ch
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
3 721
订阅者
+4524 小时
+1767 天
+1 15530 天
帖子存档
#ጠላት_በደፈጣ_ተመታ‼️ በዛሬዉ እለት በቀን 01/06/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ እንዲሁም 1ኛ ሻለቃ ከፍኖተ ሰላ
#ጠላት_በደፈጣ_ተመታ‼️ በዛሬዉ እለት በቀን 01/06/2018 ዓ.ም  የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ እንዲሁም 1ኛ ሻለቃ ከፍኖተ ሰላም ወደ ጂጋ ሆዳንሽ ከተማ ሲገባ የነበረን ሃይል ከንጋቱ  12:00 ሰዓት አካባቢ በወሰዱት እርምጃ በርካታ የጠላትን ሀይልን መደምሰስ እና ማቁሰል ተችሏል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!         ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ 77ተኛ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ 01/ዐ6/2018 ዓ.ም

የደጋው መብረቅ ኮር ቀኛዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር ለሶስተኛ ዙር በርካታ እግረኛ ፋኖዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመረቁ‼️ አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር ለበርካታ ወራቶች ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን ፋኖዎች የካቲት 1/2018 ዓ/ም የኮሩ አመራሮች በተገኙበት መድረክ ላይ አስመርቋል! ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር በርካታ እግረኛ ፋኖዎችን ለሶስተኛ ዙር ያስመረቀ ሲሆን በዚህ የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ የደጋው መብረቅ ኮር የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አርበኛ ብርሃን አረጋ በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የእንኳን ደሳላችሁ መልክት ያስተላለፉ ሲሆን "የአማራ ህዝብ የብረት አጥር ናችሁ!! የአማራን ህዝብ ጥላት የሚያጠቃው በእናተ አስከሬን ላይ ተረማምዶ ነው። ስለዚህ እናተ የአማራ ህዝብ መታፈሪያና መከበሪያ የብረት አጥር ናችሁ!" በማለት ለተመራቂዎች መልክት ያስተላለፈ ሲሆን:: የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አርበኛ መኩሪያ አጋዡ(መምህሩ) "እናተ አማራ ናችሁ! በአማራዊ የሞራል ልዕልና ቁማችሁ የተገኛችሁ!" በማለት ለተመራቂዎች መልክት አስተላልፈዋል። የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ አርበኛ በለጠ መኩሪያው በበኩላቸው ለተመራቂ ፋኖዎች የአማራን ህዝብ ነፃ የማውጣት ሀላፊነት የዚህ ተመራቂ ጭምር ነው ሲሉ ለተመራቂዎች አሳስበዋል። በዚሁ የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ የአሰልጣኞች ምስጋናና እየፈፀሙት ላለው ህያው ገድል የሽልማት ፕሮግራም የተበረከተ ሲሆን፤ይህ የአሰልጣኞች ማነሻሻ የምስጋና እውቅና ለቀጣይ የተልዕኮ መሰላል ይኖን ዘንድ ታስቦም የተደረገ ነው። እየተዋጋን እንሰለጥናለን እየሰለጠን እንዋጋለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ እዝ የካቲት 1/2018 ዓ.ም 01/ዐ6/2018 ዓ.ም

ሲነግሩት ያልሰማን እያየ ቅበረው ✊ ደጋ ዳሞት - ያስተፋል ሀሞት ከፈረስ ቤት ከተማ ከሌሊቱ 11:20 ጀምሮ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ደጋ ዳሞት ሻለቃን ለመክበብ ቢሞክርም
+1
