ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多3 613
订阅者
+1324 小时
+4187 天
+1 05630 天
帖子存档
በሸኔ እና በአብይ አህመድ ጡት ቆራጭ ኃይል ሰባት ንፁሀን ዜጎች ተገደሉ !!
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ውስጥ ባለፉት ሁለት ቀናት በሸኔ ታጣቂዎች የተፈጸሙ ጥቃቶች ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት አድርሰዋል። በተለይ አማርኛ ተናጋሪ ማህበረሰቦች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈጸመ ይገኛል። መጀመሪያ የተፈጸመድ እሑድ የካቲት 19 ማታ ሲሆን፣ በደንበዛ ጅብ በሚባል ቀበሌ ላይ ነበር። በዚህ ጥቃት ቁጥር የማይታወቅ መኖሪያ ቤቶች እና ንብረቶች ወድመዋል። ነዋሪዎቹ ከዶሮ፣ ከብት እና ሌላ ንብረታቸው ጋር ምንም ሳይዙ ለሕይወታቸው በመሸሽ ላይ ናቸው።
አርብ ማታ (የካቲት 21) ደግሞ ጥቃቱ በጊርሚ ጎባ እና በቢስጭኖ ጤራ ቀበሌዎች ላይ ተከስቷል። በዚህ የዘመቻ ማግስት ብቻ ሰባት ንፁሀን ዜጎች የተገደሉ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል አሮጊቶች እንደሚገኙበትና አንዲት አሮጊት በመኝታ አልጋዋ ላይ እንደነበረች እሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋለች። በተለይም ሰዎችን እየጎተቱ እሳት ውስጥ እየከተቱ ቤት ዘግተው ነው ያቃጠሏቸው። በእውነት ከእግዚአብሔር የተፈጠሩ ፍጡራን በማይመስል መልኩ ግፍን ተፈፅሟል።
ጥቃቱን የፈጸሙት የሽመልስ አብዲሳ የዳቦ ስም ታጣቂዎች ሸኔ ሲሆኑ ከባድ መሳሪያ ጭምር በመያዝ RPG እና ስናይፐር ይዘው እንዲሁም በዚህ በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ አማርኛ ተናጋሪ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ናቸው። የኦሮሞ የእነሱ ሰው ቤቱ አይቃጠልም... ይሄንን ሕዝብ ደግሞ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት እየታገሉ እየሰሩ ይገኛል። በሌሊቱ አንድ የአካባቢው ነዋሪ እስከ ፌዴራል ደረጃ ድረስ ቢደውልም በዚህ ሰዓት መንቀሳቀስ መውጣት አንችልም" የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ከገዥው ስርዓህ መልስ ተስጥቷል ።
ሆኖም ነዋሪው በማህበረሰቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ በተመለከተ ከሸኔ ታጣቂዎች ባሻገር በአካባቢው ያሉ የፖለቲካ አካላትንም በሕዝቡ ላይ ይሄንን ግፍ እየሰሩ ያሉት የብልፅግና አባል ሰዎች ናቸው እነዚህ አካላት ከሸኔ ታጣቂዎች ጋር በመቀናጀት ወይም መረጃ እየሰጡ ማህበረሰቡን ለጥቃት እያደረጉ ይገኛሉ። ሆኖም አሁን ላይ ሴቶች፣ ሕፃናት እና አረጋውያን ጨምሮ በርካታ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀበሌዎቻቸው ተፈናቅለው በአባይ በረሃ አካባቢ ለሕይወታቸው ሲሉ በመሰደድ ላይ ናቸው።
ማህበርሰቡም እኛ ወዴት እንደምንደርስ ግራ ገብቶን ነው ያለነው ብለዋል። ማንም የደረሰለት አካል የለም እስከ አሁን ድረስ" በማለት ተስፋ መቁረጣቸውን ገልፀዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !!
