ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多3 721
订阅者
+4524 小时
+1767 天
+1 15530 天
帖子存档
+1
በደብረ ማርቆስ ከተማ 206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከሌሊቱ 7:35 በጠላት ፓትሮል ላይ በፈፀመው የቦንብ ጥቃት 9 ሚኒሻዎች ሙትና ቁስለኛ ሁነዋል።
ይካቲት 2/2018 ዓ.ም
======================:============
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን መፈንጫ በሆነችው ደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:35 ከማረሚያ ቤት ወደ መሐል አደባይይ ሲሔድ በነበረ ፓትሮል ላይ የኮሩ አዳኝ ቡድን በፈፀመው የቦንብ ጥቃት 3 ሚኒሻዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ 6 ሚኒሻዎች ከባድና ቀላል ቁስለኛ ሁነዋል።
ጨለማን ተገን በማድረግ በሌሊት ንፁሐንን አፍነው ማረሚያ ቤት አድርሰው ሲመለሱ በነበሩ ሚኒሻዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የከፈተው አዳኝ ቡድኑ በፓትሮሏ ስፖንዳ መሐል የተሳካ የቦንብ ጥቃት በመክፈት የጠላትን ኃይል ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል።
ከቀናት በፊት በደብረ ማርቆስ ከተማ አስደናቂ የቦንብ ጥቃት የፈፀመው አዳኝ ቡድኑ ከሁለት ቀን በኋላ ተመሳሳይ ድል የተቀናጀ ሲሆን እስከ አሁን በተፈፀሙ ተከታታይ አስደናቂ የከተማ ኦፕሬሽኖች ምንም አይነት መስዋትነት በወገን ኃይል በኩል አልተመዘገበም።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ከሀገር መነጠቅ ወደ ነፃነት/የሀገር ባለቤትነት — የህልውና ጥሪ ለአማራ ልጅ ሁሉ!
ዛሬ አማራ መሆን ዋጋ እየአስከፈለ ባለበት፣ በገዛ ሀገሩ እንደ ባዕድ በሚቆጠርበት እና የመጠለያ ካምፖች የብዙዎች ብቸኛ "ቤት" በሆኑበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። ከታዳጊ ተማሪው እስከ አንጋፋው ምሁር፤ ከገበሬው እስከ ነጋዴው ድረስ ልባችንን ለአንድ እውነት እንክፈት።
ለምን አሁን?
የንጹሐን ሰቆቃ፦ እናቶች በየሜዳው ሲወልዱ፣ አባቶች ልጆቻቸውን በረሃብ ሲቀብሩ፣ ተማሪዎች የትምህርት ገበታቸው በመጠለያ ድንኳን ሲተካ ዝምታው ይብቃ።
የማንነት ጥቃት፦ መሳደድ፣ መፈናቀል እና መገፋት የአማራ ዕጣ ፈንታ ሊሆን አይገባም።
የምሁራንና የተማሪዎች ኃላፊነት፦ እውቀትና ጉልበት ካልተባበረ፣ ታሪክ ነገ በሁላችንም ላይ ይፈርዳል።
ጥሪያችን፡
ይህ የዘር ማዳን ጥሪ ነው። መከፋፈልን ወደ ጎን ትተን፣ በምክንያታዊነት እና በበሰለ መንገድ ተሰባስበን ለወገኖቻችን ድምፅ እንሁን። በመጠለያ ካምፕ ላለው ወገናችን ነፃነት፣ ለተሳደደው ወንድማችን መከታ፣ ለቆሰለችው እናታችን ፈውስ የምንሆነው በአንድነት ስንቆም ብቻ ነው።
"አንድነት ኃይል ብቻ ሳይሆን፣ ህልውናም ጭምር ነው!
መነሻቸውን ከፍኖተሰላም አድርገው ወደ ጂጋና ሆዳንሻ እየተቀሳቀሱ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ በተወሰደ ሽምቅ ጥቃት ከ24 በላይ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ!
