ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
4 478
订阅者
+824 小时
+657 天
+91030 天
帖子存档
የወልድያ ካድሬ ባሁን ሰዓት እሳት እየዘነበበት ነው! ከንጋት ጀምሮ በከተማዋ ከባድ ትንቅንቅ እየተደረገ ነው። ትናንት አገዛዙ ወልድያ ላይ ትልቅ የስም ማጥፋት ድግስ ደግሶ ነበር። የከተማዋ ካድሬዎች
የወልድያ ካድሬ ባሁን ሰዓት እሳት እየዘነበበት ነው! ከንጋት ጀምሮ በከተማዋ ከባድ ትንቅንቅ እየተደረገ ነው። ትናንት አገዛዙ ወልድያ ላይ ትልቅ የስም ማጥፋት ድግስ ደግሶ ነበር። የከተማዋ ካድሬዎች ከክልሉ ፀጥታ ቢሮ በተሰጣቸው ቀጥተኛ ትዕዛዝ ከሐራ ወደ ወልድያ ተመልሰው የመስቀል ደመራ በዓልን ከሕዝቡ ጋር ተቀላቅለው እንዲያከብሩና ወልድያ ሰላም ናት የሚል ፕሮፖጋዳ እንዲሰሩ በታዘዙት መሠረት ወልድያ ላይ ተገኝተው ነበር። ፋኖም ካድሬዎቹን ለመምታስ በምወስደው እርምጃ በዓሉን ለማክበር አደባባይ የወጡ የክርስትና እምነት ተከታይ ምዕመናን ይደናገጡብኛል፣ በሚል "ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ" ስልት ተጠቅሞ ውሏል። ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን አክብሮ ወደ ቤቱ እስኪመለስ ድረስም ተኩስ አቁሞ ነበር። ነገር ግን ዛሬ ከንጋት ጀምሮ ድጋሚ በከፈተው ማጥቃት የከተማዋን አንድ ሦስተኛ በቁጥጥሩ ስር አስገብቷል። በከተማዋ ጉቦ፣ ከፊል መቻሬ፣ኬላ፣ ጎንደር በር፣ አደንጉር፣ መብራት ኃይል፣ ሌሎች የከተማዋ አከባቢዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብተዋል። ውጊያው ቀጥሏል። ትናንት ከክልሉ ፀጥታ ቢሮ በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ከሐራ ወደ ወልድያ ተመልሰው የነበሩ ካድሬዎች እጅ ከፈንጅ እየተያዙ ነው።

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ወድ የትግል አጋሮቸ እነዚህ ዲሁም ደጋፊዎች በሙሉ አማራዊያን ቤተሰቦቼ
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ወድ የትግል አጋሮቸ እነዚህ ዲሁም ደጋፊዎች በሙሉ አማራዊያን ቤተሰቦቼ

🔥#መረጃ_ሰሜን_ኮርያ_ወልድያ‼️ ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ፬ኛ ቀን ተጠናክሮ በበርካታ ግምባር የቀጠለ ሲሆን ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ የሰሜን ወሎ መናገሻ የሆነችው #ወልድያ (#ሰሜን_
🔥#መረጃ_ሰሜን_ኮርያ_ወልድያ‼️ ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ፬ኛ ቀን ተጠናክሮ በበርካታ ግምባር የቀጠለ ሲሆን ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ የሰሜን ወሎ መናገሻ የሆነችው #ወልድያ (#ሰሜን_ኮርያ ) ላይ ሞርተር እያጓራ ፣ ዲሽቃ እያሽካካ ፣ ክላሽ እንደ እርችት እየንጫጫ ምድሪቷ #ምድራዊ_ሲኦል ሆናለች ሲሉ አናብስቶች ለንስር አማራ ገልፀዋል። በምድር ሜካናይዝድ ጦር እየደበደበ ሲሆን በሰማይ #ድሮን ቀጠናው እያሰሰ ይገኛል ይሁን እንጅ ጀግኖቻችን በእሳት ተፈትነው ያለፉ ናቸውና ወይ ንቅንቅ💪 ትንቅንቁ የቀጠለ ሲሆን በከባድ መሳሪያ ወልድያ ከተማ ዙሪያ ቤቶች እየወደሙ ነው ንፁሀን እየተገደለ ነው። ድሮንም አጠናክሮ ድብደባ ሊፈፅም ስለሚችል ህዝባችን በዓልን ምክንያት በማድረግ መሰባሰብ እንዳይኖር ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን 17/ዐ1/2018 ዓ.ም