የካቲት 28/06/2018 ዓ.ም
+3
ፓራ ኮማንዶዎች ፋኖን ተቀላቀሉ‼️
የካቲት 28/2018 ዓ/ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር
ፓራ ኮማንዶ ተብለው ሰከላ ወረዳ የሰለጠኑት የራው አባላት ፣ከሰከላ ወረዳ በመውጣት 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር ግዮን ሻለቃን ተቀላቅለዋል።
1ኛ.ቻሌ አታላይ_የፓራ ኮማንዶ አባል የነበረ
2ኛ. እንደሸው አድማስ የፓራ ኮማንዶ አባል የነበረ ሲሆኑ፣
አባላቱም ከጠላት የተቀላቀልነው ትጥቅ ለመታጠቅ እንጂ ታላቁ የአማራን ህዝብ ለመዋጋት አልነበረም ብለዋል። ከመግባታችን በፊት ሴራውን ስለምናቅ የምንወጣበትን ቀን አመቻችተን ፋኖዎችን ተቀላቅለናል ብለዋል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ከ3 በላይ የጠላት ምሽጎችን በመስበር በርካታ የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ አደረገ
=====================
በትናንትናው ዕለት በ27/06/2018 ከደምበጫ እስከ አማኑኤል ከተማ ለአምስት ተከታታይ ቀናት መስመር ሙሉ በሙሉ ዘግቶ የመንገደኛ ስልክ፣የአንገት ሀብልና ገንዘብ ሲዘርፍ የሰነበተውን የጠላት ሀይል በ109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ተርቦች መብረቃዊ ጥቃት የተሰነዘረበት ሲሆን በርካታ የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወደ መጣበት ደንበጫ እና አማኑኤል ከተማ እንዲፈረጥጥ ማድረግ ተችሏል።
አይበገሬዎቹ 99ኛ ክ/ጦር ከቀኑ 11:30-12:30 በአደረጉት አውድውጊያ የጠላትን ሦስት ምሽግ በመደረማመስና ከምሽግ ምሽግ በመረማመድ ጠላትን በቆፈረው ጉድጓድ ሲረፈረፉት አምሽተዋል።
በትናንትናው ዕለት በነበረው አውደ ውጊያ 10 የጠላት ሀይል የተደመሰሰ ሲሆን 13 ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ማድረጋቸውን አውደ ውጊያውን የመራው የ109ኛ ኮር ዘመቻ መምሪያ ፲ አለቃ ንብረት ደሴ መረጃውን አድርሶናል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 28/2018 ዓ.ም
+2
ሰበር የድል ዜና አቸፈር ወንድዬ ‼️
የአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ የ105ኮር 55ክ/ጦር የቢትወደድ አያሌዉ መኮነን ሻለቃ ዛሬ ጠላትን ከጠዋቱ ጀምሮ ሲቀጠቅጠዉ ዉሏል ‼️
ከቁንዝላና ዳርፉር በመነሳት መድረሻዉን#አዉትሌት ያደረገዉ የጠላት ሀይል ያሰበዉን ሳያሳካ ተመልሷል።እንደ አመጣጡ የሸኙት የቢትወደድ አያሌዉ መኮነን አናብስቶች ጠላት አቅጣጫዉን በሶስት አድርጎ ለመግባት ቢያስብም አናብስቶቹ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ተሸኝቷል።በዚህ የተበሳጨዉ የጠላት ሀይል የአርሶ አደርን ዳጉሳ ክምር ያቃጠለ ሲሆን በአዉደ ዉግያዉ
ብዛት ያለዉ የጠላት ሀይልን ወደ ላይኛዉ ሲላክ ከጠላት ጥቁር_ክላሽ በመማረክ ቁስለኛዉን እየጫነ ወደ መጣበት እንዲመለስ ተደርጓል።
ይበልጣል የዉነቱ ጀግናዉ
የደጀኑ ጦራችን ሁለንተናዊ ዝግጁነት እና የንቅናቄ መድረክ ተጠናክሮ ቀጥሏል‼️
****
የካቲት 28/2018 ዓ.ም
#አፋብን |201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር በሰዴ ወረዳ የሚገኙ 5 ቀበሌወች የሗላ ደጀን ጦር ባርነት በቃን በማለት ከጫፍ እስከ ጫፍ በቁርጠኝነት ተነስቷል።
.....
