ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多4 312
订阅者
+17324 小时
+2467 天
+1 36830 天
帖子存档
ሰበር
በተሳሳተ መንገድ ከአረመኔው የብልፅግና ስርአት ጋር ወግነው ህዝባቸውን ሲወጉ የነበሩ
መቅደስ ንጉሴ
ታዘብ ፍቃዱ የተባሉ የአድማ ብተና አባላት ከዳንግላ ከተማ በመውጣት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል ።
ግለሰቦቹ እስካሁን ከብልፅግና ጋር ሁነን ያስከፋነውን ህዝባችንን ለመካስ ጠንክረን እንታገላለን ብለዋል ።
ምስጌ ዘድንግል
ደጃዝማች ፬ኛ ኮር በሚንቀሳቀስባቸው ወረዳዎች ከፋሽስቱ አገዛዝ ነፃ የወጡ ከተሞችና ቀበሌዎች የሚከተሉት ናቸው።
👉1,ጠገዴ ወረዳ
✅አዲት አመራ
✅ሰጋሎ
✅ማያአጋም
✅አዲስ አለም
✅ማክሠኞ ገብያ
✅እርጎዬ
✅ኪሻ
✅ጎንደር ደዮ
✅ማዋት አድጊ
✅ቴፋ
✅ምስላል
✅ማር ዘነብ በረሃ
👉2, ታች አርማጭሆ ወረዳ
✅ማሂን
✅ዋልያ
✅ገንበራ
✅ፉጨና
✅ዶጋው
✅ሙሴባንብ
✅ኩርቢ
✅ጅንግር
✅ማሪያምዬ
✅መሬና
👉3,ማእከላዊ አርማጭሆ ወረዳ
✅በደይ (ጭርክኝ)
✅ደረቅ አንቦ
✅ደለሣ
4,ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ
✅ሞገሴ
✅ማህርሽ
✅ቶርካ
👉5,ጭልጋ ወረዳ
✅ዳዋዳንጉራ ንዑስ ወረዳ
በሥር 7ቀበሌዎችን የያዘ
👉6,መተማ ወረዳ ቀጠና
✅አበባ መስክ
✅አለንጌ
✅ናዝሬት
✅ጋጅ
✅ላምሽ
✅ወርኪ
✅ዘባጭ ባህር
✅አቸራ
✅አሻሚት
✅ላስታ
✅መሽኀ
✅አጋም ውሃ
✅ታጉር
✅ ደለሎ ቁጥር አንድ የሚገኙበት ሲሆን በውስን አካባቢ ተከማችቶ የሚገኘውን የጠላት ዓብይ አህመድ ወረሪ ሰራዊት የማፅዳት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
©አርበኛ ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ የአፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ
ብዙ ገንዘብ በባንክ (በተለይ CBE) ያላችሁ ባለሀብቶች በየቀኑ አካውንታችሁን ተከታተሉ!
ዝርዝር አያስፈልገውም!
ኢትዮጲያ ከየት ወደ የት??
*
ቀውስ ጠማቂው የብልፅግና አገዛዝ በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ አድስ የማያባራ ጦርነት ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል።
በተለይም የአፍሪካ ቀንድ ጅኦ ፓለቲካ ተለዋዋጭ በሆነበት ምስራቅ አፍሪካ እና ከቀይ ባህር ጋር የተያያዘው የገልፍ ሃገራት ፍላጎት በኢትዮጲያ ሃገረ መንግስት ላይ አድስ ፈተና ሆኗል።
በወታደራዊ ቴክኖሎጅዎች እና ፋይናንስ እገዛ በአፍሪካ ቀንድ ያሉትን ሃገሮች ሰላም የመንሳት ፕሮጀክት ከፋረንጆች 2021 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የግጭት መነሻቸው ደግሞ የምዕራባውያንና የገልፍ ሃገራት አጋጭቶ አደር ፓሊሲያቸው ውጤት ነው!!
በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ የሚካሄዱት ጦርነቶች እና ግጭቶች ዓላማቸው ቀጠናውን የሙት መንግስታት /የደካማ መንግስታት/ መናሃሪያ ለማድረግ ሲሆን ሃገራቱ ራሳቸውን ችለው እንዲቆሞ ነው።
በውክልና ጦርነት የውስጥ ሰላምን ማናጋት ነው።
አልያም ሃገራት ልክ እንደ የመን እና ሊቢያ ማድረግ ነው።
ቀጥሎ በውክልና ጦርነት እንዲፈርሱ ወጥመድ ውስጥ የገቡ ሃገራት ደግሞ ሱዳን፣ኢትዮጲያ፣ጅቡቲ፣ሶማሊያ እና ኬንያ ይገኙበታል!!
በተለይም ሱዳንና ኢትዮጲያ ላይ የተባበሩት አረብ ኤምሬት /UAE/ የምስራቅ አፍሪካን የሃይል የበላይነት ለመያዝ በሚል ሙሉ የሃገራቱን የውስጥ ሰላም እያናጋችው ትገኛለች!!
የUAE ዓላማ በሱዳን እና ኢትዮጲያ የእርስ በእርስ ግጭት የቀይ ባህር ቀጠናን መቆጣጠር የሃገራቱ ሃብት ጭምር የመቀራማት ዕሳቤ ነው።
በአብይ አህመድ ይሁንታ አማካኝነት ለሱዳን ፈጥኖ ደራሺ ሃይል በርካታ ድጋፎችም እየተሰጠ ይገኛል!!
የUAE በኬንያ የሚገኘውን ላሙ ወደብን ድርጅቷ በሆነው/ Depi world / አማካኝነት ለረጅም ዘመናት የገዛችው ሲሆን ቤሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ አካባቢ /RSF/ የሱዳን ፈጥኖ ደራሺ ሃይል ላቋቋመው አድሰ ወታደራዊ ቤዝ ድሮንን ጨምሮ ከባድ መሳሪያዎች እየገቡ መሆኑ ታውቋል!!
