉ ጭምር መሆኑንን ለማረጋገጥ ተችሏል። በተያያዘ የፋሽሽቱ አገዛዝ የእውር፣ድንብር የአየር ጥቃት ለመመከት ማንኛውም ፋኖ ከምንጊዜውም በላይ በቀንም ሆነ በሌሊት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲዎስድ መረጃውን በተለያየ መድረክ እናሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስሉ እና ፎቶዎች በትናንትናው ዕለት ሆሮ ጉድሩ፣ወለጋ ዞን፣አቢ ደንጎሮ ወረዳ፣ጎርቴ ቀበሌ "ኩራ ዱርባ" ት/ቤት ከድሮን እና ከጦር ሚግ ጀት ድብደባው በኋላ የተወሰደ ነው!!

አፋብኃ ቴወድሮስ እዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር  አጭር የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጠ። መጋቢት 21/ 2018 ዓ.ም አፋብኃ ቴወድሮስ እዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር  የመጀመሪያ ዙር የሆነ    የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለክ/ጦሩ የቃኝና መሃንዲስ አባላት ሰጠ። ከሽምቅ ተወጊዎች እና የፋኖ ጦር የሚጠበቅ  የአንድነት የስነ-ምግባርና የማህበረሰብ አያያዝን የተመለከተ አጭርና ግልፅ  ስልጠና ተሰጥቷል።  ስልጠናው በዋናነት፡- © የጋራ ራዕይና የውስጥ አንድነት ግንባታ © ስነ-ልቦናዊ ጥንካሬና ጽናት © የሥነ-ምግባር ደንቦች (Rules of Conduct) © ማህበረሰባዊ  መሰረትን መገንባትና ማፅናት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ  ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።   የ102ኛ ኮር  11ኛ ክ/ጦር  የፖለቲካ መምሪያ ሃላፊ የክ/ጦሩ ፅ/ቤት ሃላፊና የስልጠና መምሪያ ሃላፊዎች በተገኙበት የተሰጠው ይህ ስልጠና የአባላቱን እና የታጋዩን የትግል የስነልቦና ግንዛቤ የጨመረ እና በቀጣይ ለሚደረጉ ግዳጆች ዝግጁ እንደሚያደርጋቸው ገልፀዋል። ስልጠናው በታጋዩ መካከል ያለውን አንድነትና  የትግል አላማ መዳረሻ  የግንዛቤ አረዳድ ከፍ እንዳደረገው  ጨምረው የስልጠና ተሳታፊ አባላት ተናግረዋል። በስልጠናው የተሳተፉ የተወርዋሪ አባላት ሀሳባቸውን እንዳካፈሉት ከሆነ እንደዚህ አይነት መሰል ስልጠና በተከታታይ መኖሩ ለትግል ያለንን ሞራልና የፅናት መንፈስ እንደጨመረው ገልፀዋል። በመጨረሻም በቀጠናው ለሚደረግ የትኛውም ግዳጅ  በወትሮ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኙ እና ጠንካራ የስነልቦና ሞራል ላይ መሆናቸውን  አረጋግጠውልናል።                                      የ102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር ህ/ ግንኙነት

~~|||| ማሳሰቢያ❗️ ከድተው ለጠላት እጅ የሚሠጡ የፋኖ አባላት እና አመራሮች ሁል ጊዜም የሚያውቁትን ምስጢር በተለይ አመራር ከሆነ:- ~> እቅዶችን እና ድርጅታዊ ሥትራቴጅክ ሠነዶችን ~> የመንቀ
~~|||| ማሳሰቢያ❗️ ከድተው ለጠላት እጅ የሚሠጡ የፋኖ አባላት እና አመራሮች ሁል ጊዜም የሚያውቁትን ምስጢር በተለይ አመራር ከሆነ:- ~>  እቅዶችን እና ድርጅታዊ ሥትራቴጅክ ሠነዶችን ~> የመንቀሳቀሻ ቦታዎችን፣ ~> መተላለፊያዎች፣ ~> የከተማ አባሎችን የኮድ ስም(ማንነት)፣ ~> የፋይናንስ እንቅስቃሴ ስልቶች እና ምንጮችን፣ ~>የስልክ አድራሻዎችን፣  ~> ወሳኝ የሚባሉ አመራር/አዋጊዎችን ግላዊ ሚስጥሮች፣ ~> የከተማ መግቢያ መውጫ  ስልቶችን እና ሽፋኖችን ~> አባሉ ውስጥ ያለውን ማንኛውንም ሁኔታዎች ~> ሊመለመሉ የሚችሉ አመራሮች እና አባላትን ወይም ተጋላጭነታቸውን ወ-ዘ-ተ የሚያውቋቸውን ሚስጥሮች እና ማነኛውም የተቀረፁ ማስረጃዎችን ለጠላት አሳልፈው እንደሚሰጡ መገንዘብ ያስፈልጋል። ሰሞኑን በሸዋ ቀጠና እየተከሰተ ያለውም ከዚህ ዓይነት ውስጣዊ መረጃ የመነጩ እንደሆኑ መገመት ይቻላል። በመሆኑም ከድቶ ከሚወጣበት የፋኖ ሠራዊት አሃድ/ክፍለጦር ወይም ኮር ግለሠቡ ሊያውቃቸው የሚችሉ ሚስጢሮችን ቁጭ ብሎ በመገምገም በፍጥነት አሠራርም ሆነ፤ ማነኛውም ጠላት ዘንድ የደረሱ ተጠቅሞ ጉዳት ሊያደርስባቸው የሚችሉ ሁኔታዎችን መቀየር ቀዳሚ ተግባር መሆን ይኖርበታል። በሚከዱት ግለሰቦች ዙሪያ የነበሩ ታጋዮችንም ስለ ከጅ ግለሰብ ሁኔታ እና ማንኛውምን መረጃዎች በፍጥነት በምርመራ መልክ በመያዝ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል። © በዛብህ በላቸው!

#25ኛ ክ/ጦር ድል ተቀዳጀ‼️ አፋብን ም/አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ 104ኛ ኮር 25ኛ ክ/ጦር ለወረራና ጭፍጨፋ 25ኛ ክ/ጦር ወደሚገኝበት ዛሬ ማለትም መጋቢት 21/2018 ዓ.ም በ3 አቅጣጫ ማለትም
#25ኛ ክ/ጦር ድል ተቀዳጀ‼️ አፋብን ም/አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ 104ኛ ኮር 25ኛ ክ/ጦር ለወረራና ጭፍጨፋ 25ኛ ክ/ጦር ወደሚገኝበት ዛሬ ማለትም መጋቢት  21/2018 ዓ.ም በ3 አቅጣጫ ማለትም በአካድ ፣በፉርሴና በቁልቢ ግንባሮች የቁም ቅዥት ይዞ ለመንቀሳቀስ ቢሞክርም በተለይ በአካድ ግንባር የ25ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት ልዩ ደፈጣ በማድረግ እንዲሁም የሞርተር ምድብተኞች የተጠና ጥቃት በመሰንዘር 12 ጥላት የተደመሰሰ ሲሆን በርካታ ቁስለኛ ሆኖ ወደመጣበት አስከሬን ሳያነሳ ፈርጥጧል።በዚሁ ግንባር የተገኘ 👉08 ክላሽ 👉1000 የብሬን ተተኳሽ 👉2500 የክላሽ ተተኳሽ 👉አንድ ከነተተኳሹ የብሬን ሸንሸልና ወታደራዊ አልባሳቶች ተገኝቷል። በፉርሴ ግንባርም የተሰለፈው ግትልትል ለዘረፋና ወረራ የመጣ ሰራዊት በክ/ጦሩ 2ኛ ሬጅመንት አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ አሯሩጦ ወደመጣበት መልሶታል።በቁልንቢ ግንባር  የተሰለፈውን የጠላት ሀይል ደግሞ የ104ኛ ኮር ቃኝዎች ጥላት ያሰበውን ሳይፈፅም ወደመጣበት በጀግኖቹ ተመትቶ እንዲመለስ ተደርጓል ሲል የክ/ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን ልኳል።    መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!        ህልውናችን በተባበረ ክዳችን💪💪💪        ©አርበኛ ሱልጣን የሱፍ  የ104ኛ ኮር ህዝብ ክንኙነት 21/ዐ7/2018 ዓ.ም

በ3 አቅጣጫ ደቡብ አቸፈር ወረዳ አሹዳ ከተማን ለመውረር የተንቀሳቀሰው የmላት ሀይል በ55ተኛ ክ/ጦር ተቀጥ,ቅጦ እና ተበታትኖ በደ መጣበት ተመልሷል ። በ21/07/2018 በሀሙሲት ፣ከዝህብት እና
በ3 አቅጣጫ ደቡብ አቸፈር ወረዳ አሹዳ ከተማን ለመውረር የተንቀሳቀሰው የmላት ሀይል በ55ተኛ ክ/ጦር ተቀጥ,ቅጦ እና ተበታትኖ በደ መጣበት ተመልሷል ። በ21/07/2018 በሀሙሲት ፣ከዝህብት እና ቀደምት ላሊበላ (ዲላሞ )አቅጣጫ በመንቀሳቀስ አሹዳ ከተማን ለመውረር የተንቀሳቀሰው የአረመኔው የብልፅግና ሰራዊት በአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦር 3ተኛ ሻለቃ እና በኮሩ ቃኝ እና መሀንዲስ ከፍተኛ የመከላከል ውጊያ የገጠመው ሲሆን የmላትን ሀይል በማዛባት እና ወደ ፈጣን ማጥቃት በመቀየር በተደረገ መልሶ ማጥቃት በርካታው ሀይል ሙ,ትእና ቁ.ስ.ለ.ኛ ሲሆን የተረፈው የmላት ሀይል ተበታትኖ ወደ መጣበት ፈርጥጧል ። አሁን አሹዳ ከተማ በወገን እጅ ትገኛለች ። ውጊ.ያውን የቴዎድሮስ እዝ ም/ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ መቶ አለቃ ማርቆስ አሞኘ በተለመደ ቆራጥነት በአካል በመገኘት መርቶታል ። አህዛዊ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን ። ምስጌ ዘድንግል የ55ተኛ ክ/ጦር ሕ/ግ ሀላፊ

ሰበር የድል ዜና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ እና ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ታሪካዊ የአንድነት ስምምነት ካደረጉ ማግስት ጀምሮ፣ በሸዋ ሰንሰለታማ ተራሮች ላይ የአብይ አህመድ አየር ወለድ ኮማንዶ ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ድልን አስመዘገቡ!! ዛሬ ማለትም ሌሊት 11:00 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ ግንባሮች በተቀናጀ ሁኔታ ከፍተኛ ወታደራዊ ስልት የታከለበት ማጥቃት የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ሚሊሻ አድማ መከላከል እና የብአዴን ቡችላ የህዝብ ፖሊስ በጠላት በኩል ሁለት መድፍ እና በርካታ ዙ23 እና ሞርታሮች በታገዘው አውደ ውጊያ የአብይ አህመድን ሰራዊት በገባበት ገብተው በማዳፋት የበላይነት በመውሰድ ድላቸውን አስመዝግበዋል። በተመሳሳይ የምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ 104ኛ ኮር 25ኛ ክፍለ ጦር በአካድና ፋርሲ የሶስቱ ግንባሮች የተቀናጀ ውጊያ በግሼ ግንባር የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር እና ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር አስቴጉማ ተራራ ክፍለ ጦር የጠላትን ኃይል መፈናፈኛ አሳጥተውት ውለዋል። በዚህ ግንባር ​እነዚህ ሁለት ክፍለ ጦሮች ​በመቀናጀት በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ የአብይ አህመድ ቅጥርኛ ሰራዊት ከፍተኛ ኪሳራ ማድረስ ችለዋል ። የሸዋ ዳገቶች ለፋኖዎቹ የድል አውድማ፣ ለጠላት ደግሞ የሽንፈት ማማ ሆነዋል። እንዲሁም ​በወጀድ ግንባር የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ​ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ​የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር እና ​የዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር​ በቅንጅት በሰነዘሩት ማጥቃት የጠላት ጦር በከፍተኛ ድንጋጤና ውዥንብር ውስጥ በማስገባት እያርበደበዱት ከመገኘታቸውም በላይ ከፍተኛ የአገዛዙ አመራሩ ጨምሮ ሙትና ቁስለኛ ሁኗል። ​ይህ ከአንድነት ማግስት የተጀመረው የተቀናጀ የግንባር አውደ ውጊያ የፋኖን ክንድ ይበልጥ ያጠነከረና የጠላትን የጥፋት ዕድሜ የሚያሳጥር በመሆኑ በሸዋ ተራሮች ላይ የሚካሄደው እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ድልን ያስመዘገቡ በመሆኑ ውጊያውም እስከ አሁን የቀጠለ ሲሆን የአንድነቱ ኃይል ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል። ​ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት አማረ ታዘዘ!!!!!! መጋቢት 22 /06/2018 ዓ.ም

አንድ የፎቶ ሾፕ ታጋይ ከዳ አልከዳ ምን ለውጥ አለው
አንድ የፎቶ ሾፕ ታጋይ ከዳ አልከዳ ምን ለውጥ አለው

⏰የክህደት ጽዋ፡ በጀነራል አሳምነው ስም የተፈጸመ የባንዳነት ውርደት! የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የብዙ ሺህ ጀግኖችን ደምና አጥንት የጠየቀ፣ አሁንም እየጠየቀ ያለ የመኖርና ያለመኖር ፈተና ነው። በዚህ መራራ የትግል ጉዞ ውስጥ፣ እንደ ብረት የጠነከሩ ጀግኖች ታሪካቸውን በደማቸው ሲጽፉ፤ ለጊዜያዊ ጥቅም፣ ለሆዳቸውና ለፍርሃታቸው ያደሩ ደግሞ በገዛ ሕዝባቸው ላይ ክህደት በመፈጸም የታሪክ ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ይወድቃሉ። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የወሎ (ቤተ-አማራ) ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የግዙፉ አሳምነው (303ኛ) ኮር ዋና ሰብሳቢ የነበረው ፍቅሩ ሙልዬ የዚህ የታሪክ ዝቅጠትና የውርደት ማሳያ ሆኗል። ይህ ግለሰብ የሕዝቡን አደራ፣ የትግል ጓዶቹን ደምና የቆመበትን ህዝባዊ ዓላማ ወደ ጎን በመተው ለአገዛዙ እጅ መስጠቱ የክህደት ሁሉ ጥግ ነው። ከሁሉ በላይ የሚያሳዝነውና የሞራል ዝቅጠቱን አጉልቶ የሚያሳየው፣ ይህ ግለሰብ በትግል ሜዳ ቁሞ በታላቁ ሰማዕት በጄኔራል አሳምነው ጽጌ ስም ሲምልና ሲገዘት የነበረ መሆኑ ነው። በአሳምነው ስም መማል ማለት ለእውነት መቆም፣ ለሕዝብ ነጻነት እስከ መጨረሻዋ የደም ጠብታ መሰዋት ማለት እንጂ፣ ቃለ-መሐላን አረክሶ ገዳይ ሥርዓት ፊት መንበርከክ አልነበረም። የጀግናን ስም ለከንቱ ሽንገላና ለፖለቲካ ንግድ መጠቀሙ ትውልድ ይቅር የማይለው፣ የታሪክ ፍርድ የሚያስከትል ኃጢአት ነው። የሕዝቡን ስቃይ እያየ፣ በሕዝብ ላይ ሞት ለሚያዘንብ ኃይል እጅ መስጠቱ የጓዶቹን መስዋዕትነት የሚያቃልል ጥሬ የባንዳነት ተግባር ነው። ሆኖም፣ ይህ ክህደት ማሳየት ያለበት አንድ ትልቅ እውነት አለ። የአማራ ሕዝብ ትግል በግለሰቦች ትከሻ ላይ የተንጠለጠለ ሳይሆን፣ በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ የሰረጸ ትልቅ የህልውና ማዕበል ነው። የአንድ ፍቅሩ ሙልዬ ክህደት የሚያሳየው የትግሉን መዳከም ሳይሆን፣ የትግሉን መጥራትና ጽዳት ነው። አብዮት ሁልጊዜም በጉዞው ላይ ገለባውን እያበጠረ፣ ፍሬውን እያጠነከረ ይጓዛል። እንዲህ ያሉ በውስጥ ተሰግስገው የነበሩ፣ ዓላማ ቢስና ፍርሃት ያሸነፋቸው ግለሰቦች ራሳቸውን አጋልጠው ከትግሉ መለየታቸው፣ ንቅናቄው በንጹሐንና በጽኑዓን ጀግኖች ብቻ ተከቦ ወደፊት እንዲራመድ ትልቅ አቅም ይፈጥርለታል። ትግሉ ይቀጥላል! የነጻነት ጉዞው በአንድ ከዳተኛ ማፈንገጥ አይገታም። ታሪክ ለከዳተኞችና ለባንዳዎች የውርደት ሐውልት ሲያቆም፣ እስከ መጨረሻው ለጸኑት ግን ዘላቂ ክብርን ይለግሳል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ይህንንና መሰል የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን በጽናት እያለፈ፣ የሕዝቡን መከራ ወደሚያሳጥርበት የድል ማማ መውጣቱ አይቀሬ ነው! የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ወሎ (ቤተ አማራ)   ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር 19ኛ ክፍለ ጦር  በአገዛዙ ሰራዊት ላይ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ድል ተጎናፀፈ። ጠላት መነሻውን አይና ከተማ አድርጎ ቡግና ወረዳ 010 ቋሮ ቀበሌ  ለመግባት እና ህዝብን ለማሰቃየት የተንቀሳቀሰው የጁል ሠራዊት ቡግና ወረዳ 08ደብረ ሮሃ ቀበሌ ልዬ ስሙ ሲቃን እየተባለ ከሚጠራው ቦታ የደፈጣ እና የቆረጣ ዉጊያ በመክፈት የአብይ አህመድ ዙፋን አሰጠባቂ ሰራዊት ከባድ ሸንፈትን ተከናንቧል። አይበገሪዎቹን መቋቋም ያቃተው የጁላ ሰራዊት ገደል በመግባት እና ቀሪው ደግሞ ሲቃን ጎራ ተንጠልጥ የድረሱልኝ ጥሪ እየተማፀነ ይገኛል። ዉጊያዉም ከትላንት ማለትም ከቀን20/07/2018ዓ.ም ከቀኑ 8:00_ሌሊቱ 6:00 ድረስ  የተካሄደ ሲሆን በረካታ ድሎችም ተመዝግበዋል ። በዚህም 1ብሬን 10ክላሽእንኮፍ  ከ2000በላይ የብሬን ተተኳሽ ፣ 4500የክላሽ ተተኳሽ እና በርካታ  ቦምቦች ገቢ ተደርጓል። የአበገሬዎቹ የአሳመነው ፅጌ ግልገሎች በብርኮ በኩል ሰርገው በመግባት አይና ከተማ ካድሪ ለመጠበቅ የተቀመጠውን የጁላ ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት የተቀጣ ሲሆን አይና ገብሬል እና አይና ሸብራ አጠጌ የተከማቸውን የጁላ ሠራዊት በሞርተር ቅንቡላ እራት ሆነው አምሽተዋል ከሸብራ አጠጌ እና አይና ገብርኤል 28 የተደመሠሠ ሲሆን 2 አንቡላንስ እና 1 ኦራል ቁስለኛ ይዞ እደተመለሰ የውስጥ ምንጮቻችን አድርሰውናል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ወሎ (ቤተ አማራ)  ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ !! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት21/2018ዓ.ም

⏰የክህደት ጽዋ፡ በጀነራል አሳምነው ስም የተፈጸመ የባንዳነት ውርደት! የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የብዙ ሺህ ጀግኖችን ደምና አጥንት የጠየቀ፣ አሁንም እየጠየቀ ያለ የመኖርና ያለመኖር ፈተና ነው። በዚህ መራራ የትግል ጉዞ ውስጥ፣ እንደ ብረት የጠነከሩ ጀግኖች ታሪካቸውን በደማቸው ሲጽፉ፤ ለጊዜያዊ ጥቅም፣ ለሆዳቸውና ለፍርሃታቸው ያደሩ ደግሞ በገዛ ሕዝባቸው ላይ ክህደት በመፈጸም የታሪክ ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ይወድቃሉ። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የወሎ (ቤተ-አማራ) ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የግዙፉ አሳምነው (303ኛ) ኮር ዋና ሰብሳቢ የነበረው ፍቅሩ ሙልዬ የዚህ የታሪክ ዝቅጠትና የውርደት ማሳያ ሆኗል። ይህ ግለሰብ የሕዝቡን አደራ፣ የትግል ጓዶቹን ደምና የቆመበትን ህዝባዊ ዓላማ ወደ ጎን በመተው ለአገዛዙ እጅ መስጠቱ የክህደት ሁሉ ጥግ ነው። ከሁሉ በላይ የሚያሳዝነውና የሞራል ዝቅጠቱን አጉልቶ የሚያሳየው፣ ይህ ግለሰብ በትግል ሜዳ ቁሞ በታላቁ ሰማዕት በጄኔራል አሳምነው ጽጌ ስም ሲምልና ሲገዘት የነበረ መሆኑ ነው። በአሳምነው ስም መማል ማለት ለእውነት መቆም፣ ለሕዝብ ነጻነት እስከ መጨረሻዋ የደም ጠብታ መሰዋት ማለት እንጂ፣ ቃለ-መሐላን አረክሶ ገዳይ ሥርዓት ፊት መንበርከክ አልነበረም። የጀግናን ስም ለከንቱ ሽንገላና ለፖለቲካ ንግድ መጠቀሙ ትውልድ ይቅር የማይለው፣ የታሪክ ፍርድ የሚያስከትል ኃጢአት ነው። የሕዝቡን ስቃይ እያየ፣ በሕዝብ ላይ ሞት ለሚያዘንብ ኃይል እጅ መስጠቱ የጓዶቹን መስዋዕትነት የሚያቃልል ጥሬ የባንዳነት ተግባር ነው። ሆኖም፣ ይህ ክህደት ማሳየት ያለበት አንድ ትልቅ እውነት አለ። የአማራ ሕዝብ ትግል በግለሰቦች ትከሻ ላይ የተንጠለጠለ ሳይሆን፣ በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ የሰረጸ ትልቅ የህልውና ማዕበል ነው። የአንድ ፍቅሩ ሙልዬ ክህደት የሚያሳየው የትግሉን መዳከም ሳይሆን፣ የትግሉን መጥራትና ጽዳት ነው። አብዮት ሁልጊዜም በጉዞው ላይ ገለባውን እያበጠረ፣ ፍሬውን እያጠነከረ ይጓዛል። እንዲህ ያሉ በውስጥ ተሰግስገው የነበሩ፣ ዓላማ ቢስና ፍርሃት ያሸነፋቸው ግለሰቦች ራሳቸውን አጋልጠው ከትግሉ መለየታቸው፣ ንቅናቄው በንጹሐንና በጽኑዓን ጀግኖች ብቻ ተከቦ ወደፊት እንዲራመድ ትልቅ አቅም ይፈጥርለታል። ትግሉ ይቀጥላል! የነጻነት ጉዞው በአንድ ከዳተኛ ማፈንገጥ አይገታም። ታሪክ ለከዳተኞችና ለባንዳዎች የውርደት ሐውልት ሲያቆም፣ እስከ መጨረሻው ለጸኑት ግን ዘላቂ ክብርን ይለግሳል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ይህንንና መሰል የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን በጽናት እያለፈ፣ የሕዝቡን መከራ ወደሚያሳጥርበት የድል ማማ መውጣቱ አይቀሬ ነው!