ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多3 222
订阅者
+2224 小时
+2707 天
+65730 天
帖子存档
በአርማጭሆ ግንባር እየተካሄደ በሚገኘው ተጋድሎ እስካሁን ባለው ከ90 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች መደምሰሳቸው ታወቀ!
በተጨማሪም፡ አገዛዝ ስርአቱ ተጨማሪ ህዝብ የሚጨፈጭፍበት ጊዜን ለማገኘት የሚያጭበረብርበት የምርጫ ካርድና ኮሮጆም እንዲበታተንና እንዲቃጠል ተደርጓል።
በተያያዘም፡ ከጃንሱማ ወደ ጋብላ ለእገዛ በተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ላይ ልዩ ስሙ ሽመል በር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከባድ የቆረጣ ጥቃት ተፈፅሞበት ከባድ ኪሳራን መከናነቡ ታውቋል።
+9
ሰበር የድል ዜና !
የአፋብን ወሎ ቤተአማራ ሚኒሊክ ዕ ዝ 105'ኛ ኮ ር( የቀድሞው ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር) በምዕራባዊ ቤተአማራ ቀጠና በመካነሰላም ግንባር ጠላትን በዚህ መልኩ ደም*ስሶ አዝረክ*ርኮታል!!
ጀብደኛው ሚኒሊክ ዕዝ ይችላል✊
የአባቶቹ ልጅ ፋኖ በቅርቡ ዘር ጨፍጫፊውን የብልፅግና አገዛዝ አስወግዶ የህዝባችንን ህልውና አስጠብቆ የተረገጠውን ባንዲራችንን ከፍ አድርጎ በክብር ያውለበልባል።
እየመጣን ብቻ ሳይሆን እየደረስን ነው💪
የዚህ ታሪካዊ ትግል አካል ይሁኑ!!!
ፍቅርን ብየ እንጂ ተግቼ ለሰላም እኔስ መታገሴ፣
መች ከሀገር ይበልጣል እኔስ አንድ ነፍሴ።
ወይድ አንተ አትንገረኝ ማንነቷን፣
ምጥ አታስተምር ልጅ እናቷን።
ወይድ አታስቆጥረኝ ማንነቴን፣
እኔ አውቀው የለም ወይ ደም አጥንቴን።
ወይድ አንተ ላንሳበት ባንዲራየን፣
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማየን።
💚💛❤
መንጋው ተንጫጫ! ወገን መልካም ቀን🙏Ayinades Walelgnelgne
የአባት አርበኞች ጦር ተደራጅቷል !!!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ጀኔራል ኃይሌ ዘ ውባንተ ክፍለ ጦር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና በክፍለ ጦሩ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ሻንበል ማርዬ አስራት እና በክፍለ ጦሩ ህዝባዊ አስተዳደር ኃላፊ አርበኛ ዋሴ ታደሰ ጋር ውይይትና ምክክር በማድረግ የአባት አርበኞችን ጦር በማደራጀት ላይ ነው።
ስርዓቱ ከምንጊዜውም በላይ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ኢ - ሰባዊ እልቆ መሳፍርት የሌለው በደልና ግፍ እየፈጸመ በመሆኑ ራስንን በማደራጀትና መሰልጠን ተገቢ መሆኑን በመረዳት በስማዳ ወረዳ ጎሽሜዳ ቀበሌ :-
1ኛ .ግራዝማች ለውጤ ====ሻንበል
2ኛ .ግራዝማች ይሁኔ======= ሻንበል
3 ኛ.ግራዝማች አወቀ ======ሻንበል
4 ኛ.ግራዝማች መብራቱ====== ሻበል
በሚል ሲደራጂ መታሰቢያነቱ በጀኔራል ኃይሌ ዘ ውባንተ ክፍለ ጦር ስር ሲታገል በተሰዋው አርበኛ ግዛቸው ምትኩ ሬጂመንት ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ለየትኛውም ወታደራዊ ግዳጂ ዝግጁ በማድረግ በቀጠናው ህግ የማስከበር ስራ የሚሰራ ሁኖ ተደራጂቷል ።
ድል ለአማራ ፋኖ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር ቃል አቀባይ ክፍል!!