የአብይ አህመድ መንግስት የኢትዮጲያን አንጡራ ሃብትን ለUAE አሳልፎ በመስጠት በርካታ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሺ ቅርሶችን እያወደመ ሲሆን በዋናነት ወርቅን በኮንትሮባንድ ከናይጀሪያ እና ከቱርክ ጭምር ወደ ሃገር ውስጥ በማስገት ለሙሃሙድ ቢንዛይድ መንግስት እየሰጠ ይገኛል!!
የብልፅግናው አገዛዝ ሃገረ መንግስቱ ማህበራዊ መሰረት የሌለው፣የተደራጀ የፓለቲካ፣የኢኮኖሚ እና የውጭ መለሰ የሌለው የደካማ መንግስት ባህሪያትን እንኳ የማያሟላ ነው።
በአብይ አህመድ አገዛዝ እና ቡድኑ ኢትዮጲያ ልትበተን ጫፍ የደረሰች ሃገር ሆናለች!!
ተምኔታው ሃሳብ እንጅ ኢትዮጲያ በ9 ክልሎች በ02 ከተማ አስተዳደሮች የተዋቀረችበት ሃገር ነበረች!!
አሁን ግን ህገ መንግስቱ በጣሰ መልኩ ሌላ 04 ክልሎች ተወልደዋል!!
so ወሰን አልባ እና ድንበር የሌላት የአንድ ሰውን ሃገር ሆናለች!!
የሃገሪቱን ድንበሮች ይጠብቃል የተባለው መከላከያ ስራዊት ደግሞ የአብይ መንግስት ስልጣን አስጠባቂ እና የራሷን ህዝብ የሚጨፈጭፍ ነው።
!!በጎረቤት ሃገራት ታጣቂዎች ጭምር ሉአላዊነታችን ተደፍሯል።
የደቡብ መዳን የታጣቂዎች፣አልሸባብ እና RSF ማሳያ ናቸው!!
የይስሙላ ም/ቤቶቻችን ውስጥ የትግራይ እና የተወሰኑት የአማራ ተወካዮች ጭምር የሉበትም!!
የሃገር መከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ የተሞላች ኢትዮጲያ የለችም!!
so ሃገሪቱ ወደ የት እየሄደች ነው??
ኢትዮጲያ በአብይ አገዛዝ እየፈረሰች ነው ስንል በተግባር ነው!!
አገርህን እና ህዝብህን የምትወድ ከሆነ በአብይ አህመድ አገዛዝ ላይ ተስፋችሁን መረጡ!!
የአብይ ስርዓት ሃገር አፍርሻለሁ እና ኢትዮጲያን ታሪኳን የሚያወድም ስርዓት ነው!!
ሃገርን ለባዕዳን አሳልፎ ፣ ታሪኳን አዋርዶ እና በፍርስራሿ ላይ አድሰ ሉአላዊ ሃገር ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት ህዝባችን ሊያከሺፈው እና ሃገርን ከብተና ሊያድን ይገባል!!
የሰሞኑ የጋምቤላ የእርስ በእርስ ጦርነት ጨምሮ በአማራ፣በትግራይ እና በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት መቋጫው ኢትዮጲያን ማፍረስ ነው።
የኢትዮጲያ ሃገር ሆኖ መቀጠል የሚያሳስባችሁ ሁሉ በአብይ አህመድ መንግስት ላይ ከአመፁ ሃይሎች ጎን ልትሰለፉ ይገባል!!
የሀገር ህልውና ጉዳይ የሚያሳስበው ማንኛውም ዜጋ ሃገሩን የማዳን ሃላፊነት እንዲወጣ እያሳስብን በአብይ አህመድ መንግስት እና በስርዓቱ ላይ ደግሞ የማያዳግም ዕርምጃ መውሰድ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው!!
አማራ ሆይ ንቃ!!
የኖህ መርከባችን የሆነውን አማራነት እንስራ!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዝንታለም አማራ
ወይራው አማራ
ታህሳስ 12/04/2018
ወልቃይትን ሰጪና ነሺ የሆነ ፋኖ የለም። ወልቃይት የግለሰብ ወይም የቡድን ጉዳይ ሳይሆን ወልቃይት የአማራ ሕዝብ ጉዳይ ነው ሲል አርበኛ አስረስ ተናገረ።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ ምክትል ሰብሳቢና የፖለቲካ ዘርፍ ሓላፊ አርበኛ አስረስ ማረ ከኢትዮ ኒውስ ጋር ቆይታ አድርጓል።
አርበኛ አስረስ በነበረው ቆይታ፡ አገዛዙ ትጥቅ ላስፈታ ብሎ ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሣሪዎችን እንዲሁም ዘመናዊ የሠለጠኑ ወታደሮችን ከጥቅም ውጭ አድርገናቸዋል። አገዛዙ ደመሰስናቸው አጠፋናቸው በሦስት ወራት እና በሁለት ወራት ውስጥ እናጠፋቸዋለን እየተባለ የነበረ ቢሆንም አልተሳካም፡ በዚህ ሂደት ለውጭ ሀገራትም ጭምር አሸንፋለሁ ብሎ ተስፋ እየሰጠ የነበረበት ክሥተት ነበር ብሏል።
አሁን አለሁ ለማለትና ተስፋ ለመስጠት የማታለል ሥራ እየሠራ ነው። ይኸን ሲያደርግም መንገድ እየዘጋ ዝርፊያና ግድያ እየፈጸመ ነው። አዳራሽ ውስጥ ሰላም ይሰብካል ከውጭ ዘግናኝ ነገር ይፈጽማል። ሕዝቡ ከብልጽግና ምንም ተስፋ አያደርግም ፍላጎቱ ፋኖ ጦርነቱን አሸንፎ እንዲመራ ነው።
አርበኛ አስረስ ብልጽግና በየከተማው ሕዝብ እያወያየ ነው ግን ፋኖ የት ነው ለሚለው ጥያቄ ሲያብራራ፡ ፋኖ በየትኛውም ቦታ አለ ሕዝብ እያስተዳደረ ነው። ግን አገዛዙ ሪሶርሱን ለመጠቀም እየሞከረ ለአጭር ሰዓት እየሰበሰበ ነው።
መንግሥት የለም። መንግሥት አለ የሚባለው መዋቅሩን በትክክል ተግባራዊ ሲያደርግ ነው። አለን ለማለት ከተማ ላይ ይገኛሉ እንጂ የተለየ ነገር የለም። ከአዳራሻቸው ራቅ ብለው ተንቀሳቅሰው መሥራት አይችሉም። መንግሥት የሚባለው ሚዲያና ሌላ ሪሶርስ ስላለው እያስተዳደርሁ ነው ብሎ ይናገራል። እኛ ከባሕር ዳር ጎንደር፣ ከባሕር ዳር ደብረ ማርቆስ በአንድ ትዕዛዝ መንገድ እየዘጋን ነው። እናም ብልጽግና በዘመቻ ነው ስብሰባዎችን እያደረገ ያለው። በዘመቻና በስብሰባ መንግሥት መሆን አይቻልም። ከዚህ በፊትም እነ አበባው ታደሰና የክልሉ ካድሬዎች በኮምፖልቻና በሌሎች ከቶሞች ስብሰባ ሲያደርጉ ነበር ግን የተለየ ለውጥ የለም ነው ያለው አርበኛ አስረስ።
መንግሥት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴና ዘመቻ ሁሉን አቀፍ በመሆኑ በሕዝባችን ላይ ከባድ ጫና ስለተፈጠረ በሕዝቡና በአገዛዛዙ ዘንድ ከፍተኛ አለመተማመን ተፈጥሯል። በእያንዳንዱ ገጠርና ከተማ ያለን ሕዝብ ብንጠይቀው መንግሥት ይጨፈጭፈኛል ብሎ ነው የሚያስበውና ባለፉት ዓመታት የተሠራው ግፍ በሕዝቡ ላይ ከባድ ተጽኖ አሳድሯል። ሆኖም አገዛዙ ሠራዊት ስላለው የቴክኖሎጂ ብልጫ ስላለው ከተማ ላይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል። ነገር ግን በእኛ ላይ የሚያመጣው አንዳች ተጽኖ የለም። በሚዲያ መሠረታዊ ለውጥ ሊያመጣ አይችልም። ከዚህ በፊት ሲያደርጋቸው የነበሩትን ነው እየፈጸመ ያለው ብሏል።
አርበኛው ቀጥሎም፡ መዋቅሩ ፈርሷል ስንል ፕሮፓጋንዳ እየሠራን አይደለም። ሕዝብን በአዳራሽ ሰብስቦ ሽማግሌዎችንና ሌሎች ተሰብሳቢዎችን ፋኖን ለምኑልኝ አስታርቁኝ ማለቱኮ አንዱ የውድቀቱ ማሳያ ነው። በብልጽግና መዋቅር በኩል የአማራን ሕዝብ የሚወክል አካል የለም። ብአዴንም ፈርሷል። ለዚያም ነው በመከላከያ ክልሉ እየተመራ ያለው። እናም በአዳራሽ ውስጥ የሚደረገውም ሐሜት ነው እንጂ ሐሳብ ላይ አያተኩሩም። ለዚያም ነው ጠቅላይ ሚንስትሩም ጩኸት ነው እያለ ሐሳባችንን ሲያጣጥል የነበረው። አክቲቪስታቸውም ካድሪያቸውም ወታደራቸውም ቋንቋቸው አንድ ነው የተሻለ ሐሳብ የለም። ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ሲሄድም በደፈጣ ውጊያ ዋጋ ከፍሎ ነው።
አርበኛ አስረስ ስለ ፋኖ ሥነ ምግባር ሲናገር፡ ከዚህ በፊት እንዳልሁት የፋኖ ስብስብ የመላእክት ስብስብ አይደለም፣ ከተለያየ ቦታ የመጣ ነው፣ አዲስ ኃይል ነው፣ የማኅበራዊ ንቅናቄ ውጤት የሆነ መሪና ሠራዊት ነው ያለንና ችግር ሊፈጠር ይችላል። በትግል ሂደት ውስጥ ሊከሠት የሚችል ነው። ሠራዊቱን እያሠለጥን ነው እየፐወዝነው ነው። አሳሳቢው ይኸ ሳይሆን የአገዛዙ የጅምላ ደፈራና ዝርፊያ እንዲሁም ግድያ ነው። ግን አገዛዙ ፈጥሮም ሆኖ ያየውን ትንሽ ስሕተት ያጮኸዋል። ዓላማውም ፋኖ የፖለቲካ ዓላማ እንደሌለው ለማስመሰል ነው ነው ያለው።
ዐቅም ካለው ማስተካከልና ማሸነፍ ይችል ነበር፣ ግን ምርጫው መጮህ ብቻ ነው ምክንያቱም ማድረግ ስለማይችል። ሌላም ግድያውን ማቆም የማይችለው እንደ ጦር ስልት ስለወሰደው ነው መንገድ ዘግቶ የሚገድለው የሚዘርፈው።
የእኛ ትልቁ ክፍተታችን የፋኖ አንድነት አለመኖር ነው። በዚህ ጉዳይ ማስተባበል አያስፈልግም። ትግሉ ስለትና ጠንካራ አንድነትና መሪ ይፈልጋል። ባለፉት ጊዜያት የነበሩት የሕዝባዊ ትግልና የመዋቅር መፍረስ ዘመቻ ውጤታማ ትግል ነበር። አሁን ግን አንድነት ባለማምጣቱ እንደ አንድ ችግር ሊወሰድ የሚገባና ሁሉም አመራር ሓላፊነት ሊወስድ ይገባል። በሁሉም ቀጠና ያለ አመራር ደፍሮ ለአንድነቱ ታሪካዊ ውሳኔ ሊወስን ይገባል ብሏል አርበኛ አስረስ።
