ch
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
2 966
订阅者
+424 小时
+127 天
+38830 天
帖子存档
በ74ኛ ክ/ጦር ስር በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ አውጃ ንዑስ ከተማ ሚያዚያ 29 ህዝባዊ ውይይት ተደረገ። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ግንቦት 01/2018 ዓ.ም በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ
+3
በ74ኛ ክ/ጦር ስር በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ አውጃ ንዑስ ከተማ ሚያዚያ 29 ህዝባዊ ውይይት ተደረገ። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ግንቦት 01/2018 ዓ.ም በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ የሆነ ህዝባዊ ውይይት ተደርጓል፦ 👉.የአብይ ዓህመድ የይስሙላ ምርጫ 👉.በህዝባችን እና በፋኖ መካከል ያለው ግንኙነት ምን እነደሚመስል 👉.የፋኖ ተጋድሎ ግስጋሴ እና የደረሰበት ተቋማዊ ዕድገት ደረጃ 👉 በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ወዘተ ጉዳዮች የቀረቡ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ ከተወያየ በኃላ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ የክ/ጦሩ አመራሮች እና የወረዳው ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች መልስ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮርህ/ግንኙነት

propoganda(ፕሮፖጋንዳ) አንድ የትግል ሥልት ነው ልክ እንደታጠቅነው መሣሪያ ነገር ግን መሣሪያውን በትክክል ሎድ ሞልተን በሚገባ ጠላት ላይ አነጣጥረን ካልተኮሥነው እና በእንዝህላልነት ከያዝነው
propoganda(ፕሮፖጋንዳ) አንድ የትግል ሥልት ነው ልክ እንደታጠቅነው መሣሪያ ነገር ግን መሣሪያውን በትክክል ሎድ ሞልተን በሚገባ ጠላት ላይ አነጣጥረን ካልተኮሥነው እና በእንዝህላልነት ከያዝነው ጠላትን መታት ቀርቶ እራሣችንን ተባርቆ ሊመታን እንደሚችል ሁሉ ፕሮፖጋንዳም በአግባቡ በመረጃ ሠዎች ተተንትኖ፤ በፖለቲካ ሠዎች ተቃኝቶ፤በሥነልቦና ምሁራን ተፈትሾ እና በሥትራቴጂሥቶች ተጠንቶ ካልሆነ ይባረቅብናል። ሥለዚህ ከመሣሪያ መባረቅ መጠንቀቅ እንዳለብን ሁሉ ከ counter ፕሮፖጋንዳም መጠንቀቅ ቁልፍ ጉዳይ ነው። ቢዛሞ ሚዲያ   01/09/2018 ዓ.ም

አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር የተሰጠ ማብራሪያ ======🌳🌳🌳========= "መሪን በማዋከብ የአማራን ትግል መሪ አልባ የማድረግ ተልዕኳችሁን አውቀናል አትችሉም" ጎንደር ካለፈው ስህተቱ የማይማር ብዙ ሰርጎ ገብ የሜጀር ጀኔራል ከፊያለው ደሴ የሜጄር ጀኔራል ውባንተ አባተ የማዋከብ አባዜ አልበቃቸው ብሎ ዛሬም እንደ እብድ ውሻ ያገኙትን ሁሉንም የሚናከሱት አሁንም እንደ አይን ብሌናችን የምናየውን ሜጀር ጀኔራል