ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
4 379
订阅者
-924 小时
+2477 天
+1 42930 天
帖子存档
74ኛ ክ/ ጦር የመጀመሪያውን መደበኛ ጉባኤ አካሄደ! ከህዳር 06 _7/2018 ዓ/ም አፋብሃ ቴዎድሮስ እዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ ጦር ድርጅቱ እያደረገ ያለውን ፈጣን የሆነ የሽግግር፣ የኮር እና የ
+3
74ኛ ክ/ ጦር የመጀመሪያውን መደበኛ ጉባኤ አካሄደ! ከህዳር 06 _7/2018 ዓ/ም አፋብሃ ቴዎድሮስ እዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ ጦር ድርጅቱ እያደረገ ያለውን ፈጣን የሆነ የሽግግር፣ የኮር እና የክ/ጦር አደረጃጀቶችን በፍጥነት የማሳደግ፣ጦሩን  የመፐወዝ እና ጊዜያዊ የወረዳና የቀበሌ መዋቅሮችን አደራጅቶ በማጠቃለል ያጋጠሙ ችግሮችን፣የተወሰዱ መፍትሄወችን በማንሳት የመጀመሪያውን መደበኛ ጉባኤ በተነቃቃ ሁኔታ አካሂዷል።    በውይይቱም የፕወዛ ሂደት መገምገም ፣ የማኔጅመንቱን አንድነትና ቁርጠኝነት መገምገም፤ የክ/ጦሩን የተለያዩ ከፍሎችን ተግባርና ሃላፊነት ከድርጅት መርህ አኳያ መለየት፤ የፋይናንስ እና ንብረት አስ/ር እና የስልጠና ሂደትን አስመልክቶ ጥልቅ ውይይቶች ተካሂደዋል። በቀጣይ 1 ወር ውስጥ መሰራት ስላለባቸው ነገሮች ጥልቅ ውይይት ተደርጎ ስራ ቆጥረው የስራ ስምሪት በመስጠት ክፍለጦሩ ወደሚያስተዳድራቸው ቀጠናወች ተንቀሳቅሰዋል። የቴዎድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኘነት ህዳር 08/2018 ዓ.ም

‎ ‼️‼️‼️ሰበር ሰበር ‼️‼️ አመራሩ ስናይፐር እና ክላሽ በመያዝ ፋኖን ተቀላቅሏል። ጀብደኛው ዘሪሁን ገዛኸኝ ካሳሁን የ602ኛ ኮር 25ኛ ክ/ጦር 2ኛ ሬጅመንት1ኛ ሻንበል ሰዴ ከተማ መሽጎ ከሚገ
+1
‎ ‼️‼️‼️ሰበር ሰበር ‼️‼️ አመራሩ ስናይፐር እና ክላሽ በመያዝ ፋኖን ተቀላቅሏል። ጀብደኛው ዘሪሁን ገዛኸኝ ካሳሁን የ602ኛ ኮር 25ኛ ክ/ጦር 2ኛ ሬጅመንት1ኛ ሻንበል ሰዴ ከተማ መሽጎ ከሚገኘው ከአብይ ቡድን በመክዳት ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር የተቀላቀለ ሲሆን በአመራሮች አቀባበል ተደረገለት። ‎ በህዝብ ላይ የሚያደርገውን በደልና እንግልት አልፎም እህቶቻችንን መድፈርና ንፁሃንን መረሸኑ ያንገበገበው ከጠላትወደ ወገኖቹ ተመልሷል። ‎ ‎1ኛ አንድ ስናይፐር ‎2ኛ አንድ ኮፍ ክላሽ ‎3ኛ 250 ተተኳሽ በመያዝ የወገን ጦርን በዛሬው ዕለት በቀን 08/03/2018 ዓ.ም ተቀላቅሏል። ‎ ‎ድል ለአማራ ፋኖ ‎ክብር በጀግንነት ለተሰው ሰማዕታት ‼️ ‎የቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ ህዳር 08/2018 ዓ.ም

ምርኮኛ የአገዛዙ ወታደሮች የተሀዲሶ ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ ወደቤተሰቦቻቸው አንሄድም ብለዋል። ምርኮኞቹ "ከእንግዲህ በኋላ አላማችሁ አላማችን ነው፡ ከእናንተ ጋር እንሰለፋለን" ነው ያሉት።
ምርኮኛ የአገዛዙ ወታደሮች የተሀዲሶ ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ ወደቤተሰቦቻቸው አንሄድም ብለዋል። ምርኮኞቹ "ከእንግዲህ በኋላ አላማችሁ አላማችን ነው፡ ከእናንተ ጋር እንሰለፋለን" ነው ያሉት።

2. በየእስር ቤቱ ያለ ፍርድ ታጉረው የሚገኙ እና የፍርድ ሂደታቸው ኾን ተብሎ እየተራዘመ ያለው የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እና በምርጫ ሂደቱ በነፃነት እንዲሳተፉ እንጠይቃለን። 3. በየእስር ቤቱ ታጉረው የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ያለምንም ቅድመ ኹኔታ እንዲፈቱና በነጻነት እንዲዘግቡ ብሎም ሕዝብ ግብር እየከፈለ ያቋቋማቸው በመንግሥት ቁጥጥር ስር  ያሉ መገናኛ ብዙኃን ከሥርዓት አገልጋይነትና ግለሰብ አወዳሽነት ወጥተው የተቃዋሚውንም ድምጽ እንዲያሰሙ፣ ለምርጫውም ተገቢውን ሽፋን እንዲሰጡ እንዲደረግ በጥብቅ እናሳስባለን። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ኅዳር ፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ: #ምርጫ_የዴሞክራሲያዊ_ሂደት_ማሳለጫ_እንጂ_የይስሙላ_መርሐ_ግብር_ማሟያ_ሊኾን_አይገባም! በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰጠ መግለጫ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሰፈነባቸው አገራት ሥልጣን በሕዝብ ድምፅ የሚሸጋገርበት ብቸኛው መንገድ ነው። ኢትዮጵያ አገራችን ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ስድስት ዙር ምርጫዎች ያካሄደች ቢሆንም በምርጫ የተለወጠ ሥርዓት ሳይኖር ሰላሳ ረጅም ዓመታት እና ስድስት ከፍተኛ የአገር ሃብት በከንቱ የፈሰሰባቸው የይስሙላ “ምርጫዎች” አካሂዳለች። በያዝነው 2018 ዓ.ም በሕገ መንግሥቱ በተደነገገው መሰረት አገራችን ሰባተኛ ዙር አገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫዎች እንድታካሂድ የሚጠበቅ ሲኾን ምርጫና ምርጫ ነክ ጉዳዮችን በባለቤትነት የሚመራውና የመንግሥት አካል የኾነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም በያዝነው ዓመት ግንቦት ወር ምርጫ ለማካሄድ ረቂቅ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ ለፖለቲካ ፓርቲዎች እና ለሲቪክ ማኅበረሰቡ ማቅረቡ ይታወሳል። መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም በጋራ ለመሥራት ቅንጅት የመሠረትን አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰላማዊ መንገድ ታግለን በነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ ተሳትፈን በማሸነፍ የመንግሥት ስልጣን በመያዝ የምንወዳት አገራችን ኢትዮጵያን ከገባችበት ምስቅልቅል ለማውጣት የምንታገል እንደመኾናችን ምርጫ የዓላማችን ማስፈጸሚያ ብቸኛ መሣሪያ ነው። በዚኹ መሠረት ቦርዱ ያዘጋጀውንና በቦርዱ እቅድ መሰረት በቅርቡ እንዲጀመር የሚጠበቀውን የምርጫ ሂደት እንደ ከፍተኛ ባለ ድርሻ አካል በቅርበት እየተከታተልን እንገኛለን። በየትኛውም አገር ምርጫ ሲካሄድ ብዙ ያልኾኑ ነገር ግን ለምርጫው ስኬታማነት ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ እጅግ መሠረታዊ የኾኑ ቅድመ ኹኔታዎች ሊሟሉ እንደሚገባ እሙን ነው። እነሱም ምርጫ በሚካሄድበት አገርና አካባቢ ምርጫን በነጻነት ማከናወን የሚያስችል የተረጋጋ ሰላምና ፀጥታ መኖር ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው። የምርጫውን ተአማኒነት ለማረጋገጥ ነፃ የምርጫ እንቅስቃሴ ዘገባ እና የምርጫ ሂደት መታዘብ መሠረታዊ ነጥቦች ሲኾኑ የእነዚኽ አለመሟላት የምርጫው ሂደት ላይ ከፍተኛ ጥያቄ በማስነሳት ምርጫውን እና የምርጫውን ውጤት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንደሚመሩ በዓለማችን የተለያዩ አገራት የታየ ነው። አገራችን ኢትዮጵያ ልታካሂድ የምትዘጋጀው ምርጫ ከዚኽ የተለየ አይደለም። ለምርጫ ክንውን መሠረታዊ ተብለው ከሚጠቀሱት ግንባር ቀደም ጉዳዮች ውስጥ የአገራችን ሰላምና ፀጥታ የተረጋጋ አለመኾኑና አገራችን ለተከታታይ ዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መቀጠሏ የምርጫውን በአግባቡ መከናወን መቻል ከፍተኛ ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው። በትግራይ ክልል ከፌደራል መንግሥት ጋር የተገባበት ፍጥጫ፤ በትግራይና አፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ያረገዘው የግጭት ደመና፤ በሶማሌና በአፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተደጋጋሚ ጊዜያት የሚመላለሰው ግጭት፤ በኦሮሚያና ሦማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ያሉ ውጥረቶች፣ በቢኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ያለው ተደጋጋሚ እልቂትና መፈናቀል፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲኽ በጉራጌ ዞን እያጋጠሙ ያሉ የፀጥታ ችግሮች፣ በአማራ ክልል ከኹለት ዓመታት በላይ የዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት፣ በኦሮሚያ ክልል ከአምስት ዓመታት በላይ የቀጠለው የእርስ በርስ ጦርነትና ተደጋጋሚ የዜጎች እገታ በእነዚህ አካባቢዎች ምርጫ ማካሄድ የማይቻልበት ኹኔታን ፈጥረዋል። በሌሎች የጦርነትና የጥይት ድምጽ የማይሰማባቸው  የአገራችን አካባቢዎችም ቢኾን የሰፈነው መንፈስ ጦርነት እየተካሄደ ከሚገኝባቸው አካባቢዎች የተለየ እንዳልኾነ በየቀኑ የሚደርሱን የቀን ተቀን መረጃዎች ማሳያ ናቸው። እኛ የቅንጅቱ አባል ፓርቲዎች በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ ላሉ ጦርነቶች ሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሔ ሊበጅላቸው ይገባል ብለን በተደጋጋሚ ያሳሰብን ቢኾንም ለጥሪያችን ተገቢው ትኩረት ተችሮ ምላሽ ባለመሰጠቱ አገር ዛሬም ከዳር እስከ ዳር በጦርነት ውስጥ ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎንደር ከተማ በቅርቡ ባደረጉት ጉብኝት ከጎንደር እስከ ጎርጎራ ያለ አጃቢ መንቀሳቀስ አለመቻሉን መግለጻቸው የአገርን ነባራዊ ኹኔታ በግልጽ የሚያሳይ ሲኾን ለዚኽ የአገሪቱን ከፍተኛ የሥልጣን መንበር ከጨበጡ ሰው የላቀ ሌላ ተጨማሪ ምስክር አይሻም።  በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በቅርቡ እየተካሄደ ባለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በውስን ወራት ውስጥ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአሰቃቂ ኹኔታ መገደላቸውና ጭፍጨፋውን ለማድበስብስ የተሄደበት ርቀት በቂ ማሳያ ነው። አገር እንዲኽ ባለ ኹኔታ ውስጥ በምትገኝበት በአኹኑ ወቅት ምርጫ ማካሄድ እንደከዚኽ ቀደሞቹ የይስሙላም ቢኾን የማይቻል መኾኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም። ሌላው ጉልህ ማሳያ የሾፌሮች እገታና ግድያ ነው። የእርስ በርስ ጦርነቱ እንዳለ ኾኖ በጋዜጠኞች ላይ በተለያዩ ጊዜያት የሚደርሰው ዛቻ፣ እስራትና አስገድዶ መሰወር ለምርጫው በነጻነት ሽፋን ሊሰጡ በሚገባቸው የመገናኛ ብዙኃን ላይ የፍርሓት ደመና እንዲያጠላና በዚኽም ምክንያት ከእይታ ውጭ በጓዳ የሚከናወን ምርጫ ሊኾን መቻሉ ጥርጥር የለውም። የእኛን ጨምሮ የተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ፍትሕ ተነፍጓቸው በገፍ በየእስር ቤቱ ታጉረው መገኘት ምርጫን ለማካሄድ ያለውን ዕድል ጥያቄ ውስጥ የሚከት ኾኗል። ቀደም ሲል እንደገለጽነው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ወደ ስልጣን መንበር የሚያደርሰን ብቸኛው መንገድ ምርጫ መኾኑን በጽኑ የምናምን ቢኾንም አገር የገባችበትን የእርስ በርስ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ መፍታት ባለመፈለግ፤ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን በጅምላ በማሰር እና ጋዜጠኞች እና የማኅበረሰብ አንቂዎች በየእስር ቤት በማጎር መንግሥት ለምርጫው አስቻይ ኹኔታዎች እንዳይኖሩ በማድረግ ብቻውን ሮጦ ክር በመበጠስና 99.9 በመቶ ድምጽ አገኘኹ በማለት ለቀጣዩ አምስት ዓመታት ሕዝቡ ድምጹን ሰጥቶኛል በሚል ሽፋን የሥልጣን መደላድሉን እያበጀ መኾኑን መሬት ላይ ካለው አካሄድ መረዳት ይቻላል። በዚኽ መልኩ ገዢው ፓርቲ የራሱን የስልጣን ቆይታ ሲያመቻች በሌላ በኩል የእኛ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ወደ ስልጣን መምጣትን እየገደበ መኾኑንና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተሳትፎ በአጃቢነት ብቻ በመወሰን የገዥውን ፓርቲ በምርጫ ማሸነፍ ሕጋዊ (legitimize) ለማድረግ እየተሠራ መኾኑንና  በዚኽ የሚታለል የቀነጨረ አዕምሮ ያለው ስብስብ እንዳልሆንም ግልጽ ማድረግ እንወዳለን። ከዚኽ በመነሳት የምርጫ የጊዜ ሠሌዳው በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሕዝብ ይፋ ከመደረጉ አስቀድሞ ወይም ደግሞ እስከ ኅዳር ወር መጨረሻ ሣምንት ድረስ (ከኹለቱ በቀደመው) መንግሥት የሚከተሉትን ተግባራዊ በማድረግ ለምርጫው ምቹ መደላድል እንዲፈጠር ጥብቅ መልዕክት እያስተላለፍን በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ መንግሥት እነዚኽን ተግባራት ሊፈጽም ካልቻለ ጉዳዩን በመመርመር በቀጣይ የምንወስደውን እርምጃ ለሕዝባችን ይፋ የምናደርግ መኾናችንን እንገልጻለን። በዚኽ መሠረት፣ 1. በአገራችን እየተካሄደ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም። ለዚኽም የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ወደ ተግባር ከመሸጋገሩ ቀደም ብሎ በተግባር የተረጋገጠ እርምጃ በመውሰድ ለምርጫ አመቺ ኹኔታ መፈጠሩን መንግሥት ግልጽ እንዲያደርግ ተዋጊ ኃይሎችም ይኽንኑ እንዲያረጋግጡና ሕዝብም ይኽንኑ እንዲመሰክር አበክረን እናሳስባለን።

የአፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት አስተዳደር ህዳር 07/2018 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ 3 ቀበሌወች መንግስቶ ፣ ሰቀላ፣የቀጋን ቀበሌዎች ላይ ➢የቀበሌ
+4
የአፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር  የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት አስተዳደር ህዳር 07/2018 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ 3 ቀበሌወች መንግስቶ ፣ ሰቀላ፣የቀጋን ቀበሌዎች ላይ ➢የቀበሌ አስተዳደር ➢የቀበሌ ፀጥታ ጉዳይ ➢የቀበሌ ፍርድ ሸንጎ ➢የቀበሌ ወጣቶች ተጠሪ እንዲሁም የቀበሌ ችግር ፈች የሀገር ሽማግሌዎችን አዋቅሯል። በክፍለ ጦሩ ጊ/መንግስት ሰብሳቢ እና የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች የተመራው የህዝብ ውይይት የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያለበት ወቅታዊ ቁመና በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በውይይት መድርኩ ተሳታፊ የነበረው የህብረተሰብ ክፍል ለፋኖ ያለቸውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!     አፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ    ህዳር 08/2018 ዓ.ም

የአማራ ባንክ ሰራተኛው አማራ በመሆናቸው በአገዛዙ የሚደርስባቸውን እንግልት ለመመከት ጫካ መግባት እና ነፍጥ ማንሳቱ ብቻ አዋጭ እንደሆነ በመረዳት የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚንልክ ዕዝን እየተቀ
+2
የአማራ ባንክ ሰራተኛው አማራ በመሆናቸው በአገዛዙ የሚደርስባቸውን እንግልት ለመመከት ጫካ መግባት እና ነፍጥ ማንሳቱ ብቻ አዋጭ እንደሆነ በመረዳት የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚንልክ ዕዝን እየተቀላቀሉ ነው።

"ወሬን ለወሬኛው ትተን ወደፊት በንስር ከፍታ እየተጓዝን ነው"!! መሰባሰብ መምከር ሀይልን ይፈጥራል። ስንሰባሰብ፤ ስንመካከር ፤ ለጋራ ዓላማችን ስንወያይ ችግሮቻችንን እንቀርፋለን፤ አንድነታችንን እ
"ወሬን ለወሬኛው ትተን ወደፊት በንስር ከፍታ እየተጓዝን ነው"!! መሰባሰብ መምከር ሀይልን ይፈጥራል። ስንሰባሰብ፤ ስንመካከር ፤ ለጋራ ዓላማችን ስንወያይ ችግሮቻችንን እንቀርፋለን፤ አንድነታችንን እናጎለብታለን፤ ትግላችን ወደፊት ይራመዳል፤ በተቃራኒው ደግሞ እኛ ስንሰባሰብ የጠላት ስነልቦና ይበተናል። ስለዝህ መሰባሰብ፥ መምከር፥ መመካከር ሀይልን ይፈጥራል። ሀይል ደግሞ ዓላማችንን ከግብ ለማድረስ ወሳኝ ነው። ምክንያቱም ዓለማችን ሀይል ወዳለው ብቻ ታዘነብላለች። ዓለም የሀያላን ናት።

የአዴት ዳቫል ውጊያ! በትላንትናው ዕለት ዳቫል እና ሮብ ገበያ እና ላይ ጠላት እንደ እባብ ሲቀጠቀጥ ውሏል። የ102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር እና 22ኛ ክ/ጦር በጥሞረት ጠላትን እሮብ ገበያ እና ዳቫት
+1
የአዴት ዳቫል ውጊያ! በትላንትናው ዕለት ዳቫል እና ሮብ ገበያ እና ላይ ጠላት እንደ እባብ ሲቀጠቀጥ ውሏል። የ102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር እና 22ኛ ክ/ጦር በጥሞረት ጠላትን  እሮብ ገበያ እና ዳቫት ላይ ሲያስጨንቁት የዋሉ ሲሆን፦ በተቀናጀ መልኩ የጠላትን የሀይል አሰላለፍ በቂ መረጃ ቀድሞ በማወቅ እልህ አሰጨራሽ በሆነ የእጅ በእጅ ውጊያ በማድረግ ተላላኪውን የአብይ ሰራዊት ሲያዝረከርኩት ውለዋል። በተደረገው ውጊያ ከ13 በላይ ጠላት ሲደመሰስ 09 ቁስለኛ በማድረግ እየቀጠቀጡ ወደ አዴት ከተማ በመጣበት እግሩ እያባረሩ አስገብተውታል። አፋብኃ|ቴዕ/ሕ/ግ/መምሪያ    ህዳር 08/2018 ዓ.ም

👉በዓሉ ካለቀ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን የፍትሕ ጥያቄ እንመለስ። የኦርቶዶክሳውያን ዋና ገደያችን ራሳችን ነን።ለምን?? 👉1.)ሕይወት አልባ ሊበራል ክርስቲያኖች መብዛታቸው። 👉2.)ቅጥረኛ ምንደኛ
👉በዓሉ ካለቀ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን የፍትሕ ጥያቄ እንመለስ። የኦርቶዶክሳውያን ዋና ገደያችን ራሳችን ነን።ለምን?? 👉1.)ሕይወት አልባ ሊበራል ክርስቲያኖች መብዛታቸው። 👉2.)ቅጥረኛ ምንደኛ አገልጋዮች መብዛታቸው። 👉3.)ፈዛዛ ደንዛዛ ክርስቲያኖች መብዛታቸው። 👉4.)መከራውን የተለማመዱ አደንዛዦች ጆሯችንን ስለጨመደዱት። 👉5.)ቤታችንን የአማሳኞች አውድማ አድርገን በመቀመጣችን ምክንያት። 👉6.)አንድ ሁነን የመፍትሄ መንገድ ባለመፈለጋችን። 👉7.)ባለወጎች በሚነግሩን በትንሽ ተስፋ መጽናናታችን። 👉8.)ክፉዎችን አምነን ዝም ብለን መቀመጣችን። 👉9.)ቀድመው የተረዱ ቀድመው የነቁ ወንድም እኅቶችን እያስበላን መቀጠላችን። 👉10)የስንፍናችን እና የአስመሳይነታችን መብዛት። 👉11.)በሰው ድካም እኛ ለመኖር መፈለጋችን የማያድነንን ራስ ወዳድነታችን። 👉12.)በሃይማኖቻችን ውስጥ ለውስጥ የሚሠርጉ ቀሚስ የለበሱ ቆብ ያጠለቁ ሻሽ ያመሙ የጥፋት አገልጋዮችንን ከእውነተኛ አባቶች ጋራ እኩል ማመናችን። 👉13.)የአጭበርባሪ ባሕታውያን፣አጥማቅያን ሰለባ በመሆናችን።.... 👉በሉ አሁን የእንቅልፍ ጊዜ ከይደለም፣አሁን የስንፍና ጊዜው አይደለም፣አሁን የጸጸት ጊዜ አይደለም፣አሁን የማስመሰል ጊዜው አይደለም።... 👉ክርስቲያን የሆነ ሰውን ሁሉ የቤተ ክርሶቲያን ጉዳይ ይመለከተዋል። 👉የተረጋገጠ ፍትህ እስክናገኝ ድረስ ጀመርነውን ከግብ ሳናደርስ መመለስ አይቻልም። 👉በዚህ ሰዓት ከቤተ ክርስቲያን ጥፋት በላይ የሆነ የገብረ መድኅን እንየው © ገብረ መድኅን እንየው