አርበኛው ስለ ወሰንና ስለ ባንዳዎች ሲናገር፡ ብልጽግና ከኢሕአዴግ ከወረሳቸው ልምዶች አንዱ ጉዳዮችን ከሻብያና ከወየኔ ጋር ማገናኘት ነው። እናም አሁን ፋኖ ወልቃይትን ለህውሓት ይሰጣል ህውሓት ደግሞ አራት ኪሎን ለፋኖ ይሰጣል የሚለው የባንዳዎች ንግግር ከንቱ ወሬ ነው። ህውሓት ምን በወጣው ነው አራት ኪሎን ከተቆጣጠረ በኋላ ለፋኖ የሚሰጠው? አሁን እያየነው ያለ ነገር የባንዳዎች የወሬ ወይም የፕሮፓጋንዳ ፉክክር የገጠሙ ዐቢይን ለማስደሰት ነው። ዐቢይንና የብልጽግናን መዋቅር ለማስደሰት የሚደረግ ነው።
አሁን እጅ ሰጡ የተባሉት ግለሰቦች እንደማይጠቅሙ ያወቅናቸውና የጣልናቸው ገና ድሮ ነው። አመራር ነን ብለው የቆዩት የፋኖ አንድነት ስላልመጣ ነው። አሁን ወጥተው ቢናገሩም ምንም የሚያውቁት ምሥጢር የለም። የከዱ ባንዳዎች ቢገረፉም የሚናገሩት የኮር ሊደር ሺፕ ንግግር፣ ምሥጢርና ምክክር የለም። የአርቲስቶችን ድራማ ነው የሚያወሩት። ሌላው ወልቃይትን ሰጪና ነሺ የሆነ ፋኖ የለም። የግለሰብ ወይም የቡድን ጉዳይ ሳይሆን ወልቃይት የአማራ ሕዝብ ጉዳይ ነው። እንደዚህ የሚናገሩት የአማራን ሕዝብ ስለናቁት ነው ሲል ነው የገለጸው። አርበኛ አስረስ ስለ ዐቢይ ዲፕሎማሲ ሲናገር፣ ዐቢይ ጭራሽ የዲፕሎማሲን አካሄድ አያውቅም። አይዲዎሎጂ የለውም። በዚህ ዘመን ዲፕሎማሲ ማለት ሰጥቶ መቀበል ነው። አማራጭ ገበያዎችን ማጥናትና ትኩረት ማግኘት ያስፈልጋል። ከዚህ በፊት የደህንነት ጉዳዮችን ስትሸጥ የነበረች ሀገር ናት። ልምድ ያላት የዲፕሎማሲ ሀገር የነበረች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትትና ተመድን እንዲመሠረት ያደረገች አባልም የነበረች ናት።
ዐቢይ አሕመድ ከሕንድ መሪ ጋር ፎቶ መነሳቱ ለዝናው እንጂ ለሀገሪቱ ምንም አይጠቅምም። ሕንድ ምን ትሰጣለች ኢትዮጵያ ምን ትቀበላለች የሚለውን ማየት ግድ ይላል።
በፊት ከቱርክ ጋር ከቴክስታይልና ከባቡር ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበር አሁን ግን ግንኙነቱ በድሮን ጉዳይ ነው። የትም ሀገር ሂዶ በጦር መሣሪያ ዘሪያ ግንኙነት ነው እያደረገ ያለው። በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ጦርነት ላይ ስለሆነች ምንም የምትሰጠው ነገር የለም። በመጨረሻም የፋኖ ተጋድሎን ሰላምንና ሕልውናን የሚፈልግ ሰው ሁሉ መደገፍ አለበት። ሁሉም የራሱን ድርሻ መወጣት አለበት ሲል ተናግሯል አርበኛ አስረስ።
#በድሮን_የታገዘ_ዉጊያ_በሰከላ_ወረዳ_ተካሄደ‼
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር እና 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ጥምር ሀይል በድሮን የታገዘዉን ተጋድሎ በመቋቋም ከተለያዬ አካባቢ ተሰባስቦ የመጣውን በርካታ አረመኔ ቡድን አጉት ላይ ደምስሶታል‼
በትላንትናው ዕለት ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 እስከ ምሽት 1:00 ድረስ በተደረገዉ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ሰከላ ወረዳ አጉት ቀበሌ ዙሪያ ከሚገኙ ሁለት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ መሽጎ የሚገኘውን ዙፍን ጠባቂ ሰራዊት የያዘዉ የድንጋይ ካብ ሳያተርፈው ተደምስሷል።
ለተከታታይ 3 ሰሃት በተደረገዉ የእጅ በእጅ የቦምብ ትንቅንቅ ለማትቀረዋ የነገ ነፃነት፤ ጀግኖቹ 44ኛ እና 77ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎች ዉድ ዋጋ በመክፈል ጡት ቆራጩን ቡድን፣ ጡትና ምላስ ብልት በቆረጠበት፤አሰቃቂ ድርጊት በፈፀመበት ሰከላ ቀጠና አጉት ላይ ቀብረዉ አስቀርተዉታል።
