ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
4 132
订阅者
无数据24 小时
+4577 天
+1 19430 天
帖子存档
ሠራዊታችን ይልቅ በማይረባ ሰበባሰበብ ድጋፋችሁን ማስተጓጎል እንደማይገባችሁና በጽናት ከጎናችን እንድትቆሙ  ጥሪያችንን እናቀርብላችሗለን። 3ኛ ለፀረ-ብልጽግና ትግሉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ሀገራችን እና አጎራባቾቿ ሁሉ እየተተራመሱ ወደ ከፋ እልቂት እየገሰገሱ በሚገኙበት በዚህ አደገኛ ወቅት አተራማሹንና የእጅ አዙር ጦርነት ተላላኪውን አረመኔያዊ የብልጽግና አገዛዝ የሚታገለው ማህበረሰብ መበራከቱ ለሀገራችንም ሆነ ለቀጠናው ተስፋን አጭሯል። የነበረው ተናጠላዊ ጥረት ለጠላት ምቹ አጋጣሚ እንደሆነለት ሁሉ የተጀማመሩ መቀራረቦች ጠላትን ሲያስበረግጉት በአደባባይ ተመልክተናል። ኢትዮጵያዊያን የትግሉ ማህበረሰብ አካላት የጠላትን የጥፋት ፍጥነትና የመፍትሔውን አስቸኳይነት በመገንዘብ ከነበረው ቀርፋፋ አካሄድ የተላቀቀ ትብብር በማድረግ ከቀጠናው የፀረ-ብልጽግና ኃይሎች ጋር በመቀናጀት እንዲሁም የተሳለጠ የጋራ ዲፕሎማሲ በመስራት ድላችንን በአጭር ጊዜ እናደርግ ዘንድ ብርቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በበኩላችን የህዝባችንንና የሀገራችንን ጥቅም ለሚያስከብር ትብብር ሁሌም ዝግጁነታችን እናረጋግጣለን። 4ኛ ለአማራ ሕዝብ የተከበርህው ህዝባችን ሆይ እኛ የገጠመንን ህዝባዊ አደጋ ለመቀልበስና መፃኢ ተስፋችንን በጎ ለማድረግ የአደጋው ባለቤት የሆነውን አረመኔያዊ አገዛዝ ጠላትን እየተናነቅን የምንገኝ መሆናችንን አቅፈህና ደግፈህ እያታገልህን ለምትገኘው ጀግና ህዝባችን ለማስረዳት የምንኳትን አይደለንም። ይልቁንስ የገጠመንን ውስብስብ አደጋ በቀላል መስዋእትነትና በአጠረ ጊዜ ለመቀልበስ ሠራዊታችንን ማጠናከር፣ በየዘርፉና በያለንበት ሁሉ የትግሉ አካል መሆንን ይጠይቃል። ራሳችንን ከጥፋት ለመከላከል ከጠላታችን የማጥፋት ርብርብ የላቀ ርብርብ ያስፈልጋል። 5ኛ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ የተከበርህው የታላቋ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ የዘመናት ተጨባጭ ህዝባዊ ፍላጎትህና ተስፋህ በውስን ቡድናዊ ፍላጎትና አንባገነናዊ እንዲሁም ሗላቀር የፖለቲካ ከባቢ ምክንያት አርቲስቱ እንዳለው ከዓለም ፊት እንዳልነበርህ ወደሗላ ቀርተህ በማይመጥንህና አዋራጅ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለህ። በፖለቲካ ወለድ የጋራ ራዕይ ማጣት፣ የእርስ በርስ መጠራጠርና መጠቃቃት፣ ርሀብ፣ መፈናቀልና መሰደድ፣ አፈናና ከባድ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲሁም ከቅርብና ሩቅ ዓለም አቀፍ መገለልና መናቅ ገጥሞሀል። በጥቅሉ ተጨባጭ ሀገራዊ የጋራ የህልውና አደጋ ውስጥ እንገኛለን። በመሆኑም ለዚህ ሁሉ ችግር ባለቤት የሆነውን አረመኔያዊ አገዛዝ ለማስወገድና በሁላችን ድርሻና መዋጮ ላይ ቆማ ለሁላችን የምትሆን ታላቅ አፍሪካዊትና ዓለም አቀፋዊት ሀገር ለመገንባት የጋራ የመስዋዕትነት አሻራ ለማስቀመጥ እንድትንቀሳቀስና የሚደረጉ የቅርብም ሆነ የሩቅ የፀረ-ብልጽግና ትግል ትብብሮችን በቀናነት በመረዳትና በመደገፍ የመከራችንን ጊዜ በማሳጠር ተስፋችንን ቅርብ እንድናደርግ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርብልሀለን። 6ኛ በጠላት አሰላለፍ ውስጥ ለምትገኙ አመራርና አባላት እናንተ በቀጥታ የጠላት አሰላለፍ ውስጥም ሆነ በባንዳነት የተሰለፋችሁ ዘመኑን ያልዋጃችሁ "ወገኖቻችን" ያደረሳችሁት ህዝባዊና ሀገራዊ በደል ከበቂ በላይ ሆኖ ሞልቶ የፈሰሰ መሆኑን ተረድታችሁ ከግለሰባዊ ጊዜያዊ ጥቅምና ፍላጎታችሁ በመላቀቅ ለህዝባዊና ሀገራዊ ጥቅምና ፍላጎቶቻችን ትገዙ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርብላችሗለን። ትግል ነውና በጠላት አሰላለፍ እስካላችሁ ድረስ መራራ እርምጃዎችን ወስደናል፤ ይህ ተጠናቅሮ የሚቀጥል ይሆናል። ሆኖም አሰላለፋችሁን ብታስተካክሉና ባሉን አማራጮች ሁሉ ብትቀላቀሉ የምህረት በራችን ሁሌም ክፍት መሆኑን እያሳወቅን ለራሳችሁም ሆነ ለቤተሰቦቻችሁ ብሎም ለህዝብና ሀገር የሚያኮራ ታሪክ ብቻም ሳይሆን የዘመን ግዳጅም ነውና ተጨማሪ ጊዜ እንደማታጠፉ ተስፋ እናደርጋለን። 7ኛ  ለዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተቋማትና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአማራ ህዝብ ሁኔታ፤ የኢትዮጵያ ሁኔታ ለውስጣዊ ሰብዓዊ ቀውስ ብቻም ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድና ለመካከለኛው ምስራቅ ሁሉ የትርምስ ምንጭና አካል እየሆነ በመሆኑ የትርምሱ ምንጭ የአረመኔው አብይ አህመድ አገዛዝ እንዲያበቃና በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ቀንድና በመካከለኛው ምስራቅ የዴሞክራሲ አየር ነፍሶ ነፃነት፣ ሰላም፣ ፍትህና እኩልነት እንዲረጋገጥ በሰብዓዊነት ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች፣ በጦር ወንጀል፣ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተጨማለቀውን አረመኔያዊ አገዛዝ ባለመደገፍና በማውገዝ፣ ልዩ ልዩ አስገዳጅ የለውጥ ማዕቀቦችን በመጣልና የትግሉን ማህበረሰብ በመደገፍ ዓለም አቀፋዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እያሳሰብን ለመሰል ትብብር ቀናኢ መሆናችንን እናሳውቃለን። በተጨማሪም በየአውደ ውጊያው የሚማረኩ እና ወዶገብ የጠላት ሠራዊት አባላትና አመራሮችን ዓለምአቀፍ የጦር ህግን ተከትለን ለመያዝ እየተጋን ያለን መሆኑ ታውቆ ያደረ ጉዳይ ነው። በአሁኑ ወቅት ለረጅም ወራት የቆዩ እና አዳዲስ ምርኮኛና ወዶ ገቦች በስፋት በጊዜያዊ ማቆያ ካምፖቻችን የሚገኙ ሲሆን እንደ ቀይ መስቀል ያሉ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና ረጅዎች ፈጣን ሰብዓዊ ድጋፍ በማቅረብ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እና በተለይም ዓለምአቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር ምርኮኞችን እንደተለመደው ለአገዛዙ የአየር ጥቃትና መሰል የከፋ አደጋ ከመጋለጣቸው በፊት በፍጥነት እንዲረከበን ጥሪያችንን እናቀርባለን።በመጨረሻም በጉጉት የምትጠብቁት አማራዊ አንድነታችን የመጨረሻው ከፍታ ላይ የደረሰ ሲሆን ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ትልቁን ብስራት ይዘን እንወጣለን ። አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ

የጠላት ሀይል እየተናደ ነው ተቋሙኝ እየፈረሰ ነው ‼️ ጥር 01/2018 ዓ.ም ከመከላከያ ተቋም በመውጣት በዛሬው እለት 201ኛ ክር 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። 1ኛ ዳንኤል ፈይሳ 602ኛ ኮር
+1
የጠላት ሀይል እየተናደ ነው ተቋሙኝ እየፈረሰ ነው ‼️ ጥር 01/2018 ዓ.ም ከመከላከያ ተቋም በመውጣት በዛሬው እለት 201ኛ ክር 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። 1ኛ ዳንኤል ፈይሳ 602ኛ ኮር 25ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት 2ኛ ጫላ ጉታ 602ኛ ኮር 25ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት የነበሩ በዛሬው እለት በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ እና መከራ እያየን መቋቋም ስላቃተን በቀሪ ጊዜያችን ህዝባችን ለመካስ ቆርጠን ተነስተናል። ጥር 01/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር ድልን እየተቀናጀ ይገኛል!! የአብይ አህመድ አረመኔያዊ ሰራዊት ኃይል በየትኛውም የአማራ ግዛቶች በመግባት እንደ ቄራ ከብት እያርደንና እያሳደደን የቆየ መሆኑ የሚታወቅ የምድር ሀቅ ነው ሁኖም በሸዋ ደራ የበፍቃዱ በላይ ክፍለጦር ከሰው በላው አብይ አህመድ ሰራዊት ጋር ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ይገኛል። በዚሁም በትናትናው ዕለት ማለትም በቀን 01/05/2018 ዓ.ም ከጀማ ወንዝ እስከ ሰለልኩላ በሻለቃ አባዬ አብዬ የሚመራው የጀማ ዘቦቾ ባደረጉት ትንቅንቅ ጠላት ሙትና ቁስለኛ የሆነ ሲሆን እግረኛ ኃይሉም በኦራል ሲንቀሳቀስ የነበረ ተጨማሪ ኃይል ተደምስሷል። በዚህ አውደ ውጊያ ያለምንም የወገን መሰዋትነት የመጣው ድልም የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የበፍቃዱ በላይ ክፍለጦርን የሽምቅ ውጊያ ብቃትና አይን ከቅንድብ ለይቶ የመምታት ብቃት በጠላት ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ እንዲፈጥር በማድርግ እየሰሩ ይገኛል።በተመሳሳይ ማሞ መሳለሚያ አገዛዙ ለመረጃ በሞተር የላከው ሚኒሻ በአሳምነው ተርቦች እስከወዲኛው የተሸኘ ሲሆን የደራ አማራን ህዝብ ሳልጨርስ እንቅልፍ አልተኛም ያለው ብልፅግና የጫካው ሸኔን ተጠጉልኝ በማለት ጩኸቱን እያሰማ ይገኛል። ስለሆነም ማህበረሰቡ ከመሰል ጥቃቶች ራሱን እንዲጠብቅ፤እንዲሁም ጥር በተለይም በክርስቶስ እምነት ዘንድ የአስተርዮ ባዓል በሰላም እንዲከበር ማህበረሰቡና አባት አርበኛው ሳይዘናጋ አከባቢውን እንዲጠብቅ በዚሁ አጋጣሚ መልዕክቴን ማቅረብ እወዳለሁ። መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማርረ ታዘዘ ነው " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ‎አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል ጥር 03/2018 ዓ.ምየአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር ድልን እየተቀናጀ ይገኛል!! የአብይ አህመድ አረመኔያዊ ሰራዊት ኃይል በየትኛውም የአማራ ግዛቶች በመግባት እንደ ቄራ ከብት እያርደንና እያሳደደን የቆየ መሆኑ የሚታወቅ የምድር ሀቅ ነው ሁኖም በሸዋ ደራ የበፍቃዱ በላይ ክፍለጦር ከሰው በላው አብይ አህመድ ሰራዊት ጋር ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ይገኛል። በዚሁም በትናትናው ዕለት ማለትም በቀን 01/05/2018 ዓ.ም ከጀማ ወንዝ እስከ ሰለልኩላ በሻለቃ አባዬ አብዬ የሚመራው የጀማ ዘቦቾ ባደረጉት ትንቅንቅ ጠላት ሙትና ቁስለኛ የሆነ ሲሆን እግረኛ ኃይሉም በኦራል ሲንቀሳቀስ የነበረ ተጨማሪ ኃይል ተደምስሷል። በዚህ አውደ ውጊያ ያለምንም የወገን መሰዋትነት የመጣው ድልም የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የበፍቃዱ በላይ ክፍለጦርን የሽምቅ ውጊያ ብቃትና አይን ከቅንድብ ለይቶ የመምታት ብቃት በጠላት ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ እንዲፈጥር በማድርግ እየሰሩ ይገኛል።በተመሳሳይ ማሞ መሳለሚያ አገዛዙ ለመረጃ በሞተር የላከው ሚኒሻ በአሳምነው ተርቦች እስከወዲኛው የተሸኘ ሲሆን የደራ አማራን ህዝብ ሳልጨርስ እንቅልፍ አልተኛም ያለው ብልፅግና የጫካው ሸኔን ተጠጉልኝ በማለት ጩኸቱን እያሰማ ይገኛል። ስለሆነም ማህበረሰቡ ከመሰል ጥቃቶች ራሱን እንዲጠብቅ፤እንዲሁም ጥር በተለይም በክርስቶስ እምነት ዘንድ የአስተርዮ ባዓል በሰላም እንዲከበር ማህበረሰቡና አባት አርበኛው ሳይዘናጋ አከባቢውን እንዲጠብቅ በዚሁ አጋጣሚ መልዕክቴን ማቅረብ እወዳለሁ። መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማርረ ታዘዘ ነው " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ‎አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል ጥር 03/2018 ዓ.ም

