ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多3 712
订阅者
+2624 小时
+3797 天
+1 10930 天
帖子存档
ፀረ-አማራው አገዛዝ የጤና ተቋማትን እየዘጋ ነው‼️‼️
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ በ105ኛ ኮር በ44ኛ ክ/ጦር ቀጠና ስር የሚገኙ አስር (10) የህዝብ አገልግሎት መስጫ ጤና ተቋማት በወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ቀጥታ ትዕዛዝ ሰጭነት ከጥር 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተዘግተዋል።
ተቋማቱ በመዘጋታቸው ምክንያት ከ 85 በላይ የሚሆኑ የተቋማቱ ሰራተኞች ደመወዝ እንዳይከፈል ለወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት የዕግድ ደብዳቤ በፍሬህይወት መኩሪያው በኩል ተጽፎ ደርሷል ተብሏል።
አሸባሪው ስርዓት የህክምና አገልግሎት መሰጫ ተቋማት እንዲዘጉ ትዕዛዝ ቢያስተላልፍም ለሰውነት ቅድሚያ የሚሰጡት የተቋማቱ ሰራተኞች ግን የምንበላው እስክናጣ ድረስ የተገፋውን ህዝባችን እናገለግላለን በማለት ብልፅግና ከዘጋቸው ተቋማት አሁንም በመስራት ላይ ይገኛሉ።
በባንጃ ወረዳ አስተዳድር ምክር ቤት እና በወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ቀጥታ ትዕዛ ሰጭነት የተዘጉት የህዝብ አገልግሎት መስጫ የጤና ተቋማት
1) ህዳር 10/2017 ሙሉ በሙሉ አውድሞትና ዘርፎት የነበረው ዳንጊያ ጤና ጣቢያ
2) ሱርታ ጤና ጣቢያ
3) ዳንጊያ ኪዳነምህረት ጤና ኬላ
4) አከና ጤና ኬላ
5) አሰም ጤና ኬላ
6) ጃንጉታ ጤና ኬላ
7) ሱርታ ጤና ኬላ
8) ጉርጃ ጤና ኬላ
9) ጋጋስታ ጤና ኬላ
10) አተታ ጤና ኬላ ናቸው።
እነዚህ ተቋማት ተዘግተው የህክምና አገልግሎት ፣ የነፍሰጡር ክትትል አገልግሎት ፣ የወሊድ አገልግሎት እና የህፃናት የክትባት አገልግሎቶች እንዲቋረጡ የተደረገበት ዋና ዋና ምክንያቶችም፦
1) የቀጠናው ህዝብ ለፋኖ ሁለንተናዊ ድጋፍ እየሠጠ ስለሆነ፣
2) ህዝቡ የጤና መድህን ክፍያ ባለመክፈል የመንግስትን የፋይናንስ ሀቅም አዳክሞ ከአማራ ህዝብ ጋር እያደረግን ያለውን ጦርነት መመከት እንዳንችል አድርጓል፣
3) የፋኖ ሐይሎች ተቋማቱን እየተጠቀሙበት ስለሆነ በማሉ ተልካሻ ምክንያቶች ሊዘጉ ችለዋል።
ይህ ግፈኛውና ፀረ-ህዝብ ስርዓት የአማራን ህዝብ የሚበድለው ለእናቶች የወሊድ አገልግሎት የሚሰጡ አምቡላንሶችን ለጨፍጫፊውና ለወንበር አስጠባቂው የፀጥታ አካላት የትንስፖርት አገልግሎት መስጫ እና የብልፅግናው ስርዓት አመራር ቤተሰብ መጓጓዣና የአስቤዛ ማመላለሻ በማድረግም ጭምር ነው።
የህክምና ባለሙያዎችን መግደልና፣መሰወር እና ከፖለቲካ ነፃ የሆኑ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለርካሽ አገር አፍራሽ ፖለቲካው ፍጆታ መጠቀም ዋነኛ ተግባር ካደረጋቸው ውሎ አድሯል።
ከዚህ በተጨማሪ የአብይ አህመድ ስርዓት በባንጃ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ በስድስት (6) ጤና ጣቢያ እና በሃያ አምስት (25) ጤና ኬላዎች የሚሰሩ ሰራተኞችን በሚሰሩበት የህክምና ተቋም ውስጥ የጤና መድህን አባል ሆናችሁ ክፍያ ካልከፈላችሁ በማለት ህክምናን መከልከልን ጨምሮ ሌሎች ህጋዊ ጥቅማጥቅሞቻቸውን እየተነጠቁ እንደሆነ ከአባላቱ ማረጋገጥ ችለናል።
እነዚህ የጤና ባለሙያዎች በከፍተኛ በደል ላይ ሆነው ህዝብን በቅንነት እያገለገሉ በመሆናቸው የተበሳጨው የብልፅግናው ተላላኪ የብአዴን አመራር ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመባቸው ይገኛል ሲል የቀጠናው የጤና መምሪያ ሀላፊ አስታውቋል።
አዲስ ትውልድ፥ አዲስ አስተሳሰብ፥ አዲስ ተስፋ!
አፋብን ምዕ/አ/ቀ/ቴወድሮስ-ዕዝ የ105ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የአማራ የደም ሰነድ
እስከመጨረሻዉ አንብቡት ጀግናም ብትሆኑ እንባ ይተናነቃችኋል።
ከ2011 ወዲህ የተፈጸሙ የዘር ማጥፋት (Genocide) ወንጀሎች
ይህን መረጃ ከሰባዊ መብት ተሟጋቾች እና በገለልተኛ አካላት ከታወቀዉ ብቻ ነዉ ያገኘሁት።
ሌላዉን እና ጅብ በልቶት አልጮህ ያለዉን፤ የምዕራብ ኦሮሚያ ናኖ አሎ/ጉዲና እናም የተማሪዎችን ነገር ማንም አያዉቀዉም። ከዚህ ቁጥር ጋር የማልደምረዉ።
የተበላዉ አማራ ከ10 ሚሊዮን ይበልጣል።
ይህ ግን
የማንነታችን ዋጋ በደም የተከፈለባቸውን መርዶዎች ይዟል። ቆመን የምንሟገትላቸው ወገኖቻችን ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ፣ ዛሬ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በመጠለያ ካምፕ ይገኛሉ።
የጥቃቱ ቦታ ቀን (በኢ.አ) የሟቾች ቁጥር (ግምት) የቆሰሉና የተፈናቀሉ (ግምት) አጭር መግለጫ ይሄዉላችሁ
👉 መተከል (ቡለን) መስከረም 2013
120+ በሺዎች የሚቆጠሩ በቤታቸው ውስጥ እያሉ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል።
👉 ጉሊሶ (ጋዋ ቆንቃ) ጥቅምት 2013
54+ መላው መንደር በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በጅምላ ተረሽነዋል።
👉 መተከል (በቆጂ) ታኅሣሥ 2013
207+ 40,000+ ተፈናቃይ እጅግ ዘግናኝ የሆነ የጅምላ ጭፍጨፋ።
👉 አሙሩ (ሆሮ ጉድሩ) መጋቢት 2013
100+ ከፍተኛ ቁጥር ቤትና ንብረት ወድሟል፤ ሕዝቡ ተሰዷል።
👉 አጣዬና ከሚሴ መጋቢት 2013
300+ 250,000+ ተፈናቃይ ከተሞች ሙሉ በሙሉ ወድመው አመድ ሆነዋል።
👉 ቶሌ (ጊምቢ) ሰኔ 11/2014
400 - 600 መላው ቀበሌ "አማራ አልሆንም" ያሉ ሕፃናት የታረዱበት።
👉 ሀዋ ገላን ሰኔ 27/2014
150+ በሺዎች የሚቆጠሩ አማራ በመሆናቸው ብቻ ተለይተው ተረሽነዋል።
👉 ጃርደጋ ጃርቴ ነሐሴ 2014
100+ 50,000+ ተፈናቃይ ለአሰቃቂ ስደትና ሞት ተዳርገዋል።
👉 አንገር ጉትን ኅዳር 2015
80+ በሺዎች የሚቆጠሩ አምራች ገበሬዎች ከነማረሻቸው ተገድለዋል።
👉 መተከል (ጋሊላ) 2013 (ተደጋጋሚ) 150+ በመቶ ሺዎች "መሬቱን ልቀቁ" በሚል በየቀኑ የሚፈጸም ጥቃት።
👉 ጊዳሚ (ቄለም) ሰኔ 2014
150+ ከፍተኛ ቁጥር በጅምላ የመረሽን ጥቃት ተፈጽሟል።
👉 ቆሬ (አርሲ) ጥቅምት 2016
50+ በሺዎች የሚቆጠሩ የሃይማኖት አባቶችና ሕፃናት በቤታቸው የታረዱበት።
👉 አሙሩ (ዳግም) ነሐሴ 2014
60+ ከፍተኛ ቁጥር አማራዎች ተለቅመው የተገደሉበት ጥቃት።
👉 ሜቲ (ደንቢ ዶሎ) ጥቅምት 2013
34 - ከአውቶቡስ ወርደው በማንነት ተለይተው ተረሽነዋል።
👉 ሜታ አቦ (ወሎ) 2013
በመቶዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታታይ በሆኑ ጥቃቶች ሕዝብ ተፈናቅሏል።
👉 ኪራሙ (ወለጋ) 2015
100+ 100,000+ ተፈናቃይ መላው አማራ ከአካባቢው እንዲጸዳ ተደርጓል።
ድምር ከ16 በላይ ቦታዎች 2011 - 2016
ከዚያ ወዲህም መፈናቅሉ እና ስደቱ ሞቱ እስከዚች ሰዓት አለ።
ከ 2,500 በላይ ከ 3 ሚሊዮን በላይ የዘር ማጥፋት (Genocide) ጥቃት
ዛሬ ላይ ሆነን ስናሰላው፣ ከ2,500 በላይ ንጹሐን አማራዎች በግልጽ የተሰረዙበት፣ ከ3 ሚሊዮን በላይ ወገኖቻችን ሀገር አልባ ሆነው በመጠለያ የሚማቅቁበት እውነት ፊታችን ላይ ተደቅኗል።
ያች ሕፃን "ወላሂ... አማራ አልሆንም!" ብላ ስትማፀን የዝምተኞችን አማራ ሀጢያት የመዘገበችበት ነዉ።
ይህ ነገር ያልተሰማህ የሠዉ ልጅ እስከሰባት ትዉልድህ የመከነ ይሁን።
የአማራ ምሁራን ዝምታ፣ የተማሪዎች ዳተኝነት እና የነጋዴው ቸልተኝነት ታሪክን ለገዳዮች አሳልፎ መስጠት ነው።
ይህ ጥሪ ነው!
ይህ ዝርዝር በየቀኑ በጸሎታችሁ፣ በውይይታችሁና በድርጊታችሁ ውስጥ ይኑር።
ዝምታችንን በሰላና በበሰለ እውቀት እንስበረው። ለወገናችን ነፃነት፣ ለአማራ መሸማቀቅ፣ ለመጠለያ ካምፕ ስቃይ ማክተሚያ በአንድነት እንነሳ!
አሌክስ/አዲስ ነኝ ከፈረሰዉ መንደሬ
ለሁሉም ሼር በማድርግ እንድታደርሱልኝ በአማራ ስም እጠይቃችኋለሁ።
የአማራ የደም ሰነድ
እስከመጨረሻዉ አንብቡት ጀግናም ብትሆኑ እንባ ይተናነቃችኋል።
ከ2011 ወዲህ የተፈጸሙ የዘር ማጥፋት (Genocide) ወንጀሎች
ይህን መረጃ ከሰባዊ መብት ተሟጋቾች እና በገለልተኛ አካላት ከታወቀዉ ብቻ ነዉ ያገኘሁት።
ሌላዉን እና ጅብ በልቶት አልጮህ ያለዉን፤ የምዕራብ ኦሮሚያ ናኖ አሎ/ጉዲና እናም የተማሪዎችን ነገር ማንም አያዉቀዉም። ከዚህ ቁጥር ጋር የማልደምረዉ።
የተበላዉ አማራ ከ10 ሚሊዮን ይበልጣል።
ይህ ግን
የማንነታችን ዋጋ በደም የተከፈለባቸውን መርዶዎች ይዟል። ቆመን የምንሟገትላቸው ወገኖቻችን ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ፣ ዛሬ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በመጠለያ ካምፕ ይገኛሉ።
የጥቃቱ ቦታ ቀን (በኢ.አ) የሟቾች ቁጥር (ግምት) የቆሰሉና የተፈናቀሉ (ግምት) አጭር መግለጫ ይሄዉላችሁ
👉 መተከል (ቡለን) መስከረም 2013
120+ በሺዎች የሚቆጠሩ በቤታቸው ውስጥ እያሉ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል።
👉 ጉሊሶ (ጋዋ ቆንቃ) ጥቅምት 2013
54+ መላው መንደር በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በጅምላ ተረሽነዋል።
👉 መተከል (በቆጂ) ታኅሣሥ 2013
207+ 40,000+ ተፈናቃይ እጅግ ዘግናኝ የሆነ የጅምላ ጭፍጨፋ።
👉 አሙሩ (ሆሮ ጉድሩ) መጋቢት 2013
100+ ከፍተኛ ቁጥር ቤትና ንብረት ወድሟል፤ ሕዝቡ ተሰዷል።
👉 አጣዬና ከሚሴ መጋቢት 2013
300+ 250,000+ ተፈናቃይ ከተሞች ሙሉ በሙሉ ወድመው አመድ ሆነዋል።
👉 ቶሌ (ጊምቢ) ሰኔ 11/2014
400 - 600 መላው ቀበሌ "አማራ አልሆንም" ያሉ ሕፃናት የታረዱበት።
👉 ሀዋ ገላን ሰኔ 27/2014
150+ በሺዎች የሚቆጠሩ አማራ በመሆናቸው ብቻ ተለይተው ተረሽነዋል።
👉 ጃርደጋ ጃርቴ ነሐሴ 2014
100+ 50,000+ ተፈናቃይ ለአሰቃቂ ስደትና ሞት ተዳርገዋል።
👉 አንገር ጉትን ኅዳር 2015
80+ በሺዎች የሚቆጠሩ አምራች ገበሬዎች ከነማረሻቸው ተገድለዋል።
👉 መተከል (ጋሊላ) 2013 (ተደጋጋሚ) 150+ በመቶ ሺዎች "መሬቱን ልቀቁ" በሚል በየቀኑ የሚፈጸም ጥቃት።
👉 ጊዳሚ (ቄለም) ሰኔ 2014
150+ ከፍተኛ ቁጥር በጅምላ የመረሽን ጥቃት ተፈጽሟል።
👉 ቆሬ (አርሲ) ጥቅምት 2016
50+ በሺዎች የሚቆጠሩ የሃይማኖት አባቶችና ሕፃናት በቤታቸው የታረዱበት።
👉 አሙሩ (ዳግም) ነሐሴ 2014
60+ ከፍተኛ ቁጥር አማራዎች ተለቅመው የተገደሉበት ጥቃት።
👉 ሜቲ (ደንቢ ዶሎ) ጥቅምት 2013
34 - ከአውቶቡስ ወርደው በማንነት ተለይተው ተረሽነዋል።
👉 ሜታ አቦ (ወሎ) 2013
በመቶዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታታይ በሆኑ ጥቃቶች ሕዝብ ተፈናቅሏል።
👉 ኪራሙ (ወለጋ) 2015
100+ 100,000+ ተፈናቃይ መላው አማራ ከአካባቢው እንዲጸዳ ተደርጓል።
ድምር ከ16 በላይ ቦታዎች 2011 - 2016
ከዚያ ወዲህም መፈናቅሉ እና ስደቱ ሞቱ እስከዚች ሰዓት አለ።
ከ 2,500 በላይ ከ 3 ሚሊዮን በላይ የዘር ማጥፋት (Genocide) ጥቃት
ዛሬ ላይ ሆነን ስናሰላው፣ ከ2,500 በላይ ንጹሐን አማራዎች በግልጽ የተሰረዙበት፣ ከ3 ሚሊዮን በላይ ወገኖቻችን ሀገር አልባ ሆነው በመጠለያ የሚማቅቁበት እውነት ፊታችን ላይ ተደቅኗል።
ያች ሕፃን "ወላሂ... አማራ አልሆንም!" ብላ ስትማፀን የዝምተኞችን አማራ ሀጢያት የመዘገበችበት ነዉ።
ይህ ነገር ያልተሰማህ የሠዉ ልጅ እስከሰባት ትዉልድህ የመከነ ይሁን።
የአማራ ምሁራን ዝምታ፣ የተማሪዎች ዳተኝነት እና የነጋዴው ቸልተኝነት ታሪክን ለገዳዮች አሳልፎ መስጠት ነው።
ይህ ጥሪ ነው!
ይህ ዝርዝር በየቀኑ በጸሎታችሁ፣ በውይይታችሁና በድርጊታችሁ ውስጥ ይኑር።
ዝምታችንን በሰላና በበሰለ እውቀት እንስበረው። ለወገናችን ነፃነት፣ ለአማራ መሸማቀቅ፣ ለመጠለያ ካምፕ ስቃይ ማክተሚያ በአንድነት እንነሳ!
አሌክስ/አዲስ ነኝ ከፈረሰዉ መንደሬ
ለሁሉም ሼር በማድርግ እንድታደርሱልኝ በአማራ ስም እጠይቃችኋለሁ።
የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ድል በእጅጉ ተጠናክሮ እሥከ ሌሊቱ 05:00 ቀጥሏል🔑✊
ጣና ገላውዴዎሥ ክ/ጦር
[የካቲት 03/2018ዓ.ም ሌሊት]
ምሽት 11:00 ከአምበሳሜና ሐሙሲት መሐከል ከሚገኙት ''ግብጻዊት ማርያምና ገነት ወንዝ'' የጀመረው ትንቅንቅ አድማሱ ሰፍቶ ጠላት በውባንተ አባተ ልጆች ክንድ እየተደቆሰ ይገኛል። በዚህ የኦሕዴድ ብልጽግና ሌሊት 03 የአገዛዙ ተሽከርካሪዎች በጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ተማርከዋል፣ 03ቱም ብርጌድ የጠላትን የቡድንና የነፍሥ ወከፍ መሣሪያ እየማረኩ ይገኛሉ።
የኦሕዴድ ብልጽግና አገዛዝ እየተቀጠቀጠ ያለው የሆድ ዘመዱን ለማዳን ከባሕር ዳር ፈጥኖ ደርሷል። ያድነዋል ወይ ሥንል? መልሱ ጊዜ ዳኛ ነው የሚል ይሆናል። ኮርቻው ብአዴን መዳረሻው ቁላላ ይሁን ጥልቁ የግዮን ሐይቅ አልታወቀም።
ዓምሐራ ከጠላቶቹ በላይ መጨከን አለበት።
የብአዴን ታጣቂ የእንግዴ ልጅነቱን በ11ኛው ሰዓት እንኳ አያውቅም።
ውባንተነት
✔ ዕምነት
✔አሸናፊነት
✔አይበገሬነት
✔ፍጹም ዓምሐራነት🔑✊
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑✊
አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
ጎንደር/ዓምሐራ/ኢትዮጵያ
'መሳሪያ ማርኮ ከመታጠቅ እስከ የክፍለጦር ስም መንጠቅ!'
የኦህዴድን አገዛዝ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት እያፈረስን የአማራ ሠራዊት እየገነባን ነው። ጀብደኛዉ ምኒልክ ዕዝ የአገዛዙን ሰሜን ምስራቅ ዕዝ 12ኛ ክፍለጦርን በመደምሰስ እና ሰራዊቱን በመማረክ ከአገዛዙ የክፍለጦር ስም ዝርዝር እንድትሰረዝ ማድረጉ አይዘነጋም። እንሆ በምትኩ የክፍለጦር ስያሜዋን ለዞብል አምባ ክፍለጦር ሰጥቷል። የፋኖ 12ኛ ክፍለጦር።
ከእንግዲህ መሳሪያዉን እና የክፍለጦር ስያሜዉን ብቻ ሳይሆን መንግስትነቱን እንቀማዋለን። ምክንያቱም እኛ የዛሬዎቹ አማሮች የጀኔራል አሳምነው ፅጌ ልጆች ነን።
አገዛዙን በዚህ ሶስት ዓመት፦
የጦርነት አቅሙን አክሽፈነዋል፣ ስነልቦናዉን ሰብረንዋል፣ ሰራዊቱን አፍርሰንበታል፣ ቅቡልነቱን አሳጥተነዋል፣ የማድረግ አቅሙን አዳክመነዋል ወዘተ ወዘተ... አሁን የቀረን መንግስታዊ ሥርዓቱን መቆጣጠር ነው። መንግስታዊ ሥርዓቱ ያለው አባቶቻችን የመሰረቷት እና የአፍሪካ መናገሻ የሆነችው 'በረራ' ላይ ነው። በረራ አዲስ አበባ።
የአማራን ህዝብ በዘላቂነት ህልው ለማድረግ ሥር-ነቀል የሥርዓት ለዉጥ ማድረግ ግባችን ሲሆን አራት ኪሎን በመቆጣጠር ይፈፀማል።
አሳምነውነት/አማራነት የትዉልዱ ርዕዮት!
ምስል፦ የምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር 12ኛ ክፍለጦር ሰራዊት በከፊል
በመሃል ደብረማርቆስ ከተማ በተፈፀመ የቦንብ ጥቃት ዘጠኝ የሚኒሻ አባላት ሙትና ቁስለኛ ተደረጉ!
"የብልፅግና መንግስትን በገንዘብ አልደገፋችሁም" በሚል ንፁኋንን በጅምላ በማሰር ድርጊት ላይ ተሰማርተው የነበሩ የሚኒሻ አባላት ናቸው የቦምብ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው።
በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ206ኛ ኮር የሰርጅካል ኦፕሬሽን ምድብተኞች ትናንት የካቲት 01/2018 ዓ/ም ለዛሬ አጥቢያ ለሊት ላይ በደብረማርቆስ ከተማ በመግባት የኦህዴድ ተላላኪ ለሆነው የበአዴን ተላላኪዎች ላይ የቦምብ ጥቃት መፈፀማቸውን መረብ ሚዲያ ከኮሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።
ጥቃቱ የተፈፀመው እኩለ ለሊት 7:35 ላይ ሲሆን፡ በከተማዋ ከማረሚያ ቤት ወደ መሃል አደባባይ በወታደራዊ ፓትሮል ተሳፍረው ሲጓዙ በነበሩ የሚኒሻ አባላት ላይ ነው የቦምብ እሳት የወረደባቸው።
የተላላኪ ተላላኪ የሆኑት የሚኒሻ አባላቱ የቦምብ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ተሳፍረውበት የነበረው ተሽከርካሪው በፍጥነት እየተጓዘ እንዳለ ሲሆን፡በዚህም ሦስቱ ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ ስድስቱ የሚኒሻ አባላት ደግሞ ክፉኛ ቆስለው በሞትና በሕይወት መካከል እንደሚገኙ ታውቋል።
የሚኒሻ አባላቱ ጨለማን ተገን በማድረግ በሌሊት ንፁሐንን አፍነው ማረሚያ ቤት አድርሰው እየተመለሱ እንዳሉ ነው የቦንብ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው።
እነዚህ የኦህዴድ ተላላኪ የሆነው የበአዴን ተላላኪዎች "የብልፅግና መንግስትን በገንዘብ አልደገፋችሁም" በሚል ምክኒያት እና "የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ" በሚል ንፁኋንን በጅምላ በማሰር ሲያስገድሉና ከታሳሪዎች ከመቶ ሺ ብር ጀምሮ በግዳጅ ገንዘብ ሲቀበሉ የነበሩ የሕልውና ትግሉ አሜካላ እሾሆች ናቸው።
እነዚህ የሚኒሻ አባላት አገዛዙ በሕዝባቸው ላይ ለሚፈፅመው ጭፍጨፋ ተባባሪ ከመሆን እንዲታቀቡ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያና ማሳሰቢያ ሲሰጣቸው የቆየ ቢሆንም፡ ነገር ግን ከዚህ ድርጊታቸው ሊቆጠቡ ባለመቻላቸው በመጨረሻም የቦምብ ሲሳይ ሆነው ቀርተዋል።
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት
አገዛዙ የአማራ ህዝብን አፍኖ ለመጨፍጨፍ የጀመረውን ማጥቃት በጽኑ ብሔራዊ አንድነት እንመክተዋለን !
የካቲት 03 ቀን 2018 ዓ.ም
የአብይ አህመደ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ ይፋዊ የዘር ማጥፋት ጦርነት ከጀመረ ሶስት ዓመታትን ሊደፍን ተቃርቧል። በእነኝህ ጊዜዎች ሁሉ የአማራ ህዝብ የታወጀበትን የዘር ማጥፋት ጦርነት በመመከት ህልውናውን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ ቀጥሏል። ሆኖም በህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀው አገዛዝ የገጠመውን ህዝባዊ ተጋድሎ ተረድቶ ጦርነት ከማቆም ይልቅ በእጁ የገቡትን የጥፋት መሳሪያወች ሁሉ ተጠቅሟል። በዓለም ታሪክ በማይታወቅ ሁኔታ በመንግስትነት ስም ቤተ መንግስት የከተመው አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ ስትራቴጅክ ድሮኖችን በመጠቀም በሽህ የሚቆጠሩ ንፁሃንን ጨፍጭፏል። ቱርክን ጨምሮ አዳዲስ የጦር መሳሪያ አምራች ሀገራት ያመረቷቸውን ድሮኖች በአማራ ህዝብ ላይ ይሞክሩ ዘንድ አብይ አህመድ እና አገዛዙ በጭካኔ ፈፅመውታል።
አገዛዙ የባህረ ሰላጤው ኃይሎችን ፖለቲካዊ ፍጥጫ ጎትቶ ሀገር ውስጥ በማስገባት በተላላኪነት በሚያገኘው ወታደራዊ እና የመረጃ ድጋፍ ተጠቅሞ በህዝባችን ላይ ያወጀውን የዘር ማጥፋት ጦርነት አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህም አገዛዙ ጌቶቹ በቀጠናው ላቀዱት የተልዕኮ ጦርነት አማራን ማጥፋትን እንደ መንደርደሪያ ቆጥሮ፣ በድጋፍ ያገኘውን የማጥፋት አቅም በሙሉ ተጠቅሞ በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎጃም እና በጎንደር የተለያዩ ቀጠናወች የስልክ እና የኢንተርኔት መሰረተ ልማቶችን በመዝጋት የተጠናክረ ጭፍጨፋ እያደረገ ይገኛል።
በተለይም በጥር ወር የመጨረሻ ሳምንት በሸዋ የአገዛዙ ሰራዊት የተለያዩ አሀዶች የኦሮምያ ልዩ ዞን ታጣቂወችን በመጨመር በሌሎች አካባቢወች ደግሞ በመደበኛወቹ እዞች እና የአየር ወለድ እና ኮማንዶ አሃዶቹ የከፈተው ማጥቃት በህዝባዊው የአፋብን ሰራዊት በሚገባ እየተመከተ ይገኛል።
ከየካቲት 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሰራዊታችን በተደረገው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በጎንደር ቀጠና በርካታ ጀብዱወች ተፈፅመዋል። በተለይም በደቡብ እና ማዕከላዊ ጎንደር የወረዳ ዋና ከተሞችን ጨምሮ በርካታ ይዞታወችን ከጠላት መንጠቅ ተችሏል። በዚህ አስደናቂ ተጋድሎ በሺወች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ሰራዊት በምርኮኛነት እና በፈቃዳቸው የወገንን ኃይል መቀላቀል ችለዋል። የወገን ሰራዊት በርካታ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያወች፣ ተተኳሾች እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶችንም መማረክ ችሏል።
በጎጃም ቀጠና አገዛዙ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ያሰማራበት የጃዊ አካባቢ ሰራዊታችን በወሰደው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ አገዛዙን ሰራዊት ጨምሮ በርከት ያለ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ከነተተኳሹ ከጠላት እጅ ተማርኳል።
እድል ባገኘ ግዜ ሁሉ ህዝብ ለመጨፍጨፍ የማያመነታዉን አረመኔ ሰራዊት በምርኮ፣ በድምሰሳ እና በማንኛውም መንገድ ከስምሪት ውጭ ማድረግ እና በእያለበት ውጦ ማስቀረት ሰራዊታችን በሚገባ እየፈጸመው ያለ ተልዕኮ ነው። ለዚህም የዘር ማጥፋት ጦርነቱ ዒላማ የተደረገው መላው የአማራ ህዝብ ለሰራዊታችን ያሳዬው ቁርጠኛ ደጀንነት በግምባር ለተገኙት ድሎች አስተዋጽኦው ትልቅ ነው። ሰራዊታችን በተቆጣጠራቸው የተለያዩ ከተሞች ህዝቡ ለሰራዊታችን የሞቀ አቀባበል ከማድረግ ባሻገር በመልሶ ማጥቃቱ የተገኙ ድሎች እንዲቀጥሉ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
እነኝህ ድሎች ይገኙ ዘንድ የድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መወለድ በሰራዊታችን እና በህዝቡ ዘንድ የፈጠረው አዲስ ወኔ እና መነቃቃት ለድሎቹ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በተጨማሪም የአደረጃጀት አንድነቱ አቅማቸንን አቀናጅተን በውጤታማ የሀይል አጠቃቀም በጠላት ላይ ወሳኝ ምት ለማሳረፍ በማስቻሉ ብሔራዊ አንድነቱ የዘር ማጥፋቱን ጦርነት ለመመከት ያለው እምቅ አቅም የታየበት ነው። ህዝብን ታግሎ ያሸነፈ አገዛዝ በታሪክ እንደሌለው ሁሉ የህዝብ ልጅ የሆነው ሰራዊታችን፣ የአማራን ህዝብ ሙሉ ድጋፍ ያገኘው ድርጅታችን አፋብን የብሔራዊ አንድነትን አቅም ተጠቅሞ በተሰላ እና በተጠናከረ ሁኔታ የህልውና ተጋድሎውን ለድል እንዲበቃ ሁሉም አመራሮች እና አባላት የተሰጣቸውን ሀላፊነት ለመወጣት በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ።
ሰራዊታችን እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ በተቆጣጠራቸው ቦታወች ሰላም እና ፀጥታን በማስከበር እና በወታደራዊ ጨዋናት ጠላትን ብቻ የለዩ ዒላማወች ላይ በማተኮር ተገቢውን ጥንቃቄ እያደረገ እንደሚቀጥል ለመላው የአማራ ህዝብ፣ ለኢትዮጵያዊያን እና ለዓለም አቀፋ ማህበረሰብ እናሳውቃለን።
በመጨረሻም በመልሶ ማጥቃት የተመከተው የአገዛዙ የጥፋት እጅ ዳግም በማያንሰራራበት ሁኔታ ይመታ ዘንድ መላው ሰራዊታችን እና ህዝባችን የሚያደርገውን ርብርብ አጠናክሮ እንዲቀጥል እናሳስባለን።
ሰማታ ይሆን እንዴ?
ቅንጭሪት አያሌው መንበሩ ምንም እንኳን ደቡብ ጎንደርን እንደ ጋሽ መንበሩ ማሳ እያየች እኔ ጎልጉዬ ካልዘራሁበት መሬት እያፈራም ወደማለቱ ደርሳ ነበር።
ይህች ቅንጭራም ከአርብ ገበያ አፈርናዋት ቀበሌ ተንደርድራ የወልቃይትን ሰሊጥ መዝገንን የመጨረሻ ህልሟ ያደረገች የከርሷ መናኝ ሰምታ ይሆን? ደቡብ ጎንደር የቅንጭሪትን አለቆች አርባ አለንጋ እየገረፉለት ነው። እንግዲህ እሪሪሪ በየ ቅንጭሪት! ለማነኛውም እኛ ከግንባር መሬት ላይ ያለውን እውነት አብረን ከትግል ጓዴቻችን ጋር እውነተኛው የፋኖ መርጃ ስናደርሳችሁ ከምንም በላይ ክብር ይሰማናል እና አላችሁን ወይ ቤተሰብ ይወዳጁን አንድ አማራ እስከ እለተ ምፃት ድርስ
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር ተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር ድልን ተቀዳጀ።
ዛሬ የካቲት 02/2018 ዓ.ም የተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር አካል የሆነችው ወልቃይት ብርጌድ አባሎች ከእስቴ ወረዳ መካነ እየሱስ ከተማ ተነስቶ ወደ ልዋየ እንቅስቃሴ ላይ የነበረን የአገዛዙ ኃይል ላይ እርምጃ የወሰደች ሲሆን፡በዚህም
01--------ዲሽቃ
01-------ብሬን
10-----ክላሽ ኮፕ
4------አብራረው
01------የድሽቃ አፈሙዝ
በርካታ ያልተቆጠረ ተተኳሽ ማርካ ታጥቃለች ሲል የኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል።
###
በአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በዛሬው ዕለት በደቡባዊ ጎንደር ዞን 2 ዲሽቃዎችን ከጠላት ማርኳል። በተመሳሳይ በላይ ዘለቀ ዕዝም 2 ዲሽቃዎችን በዚሁ ቀጠና ከጠላት ማርኳል። ጠቅለል ሲል 4 ዲሽቃ በሰሜን አማራ ቀጠና ናደቡባዊው አከባቢ ተማርኳል። ከዚህ በተረፈ የተማረከው ብሬን ፣ ስናይፐር ፣ ክላሽንኮቭ ገና በቆጠራ ላይ ያለ ሲሆን የተጣራ ውጤቱን ይዘን እንመለሳለን።
አራት ዲሽቃን ምርኮ ጨምሮ ጉድ የሚያስብሉ የድል መረጃወች ✊✊
፨ ጋይንት ሁለቱም ወረዳወች ነፃ ወጥተዋል። ትልቁ ማረሚያ ቤት ተሰብሯል። ከ 200 በላይ ክላሽን ጨምሮ ስናይፐርና መትረጊስ ተማርኳል።
፨ አርማጭሆ ማሰሮ ደምብ የነበረው ሚሊሻና አድማ ብተና ሙሉበሙሉ እጅ ሰጥቷል። በግሉ ደም ያለበት ተደ#ምስ#ሷል። በተመሳሳይም ከ 200 የሚበልጥ ክላሽ ተማርኳል።
፨ ጣቁሳ ድኩል አርባ ላይ ምሽጎቹ ፈራርሰው ተከቧል። እጅ ለመሴጠት እየተሰናዳ ነው።
፨ እስቴና ጋይንት ጫፍ ላይ ሌላውን መሳሪያና ተተኳሽ ትተነው አራት ዲሽቃ ተማርኳል። አራት ✊ ተራራው ራስ ጉና አንድ፣ እስቴ ዴንሳ ሁለት፣ ደጄን ብርጌድ አንድ ማርከዋል።
፨ በለሳ ያለው ሀይል ለቆ ሲወጣ ከጀርባው በተደረገበት ቆረጣ ከ 25 በላይ የሚሆኑ መካላከያ ከጥቅም ውጭ ሁነዋል። የተረፉት ማክሰኝት ገብተዋል።
ፋኖነት✊✊
አማራነት✊✊
ብሩህ ተስፋ✊✊
+2
የጀግንነትና የፅናት ተምሳሌቶች
የአማራ እናት "አምጣ የወለደቻቸው ጀግኖች አርበኛ ሽመልስ ንጉሴ እና አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ በጦር ሜዳ ውሎአቸው ብቻ ሳይሆን፣ በሁሉም ስብዕናዎች የተገነቡ እንደ እሳት የሚነድ የትግል ወኔ ቢኖራቸውም፣ ያ ወኔ በእውቀትና በአስተሳሰብ የተገራ ፈጣሪ የሰጣቸው የመልካምነትና የትሕትና ጸጋ ያላቸው፣ የሸዋ ፋኖ ጠንሳሾችና መሠረት ጣዮች እነዚህ አርበኞች ዛሬ ለደረሰው የፋኖ ትግል ስር የሰደደ መሠረት የጣሉ ጎልቶ የሚታይላቸው።
ትግሉ ገና በጅምር በነበረበት ግዜ ብዙዎች ግራ በሚጋቡበት ወቅት ሳይሰለቹና ተስፋ ሳይቆርጡ መዋቀራቸውን የበርሃው ቃጠሎ፣ የተራራው ቁልቁለት እና ብርዱ ሳይበግራቸው ለዓላማቸው የቆሙ
የጂኦግራፊያዊ የትግል ስፋት የጀግኖቹን የትግል አሻራ ከኤፍራታ እስከ ደራ፣ ከከሰም እስከ መንዝ ድረስ ባለው ስፋት የሕዝብን አንድነት በመፍጠርና ታጋዮችን በማደራጀት ረገድ የነበራቸው ትግላቸው በአንድ መንደር ያልተገደበ፣ መላውን የሸዋን ፋኖ ያነቃቃው የታሪክ ተተኪነት (የሚኒልክ ልጆች) የሚኒልክን ታሪክ እየደገሙ ያሉ የሸዋ አናብስቶች።
እንደ ዳግማዊ ምኒልክ ሁሉ ለሀገርና ለወገን ሉዓላዊነትና ክብር የሚቆሙ። መስዋዕትነትን በመክፈል ረገድ ወደ ኋላ የማይሉና የታሪክ አደራን የተረከቡ አርበኛ ሽመልስ ንጉሴ እና አርበኛኢሳያስ ደመቀ የፋኖን ትግል በፅኑ መሠረት ላይ እንዲቆም ያደረጉ፣ በሰውነት ባህሪያቸው የተመሰገኑ እና በጀግንነታቸው የጥንቱን ታሪክ ያደሱ የዘመኑ ጀግኖች ናቸው ይቀጥላል ....!
+2
ታጭዶ የተከመረው የጠላት መሳሪያ‼️‼️
በዛሬዉ ዕለት ፓዊ ወረዳ መንደር 21 ቀበሌ የተማረኩ የጦር መሳሪያ በከፊል !!!
በመተከል አዉራጃ ፓዊ ወረዳ ፋኖ የተቆጣጠራቸዉ ቀበሌዎች መንደር 29፣28፣12፣11፣26፣24፣17፣21 ናቸዉ።
አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ-ዕዝ 105ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