ሲነግሩት ያልሰማን እያየ ቅበረው ✊ ደጋ ዳሞት - ያስተፋል ሀሞት ከፈረስ ቤት ከተማ ከሌሊቱ 11:20 ጀምሮ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ደጋ ዳሞት ሻለቃን ለመክበብ ቢሞክርም በክንደ ነበልባሎች ቀምሶ ሬሳውን እንኳን ሊቀብር ቀርቶ ቁስለኞችን ትቶ  ከቆፈረው ጉድጓድ ገብቷል። ቀጣይ በዜና ደግሞ የአሳምነው አናብስቶች ድልን እንመለሳለን እስከዛ ሸርና ጆይን በማድርግ አጋርነታችሁን አሳዩን

አገዛዙ የግንኙነት መስመሮችን ዘግቶ ሲቪሊያንን በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛል የካቲት 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከአፋብን የተሰጠ መግለጫ ትላልቅ ከተሞችን የሚያገናኙ አውራ መንገዶችን በመዝጋት በህዝቡ ላይ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ሲያደርስ የቆየው የብልፅግና አገዛዝ በከባድ መሳሪያወች ሲቪሊያንን በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛል። ከጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት በጀኔራል አድማሱ አለሙ እና በጀኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ የሚመራው 11ኛ ዕዝ እና ቀጠናው ላይ የተሰማራው ሪፐብሊካን ጋርድ ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌወች ድሮን፣ ቢኤም እና መድፍን በመጠቀም ከ 100 (አንድ መቶ) በላይ ንፁሃንን በግፍ ጨፍጭፏል፤ ከአርባ በላይ መኖሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ አውድሟል፤ በርካታ ቁጥር ያላቸው የቤት እንስሳትን ገድሏል።በዚህ ጥቃት የአንድ ቤተሰብ ስድስት አባላትም በቤታቸው ባሉበት ተጨፍጭፈዋል። በተመሳሳይ ግዜ ውስጥ በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳም የአገዛዙ ሰራዊት ከኦሮምያ ልዩ ዞን ታጣቂወች ጋር በመቀናጀት በፈፀመው ጭፍጨፋ በበርካታ ሲቪሊያን ላይ የከባድ መሳሪያ ድብደባ በማድረግ ከ20 በላይ ንፁሃንን ገድሏል፤ በርካታ ቤቶችን አውድሟል፤  እንዲሁም የቤት እንስሳትን ዘርፏል። በምስራቅ ጎጃም ሸበል በረንታ ወረዳም ምንም አይነት ውጊያ በሌለበት የአርሶ አደር መንደሮችን በመድፍ ደብድቧል። በመሆኑም ይህ አረመኔ አገዛዝ እንደ ህዝብ ያወጀብንን የዘር ማጥፋት ጦርነት መመከት ብሎም መቀልበስ አማራጭ የሌለው የትውልዱ ግዴታ በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ መላው ህዝባችን ለህልውናው በጋራ እንዲታገል ጥሪ እናቀርባለን። በተጨማሪም የስልክ እና የኢንተርኔት ግንኙነቶችን በሰሜን ሸዋ፣ በምስራቅ ጎጃም እና በደቡብ ወሎ አዋሳኝ ቦታወች ሙሉ በሙሉ በመዝጋት አረመኔው አገዛዝ በንፁሃን ላይ ያነጣጠሩ ተመሳሳይ ወንጀሎችን በመፈፀም ላይ ስለሆነ መሠል ጥቃቶችን ለመከላከል ህዝቡ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን። አገዛዙ የዓለም አቀፍ የጦርነት ህግ መሰረታዊያን የሆነውን ንፁሃንን ከጥቃት የመጠበቅ ግዴታን በመተላለፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ በመሆኑ የአፍሪካ ህብረት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት፣ የተባበሩት መንግስታት እንዲሁም በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ዘር ማጥፋት የሚገዳችሁ እና ጉዳዩ የሚመለከታችሁ አካላት ሁሉ ይህንን የጦር ወንጀል በመቃወም የሰብአዊነት ግዴታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ

በደቡብ አማራ ሸዋ ደራ አካባቢ የአረመኔው አብይ አህመድ መከላከያ ኃይሎች እና የሽመልሽ አብዲሳ ታጣቂ ኦነግ ሸኔ ቡድን በህዝባችን ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ሰብዓዊ ጫና እያደረሰ ይገኛል!! በመላው ሸዋ ፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአብይ አህመድ ተስፋፊ ሰራዊት እንደለመደው በደራ አማራ ማህበረሰብ ላይ መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ፣ የማህበራዊ እና ሰብዓዊ ጫናዎችን እያደረሰ ይገኛል። በመሆኑም የአረመኔው መከላከያ ሰራዊት ከፋኖ ጋር በሚያደርገው ውጊያ በገጠመው ሽንፈት ምክንያት ህዝቡን ኢላማ ያደረጉ እርምጃዎችን እየወሰደ ​ህዝቡ መሰረታዊ የግብይት ስራን ከገጠር ወደ ከተማ ወይም ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመገደባቸው ህዝቡ መሰረተ ልማቶችን እና የፋብሪካ ምርቶችን መጠቀም እንዳይችል ተደርጓል። የአርሶ አደሩን ከብቶች የመውሰድ እና የማረድ ድርጊት እየፈጸመ ቀጥታ የሽፍትነት ስራ እየሰራ ይገኛል። ​ ይህ እርምጃ የታቀደ አማራውን በኢኮኖሚ እና በሰብዓዊ ዘርፎች ላይ ማዳከም ፕሮጀክት አካል በመሆኑ አላማውም ህዝቡን ከፋኖ እና ከትግሉ በማቆራረጥ እና በችግር እንዲሰለች እና እንዲፈናቀል በማድረግ የአካባቢውን መሬት ለመቆጣጠር የታለመ ሲሆን ​የአብይ አህመድ እና የኦነግ ሸኔ የጋራ ግብ፧ ​በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ሸኔ ቡድንም በተመሳሳይ በንጹሃን ላይ አፈና እና ግድያ እየፈጸመ ከመሆኑም በላይ ቡድኑ በመኪና የሚንቀሳቀሱ መንገደኞችን በማገት እስከ 500 ሺህ ብር ገንዘብ ግዴታ እየተቀበለ ይገኛል። በአብይ አህመድ ጡት ቆራጩ መከላከያ እና በሸኔ የሚፈጸሙት ተግባራት ተመሳሳይነት ያላቸውና ሁለቱም አካላት ህዝብን የማጥፋት እና የማሸበር የጋራ ግብ ያላቸው ኃይሎችም ናቸው።​የአብይ አህመድ ስርዓት ተስፋ በመቁረጡ እና መፈራረሱን የሚያሳይ ከመሆኑም ባሻገር ​በአሁኑ ወቅት በሸዋ ደራ አካባቢ ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ሲሆን፣ ማህበረሰቡ በአስቸጋሪ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ እንዲገባ እያደርገ ይገኛል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ ይካተት 01/06/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና፣ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር የሰባት ልሰባ ክፍለ ጦር አናብስቶች፤ ዛሬ በጥዋቱ የአረመኔው አብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂና የብልፅግና 'ጡት ቆራጭ'
+1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና፣ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር የሰባት ልሰባ ክፍለ ጦር አናብስቶች፤ ዛሬ በጥዋቱ የአረመኔው አብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂና የብልፅግና 'ጡት ቆራጭ' መከላከያ ኃይልን መንገድ እየመራ ህዝባችንን ሲያሳድድ የነበረውን የሚኒሻ ኃይል በመምታት፣ የፈርዶሃ ቀበሌን በወገን ክንደ-ብርቱ ቁጥጥር ስር አስገብተዋል። ዝርዘር መረጃው እንመለስ ትኩስና ዕለታዊ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይወዳጁን!!

ቡም ቡም እናታለም ሽዋ አለ ነገር ዘንድሮ አለ ነገር።
ቡም ቡም እናታለም ሽዋ አለ ነገር ዘንድሮ አለ ነገር።

አሸባሪው የብልፅግና ስርዓት ሀገሪቱ ያላትን አራዊት ሰራዊት በመጠቅለል ሸዋ ገብቷል። ኔትወርክ የጠፋባቸው የሸዋ ቀጠናዎች። 1ኛ. በቡልጋ * በረኸት ወረዳ *ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ * አሳግርት ወረዳ