የወልድያ ካድሬ ባሁን ሰአሁ እሳት እየዘነበበት ነው! ከንጋት ጀምሮ በከተማዋ ከባድ ትንቅንቅ እየተደረገ ነው። ትናንት አገዛዙ ወልድያ ላይ ትልቅ የስም ማጥፋት ድግስ ደግሶ ነበር። የከተማዋ ካድሬዎች
የወልድያ ካድሬ ባሁን ሰአሁ እሳት እየዘነበበት ነው! ከንጋት ጀምሮ በከተማዋ ከባድ ትንቅንቅ እየተደረገ ነው። ትናንት አገዛዙ ወልድያ ላይ ትልቅ የስም ማጥፋት ድግስ ደግሶ ነበር። የከተማዋ ካድሬዎች ከክልሉ ፀጥታ ቢሮ በተሰጣቸው ቀጥተኛ ትዕዛዝ ከሐራ ወደ ወልድያ ተመልሰው የመስቀል ደመራ በዓልን ከሕዝቡ ጋር ተቀላቅለው እንዲያከብሩና ወልድያ ሰላም ናት የሚል ፕሮፖጋዳ እንዲሰሩ በታዘዙት መሠረት ወልድያ ላይ ተገኝተው ነበር። ፋኖም ካድሬዎቹን ለመምታስ በምወስደው እርምጃ በዓሉን ለማክበር አደባባይ የወጡ የክርስትና እምነት ተከታይ ምዕመናን ይደናገጡብኛል፣ በሚል "ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ" ስልት ተጠቅሞ ውሏል። ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን አክብሮ ወደ ቤቱ እስኪመለስ ድረስም ተኩስ አቁሞ ነበር። ነገር ግን ዛሬ ከንጋት ጀምሮ ድጋሚ በከፈተው ማጥቃት የከተማዋን አንድ ሦስተኛ በቁጥጥሩ ስር አስገብቷል። በከተማዋ ጉቦ፣ ከፊል መቻሬ፣ኬላ፣ ጎንደር በር፣ አደንጉር፣ መብራት ኃይል፣ ሌሎች የከተማዋ አከባቢዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብተዋል። ውጊያው ቀጥሏል። ትናንት ከክልሉ ፀጥታ ቢሮ በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ከሐራ ወደ ወልድያ ተመልሰው የነበሩ ካድሬዎች እጅ ከፈንጅ እየተያዙ ነው።

