ch
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
3 613
订阅者
+1324 小时
+4187 天
+1 05630 天
帖子存档
ዜሮ_ዜሮዉን_ይዘዉት_እየመጡ_ነዉ‼️ አዲስ ቅዳም ከተማ ከተከማቸዉ የብልፅግና ታጣቂዎች ዉስጥ አብዛኞቹ ህልዉናዉ ያበቃለትን የብልፅግና ስርዓት በመተዉ ወደ ፋኖ እየተቀላቀሉ ነዉ። ዛሬም ወጣት ገድፈዉ
+2
ዜሮ_ዜሮዉን_ይዘዉት_እየመጡ_ነዉ‼️ አዲስ ቅዳም ከተማ ከተከማቸዉ የብልፅግና ታጣቂዎች ዉስጥ አብዛኞቹ ህልዉናዉ ያበቃለትን የብልፅግና ስርዓት በመተዉ ወደ  ፋኖ እየተቀላቀሉ ነዉ።  ዛሬም ወጣት ገድፈዉ አበረ የተባለ የስርዓቱ ታጣቂ ይካቲት 29/ 2018 ዓ/ም  ከአዲስ ቅዳም ከተማ  በመዉጣት የትም ቦታ ያልተተኮሰባትን ክላሽ ከበቂ የክላሽ ተተኳሿ ጋር ይዞ የአፋብን ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ሻለቃን  በሰላም ተቀላቅሏል ዜናው የ44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ነው። አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ🙏 መጋቢት 01/2018 ዓ/ም

በሸበል በረንታ አራጢ ቁጥቋጥ በእነማይ ለምጨን አካባቢ በርካታ የመድፍ ቅንቡላ ሲወርውር ውሏል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ➺➺ የካቲት 30 /2018 ዓ.ም የአፋብን አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያቆብ ፩ኛ
+3
በሸበል በረንታ አራጢ ቁጥቋጥ በእነማይ ለምጨን አካባቢ በርካታ የመድፍ ቅንቡላ ሲወርውር ውሏል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ➺➺ የካቲት 30 /2018 ዓ.ም የአፋብን አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያቆብ ፩ኛ ኮር ናደው ክፍለ ጦር እና የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 64ኛ ክፍለ ጦር በጋራ በፈፀሙት የመከላከል እና የመልሶ ማጥቃት ውጊያ ➤28 የአገዛዙ እግረኛ ሰራዊት ሲደመሰስ ➤13 ከባድ እና ቀላሌ ቁስለኛ ሆኗል። የአገዛዙ ሀይል በሸበል በረንታ አራጢ ቀበሌ ይዞት የሄደውን መካናይዝድ ጦር ወደ ቢቸና ከተማ ተመልሶ ገብቷል። አፋብንቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ለዲያስፓራዉ የተላለፈ ጥሪ ከአፋብን የዉጭ መምሪያ አርበኛ ብሩክ ስለሽ!
+1
ለዲያስፓራዉ የተላለፈ ጥሪ ከአፋብን የዉጭ መምሪያ አርበኛ ብሩክ ስለሽ!

የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ .ም በአፋብን ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ባዩ አለባቸው የተመራው ውጊያ በሸበል በረንታ! ዛሬ የካቲት 30 ከሌሊት 10:09 በሸበል አራጤ እና ቁጥቋጥ አቅጣጫ መድፍ፣ ዙ
+2
የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ .ም በአፋብን ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ባዩ አለባቸው የተመራው ውጊያ በሸበል በረንታ! ዛሬ የካቲት 30 ከሌሊት 10:09 በሸበል አራጤ እና ቁጥቋጥ አቅጣጫ መድፍ፣ ዙ-23 እና ሞርተሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሰራዊት ይዞ በወገን ላይ ውጊያ የከፈተው ጠላት ሙሉ ቀን ሙት እና ቁስለኛውን ሲሰበስብ ውሏል። በጠላት ስድስተኛ እዝ ምክትል አዛዥ ጀነራል ለጋሮ የተመራው እና ሰፊ ዝግጅት የተደረገበት የጠላት ማጥቃት በእነማይ ለምጨን አካባቢ በርካታ የመድፍ አረሮችን በመወርወር፣ በሸበል አራጤ እና ቁጥቋጥም ብዙ የመድፍ እና የሞርተር ቅንቡላወችን በማስወንጨፍ የወገንን ይዞታ ለማስለቀቅ ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም። የአፋብን አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያቆብ ፩ኛ ኮር ናደው ክፍለ ጦር ቀኝ አዝማች ይታገሱ ሻለቃ እና በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 64ኛ ክፍለ ጦር በጋራ የፈፀሙትን የመከላከል እና የመልሶ ማጥቃት ውጊያ የአፋብን ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ባዩ አለባቸው በግንባር የመራው ሲሆን በጠላት በኩል 28 እግረኛ ሰራዊት ሲደመሰስ 13 ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሆኗል። ከሌሊቱ 10:09 እስከ ምሽቱ 12:30 ድረስ በወሰደው አውደ ውጊያ ጠላት በሞርተር፣ በመድፍ እና በዙ -23 ባደረገው ደመ-ነፍሳዊ ከፍተኛ ድብደባ የአርሶ አደር መኖሪያ ቤቶች እና የቤት እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረሱ በስተቀር በወገን ኃይል ላይ አንዳችም ጉዳት አላደረሰም። በመጨረሻም ጠላት በሰው ኃይል እና በሜካናይዝድ ርብርብ ጨለማን ተገን በማድረግ አስከሬኑን ለቅሞ ወደ ብቸና ከተማ ገብቷል።

‎ከአማኑኤል ከተማ እና ከደምበጫ ከተማ በመውጣት ወደ እምቡሊ ከተማ የተንቀሳቀሰው የአብይ ስልጣን ጠባቂ ሰራዊት #በፋኖዎቻችን #ተመ*ቷ*ል። ‎ ‎በአፋብን የደረሰበትን ሽንፈት መቋቋም ያልቻለው የብል
+1
‎ከአማኑኤል  ከተማ እና ከደምበጫ ከተማ በመውጣት ወደ እምቡሊ ከተማ የተንቀሳቀሰው የአብይ ስልጣን ጠባቂ ሰራዊት  #በፋኖዎቻችን  #ተመ*ቷ*ል። ‎ ‎በአፋብን የደረሰበትን ሽንፈት መቋቋም ያልቻለው የብል(ፅ)ግና  ስርዓት የንፁሐንን ባጃጅ አቃጥሎ ንፁሐን  እናቶችን ገ*ድ*ሎ #ተመል*ሷል። ‎ ‎ድል  ለአፋብን! ‎ ፍትህ ለአማራ ህዝብ! ‎አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ፤

የነፃነት ቃል-ኪዳን፡ የሸዋ ተራሮች ምስክርነት ​የካቲት ፳፱ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም. ፀሐይ በሸዋ ተራሮች ላይ ስትወጣ እንደ ወትሮው አልነበረም የብርሃን ጨረሯ ተስፋን ሰንቃ ነፋሱም የድል አዝማች እያዜመ የመጣበት ላለፉት ሁለት ዓመታት በውስጥና በውጭ ታሪካዊ ጠላቶች አማራ መስለው በሚንቀሳቀሱ የጥፋት ሎሌዎችና በሴራ ሚዲያዎቻቸው አማካኝነት ወንድም ከወንድሙ እንዲጋጭ ሲያደረጉ የቆዩ የክፋት ደመና ዛሬ በሽዋ ተራሮች ላይ ድባቅ የተመታበት ታሪካዊ ውህደት የተፈጠረበት ቀን። ​በሸዋ ምድር ላይ የአንድነት ቃል-ኪዳን የታተመበት፣ የከፋፋዮች እጅ የተቆረጠበት ታሪካዊ ዕለት ሆኖ የተመዘገበት። የኦሮሞማ ቡድን ጥምረት የጥፋት ድግሱን ሲደግስ፣ በሌላ በኩል ደግሞ አማራን እወክላለሁ የሚለው ብአዴን የጠላትን መንገድ እየጠረገ የህዝቡን ህልውና አደጋ ላይ ጥሎ አማራን ከምድር ገፅ ለማጥፋት ከብልፅግናው አብይ አህመድ ጋር ያላቻ ጋብቻ አግብቶ ፍሬ ሊያፈራ ሲቃረብ፣ በሸዋ ተራሮች አናት ላይ ግን ሌላ ታሪክ የተፃፈበት። ​የአማራን ህዝብ የመኖር ነፃነት ለማብሰር አፋብን የነፃነት ወፎች ክንፋቸውን አውለብልበው መገናኘት እንዲጀምሩ። ከምስራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከደቡብ እስከ ሰሜን ያሉ ወንድማማቾች እጅ ለእጅ ለመያያዝ ተፈላልገው የተገኙበት የአማራ ልጆች ውህደት ምዕራፍ የሆነበት ነገሩ እንዲህ ነው የሦስቱ አርበኞች ጉዞ ​ብርዱና ሙቀቱ ሳይበግራቸው የሚኒልክን አጥንት በልባቸው አኑረው፣ የአስራት ወልየንና የአስማረ ዳኘን ማህተም በግንባራቸው ላይ አትመው የተነሱ ሦስት የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች እነዚህ የሸዋና የወሎ የቁርጥ ቀን ልጆች ለሁለት አመታት በሽዋ ሁለቱ ዕዞች የቆየውን ልዩነት በጥበብ ለመፍታት ቆርጠው የተነሱበት ታሪካዊ ቀን ​አርበኛ ድርሳን ብርሃኔ (የአፋብን ልዩ ዘመቻ አዛዥ): የወሎን ማርሽ ቀያሪ በልበ ሙሉነቱና በስትራቴጂካዊ እውቀቱ የታወቀው የጦር መሪ፥ ​አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ የአሳምነ ደቡብ አማራ ቀጠናና የአሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ አንድነትን ችቦ ለኳሽ የምድር ድሮኑ የአማራን ህዝብ የመኖር ነፃነት በልቡ ያተመ ጀግና፥ ​አርበኛ አማን እሸቱ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዘመቻ አዛዥ የሸዋን ተራሮችና ሸለቆዎች አሳምሮ የሚያውቅ፣ ለታላቁ ውህደት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የሰሩ የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸው። ​እነዚህ ሦስት ጀግኖች ለአመታትለቀናትና ለወራት ሲሰሩ የቆዩት ሥራ ፍሬ ያፈራበት ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ፣ በሃሳብ የበላይነትና በንግግር የፈቱበት የጥላቻ ሚዲያዎች የገነቡትን ግንብ በወንድማማችነት ፍቅር የአፈረሱበት ​የካቲት ፳፱ ቀን ላይ ሲደርሱ ሁለቱ ታላላቅ ዕዞች አሳምነው ዕዝ እና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ) አንድ እንዲሆኑ ያደርጉበት ታሪካዊ ቀን። በዚያ ቅጽበት የሸዋ ተራሮች አፍ አውጥተው የዘመሩበት። ወፎቹም በዛፎች ላይ ሆነው የአንድነትን ዜማ ያሰሙበት። የጥፋት ኃይሎች አማራ አይስማማም" ሲሉ የነበረው ትረካ መክኖ የቀረበበት። ​ዛሬም በታሪክ መዝገብ ላይ በደማቅ ቀለም የተፃፈበት የሸዋ ልጅ ጀግኖችና የአማራ ህዝብ በጠላቶቻቸው ደባ ሳይበገሩ በአንድነት እንዲቆም የተደረገበት። ያ በወንድሞቻችን ላይ የታቀደው የሴራ የክህደት እጅ የተቆረጠበት፣ የነፃነትና የአንድነት ቃል-ኪዳን የታደሰበት ታላቅ ቀን ሆኖ ለዘላለም ይኖራል። ወድ ጀግኖቻችን ለእናንተ ታላቅ ክብር ይሰማኛል። ​ለአማራ ህዝብና ለጀግኖቻችን ዘላለማዊ ክብር ይሁን! Dawit Amhara

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያቆብ ፩ ኮር ናደው  ክፍለ ጦር እና በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር በምዕራብ አማራ የቴዎድሮስ አናብስቶ ይዞታ በሆነችው ሸበል በረንታ አራጤ ከተማ ላይ ታሪካዊ የተጋድሎ ድል እያስመዘገቡ ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአብይ አህመድ አረመኔያዊ ጡት ቆራጩ ኃይል ከእነማይ ተነስቶ፣ በከባድ መካናይዝድ፣ በዙ-23 እና በሞርተር ታጅቦ፣ መንገድ ጠራጊ ሚሊሻና ፖሊሶችን በማሰለፍ በለሊቱ 10:30 ላይ ወደ አራጤ የፋኖ ቀጠና ሰርጎ ለመግባት ሞክሮ የነበር ቢሆንም ። የአሳምነው አናብስቶች የአንበሳ ጉሮሮ" ውስጥ የገቡት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ያልጠበቁት የደፈጣና የቆረጣ ውጊያ በማድርግ አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል። ​በዚህም  አውደ ውጊያ በለሊቱ ከአንድ ሻንበል በላይ የሚሆን የጠላት ኃይል መደምሰስ ተችሏል። በመጨረሻም ጠላት ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ በድሮን ቅኝትና በከባድ መሣሪያ ድጋፍ ኃይል ቢፉጨረጨርም ክንደ ነበልባል ተዋጊዎችን ፍርሃት ውስጥ ሊከታቸው አልቻለም። ​ይህ ውጊያ የጠላትን ኃይል ከመደምሰስ ባለፈ፣ በአሳምነው ዕዝ እና በቴዎድሮስ ዕዝ መካከል ያለውን የማይበገር የአንድነት ትስስር ለወዳጅም ለጠላትም ያሳየ ሆኗል። ፋኖ በማንኛውም የአማራ ግዛት ተንቀሳቅሶ የመዋጋትና ህዝቡን የማንቃት ብቃት እንዳለው በተግባር ተረጋግጧል። ይህ የለሊት ተጋድሎ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የአረመኔውን ኃይል ከምድር ገፅ ጠራርጎ በማጥፋት የነፃነታችንን የመጨረሻ ምዕራፍ የሚያበስርበት ማሳያም ነው። ሆኖም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ናደው ክፍለ ጦር እና በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር በአሁኗ ሰዓት ድረስ የፋኖ አናብስቶች በጽናት ከአብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት ጋር ግንባር ለግንባር እየተፋለሙ ይገኛሉ። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !! የካቲት 30/06/2018 ዓ.ም ሁሌም አዲስ መረጃ እንዲደርሳችሁ ቴሌግራም ፒጃችን ይወዳጁን https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር እና በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር በምዕራብ አማራ የቴዎድሮስ አናብስቶ ይዞታ በሆነችው ሸበል በረንታ አራጤ ከተማ ላይ ታሪካዊ የተጋድሎ ድል እያስመዘገቡ ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአብይ አህመድ አረመኔያዊ ጡት ቆራጩ ኃይል ከእነማይ ተነስቶ፣ በከባድ መካናይዝድ፣ በዙ-23 እና በሞርተር ታጅቦ፣ መንገድ ጠራጊ ሚሊሻና ፖሊሶችን በማሰለፍ በለሊቱ 10:30 ላይ ወደ አራጤ የፋኖ ቀጠና ሰርጎ ለመግባት ሞክሮ የነበር ቢሆንም ። የአሳምነው አናብስቶች የአንበሳ ጉሮሮ" ውስጥ የገቡት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ያልጠበቁት የደፈጣና የቆረጣ ውጊያ በማድርግ አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል። ​በዚህም አውደ ውጊያ በለሊቱ ከአንድ ሻንበል በላይ የሚሆን የጠላት ኃይል መደምሰስ ተችሏል። በመጨረሻም ጠላት ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ በድሮን ቅኝትና በከባድ መሣሪያ ድጋፍ ኃይል ቢፉጨረጨርም ክንደ ነበልባል ተዋጊዎችን ፍርሃት ውስጥ ሊከታቸው አልቻለም። ​ይህ ውጊያ የጠላትን ኃይል ከመደምሰስ ባለፈ፣ በአሳምነው ዕዝ እና በቴዎድሮስ ዕዝ መካከል ያለውን የማይበገር የአንድነት ትስስር ለወዳጅም ለጠላትም ያሳየ ሆኗል። ፋኖ በማንኛውም የአማራ ግዛት ተንቀሳቅሶ የመዋጋትና ህዝቡን የማንቃት ብቃት እንዳለው በተግባር ተረጋግጧል። ይህ የለሊት ተጋድሎ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የአረመኔውን ኃይል ከምድር ገፅ ጠራርጎ በማጥፋት የነፃነታችንን የመጨረሻ ምዕራፍ የሚያበስርበት ማሳያም ነው። ሆኖም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ናደው ክፍለ ጦር እና በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር በአሁኗ ሰዓት ድረስ የፋኖ አናብስቶች በጽናት ከአብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት ጋር ግንባር ለግንባር እየተፋለሙ ይገኛሉ። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !! የካቲት 30/06/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኛ ኮር ዓፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር በኤፍራታ ግድም ወረዳ ካራ ቆሪ ከተማ አካባቢ ባካሄደው ውጊያ የአ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኛ ኮር ዓፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር በኤፍራታ ግድም ወረዳ ካራ ቆሪ ከተማ አካባቢ ባካሄደው ውጊያ የአብይ አህመድ ጡት ቆራጩን ኃይል አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሲያሯርጡት ውለዋል። በአካባቢው ህዝብን እያሰቃየ የነበረው የአብይ አህመድ ጥምር ኃይል ላይ ከሁለት አቅጣጫ በመግባት ከፍተኛ ጉዳት በማድርስ ከአጣዬ ከተማ እና ከኬሚሴ አቅጣጫ በመነሳት ወደ ካራ ቆሪ የገባውን የጠላት ኃይል ሙት እና ቁስለኛ አድርገውታል። የኦሮሞ ልዩ ዞኑን ሚሊሻ እና ፖሊስ የአጣዬ ከተማ ሚሊሻ እና ፖሊስን ከአካባቢው ከሚገኙ ጡት ቆራጩ የአብይ አህመድ ኃይል ጋር በማጣምር በህዝቡ ከፍተኛ ግፍ እና በደል ሲያደርስ ቆይቷል። ይህ ሰራዊት ዓላማውም የአማራ ሕዝብ ፖለቲካዊና ፣ኢኮኖሚያዊ እና ሰብዓዊ ውድመት እንዲደርስ ማድረግ ነው። በተለይም በዚህ በአካባቢ ነዋሪዎች ላይ እየደረሰ የነበረውን በደል ለማስቆም ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር ባደረሰችበት ምት በርካታ የአብይ አህመድ ኃይሎች በአሳምነው አናብስቶች ከጥቅም ውጭ ሁነዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !! የካቲት 30/06/2018 ዓ.ም

77ኛ ክፍለጦር በጃቢ ጠህናን ወረዳ ከአባት አርበኞች ጋር ውይይት አካሄደ! በአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ስር የሚገኘው 77ኛ ክ/ጦር በተቆጣጠራቸው አከባቢዎች የአርበኞች
+2
77ኛ ክፍለጦር በጃቢ ጠህናን ወረዳ ከአባት አርበኞች ጋር ውይይት አካሄደ! በአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ስር የሚገኘው 77ኛ ክ/ጦር በተቆጣጠራቸው አከባቢዎች የአርበኞች ጦር እያደራጀ ለውጊያ ብቁ እያደረገ ሲሆን፡ ከነዚህ የአባት አርበኞች ጦር ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ጭምር መስጠቱን ክፍለጦሩ በላከው መረጃ አስታውቋል። ክፍለጦሩ በጃቢ ጠህናን ወረዳ ጊዜያዊ መንግት ያቋቋመ ሲሆን፡ በሕዝብ የተመረጡ አስተዳዳሪዎችና የኮሩ ተወካዮች በተገኙበት ነው ከአባት አርበኞች ጦር ጋር ውይይት ያካሄደው። በመድረኩ ተጋብዘው፡ የአባት አርበኞች ጦር ቁመናን እና ቁርጠኝነታቸውን በመመልከት ያደነቁትና ያበረታቱት የ109ኛ ኮር አመራሮች፡ አማራ የታወጀበትን የጥፋት ዘመቻ ለመመከት ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስበዋል ብሏል ክፍለጦሩ በሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ በላከው መረጃ። የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት የጃቢ ጠህናን ወረዳ የአባት አርበኞች ጦር አባላትም፡ ከኮሩና ከክፍለ ጦሩ እንዲሁም ከወረዳው አመራሮች የተላለፉ መልዕክቶችን በሞራል ተቀብለው ለትግሉ ያላቸውን ቁርጠኝነት የገለፁ ሲሆን፡ የሚሰጣቸውን ግዳጅ ለመፈፀም ዝግጁነታቸውን አሳውቀዋል ተብሏል።

+2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ፣ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር በኤፍራታ ግድም ወርዳ በአምቦበርና በጣርማ ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ውይይት አካሔደ!! ​ ህኖም ​የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ዳዊት ገብረመስቀል እና የክፍለ ጦሩ ወታደራዊ አስተዳደር አርበኛ እንዳለ ሸዋዬ በተገኙበት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከተመሰረተ ጀምሮ ዛሬ የደረሰበት የፖለቲካና የወታደራዊ ቁመና፣ የአማራ ሕዝብ ለህልውናው የሚያደርገው ትግል የመጨረሻ ምዕራፍ ማሳያ መሆኑን ለማህበረሰቡ የድርጅቱን መርህና ዓላማ ለሕዝቡ ሰጠዋል። ሕዝቡ የራሱን ልጆች የትግል ጉዞ በትኩረት ከአደመጠ በኃላ የሕዝቡ መኖርና ነፃነት የሚረጋገጠው በዚህ የጋራ ክንድ መሆኑን አፅንዖት ከመስጠትም በላይ እናንተ ልጆቻችን ናችሁ እስካሁን ያስመዘገባችሁት ድል ለኛ ኩራትና ተስፋ ነው።ፋኖ እስካሁን ባስመዘገበው ድል ያለውን ከፍተኛ እርካታም ነው። ልጆቻችን ለኛ የቁም ዋስትና ናቸሁ። በመጨረሻም ማህበርሰቡም ከፋኖ ጎን ቆሞ እስከ ድል መጨረሻ ድረስ አብሮ እንደሚዘልቅ ቃል ገብቷል።በአምቦበርና በጣርማ የታየው ውይይት፣ በትግሉና በሕዝቡ መካከል ያለውን የማይበጠስ ሰንሰለት ይበልጥ አጥብቆታል በማለት ውይይት በሰላም ተጠናቋል። ​ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !! የካቲት 30/06/2018 ዓ.ም

ህዝባዊ ውይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል ‼️ በአነብሴ ሳርምድር እና እነማይ ወረዳ ቀጠና በሚገኙ ቀበሌወች የኮር፣ የክፍለ ጦር እና የጊዜያዊ መንግስት አመራሮች በተገኙበት የካቲት29/06/2018 ዓ.ም ጥልቅ ህዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል። ➻➻➻➻➻➻➻◊◊➻➻➻➻➻➻➻➺ በውይይቱ መድረኩ ➣የአፋብን ምስረታን በተመለከተ ➣የድርጅቱ አሁናዊ ቁመና በተመለከተ ➣የመልካም አስተዳደርን በተመለከተ ህዝባችን ከተደቀነበት የህልውና ችግር ለመውጣት እና አገዛዙ በህዝባችን ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ግንዛቤ በመስጠት የአማራን ህዝብ የትጥቅ ትግል በአጭር ለመቋጨት በመረጃ በሎጅስቲክ አስፈላጊ በሆኑ መንገዶች ሁሉ ከጎናችን እንደሚሆኑ በመግባባት የኮር እና የክፍለ ጦሩ አመራር እና የወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተሰጥተዋል። የካቲት 30/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስ/አማራ ቀጠና - ምኒልክ ዕዝ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ በማንነትና ወሰን ጥያቄያችን ሽፋን የብልፅግናን ስርዓት ለመጠበቅ በራያ ቆቦ ለተሰበሰባችሁ ለራያ አላማጣ: ባላና ኮረም-ወፍላ የስርዓቱ ታጣቂዎችና ምልምል ሰልጣኞችን በሙሉ! የአማራ ህዝብ ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ አጀንዳ አድርጎ የታገለባቸው የማንነትና የርስት ጥያቄ ዛሬም ግንባር ቀደም ጥያቄና የመታገያ አጀንዳችን መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን 2010 ዓ.ም በለውጥ ስም ከመጣው አብይ አህመድና የብልፅግና አገዛዝ ማግስት ጀምሮ ግን የአማራ ህዝብ ጥያቄ ከማንነትና ከርስት ተሻግሮ የህልውና መሆኑን አደጋው ላይ ያለው ህዝባችንና በርካታ ኢትዮጵያውያን የተስማሙበት ጉዳይ ነው::  ለአማራ ህዝብ የአገራችን ኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታና ሐቁ ይህ ሆኖ እያለ በተጠቀሱት የራያ አካባቢዎች ተወላጅ የሆናችሁ የአማራ ልጆች ከአብይ አህመድና ፓርቲው ብልፅግና ጋር ሆናችሁ የምታመጡት አንዳች ውጤት እንደሌለና ወቅቱን የዋጀ ትግል አድርጋችሁ ዘላለማዊ ነፃነት