ጥቃቱ የተጠናና እጅግ ፈጣን ነበር የተባለ ሲሆን፡ የጠላት ወታደሮች ተሳፍረውበት ከነበረው ተሽከርካሪ ሳይወርዱ ነው በቦምብና በክላሽ ያለቁት።
በተመሣሣይ፡ ከፈረስቤት ከተማ ወደ ዳማ ቀጠና መንቀሳቀስ ላይ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ፋኖ በፈፀመው የከበባ ጥቃት ታላቅ ድል ተቀዳጅቷል።
በዚህም የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛውን የሚያነሳበት አፍታ እስኪያጣ ድረስ ከባድ የጥቃት ዶፍ ወርዶበታል።
*
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ እንዲሁም 1ኛ ሻለቃ አባላት ትናንት የካቲት 01/2018 ዓ/ም ማለዳ ከፍኖተ ሰላም ወደ ጂጋና ሆዳንሽ ከተማ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ በፈፀሙት የሽምቅ ጥቃት ከ24 በላይ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል መቀዳጀታቸውን ጣቢያችን ለማረጋገጥ ችሏል።
ጥቃቱ የተፈፀመው ዛሬ ከማለዳው 12:00 ሰዓት አካባቢ ላይ ሲሆን፡ የጠላት ወታደሮች ተሳፍረውበት ከነበረው ተሽከርካሪ ሳይወርዱ ነው በቦምብና በክላሽ ያለቁት።
በዚህ ጥቃት ዘጠኝ የአገዛዙ ወታደሮች ወዲያውኑ ሲገደሉ ከ15 በላይ የሚሆኑት ክፉኛ የቆሰሉ ሲሆን፡ በድምሩ ከ24 በላይ ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸውን ነው መረብ ሚዲያ ከ109ኛ ኮር ለማረጋገጥ የቻለው።
በተመሣሣይ፡ ከፈረስቤት ከተማ ወደ ዳማ ቀጠና መንቀሳቀስ ላይ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ፋኖ በፈፀመው የከበባ ጥቃት ከባድ ጥቃት በመሰንዘር ታላቅ ድል ተቀዳጅቷል።
በዚህም የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛውን የሚያነሳበት አፍታ እስኪያጣ ድረስ ከባድ የጥቃት ዶፍ ወርዶበታል።
በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ከፈረስቤት ከተማ ወደ ዳማ ቀጠና መንቀሳቀስ ላይ በነበረ የጠላት ኃይል ላይ በወሰዱት የቆረጣ ጥቃት ድል መቀዳጀታቸው ታውቋል።
የፋኖ አባላቱ፡ ወደ ዳማ ማርቆስ እየተጓዘ የነበረውን የጠላት ሰራዊት ነው ከበባ ውስጥ በማስገባት በፈፀሙበት ጥቃት አስከሬኑን ሳያነሳ ወደ መጣበት እንዲፈረጥጥ ያስደረጉት።
ይህ በእንዲህ አንዳለ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99 ክ/ጦር ስር 3ኛና 4ኛ ሬጅመንት በጋራ በመሆን ወደ ደጋ ዳሞት ፈረስ ቤት ከተማ እየተጓዘ በነበረ የጠላት ኃይል ላይ በወሰዱት እርምጃ በርካታ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል ተቀዳጅተዋል።
አፋብን ለዓለም አቀፍ ሚዲያወች ስለ ወቅታዊ የአማራ ትግል ማብራሪያ ሰጠ።
የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ባዘጋጀው የሚዲያ ብሪፊንግ መድረክ የአማራ የህልውና ትግል ጠቅላላ ሁኔታ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስረታ፣ የጦርነቱ አጀማመር፣ ትግሉ ያለበት ነባራዊ ሁኔታ፣ ስለ ሰብአዊ መብት አያያዝ፣ ስለ ምርኮኞች እና የጦርነት ህግ አተገባበር፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአማራን የህልዉና ትግሉን በመረዳት ረገድ ስላለው ክፍተት እና ሌሎችም ጉዳዮች ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ቀርቧል።
በተጨማሪም ከጋዜጠኞቹ ለቀረቡት ጥያቄወች በመምሪያ ኃላፊው በኩል ማብራሪያ እና ምላሽ ቀርቧል። በሚዲያ ብሪፊንግ መድረኩ ላይ ሮይተርስ፣ ኒውዮርክ-ታይምስ፣ ፍራንስ-24፣ አሶሼትድ-ፕሬስ፣ አልጃዚራን ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያወችን የወከሉ እና ሌሎች የውጭ ሚድያ የግል ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል።
አንድ ስንሆን እንዲህ መደመጥ እንጀምራለን!!
“ዘመነ ካሴ ከኤርትራ ሁኖ የፋኖን ሰራዊት ያዝዛል” ብለው ፕሮፓጋንዳ ሊሰሩ የሚሞክሩት ‘የአስተሳሰብ ድንክ መሀይማን’ አብይ አህመድ ከአረብ ኢምሬቱ ቢንዛይድ በቀጥታ እንደሚታዘዝ የምትነግሩን ራሳችሁ አይደለም ወይ? ብለን አቻ ምላሽ አንሰጥም። ተላላኪነትን በታሪክም ሆነ አሁናዊ ታሪካችን ላይ አይገኝም። እንደ ህዝብ የተደረገብንን የዘር ፍጅት ‘ተላላኪነት በሚል ሾተላይነት’ እንዲዳፈን (Deny) እንዲደረግ አንፈቅድም። የሆነብንን ሁሉ አንረሳም።
፤
የትም ቦታ ላይ ይሁን ግን ‘በመሪ የሚታዘዝ ኃይል መኖሩን’ ማመናችሁ በቂ ነው። It is enough for them to believe that there is a millitary power that is guided by a chain of command from wherever you are.
፤
የቦሌ መንገዱ በር በእጃችን እስኪገባ በሱዳንም ሆነ በሱማሌ፣ በኤርትራም ሆነ በጅቡቲ፣ በኬንያም ሆነ በደቡብ ሱዳን መሿለኪያ በሮች ሁሉ ተዟዙረን የዲፕሎማሲ አቅማችንን እየገነባን “ዓለም ላይ ሊኖረን የሚገባውን የግንኙነት መረብ” እናሳልጣለን። በዚያ መስመር ውስጥ አፍሪካም ሆነ አሜሪካ፣ አውሮፓም ሆነ ኤስያ እንዲሁም አረቡ ዓለም አሉ።
፤
በህፃን ልጅ እጅ ላይ ያለውን ስልጣን እንዳይፀና እንዳደረግነው ሁሉ ከእጁ ነጥቀን ለሀገር የሚበጅ ተግባርን እንሰራበታለን። ይህ የነገን ጮራ መውጣት ያክል ቅርብ ነው።
፤
ፍርሀትና ስጋት ብዙ እንደሚያናግር ብናውቅም ከመሆን የማይገድበንን ነገር “የአብይ ሳይበር፣ የጁላ እግረኛና የይልማ አየር ሀይል” ተረባርበው ያልቀለበሱትን የፋኖን ትግል በከዳተኛ የወሬ ድሪቶ ልትመክተው አትችልም።
፤
እንዴትስ ተሁኖ!?
፤
የቁስ ሰቀቀን ያለባቸው ሁሉ የዚህን ትግል ቅድስና በፍፁም ሊረዱት አይችሉም። እኛ የረከባ ጥጃ ጠብቀን አላደግንም። የነፃነትን ታሪክ ሀሁ ብሎ ያስተማረን ህዝብ ልጆች ነን። በትግላችን የክብር (Dignity)፣ ኩራት (pride)ና ማንነት(identity) ታሪክ እየተፃፈ ነው።
፤
📷 ለማንኛዉም ከታች ያለው ምስል ጎዣም አማራ ውስጥ ሲሆን በቪዲዮ ጥሪ ከኤርትራ የሚያዝዘው ዘመነ ካሴና በቪዲዮ ጥሪ ከኤርትራ የሚታዘዙት የተባሉት እነ ማንቼ የትላንት ውይይታቸው ላይ የተነሳ ፎቶ ነው።
©️Manchilot
የአፓርታይዱ የአብይ አህመድ አገዛዝ በንፁሃን ላይ የድሮን ጥቃት ፈፀመ።
ጥር 30/2018 በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ 011 ቀበሌ ሰርኮ አማራ ጠሉ የአብይ አህመድ ስርዓት ንፁሃንን በድሮን በመጨፍጨፍ ጠላቻውን በአደባባይ ገልጿል።
በድሮን ጥቃቱ አንድ ወጣት ህይዎቱ ሲያልፍ ከ 6 ቱ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በጥቃቱ በርካታ እንስሳቶች መገደላቸውንም ማረጋገጥ ተችሏል። የአማራ የሆነን ሁሉ ማጥፋት የሚያስደስተው ጨፍጫፊ ስርዓት ስድስት የንፁሃንን ቤት ማውደሙም ተረጋግጧል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 1/2018 ዓ.ም
ጉና ክፍለ ጦር
የዓምሐራ ፋኖ በሥማዳ መዳረሻ ወገዳ ከተማና ዙሪያ ገባው ድልን ተቀዳጅቷል❗
[የካቲት 01/2018ዓ.ም]
ዓምሐራን የነካ
የለውም በረካ
እንዲል የቤተ ዓምሐራው ዓምሐራ በዓምሐራ ሕዝብ ላይ ዘርፈ ብዙ ጥፋትን ሲፈጽም የነበረው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ጠርንፎ ለመውጣት በተዘጋጀበት ሰዓት የጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የባዬው መልካሙ፣ የፍቃዴ አለባቸው፣ የአበበ፣ የሸጋው (ገብርዬ)ና ጥንቅሹ የግብር ልጅ የሆነችው ጠንካራዋና አይበገሬዋ እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ እና የሢሣይነው ራዕይ አሥቀጣይ የሆነችው ሥማዳ ሐገረ ቢዘን ብርጌድ በጋራ የተቀናጀ አውደ ውጊያን ሲያደርጉ ውለዋል። የዓምሐራ ፋኖ የአገዛዙን የተለያዩ ምሽጎችን በክንዱ ሰባብሯል፤ ተቆጣጥሯል። ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ እሥከ ቀኑ 11:00 በዋለው እልህ አሥጨራሽ ትንቅንቅ የዓምሐራ ፋኖ ድልን ተቀዳጅቷል። ዓምሐራ ፋኖ በጠላት ላይ ከፍተኛ የሆነ የአካል፣ የቁሥና የሥነልቦና ኪሳራ አድርሷል። የአገዛዙ ታጣቂዎችና የአገዛዙ የቡድን መሣሪያ እሥከነፍሥ ወከፍ መሣሪያ ምርኮ ሆኗል። የወገዳ ከተማ ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ሥር የሚገኝ ሲሆን ጠላት የምጽአት ቀን ይደርሥለት ዘንድ ''ሸረፍ ጎዴ'' ተራራን እየተማጸነ ይገኛል።
በኮንክሪት የተሰራው የአቦ ምሽግ በዓምሐራ ልጆች ተጋድሎ ተሰብሯል። የጠላት ብዙዎቹ ምሽጎች ሲሰባበሩ ጠላት የመጨረሻ መዳኛዬ ወዳለውና የቁም ምሽግ ወደሰራበት ''ሸረፍ ጎዴ'' 360° ተራራ ሩጦ ገብቷል። ጠላት ሸረፍ ጎዴ ተራራን አድነኝ ሲል በተማጽኖ ይገኛል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑✊
አፋብን
ሰሜን ዓምሐራ ቀጠና
በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
ጎንደር/ዓምሐራ/ኢትዮጵያ
የካቲት 01/20178ዓ.ም
+1
የብልፅግና ካዝናና የጦር ካንፕ ባዶውን እየቀረ ነው!!!
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
✔️ አያሌው ደመቀና ደጉ ደረበ የተባሉ ሁለት የአገዛዙ ሚሊሻዎች ከአዴትና ከባህርዳር አንድ ሁለት እግርና አንድ ሰደፍ ክላሽ በመያዝ በቀን 01,06,2018ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦርን ተቀላቀሉ።
➯ በሌላ ዜና :-
✔️ በቀን 01,06,2018ዓ.ም የብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት መነሻውን መኮድ በማድረግ የ22ኛ ክፍለጦር ሻለቃዎችን ለማጥቃት ወደ ባህርዳር ዙሪያ ተንተላ ይጎዲ ቀበሌ የተንቀሳሰቀሰው የጠላት ሀይል ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ልዩ ስሙ ተንተላ ይጎዲ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ በ22ኛ ክፍለጦር ሻለቃዎች በተደረገበት ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት የተበሳጨው ሰው በ*ላው የፋሽስቱ ሰራዊት ሞላ ሳለ የተባለ የ60 አመት ንፁሀን አዛውንትን ባህርዳር ዙሪያ ይጎዲ ቀበሌ ላይ በግፍ እረሽኗል።
ፋኖ አማረ ጌታቸው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር ህዝብ ገልጿል ግንኙነት!
የካቲት 01,2018ዓ.ም
ክፋት ለማንም! በጎነት ለሁሉም!
አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!
አዲስ ተስፋ!
+2
የዐብይ አህመድ አገዛዝ በግንባር ከባድ ሽንፈት ሲገጥመው ንጹሃን ላይ ወዳተኮረ ጅምላ ፍጅት ተሸጋግሯል
ኔትዎርክ እና የስልክ አግልግልት በማቋረጥ ልዩ የማጥቃት ዘመቻ የከፈተው የዐብይ አህመድ ሰራዊት በአጠመበት ግንባር ሁሉ እየተማረከና ሙትና ቁስለኛ እየሆነ መበተኑ በፈጠረበት ስጋት በዐብይ አህመድ ትዕዛዝ እየተወሰደ ያለው የበቀል እርምጃ የሥርዓቱን ተራ ሽፍታነት የሚያሳይ ነው።
የንጹሃን አርሶአደሮችን ቤት በከባድ መሳሪያ ማፍረስና ማቃጠል፥ ከግንባር ፈርጥጦ ያመለጠው ሰራዊት ከተማ ላይ ንጹሃንን መረሸን ዋነኛ ተግባሩ በማድረግ የጦር ወንጀል መፈጸሙን ቀጥሏል።
እያንዳንዱ በከባድ መሳሪያ እና በድሮን እየፈረሰ ያለው የአርሶ አደር ቤት እና ቤት ለቤት የመረሸን ተግባር በማስረጃ መሰነዱ ይቀጥላል። ይህ የወንጀል ፋብሪካ የሆነ አገዛዝ ምን እየፈጸመ እንደሆነ ዓለም ሊያውቀው ይገባል።
አፋብን| ቴዎድሮስ ዕዝ
የካቲት 01/2018 ዓ.ም
__፩
201ኮር ድልን ተቀዳጀ።
በአማራ ህዝብ ላይ የተቃጣውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ቆርጦ የተነሳው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በየግንባሩ እያስመዘገበ ያለው ድል ቀጥሏል።
የአገዛዙ ሠራዊት በጀግኖች ፋኖዎቻችን እና ነቅቶ በታጠቀው አርሶ አደር ክንድ ክፉኛ እየተመታ መሣሪያውን እያስረከበ ይገኛል።
በሰከላ ግንባር፦ ከአበስከን ወደ ብር አዳማ ሲንቀሳቀስ የነበረው የብልጽግና ሠራዊት በጀግኖች የቁርጥ ቀን ልጆች አይቀጡ ቅጣት ደርሶበታል። ሠራዊቱ ካረፈበት ጦር ሠፈር እስኪገባ ድረስ በፋኖ ብርቱ ክንድ ሲገረፍና ሲናዘዝ ውሏል።
በአርሶአደሩ እና አዳኞቹ መሳሪያን መማረክ የቻሉ ሲሆን አረመኔው ሰራዊት ደግሞ የደረሰበት ሽንፈት ሕዝብ እንጨፍጭፍ አናስጨፈጭፍም በሚሉ መካከል በተነሳ ተኩስ ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል።
__፪
102ኛ ኮር በርካታ የአገዛዙ ሀይልን በደፈጣ ጥቃት ተደመሰሰ
➡️1ኛ
በዛሬዉ እለት በቀን 01/06/2018 ዓ.ም ከፍኖተ ሰላም ወደ ጂጋ ሆዳንሽ እንቅስቃሴ የነበረ የጠላት ሃይል ላይ በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ እና 1ኛ ሻለቃ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ በወሰዱት የደፈጣ መብረቃዊ ጥቃት በርካታ የጠላትን ሀይል ተደመስሷል።
ዘራፊውና ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ ወራሪ ሀይል መነሻውን ከፍኖተሳላም ወደ ሆዳንሻ በሚንቀሳቀስበት ሰአት በጦር ጠበብቶቹ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር በወሰዱት የሁለቱ ሻለቃዎች የተቀናጀ የደፈጣ ጥቀታ ዘጠኝ(9) የጠላት ሀይል የተደመሰሰ ሲሆን ከ15 በላይ የጠላት ሀይል ከባድና ቀላል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
➡️2ኛ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ክ/ጦር በቀን በቀን 29/05/ 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 4:00 ከፈረስቤት ከተማ ወደ ዳማ ቀጠና መንቀሳቀስ ላይ በነበረው የጠላት ሀይል ላይ በሻለቃ 3 በወሰደችው መብረቃዊ ጥቃት ታላቅ ጀብድ ፈፅሟል።ወደ ዳማ ማርቆስ የመጣውን ሰራዊት ከበባ ውስጥ በማስገባት ሲያስጨንቁት የዋሉ ሲሆን አስከሬኑን ሳያነሳ ወደ መጣበት ፈርጥጧል።
ይህ በእንዲህ አንዳለ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99 ክ/ጦር የሻለቃ 4 ከአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ከሻለቃ 3 ጋር በመናበብ ወደ ደጋ ዳሞት ፈረስ ቤት ከተማ በመግባት በጠላት ኃይል ላይ በወሰዱት ጥቃት በርካታ የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 01/2018 ዓ.ም
ሰበር የድል ዜና‼️
ደቡባዊ ጎንደር ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ ከጠዋቱ 2:20 እስከ 10:00 ሰዓት በተደረገ ው*ጊያ የአብይን ሰራዊትን በመደምሰስ ፋኖ ሙሉ በሙሉ ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማን ተቆጣጥሯል !!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ✅
#ኑ_ፋኖን_ተቀላቀሉ‼️
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ከየ አቅጣጫው ወደ ጦርነት ሊገባ መሆኑን የተገነዘበው ሰራዊቱ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም የአድማ ብተና አባላት ከኦህዴድ ብልፅግና ጋር ሆነን ወገናችንን አንወጋም በማለት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 1/2018 ዓ.ም
ከአርባያና ከደጎማ የፈረጠጠው የአብይ ወንበር አስጠባቂ ኃይል ክፉኛ ተመታ።
ዛሬ የካቲት 02/2018 ዓ.ም የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካሎች ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ጎንደር ብርጌድና ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ድል በር ብርጌድ ከቃሃሪ እስከ ጭንጫየ የሸፈነ አውደ ውጊያ በማድረግ ጡት ቆራጩን የአብይ ኃይል ሙት ቁስለኛና ምርኮኛ ተደርጓል።
በድንገት ከፍተኛ ምትን ያስተናገደው ጠላት እግር አውጭኝ ፈርጥጦ ማክሰኝት ከተማ ሊገባ ችሏል።
➧ በዚህ ውጊያ ከተገኙ ድሎች መካከል
➧ 08 የሞተ /3 መከላከያ ፣ 5ሚሊሻ /
➧ 02 የተማረከ /1 ፖሊስና 1 ሚሊሻ / በድል በር ብርጌድ ተመርከዋል።
-- ቁጥሩ በእውን የማይታወቅ የጠላት ኃይል እስከ ወዲያኛው በክንደ ፈርጣማዎቹ ፋኖዎች እንዲያሸልብ ተደርጓል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አብነት ሞላ
ጥር 01/2018 ዓ.ም
አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ገድል ተሰርቷል!!
አገዛዙ የቴሌኮም አገልግሎቶችን በመዝጋት በሸዋ አማራ ላይ የሰነዘረው ጥቃት ከሺፏል።
በሸዋ ሁሉም ቀጠናዎች በሚባል ደረጃ የተጀመረው መጠነ ሰፊ ማጥቃት በሰራዊታችን ጠንካራ ክንድ ተመክቷል።የፋሺስቱ አገዛዝ ከምስራቅ ሸዋ እና ሸገር ከተማ አስተዳደር ከተቋቋመው የገዳ ኮማንዶ እና የሪፐብሊክ ኮማንዶ እንድሁም ባህር ሃይል በማዝመት በመላው ሸዋ ከፍተኛ ወረራ እየተካሄደ ሲሆን የአፋብን ከፍተኛ አመራር ጉዳዩን ትኩረት በመስጠት ተጨባጭ የአፀፋ እርምጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረግ!!
ሰሞነኛው የብልፅግና አገዛዝ በሁሉም የአማራ ቀጠናዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል ስለሚችል ሁሉም በየደረጃው ያለው አመራር ጠንካራ ዝግጁነት ሊኖረን ይገባል!!
መዳረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሸንፋል!!
+1
የኦሮሙማ ስራ ሲገለጥ ፀረ ገዳማውያን ፀረ መነኮሳት ፀረ ቤተክርስቲያን ፀረ ሰው ፀረ ኢትዮጵያ ፀረ አማራ ።
እሔው እንሂ መናኒያን አባት አሁን ምን አድርገው ነው ? የሳዊሮስ ስራ ሲገለጥ እሔው ነው🥺😥
📝አሳዛኝ ዜና በአሰቦት ገዳም
👉 እጅግ ልብ የሚሰብር ሀዘን ጥር 28, 2018ዓ.ም አሰቦት ገዳም በዓታቸው ውስጥ ተገድለው የተገኙት ባሕታዊ አባ መብራቱ ፣ ለብቻቸው ዘግተው የሚኖሩ ባሕታዊ ነበሩ ፣በመሳሪያ ተገድለው ነው እንደተገኙ የመረጃ ምንጮች ከቦታው አድርሰውናል ፣
👉 ይህን ድርጊት ማን ፈጸመው ? ግድያው በር ዘግተው ለቤተክርስቲያን እና ለሀገር በሚጸልዩ መናንያን ላይ መሆኑ ልብ ይሰብራል፣ ይህ ለምንደኞች ካህናት በሀገርም በውጭም ላሉ ምን ላይመስላቸው ይችላል ፣ ግን እግዚአብሔር ፍርዱን ይሰጣል ፣ የአባታችን በረከት በሁላችን ላይ ይደር 🙏
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር "ሰባት ለሰባ" ክፍለ ጦር በኢፍራታ ግድም ወረዳ ድል ተቀዳጀ!!
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ስር የሚንቀሳቀሰው የደቡብ አማራ ቀጠና፣ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር "ሰባት ለሰባ" ክፍለ ጦር አናብስቶች በኢፍራታ ግድም ወረዳ፣ ፈርድ ውሃ ቀበሌ ላይ በወሰዱት ወታደራዊ እርምጃ ድል አደርጉ።
ከአንድ ወር በፊት በግፍ የተሰዋውን የክፍለ ጦሩን ቃኘ መሪ አርበኛ ሸጋው ግርማን በማስታወስ የክፍለ ጦሩ ንስሮች ዛሬ ጠዋት 12:00 ስዓት በፈርድ ውሃ ቀበሌ ላይ ካምፕ መሽጎ ህዝብን ሲዘርፍና ሲያሰቃይ በነበረው የአረመኔው አብይ አህምድ ወንበር አስጠባቂ ሚኒሻ ኃይል ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር ሙትና ቁስለኛ በማድርግ ድልን ተጎናፅፋዋል።
በመሆኑም አይቀጡ ቅጣት የተቀጣው የብአዴን ቅጥርኛ ሚሊሻዎች ላይ ሙትና ቁስለኛ አድረገው የተወሰኑት ደግሞ እስከ ወዲያኛው መሰናበታቸው ተረጋግጧል፦
1,ሞገስ ክፈተው
2,ቸርነት አደፍርስ
3,ቻለው ጥላሁን
4,ዳምጠው ጌቱ እና 3 ሶስት በስም ያማይታወቁ ባንዳ ሚሊሻወች እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል
የተማረኩ የጠላት የነፍስ ወከፍ መሳሪያ
1 ባለ ሁለት እግር (2) ሁለት ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች
2 , አንድ m14 መሳሪያ ከሙሉ ትጥቅ ጋር በመማረክ ደማቸውን መልሰዋል። በመጨረሻም የአካባቢውን ህዝብ ለአንድ ዓመት ያህል በከባድ እንግልትና በዝርፊያ ሲሰቃይ የነበረው የፈርድ ውሃ ቀበሌ ህዝብ በታልቅ ክብር ፋኖን እንኳን መጣችሁልን ብሎ አብልቶ አጠጥቶ አጋርነቱን አሳይቷል። የወገኖቻችንን ደም በከንቱ እንደፈሰሰ አይቀርም" በሚል ቃል በገቡት መሰረት፣ የጥፋት ኃይሎችን የማጽዳት ስራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።
ድል ለአማራ ህዝብ!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
አርበኛ አማረ ታዘዘ
ይካቲት 01/06/2018 ዓ.ም