ሰበር ዜና አሁን ከመሼ! አንድ ኮሎኔል ተማርኳል:: ስሙ ኮሎኔል ሀብታሙ አሰፋ ይባላል:: በተጨማሪም 8 ክላሽ ተማርኳል፣ መካነሰላም ከተማን ተቆጣጥረናል። በተያያዘ ዜና ደቡብ ወሎ ዞን የለገሂዳ ወረዳ ዋና መቀመጫ ወይናምባ ከተማ ፋኖ በቁጥጥር ስር ገብቷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 16/2018 ዓ.ም 16/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ለመላው ሰራዊትና ለመላው ህዝባችን፤ ለትግሉ ደጋፊዎች እና ለሁሉም  የክርስት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ። የዛሬ የእንኳን አደረሳችሁ መልክቴ በአማራን ህዝብ ላይ የተከማቸውን የመከራ ቆሻሻ ቆፍረን የህዝባችን መዳኛ እና ኢትዮጵያዊያን የሚፈወሱበትን የትግሉን ቅዱስ መስቀል ለመትከል በድርጅታችን አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በአጥቂነት ጠላትን እየደመሰሰ ከተሞችን እቸተቆጣጠረ ወደፊት በሚገሰግስበት ሰዓት ስለሆነ በደስታ መንፈስ ጭምር ነው። ለዘመናት የተጠራቀመና የተከመረ ቆሻሻ የክርስቶስን መስቀል ሊቀብር እንደ ተራራ ገዘፈ። ጊዜና ወቅት ስለሰጠው ብቻ ለአለም ድህነትን የሚሰጥ እፀ መስቀል ተዳፈነ። ይህ እቡይነት ነው። ቅዱሳት መፅሀፍ በመስቀለ ክርስቶስ መቀበር ብዙ ነገር ሲሉን ልንማርበት የሚገባ ብዙ ነገር ስላለ ነው። የዘመን መቀየር ከዚህ ላይ ሲያደርሰን ‘ታሪክ መሰቀልን የፈቀደለት’ ብቻ ይመስል የአማራ ህዝብ በዚህ የመከራ ወቅት ላይ ተገኘ። ዘመንን ሊዘልቅ ያለ፣ ዓመታትን ያስተናገደ ‘የሀሰት ትርክት’ ህዝባችን ላይ እንደ ዶፍ ዝናብ እየዘነበ ከረመ። መራር የመከራ ተራራ ህዝባችን ላይ ተቆለለበት። ከ “ያ ትውልድ እስከ አብይ አህመድ” የተፈራረቁ ትርክቶች፣ የተሳሉ ስለቶች፣ የተተኮሱ ጥይቶች፣ የወረዱብን አሩሮች ሁሉ ህዝባችንን ለእልቂት ዳረጉ። ይህ ሁሉ የእዳና እልቂት፣ የሞትና ስደት፣ የመፈናቀልና ዘር ማጥፋት ተራራ ተገርስሶና ተንዶ ህዝባችን ነፃ ሊወጣ ግድ ይለዋል። ለዚህም ሲባል የመከራችንን ቀን በማሳጠር የነፃነታችንን ደመራ ለማየት የመጨረሻው ሰዓት ላይ እንገኛለን። በመጨረሻም በምስራቅ አማራ ቀጠና የተጀመረው የማጥቃት ዘመቻ የሚቀጥል ይሆናል። ሌሎች ጉዳዮች በስራ ይገለጣሉ። ትግላችን አርነት ያወጣናል! የአማራ ህዝብ ትግልም ያሸንፋል! አዲስ ትውልድ፤ አዲስ አስተሳሰብ፤ አዲስ ተስፋ፤ ዝናቡ ልንገረው የአፋብኃ ኮማንድ አባልና የቴወድሮስ ዕዝ ም/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ 16/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

#የአደረጃጀት_ዜና‼️ በአፅመ እርስታች መተከል ዳንጉር ብርጌድ ተመስርቷል። አፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ በአፅመ እርስታችን መተከል ዳንጉር ወረዳ በሻለቃ ደረጃ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን የፋኖ አደረጃጀቶች በማቀናጀት የዳንጉር ብርጌድን በዛሬው እለት እውን አድርገናል።ይህ የሆነ የጠላትን አደረጃጀት ሙሉ በሙሉ በማፍረስ ህዝባችንን ማስተዳደር የሚያስችል መዋቅር በመዘርጋት ነው ። የቴዎድርስ እዝ ከፍተኛ ትኩረት ሰጦ ከሚንቀሳቀስባቸውን እና ልዩ ክትትል ከሚያደረግባቸው ቀጠናዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት መካከል መተከል አንዱ ነው ። ግዙፉን የዳንጉር ብርጌድ የቴዎድሮስ እዝ ከፍተኛ አመራሮች ፦ዶ/ር ጋሹ ክንዱ፣አዲሱ ፈጠነ፣ኃይለሚካኤል ባየህ እንዲሁም የጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ሰብሳቢ ግርማ አየለ እና ሌሎች የክ/ጦሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሙሉ የዳንጉር ብርጌድ ስራ አስፈፃሚ አመራሮችን አስመርጠናል ።የተመረጡ ስራ አስፈፃሚ አመራሮችም ለወጣንለት ቅዱስ አላማ በታማኝነት ለማገልገል ቃለ መሃላ ፈፅመዋል ። ክፋት ለማንም፣በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ! ኃይለሚካኤል ባይህ የቴዎድሮስ እዝ የውጭ ግንኙነት እና ዲያስፓራ ጉዳዮች መምሪያ ም/ሃላፊ 16/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ የከባድ መሳሪያ ጥቃት እየፈፀመ የሰው ህይወት እየቀጠፈ እንዲሁም በንብ
+1
በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ የከባድ መሳሪያ ጥቃት እየፈፀመ የሰው ህይወት እየቀጠፈ እንዲሁም በንብረት ላይ ውድመት እያደረሰ ይገኛል:: በፋኖ ቁጥጥር ስር ልትወድቅ በተዳረሰችው ወልድያ ከተማ ዙሪያ ዙሪያ ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ ሞርተርና መድፍ በማስፈንጨፍ የንፁሃንን ህይወት እየቀጠፈ ንብረትም እያወደመ ይገኛል:: ዛሬ መስከረም 16/2018 ዓ.ም ጥቁር ውሃ ሳር በመሸጥ የምትተዳደር ደካማ እናት ህይወት ቀጥፏል:: ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ /ዐ1/2018 ዓ.ም

ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ልጅ እያሱ ኮር የየጎፍ ክፍለጦር እና ቤተ-አማራ ክፍለጦር አሃዶች በጥምረት ከደሴ ከተማ በምዕራብ በኩል ያለ ዋና የገራዶ መስመር እንዲሁም ጉጉፍቱ ጌልሻ እና ጠባሲት የተባሉ ከተሞችን ተቆጣጠሩ:: ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ዘመቻ አደም አሊ (አባ ናደው) በርካታ የደቡብና ምዕራብ ወሎ ቀጠናዎች የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት በከበባ ውስጥ ያለ ሲሆን ቀሪው ባገኘው አጋጣሚ እየሸሸ ይገኛል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 16/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

#ሰበር_ዜና‼️ ምኒልክ ዕዝ ደሴ ዙሪያ ወረዳ ስምንት ቀበሌዎችን ተቆጣጠረ‼️ 3ተኛ ቀኑን በያዘው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በርካታ ድሎች እየተመዘገቡ ያለ ሲሆን የምኒልክ ዕዝ አንድ ተወርዋሪ ሻለቃ እና ልጅ እያሱ ኮር ቤተ-አማራ ክፍለጦር በጥምረት እያደረጉት ባለው ተጋድሎ ዛሬ መስከረም 16/2017 ዓ.ም ደሴ ዙሪያ ወረዳ ስምንት ቀበሌዎች በቁጥጥር ስር ገብተዋል:: በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ሶስተኛ ቀን ተጋድሎ በርካታ ድሎች የተመዘገቡ ሲሆን ደሴ ዙሪያ ወረዳ ስምንት ቀበሌዎችና ታዳጊ ከተሞች በምኒልክ ዕዝ ቁጥር ስር ገብተዋል:: አሁንም ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረግን እንገኛለን። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 16/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

🔥#ሰበር_መግለጫ‼️ ከአርበኛ ምሬ ወዳጆ (ዋርካው) በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ- -ምርኮኛ መግደል -ተቋማት መቆርቆር -ታርጋ ለጥፎ ማጥቃት ፈፅሞ አይቻልም ፣ቀይ መስቀል በምርኮኛ በኩል ድጋፍ ያድርግ ሲል የአፋብኃ ሴንተራል ኮማንድ አባልና የምኒሊክ ዕዝ ሰብሳቢ አርበኛ ምሬ በዘመቻ አባ ናደውን አስመልክቶ ዘመን አይሽሬ መልዕክት አስተላልፈዋል። መግለጫውን ዩቱዩብ ላይ ተመልከቱ 👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/e8Rn_Jx9CQA?feature=shared

የዋርካው ምሬ አስቸኳይ እና ጥብቅ መልዕክት https://youtu.be/wmt3OB5CMVA?si=hiwQeJfKN3bO8G8n

🔥#እረ_ጎበዝ_አጨብጭብ👏👏👏 የምስራቅ አማራ ቀጠና ሙሉ በሙሉ ሊፀዳ ነው ጎበዝ #እረ_ጎበዝ_አጨብጭብ👏👏👏 የዛሬ ደግሞ ጫን ያለ ነው💪 #ቀይ_መስቀል_ይረከበን‼️
+3
🔥#እረ_ጎበዝ_አጨብጭብ👏👏👏 የምስራቅ አማራ ቀጠና ሙሉ በሙሉ ሊፀዳ ነው ጎበዝ #እረ_ጎበዝ_አጨብጭብ👏👏👏 የዛሬ ደግሞ ጫን ያለ ነው💪 #ቀይ_መስቀል_ይረከበን‼️