ቴዲ አፍሮን [ለሆነ] ሕዝብ (አካባቢ) ብቻ አጥበው ለመስጠት ያልተሞከሩት ነገር የለም። ቴዲን በምኒልክ በኩል"አማራ ነው" ሲሉት፤ በሐብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ በኩል ጉራጌ ይሆንባቸዋል። የተወሰነ ዘር ቆጥረው ጉራጌ ሲያደርጉት በጀግናው ጎበና ዳጨ በኩል ኦሮሞ ይሆናል። አክራሪ ክርስቲያን ነው ሲሉት በጀግናው የሶማሌ ተወላጅና ሙስሊም ኡመር ሰመተር በኩል ሶማሌ ይሆናል። አክራሪ ነው ሲሉት፦
"አንችም በሃይማኖትሽ፣ እኔም በሃይማኖቴ፣
መኖር እንችላለን፣ አይጠበኝም ቤቴ።" እያለ ይዘፍናል።
ምናልባት የቴዲ "አንዲት ኢትዮጵያ" ሕልም ላይስማማህ ይችላል። የሚከተሉትን ብዙሐኖች ግን አክብር። ለምን ተከተሉት ማለት ውርደት ነው። ቴዲ በራሱ መንገድ ስለተባበረችው ጠንካራ ኢትዮጵያ ዘመረ እንጅ የትኛውንም ኃይል አልገፋም። ቴዲን ይኼዱበታል እንጅ አይመጣባቸውም። በምናቡ የሚስላትን ሐገር በእውነተኛው የጥበብ ዓለም መዝፈን መብቱ ነው። "የድሮ ሥርዓት ናፋቂ ነው" እንዳትል፥ ጎበና፣ ምኒልክ፣ ኡመር፣ አሉላ፣ ባልቻ....የተችዎቹ የጎሳ ብሔርተኞች የትናንት ታሪካቸው እንጅ የቴዲ ብቻ አይደሉም😃
አንዳንድ "የአማራ ብሔርተኛ ነን" ባይ ደንቆሮዎችስ ስንቴ ዘመቱበት😃 ስንት ጊዜ ሰደቡት😃 በቃ ቴዲ "ቴዲ" ብቻ ነው። ትከተለዋለህ እንጅ አይከተልህም። ነገር ግን፥ ሳትወድ በግድ ታደንቀዋለህ።
በቃ ቴዲ "ኢትዮጵያዊ" እንጅ ኦሮሞ ወይም አማራ አልያም ትግሬ አይደለም።
ኧረ ነገ የሚመጣው መቼ ነው🙄#Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር
የመከራው ጽዋ እና የነፃነት ንጋት አፋብን ድርጅታችን!!