ተሾመ አበባውን ; ሌሎች አመራሮችን እና የሚመራውን 204ኛ ኮርን የማዋከብ እና ያልሆኑ ስሞችን በማህበራዊ ሚዲያ የማሰራጨት ተግባር እያየን ነው። በእርግጥ በፌክ አካውንት ለሚንጫጫ መልስ መስጠት የማያውቁት ሀገር እንደመናፈቅ ይሆናል። ነገር ግን መላው ህዝባችን እና ደጋፊያችን ያለሆነ ውዥንብር ውስጥ እንዳይገባ ሀቁን በመግለጫ ማሳወቅ አስፈላጊ ሁኖ አግኝተነዋል!! ስለሆነም 1/ እንደሚታወቀው 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ተቋማዊ አሰራሩን በመጠበቅ ባለፉት ጊዚያት ለተከታታይ ቀናት ውይይቶችን እና ግምገማወችን ስናደርግ መቆየታችን ይታወቃል!! ከውይይታችን በኃላም ኮሩ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በኮሩ ስር ያሉ ክፍለ ጦሮችን ; ብርጌዶችን; ሻለቃወችን በያሉበት አካባቢ እየተንቀሳቀስን ያሉበትን ቁመና የማየት እና የማደረጃጀት ስራ እየሰራን  እንገኛለን! ነገር ግን ይሄን የትግል እንቅስቃሲያችን በማይሆን አረዳድ የተረዱ አንድነትን የማይፈልጉ;  መገለጫቸው የሌብነት; የግድያ እና የዕገታ የሆኑ ሀይሎች ተቋምን መጠጊያ በማድረግ ባስቀመጧቸው የሚዲያ ሰራዊቶች በኩል  የሀሰት ዘመቻ የከፈቱብን መሆኑን ህዝባችን እንዲያውቅልን። 2/ እነዚህ ግለሰቦች ከዚህ በፊት በዕትጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር ስር ሁነው አባል ገለው የቡድን መሳሪያ ብሬን ; ስናይፐር እንዲሁም ነብስ ወከፋ መሳሪያወችን የወሰዱ  መሆናቸው ምን አልባት ወገን ጋር አንተኩስም ተቋም ተሰርቶ ወጥ የሆነ የዕዝ ሰንሰለት ከተጠበቀ  ሁሉንም አንድነት ከመጣ በኃላ መፍትሄ ይኖረዋል ብለን በማሰብ ዝም ብለን ቆይተናል። ነገር ግን ከዚህ በፊት የሰሩት ወንጀል ያስጠይቀናል ብለው በማሰባቸው ዘላለም ጎንደር አንድ እንዳይሆን አንድነትን የሚፈልጉ መሪወችን ማዋከብ; ተቋማዊ አሰራርን አለማክበር; ሁሌም የሽፍትነት ስራ በመስራት የግል ፍላጎትን ማሟላት ግባቸው ያደረጉ መሆናቸው መላው ህዝባችን የሚያውቀው ሀቅ ነው!! 3/ ከዚህ በፊት ሜጀር ጀኔራል ተሾመ አበባው በሚመራው ጦር ስር ሁነው እርሱ ባስታጠቃቸው መሳሪያ በተደጋጋሚ እትጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር ባለችበት ቀጠና እየተንቀሳቀሱ በተደጋጋሚ አባል ገለው መሳሪያ የወሰዱ  የእሩቁን ወንጀላቸውን ህዝብ የሚያውቀውን እንተወውና በቅርቡ ሰለማያ ሁለት ስው በመግደል ገላ ማጠቢያ ሁለት ሰው በመግደል!!  ያለምንም ምክንያት ቄስ ሳይቀር በግፍ የሚገድሉ; የሚዘርፋ መሆናቸው ከብዙወቹ ውስጥ ትንሾቹ ወንጀሎች ናቸው። ይሄ ሁሉ ግፍ በታጋያችንም በህዝባችንም ላይ ሲፈጸም ለትግሉ እና ለአንድነቱ ሲባል ችግሩን በተቋም ይፈቱታል በሚል በሆደ ሰፊነት መቆየታችን ህዝባችን የሚያውቀው ሀቅ ነው። ይሄ ሁሉ ድርጊት ሲፈጸም ዝም ያልነው ሳይሰማን ቀርተን ሳይሆን ኮራችን 204ኛ ኮር ትላንትም ወገን ላይ አልተኮሰም ዛሬም አይተኩስም  ነገም እንደማይተኩስ እርግጠኞች ስለሆን እና ተቋማዊ አሰራርን ስለምናምን  መሆኑ ህዝባችን እንዲያውቅልን 4/ እንደ ጎንደር በላይ ዕዝ ላይም ይሁን 5ኛ ኮር ላይም ያለውን ችግር