ለተከታታይ ሶስት ዓመት ሙሉ በአማራነታችን ብቻ በርካታ ግፎች አስተናግደናል ከዚህ በላይ ቁመን የምናይበት ጊዜ ይበቃናል በማለት ለማይቀረው ግዳጅ ራሳችን ማዘጋጀት አለብን' አማራነት ወይንም ሞት' ብለዋል።
በሰዴ ወረዳ ያሉ 5 ቀበሌወችን በማስተባበር የ54ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች አደራጅተው ከተዋጊው ጋር በማስተሳሰር
1.ጎማድር
2.ወፍጠም
3.አቢብ ደብረ ቁስቋም
4.ደብረ ይባቤ
5.ብሩር ሽሜ
በተደረገ የምክክር ና ንቅናቄ መድረክ ላይ የደጀን ጦሡ አባላት በቀጣይ ኮሩ እና ክፍለ ጦሩ የሚሰጠውን ግዳጅ ተቀብሎ በቀጠናው ያለውን ጠላት ለማፅዳት በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን በአጽኖት አስገንዝበዋል።
በየቀኑ መገደል ይበቃናል የመጣብን የሰው ስነ_ምግባር የሌለው የአንስሳትን ባህሪ የተላበሰ ንፁሀንን ሴቶች እና ህፃናትን በይፋ እያጠፋን ስለሆነ ለአንዴ እና ለመጫረሻ ጊዜ ክተት አውጀን አካባቢያችን ነፃ ማድረግ አለብን በማለት ተነቃንቋል።
የካቲት 28/2018 ዓ.ም
<< ነፃነታችን የምናገኘው በመለማመጥ ሳይህን በክንዳችን ነው >>
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ያ ከአፈር ጋር ታርቆ፣ ከጎረቤት ጋር ተዋዶ፣ አምላኩን ፈርቶ የሚኖረው የአማራ ሕዝብ በወለጋ ምድር በምታዩት መልኩ ደሙ እንደ ጎርፍ እየፈሰሰ ነው።
ይህ አከባቢ የሰው ልጅ የመጨከን ጥግ የሚለካበት መለኪያ ነው፡ የሰብአዊነትና የእዝነት እርካሽነት የሚመዘንበት ስፍራ ሆኗል።
የአማራው ደም እየፈሰሰ የፍትሕ ሚዛን ዝምታን የመረጠችበት አንዳች አስፈሪ ጥላ የሰፈነበት...ወለጋ።
ምድርን የሚያንቀጠቅጥ ሰሚ አልባ የፍጥረታትት"የድረሱልን" ጩኸት እዚህ አለ።
የወለጋ አፈር በገፍ የተጨፈጨፈውን የአማራን ደም ዋጋ ይናገራል። እዚህ አከባቢ የሚነፍሰው ንፋስ የአማራን የሲቃ ድምፅ ያስተጋባል።
ይህ የምትመለከቱት የእልቂት ምስል፡ 2018 ዓ/ም መጀመሪያዎቹ ወራት ላይ በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ስር በሚገኙ አከባቢዎች በአሰቃቂ ሁኔታ የተጨፈጨፉ የአማራ ተወላጆ ምስል ነው።
ያለቀው አልቆ ቀሪው ሕይወቱን ለማዳን መንደሩን ለቆ ተሰድዶ ነበር። የወደቀውን አስከሬንና ቁስለኛ የሚያነሳ የቅርብ ቤተሰብ በመጥፋቱ በአከባቢው የሚኖሩ አንዳንድ ደጋግ የኦሮሞ ተወላጅ አርሶ አደሮች እያነሱ ሲቀብሩ የሚያሳይ ነው።
አሁን ደግሞ➞
በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጎሮ ወረዳን ጨምሮ በጉዳያቢላ፣ በአሙሩ ወረዳና በሌሎች የዞኑ አከባቢዎች እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ አያና ወረዳ፡ በሊሙ ገሊላ እንዲሁም በሌሎች የዞኑ አከባቢዎች በአሁን ሰዓት ተመሳሳይ ጭፍጨፋ ተከፍቶ በርካታ ንፁኋኖች እያለቁ ነው።
ጭፍጨፋውና የንብረት ዘረፋው እንዲሁም ከመኖሪያ ቤት ጀምሮ ንብረትና መንደር የማውደሙ ድርጊት የሚመራው በክልሉ መንግስት ፀጥታ ኃይል ነው።
ጭፍጨፋው እንደ አዲስ የተጀመረው እየተገባደደ ባለው በዚህ የካቲት ወር አጋማሽ ጀምሮ ነው።
+7
201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በእነማይ ወረዳ ዴንሳ እነቆራ እና ሸበል በረንታ ወረዳ አራጤ ቀበሌ ሰፊ ህዝባዊ ውይይቶች አካሂዶል።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
የካቲት 28/2018 ዓ.ም
የአብይ አህመድ አረመኔዊ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማስቆምና የአማራ ህዝብ ከተደቀነበት የህልውና አዳጋ ለመመከት ህዝባችን ዛሬም ከትላንቱ የተሻለ ተሳትፎ ማድርግ እንዳለበት የጀመርነው የትጥቅ ትግል ህዝባችን በፋይናስ በመረጃ መሰል ጉዳዩችን ዛሬም እንደትላንቱ ከፋኖ አባላቱ ጎን መሆን እንዳለበት በስብሰባ መድርኩ ለተገኙት የማህበረሰብ ክፍል በክፉለ ጦሩ አመራሮችና በወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች ሰፊ ግንዛቤ ተሰጥተዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
የካቲት 28/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
ሙሴ የሬሳ፣ ወንድምአገኝ በነዛና፣ ፈንድሽ ሱልጣን የተባሉ ሶስት አረመኔው ሰራዊት አባላት 206ኛ ኮርን ተቀላቀሉ።
የካቲት 28/2018 ዓ.ም
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በሜጀር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን ከሚመራው ስድስተኛ ዕዝ 602ኛ ኮር 32ኛ ክ/ጦር አራተኛ ሬጅመንት አባል የሆኑት እነዚህ የአገዛዙ ወታደሮች ፣ በከተማ እየተንቀሳቀሱ ባሉበት በሚኒሻ ታፍሰው ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እንደተወረወሩ ይናገራሉ።
በፀራራ ፀሀይ ታፍነው በድቅድቅ ጨለማ በሲኖትራክ ታጭቀው ሲጋዙ ቤተሰቦቻቸው ሆነ የአካባቢ ማህበረሰብ አልተመለከታቸውም ፣እናቶቻቸው በልጆቻቸው ደብዛ መጥፋት ተጨንቀው ረጃጅም ሌሊቶች የማይገፉ ቀናቶችን በእንባ እየተራጩ አሳልፈዋል።
እነዚህ ወታደሮች ወደ ማያውቁት ሀገር ተወስደው በግድ ታፍሰው ከመጡ ሌሎች ታዳጊዎች ጋር ሰልጥነው ክላሽ ከታጠቁ በኋላ ጎጃም የተገኙት ሞት በረከሰበት የጥይት ሀሩር ወጣቶችን በሚቀጭበት እሳት በሆነው ጦርነት ማገዶ ሁነው ነበር።
የ32ኛ ክ/ጦር አባል በመሆን በዋናነት በደንበጫ፣ አማኑኤል፣ ደብረ ኤልያስ፣ ጎዛምን የተንቀሳቀሱት እነዚህ የክፉ ቀን ጓደኛማቾች በአንድ ጋንታ አብረዋቸው ከነበሩት 9 ወታደሮች መካከል ሶሶስቱ በተአምር ከሞት የተረፉ ናቸው።
ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የገጠማቸውን አጫውተውናል ። አሁን ጭንቀት ፍርሀት ሰቀቀን ርሀብ ከፊታቸው አይነበብም። በሞት ላይ መራመድ፣ ሜዳ ወድቆ ማደርም የለም። ነፃ ሁነናል አብይ ካስታጠቀን ይልቅ ትጥቅ የሰጠነው ፍኖ ከቤተሰቦቻችን ጋር አገናኝቶናል፣ ሸክማችን አራግፎ ሸክማችንን ተሸክሟል በእውነት እንደዚህ እንከበራለን ብለን አላሰብንም ነበር እያሉ የሚናገሩት እነዚህ ወታደሮች የለበሱትን ሚሊተሪ አውልቆ ለመጣል እየተቻኮሉ ባለበት ነው።
ከአረመኔው ሰራዊት ምሽግ ወጠው 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ከተቀላቀሉ በኋላ ወደ እናቶቻቸው ደውለው ከሞት መትረፋቸውን ተናገሩ ከማዶ የሚሰማው የኦሮሞ እናቶች ልቅሶ ግን እጅግ ፈታኝ ስሜትን የሚፈታተን ያሳለፉትን ሰቆቃና አስጨናቂ ጊዜ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይነው።
ኮሩ እንዲህ ነው በጭንቅ ለተያዙ የአረመኔው ሰራዊት አባላት እፎይታን ይሰጣል ባለፉ ሶስት ወራት ብቻ ከ85 በላይ የአብይ አሕመድ ሰራዊት ትክሻችንን ተደግፎ የተደቀነበትን የሞት ጥላ ያለፈው በሰራዊታችን እና በየደረጃው ባለው አመራር ጥቅብ ዲስፒሊን ነውና ኑ ሰላምን በሚሰጠው ትግላችን ጥላ ከለላ በሚሆነው ሰራዊታችን ተጠለሉ ብለን ጥሪ እናቀርባለን።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዳስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
👇
https://t.me/fanofano2112