ሰማዩ በጭስ ታፍኗል። ምድሪቱ ግን ዝምታን መርጣለች። የአማራ ልጅ መሆን በገዛ አገሩ እንደ እንግዳ፣ በገዛ ቤቱ እንደ ስደተኛ የሚቆጠርበት ዘመን ከጀመረ ውሎ አደረ። በየትኛውም የኢትዮጵያ ጠርዝ የደም አሻራው ያልፈሰሰበት፣ የእግሩ ኮቴ ያልታተመበት መሬት ባይኖርም፤ ዛሬ ግን ያ መሬት ክዶታል። እንደ አማራ ተለይቶ መታደድ፣ እንደ ጽዮን ልጅ መሰደድ ዕጣ ፈንታው ሆኖ ከቀጠለ ዓመታት ነጎዱ። የውስጥ ደም መላሾችና የውጭ ሴራ ይህ ሁሉ መከራ ግን በጠላት ብቻ አልነበረም።
በቤተ መንግሥቱ ዙፋን ላይ የተቀመጡት አብይ አህመድና ግብረ አበሮቻቸው፣ የብአዴን "ታዛዥ አሽከሮች" ጭምር በሕዝቡ ስቃይ ላይ የራሳቸውን ታሪክ ሲጽፉ ከረሙ። የሚገርመው ግን ጭካኔያቸው በዚህ አላበቃም። በአማራ ስም ሚዲያ ከፍተው፣ በአማራ ካባ ተሸፍነው፣ በምድሪቱ ላይ የሚገኙትን እንቁ መሪዎችንና ቆራጥ ታጋዮችን ስም በመስጠት ለሞት አሳልፈው ለመስጠት ሌት ተቀን ይተጋሉ። እነዚህ "ተኩላዎች በበግ ለምድ" ዛሬም በሕዝብ ትከሻ ላይ ሆነው ሕዝቡን ወደ ስደትና ወደ ሞት አፋፍ እየገፉት ይገኛሉ።
ታሪክ ግን እዚህ ጋር አያበቃም። የአረመኔዎች ግፍ ገደብ እንዳለው ሁሉ፣ የጭቁኑ ሕዝብ ትዕግሥትም መጨረሻ አለው። መሪር መከራን የቀመሰው ይህ ትውልድ፣ ነፍሱን ለአንድዬ አሳልፎ ለመስጠት የማይሳሳ፣ ስለ አማራ የመኖር ነፃነት ደሙን ለማፍሰስ ቆርጦ የተነሳ ትውልድ ነው።
ከግብፅ እስከ አሌክሳንድሪያ፣ ከዲዮቅልጣኖስ እስከ ማዳጋስካር በገቡበት ገብተን፣ የአማራን የነፃነት አዋጅ የምናበስርበት ቀን እጅግ ቅርብ ነው።
በትግሉ ስም ዳቦና በርገር በአሰፋው አፋቸው "እኔ ካልመራሁት" እያሉ የሚፎክሩ፣ በትግሉ መስዋዕትነት ላይ ቁጭ ብለው የሚሳደቡ ስልጣን ጥመኞች ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል። የአማራ ትግል የጥቂት ግለሰቦች የዝና መወጣጫ ሳይሆን የሕዝብ የመኖርና ያለመኖር ትግል ነው።
ለእነዚህ ሆዳሞች የሚነገራቸው አንድ ሀቅ ብቻ ነው፦ አደብ ግዙ! የሕዝብ ቁጣ እንደ እሳተ ጎመራ ከመገንፈሉ በፊት፣ የነፃነቱ ውበትና ጭፍራው ከመምጣቱ በፊት፣ ከክፋት መንገዳችሁ ተመለሱ።
የአማራ ህዝብ ታሪክ በመከራ ቢጀምርም፣ መጨረሻው ግን በድልና በነፃነት መዝሙር እንደሚደመደም ጥርጥር የለውም። የነፃነት ፀሐይ መውጣቷ አይቀርም! #Dawit Amhara@ ከንጉሶች መንደር!!
የአገዛዙ ፓራ ኮማንዶና ሚሊሻ የነበሩት ወደ ቀድሞ ቤታቸው አማራ ህዝብ እየተመለሱ ነው!!!
ሚያዚያ 10/2018 ዓ.ም አፋፋብን 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል
በአፋብን ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ከሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች አንዷ ከሆነችው ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማ መሽጎ ከሚገኘው የአረመኔው አገዛዙ ሰራዊት ጋሻ ጃግሬ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት በደም አማራ የሆኑ በግብር የገዳዩ አብይ አህመድ ሎሌ የነበሩት #ፓራ_ኮማንዶ_ደባሱ_አለምነው እና #ሚሊሻ_ሙሉሰው_ቢያድጌ እስከ አሁን ከገዳይ ጎን ቆመን የህዝባችንን መከራ ማራዘማችን ቆጭቶናል ከእንግዲህ ግን የአማራን ህዝብ ከሚጨፈጭፍ ሰረዓት ጋራ በመሆነ የራሳችንን ህዝብ አንጨፈጭፍም የበደልነውን ህዝብም ይቅርታ በመጠየቅ በቀጣይ በፋኖ አደረጃጀት ሆነን ለመካስ ዝግጁ ነን በማለት በታላቅ አማራዊ ወኔ የደባይ ጮቄ ሻለቃን በክብር ተቀላቅለዋል!!!ደባይ ጮቄ ሻለቃ ጠላትን ስቦ በማስከዳትም ይሆን በመምታት እና የጠላትን ኃይል በማፈራረስ በኩል በርካታ ስራዎችን እየሰራች ሲሆን በዛሬው ዕለት ለተቀላቀሉ ጀግኖችም የክብር አቀባበል አድርጋለች!!!
አዲስ ትውልድ አዲስ ተስፋ አዲስ አስተሳሰብ !!!
ድል ለአማራ ፋኖ!!!!!!
24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል
+1
የአፋብን ወሎ ጠ/ግ/ሚ/እዝ 104ኛ ኮር 25ኛ ክ/ጦር እና ሸዋ ጠ/ግ/አሳ/እዝ አፄ ዘርያእቆብ ኮር1 ብሩኬ ደምሴ ክ/ጦር ከሁለቱም እዞች በስራ ስምሪት ላይ ያሉ የእዝና የኮር አመራሮች የክ/ጦር አመራሮችን ያካተተ በቀጠናዊ ጉዳይ ላይ በቀን 07/08/2018 ዓ.ም የጋራ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም ላይ የሁለቱም የእዝ ክ/ጦሮች በቅርበት ተደራራሽ ከመሆናቸው አንጻር በሚሸፍኑት ቀጠና ላይ የጋራ ጠንካራ ሀይል በመያዝ ኦፐሬሽን ከመስራት ጀምሮ በማህበረሰብ አያያዝ ፣ በማህበራዊ ፍትህ ፣ በምርኮኛ አያያዝ ፣ በሰራዊት ግንባታ እና በቀጠናው ቀጣይነት ላለው አጠቃላይ የትግል ሁኔታ በጋራ እቅድ ለመንቀሳቀስ ጭምር አጀንዳዎች ላይ ለሌሎችም እዞች ፈር ቀዳጅ የሆነውና የተጀመረውን አንድነት ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ተደርጓል።
ይህ ጅምር ተጠናክሮ የሚቀጥል እና ክ/ጦሮቹ በየግዜው የተሰሩ ስራዎችን ለኮር እና እዞቻቸው የጋራ ሪፖርት እንደሚልኩ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በመቀጠል የጋራ ውይይቱን መሰረት በማድረግ በቀን 09/08/2018 ዓ.ም በግሼራቤል ወረዳ ደል ቀበሌ በጋራ የህዝብ ውይይት እና የግንዛቤ ፈጠራ የተደረገ ሲሆን ህዝቡ ከፋኖ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆኖ ራሱን በራሱ ማስተዳደር የሚችልበትን የቀበሌ መዋቅር ማሻሻያ ማድረግ ተችሏል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ
ሚያዝያ 10/08/2018 ዓ.ም
ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር በልጓማ ከተማ ባካሄደው ተጋድሎ በርካታ የጠላት ወታደሮችን በመደምሰስና ሁለት የጠላት ተሽከርካሪዎችን በማውደም አንፀባራቂ ድል ተቀዳጀ!
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ስር ከሚገኙት ከ33ኛ ክ/ጦር እና ከ71ኛ ክ/ጦር የተወጣጡ አሃዶች በጋራ በመሆን ትናንት ሚያዚያ 08/2018 ዓ/ም በልጓማ ከተማ በወሰዱት ስልታዊ እርምጃ የጠላት ኃይልን አሽመድምደውና አፍረክርከው ታላቅ ድል አስነዝግበዋል።
በከተማዋ የ33ኛ ክ/ጦር አርበኞች የጠላት ኃይልን በስልታዊ ማጥቃት ሦስትና አራት ቦታ ቆርጠው ሲያሽመደምዱት በተመሣሣይ፡ የ71ኛ ክ/ጦር አርበኞች በከተማዋ ውጊያ ከመሳተፍ ጀምሮ ተጨማሪ ጠላት እንዳይገባም ሆነ ከውስጥ ያለው እንዳይወጣ የልጓማ ከተማ መግቢያ መውጫ አቅጣጫዎችን ክርችም አድርገው በመዝጋት ድንቅ የተናበበ ተጋድሎ በማድረግ ነው የጠላት አከርካሪን መስበር የቻሉት።
በተጋድሎው አንድ አይሱዙ እና አንድ ወታደራዊ ፓትሮል ሙሉ ወታደሮች ከነ ተሽከርካሪዎቹ ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፉ ዶግ አመድ መደረጋቸው ታውቋል።
የፋኖ የከተማ ውስጥ ለውስጥ ውጊያ መሃንዲሶች በፊታውራሪነት በመሩት በዚህ ተጋድሎ፡ የጠላት የቁም ምሽጎች ጭምር ተደረማምሰዋል፡ በርካታ ክላሾች ከነተተኳሾቻቸው እንዲሁም ወታደሮችና ካድሬዎች በፋኖ ተማርከዋል።
ልጓማ ከተማን በመቆለፍና ጠላትን በመቁረጥ በተወሰደ እርምጃ፡ በተሽከርካሪ ላይ እንዳሉ ከተመቱት በተጨማሪ ሌሎች በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል።
በዚህ ተጋድሎ ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን ስልታዊ እርምጃ መቋቋም ያልቻለው የአገዛዙ ኃይል የዘፈቀደ የሞርታር ድብደባ በመፈፀም በልጓማ ከተማ ማንፁኋኖችን መግደሉ ታውቋል።
ከተገደሉት ንፁኋኖች በተጨማሪ በርካታ ሀብት ንብረት ወድሟል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 09/2018 ዓ.ም
" የህዝብን መከራ እናጋልጥ"
የዘመኑ ጊዜ የሰጠው ኦሮሙማው ብልፅግና በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፅመው ህዝባዊ ፍዳና ታሪካዊ ጠባሳ ማስቀመጡንና ይበልጥ አማራ መሬት ላይ እንዳይኖር ምኞቱን ቀጥሎበታል።ምንም እንኳ የአማራን ህዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ያልፈፀመው ግፍ ባይኖርም የሚዲያ ላይ ሀገር አሳዳጊው ፋሽስቱ ብልፅግና የመከራ በትሩን እየቀያየረ ትውልድ የማይረሳው በደል እየፈፀመ ይገኛል።ይህ ፋሽስታዊ የህፃን ዕሳቤ ያለው አገዛዝ ህዝብንና ታሪክን እየበደለ፣ሀገራችንን ደግሞ ልትወጣው ወደ ማትችለው ገደል እየከተታት ይገኛል።የህዝብ እምባና ሀዘን ግድ የማይሰጠው ይህ ጊዜ ሰጥ ነገን ያላዬ አገዛዝ በተለያዩ የአማራ ክልል ግዛቶች ላይ ተዘርዝረው የማያልቁ ግፎችን እየፈፀመ ይገኛል።ለምሳሌ ያህል:-
1.እነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ በህትመት ስራ ኑሯቸውን የሚገፉ አማራዎች ያለ ምንም ምክንያት መስሪያ ቦታቸው በአገዛዙ ከተዘጋ ሁለት(2) ሳምንት አልፎታል።
2.በሁሉም የክልሉ ቀጠናዎች የነዳጅ ፍጆታ ለህዝብ ሳይሆን ለአገዛዙ ብቻ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል።
3.ማዳበሪያ አንድ ኩንታል ጥቁር 11300 ሀተብር፣ነጭ 10000 ብር ሲሸጥ ለፍዳ መታወቂያ ከግለሰብ 500 ብር፣ለሚሊሻ ከግለሰብ አንድ ሺ(1000)ብር በአጠቃላይ አስር አይነት ካርኒ አለ በዚህ መልኩ ህዝብ እየተሰቃዬ ነው።
እንዳንጠይቅ መልስ የለሽ ሆነና ነገሩ፣
ያለ ሀገር ኑሮ ሆነብን ቀመሩ።
ጊዜና ወንበሩ ድንገት ተገናኝተው፣
ሀገር በላ ሆኑ ሀገርን ከድተው። እንዲሉ መከራ በመከራ ግፍ በግፍ መደጋገም ሆነ።ስለሆነም መሬት ላይ የለን እውነታና የአማራን ህዝብ በደል ለአለም ማሳወቅና በታሪክ ከትቦ ለትውልድ ማስተላለፍ የዜግነት ግዴታችን ነው።
ድል ለተገፋው ለአማራ ህዝብ
ድል ለአፋብን
እናሸንፋለን
ቀኘ ነኝ
ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ስር የሚገኙት የ71ኛ ክፍለ ጦር አርበኞች ትናንት ሚያዚያ 08/2018 ዓ/ም በስድስት የተለያዩ ግንባሮች ባካሄዱት ኦፕሬሽኖች፡ የአገዛዙ ወታደሮችና ካድሬዎችን በመደምሰስ፡ የምርጫ ቁሳቁሶችም በማውደም ድል አስመዝግበዋል‼️
ኦፕሬሽኑ የአገዛዙን ወታደራዊና አስተዳደራዊ መዋቅር ክፉኛ ያናጋ ነው ተብሏል። በመጀመሪያው ግንባር በክፍለጦሩ ስር ከአንደኛና ከሁለተኛ ሬጅመንቶች የተወጣጡ አሀዶች በጋራ ባከናወኑት ተጋድሎ ባከት ላይ ከፍተኛ ድል ተመዝግቧል።
ከልጓማና ከቲርቲራ ተውጣጥቶ ወደ ባከት የተላከው የፀረ አማራው አገዛዝ ሰራዊትና ካድሬ በሞርታር ድብደባ ህዝብን ለማሸበር ቢሞክርም፡ አርበኞች በወሰዱት ፈጣን እርምጃ 18 ወታደሮችና ካድሬዎች ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል።
በሁለተኛ ግንባር በመረቆ አካባቢ ሲሆን፡ የአባናደው ቃኝ ቡድን በወሰደው መብረቃዊ ደፈጣ በ14 የአገዛዙ ወታደሮች ተደምስሰዋል።
በፓትሮል ተሽከርካሪ ተሳፍረው እየተጓዙ በነበሩ የአገዛዙ ኃይሎች ላይ ነው እርምጃው የተወሰደው። በዚህም ከወታደሮቹ በተጨማሪ ተሽከርካሪው መውደሙ ታውቋል።
በሶስተኛው ግንባር፡ በክፍለጦሩ የሸዋንግዛው ሬጅመንት አባላት ፈረስ ሜዳ ተብሎ ለሚጠራው ስፍራ ላይ በወሰዱት የተሳካ እርምጃ 11 የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል።
በተጨማሪም በአራተኛውና አምስተኛው ግንባር በክፍለጦሩ ስር ከ1ኛና ከ2ኛ ሬጅመንቶች የተወጣጡ አሃዶች በጋራ በመሆን በአከባቢው ኩታና አጋሙ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በፈፀሙት ጥቃት ሰባት ወታደሮችን ሲገድሉ፡ በተጨማሪም ልጓማ ላይ ውጊያ እያደረገ ለነበረው የወገን ጦር ጫና እንዳይበዛበት በልጓማና በቲርቲራ መካከል ያለውን መስመር በመዝጋት የአገዛዙን እንቅስቃሴ ሽባ አድርገውታል።
ስድስተኛው ግንባር ከጃማ የ71ኛ ክፍለጦር አርበኞች ከ33ኛ ክፍለ ጦር አርበኞች ጋር በጋራ በመሆን ልጓማ ከተማ ላይ የነበረውን ጦር ደምስሰው ከተማዋን ሙሉ በሙሉ የተቶጣጠሩበትን ድል አስመዝግበዋል።
በከተማዋ የሚገኘውን የብልፅግና ቢሮ በመስበር ህዝብን ለማሳሳት የተዘጋጀውን የምርጫ ካርድና መዝገብ በማቃጠል የአገዛዙን የውሸት ምርጫ ድራማ አክሽፈውታል።
በአጠቃላይ ሳጅን አባናደው ክፍለጦር በትናንቱ ተጋድሎ 26 የአገዛዙ ወታደርችን ሲገድል 24 ወታደሮችን ደግሞ ቆለዋል። እንዲሁም አንዲት ወታደራዊ ፓትሮል ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ መውደሟ ተረጋግጧል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
© ምኒልክ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ሚያዚያ 9/2018 ዓ.ም
ከአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት (አሳምነው ዕዝ) የተሰጠ መግለጫ!