አረመኔው ቡድን ለሳምንት ሲቆፍር ሲዘጋጅበትና አንገት ድረስ ሲሰራዉ የሰነበተዉ ምሽግ በነበልባሎቹ ሲደረማመስ መድረሻ ያጣዉ ወንበዴ ቡድን በእግር አልችል ብሎ በድሮን የታገዘ ዉጊያ በማድረግ ተከታታይ ሁለት የድሮን ቅንቡላ ቢጠቀምም ከመደምሰስ አላተረፈዉም።
ቤተክርስቲያንን፣ንፁሃንንና፣ተራራ ላይ ጉድጓድ እንደ ቀበሮ በመቆፈር ለማምለጥ የሚሞክረዉ ዙፋን ጠባቂዉ ሰው በላው ቡድን በጀግኖች ከባድ ምት ተደቁሶ በቆፈረዉ ጉድጓድ አፈር ለብሶ ቀርቷል።
በ105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር እና በ109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ጥምር ሀይል የደረሰበትን ሽንፈት መቋቋም ያቃተው ጡት እና ምላስ ቆራጩ የጠላት ሀይል ከሽንዲና ከተለያዬ ቦታ በማሰባሰብ መቀበሪያው ወደ ሆነው ወደ ሰከላ ወረዳ አጉት ከተማ ተጨማሪ ሀይል አስገብቷል።
#ላንጨርስ_የጀመርነዉ_ትግል_የለም_ድላችን_ቅርብ_ነዉ_እንበርታ💪
#በደማችን_ታሪካችንን_እናድሳለን💪
የ44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ‼
ያልተነገረለት አንድ ጀግና ላስተዋውቃችሁ
👉ፋኖ ኤፍሬም ባዩ ይባላል በሽዋ ክፍለሀገር በይፋትና ጥሙጋ በላኛው ሳራባ የሰርዶ ቀበሌ በ1980 ዓ.ም ከአባቱ ከአቶ ባዩ በላቸው እና ከእናቱ ከወ/ሮ የሸዋጣይ መግስቱ ተወለደ፤
እድሜው ለትምር ሲደርስ ከ1-8ኛ ክፍል በበርግቢ ትምርት ቤት ትምርቱን መማር ቻለ ፤ በዚሁ በመቀጠል ከ9-10ኛ ክፋል በአጣዬ ሁለተኛ ደረጃ ተምሮ በማጠናቀቅ በደብረብርሀን መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲፕሎመውን በሂሳብ ተመረቀ ።
አርበኛ ኤፍሬም እጅግ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነበረ በስነምግባሩ ዝምተኛ ጨዋ እደሆነ ይነገርለታል ። ተወልዶ በአደገበት አካባቢ ህብረተሰብ ፈገግ ከማለት ውጪ እና ሰውን በጣም ያከብራል በትምርት ቤትም እስፖርታዊ ጨዋታ በተለይ መረብ ኳስ ይጫወታል ። በ2000 ዓ.ም የበርግቢ ጉድኝት ማዕከልን ትምርት ቤት ወክሎ ተከሰያት ጉድኝት ማዕከልትምርት ቤት፣ ከመኋል ወዝ ጉድኝት ትምርት ቤት ፣ከመስቀልበር ጉድኝት ማዕከል ትምርት ቤት እና ከሉልጌ ሰረት ጉድኝት ማዕከል ትምርት ቤት በ400 ሜትር ሩጫ አንደኛ በመውጣት የተጨበጨበለት በውድድሮች ላይ በመረብ ኳስ እና በእግር ኳስ ጨዋታ በመወዳደርም የተሻለ ብቃት አሳይቷል አንዳንድ ሰዎች ይሄን ብቃቱን ይኮሩበታል ።
አርበኛ ኤፍሬም በ2006 ዓ.ም በቀወት ወረዳ ትምርት ፅፈት ቤት ልዩ ስሙ እራሳ ጅምደሬ ትምርት ቤት በሂሳብ መምህርነት ተመድቦ በዚሁ ትምርት ቤት ሂሳብና ፊዚክስ ሲያስተምር ቆይቶ የተሻለ ጠንካራ መምህር እደሆነ ተማሪዎች ፣ መምህራን እና ወላጆች ይመሰክሩለታል። ከ2007 -2009 ዓ.ም በኤፋራታና ግድም ወረዳ በላ/ሳ/የሰርዶ ቀበሌ ጎሽበር ትምርት ቤት ተመድቦ መስራት ጀመረ በዚህ ትምርት ቤት በመምህርነት እና በተወካይ ርዕሰ መምህርነት በመስራት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ቻለ ከሰዎች ጋር ተግባቢ ትምርት ቤቱ በወረዳ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ ስሙ በአደባባይ መጠራት መታወቅ ጀመረ አድናቂዎት ከተማሪዎች ፣ በአካባቢው ህብረተሰብ ፣ ከመምህራን ፣ሌሎች ትምርት ቤቶች እና በወረዳ ደረጃ ታዋቂ ሆነ እጅግ በጣም ታታሪ ጎበዝ እና ጠንካራ ነው ።