የምትጎናፀፉት በፋኖ ትግልና መንገድ ብቻ እንደሆነ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን! አብይ አህመድ የራያን ህዝብ ጥያቄ "ካርድ" ዛሬም አንድና ያው በሆነው በአማራ እና በትግራይ ህዝብ መካከል ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዲካሄድና እንዲቀጥል በሂደቱም ስልጣኑን ማራዘም ከቻለም ማፅናት እንጂ ሌላ ዘላቂ መፍትሔ እንዲመጣ እንደማይፈልግ ተደጋጋሚ በተግባር የታየ ሲሆን እኛም እንደ ፋኖ ከአብይ አህመድ የምንጠብቀው መፍትሔ የሚወስንልን እጣ ፈንታም እንደሌለ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን! ስለሆነም ይህንን ሐቅና እውነታ ወደ ጎን በመተው ከብልፅግና ጎን ተሰልፈው በራያ ህዝብ ስም በሚነግዱ የደም ነጋዴ አመራሮች እየተመራችሁ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ተታላችሁ በብልፅግና ተደራጅታችሁና ታጥቃችሁ ለውጥ እናመጣለን በሚል ከጨፍጫፊው አገዛዝ ጎን ተሰልፋችሁ ፋኖን ለመውጋት ያሰባችሁ የአካባቢው ተወላጆች ከአድማ ብተናና ሚሊሻ ለይተን እንደማናያችሁ አውቃችሁና የያዛችሁት መንገድ የተሳሳተ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ስንል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መልክታችንን እናስተላልፋለን! በመጨረሻም በገዳዩ የብልፅግና አገዛዝ ላይ ሰይፍ ማንሳት ሲገባችሁ ሠላሳ ዓመት የተሻገረ ሰልፍን መርጣችሁ በተለያዩ ሰብአዊነት በማይከበርባቸው የመጠለያ ጣቢያዎች እና ከተሞች የተቀመጣችሁ የአካባቢው ተወላጅ ወጣቶች የአማራ ፋኖን በመቀላቀል ትግላችሁን እንድትታገሉ: ነፃነታችሁን በትግላችሁ እንድትጎናፀፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!!! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የካቲት 30/2018 ዓ.ም

የአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግሉ ያለበትን ወቅታዊ ቁመና እና በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ግፎችን የግንዛቤ ማስጨበጫ መድርክ ስራዎች ተሰረተዋል። የካቲት 30/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር የካቲት 29/2018 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ ቅድስጌ እና ስር እየሱ ቀበሌ ህዝባዊ ውይይቶችን አካሂዶል። በውይይት መድርኩ የአማራን ህዝብ የትጥቅ ትግል ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ እና የአማራ ህዝብ በገዥው አብይ አህመድ አገዛዝ እየደረሰበት ያለውን ግፍ፣ በደል፣ ዝሪፊያ፣ የጅምላ ግድያ በማስመልከት በስብሰባ መድርኩ ለተገኙት የማህበረሰብ ክፍል ሰፋ ባለ መልኩ ትምህርት ተሰጥቷል። የአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል በአጭር ግዜ ለመቋጨት ህዝባችን ዛሬም እንደ ትላንቱ በመረጃ፣ በሎጀስቲክ እና መሰል ድጋፎች ማገዝ እንዳለበት ህዝባችን ትግሉን ሊጠልፍ ከጠላት ተልዕኮ ይዘው ከሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች መጠንቀቅ እንዳለበትና ይህ ስረዓት በዚህ የትጥቅ ትግል ካልተወገደ የአማራ ህዝብ ዘግናኝ ሰቆቃዎች፣ ግድያዎች እየጨመሩ እንደሚሄዱ የአማራ ህዝብ በገዥው አብይ አህመድ ስረዓት ከምድርገፅ እንደሚጠፋ በውይይት መድረኩ በክፍለ ጦር አመራሮች እና በወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች በሰፊው ተብራርቷል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!! የካቲት 30/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት