ch
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
3 011
订阅者
+2324 小时
+367 天
+41430 天
帖子存档
የአማራ ሚዲያ ካውንስል (AMC) በሳተላይት ቴሌቪዥን ምስረታ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ! በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ከ15 በላይ የሚሆኑ ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚዲያ ተቋማት፣ የሕዝባችንን የህልውና ትግል፣ ሰብዓዊ መብትና ሁለንተናዊ ፍላጎት ለማስከበር የአማራ ሚዲያ ካውንስልን (AMC) በማቋቋም ላለፉት ሁለት አመታት በጋራ ስንሰራ መቆየታችን ይታወቃል፡፡ አሁን ደግሞ ሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ ለመመሥረት ባለፉት ሁለት ወራት በጠንካራ ዝግጅት ላይ መሆናችንን ስንገጽ በታላቅ ኩራት ነው።  ይህ ካውንስል ከሁለት ዓመት በፊት ሲመሠረት በተበታተነ መልኩ የሚደረጉ የሚዲያ ሥራዎችን ወደ አንድ ወጥና ጠንካራ የጋራ አጀንዳ (Unified Narrative) ለማምጣት እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎችንና ተቋማትን አቅም በማቀናጀት የሕዝብን ድምፅ ከፍ ለማድረግ ነው። በተለይም በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የመረጃ አፈና ለመስበር፣ በጨለማው ውስጥ ላለው የአማራ ሕዝብ እና ድምፅ ለሌላቸው ኢትዮጲያዊያን ድምፅ ለመሆን፣ በዲጂታልና በሳተላይት አማራጮች አማካኝነት እውነቱን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማድረስ የተቋቋመ የሙያና የትግል መድረክ ይሆናል።  ካውንስሉ ካቀዳቸው ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች መካከል ቀዳሚው፣ የኢንተርኔት መቆራረጥና ሳንሱር የማያግደው፣ ኢንተርኔት በማይደርሰበትና አገዛዙ ኢንተርኔት ለዘጋበት ሕዝብና አካባቢ ለመድረስ፣ በመላው ኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ የሚሆን "የሕዝብ ድምፅ" የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ መመሥረት ነው። ይህ ጣቢያ የአባል ሚዲያዎችን ሰፊ የሕዝብ መሠረትና አቅም በማቀናጀት፣ የሕዝባችንን የታሪክ፣ የባህል፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፍላጎቶች የሚወክል ቀዳሚ ተቋም ይሆናል።  ይህ ታላቅ ተቋም በምስረታ ላይ ባለበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ የሚከተሉት ባለድርሻ አካላት አብረውን እንዲቆሙና እንዲሰሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን፦ • ለሚዲያ ባለሙያዎችና ተቋማት፦ በካውንስሉ ውስጥ ያልታቀፋችሁ ሚዲያዎች የካውንስሉን አቅም በማጠናከርና የጋራ አጀንዳን በመገንባት ሂደት ውስጥ በሙያችሁ እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።  • ⁠በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እየተሳተፋችሁ ላላችሁ የህልውና ታጋዮች አብረን እንድንሰራ ጥሪ እናቀርባለን። • ለሲቪል ማህበረሰብና ሙያ ማህበራት፦ በዚህ አመራር ሂደት ውስጥ በመሳተፍ የጣቢያውን ገለልተኝነትና ሕዝባዊነት እንድታረጋግጡ ጥሪ እናቀርባለን።  • ለባለሀብቶችና ለደጋፊዎች፦ ይህንን የመረጃ አፈና የሚሰብር የሳተላይት ፕሮጀክት ከሃሳብ ወደ ተግባር ለመቀየር በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የታሪክ አሻራችሁን እንድታስቀምጡ ጥሪ እናቀርባለን።  • ለዲያስፖራው ማህበረሰብ፦ የትግሉ የጀርባ አጥንት በመሆን የካውንስሉን ዓለም አቀፍ ተደራሽነትና የፋይናንስ ዘላቂነት፣ የሀሳብ የበላይነት እንዲኖረው በምትችሉት ሁሉ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን። የአማራ ሚዲያ ካውንስል (AMC) ለፍትሕና ለህልውና የሚደረገውን ትግል በጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር ታንጾ ለመዘገብና እውነተኛ መረጃ ለሕዝብ ለማድረስ ቆርጦ ተነስቷል። ይህ የመጀመሪያው እርምጃችን ሲሆን፣ በቀጣይ በዝርዝር የምናሳውቃቸው የሥራ እንቅስቃሴዎች  ታላቅ ተስፋ ይዘው እንደሚመጡ አንጠራጠርም።  "የጋራ ድምፅ ለፍትሕና ለእውነት!"  የአማራ ሚዲያ ካውንስል (AMC) ሚያዚያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም

#ፋኖ_በደብረ_ዘቢጥ_ታላቅ_ጀብድ_ሰራ‼️ ምኒልክ ዕዝ ታላቅ ጀብድ በደብረ ዘቢጥ ሲሰራ የአገዛዙን ወንበር አስጠባቂ ሰባት አመራሮች ላይ የድምሰሳ እርምጃ ሲወሰድ ከ15 በላይ ቁስለኛ አድርገዉ ታላቅ
#ፋኖ_በደብረ_ዘቢጥ_ታላቅ_ጀብድ_ሰራ‼️ ምኒልክ ዕዝ ታላቅ ጀብድ በደብረ ዘቢጥ ሲሰራ የአገዛዙን ወንበር አስጠባቂ ሰባት አመራሮች ላይ የድምሰሳ እርምጃ ሲወሰድ ከ15 በላይ ቁስለኛ አድርገዉ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር 22ኛ ክፍለ ጦር አርበኛ ሰሎሞን ሻለቃ ሚያዚያ 25/2018 ዓ/ም  በገረገራ ከተማ ሰርገው በመግባት በሰባት የጥላት የጦር መኮነኖችን  ሲደመስስ ከ15 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ በማድረግ እርምጃ ወስዷል። በታማኝነት እስከ ህይወት ህቅታው ድረስ ታምኖ የዘለቀ እና አንድያ ህይዎቱን በማይተካ ዋጋ የከፈለ የዘመናችን ህያው ታሪክን በደሙ ጠብታ ፅፎ ያለፈ ሲሆን በአርበኛው ሰማዕታት ስም የጥላት እኩይ እንቅስቃሴ እና የጥፋት አላማ እንደ ጉም እንድሆን ተደርጓል! ​ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!! 25/ዐ8/2018 ዓ.ም

ገብርዬ፡ የሞት ሽረት ጀግንነት እና የቁርጥ ቀን አንበሳ ዛሬ ስለ አንድ ልዩ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፣ ስለ ጀግናው ገብሬ ገድልና ማንነት ጥቂት ልላችሁ እወዳለሁ። ገብሬ ማለት ለጠላት የማይበገር፣ ለሀገሩ ፍቅርና ለክብሩ የማይደራደር፣ በወንድሞቹ ዘንድ እንደ ምሰሶ የሚታይ እውነተኛ የፋኖ አርበኛ ነው። የገብሬ ልዩ ማንነትና የውጊያ ጥበብ ገብሬ ዝምተኛ ግን እንደ መብረቅ አስደንጋጭ ነበር። በጦር ሜዳ ላይ ያለው ብቃትና ቁርጠኝነት "ጀግና" ለሚለው ቃል ትክክለኛ ትርጉም የሚሰጥ ነው። እሱ ለክብሩ ሲል እንጂ ለዝና አልኖረም፤ ነገር ግን ስራዎቹ ዛሬም ድረስ በታሪክ ሲዘከሩ ይኖራሉ። የጀግንነት ታሪክ፦ ያ አስደናቂ ውጊያ ታሪክ የማይረሳው አንድ ታላቅ ገድሉ አለ። በዚያ አስፈሪ ውጊያ ላይ ገብሬ የቀኝ እጁን በጥይት ተመትቶ ነበር። ማንኛውም ሰው "አከተመልኝ" ብሎ እጁን በሚሰጥበት ወይም በሚሸሽበት ቅጽበት፣ ገብሬ ግን እንደ አዲስ ተቆጣ። በቆሰለ እጁ፦ ቀኝ እጁ ደም እየፈሰሰው፣ በግራ እጁና በሙሉ ወኔው ቃታውን እየሳበ 7 ጠላቶችን አንድ በአንድ ወደ መቃብር ላካቸው። ደረት ለደረት፦ ገብሬ ጥይት በደረቱ ላይ ሲያርፍ እንኳ አልተንበረከከም። ደረት ለደረት ገጥሞ፣ ፊቱን ሳይመልስ እስከ መጨረሻው የትንፋሽ ጠብታ ድረስ ለሀገሩና ለክብሩ ተዋድቋል። "ጀግና አይሞትም፣ ታሪኩ ትውልድ ሲያወራው ይኖራል!" እንደሚባለው፣ ገብሬ ዛሬም በእያንዳንዱ አርበኛ ልብ ውስጥ ህያው ነው። የገብሬ ባህርያት ጽናት፦ በአካል ላይ የሚደርስ ጉዳት የአእምሮን ጥንካሬ እንደማይበግረው በተግባር ያሳየ። ታማኝነት፦ ለዓላማውና ለሕዝቡ የገባውን ቃል በደሙ የፈረመ። አርአያነት፦ ለ አርበኞች የድልና የጥንካሬ ምንጭ የሆነ። ይህ ገድል ለሁላችንም ኩራት ነው። ገብሬ በቆሰለ እጁና በቆሰለ ደረቱ የጻፈው ታሪክ፣ ዛሬ ላለው ትውልድ ትልቅ ትምህርት ነው። ድል ለጀግናው ፋኖ! አርበኛ መኮንን

201ኛ ኮር ቢቡኝ ወረዳ ብቁ ወጣቶች ጋር በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል! በሚል መሪ ቃል በምስ/ጎጃም ቢቡኝ ወረዳ የኮረብታ ከተማ ቀጠና የወጣ
+2
201ኛ ኮር ቢቡኝ ወረዳ ብቁ ወጣቶች ጋር  በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል! በሚል መሪ ቃል በምስ/ጎጃም ቢቡኝ ወረዳ የኮረብታ ከተማ ቀጠና የወጣቶች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። ========================== .........ሚያዚያ 25/2018 ዓ.ም ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 201ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የወጣቶች የውይይት መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተካሒደዋል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ ቀርቧል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

+2
በሸዋ ምድር የመሸገው የአረመኔው ኮማንዶ በሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አናብስቶች ድባቅ ተመታ!! ​በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አንፆኪያ ገምዛ ወረዳ፣ ሀገረ ማርያም ሟጨራ ቀበሌ፣ የብረት አፈር ፣ ቀርቀሀ እና በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ሰፍሮ የነበረው የአብይ አህመድ የአየር ወለድ ኮማንዶ ኃይል ድባቅ እየተመታ አይገኝል። ​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከሁለት ክፍለጦር የተውጣጡ ሰራዊቶችን በመጠቀም በወሰደው መብረቃዊ ጥቃት ለቀናት በስፍራው ሰፍሮ የነበረውን የአየር ወለድ ኮማንዶ ኃይል እያስለቀሰ እና እያሯሯጡት የበላይነት እየወሰዱ ይገኛሉ። ​ ​«ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር»፣ «ሰባት ለሰባ ክፍለጦር» እና «አጼ ይኩኖ አምላክ ክፍለ ጦር በተቀናጀ መንገድ በብረት አፈር ጎጥ አካባቢ በቅዱስ ገብርኤል መካነ መቃብር አቅራቢያ የነበረው የአየር ወለድ ኮማንዶ ኃይል፣ በድንገተኛ ማጥቃት ያልጠበቀ ውድመት የደረሰበት ሲሆን፣ የአሳምነው አናብስቶች በከፈቱት የማጥቃት ዘመቻ የአረመኔው የኮማንዶ ኃይል የያዘውን ቦታ ለቆ ለመሸሽ ተገዷል። የፋኖ ኃይሎችም አካባቢውን በቁጥጥራቸው ሥር በማድረግ ላይ ይገኛሉ። መረጃው የአጼ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ነው። ክብር ለትግሉ ሰማዕታት ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !! ማያዚያ 25/2018 ዓ.ም ​የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

#ታላቅ_ድርጅት_አቀፍ_ህዝባዊ_መድረክ_በሳሲት👏 የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ባወረደው የስራ መመሪያ መሰረት በሸዋ ጠቅላይ ግዛት የተለያዩ አካባቢዎች የህዝብ መድረኮች ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እየተደረገ ይገኛል። ሚያዚያ 25/2018ዓ.ም እንደ ድርጅት አፋብን ባስቀመጠው የስራ አቅጣጫ መሰረት "በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በተቆጣጠራቸው በሁሉም የሸዋ ቀጠናዎች በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እየተካሄደ ባለው የህዝብ መድረክ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 25 ቀን 2018ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በሞጃና ወደራ ወረዳ በሣሲት ክላስተር ታላቅ ህዝባዊ መድረክ መካሔዱን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር በላከው የግንባር መረጃ ገልጿል። የአፋበን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች፣የህግና ፍትህ አመራሮች፣ በዕዙ አፄ አምደ ፅዮን ኮር ስር ያሉ የ3 ክፍለ ጦር አመራሮች፣የራንቦ ክፍለጦር ፣የ7/ለ70 ክፍለጦር፣ የንጉስ ሳህስ ሥላሴ ክፍለጦር እንዲሁም የሣሲት ክላስተር አመራሮች፣ ነሣሲትና አካባቢው እንዲሁም ከሁሉም ቀበሌ የተወጣጡ አመራሮች፣የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች እና ከሁሉም ቀበሌ የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍል በተገኙበት እንደ አፋብን በአይነቱ ለየት ያለ ታላቅ ድርጅት አቀፍ የህዝብ መድረክ በውይይቱ ላይ የተገኘው የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ገልጿል። በክላስተሩ ዙሪያ ካሉ ቀበሌዎች የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በተደረገው ወቅታዊ ድርጅት አቀፍ ውይይት በትግሉ ሒደትና ተያያዥ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሳል የመድረክ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱ ወቅታዊ ጥያቄዎች መድረኩን በመሩት የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የፖለቲካ መምሪያ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል። በመጨረሻም ባለ 10 የጋራ የአቋም መግለጫ በማውጣት መድረኩ በስኬት ተጠናቋል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሚያዚያ 25/2018ዓ.ም

በሰላም የተከለለው ምድር፤ በግፍ የተወሰደው ጉልበት፡ የእዝግዬ ጉባወጩ ምስኪኖች እንባ!! ​ከአማራ ክልል ሸዋ ጠቅላይ ግዛት የኤፍራታና ግድም ወረዳ እንዲሁም ከኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ጅሌጥሙጋ ወረዳ አዋሳኝ የሚመጣው ድምፅ የፍትህ መጓደል እና የመብት ረገጣ አሳዛኝ ምስክር ነው። እዝግዬ ጉባወጩ ቀበሌ ትናንት የሰላም እና የልፋት መኖሪያ የነበረችው ስፍራ፣ ዛሬ በግዳጅ መፈናቀል እና በስርዓተ-አልበኝነት እየታመሰች ትገኛለች። ​​በዚህ ቀበሌ የሚኖሩት የሙስሊም አማራ ማህበረሰብ አባላት ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ ከቃላት በላይ ነው። አርሶ አደሮቹ መሬቱን በላባቸው ያርሳሉ፣ ሰብሉን በአሳርና በክብር ይንከባከባሉ፣ ያጭዳሉ፣ ያስወቁታል። ነገር ግን፣ የድካማቸው ውጤት የሆኑት እህሎች ለቤተሰባቸው ማዕድ ሳይሆን፣ የሰንበቴ ከተማ የብልጽግና ካድሬዎች ለሚዘርፉት የገቢ ምንጭነት ይውላሉ። የገዛ መሬታቸው ላይ እንግዳ ሆነው፣ የራሳቸው የላብ ውጤት በግልጽ እየተዘረፈባቸው መሆኑ በፍትህ አደባባይ እየተፈጸመ ያለ ግፍ ነው። ​የትናንቱ ሰላም፣ የዛሬው ቁስል ​ቀደም ሲል በሰላም፣ በፍቅር እና በወግ ይኖሩ የነበሩት እነዚህ ወገኖች፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። የኖሩበት ቤት ሲቃጠል፣ የያዙት ንብረት ሲዘረፍ እና ክብራቸው ሲደፈር ያዩት አሳዛኝ ክስተት፣ በውስጣቸው እየደማ ያለ የማያልፍ ቁስል ሆኗል። ትናንት በሰላም ያሳለፉትን ህይወት በዓይነ ህሊናቸው እየሳሉ፣ ዛሬ በስቃይ መኖር መገደዳቸው የሁኔታውን አስከፊነት ያሳያል። ​በመጠለያ ጣቢያዎች የታጠረ ህልውና ​ዛሬ ላይ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች በኮምቦልቻና በደሴ መጠለያ ካምፖች ወይም በዘመዶቻቸው ቤት ተጠግተው፣ ለነገ ቀን እንኳን ሳይሰንቁ በችግር ውስጥ ይገኛሉ። በቦታው ቀርተው ያሉ ጥቂቶችም ቢሆኑ፣ በየቀኑ ከሚደርስባቸው የዘረፋ እና የማግለል ድርጊት ባሻገር፣ መሬታቸው እየተወሰደ ለመንግስት ገቢ መደረጉ እንደተጨማሪ ጫና እየተሰማቸው ይገኛል። ​የገዛ መሬታችን ላይ ሰርተን የራሳችንን መብላት አልቻልንም፤ የጉልበታችን ዋጋ ለሌላው እየተዘረፈ ነው" ሲሉ የተጎጂዎቹ ብሶት በምሬት ይገለጻል። ​እዝግዬ ጉባወጩ፣ ዛሬ በዜጎች መብት ረገጣ እና በፍትህ መጓደል በታሪክ መዝገብ ላይ በደል እየተፈጸመባት ያለች ስፍራ ሆናለች።

+5
201ኛ ኮር ሁለት እጅ እነሴ ወረዳ አስቴሪዮ መንግስት ሰራተኞች ጋር መክሯል ። በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል! በሚል መሪ ቃል ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። =========================== ማያዚያ 25/2018 ዓ.ም ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 201ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የመንግስት ሰራተኞች የውይይት መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ማካሔዱን አጠናክሮ ቀጥሏል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ የቀረበ ሲሆን የጤና ባለሙያዎች፣ የግብርና ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ እና የማህበራት ተጠሪዎች በንቃት ተሳትፈውበታል ። አማራን ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ሰብሮ ለመውጣት የመንግስት ሰራተኞች ሚና በጉልህ የሚገለጽ ሲሆን ትግሉን በተባበረ ክንድ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል ። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ግዙፉ የአስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር በጠላት ላይ ድል ተቀዳጅተዋል!!! ሚያዝያ 24/8/2018ዓም አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ግዙፉ አስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር ያለፉትን አምስት ሳምንት በይፋት አውራጃ አንፆኪያ ገምዛ ግሽ ራቤልና በዳዋ ጨፋ ወረዳዎች ጠላትን ቁም ስቅሉን ሲያሳዩት መቆየታቸው ይታወቃል። በአንፆኪያ ገምዛ   አገረ  ማሪያም  በአራት ቦታ  ከጧቱ  በ12 : 00 የተጀመረው  አውደ ውጊያ  ቀኑን  ሙሉ  ዘጠኝ ጊዜ የማጥቃታ ሙከራ የአብይን  ወራሪ  ሃይል ቢያደርግም ክንደ ነበልባሎቹ ከሶስት ሻለቃዎች የተውጣጡ  የጦር  ጥበብተኞቹ   የምድር  ድሮን  በሆኑት  አመራሮች  እየተመሩ  በሞርተርና  በአርቢጂ   በታገዘ  መካናይዝድ  አውደ  ውጊያ  በማድረግ   ጠላትን እሬሳና  ቁስለኛውን  ከነመሳሪያው  ጥሎ እዲሮጥ አድርገውታል።  በኩሬ የጎደል ቀበሌ ሸሃደብስና እሁድ ገበያ የገባውን የጠላት ሃይል ከሁለት ሻለቃ የተውጣጡ ሻበሎች በጋራ በመቀናጀት ተስበው በመግባት ጠላት ላይ የጨበጣ ተኩስ በመክፈት በጠላት ላይ ብዙ ኪሳራ አድርሷል። የአስቴ ጎማዎችን ውጊያ መቋቋም ያቃተው የጠላት ሃይል ተጨማሪ ሰራዊት ከግሽ ራቤል ፥ግሾጌና ሸበቶ ቀበሌ ሶስት መኪና መከላከያ ቢያመጣም የአስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር አናብስቶች የመጣውን ሃይል እዳይወጣ አድረገው ከአስራ ሁለት በላይ ሲደመሰሱ ከአስራ ስድስት በላይ ከባድና ቀላል ቁስለኛ አድርገው እሬሳውን ማንሳት ሳይችል አዘረክርኮ ፈርጥጧል። የአስቴ ጎማ ነበልባሎች አምስት የጠላትን እሬሳ በአማራው ስነ ስርአት በክብር በህዝብ አስነስተው በቀርቀሃና ሃገረ ማርያም ስርአተ ቀብራቸውን አስፈፅመዋል።     ከጠላት የተገኘ ምርኮ 1, የነፍስ ወከፍ ሁለት ጥቁር ጥርጥር ክላሽ 2, ስምንት ካዝና 3,312 ሶስት መቶ አስራ ሁለት የክላሽ ተተኳሽ 4, አምስት ወታደራዊ ሻንጣ 5, ሁለት ወታደራዊ ሳንጃ ምርኮ ማግኘት የተቻለ ሲሆን 6, የተደመሰሰ ጠላት አስራ ሁለት (12) 7,ከባድ ቁስለኛ አስራ ስድስት (16) ክፍለ ጦሩ ጠላትን ድባቅ በመምታት ነፃ ያወጣቸው ቀበሌዎች 1 ዋሻ ንገት 2 አሰለሌ ቀለበት ወንበር 3 ሳፍራ 4የጎደል 5 አፍሶ 6 ቢቆጨኝ 7 አራጣ ወጠፌ ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ ከጠላት ነፃ ወተዋል። የፋኖ የበላይነት ይቀጥላል የህዝባችን ሰላም በኛ በልጆቹ ይከበራል!! መረጃው የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር አስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክብር  ለትግሉ ሰማዕታት!! ድል ለተከበረው  የአማራ ህዝብ ‼️ ድል  ለአፋብን‼️ ድል  ለኢትዮጵያ  ህዝብ‼️      24/8/2010ዓም የአማራ  ፋኖ ብሔራዊ  ንቅንቄ   አፋብን  ሸዋ ጠቅላይ  ግዛት  አሳምነው  ዕዝ

የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር  ስር በሚገኘው በማጀቴ ክላስተር የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሰራተኞች ጋር ውይይት ተደረገ!!   በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል! በሚል መሪ ቃል የወረዳ የመንግስት ሰራተኞች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አስምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የአገልግሎት ሰጭ ሰራተኞች የውይይት መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ማካሔዱን አጠናክሮ ቀጥሏል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ የቀረበ ሲሆን የጤና ባለሙያዎች፣ የግብርና ባለሙያዎች፣ መምህራን፣   እና የማህበራት ተጠሪዎች በንቃት ተሳትፈውበታል ። አማራን ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ሰብሮ ለመውጣት የአገልግሎት ሰጭ ሰራተኞች ሚና በጉልህ የሚገለጽ ሲሆን ትግሉን በተባበረ ክንድ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል ። ክብር ለትግሉ ሰማዕታት ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !! ማያዚያ 25/2018 ዓ.ም ​የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ !!

አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ በ102ኛ ኮር 12ኛ ክፍለ ጦር በአገዛዙ ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም ድል አስመዘገቡ:: በምርጫ ስም እራሱን ብቻ በእጩነትና በመራጭነት ያቀረበው የብልፅግና አገዛዝ ህዝብን በማስገደድና በማዋከብ የምርጫ ካርድ እንድወስዱ በቀዩ ጋሪያ፣ በተኩለሽና በጮቢ በር ለመሰብሰብ ሙከራ ቢያደርግም በጀግኖቹ ክንድ ተበትኗል። በደም የጨቀየው ለሲቪሊያን ህይወት የማይጨነቀው ቆሞ ቀሩ የብልፅግና አገዛዝ አለም አቀፍ ህጎችን ሙሉ ለሙሉ በመጣስ የአማራ ክልል ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት በመፈፀም በግዳጅና በማስፈራራት የምርጫ ካርድ አውጥተው አንዲመርጡት በከፍተኛ እንእስቃሴ ላይ ይገኛል። ግትርና ቆሞ ቀሩን አገዛዝ በውል የተረዱት የ12ኛ ክፍለጦር አሀዶች በጠላት ላይ የማያዳግም ርምጃ በመውሰድ አካባቢውን የወገን ሀይል ተቆጣጥሮ ውሏል። በመሆኑም ጠላት በጧት ጀምሮ በድሮን፣ በቢ-ኤም፣በዙ-23፣ በመድፍና በታንክ የተጠናከረ ማጥቃት ቢያደርግም በ12ኛ ክፍለ ጦር የሚመሩት  አይበገሬዎቹን ማቆም ተስኖት ቀጠናውን ለወገን ሃይል አስረክቦ ወጥቷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሚያዚያ 25/2018 ዓ/ም

21ኛ ክፍለ ጦር  5ኛ ሻለቃ ልዩ ስፍራው አጣጎይ ከተባለ ቦታ ደፈጣ በመስራት ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ:: የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነው ኮር አካል የሆነው 21ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሻለቃ በአንጎት ወረዳ  ከዥጣ ወንዝ እስከ አሁንተገኝ ከተማ መንገድን ግራና ቀኝ የጠላት ጦር  በመወጠር ሚያዚያ 24 ቀን 2018 ዓ/ም ህዝብን ግዴታ ተመዝግባችሁ የምርጫ ካርድ አውጡ በማለት ገበያ የሚሄደውን ሰላማዊ ነዋሪ እና  የግብረ ሰናይ ድርጅት እርዳታ ሊያደረግላቸው ጥሪ የተደረገላቸውን የ012 ቀበሌ ነዋሪዎች ሲያሰቃይ ውሏል። ህዝብን ሲያንገላታ የዋለውን የብልፅግና ሰራዊት  የ21ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሻለቃ ፋኖዎች ልዩ ስፍራው አጣጎይ በተባለ ቦታ ደፈጣ በመስራት ከፍተኛ ውጊያ በማድረግ ስድስት የስርዓቱ ጠባቂ ወታደር ሲደመሰሱ ሰባት የሚሆኑት ቆስለው በአንቡላንስ ተጭነው ወደ ህክምና የተወሰዱ ሲሆን ወጥሮ የነበረው ሰራዊት እግሬ አውጭኝ በማለት ወደ አሁንተገኝ ከተማ ተመልሷል በወገን በኩል ምንም ዓይነት ጉዳት ያልደረሰ መሆኑን የተከዜ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል። መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል። ህልውናች በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 25/2018 ዓ/ም