አሸባሪው የብልፅግና ስርዓት ሀገሪቱ ያላትን አራዊት ሰራዊት በመጠቅለል ሸዋ ገብቷል። ኔትወርክ የጠፋባቸው የሸዋ ቀጠናዎች።     1ኛ. በቡልጋ     * በረኸት ወረዳ      *ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ     * አሳግርት ወረዳ     * ሀገረማርያም ከሰም ወረዳ ሙሉ ለሙሉ ኔትወርክ ተቋርጧል        2ኛ.ተጉለት       * አንኮበር ወረዳ በከፊል           * መንዝ ቀጠና       * መንዝ ማማ ምድር በከፊል ኔትወርክ የተቋረጠ          4ኛ.ይፋት   *  ጣርማበር ወረዳ በከፊል ኔትወርክ የተቋረጠ * ቀወት ወረዳ ሙሉለሙሉ የተቋረጠ * ኤፍራታና ግድም ወረዳ በከፊል የተቋረጠ    ጅሩና መርሃቤቴ     *መርሃቤቴ ወረዳ በከፊል   *ደራ ወረዳ በከፊል የተቋረጠ ሲሆን በዚህ ሰዓትም በከፍተኛ ደረጃ ግፍና በደል በህዝባችን ላይ እየተፈፀመ ይገኛል። ዶ/ር አብደላ እንድሪስ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

አገዛዙ የደቡብ አማራ ሸዋ ቀጠናን ጨምሮ በከፊል የምዕራብ አማራ ጎጃም ቀጠና እና የምስራቅ አማራ ወሎ ቤተአማራ ቀጠና ምዕራብ ወረዳዎች ላይ የኔትዎርክና የመብራት አገልግሎት አቋርጦ በተዋጊ ሄሊኮፍተርና ድሮን የታገዘ ውጊያ እያካሄደ ነው። በተመሣሣይ፡ በሦስቱም ቀጠናዎች የሚገኙ ፋኖዎች "አትችልም እንጂ ብትች፡ እንኳን ኔትዎርክ እና መብራት አጥፍቶ መግጠም ቀርቶ፡ ሰማይ ላይ ያለችውን ፀሐይንም ብርሃኗን አጥፍተህ ብትገጥመን ድል እንደሰማይ እርቆህ ይቀራል እንጂ እንደእሳት የሚፋጅ ክንዳችን ልትገዳደር አትችልም" የሚል ከብረት የጠነከረ ምላሽ ሰጥተውታል። አሁን በሸዋ የተሰማሩ፡ ከዚህ ቀደም ስምሪታቸው በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ የነበሩ ተዋጊ የጦር ሄሊኮፍተሮችና መድፎች ከወደ ፋኖ የሚሰነዘረውን የፀረ ማጥቃት እርምጃ ሊመክቱ አልቻሉም። አገዛዙ ሀገሪቱን ተጨማሪ እዳ ውስጥ ዘፍቆ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ከቻይና እንዲሁም ከሌሎች ሀገሮች በውድ ዋጋ የገዛቸው ድሮኖች የፋኖን ግስጋሴ ሊያስቆሙት አልቻሉም። በደቡብ አማራ ሸዋ ቀጠና እና በምስራቅ አማራ ወሎ ቤተአማራ ቀጠና ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ 23 ጊዜ ሄሊኮፍተሮች አርፈው ቁስለኛ ወታደራዊ አዛዦችና ወታደሮችን ጭነው ወደ አዲስ አበባ በረራ ማድረጋቸውን ጣቢያችን ከወታደራዊ ምንጮቹ ለማረጋገጥ ችሏል። መርጡ ለማርያም እና አካባቢውን ጨምሮ ሸበል በረንታ፣ የደጀንና የባሶ ሊበን ገጠራማው አካባቢዎች፣ መርሐቤቴ፣ ይፋት፣ መንዝ፣ ወግዲ እና መካነሰላም ዙሪያ የሚገኙ ገጠራማ አከባቢዎች የስልክ ጥሪ፣ የአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS) እና የኢንተርኔት እንዲሁም የመብራት አገልግሎት ሙሉ በሙሉና በከፊል ከተቋረጠባቸው አካባቢዎች መካከልም ዋነኞቹ ናቸው። ከመርጦ ለማርያም መካነሰላም የሚያገናኘው አውራ መንገድ ተዘግቷል። ከመርጦ ለማርያም መካነሰላም የሚያገናኘው መስመር ከወራት መዘጋት በኋላ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ ተዘግቶ በቀጠናው ከባድ የሆነ ውጊያ እየተካሄደ ነው። በሸዋ የስልክና የኢንተርኔት እንዲሁም የመብራት አገልግሎት አጥፍቶ በድሮንና በተዋጊ ሄሊኮፍተር ታግዞ ውጊያ የከፈተው የአገዛዙ ኃይል በሸዋየዎች ክንድ ተመክቶ አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ ይገኛል። በአየር ኃይልና በምድር ሜካናይዝድ መሣሪያዎች ሽፋን ታግዞ ከእግረኛ ሰራዊት እስከ አየርወለድ ኮማንዶና ሪፐብሊካን ጋርድ አባላት በአድማ ብተናና ሚኒሻ መንገድ መሪነት በቀጠናው አስገብቶ የነበረው አገዛዙ፡ ከወደፋኖ በደረሰበት አፀፋዊ እርምጃ ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ እንዲሁም ሞራላዊና ፖለቲካዊ ኪሳራ ተከናንቧል። በተጨማሪም የሚተማመንበትን ኃይል አሰልፎ ስንዝር የድል እርምጃ መራመድ ባለመቻሉም ከባድ የሆነ የፕሮፖጋንዳ ኪሳራም ደርሶበታል። በቀጠናው የተሰለፉት የፋኖ አባላቱ በወሰዱት የፀረ ሽምቅ፣ የፀረ ማጥቃትና ስኬታማ የፀረ መከላከል እርምጃ እንዲሁም ውጤታማ  የመልሶ ማጥቃት እርምጃ፡ ታሪክ በወርቅ ቀለሙ የሚከትበው፣ አዲሱ ትውልድ የሚመካበትን ድል መቀዳጀታቸውን ነው ጣቢያችኔ ለማረጋገጥ የቻለው። አገዛዙ ከጥር 26/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥር 30/2018 ዓ/ም ድረስ በሸዋ ቀጠና ብቻ ከ12 በላይ ሄሊኮፍተር አሳርፎ ካፍ እስከገደፋቸው ሙሉ ቁስለኛ ወታደር ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል አስገብቷል። ፀረ አማራው የብልፅግና አገዛዙ በፋኖ እርሳስ ግንባራቸውን ተነድለው የሚያልቁበትን ወታደሮች ለመተካት ተጨማሪ ኃይል በቀጠናው እያስገባ ይገኛል። ከወደፋኖ ያጋጠመውን የመከላከልና የመልሶ ማጥቃት እርምጃን መቋቋም አባይን በማንኪያ ጨልፎ እንደማድረቅ የሆነበት አገዛዙ፡ "ማንን ታሸንፋለህ ቢሉት ሄዶ በርሮ ሚስቱን ደበደበ" እንዳሉት አበው "የእናንተ ልጆች ናቸው የመቱኝ" በሚል ንፁኋን ላይ እልቂት ፈፅሟል። በዚህም በርካቶች ተረሽነዋል፡በርካቶች ደግሞ ታግተው ደብዛቸው ጠፍቷል።  የንፁኋን መኖሪያ ቤቶችም በድሮንና በተዋጊ ሄሊኮፍተሮች እንዲሁም በመድፍ እየተደበደቡ ነው። በልዩ ዞኑ ውስጥ የሚገኙ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር ተቀናጅተው በከባድ መሣሪያ ሽፋን በመታገዝ በንፁኋን ላይ እልቂት እየፈፀሙ መሆኑን ጣቢያችን  ለማረጋገጥ ችሏል። በኤፍራታና ግድም ወረዳ ዘምቦ ቀበሌ ልዩ ቦታው ግምብ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ 12 አርሶ አደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ድርጊቱ የተፈፀመው ጥር 28/2018 ዓ/ም ሲሆን፡ ከተገደሉት በተጨማሪ ህፃናትና ነፍሰጡር ሴቶች እንዲሁም አረጋዊያንን ጨምሮ ከ45 በላይ ንፁኋኖች ታፍነው ተወስደው ደብዛቸው መጥፋቱን ጣቢያችን ለማረጋገጥ ችሏል። ከወደ ፋኖ በሚወሰድበት እርምጃ ከባድ ኪሳራን የተከናነበው አገዛዙ፡ በቀጠናው የኔትዎርክና የመብራት አገልግሎችን በማቋረጥ ከልዩ ዞኑ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችን በማስገባት ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር አቀናጅቶ በንፁኋን ላይ የበቀል ጭፍጨፋ እየፈፀመ ይገኛል። በተመሣሣይ በምስራቅ አማራ ወሎ ቤተ አማራ ቀጠና ምዕራባማው ክፍል ላይ 4ኛ ቀኑ ያስቆጠረ ተጋድሎ እየተደረገ ሲሆን ከወግዲ በተጨማሪ የፌደራል መስመሩን ተከትሎ በመካነሰላምና በመርጦ ለማርያም መካከል የሚገኙ አከባቢዎች ላይ ከባድ ትጋድሎ እየተደረገ ይገኛል። በምዕራብ አማራ ጎጃም ቀጠና ሸበል በረንታን ጨምሮ ምስራቃዊው አከባቢ ላይ እንዲሁ ከባድ ተጋድሎ እየተደረገ ሲሆን፡ አገዛዙ ከወደ ፋኖ የሚደርስበትን እርምጃ ለመቋቋም ከተዋጊ ሄሊኮፍተሮች ጀምሮ የድሮንና የሌሎች ከባባድ መሣሪያዎች ሽፋን በመጠቀም ለማጥቃት ቢሞክርም ነገር ግን የፋኖ ክንድ የሚቀመስ አልሆነለትም። ወግዲን ጨምሮ በሁለቱ ቀጠና አጎራባች አከባቢዎች ላይ ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ እየተደረገ ባለው ተጋድሎ ከ11 ጊዜ በላይ ሄሊኮፍተሮች አርፈው ቁስለኛ ሙሉ ጭነው ወደ አዲስ አበባ ወስደዋል። በቀናው ፋኖ እየወሰደው የሚገኘውን የፀረ መከላከል፣ የፀረ ሽምቅና የፀረ ማጥቃት እርምጃን መቋቋም ያልቻለው የአገዛዙ ኃይል፡ "ሁሉም አማራፋኖ ነው" በሚል በድሮንና በመድፍ ንፁኋንን እየጨፈጨፈ ይገኛል። በወግዲ ወረዳ ከ35 በላይ ንፁኃኖች በከባድ መሳሪያ መጨፍጨፋቸውን ጣቢያችን በጥር 29/2018 ዓ/ም ዜና እወጃው መዘገቡ ይታወቃል። በወግዲ ወረዳ ጎረንጅ ቀበሌ ብቻ ስድስት የአንድ ቤተሰብ አባላት በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ በተመሳሳይ በዚሁ በጎረንጅ 014 ቀበሌ አንድ መኖሪያ ቤት ላይ ባረፈ ከባድ መሳሪያ አባት ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ እናትና ልጅ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል:: አገዛዙ በዚኸው ወረዳ በአንዲት መንደር ላይ ብቻ ከ54 ጊዜ በላይ ከባድ መሳሪያ አስወንጭፎ ከባድ ውድመት አድርሷል:: ይኸው ድርጊት ዛሬም ተባብሶ ቀጥሏል።

ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የድርጅቱን መመስረት በተመለከተ እና ስለ አማራ የህልውና ትግል ወቅታዊ ሁኔታወች ለዓለም አቀፍ ሚዲያወች ማብራሪያ ሰጠ። የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ባዘጋጀው የሚዲያ ብሪፊንግ መድረክ የአማራ የህልውና ትግል ጠቅላላ ሁኔታ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስረታ፣ የጦርነቱ አጀማመር፣ ትግሉ ያለበት ነባራዊ ሁኔታ፣ ስለ ሰብአዊ መብት አያያዝ፣ ስለ ምርኮኞች እና የጦርነት ህግ አተገባበር፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአማራን የህልዉና ትግሉን በመረዳት ረገድ ስላለው ክፍተት እና ሌሎችም ጉዳዮች ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ቀርቧል። በተጨማሪም ከጋዜጠኞቹ ለቀረቡት ጥያቄወች በመምሪያ ኃላፊው በኩል ማብራሪያ እና ምላሽ ቀርቧል። በሚዲያ ብሪፊንግ መድረኩ ላይ ሮይተርስ፣ ኒውዮርክ-ታይምስ፣ ፍራንስ-24፣ አሶሼትድ-ፕሬስ፣ አልጃዚራን ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያወችን የወከሉ እና ሌሎች የውጭ ሚድያ የግል ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል።   በርካታ አለም አቀፍ ጋዜጠኞች በተገኙበት የተደረገው ይህ የሚዲያ ብሪፊንግ ስራ በአንፃራዊነት ሲታይ ዓለም አቀፍ ትኩረት የተነፈገውን የፋኖ ትግል እና የአማራ የህልዉና ተጋድሎ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል። ድርጅታን መሰል ተግባራትን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

🔥#ሸዋ💪 የአብይ አህምድና የአረጋ ከበደ ጥምር ጦር ኔትወርክ አጥፍቶ ከእግረኛ እስከ ሜካናይዝ ፣ ከክላሽ እስከ ዲሽቃ ፣ ከሞርተር እስከ ድሮን ከሚሊሻ እስከ ኮማንዶ ቢያሰልፍም የምኒልክ ቀዬ ሸዋ
🔥#ሸዋ💪 የአብይ አህምድና የአረጋ ከበደ ጥምር ጦር ኔትወርክ አጥፍቶ  ከእግረኛ እስከ ሜካናይዝ ፣ ከክላሽ እስከ ዲሽቃ ፣ ከሞርተር እስከ ድሮን ከሚሊሻ እስከ ኮማንዶ ቢያሰልፍም የምኒልክ ቀዬ ሸዋ ረመጥ ሆኖበታል። አፋብን አሳምነው ዕዝና አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ጠላትን አይቀጡ ቅጣት እየቀጡ ይገኛሉ። ምንም ኃይል ቢያሰልፍ ወይ ንቅንቅ ሸዋ💪 የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው አገዛዝ ንፁሀን ላይ ግድያና ከባድ መሳሪያ ጭፍጨፋ እያደረገ ቢሆንም አናብስቶች የበላይነትን ወስደው ጠላታችንን እየቀበሩት እንደሚገኙ ለንስር አማራ አረጋግጠዋል💪 #በድል_ትወጡታላችሁ💪 30/ዐ5/2018 ዓ.ም

በእጁ ቢፅፍበት ሀገር የለወጠ፣ በእጁ ቢተኩስም ጠላት ያናወጠ ተንጎራደደበት ዛሬም አባታለም ሸዋ፣ ጥንትም በጁ አይደል ወይ የነፃነት ፅዋ አባታለም ሸዋ ✊ 🎼🎼🎼 ❤Dawit fano አፋብን የመኖ
በእጁ ቢፅፍበት ሀገር የለወጠ፣ በእጁ ቢተኩስም ጠላት ያናወጠ ተንጎራደደበት ዛሬም አባታለም ሸዋ፣ ጥንትም በጁ አይደል ወይ የነፃነት ፅዋ አባታለም ሸዋ ✊ 🎼🎼🎼 ❤Dawit fano አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

በግራ ጎኑ መዝሙረ ዳዊት በቀኝ ጎኑ ክላሽ  አንግቦ  የሚታገለው   ጀግና ማን ነው ? በቀድሞው ወገራ አውራጃ አምባጊወርጊስ ወረዳ በገላ ጠብጠብታ ሮቢት ቀበሌ ልዩ ስሟ ግራርጌ ማሪያም ከምትባል ቦታ  ከአባታቸው አቶ መክብብ ተከስተ እና ከእናታቸው ወ/ሮ እማዋይ ተስፋ  ሀምሌ 1 ቀን 1967 ዓ/ም  ስሙር የተባለ መልከ መልካም ልጅ የክረምቱን ጭጋግና ጉም ገልጦ ከማህፀን ተወለደ። አርበኛ ሊቀ ትጉሀን ስሙር መክብብ እድሜው ዘጠኝ አመት  እስኪሞላው ድረስ ከአርሶ አደር ቤተሰብ የተወለደ በመሆኑ ለቤተሰቦቹ ከብት እና ፍየል እያገደ እንጨትና ኩበት ለማገዶ እያቀረበ ሲያገለግል ቆይቷል። አባታቸው አቶ መክብብ ለቤተ_ ክርስቲያን ልዩ ትኩረትና ፍቅር ስለነበራቸው የዘጠኝ አመት ልጃቸውን የቤተ ክህነት ትምህርት እንዲማር ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አደራ ሰጡት እሱም  ትምህርቱን በስማም፣ ወወልድ ፣ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ ፈጣሪውን በማወቅና በማክበር  በትንሽ እድሜው  ከውሾች ንክሻና ጩኸት እራሱን እየተከላከለ  በአኮፋዳው ቁራሽ እንጀራ  እየለመነ ትምህርቱን ከቤተሰብ ስስትና ናፍቆት  ጋር እየታገለ ቀጠለ ። አርበኛ ሊቀ ትጉሀን ስሙር መክብብ በጥንታዊቷ አይባ ኪዳነ ምህረት ፣ሚካኤል ደብር ፣ደንቀዝ ዛንተራ እየሱስ በነበሩ መምህራን ወንበሮች እየተዘዋወረ   የቤተ ክህነትን ትምህርትን ከተማረ በኃላ ከዕውቀቱ ላይ ዕውቀት ፣ከጥበብ ላይ ጥበብ  ለመጨመር ወደ ጎጃም ደብረ ኤሊያስ ገዳም ፣ ሸዋ ቡልጋ ኤቲሳ  ተክለ ሀይማኖት ገዳም እና ምዕራብ ሸዋ አዲስ አለም ማሪያም ቤተ ክርስቲያን  የቅዳሴና  የቅኔን ትምህርት የተማረ ሲሆን ከአስተማሩት  ሊቃውንት መካከል  መጋቢ ሚስጢር አዲስ ወልደ ሀና፣ መርጌታ ኤሊያስ እሸቱ፣ መርጌታ መዘምር ፣መርጌታ በላይ ፋላቴ እና ሌሎች ስማቸውን ያልጠቀስኳቸው  ሊቃውንቶች ስር በሚገባ የተማረ ሲሆን ሌሎች የቤተ ክህነት  አስተምህሮቶችንም ከሊቃውንቶችና የእራሱን ጥረት ጨምሮ በማግኘት  ህይወቱን ሰምና ወርቅ አድርጎ አጣፍጧል። አርበኛ ሊቀ ትጉሀን ስሙር መክብብ ትምህርቱን ከተማረ  በኃላ ስብከተ ወንጌልን  እየዞረ እንደተማረ ሁሉ  በድጋሜ  እየተዟዟረ  ከከተማ እስከ ገጠር አብያተ ክርስቲያናት በመጓዝ የእግዚአብሔርን አስተምሮ ሰብኳል  እንዲሁም ከመስመሩ የወጡትን ገስፆ አስተካክሎ  መልሷል ። እንዲሁም ያስተማረችውን ቤተ_ክርስቲያን ከሌሎች የኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን ምዕመናንን  አስተባብሮ  አሳንፃል  ለአብነት ያክል ጎንደር ከተማ ፈለገ ህይዎት ቤዛዊት ማሪያም፣ ምስራቀ ፀሀይ አቡነ ሀራ ድንግል ፣ደብረ ብስራት ገብርኤል፣ ደብረ መዋ ቀዳሚ አድባራ ቅዱስ ጊወርጊስን  ሰንበት ትምህርት ቤትን እና ከአማራ ክልል ውጭም  አፋር ክልል  አሳይታ ዱፍቲ  ከተማ የጎንደርን ህዝብ በማስተባበር የማሪያም ቤተ ክርስቲያንን  አሳንጿል ። ከህንፃ ቤተ ክርስቲያን ውጭም  ሀብት በማሰባሰብ ቤተ ክርስቲያናት ለአገልግሎት የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁሶችና አልባሳት  እንዲያሟሉ አድርጓል በማህበራዊና በአንዳንድ ችግሮች  የተዘጉ ቤተ ክርስቲያናት ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ አድርጓል ።  