በአብይ አህመድ አገዛዝ ታፍሰው ብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም የገቡ 20 ምልምል ሠልጣኝ ሠራዊት አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛኮር 88ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀሉ * በምዕ/ጎጃም ዞን ብር ሸለቆ ወታደ
+1
በአብይ አህመድ አገዛዝ ታፍሰው ብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም የገቡ 20 ምልምል ሠልጣኝ ሠራዊት አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛኮር 88ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀሉ * በምዕ/ጎጃም ዞን ብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ከኦሮሚያ ክልልና ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ታፍሰው ወደ ብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ከመጡት መካከል 20 ወጣቶች ተልዕኮ በተሰጣቸው ቀኘዎቻችን በኩል ወደ 109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር እንዲቀላቀሉ ማድረግ ተችሏል። ወጣቶቹ ከት/ቤት፣ከመዝናኛ ቦታ(ከፑል ቤት)፣ከተለያዬ የስራ ቦታ ታፍሰው እንደመጡና ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ አሁን ላይ እንደማያወቁ የገለጹ ሲሆን አብዛኛው ምልምል ሰልጣኝ የመውጫ መንገዱን ካገኘው የመክዳት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል። 👉ከአሁን በፊት በ109ኛ ኮር :-          1.በ77ኛ ክ/ጦር 58 ምልምል ሰልጣኞችን          2.በ99ኛ ክ/ጦር 42 ምልምል ሰልጣኞችን በድምሩ 100 ሰልጣኞችን ወደ አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ተቀላቅለዋል።          አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ! 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ጥር 02/2018 ዓ.ም

በአብይ አህመድ አገዛዝ ታፍሰው ብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም የገቡ 20 ምልምል ሠልጣኝ ሠራዊት አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛኮር 88ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀሉ ***** በምዕ/ጎጃም ዞን ብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ከኦሮሚያ ክልልና ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ታፍሰው ወደ ብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ከመጡት መካከል 20 ወጣቶች ተልዕኮ በተሰጣቸው ቀኘዎቻችን በኩል ወደ 109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር እንዲቀላቀሉ ማድረግ ተችሏል። ወጣቶቹ ከት/ቤት፣ከመዝናኛ ቦታ(ከፑል ቤት)፣ከተለያዬ የስራ ቦታ ታፍሰው እንደመጡና ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ አሁን ላይ እንደማያወቁ የገለጹ ሲሆን አብዛኛው ምልምል ሰልጣኝ የመውጫ መንገዱን ካገኘው የመክዳት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል። 👉ከአሁን በፊት በ109ኛ ኮር :- 1.በ77ኛ ክ/ጦር 58 ምልምል ሰልጣኞችን 2.በ99ኛ ክ/ጦር 42 ምልምል ሰልጣኞችን በድምሩ 100 ሰልጣኞችን ወደ አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ተቀላቅለዋል። አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ! 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ጥር 02/2018 ዓ.ም

"በመጨረሻም በጉጉት የምትጠብቁት አማራዊ አንድነታችን የመጨረሻው ከፍታ ላይ የደረሰ ሲሆን ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ትልቁን ብስራት ይዘን እንወጣለን ።" ከቴዎድሮስ ዕዝ መግለጫ
"በመጨረሻም በጉጉት የምትጠብቁት አማራዊ አንድነታችን የመጨረሻው ከፍታ ላይ የደረሰ ሲሆን ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ትልቁን ብስራት ይዘን እንወጣለን ።" ከቴዎድሮስ ዕዝ መግለጫ

እንደሚታወቀው ከትግሉ የዓላማ ክብደትና የጠላት አረመኔነት አንፃር ይህ አማራዊ ተጋድሎ ሰፊ ሰብዓዊ ርብርብ ይጠይቃል። በመሆኑም ከትናንቱ ይልቅ ዛሬ እና ነገ ህዝባችንን ያስቀደመ ታጋይ ሰራዊቱንና አታጋይ ድርጅታችንን የበለጠ ለማጠናከርና ለመደገፍ እረፍት አልባ ሆኖ በትጋትና በጽናት መስራትን ይጠይቃል። ህይወቱን ያለስስት ለህዝባችን መድኅንነት የሞት ከለላ ለሆነው አዳኝ አማራዊ ሠራዊታችን ሁሌም ከጎኑ ትቆሙ ዘንድ አደራ ማለት እንፈልጋለን። በብርቱ እየተፈተነ በጽናት ከሚዋደቀው ሠራዊታችን ይልቅ በማይረባ ሰበባሰበብ ድጋፋችሁን ማስተጓጎል እንደማይገባችሁና በጽናት ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርብላችሗለን። 3ኛ/ ለፀረ-ብልጽግና ትግሉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ሀገራችን እና አጎራባቾቿ ሁሉ እየተተራመሱ ወደ ከፋ እልቂት እየገሰገሱ በሚገኙበት በዚህ አደገኛ ወቅት አተራማሹንና የእጅ አዙር ጦርነት ተላላኪውን አረመኔያዊ የብልጽግና አገዛዝ የሚታገለው ማህበረሰብ መበራከቱ ለሀገራችንም ሆነ ለቀጠናው ተስፋን አጭሯል። የነበረው ተናጠላዊ ጥረት ለጠላት ምቹ አጋጣሚ እንደሆነለት ሁሉ የተጀማመሩ መቀራረቦች ጠላትን ሲያስበረግጉት በአደባባይ ተመልክተናል። ኢትዮጵያዊያን የትግሉ ማህበረሰብ አካላት የጠላትን የጥፋት ፍጥነትና የመፍትሔውን አስቸኳይነት በመገንዘብ ከነበረው ቀርፋፋ አካሄድ የተላቀቀ ትብብር በማድረግ ከቀጠናው የፀረ-ብልጽግና ኃይሎች ጋር በመቀናጀት እንዲሁም የተሳለጠ የጋራ ዲፕሎማሲ በመስራት ድላችንን በአጭር ጊዜ እናደርግ ዘንድ ብርቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በበኩላችን የህዝባችንንና የሀገራችንን ጥቅም ለሚያስከብር ትብብር ሁሌም ዝግጁነታችን እናረጋግጣለን። 4ኛ/ ለአማራ ሕዝብ የተከበርህው ህዝባችን ሆይ እኛ የገጠመንን ህዝባዊ አደጋ ለመቀልበስና መፃኢ ተስፋችንን በጎ ለማድረግ የአደጋው ባለቤት የሆነውን አረመኔያዊ አገዛዝ ጠላትን እየተናነቅን የምንገኝ መሆናችንን አቅፈህና ደግፈህ እያታገልህን ለምትገኘው ጀግና ህዝባችን ለማስረዳት የምንኳትን አይደለንም። ይልቁንስ የገጠመንን ውስብስብ አደጋ በቀላል መስዋእትነትና በአጠረ ጊዜ ለመቀልበስ ሠራዊታችንን ማጠናከር፣ በየዘርፉና በያለንበት ሁሉ የትግሉ አካል መሆንን ይጠይቃል። ራሳችንን ከጥፋት ለመከላከል ከጠላታችን የማጥፋት ርብርብ የላቀ ርብርብ ያስፈልጋል። 5ኛ/ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ የተከበርህው የታላቋ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ የዘመናት ተጨባጭ ህዝባዊ ፍላጎትህና ተስፋህ በውስን ቡድናዊ ፍላጎትና አንባገነናዊ እንዲሁም ሗላቀር የፖለቲካ ከባቢ ምክንያት አርቲስቱ እንዳለው ከዓለም ፊት እንዳልነበርህ ወደሗላ ቀርተህ በማይመጥንህና አዋራጅ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለህ። በፖለቲካ ወለድ የጋራ ራዕይ ማጣት፣ የእርስ በርስ መጠራጠርና መጠቃቃት፣ ርሀብ፣ መፈናቀልና መሰደድ፣ አፈናና ከባድ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲሁም ከቅርብና ሩቅ ዓለም አቀፍ መገለልና መናቅ ገጥሞሀል። በጥቅሉ ተጨባጭ ሀገራዊ የጋራ የህልውና አደጋ ውስጥ እንገኛለን። በመሆኑም ለዚህ ሁሉ ችግር ባለቤት የሆነውን አረመኔያዊ አገዛዝ ለማስወገድና በሁላችን ድርሻና መዋጮ ላይ ቆማ ለሁላችን የምትሆን ታላቅ አፍሪካዊትና ዓለም አቀፋዊት ሀገር ለመገንባት የጋራ የመስዋዕትነት አሻራ ለማስቀመጥ እንድትንቀሳቀስና የሚደረጉ የቅርብም ሆነ የሩቅ የፀረ-ብልጽግና ትግል ትብብሮችን በቀናነት በመረዳትና በመደገፍ የመከራችንን ጊዜ በማሳጠር ተስፋችንን ቅርብ እንድናደርግ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርብልሀለን። 6ኛ/ በጠላት አሰላለፍ ውስጥ ለምትገኙ አመራርና አባላት እናንተ በቀጥታ የጠላት አሰላለፍ ውስጥም ሆነ በባንዳነት የተሰለፋችሁ ዘመኑን ያልዋጃችሁ "ወገኖቻችን" ያደረሳችሁት ህዝባዊና ሀገራዊ በደል ከበቂ በላይ ሆኖ ሞልቶ የፈሰሰ መሆኑን ተረድታችሁ ከግለሰባዊ ጊዜያዊ ጥቅምና ፍላጎታችሁ በመላቀቅ ለህዝባዊና ሀገራዊ ጥቅምና ፍላጎቶቻችን ትገዙ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርብላችሗለን። ትግል ነውና በጠላት አሰላለፍ እስካላችሁ ድረስ መራራ እርምጃዎችን ወስደናል፤ ይህ ተጠናቅሮ የሚቀጥል ይሆናል። ሆኖም አሰላለፋችሁን ብታስተካክሉና ባሉን አማራጮች ሁሉ ብትቀላቀሉ የምህረት በራችን ሁሌም ክፍት መሆኑን እያሳወቅን ለራሳችሁም ሆነ ለቤተሰቦቻችሁ ብሎም ለህዝብና ሀገር የሚያኮራ ታሪክ ብቻም ሳይሆን የዘመን ግዳጅም ነውና ተጨማሪ ጊዜ እንደማታጠፉ ተስፋ እናደርጋለን። 7ኛ/ ለዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተቋማትና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአማራ ህዝብ ሁኔታ፤ የኢትዮጵያ ሁኔታ ለውስጣዊ ሰብዓዊ ቀውስ ብቻም ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድና ለመካከለኛው ምስራቅ ሁሉ የትርምስ ምንጭና አካል እየሆነ በመሆኑ የትርምሱ ምንጭ የአረመኔው አብይ አህመድ አገዛዝ እንዲያበቃና በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ቀንድና በመካከለኛው ምስራቅ የዴሞክራሲ አየር ነፍሶ ነፃነት፣ ሰላም፣ ፍትህና እኩልነት እንዲረጋገጥ በሰብዓዊነት ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች፣ በጦር ወንጀል፣ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተጨማለቀውን አረመኔያዊ አገዛዝ ባለመደገፍና በማውገዝ፣ ልዩ ልዩ አስገዳጅ የለውጥ ማዕቀቦችን በመጣልና የትግሉን ማህበረሰብ በመደገፍ ዓለም አቀፋዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እያሳሰብን ለመሰል ትብብር ቀናኢ መሆናችንን እናሳውቃለን። በተጨማሪም በየአውደ ውጊያው የሚማረኩ እና ወዶገብ የጠላት ሠራዊት አባላትና አመራሮችን ዓለምአቀፍ የጦር ህግን ተከትለን ለመያዝ እየተጋን ያለን መሆኑ ታውቆ ያደረ ጉዳይ ነው። በአሁኑ ወቅት ለረጅም ወራት የቆዩ እና አዳዲስ ምርኮኛና ወዶ ገቦች በስፋት በጊዜያዊ ማቆያ ካምፖቻችን የሚገኙ ሲሆን እንደ ቀይ መስቀል ያሉ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና ረጅዎች ፈጣን ሰብዓዊ ድጋፍ በማቅረብ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እና በተለይም ዓለምአቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር ምርኮኞችን እንደተለመደው ለአገዛዙ የአየር ጥቃትና መሰል የከፋ አደጋ ከመጋለጣቸው በፊት በፍጥነት እንዲረከበን ጥሪያችንን እናቀርባለን።በመጨረሻም በጉጉት የምትጠብቁት አማራዊ አንድነታችን የመጨረሻው ከፍታ ላይ የደረሰ ሲሆን ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ትልቁን ብስራት ይዘን እንወጣለን ። ድል ለአማራ ሕዝብ! አዲስ ትውልድ፤ አዲስ አስተሳሰብ፤ አዲስ ተስፋ!

ጥር 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የአደረጃጀት ማሻሻያ መጠናቀቅ በማስመልከት የተሰጠ መግለጫ `````````````````````````````````````````````````````````` የአማራ ሕዝብ እንዲሁም ሀገራችን ኢትዮጵያ ረጅም እና ግርማዊ የትናንት ታሪክ ባለቤት መሆናችንን በሙሉ ባለቤትነት የምናምንበት ጉዳይ ነው። ለረጅም ዘመናት በፈተናዎች መካከል ሁሉ የረጋ ስርዓት መገንባትም ተችሎ ነበር። ሆኖም ከሺህ ለሚበልጡ ዓመታት በተለይም ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ የስልጣኔ ግጭት በወለደው የትውልዶች ጦርነት በዘመናዊው ታሪካችን በቀጥታ አማራን ጠላት በማድረግ ባደረገው ዘመቻ በውስጣዊ ድክመቶች ታግዞ የሀገረ መንግስት ግንባታውን በማቋረጡ ሀገራችንን ላልተረጋጋና ለሚለዋወጥ ስርዓት ህዝባችንንም ለከፋ የመጥፋት (ህልውና) አደጋ አጋልጦታል። ይህንን በራሳችን ወገኖች ኢትዮጵያዊያን ባለቤትነትና ቅጥረኝነት የሚመራ ውስብስብ ሀገራዊ እና ህዝባዊ አደጋ ለመረዳትና ለመግባባት ብሎም መፍትሔ ለማበጀት ብዙ ማገዶ ፈጅቷል። የአማራ ሕዝብ ራሱን በመዘንጋትና ሀገሩን በማስቀደም እየኖረ በራሱም ሆነ በሀገሩ ላይ የተፈጠረውን ታላቅ ተቃርኖ በጊዜው ባለመረዳቱ ራሱን ያገኘው ሀገሩን ተነጥቆ ሀገር አልባ ሆኖ እንዲሁም መንግስት መር በሆነ የዘር ማጥፋት በከፋ የመጥፋት አደጋ ውስጥ ሆኖ ነው። በእርግጥ አማራው በመጥፋት ላይ ያለ ህዝብ ነው። ይህንን ህዝባዊ አደጋ ለመቀልበስ ብሎም ሁለንተናዊ ህዝባዊ ጥቅሞቹን ለማስከበርና የተቋረጠ የሀገር ግንባታውን ዘመኑን በሚመጥን መልኩ ለማደስ፣ የቀጠለና አዲስ ስልጣኔ ለመገንባት አዲስ አማራዊ አብዮት በማካሄድ ላይ እንገኛለን። የዚህ ህዝባዊ ቁጣ መነሻ ምክንያት የህልውና አደጋው ቢሆንም አደጋውን ከመቀልበስ ባሻገር ግዙፍ ራዕይ የቀነበበ ህዝባዊና ሀገራዊ እንዲሁም ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ መሻቶችን ቀርጿል። የህልውና ትግሉ ባለፉት ከ30 በላይ ወራት ራሱን በማጠናከርና ጠላትን በማዳከም እንዲሁም በዲፕሎማሲው መስክ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ ትኩረቱን አድርጎ ቆይቷል። በዚህም ሂደት ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ስልታዊ በሆነ መልኩ በመቀነስ አያሌ ግቦችን አሳክቷል። የጠላትንም ወረራ በመመከትና ሊያደርስ ያቀደውን የዘር ማጥፋት መጠን ከመቀነስ ባሻገር በወታደራዊ፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በመረጃና በዲፕሎማሲ ግንባሮች ሁሉ ማዳከም ተችሏል። በውጤቱም ጠላት አንዲት የእረፍት ቀን እንዳይኖረውና በአዲስ አበባም ድንጉጥ ሆኖ መጨረሻውን እንዲጠባበቅ ማድረግ ተችሏል፤ በዓለማችን ኃያላን መንግስታት ዘንድም የተናቀና የተጠላ እንዲሁም በሌላ ኃይል መቀየሩ አስፈላጊ መሆኑን የታመነበት ማድረግ ተችሏል። ይህንን ሁኔታ ለብዙ ወራት የገመገመውና በተግባርም በጥናትም ያረጋገጠው ቴዎድሮስ ዕዝ ስትራቴጅክ ሰነዶችን አዘጋጅቶ በ2017 ዓ.ም የክረምት ወራት ከአባልና አመራሩ እንዲሁም ከህዝቡና ደጋፊዎቹ ጋር የሁኔታ ትንተና እና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ መግባባት በመፍጠር ህዝባዊ ትግሉን ወደላቀ ድርጅታዊ ቁመና የሚያሸጋግርና ለህዝቡ ሁነኛ ዋስትና፣ ለሀገራችንም ተዓማኒ የቀጣዩ ስርዓት ኃይል መሆናችንን የሚያረጋግጥ መዋቅራዊ ማሻሻያ ተቋማዊና ስልታዊ በሆነ መልኩ ታቅዶ ተከናውኗል። የቴዎድሮስ ዕዝ ኃይል ከአካል እስከ ዕዝ እንደገና በመዋቅራዊ ማሻሻያ በ 05ኮር፣ በ15 እግረኛ ክፍለ ጦር፤ በ01 ኮማንዶ ክፍለ ጦር እና ሻለቆች የተደራጀ ሲሆን ግዙፍ ኮሮች፣ ደምሳሽ ክፍለጦሮችና ሰባሪ ሻለቃዎች ተደራጅተው ለቀጣይ ህዝባዊና ድርጅታዊ ግዳጅ ዝግጁ ከመሆናቸውም ባሻገር የጠላትን የቡድን፣ የነፍስ ወከፍና ሜካናይዝድ መሳሪያዎች መማረክ ጀምረዋል። በሂደቱም የህዝብ አስተዳድርን እና የኃይላችንን ኃላፊነትና ግንኙነት በግልፅ በመለየት የጊዜያዊ መንግስት አስተዳድር (ጊዜአኮ) ማደራጀት ተችሏል። ዕዙ መዋቅራዊ ማሻሻያውን በጥናቱ መሰረት በዓብይ ኮሚቴ የተመራው ሲሆን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የውሳኔ ሰጭነት ሚናውን በየሰዓቱ ያረጋገጠበት ውጤታማ ድርጅታዊ ስምሪት ሆኖ ተመዝግቧል። በዚህም በየኮር የስምሪት ቀጠናው መልሶ ማደራጀቱን የመራችሁ ልዑካንና መላው የድርጅታችን በየደረጃው ያላችሁ አመራሮችና አባላት ላሳያችሁት ቁርጠኛ ርብርብ የአደረጃጀት ማሻሻያው መሪ ዓብይ ኮሚቴ ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና ያቀርባል። ይህ ግዳጃችሁ በትግላችን ታሪክ ውስጥ በደማቅ የሚመዘገብና የሚዘከር ጭምር ነው። ምክንያቱም ግዳጁ ሁነኛ ድርጅታዊ የአባልና አመራር እንዲሁም የጊዜያዊ መንግስት ቁመና የፈጠረና ትግሉን ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሻገር ወደሚፈለገው ህዝባዊ ድል መስፈንጠሪያ መሠረት ነውና። በሂደቱ የተፈጠሩ ከለውጥ ተቋቋሚነት ጋር የሚገናኙ ቀላል የማይባሉ ፈተናዎች በመላው የድርጅታችን አባላትና አመራሮች ቁርጠኛ አቋም መከላከል የተቻለ ሲሆን በተገኘው ልምድና መረጃ የድርጅታዊ የሰው ኃይል ጥራት መረጋገጥና የአቋም ፍተሻ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን እናረጋግጣለን። የበላይ መዋቅሩ ፍተሻና ማሻሻያም የሚቀጥልና የምዕራፉ ዋነኛና ተጨማሪ ተግባራችን ነው። የዚህ የቁመና ማሻሻያ መርሃ-ግብር በስኬት መጠናቀቅን ተከትሎ የዘመኑ ህዝባዊ ግዳጃችንን ለመወጣት እጅግ የተሻለ ቁመና ላይ እንደምንገኝ ስናሳውቅ በከፍተኛ መተማመን ሲሆን ይህም ለወገንና ለወዳጆች የምስራች ሲሆን ለጠላት ደግሞ ሌላ የራስ ምታት መሆኑን እየተገነዘብን በበዚህም መሠረት የሚከተለውን ጥሪ እናስተላልፋለን፦ 1ኛ/ ለዕዛችን አባላትና አመራሮች ውድ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች የሆናችሁ የዕዙ አመራርና አባላት ጓዶቻችን፤ ይህ ትግል በታሪካችን ውስጥ ልዩ ቦታ ያለው ወሳኝ ጉዳይ ነው። ታላቁ ህዝብ በህልውና አደጋ ላይ ወድቆ መገኘቱ ውርደታችን ቢሆንም ይህንን አደጋ ለመቀልበስና ወደሌለኛው ህዝባዊ ግርማዊ ነገን ለማዋለድ በትናንቱ ክቡር ታሪካችን፣ በነባራዊው አደጋ ወለድ ውርደታችንና በመፃኢው ተስፋችን መካከል ህዝባዊና ሀገራዊ ጥፋትን ለማስቆም እንደሻማ እያበራንና እየቀለጥን ከራሳችን ይልቅ ህዝባችንንና ሀገራችንን ማስቀደማችን አኩሪ ዘላለማዊ ታሪካችን ነው። ይህ ታሪክ የአዲሱ አማራዊ ትውልድ የእያንዳንዱ ፋኖ የወል ታሪክ ነው። ጓዶች ሆይ ከከፈልነው የእስከዛሬ መስዋዕትነት የከፋ ሊገጥመን አይችልምና የምንከፍለውን ክቡር መስዋዕትነት ከህዝባዊ አደጋውና ተስፋችን አንፃር በመመዘን ከነበረን የበለጠ መበርታትና መጽናት ይገባናል። ትግላችን የበለጠ ወደድል አነስተኛ መስዋዕትነትና ጊዜ መስፈንጠር እንዲችል ለማስቻል የተሰራው መዋቅራዊ ማሻሻያ የሁላችንም ርብርብ የወለደው ስኬት ነውና በያለንበት ለቀጣዩ ግዙፍ ህዝባዊና ሀገራዊ ግዳጅ ሁሌም ወትሮ ዝግጁነታችንን እንድናረጋግጥ እናሳስባለን። 2ኛ/ ለደጋፊዎቻችን በቅርብም በሩቅም የምትገኙ ውድ ደጋፊዎቻችን የእስከዛሬው ልዩ ልዩ ድጋፋችሁ መሬት ላይ ያለንን ቁመና በማጎልበት አፈፃፀማችንን አሻሽሏል፣ የጠላትን አቅም አዳክሟል፣ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ተሰሚነትን በማሻሻል ላይ ይገኛል። ለዚህም ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና እናቀርባለን።

የማረጉ ተማረ ክፍለጦር ቃኝዎች 25 የጠላት ኃይል በመደምሰስና 13 በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፀፉ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ክንፍ የሆነው ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ቃኝዎች በላስታ ወረዳ ከብልባላ እስከ ይምርሃ ቀጠና ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ የብልፅግናን የዙፋን ወንበር ለማስጠበቅ እየተፍጨረጨረ የሚገኘውን የጁላን ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ወደ መጣበት እንዲመለስ አድርገውታል። መነሻውን ብልባላ ከተማ ያደረገው የብልፅግና ስርዓት አስጠባቂ መከላከያ ስራዊት በሶስት አቅጣጫ ማለትም በዞራ፣በአርባዕቱ እንሰሳ እና በአሞራ በር እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን በክንደ ነበልባሎቹ የማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ቃኝዎች ባደረጉት ትንቅንቅ ጥር 01 ቀን 2018 ዓ/ም ከአመሻሹ 12:00 እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት በፈጀ የተጠና ኦፕሬሽን 25 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ 13ቱን በማቁሰል አምስት ጥቁር ክላሽ፣1200 የክላሽ ተተኳሽ በመማረክ በጠላት ላይ ታላቅ ጀብዱ ፈፅመዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 02/2018 ዓ.ም

ሰበር ዜና! የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች በዳውንት ወረዳ በድሮን ታግዞ የተዋጋቸውን የፋሽስቱ ሰራዊት በርካታውን ሙትና ቁስለኛ በማድረግና ከአንድ ጓድ በላይ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች በጥላት ሰራዊት ላይ በተወሰደ ጠንካራ እርምጃ ከአካል እስከ ቁስ በብርሀኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጉዳት ማድረስ ተችሏል!! ጥር 1/2018 ዓ/ም አመሻሽ 12:00ሰዓት በተጀመረው አውደ ውጊያ  ዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ ድረስ ዘልቆ በመግባት የፋሽስቱን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ የአገዛዙ ስርዓት ያገፈገፋቸውን የቀድሞ የጥምር ሰራዊት አባሎችን ከአሃዳቸው አፍርሶ በማውጣት ወደ ፋኖ እድቀላቀሉ ተደርጓል። በፋሽስቱ ሰራዊት ምሽግ ውስጥ ቦብ በመመጨቅ በጉሪያቸው ለምስጥ ሲሳይ ሲደረጉ ቀሪዎቹ እግራቸውን ሰውተዋል።ፍየል ወድህ ቅዝምዝም የዳ ይሉ ዘንድ የፋሽስቱ ስርዓት ምሽቱን በድሮን ጥቃት ንፁሀኖችን ታርጌት በማድረግ የአለምን የጦርነት ህግ በማን አለብኝ በጣሰ አረመኒያዊ ተግባር ሲደበድብ ያደረ ሲሆን በሆዳቸው ለአብይ አህመድ ያደሩ የአማራ ተዎላጆች በበኩላቸው ምሽት ላይ ያለ ኦፔ የሞርተር ቅቡላ በማስወርወር በርካታ ንፁሀኖችንና ቤቶችን አውድመዋል። በርካታ የመከላከያ ሰራዊት፤ፖሊሶችና ሚኒሾችን ከአሃዳቸው አፍርሶ የማምጣቱ ኦፕሬሽን ሙሉ በሙሉ የተሳካ ሲሆን በኩርባ ከተማ ፖሊስ ጣቢያን፣ሞቃትን፣ኪዳነ ምህረት፣መነሀሪያ ድረስ ዘልቆ በመግባት በነዙህ በከተማው አካላቶች ላይ የነበረን የፋሽስቱን ሰራዊት በማፅዳት  ወደ ገብርኤል ተራራና ወደ አዳራሹ ተኮድኩዶ ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጭ መራዎጥ ውስጥ በማስገባት የብርሀኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊትን ማኮታኮት ተችሏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 2/2018 ዓ.ም

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ትምህርት ቤቶችን ሲያድስ አሮጌ ብላክቦርዶችን አስወግዷል:: እኛ አንስተን ሰልጥነንበታል:: ብላክቦርድ ተሸክመን ጫካ ለጫካ የተጓዝንባቸው ጊዜያት የሚያስታውሱን ሰራዊታችን ለመማ
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ትምህርት ቤቶችን ሲያድስ አሮጌ ብላክቦርዶችን አስወግዷል:: እኛ አንስተን ሰልጥነንበታል:: ብላክቦርድ ተሸክመን ጫካ ለጫካ የተጓዝንባቸው ጊዜያት የሚያስታውሱን ሰራዊታችን ለመማር እና ለማወቅ ከዚያም በቅቶ እና ነቅቶ ለመታገል ጉጉት እንዳለው ነው:: ይህ ማለት ኑ ተማሩ ሲባሉ አይ ሁሉም ነገር ገብቶን ነው ትግል የጀመርነው የሚሉ አላዋቂዎች የሉም ማለት አይደለም:: ይኖራሉ ግን እነሱን እዚያው ሰፈራቸው ውስጥ አባት አርበኛ አድርገን መድበናቸው ሌላውን ማለትም መማር እና የተሻለ ታጋይ መሆን የሚፈልገውን ይዘን 4 ኪሎ እንገባለን:: ይህ ትግል ሊሰምር የሚችለው በእውቀት እና እውነት ሲመራ እንጅ በመሰለኝና ደሳለኝ እንድሁም በደም ፍላት ስንጓዝ አይደለም:: በግለሰቦች ፍላጎትም ትግል አይመራም:: ድርጅት እና ህግ ያስፈልገናል:: ለዚህም ነው ስልጠና የሚጠቅመን:: ለመሰልጠን ዝግጁ ያልሆኑትን ኃላቀሮች እያራገፍን ወደፊት እንጓዛለን:: ይህ ቃላችን ነው!! ምኒልክ ዕዝ በእምዬ ምኒልክ ወኔ፣ አስተውሎት እና ጥበብ የሚመራ ድርጅት መሆኑን በተግባር እናሳያለን:: ከዋርካው ጋር ወደፊት!! ምኒልካዊነት ያሸንፋል!! ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!!

