ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
4 039
订阅者
+22224 小时
+3937 天
+1 35930 天
帖子存档
ይህ የአረመኔው አብይ አህመድ የመከላከያ ኮለኔል በጀግኖች የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ግንባር ግንባሩን የተባለው ጡት ቆራጩ ኃይል ስብስብ ነው ተው ብለና አማራን የነካ የለውም በርካ ነው።
+5
ይህ የአረመኔው አብይ አህመድ የመከላከያ ኮለኔል በጀግኖች የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ግንባር ግንባሩን የተባለው ጡት ቆራጩ ኃይል ስብስብ ነው ተው ብለና አማራን የነካ የለውም በርካ ነው።

ብቃት ብቻ ሳይሆን ጀግንነት ከአባቶቹ የወረሰው የሽዋው አንበሳ

ቀን ጥር 27   /2018 ዓም የክፍለ ጦር ምስረታ መግለጫ =====//=======//===== ሕዝባችን የአማራ እንደ ሕዝብ የገጠመውን ሁለተናዊ የህለውና አደጋ ለመቀልበስ በሚደረገው ፖለቲካዊ የትጥቅ ትግል ለሕዝባችን እና ለትግሉ ታምነን ለድል እንደምንበቃ እርግጠኞች ነን።     የትግላችን መሰረት የሆነውን ሕዝባችንን ክደው ብቻ ሳይሆን በእጅጉ አጎሳቅለው ፣ ማህበረሰባዊ ስሪቱንና ግብሩን ጥላሸት ቀብተው በኮበለሉ ፣ የጀግኖቻችን መስዋት ባረከሱና ከንቱ ባደረጉ ፣ አንድ እግራቸውን ፋሺስታዊ ስርዓቱ ተክለው በነበሩ ፣ የአማራ ፋኖን አንድነት በእጅጉ ሲፈትኑ እና በእጅጉ ሲበጠብጡ በነበሩ ቅርብ አዳሪ ስናዳሪዎች ሕዝባችን በእጅጉ እንዳዘነ ተገንዝበናል። ይኽ ብቻም ሳይሆን ወደፊት የአባቶቻችን የእነ ገብርዬ ታሪክ እንዴት መመለስ እና መጠበቅ እንዳለብንና አበክሮ መስራትም እንደሚጠበቅብን  ሕዝባችንም  አደራ  ሰጥቶናል። እኛም በኩራት ተቀብለናል። የትግላችን መዳረሻ ግብ ሕዝባችን የገጠመውን ሁለተናዊ የህልውና አደጋ በመቀልበሰ ፣ ፍትሕ ፣ እንኩልነት ፣ነፃነት እና ሰብዓዋነትን የተላበሰ እና የአባቶቻችን የስነ-መንግስት ጥበብ  አሁን ዓለም ከደረሰበት አስተዳደራዊ ፍልስፍና ጋር በማቀናጀት የተረጋጋ ስር-ዓተ መንግስት ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በመሆን መትከል እንደሆነ ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በመግለጫው ከዚህ በፊት መግለፁ ይታወቃል። በመሆኑም የክፍለጦራችን መነሻ  የሆነውን የራስ ጋይንትና አካባቢው ማህበረሰብን በሚመጥን ለትግሉ ፍፁም ታምነን ፤ ለድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቃናቄ (አፋብን) ታዛዥ ሆነን  ራሳችን በራሳችን አደራጅተን "ራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለጦርን" የመሰረትን ሲሆን ወደ ፊት ድርጅቱ በሚያወርደውን ማንኛው ትዕዛዝ እና መምሪያ ለመቀበል ዝግጁ መሆናችም እንገልፃለን።    ስለሆነም:- 1,  ፋኖ  ታደሰ   ሀይሌ...... ሰብሳቢ 2,ፋኖ አሸናፊ   ካሳ ........ም/ ሰብሳቢ 3,  ፋኖ ስመኘው  ፈንታው ....ወተደራዊ  አዛ 4, ፋኖ  ማስሬ እባቡ......  ም/ወ/ አዛዥ 5, ፋኖ እሰየ  ሲሳይ....... ዘመቻ መሪ 6, ፋኖ ሀብቱ   ባለህ......  ም/ ዘመቻ 8, ፋኖ ወንድምነው ካሳ ......  ወታደራዊ አስተዳደር 7, ፋኖ  እያያ    አየነው.... ልዩ  ዘመቻ 8, ፋኖ  አድስ   ጌታሁን.... ስልጠና  መምሪያ 9,ፋኖ ጌታለም  ጎበዜ....   ፋይናንስ ኋላፊ 10, ፋኖ  ሳሙኤል   ጌታሁን ....ፖለቲካ ዘርፍ ኋላፊ 11,ፋኖ  አባይ አስቻለው   ......  ህዝብ አስተዳደር 12,ፋኖ  ሻምበል   ተስፋ...... ህዝብ ግንኙነት 13, ፋኖ *** .............. መረጃና ደህንነት 14, ፋኖ ጌታው.................. አድስ ሎጀስቲክ 15,ፋኖ ፍቃዴ   ሙላቴ......... ግዥ ክፍል * የአማራ ፋኖ ብሄራዊ  ንቅናቄ *ድል  ለአማራ ህዝብ *ድል ለአማራ ፋኖ * ራስ  ጋይንት  ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር

አፋብን| ቴዎድሮስ ዕዝ    ጥር 27/2018ዓ.ም የወርቅ-ሜዳ ከተማ የሰላም አየር አግኝታለች !!! በጃዊ ወረዳ ወርቅ ሜዳ ከተማ አንድ አመት ከ5 ወር ያክል በአረመኔዉ የመንግስት ስርዓት ሰራዊት የከተማዋን ማህበረሰብ ሲያሳቅቅ፣ ሲዘርፍ፣ ሴቶችን ሲደፍር፣ ዘረፈ ብዙ ሰቆቃዎችን ሲያደርስበት ቆይቷል። ይሁን እንጅ በቀጠናዉ የሚንቀሳቀሰው የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር የፋኖ ሰራዊት በአረመኔው የአብይ ገረድ ሰራዊት ላይ በሚያደርገዉ ተደጋጋሚ ጦርነት የጠላትን ሃይል በመምታት፣ ስቦ በማስከዳት፣ የከተማዋን ሙሉ ህዝብ ከፋኖ ጎን እንዲቆም በማድረግ ከፍተኛ የበላይነት ስለተወሰደበት እና ኪሳራ ስላጋጠመዉ በቀን 23/05/2018 ዓ.ም ከተማዋን ለቆ ወጥቷል። ይህ ብቻ ሳይሆን በመተከል ዞን የሚንቀሳቀሱ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ነፃነት ታጋዮች በአረመኔው የአብይ ስርዓት ላይ በከፈቱት ከባድ ጦርነት የተደናገጠው ብልፅግና ሰራዊቱን ወደ ቀጠናዉ ለማንቀሳቀስ የሞከረ ቢሆንም ጀግናዉና አይበገሬዉ የጉሙዝ ታጣቂ ግን በገባበት ቀጠና ሁሉ እየለበለበዉ ይገኛል። ከአንድ አመት በላይ የተሰቃየዉ የወርቅ ሜዳ ህዝብ በቀን 26/05/2018 ዓ.ም ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር አመራሮች እና ከፓዊ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ጥልቅ ዉይይት በማድረግ ለማንኛዉም ልማት እና እድገት መሰረቱ ሰላም ስለሆነ ሰላምን ለማምጣት እና ይህንን አረመኔ የአብይ ስርዓት ለማስወገድ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ቆርጠን እንሰራለን ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። እንዲሁም የቀበሌ ጊዜያዊ መንግስት አደረጃጀቶት መዋቅሮችንም መዘርጋት ተችሏል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!         ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ! አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ            ጥር 27/2018 ዓ.ም