2004 ዓ/ም ቤዛዊት ማሪያምን ቤተክርስቲያን እንዳሰራ በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ኤልሳ አባታዊ ቡራኬ አማካኝነት  ሊቀ ትጉሀን የሚለው ማዕረግ ተሰጠው ከመምዕመናንም  የወርቅ ሀብልና ቀለበት እንዲሁም  የክብር ካባ ልብስ ስጦታ ከምስጋናና ከአክብሮት ጋር ተበርክቶለታል  ። አርበኛ ሊቀ ትጉሀን ስሙር መክብብ በጎንደር ከተማ ውስጥ  ሲኖር  የሚያምሩ ቤቶችን ገብቶ በመሸጥ ፣ የተለያዩ ንግዶችን በመነገድ፣ በማህበራዊ ጉዳዮች በመሳተፍና በማስተባበር  የታወቀ በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተወዳጅና ተሰሚ ሁኖ ሲኖር የሰሜኑ ጦርነት ሲጀመር ወጣቱን ለማበረታታትና ወደ ግንባር እንዲዘምቱ ለማድረግ በጎንደር ከተማ  የወታደራዊ ስልጠና ሲሰጥ ከ750 በላይ ወጣቶች ጋር አብሮ ሰልጥኖ  ኮከብ ተኳሽ በመሆን ከከንቲባው እጅ ሽልማት ተበርክቶለታል ነገር ግን  ወጣቶችም ወደ ግንባር ከመዝመት   ይልቅ ሎጀስቲክና ሀብት እንዲያፈላልግ  ሀላፊነት ሰጡት እሱም  የጎንደር ህዝብ  ለጦርነቱ  ትጥቅና ስንቅ  እንዲያሰባስብ በማድረግ  ሀላፊነቱን በአግባቡ  ተወጥቷል ። አርበኛ ሊቀ ትጉሀን ስሙር የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ሁኖ እንዴት ወደ ትጥቅ ትግል እንደገባ ሲናገር የብልፅግና መንግስት የአሳደጉኝን አባቶች፣ መነኮሳት፣  ቤተ ክርስቲያንን፣ ገደማትን፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ፣ ቅርሶችንና  ምዕመናንን ሲያቃጥል ፣ሲጨፈጭፍ፣ ሲያወድም እያየሁ ማለፍ ባለመቻሌ  የኦርቶዶክስ ተዋህዶን  እምነትን  ለመጠበቅ እና የአማራን ህዝብ ከጥፋት ለመታደግ ስል ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር  በፍቅር ፣ በእውነት  እና በግልፀኝነት ለመታገል መዝሙረ ዳዊቴን እና  ክላሼን ይዥ  ለሀገሬ ክብር  እንደ አባቴ አቡነ ጴጥሮስ ራሴን  ለመሰዋትነት  አዘጋጅቼ  ጫካ ገባው  ብሎ በልበ ሙሉነት ይናገራል ። አርበኛ ሊቀ ትጉሀን ስሙር በረከቱንና አሬዴቱን ፣ፆለትና ቡራኬውን ይዞ መስከረም 17 ቀን 2017 ዓ/ም ወደ ግዙፋ  ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በመቀላቀል ክፍለ ጦሩን በአማካሪነት፣ በሀብት አፈላጊነት ፣ ወጣቶችን ደግሞ በአባታዊ ምክርና ተግሳጥ ፈርሀ እግዚአብሔር እንዲኖራቸው  በማድረግ ሌሊቱን ደግሞ እንቅልፍ  እና ድካም ሳያሸንፈው  በመፀለይ   ከፈጣሪያችን በረከትና ምህረት  እንድናገኝ ድልድይ ሁኖ እያገናኘን  ያለ አባትም አርበኛም ነው። አርበኛ ሊቀ ትጉሀን ስሙር አሁን ላይ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን ) ግዙፋ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ በመሆን መንፈሳዊይን ከአለማዊ በማዋሀድ ስጋንና መንፈስን የሚያድን ትምህርት በመስጠት ታጋዩ  ለነፃነትና ለፍትህ ህዝቡ ደግሞ  ለእምነቱና ለሀገሩ ክብር መስዋትነት ከፋይ እንዲሆን  በአጠቃላይ የአማራ ህዝብ ተኳሽ፣ቀዳሽ እና አራሽነቱን እስከ ዘላለሙ  ለማስቀጠል  በፈጣሪው እና በክንዱ  የሚደረገውን የህልውና ትግል  ለማስቀጠል ከፊት ሆኖ እየመራ  ያለ የ21 ኛውን ክፍለ ዘመን የዳዊት እና የጎሊያድን ግጥሚያ በዳዊት ልጆች አሸናፊነት እንዲጠናቅቅ በልበ ሙሉነት  እየሰራ  መሆኑን እየመሰከርኩ ታሪኩን ለታሪክ ጽሀፊዎች ትቼ እኔ  በዚሁ ጨርሻለሁ  ። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!! አርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ    ጥር  30/2018 ዓ/ም