የብልፅግና ሰላይና ስራ አስኪያጅ በቁጥጥር ስር ዋሉ❗️❗️ ➰➰➰➰➰➰ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር ቀጠና። 👁 1ኛ➔ሎሚ አላምኔ ይባላል የሰዴ ወረዳ የደብረሰላም ቀበሌ ስራ አስኪያጅ ነው ከካቢኒ ጋር
+1
የብልፅግና ሰላይና ስራ አስኪያጅ በቁጥጥር ስር ዋሉ❗️❗️ ➰➰➰➰➰➰ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር ቀጠና። 👁 1ኛ➔ሎሚ አላምኔ ይባላል የሰዴ ወረዳ  የደብረሰላም ቀበሌ ስራ አስኪያጅ ነው ከካቢኒ ጋር ተጠርንፎ  ህዝባች ላይ ሲያደርሰው የነበረው ግፍ ተነግሮ አያልቅም። በበዓለ ገና ዕለት በቆንጆዎቹ  መዳፍ በቁጥጥር ስር ውሏል። ➔2ኛ➔ ያብባል ጋሻው ድጎ ፅዮን ቢቡኝ ወረዳ የመሸገው የአረመኔ ስብስብ ወደ ፋኖ ገብቶ እንዲሰለጥን   ያደረገው፤ እየሰለጠነ መረጃ እንዲሰጣቸው የተደረገና፤ ሰልጥኖ ሲነቃበት ወደ ጠላት ተቀላቅሎ  የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የፋኖዎችን እንቅስቃሴና ያሉበትን ለመመረጅ ዳግም ተልዕኮ ተሰጥቶት ተመሳስሎ ቀጠናው ድርስ እንደመጣ በተጠና ኦፕሬሽን በንስሮቹ  እጅ ወድቋል። ➺➺➺➺ጥር 02/2018 ዓ.ም ከአዲሱ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ አፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴወድስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ                   ።።።።።።።።።።።      በሳምንት ውስጥ የአማራን ትጥቅ አስፈታለሁ ብሎ ወደ ክልላችን የገባው አረመኔ ስርዓት ለሶስት አመት ያክል በአማራ ፋኖ ብርቱ ክንድ እየተቀጠቀጠ የሚደነፋበትና የሚኩራራበት ሰራዊት ስርዓቱ እንደማያዋጣው እየተረዳ ከሞት የተረፈው በየጊዜው እየከዳ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል። የቀረውም በገፍ እየተደመሰሰና እየተማረከ ሲሆን በገና ዋዜማ በጎጃም ስናን፣ በሸዋና በወሎ ቀጠናዎች የታየውም ይሄው ነው።      ስርዓቱ በአማራ ህዝብ ላይ ያልፈፀመው ወንጀል ያልሰራው ግፍ የለም፤ ጦርነቱ ከአማራ ምድር እንዳይወጣ ሆዳም የብልፅግና አመራርና የእናት ጡት ነካሽ ሚሊሻና አድማ ብተናን በተለያየ ጥቅማ ጥቅም እየደለለ አማራን በተለያየ መንገድ ከመጉዳት ባለፈ ወራሪው የብርሀኑ ጁላ ጦር በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሴት እህቶቻችንን እና እናቶቻችንን ደፍሯል፤ ጡት ቆርጧል፤ ብልትና ምላስ ቆርጧል አስከሬንም አቃጥሏል። በርካቶችንም ያለሀጢያታቸው አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት አድርሶባቸዋል።       በዚህ ያልረካው አማራ ጠሉ የአብይ አህመድ ቡድን በየሶስት ወሩ ግብር መሰብሰብ የጀመረ ሲሆን በክልሉ ውስጥ ያሉ መሬቶችን በሊዝ እየሸጠ ለጥይት መግዣ እያዋለና ለሚሊሻና አድማ ብተና መደለያ ለቤት መስሪያ ቦታ እንሰጣለን እያለ ስለሆነ ድርጅታችንም ሆነ የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር የአማራ ፋኖ ትግል ከጀመረበት ሐምሌ 27/2015 ዓ/ም ጀምሮ የሊዝ መሬት የገዛም ሆነ በባንዳነት ቦታ የተቀበለ እንዲሁም የባንዳ ቦታ የገዛ ሙሉ በሙሉ የሚወረስ መሆኑን ከዚህ ቀደም የገለፅን መሆኑን እያስታወስን ሰሞኑንም ሰላም አስከባሪ እያለ በከተማ ቦታ እየደለለ ምንም የማያውቁ ህፃናትና ወጣቶችን እያታለለና እያፈሰ ነው። በተጨማሪም አድማ ብተናና ሚሊሻ በማግበስበስ ላይ ይገኛል። ሁሉም ሊረዳው የሚገባው ጉዳይ ግን አይደለም የከተማ ቦታ ይቅርና ፎቅ እንኳ ቢሰጠው ሙሉ በሙሉ እንደሚወረስ በድጋሚ እንገልፃለን። ከዚህ ባለፈ ሰሞኑን የመምህራንን ደመወዝ በማገድ እያስፈራራ ወደ ገጠር ትምህርት ቤቶች በመላክ ወራሪ ሰራዊቱ በመድፍና በሞርተር ፣ በጀትትና በድሮን ካፈረሰውና የሰራዊት ካምፕ እያደረገ ካነደደው ትምህርት ቤት ላይ ፎቶ እየተነሱ ሲመጡ ደመወዛቸው እንዲለቀቅ እያደረገ የአማራ ፋኖ ትምህርት ቤቱን አውድሞታል በማለት እየለመነ ገንዘብ መሰብሰብ ፤ ፋኖ የለም ትምህርት አስጀምረናል ለማለት በትምህርትና ተማሪዎች ስም ለምኖ ለሚሊሻ ደመወዝ ለመክፈል እየተንተፋተፈ ይገኛል። በዚህ ድርጊት ላይ ተሳታፊ የሆናችሁ ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች እርምጃ እንደሚወሰድባችሁ አውቃችሁ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን። የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሀላፊ

የተግባር አማራው!! የአማራ ህዝብ ቁርጠኛው ጀኔራል ተፈራ ማሞ ክበርልኝ። የሚመክር፣የሚዘክር፣ለህልውናችን በፅናት ታግሎ መቆምን አስተምረህናል!! ሸማቂው ኮማንዶ/ የአማራይቱ ልጅ/ በሄድክበት ይቅናህ
የተግባር አማራው!! የአማራ ህዝብ ቁርጠኛው ጀኔራል ተፈራ ማሞ ክበርልኝ። የሚመክር፣የሚዘክር፣ለህልውናችን በፅናት ታግሎ መቆምን አስተምረህናል!! ሸማቂው ኮማንዶ/ የአማራይቱ ልጅ/ በሄድክበት ይቅናህ።

🔜የፋኖ መሰረታዊ መርሆዎች :- የፋኖነት መርሆች የመጀመሪያው ''ከአሳምነውነት'' ነው። 🔜)አሳምነዉነት የአማራ ፋኖ ለራሱ ለአማራ ሕዝብ ና ለኢትዮጵያ ቀርቶ ለሁሉም  የሚተርፍ ሀገር በቀል የፖለቲካ ና የመንግስት ተቋም ሆኖ ይቀጥላል ። ልክ እንደ እሰራኤል ሞሳድ የአማራ ና ኢትዮጵያ ግርማ ምልክት ሆኖ ይቀጥላል ። 1.አሳምነውነት :- .አሳምነውነት ምንድን ነው? "ጣና ዳር ለዳሩን ብዝቀዉ በአካፋ ጉርጣ ጉርጡ ወጥቶ አሳ ምነው ጠፋ?" የሚል ግጥም በማህበራዊ ሚዲያ ሳነብ የትርጉሙን ምንነቱን ሳስብ ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ሳይወለድ ስም ወጥቶ የቆያቸዉ ይመስላል። አሳምነው ፅጌ ገራሚ ሰው ነው ። በእርግጥ ሳይነገር ስም የወጣለት ለስሙም ለክበሩም ወሰን የሌለው ጌትነትና ለፈጣሪነት ባሕርይዉ ለሆነው በኋላም እኛን ለማዳን የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ ቀድሞ ስም የወጣለት መሆኑን የጀኔራል አባት መሪጌታ በመሆናቸው ያወጡለት ይመስለኛል። በነገራችን ላይ በስም የሚሰየሙ  ፍልስፍናዎች አሉ።በእኛ አገር የማውቀው አንዴ ብቻ ነው ። ይህም የአባ ገብረሃና ልጅ የሆኑት ተክላ ገብረሃና ተክለ አቋቋም የሚባል የቤተክርስቲያን ትምህርት አለ። አሳምነውነትን በግለሰብ ስም መርሕ መሰየም አዲስ አይደለም ።በተለይም አዉሮጳዉያኑ በደራሲ ስም ፍልስፍና መሰየም ይወዳሉ ። በሶቅራጥስ "ሶክራቲክ ክርክር "የሚባል አለ ። አሳምነውነት ማለት የአማራ ሕልውና ትግል የሜዳ መነፅር ነው ።የአማራ ሕዝብ የሕልውና ችግር ዉስጥ ነው ። ከዛሬ አምስት መቶ አመት በፊት የከፋ ችግር እንዲይገጥመን እንጠንቀቅ በማለት ቀጥታ የአማራን ወጣት ፋኖ እንድንሆን ነዉ ያደረገው ። በመጨረሻም እኔም ፋኖ ነኝ በማለቱ ለሞት በቅቷል ።አሳምነውነት መስፈንጠሪያ ነው ። አቶ ጌትነት ይርሳው የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ከ2012-2013 ዓ/ም ሲመራ እኔም ፋኖ ነኝ በማለቱ ከስልጣን ተባሮ ፋኖነት በሚስጢራዊዉ ጉባዓ የሚል መፅሐፍ ፅፏል። አሳምነውነት በዘህ መፅሐፍ ተገልጧል ። አሳምነዊነት ከኢህዴን ብአዴንነት ወጦ ፋኖነትጨየነፃነት ታጋይ መሸጋገሪያ ድልድይ ነው ። ስለዚህ አሳምነዉነት የሕልውና መታገያ ፍልስፍና ነው ። ከዚህ እሳቤ ዉልፍት ያለ ታጋይና መሪ መስመሩን የሳተ የአማራን ትግል የሚያጨናግፍ  ሾተላይ ስለሆነ ላለዉ ቀርቶ ወደ ፋኖ የሚገቡት የብአዴን ሆነ የብልፅግና ወታደራዊ ና የፖለቲካ መሪዎች የአሳምነዉነት ፍልስፍና ካልተቀበሉ መቀላቀል የለባቸውም ። ይሕ መርህ መፃኢ የፖለቲካ ስብራትን የአማራን ብልም የኢትዮጵን እጣ ፈንታን ተንብዮ ለሚመጣዉ ችግር ራስን የማዘጋጀት የፖለቲካ ትትንቢታዊ እዉቀትነዉ፡፡ በዚህ ፍልስፍና መመራት የፋኖነት መርህ መሆኑን አዉቀን የአማራ ችግር ትርክት ወለድ መዋቅር ሰራሽ በመሆኑ ጅኔራሉ ከ500 አመት በፊት ከነበረዉ የከፋ ነዉ ያሉት እዉነት ዉ ያን ጊዜ የኦነግ ወራሪዎች የሚጠቀሙት መሳሪያ ሹል እንጨትና ድንጋይ ነበር።  አሁን ባንክ ታንክ እስከ ድሮን የታጠቁ በመሆናቸዉ በዚህ ልክ መዘጋጀት ይጠይቃል። በመሰረቱ ብልፅግና ሲሸነፍ በመጨረሻ በዘር ጭፍጨፋ ለመምጣት አስቦ የኛን የፖለቲካ መሃይም ዳንኤል ክብረትንና ባለሐብቱን ይዞ ሂዶ ሩዋንዳን ጎብኝቶ የተመለሰዉ አማራዎችን የወሰዳቸዉ በሁለት ምክንያት ነዉ ፡፡ 1ኛ).ፖለቲካዉ ባልባዉ አማራ ለመመጠርጠር ሲሆን 2ኛ).ከዘር ማጥፋት ወንጀል አማራዎም ነበሩበት ለማስባል እና የጥፋት ታሪኩ አካል የማድረግ የታቀደ ሴራ ነዉ፡፡ ስለዚህ አሳምነዉት ወትሮ ዝግጁነት ነዉ፡፡ ከነፃነት አስፋው ቦጋለ መፅሐፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ🙏