ከሚታወቅባቸው ስራዎቹ ተማሪ በማብቃት እና 2008 ዓ .ም በተማሪ ምዝገባ በወረዳ ደረጃ አንደኛ ወጣ በወረዳ ትምርት ፅፈት ቤት ሀላፊ በአቶ አፈወርቅ እውቅና ተሰጠው በዚሁ አመት ትምርት ቤቱ በስራ አፈፃፀም እውቅና አገኘ አቅሙ እየጎለበተ መጣ መምራት እና ማስተባበር በህዝብ ላይ ቅቡልነት አገኘ። በ2010 ዓ .ም በፈረዶ ወሀ ትምርት ቤት ተመደበ የተሻሉ ስራዎችን እየሰራ አመቱን አሳለፈ ። ከዚህ ትምርት ቤት እየሰራ ካለ በ2011ዓ.ም የበርግቢ ትምርት ቤት ርዕሰ መምህር ሆኖ ተመደበ ባለው እውቀትና ልምድ ጠክሮ በመስራት የትምርት ቤቱን ችግሮች በመለየት በትኩረት መስራት ጀመረ ትምርት ቤቱ ላይ
ከሰራህቸው የሚስደስቱህን ስራዎች ንገረኝ ስለወ በትንሹ የነገረኝ ።
1ኛ.የትምርት ቤቱ እና የህብረተሰብ ግንኙነቱ የሻከረ ነበር መፍታት ችያለሁ ህዝቡ ወደ ትምርት ቤት አይመጣም ነበር እዲመጣ ማድረግ ችያለሁ ። መነሻዬ ተማሪዎችን እጠቀማለሁ ሪፖርት የተሰሩ ስራዎችን በጥንካሬ እና በጥረት ሪፖርት አቀርባለሁ ለድክመቶቼ ምክንያቶቼን ለህዝቡ ይሄን ብታግዙኝ ብዬ እጠይቃቸዋለሁ ያግዙኛል።
2ኛ.ተማሪዎችን አወያያለሁ ትምርት ቤቱ ምን ያግዛችሁ ጠንካራ እድትሆኑ ብዬ እገመግማለሁ ትኩረት ሰጥቼ እሰራለሁ
3ኛ.ከመምህራን ፣ ከወላጅና መምህራን ተወካዎች እና ከቀበሌዎች ጋር ተናብቤ እሰራለሁ አለኝ ።
4ኛ. እነዚህን እና ሌሎች ተግባሮችን ለቅሚ በመስራት በጉድኝት ፣ በወረዳ እና በዞን የሚሰጡኝን አስተያየቶች አዲሁም ቼክሊስቶችን የእቅዴ መነሻ አድርጊ እሰራ ነበር በማለት ነገረኝ ።
ካደረካቸው መልካም መልካም ስራዎች ንገረኝ ብዬ ጠየኩት እዲህ ብሎ ነገረኝ። ትምርት ቤቱ በኢንስቤክሽን ሲለካ ደረጃ ሁለት ነበር በዚህ እናደድ ነበር አለ ። ምን መፍተሄ ወሰድክ ? አልኩት ዕቅድ አቅጄ በመስራት እዲገመገም አድርጌ ደረጃ ሶስት አስገባሁት አለ። ታዲያ ምን ተሰማህ ? አልኩት ስኬት አለኝ። ተማሪም ፣ መምህርም ሆነ እርሰ መምህር ሆኖ የተሻለ የስራ አፈፃፀም እዳለው አረጋግጫለሁ ።
እስከ አሁን የትምርት ዝግጅትህ ምን ላይ ነህ ብዬ ጠየኩት ? እዲህ አለኝ መማርን ያቆምኩት ፍኖ ስሆን ነው አለኝ ማለት ? አልገባኝም ስለው እዲህ አለኝ accouting እና Educational planing managimet ድግሪ ተምሪያለሁ በባህርዳር ዪንበርስቲ Disayn and Drouing አራት አመት ተምሪያለሁ ግን አልጨረስኩትም ፍኖ ስቀላቀል አቋረጥኩት አለኝ ። አልጨረስክም አልኩት ? እዲህ አለኝ ፍኖነትን መረጥሁ አለኝ።
አርበኛው እስከ 2015 ዓ.ም በትምርት ቤት ግዜውን አሳልፎ የአማራ የህልውና ትግል ሲጠናከር ስረውን ትቶ ወደ አማራ ፍኖ ተቀላቀለ የ7ለ70 ብርጌድ ሲመሰረት ለአንድ አመት ተኩል የብርጌዱ ፖለቲካ ዘርፍ ሆኖ ሲሰራ ቆየ። በ2017 ዓ.ም ግማሽ አመት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሣምነው ዕዝ ምክትል ፖለቲካ መምሪያ ሀላፊ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። በህዝብ ማንቃት ፣ ምሁራንን በማደረጀት እና ሰራይትን በመገንባት ልዩ ችሎታ አለው ይሂም ሲባል ከሚሰራቸው መልካም ስራዎች መካከል።
1. የፍኖ የትጥቅ ትግል አመሠራረትን እና አሁን ፍኖ የደረሰበትን ደረጃ አጉልቶ በማሳየት ።
2.ገዢ ፖርቲው ብልፅግና በአማራ ህዝብ ላይ ያደረሰውን በደል ጀምላ ግድያ ፣መፈናቀል እና ዘረፍን ጎልቶ በማሳየት ምሳሌ በመስጠት ሰፊ ስራዎችን ሰርቷል።
3.አጫጭር ሰልጠናዎች እና መግለጫዎችን በማዘጋጀት ።
4.ህዝቡን በጎበዝ አለቃ እና አባት አርበኛን በማደራጀት ሰፊ ስራዎችን ሰርቷል ።
አርበኛ ኤፍሬም ባዩ ለአለመለት አላማ ቀጥ ያለ አቋም ያለው ሰው ነው ። ለውሳኔዎች የማይቸኩል የተረጋጋ በሀሳብ የበለይነት የሚያምን የሰዎችን ችግር የሚረዳ ምክረ ሀሳቡ ገቢ መምከር የሚችል ሀሳብ ያለው ልታይ ልታይ የማይል ዝና የማይፈልግ ተወደደ ፈገግ የሚል ከጠላ ፊቱ የሚኮሳተር ለጠላት ቦታ የሌለው ሰው ነው። ምንግዜም በራሱ የሚተማመን ጓደኞቹ አክባሪ ሆደ ሰፊ ነው ። ለአማራ የህልውና ትግል ስረውን እና ቤተሰቦቹን በትኖ የወጣ ነው ።
ይቀጥላል.................