በራሳቸው ተቋማዊ በሆነ አካሄድ እንዲፈቱ በተደጋጋሚ በተለይ በኮሩ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ተሾመ አበባው በኩል ሁሉም አይነት ጥረቶች እያደረገ መሆኑ እነሱ ራሳቸው አይክዱም። ነገር ግን የራሳቸውን የተቋም ችግር መፍታት አልችል ሲሉ ሌላ ጥፋተኛ ፍለጋ ለስራ በተንቀሳቀስንበት ሁሉ የራሳቸው ጥፋት እና ወንጀል አላስቀምጣቸው ሲል 204ኛ ኮር አሳደድን ; አፈነን; እና ሌሎች ሌሎችም ስም ማጥፋቶች ፍጽም በሬ ወለደ እና ሀሰተኛ የሆኑ መሆናቸውን መላው ህዝባችን እንዲያውቅ! 5/ በመጨረሻም መላው ህዝባችን እንዲያውቅልን የምንፈልገው  በትላንትናው ዕለት በ29/08/18 ዓ.ም 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር በሜጀር ጀኔራል ተሾመ አበባው እና ሌሎች አመራሮች እየተመራ ክፍለ ጦሮችን ለመደገፍ እየተንቀሳቀስን ባለንበት ማንደፍሮ ተሰማ (ባለ አምስት ስሙ); ጌታቸው መኩሪያ; ሰለሞን;  ናትናኤል, ሲራክ, ዮናስ አያልቅበት; በላያ ጌቴ; ጌታየ እሱባለው ክፍለ ጦር ይሁኑ ሻለቃ ይሁኑ መሪያቸው ማን ይሆን የማይታወቁ ሽፍቶች በስሩ ያለውን አባል በማያውቀው በማወናበድ  የከፊ  የውባንተ አልበቃ ብሎ ዛሬም በሜጀር ጀኔራል ተሾመ አበባው ላይ እሱ ባስታጠቃቸው መሳሪያ መንገድ በመዝጋት ተኩስ ከፍተውበት አምሽተዋል። በእርግጥ እነሱ ያደረጉትን ማድረግ በጣም ቀላል ነበር ። ነገር ግን ጉዳዩን በብስለት በማየት ትላንትም አልተኮስን ዛሬም አንተኩስ ብሎ በማመን አቅጣጫ ቀይረን እነሱን ያሉበት ቦታ ንቆ በመተው  በሌላ አቅጣጫ የተባለው ቦታ ላይ ደርሰን የኮራችን ተግባር እየፈጸምን እንገኛለን። ይሄን የትግል እንቅስቃሲያችን በተቃራኒ በመገልበጥ ያልሆነ ስም በመስጠት ወከባ መፈጸም መሪወችን ማወከብ እናንተ ካለፈው ስህተት ላትማሩ ትችላላችሁ እኛ ግን ተምረንበታል አትድከሙ። መሪን የማወከብ የተለመደ ተግባራችሁ ነገም ልትደግሙት እንደምትችሉ እናምናለን። እናንተም ተንጫጩ እኛም ስራ ላይ ነን ህዝባችንም እውነቱን ያውቃል። 6/ ከዚህ በኃላ በኮራችን ስር ያሉ ክፍለ ጦሮችን ; ብርጌዶችን; ሻለቃወችን እንዲሁም ማህበረሰበችን ላይ በማንኛውም ሁኔታ ትንኮሳ ለሚያደርግ አካል እራሳችን የመከላከል  ተፈጥሯዊ መብታችን ለመጠቀም የምንገደድ መሆኑን  እንዲሁም ማህበረሰባችን ያለ አግባብ ማህበራዊ እረፍት መንሳት እኩል የምንታገለው ተግባር መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለህዝባችን ለማሳወቅ እንፈልጋለን። N.B:-  በመጨረሻም እንደነ ሜጀር ጀኔራል ከፊያለው ደሴ እንደነ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ መሪን በማዋከብ ሜጀር ጀኔራል ተሾመ አበባውንም የዚሁ ሰላባ ለማድረግ የምትፍጨረጨሩ ማንነታችሁ የማይታወቅ ሰርጎ ገቦች በጎንደር ላይ እየዘራችሁት ያለውን መርዝ አውቀንባችኋል አይሳካላችሁም ። "መሪን በማዋከብ የአማራን ትግል መሪ አልባ ማድረግ ከዚህ በኃላ አትችሉም" አንድነታችን እያጸናን ልዩነታችን እያጠበብን ድላችን ቅርብ እናደርጋለን!! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር!!

#አሳረኛው_ምኒሊክ_ዕዝ‼️ በምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር የ49ኛ ክፍለጦር አብሪዎች በራያ ቆቦ ወረዳ ሮቢት ከተማ ላይ ዛሬ አመሻሹን በወሰዱት እርምጃ የወደመ የጠላት ብልፅግና ተሽከርካሪ‼️ ዛሬ ሚያዚያ 30/2018 ዓ/ም አመሻሹን ከቆቦ ወደ ወልድያ ሲጓዙ በነበሩ የብልፅግና አመራሮች ላይ በሮቢት ከተማ ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል። 30/ዐ8/2018 ዓ.ም

#አፋብን_ሸዋ_ጠቅላይ_ግዛት_አሳምነው_ዕዝ✅ #አፄ_ዘርዓ_ያዕቆብ_፩ኛ #ኮር✅✅ #ነጎድጓድ_ክፍለጦር✅✅✅
+2
#አፋብን_ሸዋ_ጠቅላይ_ግዛት_አሳምነው_ዕዝ✅ #አፄ_ዘርዓ_ያዕቆብ_፩ኛ #ኮር✅✅ #ነጎድጓድ_ክፍለጦር✅✅✅

ሰበር ዜና! በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ሮቢት 01 ቀበሌ 49ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ ጠላት ላይ ከባድ ጥቃት በመፈፀምና አመራሩን ከነ ፓትሮሉ በመማረክ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: አፋብን ወሎ (ቤተ- አማራ) ምኒልክ ዕዝ  ምስራቅ አማራ የ102ኛ ኮር አካል የሀነው የ49ኛ ክፍለጦር ቃኝ በሮቢት ከተማ በቅርብ ርቀት ከቀኑ 11:00 መሀል አስፓልት ላይ በወሰደው መብረቃዊ ጥቃት እንድ የብልፅግና ሆድ አደር የፋይናንስ ሀላፊ እንድሁም አንድ የመኪና ሹፌርን ጨምሮ ተማረከ። የ49ኛ ክፍለጦር ቃኝ አናብስቶች በወሰዱት ድንገተኛ ጥቃት በቁጥጥር ስር የዋለውን የጥላት ላንድ ክሎዘር መኪና ሙሉ በሙሉ በማቃጠል ከጥቅም ውጭ አደረጉ። የአብይ አህመድ አምባገነኑ አገዛዝ  የአማራ ፋኖን አጥፍቻለሁ በማለት የተሳሳተ ውጅንብር በአማራ ህዝብ  ላይ በመንፋት ምርጫ ለማካሄድ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ ቢሆንም የህዝብ ልጅ ፋኖ በተግባር እያንበረከከው ይገኛል። በመጨረሻም የብልፅግና እብሪተኛና የፋሽስቱ አገዛዝ ላይ የአማራ ህዝብ የነፃነት፣ የእኩልነት፣የፍትሐዊነትና የህገ-መንግስት ጥያቄ በወርድና በቁመቱ ልክ የፖለቲካ ውክልና እስኪመለስ ድረስ የተጠናከረ የደፈጣና የፊት ለፊት ውጊያዎችን እንደሚያደርጉ የ49ኛ ክፍለጦር ዋና ወታደራዊ አዛዥና ዘመቻ መሪ ገልፀዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም

+2
የብልጽግና ግፍ!!