አገዛዙ ባህር ዳር ከተማን አኬልዳማ ማድረጉን ቀጥሏል ! --------------- በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እየፈፀመ ያለው አገዛዝ ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን የሕክምና ዶክተሮችን፣ የነቁ አማራዎችንና ባለሐብቶችን በየቀኑ ከቤታቸው  እየተጎተተ እያወጣ ማረዱን ቀጥሏል:: በመሆኑም ትላንት በቀን 26/05/2018ዓ.ም ዶ/ር ፀጋሁን ስሜ የሚባልን በምሥራቅ ጎጃም፣ የደብረወርቅ ተወላጅና የባህር ዳር ከተማ  ቀበሌ 14 ነዋሪ እንዲሁም የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሠራተኛ የነበረውን ጥዋት ሥራ ለመግባት በጉዞ ላይ እያለ  በአገዛዙ ወታደሮች ይያዛል። የአገዛዙ ወታደሮች ከያዙት በሗላ ወደ ቤቱ መልሰው በመውሰድ በቤቱ ፍተሻ ያደርጋሉ። ቤቱን በመፈተሽ ምንም ነገር ያላገኙት ወታደሮች ዶ/ር ፀጋሁንን ወደ ቤዛዊት ቤተመንግሥት አካባቢ ወስደው ገድለው ጥለውታል። የአገዛዙ ወታደሮች ዶ/ር ፀጋሁንን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉ በሗላ በማንአለብኝነት በራሱ ስልክ ለባለቤቱ በመደወል አስከሬኑን እንድትወስድ ይነግሯታል:: ዶ/ር ፀጋሁንን ምን እንዳነጋገረው ባይታወቅም ከሳምንት በፊት የአማራ ክልል ጤና ቢሮው ኃላፊ የሆነው  አብዱልከሪም መንግሥቱ ለብቻው ቢሮ እንዳነጋገረውና ከቢሮ ሲወጣም ጥሩ ስሜት እንዳልነበረው ጓደኞቹ ይናገራሉ:: ቤቱ ሲፈተሽም ምንም አይነት መረጃ እንዳልተገኘና የአገዛዙ ወታደሮችም የወሰዱት ማስረጃ እንደሌለ የዶ/ር ፀጋሁን ቤተሰቦች አረጋግጠዋል። በመጨረሻም የፖለቲካ አመራሮች አረጋ ከበደ፣ አብዱ ሁሴን፣ ይርጋ ሲሳይ፣ አብዱልከሪም መንግሥቱና ጎሹ እንዳላማው እንዲሁም የጸጥታ አመራሮች መሃመድ ተሰማ፣ እሸቱ የሱፍና ዘላለም መንግሥቴ ብሎም ሌሎች ግብር አበሮቻቸው በዚህ የንፁሃን ግድያ ዋጋ እንደምትከፍሉ ልታውቁት ይገባል። ለዶ/ር ፀጋሁን ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እንመኛለን

አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ምዕራብ ወሎ ቲርቲራና ሻፊ ላይ ታላቅ ጀብድ በመበፀም ድል አስመዘገቡ:: ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ምዕራብ ወሎ ቲርቲራና ሻፊ ከተማ ላይ ጥር 26/2018 ዓ.ም ከፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ጋር ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ ከሃያ በላይ በመደምሰስና ከሃያ ያላነሰ በማቁሰል ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል:: ተከጋድሎው ከቲርቲራና ሻፊ ከተማ ባሻገር ልዩ ስሙ ቡሶ የተባለ አካባቢ ላይ ከብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ውጭ በርካታ አድማ ብተናና ሚሊሻ በአባ ናደው ልጆች አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለባንዳ የሚገባውን ሰጥተዋል:: ባጠቃላይ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ውግዲ ዙሪያ እና ቲርቲራና ሻፊ ከተሞች ጠላትን ከባድ ምት በመምታትና በርካታ ቁስለኛ ወደ ወግዲ ሆስፒታልና ደሴ ሆስፒታል እንዲያግዝ በማድረግ ብሎም የዘመቻ እቅዱንም ባጭር በማስቀረትና በማክሸፍ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ ጥር 27/2018 ዓ.ም

ንጉስ ሚካኤል ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ወግዲ ወረዳ ዙሪያ ከባድ ተጋድሎ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ:: እንደሚታወቀው ፀረ አማራው ብልፅግና በሰሜን ወሎ እና ደቡብ ወሎ በደረሰበት ሽንፈት ወደ ደቡብ ወሎ ቀጠና እና አጎራባች ሸዋ ለመስፈር አሰቦ መካናይዝዱን ሳይቀር ሙሉ ጦሩን እያሽሽ እና እያንቀሳቀሰ ይገኛል። ከዚህ ጋር ተያይዞም በዛሬው ዕለት ሙሉ ሀይሉን ሰብሰቦ በወግዲ ወረዳ አድርጎ ወደ ሸዋ ለመውጣት የሞት ሽረት ከባድ ትንቅንቅ ለማድረግ ቢሞክርም መብረቆቹ የሚቀያይረውን ሀይል ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ በመምታት ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል:: ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ጠላት ሰብሮ ሊወጣ የነበረበትን ስትራቴጅካዊ ቦታ በወግዲ ወረዳ ጎርንጅ ቀጠና ከሌሊት 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በደፈጣና እና በፊት ለፊት ውጊያ ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል። በነበረውም ተጋድሎ ጠላትን ምድር ገበያ ላይ የገባው ሀይል በደፈጣ ሙሉ በሙሉ ሲደመሰስ መልሶ ቢደራጀም በድጋሜ ኢላላ እና አጋምሳ ከተባለ ቦታ ላይ በተሰነዘረ የፊት ለፊት ማጥቃት የብልፅግናው ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ካሰበበት ቦታ ሳይደረስ ወደ ኋላ በከባድ ኪሳራ ለመመለስ ተችሏል ። በተደረገውም ተጋድሎ ቁጥሩ በውል የማይታወቅ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጠላት ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ወደመጣበት ተመልሷል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ ጥር 27/2018 ዓ.ም

ገና ምኑ ተያዘና ሀቢብ 🥺 ለእኛ ለአማራውያን የተከፈለ ልጅነት : ወጣትነት : የመጨረሻ የሂወት እስትፋስ: የመጨረሻዋ የደም ጠብታ 😥 ሞት ሁሌ አዲስ ነው አይለመድም ። ድሮስ ታማኝ ሰው ጥሩ ሰው
+1
ገና ምኑ ተያዘና ሀቢብ 🥺 ለእኛ ለአማራውያን የተከፈለ ልጅነት : ወጣትነት : የመጨረሻ የሂወት እስትፋስ: የመጨረሻዋ የደም ጠብታ 😥 ሞት ሁሌ አዲስ ነው አይለመድም ። ድሮስ ታማኝ ሰው ጥሩ ሰው መቸ እድሜ አለውና ነብስ ይማር ሀቢብ

“ካፈነገጠ ፋኖ ጋር ተደራደርን እያላችሁ ነው ፤ እውነተኛ ድርድር ካለ ለምን በአግባቡ ከተደራጁት እና ብዙ ታጣቂ ካለው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጋር አትደራደሩም?” የተከበሩ አበባው ደሳለው (ዶ
“ካፈነገጠ ፋኖ ጋር ተደራደርን እያላችሁ ነው ፤ እውነተኛ ድርድር ካለ ለምን በአግባቡ ከተደራጁት እና ብዙ ታጣቂ ካለው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጋር አትደራደሩም?”  የተከበሩ  አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ትናንት በፓርላማ የተናገሩት

ለአማራ የሕልውና ትግል ደጋፊወች በሙሉ:- በነገው ዕለት ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስረታን አስመልክቶ በአን
ለአማራ የሕልውና ትግል ደጋፊወች በሙሉ:- በነገው ዕለት ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስረታን አስመልክቶ በአንድነት አመቻች የቴክኒካል ኮሚቴ አባላት እና በታዛቢወች አማካኝነት በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ ማብራሪያ ይቀርባል። ስርጭቱ በሁሉም የአማራ የህልውና ትግል ደጋፊ ሚዲያወች በኩል በቀጥታ ይተላለፋል። ፕሮግራሙን ለሚያስተላልፉ ሚዲያወች የዙም መግቢያ ሊንክ በውስጥ መልዕክት እናደርሳለን። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ

ሰበር ዜና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቅ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝና ምስራቅ አማራ ቀጠና በሚኒልክ ዕዝ በሁለቱ ጥምር ጦር በደራ እና በወግዲ ግንባሮች የአብይን ሰራዊት ድባቅ ተመታ!! ​ደራ ወረዳ እና በደቡብ ወሎ ወግዲ አካባቢዎች የአረመኔው አብይ አህመድ ኃይሎች በአሳምነው ልጆች በሁለት አቅጣጫዎች የከፈቱት መጠነ ሰፊ ጥቃት የጠላት ኃይል ተመታ። ሁኖም በትላንትናው ዕለት በብልፅግና ወንበር አስጠባቂ መከላከያ በኩል የተቀናጀ የማጥቃት ዕቅድ ተይዞ ነበር። ጥቃቱም በሁለት ዋና ዋና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነበር በሌላ ግንባር ከወግዲ ተነስቶ ወደ ጎረንጅ እና ደራ መስመር ለመግባት የሞከረው የጠላት ኃይል፣ በከፍተኛ መከናይዝድ የታጀበ ከ10 ሻለቃ በላይ የሚሆን የ105ኛው ክፍለ ጦር እና ተጨማሪ የእግረኛ ክፍለ ጦር በመሰለፉ በጄነራል ዘውዱ ሰጣርጌ እና በጄነራል ሞሲሳ የሚመራው ይሄው ኃይል በሚኔልክ መብረቅ ክፍለ ጦር አከርካሪው የተሰበረ ሲሆን በደራ/ቱቲ ግንባር በኩል ደግሞ የጠላት ኃይል ከደራ ተነስቶ በሰኞ ገበያ በኩል ወደ ቱቲ የፋኖ ካምፕ አቅጣጫ ጥቃት ለመሰንዘር ተንቀሳቅሶ ንጋት 11 ሰዓት ላይ የጀመረው ይህ ውጊያ ለረጅም ሰዓታት የቆየ ሲሆን፣ በናደው ክፍለ ጦርና በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር በሁለቱ አሃዶች በቅንጅት በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ መልሶ ሰረር ኩላ ከተማን መቆጣጠሩ ተችሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሁለቱ አሃዶች በተሰራ አውደ ውጊያ የከተማዋ መያዝም በአረመኔው አብይ አህመድ ኃይሎች ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠረ ሲሆን፣ በዘህም አውደ ውጊያ የጠላት ምሽግ ሲሰበርም በርካታ አገዛዙ ሲጠቀምበት የነበረውን ደረቅ እሬሽንና በረካታ ጥርንፍ ቦርሳዎችን የተገኘ ሲሆን ከፍተኛ የሰው ኃይል ጉዳት (ሙት እና ቁስለኛ) በማድረስ በመጨረሻ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጥምር ጦሩ በወሰደቱ እርምጃ ሰረር ኩላ ከተማ በፋኖ ቁጥጥር ሁናለች ። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው። ጥረ 26/05/2018 ዓ.ም

ይህ ህዝብ ነፃነቱን በክንዱ ለማረጋገጥ ከተሰለፈው የአብራኩ ክፋይ ፋኖ ጋር በአማራ ብሔርተኝነትና በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ከልጆቹ ጋር እየመከረ ይገኛል። ይህ ህዝብ ብርቱ ነው በጀርባው ቀለብ ተሸክሞ በክንዱ አፈሙዝ ጨብጦ ነፃነቱን ለማረጋገጥ ታላቅ መሰዋእትነት ከፍሏል። ተንሰፍስፎ ያሳደጋቸውን ወርቅ የሆኑ ልጆቹን ለትግሉ ያበረከተው ህዝብ ዛሬ ገዳዩን ከመለመን ወጦ ስርዓቱን በሚገረስስበት አቅም ሁሉ ይወያያል ይመክራል። ትናት ጅራፍ እያኖጋ መብቱን የጠየቀው አርሶ አደር ነፍጡን አንስቶ ገዳዩን እና የአረመኔውን ስርዓት መፋለሙን ቀጥሏል። ተለይቶ የሚገደለው ህዝብ ከገዳዩ አንዳች የነፃነት ጮራ አይፈነንቅም እና አጀንዳው ደጁ ድረስ የወረረውን ጠላት አፈር መልበስ ይሆናል። የትግሉን የወደፊት እጣፋንታ ለማረጋገጥ ትልቅ የአማራ ህዝብ ድርጅት ኮትኩቶ ካሳደገልን ህዝብ ጋር 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር የህዝብ ንቅናቄ መድረኮችን በማዘጋጀት በጠላት ላይ የኃይልና የፖለቲካ የበላይነቱን በመውሰድ በነፃ ቀጠናዎች ህዝብን እያደራጀ ወደፊት ይገሰግሳል። አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ከሱዳኑ የፈጥኖ ደራሽ ታሪክ የምንማረው የትኛውም የነፃ አውጭ ድርጅት በሂደት ድሮንን እንደ ክላሽ የሚታጠቅ መሆኑን ነው። ይህ ደግሞ በሁለት መልኩ እውን ሊሆን ይችላል፣ በአንድ በኩል ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ድሮን የሚያስታጥቁ አገሮች ይኖራሉ- ልክ ኤምሬትስ ብልፅግናን እና የሱዳኑን ፈጥኖ ደራሽ እንደምታስታጥቀው ማለት ነው። በሌላ በኩል ድሮን አምራች አገሮች እየተበራከቱ ሲመጡ  የድሮንን ዋጋ በመቀነስ፣ የተለያዩ ቡድኖች በርካሽ ዋጋ እንዲይዟቸው ያመቻቻሉ። የዘመኑ ጦርነት በቀደመው መንገድ የሚሄድ አይደለም፤ ታንክና መድፍ እያንጋጉ፣ የሚፎከርበትም አይደለም። 100 የጦር አውሮፕላን አለኝ እያሉ የሚተረተሩበትም አይደለም። (በነገራችን ላይ የአንድን አገር ወታደራዊ ሚስጢር በአደባባይ መናገር በሌሎች አገሮች በአገር ክዳት የሚያስቀጣ ነው። የትኛውም ትክክለኛና የሚያመዛዝን አዕምሮ ያለው ሰው፣ አገሩ ስለታጠቀቻቸው የጦር መሳሪያዎች አይነትና ብዛት አይናገርም- ወታደራዊ ሚስጢር ነው።) ስመለስ:- የአብይ የፉከራው ምንጭ ሰራዊቱ ወይም ደጀኑ ህዝብ ሳይሆን ድሮን ነው። እንዳልኩት ድሮን በታጠቁ ኀይሎች እጅ ሲገባ፣ ከዚያ በኃላ የሚፎከርበት ነገር ይጠፋል። ከዚያ ይልቅ የተሻለው የሚያመዛዝኑና ነገን የሚያዩ ሰዎችን ምክር ሰምቶ እውነተኛ መፍትሄ መፈለግ ነበር። አብይ ልቡም አዕምሮውም ተደፍኗል። እርሱ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ኢትዮጵያ እረፍት የምታገኝ አይመስለኝም። አንዳንድ መሪዎች የጦርነት ማግኔት ናቸው፣ ጦርነትን ሳይወዱም ሆነ ወደው ይስባሉ።