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምኒልክ ዕዝ ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በአስደናቂ ስኬት እየተካሄደ ይገኛል። የተገኙት ድሎችም ድርጅታችን እና ሰራዊታችን የአማራ ህዝብ ህልውና የመጨረሻ ምሽግ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምኒልክ ዕዝ ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በአስደናቂ ስኬት እየተካሄደ ይገኛል። የተገኙት ድሎችም ድርጅታችን እና ሰራዊታችን የአማራ ህዝብ ህልውና የመጨረሻ ምሽግ መሆናቸውን ያስመሰከረ በመሆኑ በዚህ ዘመቻ ላይ ለተሳተፋችሁ በሙሉ እና ለአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ዋና ጦር አዛዥ ፊታውራሪ ድርሳን ብርኃኔ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ። በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና የተገኙት ድሎች በሁሉም የድርጅታችን ቀጠናዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል።               ፊታውራሪ ባዩ አለባቸው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዋና ጦር አዛዥ

ከአርበኛ ኢ/ር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ የሰሞኑን ድል አስመልክቶ የተላለፈ መልዕክት! ላለፉት ተከታታይ ቀናት የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ዘመቻ -  አርበኛ - አደም አሊ (አባ ናደው) በሚል በተጠና መንገድ በጠላት ላይ ጠንካራ ክንዱን በማሳረፍ አስደማሚ ድሎችን እያስመዘገበ ወደ ፊት በመገስገስ ላይ ይገኛል።   በጠላት በኩል መደናገጥን በድርጅታችን እና በህዝባችን በኩል ብሩህ ተስፋን ያሳየን ይህ ድል ያለ በሳል ወታደራዊ ጥበብ እና ስክነት ሊመዘገብ የሚቻለው አይደለም። ለዚህም በየደረጃው ያላችሁ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች እና በአንዲት ነፍሳችሁ ተወራርዳችሁ ይኼን ድል ያስመዘገባችሁ የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ሰራዊት እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ። የአማራን ህዝብ ትጥቅ ማስፈታት የሚባል መንግስታዊ ውንብድና የአማራን ህዝብ በማስታጠቅ የሚቀጥል ይሆናል። ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ (ኢ/ር) የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ማዕከላዊ ኮማንድ አባል እና የአሳምነው ዕዝ ዋና መሪ ! 16/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

🔥#ጄትና_ድሮን_ከወሎ_ሰማይ_ስር‼️ የብልፅግና ጦር ሚግና ድሮንን ጨምሮ ሙሉ አየር ኃይሉን አሰልፏል።የፋኖ ኃይል ደግሞ አንዳች ምድራዊ ኃይል የሚያስቆመኝ የለም ብሏል። #ዘመቻው_አባ_ናደው_ነው። ናድ፣ ድቅቅ፣ ድምስስስስስስ💪 በምድር ታንክ በሰማይ ጄት ቢደባለቅ አንዴ ገጥመን መስሎኝ ወዴት ልንላቀቅ💪 #ወይ_ንቅንቅ💪 ህዝባችን ወደቤትህ ግባ ጀግኖቻችን ደግሞ በጥንቃቄ ተንቀሳቀሱ‼️ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 16/ዐ1/2018 ዓ.ም

የአርበኛ ሀብቴ ወልዴ መልዕክት... የፋሽስቱ ብልጽግና ጀንበር እየጠለቀች ነው፤ የአማራ ፋኖ የድል ፀሐይ በመሀል አራት ኪሎ እያበራች ነው፡፡ የድል ፀሐያችን ለአማራ እያበራች፤ ለጠላቶች ደግሞ እያቃጠለች ነው!! ውድ የድርጅታችን አፋብኃ ሴንተራል ኮማንድ አመራሮች፣ የደቡብ፣ ምዕራብና ምስራቅ አማራ ቀጠናዊ ዕዞች፣ በየደረጃው ያላችሁ የዕዝ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የኮርና ከዛ በታች ያሉ ኃይል መሪዎች በሙሉ ይህ መልዕክት ከሰሜን አማራ፣ አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ ከጎንደር ሰማይ ስር ለታጋዩ ሰራዊታችንና ለመላው ሕዝባችን የተላለፈ የትግል መልዕክት ነው!! በወሎ ቤተ አምሐራ ሰማይ ስር እየተደረገ ያለው የዘመቻ አርበኛ አደም አሊ ውጊያ፦ የሁለት ዓመት የትጥቅ ትግል ጉዟችን በተለይም የአፋብኃ ድርጅታዊ የትግል መስመራችን ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ ያሳየ ነው፡፡ በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) እየተዘመገቡ ያሉ ወታደራዊ ድሎች ትርጉማቸው ዘርፈ ብዙ ነው። ከብዙ በጥቂቱ  ይህ ውጊያ ቀጥታ አራት ኪሎ ላይ ያነጣጠረ፣ የአራት ኪሎን የእብሪት ጉዞ በፍርሃት ያራደ ፣ የፋኖን የትግል ግብ ወደ መጨረሻው እያደረሰ ያለ ውጊያ ነው!  ይህ ውጊያ የአገዛዙን ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት፣ የኢንሳ ተቋማትን ያፈራረሰ ያለ ውጊያ ነው!  ይህ ውጊያ ብልፅግና የሚመካበትን  ሠራዊት ፍርስርሱን ያወጣ መልሶ በሠው ኃይልም በሥነ-ልቦናም ለመገንባት እንዳይችል ያደረገ እግረኛ ሠራዊቱን በመናድ፣ በማፍረስና በመበተን ወደነፃነት ተፋላሚው እንዲቀላቀል በማድረግ ላይ ያለ ውጊያ ነው!  ይህ ውጊያ የብልፅግና ካድሬን የፍርሃት ውቂያኖስ ውስጥ የከተተ በካድሬው መካከል ቀውስን የዘራ የሞራል ድምሰሳን ያስከተለ ተዓምራዊ ውጊያ ነው!  ይህ ውጊያ የአገዛዙን የሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ያፈራረሰ፣ የአገዛዙ አፎችን የለጎመ፤ ቅጥረኛ አፈ ቀላጤዎችን ፕሮፖጋንዳ ራቁቱን ያስቀረ የአማራ ልጆች በደማቸው ታሪክ እየሰሩ ያለበት ማርሽ ቀያሪ ውጊያ ነው!  ይህ ውጊያ የትግሉ ደጋፊዎችን ሁሉ የትግል ወኔ ያስታጠቀ፤ የፋኖ  ትጥቅ የደረሰበትን የወታደራዊ፣ የመረጃና ደህንነት፣ የውጊያ ምህንድስናና ዕቅድ፤ የዘመቻ አፈጻጸም የማድረግ አቅም ያመላከተ አዲስ የውጊያ ምዕራፍ ነው። የአማራ ፋኖ ትግል ደጋፊዎች በተለይም የድርጅታችን አፋብኃ ደጋፊዎች በያላችሁት መድረክ የህልውና ትግሉ አካል ሆናችሁ መዳረሻውን ድልና ነጻነት ያደረገውን ትግላችን በፅናት እንድትደግፉ የትግል ጥሪየን አቀርባለሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታይ ወገኖች እንኳን ፤ለብርሃነ መስቀሉ በዓል አደረሳችሁ! የክርስቶስ መስቀል ተስፋ ባለመቁረጥ ፍለጋ ከተደበቀበት እንደተገኘው ሁሉ፣ የአማራ ሕዝብ የነጻነት ትግልም በልጆቹ ቆራጥ መስዋዕትነት ድልና ነጻነቱ ይገኛል፡፡ ኀልውናውንም በተባበረ ክንዱ ይረጋገጣል፡፡ ድል ለአፋብኃ! ድል ለአማራ ሕዝብ!! አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የአፋብኃ ሴንተራል ኮማንድ አባልና የሰሜን አማራ በላይ ዘለቀ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ ህልውናችን በተባበረ ክንዳች የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ‎       ‎መስከረም 16/2018 ዓ.ም ‎16/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