"ጀግና በክብር ይወድቃል እንጂ አይንበረከክም!"
በሸዋ ምድር አናት ላይ፣ ታሪክ የማይረሳውና ትውልድ የሚዘክረው የጀግንነት ታሪክ ዳግም ተፅፏል።
የብልፅግና አገዛዝ በንፁሃን ደም የጨቀየውን እጁን ወደ አርበኞች መኖሪያ ቢዘረጋም፣ ያገኘው ግን የሞት ፅዋንና የታሪክ ውርደትን ብቻ ነው።
ገና በለጋነቱ ለሀገሩ ዳር ድንበር ደረቱን ሰጥቶ፣ በጥይት መካከል ተመትሮ ያለፈ የቁርጥ ቀን ጀግና አርበኛ ይማነ ።
ይህ ታላቅ አርበኛ በጣርማ በር ወረዳ በወፍ ዋሻ ቀበሌ ተወልዶ ሕይወቱን በሙሉ ለሕዝብ ነፃነትና ለፍትህ ገብሯል።
የብልፅግና ሠራዊት አርበኛ ይማነን በቤተሰቡ መካከል በድንገት ቢከበውም፣ ጀግናው አርበኛ ግን "ለወራሪ እጅ መስጠት የሞት ሞት ነው" በማለት የአንበሳን ግሳት አግስቶ፣ ብቻውን ሆኖ በደርዘን የሚቆጠሩትን የአገዛዙን ቅጥረኞች ወደ ሲኦል በመሸኘት፣ በመጨረሻም ከልቡ ፍሬ ከሆነችው ሴት ልጁ ፍሬ ይማነ ጋር በመሆን ለነፃነት ሲል በክብር ወድቋል።
ከጎኑ ሆና እንደ አባቷ የጥላትን አፈሙዝ ስትጋፈጥ የነበረችው ወጣት ልጁ ፍሬ ይማነም በወጣትነት ዕድሜዋ ለክብርና ለማንነት መሞት ታላቅ ሹመት መሆኑን ለትውልድ አሳይታ ከአባቷ ጋር በእኩልነት ተሰውታለች።
አርበኛ ይማነ ሀብተየስ፣ የነፃነት ተጋድሎው ዳር እንዲደርስ ሕዝቡን በማደራጀትና በክላስተር አመራርነት በላቀ ጀብዱ ሲያገለግል የቆየ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበር።
ይህ መስዋዕትነትም የትውልድ ዕዳ እንጂ የለቅሶ ማስታወሻ አይደለም!