🧨በምርጫ ስም የሚነገድ ደም፦ የሽሮ ሜዳው ግድያና የብልጽግና "ነፃ እርምጃ"! (ሙሉጌታ አንበርብር) አገዛዙ "ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አደርጋለሁ" እያለ በየመድረኩ በሚያላግጥበትና የውሸት ትርክት በሚያመርትበት በዚህ ሰዓት፣ መሐል አዲስ አበባ ላይ ግን ዜጎችን አድኖ የመግደል "ነፃ እርምጃ" በይፋ ተጀምሯል። ዛሬ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት፣ የሥርዓቱን አምባገነንነትና የሕግ አልባነቱን ጥግ ለዓለም ያሳየ ሌላው ጥቁር ጠባሳ ሆኖ ተመዝግቧል። ወጣት ተገኝ ባልቻ (በቅፅል ስሙ ኦሮሮ) የተባለው የሽሮ ሜዳ ነዋሪ፣ በፖሊስ ተይዞ ከተወሰደ በኋላ በሕግ ጥላ ስር ሆኖ ሊጠበቅ ሲገባው፣ እዚያው ጽሕፈት ቤቱ በር ላይ በአራት ጥይት ተደብድቦ እንዲገደል ተደርጓል። ይህ ድርጊት "ሕግ ማስከበር" ሳይሆን በጠራራ ፀሐይ የተፈጸመ የመንግሥት ሽብር ነው። አንድን ዜጋ በቁጥጥር ስር ካዋሉ በኋላ ፍርድ ቤት ከማቅረብ ይልቅ፣ በፖሊስ ጣቢያ ደጃፍ ላይ በጥይት መረሸን፣ አገዛዙ ከሕግ በላይ መሆኑንና ለሰው ልጅ ሕይወት ቅንጣት ታክል ክብር እንደሌለው ማረጋገጫ ነው። የሚገርመው ግን፣ ይህ ግድያ የተፈጸመው ሥርዓቱ "ምርጫ እያካሄድኩ ነው" በሚል ዓለምን ለማታለል በሚሞክርበት ወቅት መሆኑ ነው። በምርጫ ስም የሚነገድ ፖለቲካና በየመንገዱ የሚፈስ የዜጎች ደም አብረው ሊሄዱ አይችሉም። ወጣት ተገኝ ባልቻ የተገደለው በፈጸመው ጥፋት ሳይሆን፣ አገዛዙ በሕዝብ ላይ የጀመረው የማሸማቀቅና የኃይል እርምጃ ሰለባ በመሆኑ ነው። "ነፃ እርምጃ" በሚል ስም በከተማው ወጣቶች ላይ እየተወሰደ ያለው ግድያ፣ የሥርዓቱን የመጨረሻ የውድቀት አፋፍና የጭንቀት መግለጫ መሆኑን ልንረዳ ይገባል። ይህ በሽሮ ሜዳ የፈሰሰው ደም፣ አገዛዙ ስለ ሰላምና ስለ ልማት የሚያወራው ወሬ ሁሉ መሠረት የሌለው መሆኑን ይመሰክራል። መሐል አዲስ አበባ ላይ ዜጎችን በፖሊስ ጣቢያ ደጃፍ የሚረሽን ሥርዓት፣ ነገ ደግሞ ወደ ማንኛው ቤት ገብቶ ጥይት እንደማያዘንብ ምንም ዋስትና የለም። የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህንን በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎችን የመረሸን አደገኛ አካሄድ በጽኑ ሊያወግዘው ይገባል። ወጣት ተገኝ ባልቻ የዛሬው የብልጽግና መሥዋዕት ቢሆንም፣ የፈሰሰው ደሙ ግን የግፈኞችን ዕድሜ የሚያሳጥር እንጂ የሚያራዝም አይሆንም። በምርጫ ስም እያላገጡ ዜጎችን መግደል የታሪክ ተጠያቂነትን ያስከትላል። ለወዳጅ ዘመዶቼ መጽናናትን እመኛለሁ፣ ፍትሕ ለወጣት ተገኝ ባልቻ! ፍትሕ በግፍ ለሚገደሉ የኢትዮጵያ ልጆች!

የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር በተጉለት አውራጃ ግፍት ክላስተር የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሰራተኞች ጋር ውይይት ተደረገ!! በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ
+8
የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር በተጉለት አውራጃ ግፍት ክላስተር የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሰራተኞች ጋር ውይይት ተደረገ!!   በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል! በሚል መሪ ቃል ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አስምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የአገልግሎት ሰጭ ሰራተኞች የውይይት መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ማካሔዱን አጠናክሮ ቀጥሏል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ የቀረበ ሲሆን የጤና ባለሙያዎች፣ የግብርና ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ እና የማህበራት ተጠሪዎች በንቃት ተሳትፈውበታል ። አማራን ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ሰብሮ ለመውጣት የአገልግሎት ሰጭ ሰራተኞች ሚና በጉልህ የሚገለጽ ሲሆን ትግሉን በተባበረ ክንድ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል ። ክብር ለትግሉ ሰማዕታት ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !! ማያዚያ 30/2018 ዓ.ም ​የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

መሐል አዲስ አበባ ላይ "ነፃ እርምጃ" ተጀምሯል። ይህ ዛሬ አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ በፖሊስ ተይዞ ከተወሰደ በኃላ እዚያው ፅ/ቤቱ በር ላይ በአራት ጥይት ተመቶ የተገደለው ወጣት ተገኝ ባልቻ በቅፅል ስ
መሐል አዲስ አበባ ላይ "ነፃ እርምጃ" ተጀምሯል። ይህ ዛሬ አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ በፖሊስ ተይዞ ከተወሰደ በኃላ እዚያው ፅ/ቤቱ በር ላይ በአራት ጥይት ተመቶ የተገደለው ወጣት ተገኝ ባልቻ በቅፅል ስሙ ኦሮሮ የተባለ የሽሮ ሜዳ ወጣት ነው።

ሰበር!! ''የተከዜ ዘብ በሚል መጠሪያ አገዛዙ በወልቃይት ምድር ያደራጀዉ የሚሊሻ ኃይል ትላንት ምሽት በቀጠናዉ በሚንቀሳቀሰዉ የፋኖ አደረጃጀት ላይ ትን*ኮሳ ፈፅሟል። @አርበኛ ፋኖ ሲሳይ አሸብር

የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነዉ ዕዝ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የነጎድጓድ ክፍለ ጦር ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ የተሃድሶ ቃል-ኪዳን አደረገ!! ​የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነዉ ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር የተሰውትን አመራሮችን የ40ቀን መታሰቢያ እና ጥልቅ የተሃድሶ ፕሮግራም የዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ፣የኮር አመራሮች እና የክፍለ ጦር አመራሮች በተገኙበት “ደማችሁ መንገዳችን ነው” በሚል የነጎድጓድ ክፍለ ጦር ተሃድሶ አድርጓል። ​ከጊዜ ወደ ጊዜ ራሱን እንደ ንስር በወታደራዊ ሳይንስ እና በወታደራዊ ስልት እንዲሁም በዘመናዊ የጦር መሣሪያ ትጥቅ ራሱን እያዘመነ የሚገኘው የነጎድጓድ ክፍለ ጦር እንደ ብረት የጠነከረ ፅናቱን ፣ህዝባዊነቱን እና አማራዊነቱን ዳግም በተሃድሶ አረጋግጧል። የነጎድጓድ ክፍለ ጦር የአማራን ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥና ለማስከበር እንዲሁም የነገውን ብሩህ ተስፋን በመሠነቅ የነገውን ድል ለማብሰር የሚያስችለውን ጥልቅ ወታደራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ተሀድሶ አድርጓል። ​በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነዉ ዕዝ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ስር የሚገኘው የነጎድጓድ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች እና መላው ሠራዊት ላለፉት ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩትን ስልጠና እና ተሀድሶ በአዲስ መንፈስ ቃላቸውን አድሰዋል። በዚህ የተሀድሶ መድረክ ላይ አመራሩ ለለውጥ ያለውን ታማኝነት ፅናትና ቁርጠኝነት በተግባር አሳይተዋል። የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አርበኛ ኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋን ጨምሮ ሌሎች የዕዝ አመራሮችም በተሀድሶው ላይ ተገኝተዋል። ​ከፍተኛ አመራሮች ባስተላለፉት መልዕክት ክፍለ ጦሩ በተለያዩ የውጊያ አውደ ግንባሮች የአስመዘገባቸው አኩሪ ድሎች ከመከላከል አልፎ ወደ መደበኛ የማጥቃት ለተደረገው ለውጊያ ስልት ሽግግር ትልቅ ማሣያ መሆኑን አብራርተዋል። ያለፈውን ከፍተኛ መተኪያ የማናገኝላቸውን አመራሮቻችንን የበላብንን ያን ክፉ ጊዜ እንደ ትልቅ መማሪያ በመጠቀም ለወደፊቱ በግልፅ አላማ ፣ራዕይና በማይበገር ወታደራዊ ስነ-ልቦናን ሰንቀን የወንድሞቻችን ደማቸው ለእኛ መንገዳችን ነው በሚል ቃል ኪዳን በመግባት ቆረጠን ተነስተናል። ይህ ተሀድሶ የአማራን ህዝብ ክብር እና የአመራሮቻችንን ደም ለመመለስ የገባነው ዳግም ቃል-ኪዳናችንን የአደስንበት ነዉ።​የክፍለጦሩ ሠራዊት ከባለፈው የውጊያ ተሞክሮ በመማር ይበልጥ በታጠቀ ወታደራዊ ሳይንስ እና ከብረት በጠነከረ ወታደራዊ ስነ-ልቦና እንደረን እና እንዲገነባ ላደረጉት የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች የክፍለ ጦሩ አባላት ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የድርጅታችንን ግብ በአጭር ጊዜ ለማሣካት በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ሠራዊቱ በአንድ ሳንባ ሊተነፍስ እንደሚገባው እና ጠላታችን የሸዋ ምድር በብሎም የአማራ ምድር እሳት እንዲሆንበት እናደርገዋለን። ​እኛ የነጎድጓድ ክፍለ ጦር ሰራዊቶች ለሸዋ እና ለአማራ ህዝብ ክብር እና ነፃነት ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ቃላችንን አድሰናል። በማለት የአላቸውን ዝግጁነት በመግለፅ የተሀድሶ መድረኩ ተጠናቋል። ​ክብር ለትግሉ ሰማዕታት ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ! አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም

ከምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተሰጠ መግለጫ ሚያዚያ 30/2018ዓ.ም --------------------------------------------------------------------- "በምርጫ ሰበብ ያለአግባብ የታፈኑ 7 የኮሌጃችን መምህራን እና 28 የተቋማችን ተማሪዎች በምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የደህንነት ሰዎች በትናትናው ዕለት ከኮሌጁ ቅጽር ግቢ ተወስደዋል። የትምህርት ተቋማት ለማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማስፈፀሚያነት እንደማይውሉ እየታወቀ በአለፉት 30 ቀና ውስጥ በኮሌጁ ግቢ ተማሪዎችን ፣መምህራን እንዲሁም የአስተዳደር ሰራተኞች በግዳጅ ከ5-7 የሚደርስ የምርጫ ካርድ በተለያዩ ስሞች እንዲያወጡ በመገደዳቸው ተቋማችን ይህ ተግባር እንዲቆምለት ለሚመለከተው አካል ማቅረባችን የሚታወስ ነው። በተደጋጋሚ በተጻፈልን ደብዳቤ መሰረት በኮሌጁ ውስጥ የምርጫ ካርድ የወሰዱ እና ያልወሰዱ መምህራን ፣ሰራተኞችና ተማሪዎችን ለይተን ሪፖርት እንድናቀርብ በመጠየቃችን ሒደቱ የአልተገባ እና ህገ-ወጥ በመሆኑ ተቋሙ በምርጫ ሒደቱ በቀጥታ እንዲሳተፍ እየተገደደ መሆኑን ለሚመለከተው አካል ብናሳውቅም አጥጋቢ ምላሽ በማጣታችን ምርጫ ካርድ የወሰዱ እና ያልወሰዱ መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎችን ለይተን በስም ዝርዝር ማሳወቃችንም የሚታዎስ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቀን 29/2018 ዓ.ም የብልጽግና ፓርቲ በደብረ ማርቆስ ከተማ በጠራው የምርጫ ቅስቀሳ አልተሳተፋችሁም፤ የምርጫ ካርድም አላወጣችሁም፤ የተባሉ 7 የኮሌጃችን መምህራን እና 28 ተማሪዎቻችን በደህንነት ሰዎች ታፍነዋል። በመሆኑም በተደጋጋሚ ኮሌጁን ለምርጫ ማስፈፀሚያነት ከመጠቀም ባለፈ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ሲንገላቱ ቆይተዋል። የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ እንዲንቀሳቀስ መደረጉን አጥበቀን እየተቃወምን በቁጥጥር ስር የዋሉ መምህራን እና ተማሪዎቻችን እንዲለቀቁልን እንጠይቃለን። መላ ህዝባችንም ከተቋሙ ጎን እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን ። የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

በአገዛዙ በአስገዳጅ ሁኔታ ተገደው ስልጠና እየወሰዱ የነበሩ አምስት ህፃናት አገዛዙን በመክዳት 64ኛ ክ/ጦር እየተቀላቀሉ ይገኛሉ። የአብይ አህመድ አገዛዝ የሚዘው የሚጨብጠው አጥቷል። 64ኛ ክ/ጦር
+4
በአገዛዙ በአስገዳጅ ሁኔታ ተገደው ስልጠና እየወሰዱ የነበሩ አምስት ህፃናት አገዛዙን በመክዳት 64ኛ ክ/ጦር እየተቀላቀሉ ይገኛሉ። የአብይ አህመድ አገዛዝ የሚዘው የሚጨብጠው አጥቷል። 64ኛ ክ/ጦር በሚያስተዳድረው ቀጠና እነማይ እና ሸበል በረንታ ህፃናትን ለጦርነት ለመማገድ በአስገዳጅ ሁኔታ አፈና በማድርግ የለብ ለብ ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት ፖራ ኮማንዶ እያለ በውሸት ፕሮፖጋንዳ ቢያሰራጭም በአስገዳጅ ሁኔታ የገቡት ህፃናት አገዛዙን በመክዳት ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቅለዋል። ከእነዚህም ውስጥ:- 1ኛ.እንቻለው ዘውዱ የትውልድ ቦታ አያልፉሽ ፖራ ኮማዶ 2ኛ.ኤርሚያስ ሚሊሻ ከየትመን ንዑስ ከተማ 3ኛ.ጥልጣል መስፍኔ ፖራ ኮማንዶ የትመን ንዑስ ከተማ 4ኛ.አትመን በላቸው ከሸበል በረንታ መርገጭ 01 ጥምር ጦር አንድ ኮሪያ ክላሽ ከ60 ጥይት ጋር 5ኛ.በልስቲ ገብሬ ፖራ ኮማንዶ ቲም መሪ የቀብሀና ተወላጅ የ15 ዓመት ህፃን ሲሆን የ2ኛ ዙሪ ፓራ ኮማንዶ ለ45 ቀናት ስልጠና የወሰዱ አገዛዙን በመክዳት 64ኛ ክ/ጦር እየተቀላቀሉ ይገኛል።       ሚያዚያ 30/02018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት