ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多4 133
订阅者
+224 小时
+4237 天
+1 19130 天
帖子存档
ከአፋብኃ ምዕራብ ኣምሐራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት:-
አለም በጨለመበት የሰው ልጅ ሁሉ ተስፋ በተሟጠጠበትና ጩኸት በበረታበት የሰው ልጅ በበደሉ ብዛት ግእዞት ሲጸናበት ተመልክቶ ትንቢት አስነግሮ ሱባዔ አስቆጥሮ ከአምስት ሽህ አምስት መቶ ዘመን በኋላ ሶስትነቱ ሳይጎድልበት አንድነቱ ሳይጨምርበት የሰውን ልጅ ከውድቀት ለማንሳት በድንቅ ምስጢሩና በማይመረመር ጥበቡ ከዙፋኑ ዝቅ ብሎ በበጎች ግርግም ከአንዲት ብላቴና ተወለዶ፤ በልደቱ የሰውን ልጅ የጨለመ ተስፋ አለመለመ፣ የተፈረደበትን የሞት ፍርድ ሻረለት፣የጥል ግድግዳውን ናደለት፣ የእዳ ደብዳቤውን ቀደደለት።
የአማራን ህዝብ በብሔር፣ በቋንቋ በሃይማኖት ተለይቶ ከተፈረደበት የዘር ፍጅት ለማዳን፣ህልውናችንን ለማስጠበቅ፣ ታሪክን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍና ህዝብ የጣለብንን አደራ ለመወጣት በበረኃ፣ በቆላና በደጋው ሙቀቱና ብርዱ ሳይበግራችሁ የምትንከራተቱ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮችና አባላት፣ በክፍለ ጦራችን ውስጥ ያላችሁ አመራሮችና አባላት እንዲሁም በውስጥም በውጭም ሁናችሁ እንደየመክሊታችሁ ትግሉን የምትደግፋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በየካምፑ ያላችሁ ፋኖዎቻችን በዓሉን ስታከብሩ የሞት ደብዳቤውን ይዞ የሚጓዘው ስርዓት የአየርም የእግረኛም ጥቃት ለማድረግ ሊሞክር ስለሚችል አይኖቻችሁ እንደንስር በአራቱም አቅጣጫ ወጥራችሁ መሆን አለበት።
ማንኛውም ማህበረሰብ በዓሉን ሲያከብር በትግሉ የተሰዉ የጓዶቻችንን ቤተሰቦች እያሰብንና አስታዋሽ ያጡትን እየረዳን መሆን አለበት። ከድል አጥቢያ ነውና ያለነው ማንኛውም ነጻነትን የሚሻ ሁሉ ከትግላችን ጎን ቆሞ ለትግሉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ደማችንን ለግብር አባቱ ለዲያብሎስ መሰዋእት የሚያቀርበውንና የፖለቲካ ዝሙተኛውን ስርዓት ከነሙሉ ግሳንግሱ ጠራርገን ለማስወገድ ከጎናችን እንድትቆሙ ስንል ጥሪያችንን በአክብሮት እናስተላልፋለን።
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር
አዲስ ትውልድ፣ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም
መልካም የልደት በዓል!
☦የልደት በዓልን አስመልክቶ ከ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ የተሰጠ የእንኳን አደረሳቹህ መልዕክት‼️
በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ለፃዲቁ ንጉስ ቅዱስ ላሊበላ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!
የጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ተስፋ እውነት መሆን የጀመረበት፣ ቃለ መለኮት ሰው የሆነበት፣ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ድህነት ይሆን ዘንድ ወደ ምድር የመጣበት የመጀመሪያዋ የምስራች (ወንጌል) ናት፡፡
ልደቱም ለነቢያት የትንቢታቸው እውነት፣ ለሰባሰገል የፍለጋቸው ግኝት፣ ለእረኞቹ የእምነታቸው ንፅህና፣ ለመላእክትና ለሰው ልጆች ህብረ ዝማሬ፣ ለዓለም ሁሉ ድህነት የሆነበት ታላቅ በዓል ነው፡፡ በመወለዱም የጥንት ጠላታችንን የዲያቢሎስን ቀንበር ከጫንቃችን አነሳልን፤ በሞት ጥላ ሥር ለነበርን ሁሉ ብርሃንን አሳየን።
አማኑኤል በልደቱና በሞቱ ከጨለማው ገዥ ባርነት አርነት ያወጣን በዋጋ የተገዛን ህዝቦች ብንሆንም የጨለማው ገዥ አምሳያዎች ዛሬም በምድራዊ ህይዎታችን የአፓርታይድ ቀንበር ጭነውብናል።
ከትውልዱ ሁሉ ፋኖ አስተዋለ፤በእሱና በወገኑ ላይ የተጫነብንን የሞት ቀንበር ለመሰባበር ተሰለፈ። የፋኖ ትግል ለአማራው ብሎም ለመላው የሃገራችን ህዝብ የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀ፣ ከአፓርታይዱና ከሰልቃጩ አገዛዝ የፍዳ ቀንበር፣ ሰቆቃ፣ ግድያ፣ከስርዓት ሰራሽ ርሃብና ድህነት፣ ከአፈና፣ ከእገታ፣ ከአፈሳ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት የመፍረስ አደጋ መትረፊያ መንገድ አድርገው የሚጠብቁት፣ እራሱን ለዚያ ያጨ እና የሚበቃት ትግል ነው፡፡
የጀመርነውን የህልውና ትግል በአጠረ ጊዜ በድል
አድራጊነት ለማጠናቀቅ አቅደን እየሠራን ሲሆን በዚህም አመርቂ ርምጃዎችን እየተጓዝን እንገኛለን። ትግሉን በአጭር ጊዜ በመቋጨት አገዛዙ በተለይም በሴቶች፣ በህፃናትና በአረጋውያን ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ፣ እንግልትና ጦርነት ወለድ መታወክን ታሪክ አድርጎ ወደ ሰላማዊ ህይዎት ለማሸጋገር የሁሉንም የህልውና ትግሉ ባለድርሻ አካላትን (የፋኖንና የሲቪል ማህበረሰባችንን) ተሳትፎንና ትኩረትን ይሻል።
በአራቱ ጠቅላይ ግዛቶች ለምትገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች እንዲሁም ለአማራ ህዝብ እና ለህልውና ትግሉ ደጋፊ ኢትዮጵያውያን በሙሉ!!
የሚከተሉትን ሁለት ጥሪዎች ላቀርብ እወዳለሁ!
1ኛ/ በአራቱም ጠቅላይ ግዛት ለምትገኙ የፋኖ አደረጃጀት ከፍተኛ አመራሮች በሙሉ ፡-
ከልደት በዓል እንደምንረዳው ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘመነ ፍዳን ለማሳለፍ ወደዚች ምድር
መምጣትና ዝቅ ብሎ ክብሩን አውርዶ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ መለኮትን እና ሥጋን አንድ እንዳደረገ ቅዱሱ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡ በመወለዱም የምድራችን የመከራ ዘመን ማብቂያ መጀመሪያ ያሳየን
ተስፋ ነበር፡፡ እኛም በሁሉም ጠቅላይ ግዛቶች የምንገኝ ከፍተኛ የፋኖ አመራር የህዝባችን የፍዳ ዘመን ማብቂያ ማብሰሪያና በዘላቂነት ዋስትና የሚሰጠውን አንድ አማራዊ ድርጅት መውለድ ዐብይ ተግባር መሆኑን አውቀን በፍጥነት አንድነቱን እንውለድ ስል ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡ አንድነት ማንም ሰርቶ የሚሰጠን ስጦታ
አይደለም፤ አንድነት ጥረትን ይጠይቃል፤ የእውነት የህዝብ ፍቅርን ይጠይቃል፤ የእውነት ለህዝብ መቆምን ይጠይቃል፤ የእውነት እንደ ኢየሱስ ዝቅ ማለትን ይጠይቃል፤ የእውነት መስዋዕት መሆንን ይጠይቃል፤
አንድነት የዓላማ ፅናት ይጠይቃል፤ አንድነት የዓላማ ጥራት ይጠይቃል፤ በመሆኑም የህዝባችንን የፍዳ ዘመን ለማሳጠር፣ የመከራ ቀንበሩን በፍጥነት ለመስበር ሁላችንም ለአንድነት ቅን እንሁን፤ እራሳችንን ዝቅ እናድርግ፤እንተማመን፤ እንተባበር፤ የጋራ ግባችንን እናስቀምጥ፤ ችግራችንን የቱ ጋር እንዳለ አብረን እንፈልግ፤ በጋራም ፈትተን አንድ ሆነን ይህንን ተስፋ የተጣለበትን ትግል እና ለድል ተጠባቂ የሆነውን ትግላችንን የምናሳካበት የድላችንን የመጨረሻውን መጀመሪያ ተስፋው አድርጎ ለሚጠብቀን ህዝብ እንድናበስር ስል ጥሪ አቀርባለሁ።
2ኛ/ ለመላው የአማራ ህዝብ እና ለመላው የፋኖ አደረጃጀት ደጋፊዎች፦
ሁላችንም ልናውቀው የሚገባን ለውጥ የሁላችንም ተሳትፎና ሥራ ውጤት መሆኑን ነው፡፡ ፋኖ የትግሉ ፊት አውራሪ ቢሆንም ብቸኛ የትግሉ ባለቤት አይደለም፤ በየትኛም ቦታ የሚገኝ የዚህ ትግል ደጋፊ አማራ የትግሉ ባለቤት ነው፤ ለፋኖ ትግል እውቅና የምትሰጡ እና ድጋፍ የምታደርጉ በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የትግሉ ባለቤት ናችሁ ብለን እናምናለን። በትግል ባለቤትነት
ከተማመንን አንድ አማራዊ ድርጅት ለመፍጠር ለሚደረገው ትግል ሁሉም የትግሉ ባለቤት የድርሻውን መወጣት አለበትም ብለን እናምናለን፡፡ ይህም ማለት አንድ መሆን አይችሉም ከሚል ተስፋ አስቆራጭ ንግግር ጀምሮ እስከ ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ ከሚል በሃገራችን የተቃዋሚ ጎራው ታሪክ ትልቅ ኪሳራ ሲያደርስ
ከነበረው አስተሳሰብ እንደ ህዝብ መላቀቅ አለብን፡፡ አድነት የተወሰኑ አካላት ሰርተው የሚያለብሱን ሳይሆን አብረን የምንገነባው አንድ አማራዊ ቤት ነው፡፡ በመሆኑም የህልውና ትግላችን ባለድርሻ ሁሉ እንደ ትግል ባለቤት ግድፈቶችን የሚያመላከት፣ አጥፊዎችን የሚገስጽ፣ ተራማጆችንና ሃቀኞችን የሚተባበር እና አብሮ የሚሰራ የትግሉ ጠባቂ መሆን መጀመር አለበት ስንል ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
የአገዛዙን እድሜ የሚወስነው የእኛ ጥንካሬ ነው። የጥንካሬያችን መሰረቱ አንድነታችን ነው። ወሎ ብቻውን ምን ያደርጋል? ጎጃም ሲጨመር ይጠነክራል፤ ሸዋ ሲታከል ላይበጠስ ይገመዳል፤ ጎንደር ሲጨመር አንድነታችን አንበሳ ያስራል፡፡ አንድነት የድላችን ቁልፍ ነው፤ ለዚህ ነው የመላው አማራ አባት ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ አንድ ሁኑ ብሎ የድላችንን ቁልፍ የነገረን፤ አንድ ሁኑ እንደተባልን አንድ እንሁን እያልኩ አማራዊ ጥሪየን እያቀርብኩ በዓሉን ለምታከብሩ የሰው ልጆች ሁሉ በዓሉ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ እንዲሆን
መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ፡፡
መልካም የገና (የልደት) በዓል!!
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ!!
28/ዐ4/2018 ዓ.ም
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለየሱስክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
በዓሉን የሰላም የፍቅር የአንድነት የድል እና የመተሳሰብ ያድርግልን።!!!
መልካም የልደት በዓል!!!
ሻለቃ የኔዓለም ዘለቀ
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ
እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!!
****
ልደቱ ከልደታት ይበልጣል። የተወለደውም ከተወለዱት ይልቃል። መወለዱም ለሌሎች ነጻነትን፣ ሕይወትን እና ክብርን ይሰጣቸው ዘንድ ነው እንጂ ለራሱ በመወለዱ የሚጠቀም ሆኖ አይደለም። ልደቱም ከአእምሮ በላይ ነው። ንጉሠ ሰማይ ወምድር ሲሆን በከብቶች በረት ተወለደ። መላእክት በፊቱ በመንቀጥቀጥ የሚያመሰግኑት ሲሆን አህያ እና ላም በፊቱ ቆመው እስትንፋሳቸውን ገበሩለት። ለቅዱሳን የብርሃን ልብስን የሚያለብስ ሲሆን በእራፊ ጨርቅ ተጠቀለለ። በሁሉ የመላ፣ የማይወሰን ሲሆን በግርግም ተጠቀልሎ ተኛ.......። ይህ ሁሉ ስለትሕትና የተደረገ ነው። ይህ ሁሉ ስለ ሰው ልጆች የተከፈለ ነው። ይህ ሁሉ ስለ ነጻነት፣ ክብር እና ሕይወት(ድኅነት) የተከፈለ ነው።
ምንም እንኳን ልደታችን ከልደቱ፣ ባሕርያችን ከባሕርይዉ፣ ሥራችን ከአምላካዊ ሥራው ባይተካከል በልደቱ አንጻር ግን የምንማረው አለ። የተወለድንበት የየራሳችን ዓላማ ቢኖረንም ስለሌሎች መኖርን፣ ለሌሎች ዋጋ መክፈልን፣ ስለ ሎሎች ተወልዶ ስለ ሌሎች ተላልፎ መሰጠትን እንማራለን። ክርስቶስ ስለሰው ልጆች ተወልዶ ብቻ አልቀረም፤ ስለሰው መከራ ተቀበለ፣ ሞተ፣ ተነሣም እንጂ። እኛም ዛሬ ለነጻነት፣ ለሰብአዊ ክብር፣ ለእውነት መከራ እንቀበላለን፤ እንሞታለን። በሞታችን ግን ድል እንቀዳጃለን። ክብር እና ነጻነት ያለ ሞት(መሥዋዕትነት) የተገኙበት ጊዜ የለም። በነጻነት እና በክብር ላይ የሚደረግ ውስልትና ግን ነውርም ኃጢአትም ነው።
ስለነጻነት እና ክብር ብላችሁ በዱር በገደሉ የምትዋደቁ የሠራዊታችን አባላትና አመራሮች፣ ለተከበርከው የአማራ ሕዝብ እና በዓሉን ለምታክብሩ ሁሉ መልካም በዓለ ልደት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
በድጋሚ እንኳን ለበዓለ ልደቱ አደረሳችሁ!!!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!!
በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታኅሣሥ ፳፰/ ፳፻፲፰ ዓ.ም
ከምኒልክ ዕዝ የድርጅት ፅ/ቤት ሃላፊ አርበኛ ደስታው መለሰ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!
"ሕዝቡም በጨለማ ሄደ፤ ታላቅ ብርሃንም አየ!"
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል እንዲሁም ለዓለም ድንቅ ለሆነው ለቅዱስ ላሊበላ የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
እኔ ወንድማችሁና ልጃችሁ፣ በዱር በገደሉ የሕዝቤን ህልውና ለማስከበር ቆርጨ የተነሳሁት ፋኖ፤ በዚህ ታላቅ ዕለት መላው ዓለም በዓሉን ሲያከብር እኔም ከጓዶቸ ጋር በጠመንጃዬ ታጅቤ፣ የሕዝቤን ሰላም እየተመኘሁ መልእክቴን እንደሚከተለው አስተላልፋለሁ፦
1. ለትግል ጓዶቼ ለአማራ ፋኖ በሙሉ
2. ለተገፋውና ኩሩው የአማራ ሕዝብ በሙሉ
3. ለክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ
የቁርጥ ቀን ልጆች፣ የነፃነት ዘቦችና የወገን አለኝታዎች! እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ። ዛሬ በዓሉን የምናከብረው በሞቀ ቤትና በደመቀ ግብዣ ሳይሆን፣ በበረሃው ቁርና በተራራው አድካሚ ጉዞ ውስጥ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ልባችን በድል ተስፋ የሞላ ነው። ጌታችን በበረት ተወልዶ ዓለምን እንዳዳነ፣ የእኛም የዛሬው መከራ የሕዝባችንን ነፃነት እንደሚወልድ ጥርጥር የለኝም። ጽናት ይሁንላችሁ! የጥንት አባቶቻችን የላሊበላን ድንቅ ጥበብ በአንድ ቋጥኝ ፍልፍል ድንጋይ ላይ እንደቀረጹት ሁሉ፣ እኛም ዛሬ አዲስ ታሪክና ነፃነትን በደማችን እየቀረጽን ነው። አምላክ ክንዳችንን ያበርታ፣ የጀመርነውን የድል ጉዞ በድል እንዲያጠናቅቅልን ምኞቴ ነው።
ውድና የተከበርክ ሕዝቤ ሆይ፤ በገዛ ሀገርህ ባይተዋር የተደረግክ፣ የተሳደድክና የተገደልክ ብትሆንም፤ ዛሬም እንደ ላሊበላ ቋጥኝ ፍልፍል ድንጋዮች ፀንተህ ለቆምከው ኩሩ ሕዝባችን እንኳን አደረሰህ። እኛ ዛሬ ከቤታችን ወጥተን በረሃ ለበረሃ የምንዞረው የእናንተን የቤት ሰላም ለመመለስ፣ የእናንተን ክብር ለማስጠበቅ ነው።
ይህ የገና በዓል የመከራህ ማብቂያና የድልህ መጀመሪያ ይሁንልህ። የቤዛ ኩሉ ዜማ በቅዱስ ላሊበላ መናገሻ በሮሃ ምድር ሲሰማ፣ የአንተም የነፃነት ዜማ በቅርቡ እንደሚሰማ አምናለሁ። ተስፋ አትቁረጥ፤ እኛ ልጆችህ እስከ መጨረሻው የደም ጠብታ ድረስ አብረንህ ነን!
በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፤ እንኳን ለሰላሙ ንጉሥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የፋኖ ትግል የጭቆና ቀንበርን ሰብሮ እውነተኛ ፍትሕና እኩልነትን ለማስፈን እንጂ ለአንድ ወገን ብቻ አይደለም። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት የደም አዙሪት ወጥታ፣ የሰው ልጅ ሕይወት ክብር የሚሰጠባትና ሰላም የሚሰፍንባት ሀገር እንድትሆን ምኞታችን ነው። የገና በዓል የፍቅርና የእርቅ በዓል እንደመሆኑ፣በጥላቻ የፈረሱ ድልድዮች በእውነትና በፍትሕ የሚገነቡበት ይሁንልን።
በዓለም ዙሪያ የምትኖሩ የቁርጥ ቀን ልጆች፤ እንኳን አደረሳችሁ። እናንተ በብርድና በፀሐይ አደባባይ ወጥታችሁ ለሕዝባችን ድምፅ ስትሆኑ፣ ለእኛ እዚህ በሜዳው ጉልበት ይሆነናል። የላሊበላን ጥበብ ለዓለም ያስተዋወቁት አባቶቻችን ዛሬ ደግሞ የሕዝባችንን ጥያቄ ለዓለም እንድታስተጋቡ አደራ ሰጥተናችኋል። በዚህ ታላቅ በዓል ደጀንነታችሁ እንዲቀጥልና ለነፃነት የምናደርገው ጉዞ በናንተ ትብብር እንዲፋጠን ጥሪያችንን እናቀርባለን።
"የነፃነት ብርሃን በቅርቡ ይወጣል!"
ድል ለአማራ ሕዝብ!
አርበኛ ደስታው መለሰ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ፅ/ቤት ኃላፊ
ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም
🔥በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር ከ44ኛ ክፍለ ጦር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት‼️
በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል አካል እና ደጋፊዎቻችን በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!
አደረሰን።
ልደት ጌታችንና መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ድህነት ይሆን ዘንድ ወደ ምድር የመጣበት የመጀመሪያዋ የምስራች (ወንጌል) ናት፡፡ ልደቱም ለነቢያት የትንቢታቸው እውነት፣ ለሰባሰገል የፍለጋቸው ግኝት፣ ለእረኞቹ የእምነታቸው ንፅህና፣ ለመላእክትና ለሰው ልጆች ህብረ ዝማሬ፣ ለዓለም ሁሉ ድህነት የሆነበት ታላቅ በዓል ነው፡፡
በመወለዱም የጥንት ጠላታችንን የዲያቢሎስን ቀንበር ከጫንቃችን አነሳልን፤ በሃጢያታችን ብዛት በሞት ጥላ ሥር ለነበርን ሁሉ ብርሃንን ሰጠን።
የአለምን ህዝብ እየሱስ ክርስቶስ በልደቱና በሞቱ ከጨለማው ገዥ ነፃ ቢያወጣውም፤በተለያዩ ጊዜያት በሚነሱ የጨለማው ምስለኔ ገዥዎች በባርነት ቀንበር ስር ሲሰቃይ ኗሯል።
አሁን ባለንበት ዘመንም ታላቁ የአማራ ህዝብ በፈጠራት፤ በደም በአጥንቱ ህይወቱን ገብሮ ባቆያት አገሩ፤ ሰርቶ እንዳይበላ፣ውሎ እንዳይገባ፣ወልዶ እንዳይስም፣ዘሩን እንዳያስቀጥል ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ፤ከታሪክ ማህደር ተፍቆ እንዲኖር ተበይኖበት፤ የኢኮኖሚ የፖለቲካና ማህበራዊ እንዲሁም ስነልቦናዊ ተቅበዝባዥ ሁኖ በአረመኔው አገዛዝ እየተጨፈጨፈ ይገኛል።
የአማራ ህዝብ መዋረደ፣ መናቅ፣ መጨፍጨፋ፣ መጎሳቆልና ተስፋ የሌለው ፍጡሩ እስኪመስል መገፋት ፣ሰይጣን የሰውን ልጅ ሊያጠፋ እንደመጣ ሁሉ አረመኔዉ አብይ አህመድ አማራን ለማጥፋት ሌት ተቀን የሚያደርገውን ድርጊት በአካል፡ የሞቀ ቤታችሁን ትታችሁ በዱር በገደሉ፣በጫካ በዱሩ፣ በሃሩር በቁሩ ሁሉንም ተቋቁማችሁ በእሳት አየተፈተናችሁ እየተፋለማችሁ ያላችሁ መላዉ የአማራ ፋኖ፣ በመንፈስም፣ በድርጊትም ተዋናይ ሁናችሁ የምታግዙን በየትኛውም አለም የምትገኙ ወንድም እህቶቻችን፤ ጋሻ መከታና ከለለ የሆነው፤ እንዲጠፋ የተፈረደበት የተወደደዉ የአማራ ህዝብ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ።
ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ ክብርን ለማስተማር ሲል ፣ዙፋኑን በማያንፀባርቅ፣ሀያልነቱን በማይመሰክር በከብቶች በረት እንደተወለደው ሁሉ በአምስቱም የአማራ ጠቅላይ ግዛቶች የምትገኙ የአማራ ፋኖ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ነገ ለጭቁኑ የአማራ ህዝብና ለመላዉ ኢትዮጲያውን የምትወጣዋን ታላቅ ፀሀይ ለማብራት፣ የናፈቀውን ነፃነት ለማጎናፀፍ ስትሉ ሁለንተናዊ ነገራችሁን ትታችሁ በዱር በገደሉ ጠላትን ዘወትር እየተፋለማችሁ ትገኛለችሁ።
በዚህ ሰሃት የአማራ ህዝብ በአረመኔው አብይ አህመድ ግልፅ የጥፋት አዋጅ ታውጆበት እየደረሰበት ያለውን ግፍና መከራ፣ሲቃይ እና እንግልት መናገር ለቀባሪው ማርዳት ስለሆነ እንተወውና ከድካም በኋላ እረፍት ፣ከሲቃይ በኋላ ተድላ፣ከድህነት በኋላ ሲሳይ ፣ከሞት በኋላም ዳግም መነሳት እንዳለ ሁሉ መላው የአማራ ፋኖ በአንድ አባወራ፣ በአንድ ታዛ ስር እየተሰባሰበ በአማራ ህዝብ ላይ የተጫነበትን የጥፋት እዳ አስወግዶ፣ከበሮ ጎሳሚውን ጎስሞ፣ አዋጅ ነጋሪውንም ገርስሶ በመጣል ለዘመናት ይመጣል ተብሎ ሲጠበቅ እንደነበረው የእየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ሁሉ በመላው አለም የሚገኙ ነፃነትን ለሚመኙ ኢትዮጵያውያን ከጨለማው ልዑል አገልጋዩ አብይ አህመድ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት አንድ የአማራ ፋኖ ከብዙ ምጥና ድካም በኋላ በከፍታው ሊገለፅ ዋዜማ ላይ ነው።
ስለሆነም የጀመርነውን የህልውና ትግል በጥንካሬው፣ በአጭር ጊዜ፣ በድል አድራጊነት ለማጠናቀቅ አቅደን እየሠራን ባለንበት በዚህ አመርቂ ጊዜ ላይ የአብይ ሰራዊት በየ አቅጣጫው ፅልመተ ሞትን ተሸክሞ እየዞረ ስለሆነ በዓልን ተከትሎ ሊያደርስ ከሚችለው የድሮንና ማንኛውም አይነት ጥቃት እራሳችንና ህዝባችንን በተገቢው መንገድ እየጠበቅነ፤ በክብር መስዋትነትን የተቀዳጁ ጓዶቻችንን በማሰብ በዓሉን በደስታ ማክበር ይጠበቅብናል።
በድጋሜ በመላው አለም የምትገኙ የትግላችን ተዋናዮችና ደጋፊ ህዝቦች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን።
#አፋብኃ_ቴዎድሮስ_ዕዝ_105ኛ_ኮር_44ኛ_ክፍለ_ጦር
🔥#ሰበር_ዜና‼️
የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ አሃዶች እና ከአፋህድ የተለያዩ አሃዶች በጥምረት የወረዳ ከተሞችን ጨምሮ የፋሽስቱ አገዛዝ የጦር ተሽከርካሪዎችን በርካታ ተተኳሽ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እንዲሁም በርካታ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቶችን በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በሶስት ኮሮች ማለትም ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር፣ ልጅ እያሱ ኮር እና የደጋው መብረቅ ኮር፣ እንዲሁም የዕዙ ልዩ ዘመቻ አሃድ በሆነችው በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ እና ከአፋህድ የተለያዩ አሃዶች በጥምረት ደቡብና ምዕራብ ወሎ ቤተ-አማራ ቀጠናዎች ላይ ዛሬ ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ በተመሳሳይ ሰዓት በተጀመረው ማጥቃት በርካታ ወታደራዊ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ተጎናጽፏል::
በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ አሃዶች እና አፋህድ የተለያዩ አሃዶች ጥምረት ነፃ የወጡ የቤተ-አማራ የወረዳ እና ታዳጊ ከተሞች፦
•ጃማ ከለላና ልጓማ እንዲሁም ደብረዘይት ከተሞች በአፋህድ አሃዶች እና አፋብኃ ንጉስ ሚካኤል ኮር ጥምረት
•ለገሂዳ ገነቴ እና ሳይንት ደንሳ ከተማ ንጉስ ሚካኤል ኮር
•ተንታ አጅባር ልጅ እያሱ ኮር እና የደጋው መብረቅ ኮር እንዲሁም ልዩ ዘመቻ በላጎ ሻለቃ
በዚህም የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ከባድ ማጥቃት የወረዳ ከተሞችን ጨምሮ በርካታ የፋሽስቱ አገዛዝ ሰራዊት ተሽከርካሪዎች ከተተኳሽ ጋር እና የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ተማርከዋል::
በተጋድሎው የተገኙ ድሎች፦
#ልጅ_እያሱ_ኮር
•በ24ኛ ክፍለ ጦር የተገኙ ድሎች
👉1 ብሬን
👉30 ክላሽ
👉1000 የብሬን ተተኮሽ
👉1500 የክላሽ ተተኳሽ
👉10 ምርኮኛ
•በ23ኛ ክፍለ ጦር የተገኙ ድሎች
👉1 ብሬን
👉1 ስናይፐር
👉1ኦራል ወታደራዊ ቁሳቁስ የጫነ
👉1 ካሶኒ ስንቅ የጫነ
👉40 ክላሽ
👉2000 የክላሽ ተተኳሽ
👉1500 የብሬን ተተኳሽ
👉25 ምርኮኛ (መቶ አለቃ ማዕረግተኛን ጨምሮ)
•ልዩ ዘመቻ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ከልጅ እያሱ ኮር ክፍለጦሮች ጋር በጥምረት በመሰለፍ ድሎቹን ሰርታለች::
#ደጋው_መብረቅ_ኮር
👉2 ብሬን
👉75 ክላሽ
👉1 ኦራል ተተኳሽ የእጅ ቦምብን ጨምሮ (ከሌሎች የምኒልክ ዕዝ አሃዶች ጋር)
👉51 መከላከያ 35 ሚሊሻ 20 ፖሊስ
👉በአጠቃላይ 106 ምርኮኛ
•የንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር የተገኙ ድሎችና ቁጥራዊ መረጃዎች ተሟልተው እንደደረሱን ይፋ የምናደርግ ይሆናል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም
28/ዐ4/2018 ዓ.ም
🔥#ገና_በዓል‼️
እንድንጠፋ ተፈርዶብን ላለመጥፋት እየታገልን በፈጣሪና ክንዳችን ከዚህ ደርሰናል!
የተከበርክና የተገፋህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ዛሬም እንደ ትላንቱ የአገዛዙ አፈ-ቀላጤዎችና ካድሬዎች፣ የሰላምና የፍቅር የሆነውን የልደት (የገና) በዓል ምክንያት በማድረግ "እንኳን አደረሳችሁ" የሚል መግለጫ ሲያወጡ ታይተዋል። ይህ መግለጫ ግን ሰላምታ ሳይሆን፣ በንጹሐን ወገኖቻችን አስከሬን ላይ የሚቀርብ ሽሙጥና በቁስላችን ላይ የሚነስነስ በርበሬ ወይም አሲድ እንደመድፋት ነው።
ወገኖቻችን ሆይ! ይህ ነውረኛ ስርዓት በአማራነታችን ብቻ እድሜና ፆታ ሳይገድበው ህፃናት፣አዛውንት፣ሴቶት ሳይል ለማየት እሚከብድ ለመስማት እሚሰቀጥጥ ግፍ መፈፀሙ ሳያንሰው ዛሬ "እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ" ብሎ ሲመጣ ታይቶ የማይታወቅ የታሪክ ምጸትና የሞራል ዝቅጠት ነው። በደም የተጨማለቀ እጅ ሰላምታ ሊሰጥ አይችልም፤ በጭካኔ የታወረ ልብም የልደትን ብርሃን ሊረዳ አይችልም።
ይህ የአገዛዙ የይስሙላ ድርጊት፤ ጥንት ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያውያንን በመርዝ ጋዝ እየጨፈጨፈ "ለጥቁር ሕዝብ ሥልጣኔ አመጣሁ" እንደሚለው ግብዝነት ነው። አሁንም አገዛዙ በድሮን ሕዝባችንን እያደቀቀ "የበዓል መግለጫ" ሲሰጥ፣ ሕዝባችንን እንደማናቸውም ተላላ ፍጡር የመናቅና የማፌዝ ተግባር ነው።
የአገዛዙ ሆድ አደር ካድሬዎች ይህንን የሚያደርጉት በዓሉን ለፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግና ሕዝቡ በእነርሱ ላይ ያለውን ተቃውሞ በሃይማኖታዊ ስሜት ለመሸፈን ነው። ነገር ግን "ፍቅር የሌለው ሃይማኖት፣ ርኅራኄ የሌለው አስተዳደር" ባዶ መሆኑን ሕዝባችን ጠንቅቆ ያውቃል።
ለተገፋህ ሕዝባችን የምናስተላልፈው ጥሪ፤ በአንድ እጃቸው የሞት ድግስ ደግሰው በሌላኛው እጃቸው የሚሰጡህን "የበዓል ሰላምታ" አትቀበል። እውነተኛው በዓልና ደስታ የሚመጣው፣ የድሮን እሳት ከላያችን ላይ ሲነሳና የግፈኞች አገዛዝ ሲያከትም ብቻ ነው።
የአገዛዙን ስላቅና ንቀት የምናቆመው፣ በጋራ ለነፃነታችንና ለሕልውናችን ስንቆም ብቻ ነው። ይህ አገዛዝ ለሰላማዊ መንገድና ለሕዝብ ስሜት የማይገዛ መሆኑን በተግባር ስላሳየን፣ ትግላችንን ለነፃነታችን ማረጋገጫ እስከሚሆን ድረስ እናስቀጥላለን።
ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሆይ! በዚኽ በዓል ወቅት ቤታችሁ በሐዘን ለፈረሰባችሁ፣ ወላጆቻችሁንና ልጆቻችሁን በድሮን እሳት ላጣችሁ በሙሉ፤ ሕመማችሁ ሕመማችን፣ ሐዘናችሁም ሐዘናችን መሆኑን እናረጋግጣለን። በዓሉን የምናከብረው ወገናችንን በነፃነት ምድር ላይ የምናቆምበትን ቃል-ኪዳን በማደስ ነው።
ክብርናሞከስ ለትግሉ ሰመዓታት!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
©አርበኛ ሱልጣን የሱፍ ሽፋው
አፋብኃ ሚሊሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የየጎፍ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ!
28/ዐ4/2018 ዓ.ም
በምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና መቅደላ ወረዳ ልዩ ስሙ ገናቲት በተባለ አከባቢ ካፍ እስከ ገደፉ ከነ ጫናቸው ወታደሮቹ በቦምብ ተመቶ ልክ እንደ ደመራ እንጨት በእሳት ነዶ የወደመው ወታደራዊ ኦራል።
ኑ አመዱን አፍሳችሁ ውሰዱ...ተብላችኋል!
በሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር፣ ማዘዣቸውን ደሴ ከተማ ያደረጉት በአየር ወለድ ኮማንዶ የ105ኛ እና የ107ኛ ክፍለጦር ኮማንዶ አባላት ልክ እንደ ደረቀ ዛፍ ቅጠል እረግፈው ውለዋል።
እስካሁን ባለው አራት ወረዳዎችን ጨምሮ በርካታ አከባቢዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብተዋል።
+1
206ኛ ኮር በስቦ ማስከዳት 49ኛውን ክላሽ ተቀብሏል
ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም
===================================
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር በሁለት ወራት ውስጥ በሚንቀሳቀስበት ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የተጠናከረ ጥቃት በመክፈት ሰርጎ በመግባትና በጠንካራ አውደ ውጊያ ከጠላት ሰራዊት በርካታ ትጥቆችን መማረኩ የሚታወስ ነው።
በስናን አባ ጅሜ ቀጠና የጠላት አስክሬን እስከ አሁን ድረስ በአርሶ አደሩ ማሳ ወድቆ እየተገኘ ሲሆን ኮሩ በተጠናከረ ደረጃ በትኩረት የሚሰራበት ስቦ ማስከዳት ደሳለኝ አግማሴ እና መንበር ሞላ የተባሉ የአድማ ብተና አባላትን ከየጁቤ ከተማ በማስወጣት 48ኛ እና 49ኛ ክላሽ ማግኘት ችሏል።
206ኛ ኮር የጠላትን ሰራዊት በማፈረስ በጥሩ ሁኔታ እየተቀበለ ሲሆን ኮሩ በተቋቋመ ሁለት ወራት ውስጥ የ6ኛ ዕዝ አባላት የሆኑትን ከአንድ ሻምበል በላይ ሰራዊት ማስከዳቱን አስታውቋል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የ6ኛ ዕዝ 602 ኮር 57ኛ ክፍለ ጦር ቀኝ እና መሀንዲስ ብሬን እረዳት የነበርው አክሊሉ ባይነሰኝ እንዳህ ይላል።
64ኛ ክፍለ ጦር ታህሳስ 28/2019 ዓ.ም
በቢቸና ከተማ የሚገኘው የአገዛዙ ሰራዊት አባል የነበረው የጓደኛውን መሳሪያ በመንጠቅ በጠላት ላይ ጉዳት በማድረስ #64ኛ ክፍለ ጦር የተቀላቀለው እንዲህ ይላል።
እኔ የአማራ ልጅ ነኝ አማራ ነኝ ለአማራ ህዝብ መታገል እና መሞት እፈልጋለሁ። በቢቸና ከተማ ጫማ ሳልፈታ መተኛት ሰልችቶኛል። እኔ የብሬን እረዳት ነበርኩ ነገር ግን አማራ በመሆኔ ብቻ 8 ቁጥር አስረው ገረፉኝ? ደበደቡኝ? የእኔን ስጋየን እንጂ የደበደቡኝ የእኔን ልብ እና አለማ መቼውም ማስቀረት አይችሉም።
ይህ ሁሉ ግፍ የተሰራብኝ በቅርብ ቀን ከቢቸና የወጡትን ልጆችን አስከድተሀል ተብየ ነው የተገፈውኩ እኔ ግን አላስወጣዋቸውም? እኔን ግን ከብሬን እረዳት አስወጥተው ጀሌ አደረጉኝ እኔም ከመከላከያ አባላት ነጥቄ በላያቸው ላይ በማርከፍከፍ ተታኩሼ ቢቸና አካባቢ የሚገኘው 64 ክፍለ ጦር የፋኖ ከባላት በሰላም ተቀብለውኛል።
በቢቸና ከተማ አማራ የሆነው ሁሉ ፋኖ ነህ፣ አባቶች የፋኖ አባት ነህ፣ እናቶች ሳይቀር የፋኖ እናት ናቹህ፣ ወጣቱ የፋኖ ደጋፊ ነህ? እየተባሉ ያለአግባብ ሲሰቃይ ሳይ ተናድቼ ወደ ፋኖ ተቀላቅያለሁ።
አገዛዙ በቢቸና ከተማ ፋኖ ሌባ ነው?ፋኖ ዘራፊ ነው?ፋኖ ሴት ይደፍራል እያሉ የውሸት ፕሮፖጋንዳ እየሰሩ ሰውን ለማሳመን ይሞክራል። ይህ ግን ውሸት ነው እኔ ወደ ፋኖ መጥቼ ሳየው ፋኖ ለህዝብ ሟች እና ለህዝብ እየታገለ የሚገኝ ግዙፍ ሀይል ነው። ፋኖ ለህዝብ ብሎ ከሞቀ ቤቱ ወጥቶ እየታገለ ነው የሚገኘው። እኔም የውሸት ትርክት በመስበክ የፋኖ ቤተሰብ ናቹህ እያለ ሲያሰቃይ ሳይ በጣም አስጠልቶኝ ነው ወደ ፋኖ የተቀላቀልኩ።
የመከላከያ ቁመና የደከመነ ነው። መከላከያ የሞተ ቁመና ነው ያለው። የመከላከያ ሰራዊት ተበትኖል። ምግብ የለም? ኮችሮ ነው የሚበላ ኮቸሮ እራሱ ብዙ ግዜ አይገኝም። መከላከያ በብዙ ነገር የተጎዳ ነው። በስነልቦና እና በስሜት በጀግንነት እየተጎዳ ነው ያለው። መከላከያ ህዝቡን በሙሉ እየጎዳ ነው ያለው። ይህ ሁሉ የሚሆነው መከላከያ ህዝቡን ከማገልገል ይልቅ በማይረፖ የአብይ የፖለቲካ ቁማር ብሎ ህዝቡ ላይ ብዙ ግፎችን እነፈፀመ በመገኘቱ ነው።
እኔ አማረኛ በመናገሬ እና አማረኛ የሚናገሩ የደቡብ፣ የወላይታ፣ የሱማሌ የሌሎች ብሔር ተወላጅችን መብታችንን አይከበርም? መከላከያ ከሆን የሀገርን ዳር ድንበር ማስከበር እንጅ ከህዝብ ጋር ለምን እንገጥማለን ብለን ስንጠይቅ አንተ ምንድን ነው የምታወራ እንባላለን?
እንታሰራል እንገደላለን። ለዛም ነው ወደ ፋኖ የመጠሁት።
ፋኖ አቅም የለውም ይሉናል? ግን አሁን ወደ ፋኖ ገብቼ ሳየው በጣም ነው የተደሰትኩት አማራ ሆኜ በጣም ነው የኮረሁት። እዚህ ለብዙ ወራት በልቼ የማላውቀውን የጤፍ እንጀራ ምግብ በለው ውሀ ጠጠው ስልክ ተገዝቶልኛል።
ቢቸና ከተማ ሴትም ሳይቀር አማራ ነው በሎቸው እንባል ነበር?
አማራ በመሆኔ ብቻ ደስተኛ ነኝ የአማራ ፋኖ እውነት ነው ይዋጋል ጀግና ነው። ሀገር ያስከብራል ያኮራል 64ኛ ክፍለ ጦር ያለው መሳሪያ መከላከያ የለውም መንግስት ላይ የለለ መሳሪያ እዚህ እኔ በአይኔ አየሁት ሹተር የሚባል መሳሪያ አይቼ ሰምቼም አላውቅም እዚህ ግን ታጥቋል። ይሄ መሳሪያ ነው ስትለኝ ደንግጫለሁ ምክንያቱም እኛ ጋር እንደዚህ አይነት መሳሪያ የለም?