የተቋም እህልን ለመዝረፍ የመጠው የአገዛዙ ወራሪ ዘራፊ ኃይል በ64ኛ ክፍለ ጦር ጥምር ኃይል እና 1 ሬጅመንት ተደምስሶል።
ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ጥምር ኃይል እና 1ኛ ሬጅመንት ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት በሸበል በረንታ ሱሃ ተፋሰስ ቀበሌ ልዩ ቦታ ስኩት እየሱስ የተቋም እህልን ለመውሰድ የመጠው የአገዛዙ ወራሪ ዘራፊ ኃይል ላይ F1 ቦንብ የታገዘ የጨበጣ ውጊያ አድረገዋል።
በሸበል በረንታ ሱሃ ተፋሰስ ቀበሌ የተቋም እህልን ለመዝረፍ ከቢቸና፣ የዕዱኃ እና መርገጭ ከተማ የተሰባሰበው የአገዛዙ ዘራፊ ኃይል በጀግኖቹ የበላይ ዘለቀ እና የሽፈራው ገረባው ልጆች በአደረጉት ከባድ ተጋሃድሎ አገዛዙ በየጣሸው ሙት እና ቁሰለኛውን አንጠባጥቦ ያቀደውን እቅድ ሳያሳካ ተቅበዝብዞ ቀረቷል። በዚህ እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያ የአገዛዙ ዘራፊ ሀይል በቁጥር ማወቅ ያልቻልነው በረካታ ሙት እና ቁስለኛ ሆኗል።
64ኛ ክፍለ ጦር ወታደራዊ መሪዎች እና የፋኖ አባላት በ
ባደረጉት ተጋሃድሎ የአገዛዙ ኃይል ከቢቸና፣ የዕዱኃ መረገጭ ከተማ ተጨማሪ ሀይል በመያዝ በሱሃ ተፋሰስ ቀበሌ የኮሬ የኩበት እና ስኩት እየሱስ ቦታዎች ላይ በየጣሸው እና በየገደሉ የወደቁ ሙት እና ቁስለኞችን በመጫን ወደ መጣበት ቦታ ተመልሶ ሄዶል።
✍️ ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ
201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
በቢቡኝ ወረዳ የሚገኙ የከተማ ነጋዴ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ተካሂዷል።
ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም
በቢቡኝ ወረዳ ዋበር ቀበሌ የኮር እና የክፍለጦር እንዲሁም የወረዳው ጊዜያዊ መንግስት እና አመራሮች ከከተማው የነጋዴ ማህበረሰብ ጋር ውይይቶችን አካሂደዋል።
በወረዳው ዋበር ከተማ አጠቃላይ የነጋዴውን ክፍል መሠረታዊ ጥያቄወች በየደረጃው ነቅሶ በማውጣት ከህዝቡ ጋር የጋራ የሆኑ ጥያቄወች የተነሱ ሲሆን፦
➦ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን
➦ ህገ-ወጥና ግንባታ
➦ የገበያ የንግድ ቦታወችን በተመለከተ የከተማው ነጋዴ ተጠቃሚው ማህበረሰብ የሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌወች ወጣቶች በተገኙበት የጋራ መፍትሄ የተሰጠ ሲሆን ውሳኔው እንደሚከተለው ቀርቧል
1ኛ .ድንች፣ገብስ፣ ጌሾ፤እንቁላል እና የመሳሰሉት የንግድ አይነቶች በምስራቅ እስከ ቅዱስገብርኤል ቤተክርስቲያን በምዕራብ እስከ ፀደይ ባንክ በሰሜን እስከ ሁለተኛው መስመር በደቡብ ዋናውን መስመር ተከትሎ እንዲሆን
2ኛ .ወለቄ ፣ፍልቅልቅ፣ሚካኤል፣ሲቀረኝ ምንም አይነት የንግድ ግብይትማድረግ የተከለከለ ነው
3ኛ .ህገ-ወጥ የመጋዘን ቤት ከፍተው የነበሩ ወንድሞች ከዛሬ ቀን ጀምሮ መግዛት የማይችሉ ሲሆን የገዙትን ለመሸጥ እስከ ታህሳስ 30 ድረስ እንዲሸጡ ተወስኗል።
4ኛ .መጋዝኑን የዘጋንባቸው ነጋዴወች በዝርዝር ተለይተው አዲስ ከተሰራው የገብርኤል መጋዘን በድሮው መጋዘን የጫራታ ዋጋ መሠረት ቤተክርስቲያኑንም ሆነ ነጋዴወችን በማይጎዳ መልኩ በተመጣጣኝ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ተከራይተው እንዲሰሩ ተወስኗል።
5ኛ .በክርክሩ ምክኒያት ከተለያዩ ማህበራዊ ኑሮ ማለትም ከእቁብ፣ከእድር፣ከሰንበቴ እና ማህበርን ጨምሮ እንዳይገለሉ ተወስኖላቸዋል። ሌሎቹ ልማዶች እንደነበሩ ይቀጥላሉ። በመጨረሻም የአማራ ፋኖ ትግል አሁን ላይ የደረሰበትን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ አጭር ግንዛቤ የማስጨቀጥ ስራ ተሰርቷል።
አዲስትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ጊዜያዊ መንግስት አስተዳደር
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የድርጅቱ ተወርዋሪ ኮማንዶ ሃይል
ወሳኝ እር*ምጃ በጣም ወሳኝ እርምጃ ወሰዷል።
👉ከደንበጫ እስከ ፋኖተ-ሰላም
👉ከፍኖተሰላም -ቡሬ
ድረስ በየ 5ኪ.ሜትር በማይሞላ ርቀት ኬላ በመዘርጋት ማህበረሰቡን ሞባይል ስልክ ሁሉ ሳይቀር ይ*ዘ*ርፋ የነበሩ፤ ህዝቡ ተሰላችቶ የብልፅግና ደጋፊ እንዲሆን ጠላት በስው*ር ያደራጃቸው ሌ*ቦች #በቴዎድሮስ_ዕዝ_ኮማንዶ_ክፍለጦር እና #77ኛ_ክፍለጦር እር*ም*ጃ ወስ*ዶባቸዋል!
የህዝብ ድምፅ ቶሎ ስለሰማችሁ እናመሰግናለን በርቱልን 💪💪💪
ከራያ አፋፉ ላይ ያ ግድም ያ ግድም፣
ጀግና ወቶበታል
ያ ምሬ ወዳጆ ያሳምነው ወንድም፣
ጥይቱ አይናማ ነው ከተኮሰ አይስትም፣
ምሬ ወዳጆ አመለ ሸጋው የዘሜ ወንድም፣
የደሱ ወንድም ፣
የሳሚ ወንድም፣
Belayneh Setarge እንደከተበው
ስሙም ግብሩም የተመሳሰለለት ዋርካው ምሬ ወዳጆ!!
ዋርካው እውነትም ዘርፋፋ ዋርካ ነው:: ይህን ጀግና በዕለት ተዕለት የሰራዊቱ ጀብዱ እናውቀዋለን:: ምስራቅ አማራ ቀጠና ውስጥ ያለውን ወጣት አደራጅቶ በማታገል ላይ ያለ ጀግና ነው::
"ሲርባቸው ይመጣሉ" ያሉትን አይ "እነሱ ሲገባቸው ይመጣሉ" በሚለው አባባሉ ብቻ ሳይሆን "ለአይን ትንሽ ለጆሮ ብዙ አትሁኑ" ሲል ባስተላለፈው መልዕክት እናስታውሰዋለን:: "ሲገባቸው ይመጣሉ" ያላቸው እነሆ መጥተዋል::
"ሲገባቸው ይመጣሉ" የሚለው ንግግሩ የአስተውሎቱ ማሳያ መሆኑን ልብ ይሏል:: የነብዩ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ምትክ የሆነው ዋርካው ምሬ ወዳጆ ነገሮችን አጢኖ መጭውን ጊዜ የመተንበይ ቅዋ ጭምር አለው:: ለዚህም ነው መጭውን እና ሀጅውን ቀድሞ የለየው:: "
ማርኮም ይሄድና ሶልዲውም ያልቅና:)
እንዳንተዛዘብ ይሄ ቀን ያልፍና....በማለት ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ አምና ያስተላለፈውን መልዕክትም አንረሳውም:: የዘሜ ወንድም ዋርካው ጭምር "ሲገባቸው ይመጣሉ" ብሏል::
"ሞትን አልፈራም፤ እኔ ቀድሜ እሞትላችኋለሁ...ሙሀመድ ቢሆነኝ ሞትን አስተምሮኛል" ያለውም ዋርካው ነው:: "ገንዘብ ስታዩ አትደንግጡ" ሲልም መክሯል::
ስለ ሽምቅ ውጊያ ሲያስተምርም "አስር ገለው ቢቀልጡ ምንድነው ጌጡ" የሚላት ወርቃማ ንግግር አለች:: በዚህ መልኩ በምሳሌ እየተናገረ ሽምቅ ጠላትን መትቶ የመሰወር ብቃት መሆኑን ለሞት አይፈሬው ሰራዊት አስገንዝቧል::
በነገራችን ላይ አንዳንድ ሰው ስመጥሩ ይሆንና በግብር ሲገለጥ ደግሞ ስም ብቻ ሊባል የሚችል ይሆናል ነገር ግን ዋርካው ምሬ ወዳጆ እውነተኛ ዋርካ መሆኑን በነበረን ቆይታ ተረድቻለሁ::
ባለፈው እሱ ወዳለበት ቀጠና ተጉዘን ስለነበር ዋርካውን በአካል የማግኘት ዕድሉን አግኝተናል:: እኔም ያን በስራው እና በሚዲያ የማውቀውን ዋርካው ምሬን በአካል አግኝቼ ለማነጋገር በመቻሌ እጅጉን ደስ ብሎኛል::
በቆይታችን ዋርካው እጅጉን አስተዋይ እና ሊቅ መሆኑን ነው የተረዳሁት:: ከዚህ በተጨማሪ ከመጠን ያለፈ ማለትም ምድርን ወረቀት ውቅያኖስን ቀለም አድርገን ብንፅፈው ቃላት የማይገልፁት ደግነትን የተላበሰ ወንድም መሆኑን ለመረዳት ጊዜ አልፈጀብኝም:: ንግግሩስ ቢሆን መቼ ይጠገባል!? ሊጠገብ የሚችል አይደለም!!
እንደ ታላቅ ወንድም ለሁሉም የሚሰጠው ምክር እና እንክብካቤስ ቢሆን መቼ አቻ አለውና!!?
በዙሪያው ያሉት ሁሉ የሚሉት ዋርካው ካዘነብህ አለቀልህ ነው:: ካዘነብህ ቸር ነገር አይገጥምህም ምክንያቱም ይህ ሰው ንፁህ ስለሆነ ለፈጣሪ ቅርብ ነው በቀላሉም ሰውን አይቀየምም ይልቁንስ በጣም ታጋሽ ነው ይላሉ:: ትዕግስቱን አሟጦ ሲያበቃ አይይይ ብሎ ካዘነብህ ውለህ አትገባም ሲሉ በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ:: ከውሀ የጠራው ከበረዶ የነጣው ንፁሁ መሪያችን ዋርካው ምሬ ወዳጆ በጀግንነትም አቻ የለውም:: እዚህ የደረሰው ጥርሱን ነክሶ ታግሎ አታግሎ ነው:: አንድ ቲም የማይሞሉ ወንድሞችን ይዞ የጀመረው ትግል ዛሬ አሸዋ የመሰለ ሰራዊትን የያዘ ዕዝን ወልዷል::
ዋርካው ምሬ ወዳጆ ለመሪነት የተፈጠረ ሰው መሆኑን ያወኩት የፓለቲካ ግንዛቤው እና የአመራር ጥበቡን ስገመግም ነው:: እኔ ፓለቲካል ሣይንስ ተምሬያለሁ እላለሁ እንጅ በእሱ ልክ የፓለቲካ መረዳት የለኝም:: ስለ ህዝብ አስተዳደር እንድሁም ስለ ሰዎች መብት እና ነፃነት ብሎም ስለ ፍትህ እና መሰል ጉዳዮች አንስቶ አውግቶኛል:: ስለ ግጭት አፈታት እና ስለ አማራ አንድነት ጭምር አጫውቶኛል::
የበቁ የነቁ እና እጅጉን አስተዋይ እንድሁም ጀግና የሆኑ መሪዎች አሉን::
"ሕዝቡ ጠልቶናል። ምግብ ለመመገብ ምግብ ቤቶች ስንገባ እንደማንኛውም ሰው እኩል አንስተናገድም።
አንዳንድ ነገሮችን ለመግዛት ወደ ገበያ ስንገባ ነጋዴው የአድማ ማብተና አባላት መሆናችንን ካወቀ በውድ ዋጋ ይጠራብናል ወይም ለኛ መሸጥ አይፈልግም።
በውጊያ ቆስለን ወደ ሕክምና ቦታ ስንወሰድ እንደማንኛውም ተጎጅ እኩል ሕክምና አይደረግልንም። መንገድ ላይ እናቶችና አዛውንቶች ሲያገኙን ገልምጠውን ነው የሚያልፉት።
በጥቅሉ ሕዝቡ አንቅሮ ተፍቶናል"
እጁን ለፋኖ የሰጠው የአድማ ብተና አመራር ከመረብ ሚዲያ ጋር ካደረገው ቆይታ የተወሰደ!