የብልፅግና ሠራዊት በጦር ሜዳ የገጠመውን ሽንፈት በንፁሃን ላይ ለመበቀል የሚያደርገው ጥረትም ዛሬም ቀጥሏል።
በሌላኛው የጎበዝ አለቃ አርበኛ ደረጄ ጉልቴ መኖሪያ ቤት ላይ የተፈፀመው ወረራም የአገዛዙን የሞራል ውድቀትና ፈሪነት ማሳያ ነው።
ገና የ9 ዓመት ዕንጭጭ ሳለች በብልፅግና አረመኔ ሠራዊት ጥይት ተመታ ህይወቷ ያለፈው ህፃን ሰናይትም አገዛዙ በአርበኛ ደረጄ መኖሪያ ቤት ላይ በከፈተው ጥቃት ህይወቷ አልፏል። የአርበኛው ባለቤት እመቤት ልኬለህም በዚሁ ጥቃት ክፉኛ ቆስላለች።
አርበኛ ደረጄ ጉልቴ በቤቱ ላይ የተከፈተውን ድንገተኛ ከበባ በመስበርና በርካታ የአገዛዙን ወታደሮች በመደምሰስና ከበባውን በመበጠስ በጀግንነት መውጣት ቢችልም፣ የልጁን ሕይወት የቀማው ይህ ስርዓት ዋጋ የሚከፍልበት ቀን ሩቅ አይሆንም።
የብልፅግና አገዛዝ የጥፋት መንገድ መጨረሻው መቃብር መሆኑን አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት (አሳምነው ዕዝ) በጽኑ ያምናል። በንፁሃን ደም የነከረው እጁ ዛሬ በጀግኖች አርበኞች ክንድ እየተቆረጠ ይገኛል።
እኛ የአርበኞቹን አደራ፣ የሕፃናቱን ለቅሶና የአባቶችን ፅናት ስንቅ አድርገን ትግሉን ዳር እንደምናደርስ ቃል እንገባለን።
የአርበኛው ይማነ ሀብተየስና የልጁ የፍሬ ይማነ ደም፣ እንዲሁም የሕፃን ሰናይት ደረጄ ነፍስ በከንቱ አይቀሩም!
"የአማራ ህዝብ በነፃነትና በክብር ይኖራል!"
"የጀግኖች አደራ አይበተንም!"
ውድቀት ለደም መጣጩ የብልፅግና አገዛዝ!
ሚያዝያ 9/2018ዓ.ም
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ!
ከ1ቲም በላይ 12 አባላት የፓራ ኮማንዶ ጋንታ መሪ የሚሊሻ ሻንበል መሪው እና የ25ክ/ጦር አባሎች 201ኛ ኮር 74 እና 54ኛ ክ\ጦርን ተቀላቅለዋል❗️
..............ሚያዚያ 09/2018 ዓ.ም
ያለ አንድ ጥይት ተኩስ ተቋሙን እያፈረስነው ነው የጠላት ሀይል ላይ በደረሰበት ጉዳት ስነልቦናው የተሸረሸረው የስርአቱ አገልጋይ አባል የነበሩት በየተራ ወደ ፋኖ እየተቀላቀሉ ነው።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
ከተራቁጥር# 01_10ያሉት 74ኛ ክፍለጦርን የተቀላቀሉ ናቸው
1ኛ.ወንዴ ጌታ........ፓራኮማንዶ
2ኛ.ታዴ ፈንጌ ...የፓራ ኮማንዶ ጋንታ መሪ
3ኛ.እንደገና መልካሙ .....ፓራ ኮማንዶ
4ኛ.ይገረም አድኛ...........ፓራ ኮማንዶ
5ኛ.ወንድማለም ደምስ.......ፓራ ኮማንዶ
6ኛ.ምንአይቶ አብራራው ...ሁለት ክላሽ ይዞ የወጣ
7ኛ.ምኒችል ይታየው...አድማ ብተና
8ኛ.አዲስ አሸነፍ .....የሚሊሻ ሻንበል መሪ
9ኛ.ገረመው መኮነን .........ሚሊሻ
10.አዲሱ ደረጀ..........ሚሊሻ
11ኛ.ሀይለማርያም ከፋለ....25ክ/ጦር መከላከያ
12ኛ.ጌታው አንበርብር .....25ክ/ጦር መከላከያ
ስርዓቱ ምንም አቅም የሌለው መሆኑን በሰሞኑ የተሰሩ ስራወችን በአይናችን አይተናል ሴራውን ተረድተናል መተኪያ የሌለው ህይወታችን መገበር አንፈልግም በማለት በዛሬዉ እለት ቆንጆወችን የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