አማራ ክልልን ለመውረር የገበው መከላከያ ገጥሞ የሚያሸንፍ የፋኖ ሰራዊት ብቻ ሳይሆን ያለው የሀገርን ዳር ድንበር የሚስገብር ለውጭ ወራሪ የሚጠብቅ ጀግና ሰራዊት ነው ያለው፣ እዚህ የተለያዩ ኮማንዶ አሉ፣ ጠላት በእርቀት ቁመናቸው የሚያስፈራ ወጣቶች ያሉበት ፋኖ ነው ያለው።
ውሀ ሳናገኝ ምግብ ሳናገኝ ደሞዛችን ዝቅተኛ ነው። ጀሞዝ ቢሰጠንም ከተማ አንሄድም ብንሄደም ፋኖ መቷል ተብለን እሩጫ ነው። በጣም ስቃይ ነው ያለው።
ውጊያ ላይ በጣም የምወደው ጎደኛ ሲቆስል አለቃየ አንተ የምትወደው ጎደኛህ ነው ግደለው አለኝ? እኔ አልገልም ስለው እነሱ ገደሉት። ቁስለኞችን ማሳከም የማይችል መከላከያ ነው ያለው?
እኛ ስሜታዊ እንሆናለን አንዳንዴ እርስ በእርስ እንታኮሳለን ይህ የሚሆነው ሁኔታው ያስጠላል የአማራ እና የኦሮሞ የደቡብ የሶማሌ ብሔር ሲነሳ ሁላችንም አንግባባም እርስ በርስ እንገጥማለን። በዚህም ብዙ ሰው ሞቷል ቆስሏል።
ከአማራ ክልል ውጊያ ከወጣን ወደ ኤርትራ እና ሶማሌ ለመዋጋት በአለቆቻችንን ትዛዝ ተሰጥቷል። አማራን ሰላም አድርጊያለሁ ይላል በጉራ? ግን ውስጡ ለቄስ ነው ዝብሎ የውሸት ወሬ ያወራል? የአማራ ወጣት በጀግንነት ለህልውናው እየታገለ እያሳየ ነው የሚገኘው። አማራ ክልል ፋኖ የሌለበት ቦታ የለም። ፋኖ የእውነት ታጋይ ነው። አማራ በአድዋ ጦርነት ዘምቷል። በትግራይ ጦርነት ሀገሬን አላስደፍርም ብሎ ነው የሚታገለው። አማራ አማራ ነው ሀገር መምራቱ መቸውም አይቀርም ?መከላከያ ሀገር እየመራው ነው ይላል ይህ ውሸት ነው። አማራ ክልል ፋኖ ነው እየመራ የሚገኘው። ህዝቡን ሁሉ ፋኖ ነው የሚያስተዳድረው።
በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ አብዛህኛው አመራር ኦሮሞ ነው። ኦሞኛ ቋንቋ ካልተናገርክ አመራር መሆን በፍፁም አንችልም። ጄኔራል እና ኮለኔር ሳይቀር አማራ የሆነውን ሁሉ በጅምላ ጨፍጭፍ ተብለን ታዝዘናል። እንደዚህ አይነት ትዛዝ እኔን ልቤን ያመኛል? እኔ አማራነቴ ትውልዴ ስለሆነ ምቱ ሲለኝ ልቤ ተዘይጎዳል። እኔንም መግደል ይፈልጋል? ለምንድን ነው የማትገል ይሉኛል? ሰው ሴት ሳትቀር መጨፍጨፍ ቤተክርስትያን ውስጥ ገብታቹህ አቃጥሉ ይሉናል። እኔ ይህንን ተቃውሜ ወደ ፋኖ ገብቼ ተቀላቅያለሁ። እኔ የአንገት ማተም መስቀል እንዳታደረጉ ተብለን ደብቄ ነው ያለው። ቄስ ሻሽ አድርጎ ሲሄዱ ግደሉ ተብለናል? እንዴት ሰው ዝምብሎ ሰው ይገላል።
መካላከያ ወጣቱን በመግፋት ህዝቡ በስሜት እንዲነሳ እንዲያምፅ እንዲወጣ ነው እያደረገ ያለው። ወጣቱ ሰርቶ እንዲበላ አያደርግም? ስሜታዊ እያደረገ ነው ያለው? የፋኖ ቤተሰብ ነው ተብሎ ሰው እንዴት ይገደላል። ሰው ከአጠፋ በህግ እና በህግ መጠየቅ ሲገባ ገብሬኤል ሰፈር #ሚሊሻ ሙስሊም ንፁሀን ገድሏል። ባጃጅ ይዞ የሚሰራ አንድ ልጅ ገድሏል። ሌሎችን አቁስሏል። ባጃጅ አቃጥሏል። በህግ እና በህግ መጠየቅ እንጅ ንፁሀን እንዴት ይገደላል። እኔም ስሜታዊ ሆኜ የወጠሁ በዚህ ግፍ ጭምር ነው።
መከላከያ ሰራዊት ያላቹህ ወደ ፋኖ ተቀላቀሉ የእኔም ጎደኞች ወደ ፋኖ ተቀላቀሉ። የጤፍ እንጀራ እየበላቹህ ኑ ታገሉ። አትራቡ እኔ የአማራ ልጅ ነኝ ለሞት አልጨነቅም እናተም ኑ ወደ ፋኖ ተቀላቀሉ በማለት አጭር መልክቱን ለአማራ ህዝብ እና ለመላው የኢትዮጰያ ህዝብ እንዲሁም ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት በአማራ ህዝብ ላይ እየሰራው ያለውን ግፍ እና በደል የጅምላ ጭፍጨፋ በይፋ ገልፆል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ!
ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም
ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
+2
ጀግንነት+ ሰብአዊነት + ፍርድ አዋቂነት + የስነልቦና ልዕና ከፍታ + አቃፊነት + ሆደሰፊነት +ርህሩህነት = ዐምሓራነት!!!
የምርኮኞችን ስነልቦና ለማረጋጋት የጧት ፀሐይ በማሞቅ፡ አዕምሯቸውና አካላቸው እንዲፍታታ ማድረግ እና ለቁስለኛ ምርኮኞች ሕክምና በመስጠት ላይ!
(ምስል፦በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጊዜያዊ የምርኮኞች ማቆያ ጣቢያ)