👉አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት :- አገዛዙ አሁን ምሽት 4::00 ሰዓት የጦር ጄት ወደ ምዕራብ ጎጃም ባሉ ቀጠናዎች ለማሰማራት ትዕዛዝ መስጠቱን ምንጮች አረጋግጠዋል። በተለይም ቴወድሮስ ዕዝ በተቆጣ
👉አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት :- አገዛዙ አሁን ምሽት 4::00 ሰዓት የጦር ጄት ወደ ምዕራብ ጎጃም ባሉ ቀጠናዎች ለማሰማራት ትዕዛዝ መስጠቱን ምንጮች አረጋግጠዋል። በተለይም ቴወድሮስ ዕዝ በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች ከደምበጫ እስከ ባህርዳር ባሉ አካባቢዎች  ጥቃቱ ከንጋት ጀምሮ  ሊፈፀም ስለሚችል የወገን ጦር አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መረጃው ለሁሉም ይዳረስ!

የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት በሮብ ገበያ እና ዳቫት ላይ ጠላት እንደ እባብ ሲቀጠቀጥ ውሏል።            ህዳር 07/2018 ዓ.ም የ102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር እና 22ኛ ክ/ጦር በጥሞረት ሁለቱ ክፍለ ጦሮች ጠላትን በዛሬው እለት እሮብ ገበያ እናዳቫት ላይ ሲያስጨንቁት የዋሉ ሲሆን፦ በተቀናጀ መልኩ የጠላትን የሀይል አሰላለፍ በቂ መረጃ ቀድሞ በማወቅ እልህ አሰጨራሽ በሆነ መልኩ የእጅ በእጅ ውጊያ በማድረግ ተላላኪውን የአብይ ሰራዊት ሲያዝረከርኩት የዋሉ ሲሆን በተደረገው ጥቃት ከ13 በላይ ሲደመሰስ 9 ቁስለኛ በማድረግ እየቀጠቀጡ ወደ አዴት ከተማ  በመጣበት እግሩ እያባረሩ አስገብተውታል። ህዳር 07/2018 ዓ.ም ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የ201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ሲሆን ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሎ 4 የስርዐቱ ወታደር 4 ጥቁር ክላሽና ሙሉ ትጥቅ በመያዝ    ምስራቅ አማራ ኮር አንድ የባለሽርጡ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል። የሚዋጋበት አጀንዳ የሌለው የብልፅግና ሰራዊት አሁንም በሰሜን በኩል አዲስ ጦርነት ጀምሮ ሊያዋጋን ስለሆነና መምሪያም እየወረደ ስለሆነ ነው ኮብልለን ፋኖን የተቀላቀልነው ይላሉ አንድ ስናይፐርና አምስት ክላሽ ይዘው ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር አንድ የባለሽርጡ ክፍለጦርን የተቀላቀሉት  የሰራዊቱ አባላቶች:: በዚህም 4 ጥቁር ክላሽ  ከሙሉ ትጥቁና ተተኳሹ ጋር  እንዲሁም  የወገብና የደረት ትጥቅ ከተተኳሽና የእጅ ቦምቦች በመያዝ ወደ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦርን  ተቀላቅለዋል:: በሌላ የተጋድሎ መረጃ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር  እና ምስራቅ  አማራ ኮር 2 ታጠቅ ክፍለጦር  መርሳ አቅርቢያ ወረራሎ በሚባል ቦታ በተያዘ   የደፈጣ ጥቃትና በወሰዱት እርምጃ አንድ ጓድ የጠላት ሰራዊት  ቀረጥ በሚቀርጡበት ቦታ ላይ በተያዘ ዴንገተኛ ጥቃት ሙትና  ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ፋኖ ደምሌ መኮነን የምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 6/2018 ዓ.ም

አማራ ማለት ለኢትዮጵያ የታሪክ መሰረት፣ የቋንቋ ድልድይ፣ የነፃነት ጠበቃ፣ የሃይማኖትና የባህል ማዕከል ነው። የብዙኃን መግባቢያ የሆነ ቋንቋን በማፍራት፣ የሀገር ሉዓላዊነትን በማስጠበቅ እና የኢትዮ
አማራ ማለት ለኢትዮጵያ የታሪክ መሰረት፣ የቋንቋ ድልድይ፣ የነፃነት ጠበቃ፣ የሃይማኖትና የባህል ማዕከል ነው። የብዙኃን መግባቢያ የሆነ ቋንቋን በማፍራት፣ የሀገር ሉዓላዊነትን በማስጠበቅ እና የኢትዮጵያን ታላላቅ ቅርስ በመጠበቅ ለዚህች ውድ አገር የማይናቅ ውለታ የፈፀመ ሕዝብ ነው። "አማራነት"መልኳኗ ውበቷን ማነች ብትለኝ አርበኛውን ድርሳን ብርሃኔን ትመስላለች !! ወንድማለም እድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥህ!

የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አካል የሆነው የአማራን ትግል የሚመጥን ሁኖ ዲስፕሊንድ የሆነ ጦረኞች የተሰባሰበበት የአድዋ ክፍለጦር ዋና ሰብሳቢ የሳሚያችን ቀኝ
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አካል የሆነው የአማራን ትግል የሚመጥን ሁኖ  ዲስፕሊንድ የሆነ ጦረኞች  የተሰባሰበበት የአድዋ ክፍለጦር ዋና ሰብሳቢ የሳሚያችን ቀኝ እጆች የቀጠናው ሚዛን አስጠባቂዎች  አርበኛ ጌታቸው አማረ እና የክፍለጦሩ ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ጌታቸው አከለ። ድል ለአማራ ፋኖ✌️

“ሰውም ኢትዮጵያዊም ያልሆነውን ጭ ራ ቅ ከሕዝባችን አናት ላይ አንስተን ማንነታችንን አክብረንና አስከብረን የምንኖርበት ስርአትን ለመገንባት በጋራ እንነሳ።” አርበኛ ዘመነ ካሴ!!
“ሰውም ኢትዮጵያዊም ያልሆነውን ጭ ራ ቅ ከሕዝባችን አናት ላይ አንስተን ማንነታችንን አክብረንና አስከብረን  የምንኖርበት ስርአትን ለመገንባት በጋራ እንነሳ።” አርበኛ ዘመነ ካሴ!!

ሕዝባዊ ውይይት በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ 14ኛ ክፍለ ጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ ከወንቃና ዲባጎ ማሕበረሰብ ጋር ውይይት አድርጓል። በውይይቱ ስለ ትግሉ ወቅ
+2
ሕዝባዊ ውይይት  በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ 14ኛ ክፍለ ጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ ከወንቃና ዲባጎ ማሕበረሰብ ጋር ውይይት አድርጓል። በውይይቱ ስለ ትግሉ ወቅታዊ ቁመናና በመልካም አስተዳደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። ህዳር 07/2018 ዓ.ም ድል ለአማራ ፋኖ! ፋኖ ዘመን ባሳዝነው የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት

የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ አንደኛ ኮር የሰባት ለሰባ ደመላሽ ሻለቃ ክንደ ነበልባሎች የአሳምነው ልጆች አሁን በዚህ ስዓት ከጡት ቆራጩ አብይ አህመድ መከላከያ ኃይል
+1
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ አንደኛ ኮር የሰባት ለሰባ ደመላሽ ሻለቃ ክንደ ነበልባሎች የአሳምነው ልጆች አሁን በዚህ ስዓት ከጡት ቆራጩ አብይ አህመድ መከላከያ ኃይል ጋር ውጊያ በማድረግ አስደማሚ ኦፕሪሽን በመስራት ምሽቷን በአንድዬ ልጆቿ ደማቅ ድልን አስመዝግባለች ዝርዝር መረጃዎች እንመልስበታለን!!