ስድስት የ11ኛ ዕዝ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት አባላቶች በሻለቃ ዘመቻ አዛዣቸው እየተመሩ ፋኖን ተቀላቀሉ!
የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 83ኛ ክፍለ ጦር ስድስት አባላቶች በሻለቃ ዘመቻቸው እየተመሩ የካቲት 27/2018 ዓ.ም ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ!
የብልፅግናው አገዛዝ ያለ ጦርነት መኖር እንደማይችልና አሁንም በኢትዮጵያውያን መካከል ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማካሄድ ዝግጅት መጨረሱን ተከትሎ ሰራዊቱ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም በርካታ የብልፅግና ጥምር ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ያለ ሲሆን ደቡብ ወሎ ዞን እየተንቀሳቀሰ ያለው 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 83ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሻለቃ የሰራዊቱ አባላቶች ሁለት አስር አለቃ ማዕረግ ያላቸውን ጨምሮ ባጠቃላይ ስድስት በሻለቃ ዘመቻ አዛዥቸው እየተመሩ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል::
በዚህም በ72 ሰዓት ውስጥ በጀኔራል አድማሱ አለሙ እና ጀኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ ከሚመራው 11ኛ ዕዝ ውስጥ የ203ኛ ኮር 83ኛ ክፍለጦር አባል የሆኑ ሰላሳ አንድ (31) ሰራዊት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: ይህ ቁጥር የሌሎች አሃዶችን ሳይጨምር ነው!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 28/2018 ዓ.ም
ዘመቻ መሪውንና ኦፕሬተሩን ጨምሮ የ11ኛ ዕዝ የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላቶች ፋኖን ተቀላቀሉ!
በጀኔራል አድማሱ አለሙ እና ጀኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ የሚመራው 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 83ኛ ክፍለ ጦር የሻለቃ ዘመቻውንና ኦፕሬተሩን ጨምሮ መቶ አዛዡና የሻለቃ ስታፍ ጠርናፊው በአጠቃላይ አራት አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻን ተቀላቅለዋል:: አመራሮቹም አቀባበል አድርገውላቸዋል::
የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 83ኛ ክፍለ ጦር በሰማዕቱ አርበኛ ፍሬው አለና በተሰየመ ዘመቻ ሁለት ሞርተር በርካታ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ብሎም እግረኛ ሰራዊቱን ጨምሮ በልዩ ዘመቻ መማረኩ የሚታወስ ሲሆን አሁንም የአንድ ሻለቃ አራት አመራሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻን ተቀላቅለዋል::
በቀጣይም ልዩ ዘመቻ መምሪያው ኮብልለው የሚመጡ የሰራዊቱን አባላቶች ለመቀበል ቅድመ ዝግጅቱን ጨርሶ መቀመጡን አስታውቋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 28/2018 ዓ.ም
የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት በጀኔራል ሰለሞን ኢታፋ የሚመራው ደቡብ ዕዝ አባላቶች የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ!
የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ከየ አቅጣጫው እየፈረሰ ሲሆን የደቡብ ዕዝ 202ኛ ኮር 30ኛ ክፍለ ጦር አባላቶች አንድ ስናይፐር እና አንድ ጥቁር ክላሽ ከነ ሙሉ ትጥቁና ተተኳሹ በመያዝ ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል:: አመራሮቹም አቀባበል አድርገውላቸዋል::
ከመከላከያ ኮብልለው ፋኖን የተቀላቀሉት ዘመቻ መሪና ስናይፐር ተኳሽና አሰልጣኝ አባላቶች ከፍተኛ መኮነኖች የሚያወርዱልን ተልዕኮ በመጀመሪያ ፋኖን እናጠፋለን፣ ቀጥለን ወያኔን እናጠፋለን፣ በመጨረሻም ኤርትራን በመዋጋት ወደብ እናስመልሳለን እያሉ ነው ሲሉ የብልፅግናን እብደት በመግለፅ ለዚህ ውሳኔ መብቃታቸውን ተናገዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 28/2018 ዓ.ም
የአናብስቱ እረኛ አርበኛው አማረ
ፀሐይ በደቡብ አማራ ቀጠና ተራራዎች ጀርባ ልትጠልቅ ስታዘግም የሰማዩ ቀለማት ደም መስለው ይታያሉ። በዚህ አስፈሪና ግርማ ሞገስ ባለው ተፈጥሮ መካከል፣ እንደ ዓለት የጸና አንድ ሰው ቆሟል። እርሱ አርበኛው አማረ ታዘዘ ነው።
አማረ በትምህርት ገበታ ላይ ቆይቶ የዲግሪ ማዕረግን የጨበጠ ምሁር ቢሆንም የእውቀቱ ጥልቀት ግን ከጥቁር ሰሌዳና ከወረቀት በላይ ነበር። ከተፈጥሮ ጋር ያለው ቁርኝት የሚገርም የነፋሱን ሽውሽውታ የወፎቹን ዝማሬና የተራራውን ዝምታ እንደ መጽሐፍ ያነባቸዋል።
ነገር ግን የእርሱ ታላቅነት በምሁርነቱ ብቻ አይወሰንም። አማራነት የታለች? ተብሎ ቢጠየቅ፣ መልሱ የሚገኘው በአማረ ግርማ ሞገስና በፅናት የተሞላ ማንነት ውስጥ ነው።
አንድ ምሽት፣ የአሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊነቱን ጎን ለጎን አድርጎ እየሰራ፣ የጦር መሣሪያውን አነገተ አብርውት ወደ ጫካ የገቡትኝ የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር የአሳምነው አናብስቶች "አይገባህም፣ አንተ የምትመራንና የምታስተዳድረን መሪ ነህ" ቢሉትም፣ አማረ ግን ፈገግ ብሎ እንዲህ አለ
መሪነት በመድረክ ላይ መናገር ብቻ ሳይሆን፣ ከጀግኖች ጋር አብሮ ግንባር ላይ መቆም ጭምር ነው። ይላል የጦርነቱ ነጎድጓድ ሲሰማና ምድሪቱ በባሩድ ጭስ ስትታወክ አማረ በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ተሰልፎ ይታያል። ያ ምሁርነቱ ወደ ጀግንነት ያ ዝምታው ወደ ቆራጥ ውሳኔ ተቀይሯል የፈሰሰው ደምና ላብ የአማረን ስም ከሕዝቡ ልብ ጋር አጣበቀው።
"አማረ" እና "አማራ" የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ የፊደል መገጣጠም ብቻ አይደሉም፤ ይልቁንም የአንድ ትልቅ ሕዝብ ዕጣ ፈንታና የአንድ ቆራጥ አርበኛ የደም ትስስር መገለጫዎች ናቸው። አማረ ታዘዘ ለአማራ ሕዝብ ያለው ፍቅር በቃላት አይገለጽም፤ በተግባር ግን በተራራዎቹ ድንጋይ ላይ ሳይቀር ታትሞ ይገኛል።
